Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

አቡጊዳ – የነሌንጮ ኦዴፍ ኢትዮጵያ የመግባት ምኞት እንጂ ዉሳኔ የለዉም ተባለ !

$
0
0

የኦነግ መስራቾችና አንጋፋ መሪዎች፣ እነ ዶር ዲማ ነግዎ፣ አቶ ሌንጮ ለታ የመሳሰሉት፣ የኦሮሞ ጥያቄ የመገንጠል ሳይሆን የዴሞክራሲ ጥያቄ ነዉ በሚል፣ ራሳቸውን ከኦነግ አግልለው፣ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፎረም (ኦዴፍ) የሚባል ድርጅት ማቋቋማቸው ያታወሳል።

ኦዴፍም በኢትዮጵያ አንድነት እንደሚያምን ያረጋገጠ ሲሆን፣ ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮዮጵያዉያን ሁሉ እንቆማለን የሚል አቋም ፣ ድርጅቱ በተመሰረተ ሰሞን በስፋት ሲያንጸባርቅ ነበር። እንደዉም በፓልቶክ በተደረጉ ዉይይቶች፣ የኦዴፉ አቶ ሌንጮ ባቲ፣ «ካስፈለገም፣ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ተነጋግረን፣ ኦሮሞ ከማለት ኢትዮጵያ የሚል ስም ለመያዝን እንሞክራለን » እንዳሉም የሚረሳ አይደለም።

ሰሞኑን ኦዴፍ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በመጪው ምርጫ ሊወዳደር እንደሆነ የሚገልጹ ዘገባዎች በስፋት እየተነገሩ ነዉ። የኦዴፍ ሊቀመንበር ፣ ነዋሪነታቸዉ በኖርዌይ የሆኑት፣ አቶ ሌንጮ ለታ (ሌንጮ ባቲ አይደለም) «ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ሊገባ ነዉ» በተባለውና በሌሎሽ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በጀርመን ድምጽ ራዲዮ ቀርበዉ በአማርኛ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አቶ ሌንጮ አሁን በኢትዮጵያ ያለዉ በዘር ላይ የተመሰረተዉ ፌደራል አወቃቀር መቀጠል እንዳለበት አጠንክረዉ ይናገራሉ። «ችግሩ በአፈጻጸሙ ላይ እንጂ በፌደራል አወቃቀሩ ችግር የለም » ያሉት አቶ ሌንጮ፣ ኦዴፍ በተመሰረተ ጊዜ በፌደራላዚም ዙሪያ ፣ ኦዴፍን ወክለው ዶር በያን አሴቦ፣ በፓልቶክ፣ ከሰጡት አስተያየት ጋር ይቃረናሉ። በወቅቱ ዶር በያን፣ «አንዴ ስምምነት ከተደረገ በኋላ፣ መንግስት በተቀየረ ጊዜ የማይለወጥ፣ ሁሉም የሚስማሙበት አዲስ ፌደራል አወቃቀር እንዲኖር ነው ኦዴፍ የሚፈልገው» የሚል አስተያየት ነበር የሰጡት።

የአቶ ሌንጮ በፌደራል አወቃቀሩ ዙሪያ በጀርመን ድምጽ የተናገሩትን ያዳመጡ፣ ኦዴፍ በፖለቲካ አቋሙ ፣ ከኦህዴድ ጋር በጣም የሚቀራረብ እንደሆነ በመግለጽ ኦዴፍ በአገር በት ገብቶ ምን የተለየ ነገር ሊያመጣ እንደሚችል ይጠይቃሉ።
የአገሪቷ ችግሮች በሰላምና በዉይይት እንዲዲፈታ ድርጅታቸው ፍላጎት እንዳለዉ አክለው የገለጹት አቶ ሌንጮ « እኔ እዚህ ኖርዌይ ተቀምጬ ምን አደርጋለሁ ? ሕዝቡ ጋር ሆን ካልታገልን በዉጭ ሆነ የምናደርገዉ ምንም ነገር የለም» ሲሉ ከሕዝብ ርቆ በዉጭ የሚደረግ ትግል ዋጋቢስ እንደሆነ ለማሳየት ሞክረዋል። ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ፣ አገር ዉስጥ ገብተዉ፣ በምርጫ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹት አቶ ሌንጮ፣ በዚያ ዙሪይ ከኢሕአዴግ ጋርም ሆነ ከተቃዋሚዎች ጋር ለመወያየት ድርጅታቸው ዝግጁ እንደሆነ አስረድተዋል።

በዚህ ዙሪያ፣ ከኦዴፍ ጋር ቅርብ ግንኙነት ያላቸው፣ አንድ ምሁር፣ ኦዴፍ ከጅምሩ አገር ዉስጥ ገብቶ በሰላም ለመታገል ፍላጎት እንዳለው ሚስጠር እንዳልሆነ ካስረዱ በኋላ፣ ኦዴፍ ለመደራደር ጥያቄ ያቀረበዉ፣ ኢሕአዴግ ለምርጫ የሚያስፈልጉ የዴሞክራሲያዊ ተቋማትን እንዲያስተካክልና ለፍትሃዊ ምርጫ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች መሆኑን ይገልጻሉ። «በኦዴፍ ዘንድ ኢትዮጵያ የመግባትና ለምርጫ የመወዳደር ዉሳኔ በፍጹም የለም» ያሉት እኝሁ ምሁር ኦዴፍ አገር ቤት ሊገባ ነዉ ተብሎ የሚዘገበዉን «ከእዉነት የራቀ» ብለዉታል።

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘገባ፣ ኦዴፍ ኢትዮጵያ የመግባት ፍላጎትና አላማ እንዳለው እንጂ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ እንደሆነ አያመላከትም።

የጀርመን ድምጽ ራዲዮን ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ !


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>