ጤናችን ይጠበቅ በሁላችን
የሀገር ጠላት ወያኔ
የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር «ኦሮሞዉን» ጎድቷል
- አማኑኤል ዘሰላም
የኢትዮጵያ ፈዴራል ሕገ መንግስት አንቀጽ 46 «ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ የማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት ነዉ» ይላል። አንቀጽ 47 ደግሞ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሩፑብሊክ አባላት የሆኑቱን ክልሎች ይዘረዝራቸዋል። እነርሱም የትግራይ፣ የአፋር ፣ የአማራ፣ የሱማሌ፣ የቤኔሻንጉል/ጉሙዝ፣ የደቡብ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች እና የሃረሪ ሕዝብ ክልሎች ናቸው።
የዚህን የፌደራል ክልልን በተመለከተ በክልሎች እየታዩ ያሉትን አንዳንድ ሁኔታዎች ለማሳየት እንሞክራለን። ከትልቁ ክልል ኦሮሚያ እንጀምር።
ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ ሃያ ዞኖች አሉ። ሶስቱ «ልዩ ዞኖች» ይባላሉ። ናዝሬት/አዳማን ያካተተ፣ የአዳም ልዩ ዞን፣ ጂማን ያካተተው፣ የጂማ ልዩ ዞን እና የቡራዮ ልዩ ዞን ናቸው። በነዚህ ዞኖች የመጀመሪያ ቋንቋቸው አፋን ኦሮሞ የሆኑቱ ቁጥራቸው ከ45 በመቶ በታች ነዉ። በአዳማ 26%፣ በጂማ 39% እና በቡራዮ 44% ናቸው።
በአሥራ ሶስቱ ሌሎች የኦሮሚያ ዞኖች አፋን ኦሮሞ የመጀመሪያ ቋንቋቸው የሆኑ ከ90 % በታች ናቸው። እነዚህም ምስራቅ ሸዋ ( 69%)፣ ጉጂ (77%) ፣ አርሲ ( 81%)፣ ሰሜን ሸዋ ( 82%)፣ ደቡብ ምስራቅ ሸዋ (84%)፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ (85%) ፣ ምእራብ አርሲ (87%)፣ ምስራቅ ወለጋ (88%) ፣ ምእራብ ሃረርጌ (89 %)፣ ኢሊባቡር (90%) ፣ ጂማ – የጅማ ከተማ አካባቢ ( 90%)፣ ባሌ (90%)፣ ቦረና (90%) ናቸው። እንግዲህ ከሃያ የኦሮሚያ ዞኖች፣ በአሥራ ስድስቱ፣ ምን ያህል አፋን ኦሮሞ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያን በስፋት እንዳሉ እያየን ነዉ። በአራት የኦሮሚያ ዞኖች፣ በአፋን ኦሮሞ አፋቸዉን የፈቱ፣ ከዘጣና ሶስት በመቶ በላይ ናቸው። እነርሱም ምእራብ ወለጋ (97%) ፣ ምእራብ ሸዋ (93%)፣ ምስራቅ ሃረርጌ፣ (94%)፣ ቀለም ወለጋ ( 94%) ናቸው።
አሁን በሥራ ላይ እየተተገበረ ያለው የኦሮሚያ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ 33 «በክልሉ ዉስጥ ነዋሪ የሆኑና የክልሉን የሥራ ቋንቋ የሚያውቅ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በማንኛዉም የክልሉ መንግስታዊ ወይም ሕዝባዊ ሥራ ተመርጦ ወይም ተቀጥሮ የመስራት መብት አለዉ።» ይላል። አንቀጽ 5 ደግሞ « ኦሮምኛ የክልሉ መንግስት የሥራ ቋንቋ ይሆናል። የሚጻፈዉም በላቲን ፊደል ነው» ይላል።
74% የአዳማ፣ 61% የጂማ ከተማ ፣ 56% የቡራዩ ዞን፣ 31% የምስራቅ ሸዋ ዞን፣ 23% የጉጂ ዞን ፣ 25% የሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን፣ 23% የምእራብ አርሲ ዞን … ነዋሪዎች የመጀመሪያ ቋንቋቸው አፋን ኦሮሞ ባላመሆኑ፣ አፋን ኦሮሞ ካልተማሩ በቀር፣ የመመረጥ፣ በኦሮሚያ ክልል የመስራት መብት የላቸውም። ይህም አማርኛና ሌሎች ቋንቋዎች የሚናገሩ፣ በኦሮምያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን እንደ ሁለተኛና ሶስተኛ ዜጋ እንዲቆጠሩ የሚያደርግ ነዉ። በብሄረሰብ መብት ስም የግልሰበ መብት እየተረገጠ ነዉ።
