Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

ፓትርያርኩ÷ ሰንበት ት/ቤቶች በቅዱስ ሲኖዶስ በጸደቀላቸው የውስጥ መመሪያ ደንብ መሠረት እያገለገሉ አማሳኞችን እንዲያጋልጡና ሙስናን በተጠናከረ ኃይል እንዲዘምቱበት አሳሰቡ

$
0
0

Sunday School student applausing his holiness anti-corruption effort

  • በሰንበት ት/ቤቶቹ የድጋፍ መግለጫ ስብሰባ÷ የፓትርያርኩ ፀረ ሙስና መግለጫዎች፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥናት ተግባራዊነትና የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ የሚያሻው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

*           *          *

  • የድጋፍ መግለጫ ስብሰባውን ለማሰናከል የሞከሩት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ፣ ሰንበት ት/ቤቶቹ ለአደረጃጀትና አሠራር ለውጡ ድጋፋቸውን ለመግለጽና ስለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ በቅድሚያ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃን ማማከር እንደሚገባቸው በመጥቀስ ከአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራሮች ጋራ ተሟግተዋል፡፡
  • ዋና ሓላፊው፣ የአንድነት አመራሮቹን ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የሚከፍላችኹ የማኅበረ ቅዱሳን ቅጥረኞች›› በሚል እየዘለፉ በመሟገታቸው የገሠጿቸው የመምሪያው ምክትል ሓላፊና የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ÷ ሰንበት ት/ቤቶቹ የአደረጃጀትና አሠራር ለውጡን የተወያዩበት እስከኾነ ድረስ በመረጃና ዕውቀት ላይ ተመሥርተው መደገፍ ይኹን መቃወም መብታቸው መኾኑን ገልጸዋል፤ ስብሰባው በተፈላጊ አጀንዳዎች ላይ እንዳያተኩር ዋና ሓላፊው በግራ አጋቢ ንግግሮች ያደረጉት የመርሐ ግብር ማጣበብ ሙከራም ሳይሳካላቸው ብርቱ ትችት አትርፈው ወጥተዋል፡፡

 

*           *          *

  • በተሰጥኦዋቸው፣ በሞያቸውና በጉልበታቸው በሚሰጡት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከምንም ዐይነት ተጽዕኖ ነጻ ኾነው የተሳሳተውን ነገር በማጋለጣቸው አንዳንድ አለቆችና ጸሐፊዎች ለፖሊስ በሚጽፉት ደብዳቤ ብቻ ጉዳዩ ሳይጣራ ድብደባና እስር የተፈጸመባቸው የሰንበት ት/ቤት አባላት እንዳሉ ተገልጧል፡፡ በጽ/ቤት ደብዳቤ ብቻ ብልሹ አሠራርን የሚቃወሙና የሚያጋልጡ የሰንበት ት/ቤት አባላትን ማሳሰርና ማስደብደብ እንደ እንጀራ ልጅ መመልከትና ፍትሐዊ ባለመኾኑ እንዲቆም ቅዱስነታቸው መመሪያ እንዲሰጡበት ተጠይቋል፡፡
  • የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ በአማሳኝ አስተዳዳሪዎች ላይ ማስረጃ ያጠናቀረበትን ሰነድ ለፓትርያርኩና ለፀረ ሙስና ኮሚሽን እንደሚያቀርብ ተሰምቷል፡፡
  • ሰንበት ት/ቤቶች በአዲስ አበባ በዓለ ጥምቀት በሚከበርባቸው 46 የባሕረ ጥምቀት ሥፍራዎችና የታቦት ማደርያዎች የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ‹ተቃዋሚዎች› እንደሚያሰራጩ ያስወሯቸውን ኅትመቶች በመቆጣጠር በዓሉን በተለመደው ድምቀትና ሰላማዊነት እንደሚያከብሩ ገልጸዋል፡፡

*           *          *

 His Holiness Abune Mathias and His Grace Abune Markos

  • ‹‹በየደጁ ሙስናን ተዋጉ! ዲያቆንም ቄስም መነኩሴም ይኹን ሌባ ሰው ሲገኝ ማጋለጥ ነው! ይኼ ፕሮቶኮል የለውም፡፡ ቢቻል እጅ ከፍንጅ ይዞ ድረሱልኝ ማለት ነው፡፡ በከተማው ያለው ሌባ ያው እዚኹ ያለው የእምነቱ ተከታይ ነው፡፡ ከሌላ የመጣ የለም፡፡ እምነቱን ሳያውቀው ያመነ ነው፡፡ ሰው ካመነ በኋላ ይሰርቃል እንዴ!›› /ብፁዕ አቡነ ማርቆስ/
  • ‹‹የታሰሩት፣ የተደበደቡት የሰንበት ት/ቤት አባላት ምንድን ነው ያደረጉት? የት ነው የታሰሩት? ማነው የሚያሳስራችሁ? ለምንስ ተጽዕኖ ይደርስባችኋል? ምክንያቱ መጠናት አለበት፤ ምክንያቱ ተጠንቶ ከነማስረጃው ቢቀርብልን ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድ ውሳኔ ትሰጣለችኮ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆቿን ዝም ብላ አሳልፋ አትሰጥም፡፡ በጥናት ቢቀርብልን የበጀ ይኾናል፡፡››
  • ‹‹የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ቤተ ክርስቲያኒቱ የምታምንባችኹ የቤተ ክርስቲያኒቱ ታማኞች መኾናችኁን ያረጋገጣችኹ ልጆቻችን ናችኹ፡፡ እናንተ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አለኝታዎች ናችኹ፡፡ ዘመኑ የእምነት ጉድለትና የኑፋቄ ነው፡፡ ምሳሌው ጥሩ ባይኾንም እሾኽን በእሾኽ እንደሚባለው አሉ ለምትሏቸው መናፍቃን መልስ የምትሰጡ እናንተ ናችኹ፡፡ እምነት የሚያቃውስ፣ ሥርዐትና ትውፊት የሚያፋልስ ካለ በማስረጃ ተረጋግጦ ሲቀርብ ቤተ ክርስቲያኒቱ መልስ መስጠት አለባት፡፡ ፀረ ሙስናውን እንደግፋለን ብላችኁኛል፤ እኔም እንደምትደግፉኝ አምናለኹ፡፡ ሐቅ፣ መልካም አስተዳደር፣ እውነተኝነትና ሓላፊነት ጠፍቷል፤ የሚያሳዝን ኹኔታ ነው ያለው፡፡ ተይዞ ባለው የፀረ ሙስና ቅስቀሳ እናንት የሰንበት ት/ቤት አባላት በይበልጥ ብትዘምቱበት፤ በተጠናከረ ኃይል ይህን ብትረዱኝና ከዳር ብናደርሰው አመሰግናችኋለኹ፡፡›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>