«ኦሮሚያ ፈርስት» የሚል እንቅስቃሴን የሚመራው ጃዋር ሞሃመድ፣ አንድ ወቅት «Ethiopians Out from Oromia» የሚል መፈክር ያሰማበትን ቪዲዮ ተመልክቻለሁ። ጃዋር በአጭሩ አነጋገር፣ ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ብቻ እንደሆነችና ሌሎች «ኦሮሞ» ያልሆኑ፣ በኦሮሚያ ዉስጥ እንግዶች፣ ኦሮሞዎች ሲፈቅዱላቸው ብቻ ሊኖሩ የሚችሉ እንደሆኑ ነው የነገረን። ይህ የጃዋር አባባል፣ ብዙዎችን እንዳስገረመ ተመልክቻለሁ። ነገር ግን አንድ የዘነጋነው ነገር ቢኖር፣ ይህ የጃዋር አባባል ፣ ጃዋር የፈጠረዉ ሳይሆን በኦሮሚያ በአሁኑ ሕግ መንግስት፣ በሰነድ የተቀመጠ እንደሆነ ነዉ።ይህ አይነቱን ዘረኛ የጃዋር አባባል፣ የኦሮሚያ ክልል «ሕግ» ይደግፈዋል።
የኦሮሚያ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ ስምንትን ይመልከቱ። «የኦሮሞ ሕዝብ የክልሉ የበላይ ስልጣን ባለቤት ሲሆን ..» ሲል የኦሮሚያ ባለቤት «ኦሮሞው» ብቻ እንደሆነ ነው የተቀመጠው።
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ፖሊሲን ካየን ደግሞ፣ አዲስ አበባ አካባቢ ያሉ እንደ አዳማ/ናዝሬት ያሉ ቦታዎች ሕዝቡ ተቃዉሞ ስላስነሳ፣ በዚያ ተማሪዎች አማርኛም ከአፋን አፋን ኦሮሞ ጎን ለጎን እንዲማሩ ከመደረጉ በስተቀር፣ በኦሮሚያ የሚኖሩ ተማሪዎች አማርኛ እንዲማሩ አይደረግም። አማርኛ ማንበብና መጻፍ አይችሉም።
አንድ የግል ባለሃብት ከአዲስ አበባ ሄዶ አንድ ኩባንያ በአንድ የኦሮሚያ ከተማ ይመሰርታል። ሰራተኞች ቀጥሮ ያሰራል። ሰራተኞቹ ስራቸዉን በተመለከተ፣ ሪፖርት ማቅርብ ሲጠበቅባቸው ሪፖርት ሳያቀርቡ ይቀራሉ። አለቃቸው ያስጠራቸዉና ይጠይቃቸዋል። ሪፖርታቸውን በቃል ያቀርቡለታል። «እሺ በፋይል እንዲቀመጥ በጽሁፍ አምጡልኝ» ሲላቸው፣ ማንገራገር ጀመሩ። «ጌታዬ እኛ አማርኛ መጻፍ አንችልም። በቁቤ እንጻፈዉና ከፈለጉ ያስተርጉሙት፤ ወይም እኛ አስተርጉመን እንመጣለን» ይሉታል። ሰዎዬዉ ባንድ በኩል በጣም ተናደደ፣ በሌላ በኩል አዘነ። ቢዝነስ ነዉና፣ ለስራው ብቃት ከሌላቸው ሰራተኞቹ መባረር አለባቸው።
አማርኛን የመጥላት የኦህደድ እና ኦነግ ፖለቲካ ፣ ዜጎች አፋን ኦሮሞን ያዉም በቁቤ ብቻ እንዲማሩ በማድረግ፣ ትልቅ የኢኮኖሚ ጉዳት በ«ኦሮሞዎች» በትግራይ ከአንደኛ ክፍል ጀመሮ ከትግሪኛ ጎን አማርኛ እንዲማሩ ይደረጋል።
የኦሕደድ ባለስልጣናት እነ አባ ዱላ ገመዳ፣ ኩማ ደመቅሳ የመሳሰሉት ልጆቻቸዉን የሚያስተምሩት በአዲስ አበባ ሃሪፍ ተምህርት ቤቶች ነዉ። ሃብታም የሆኑና አቅሙ ያላቸው ልጆቻቸውን ወደ አዲስ አበባ እየላኩ ያስተምራሉ። ለምን ቁቤ ብቻ ተምረው ልጆቻቸው የትም እንደማይደርሱ ስለሚያወቁ።
የግል ኢንቨስተሮች የሥራ ቋንቋቸው በኦሮሚያም ሳይቀር በብዛት አማርኛ ነዉ። በናዝሬት፣ በጂማ በመሳሰሉት ቦታዎች ሂዱ፣ የንግድ ተቋማት፣ የግል መስሪያቤቶች .. የሚጠቀሙት አማርኛን ነዉ። ከክልል መንግስት ጋር አንዳንድ ደብዳቤዎች መላላክ ካስፈለገ ፣ የክልሉን የአፋን ኦሮሞ ብቻ ፖሊስ ሕግን ለማክበር ፣ ተርጓሚ ይቀጥራሉ።
በኢትዮጵያ ካሉ 9 ክልሎች በአራቱ (አማራዉ፣ ደቡብ፣ ጋምቤላና ቤኔሻንጉል ጉሙዝ) ክልሎች፣ እንዲሁም በአገሪቷ መዲና አዲስ አበባ፣ በድሬደዋ የሥራ ቋንቋ አማርኛ ነው። የፌደራልም ቋንቋ አማርኛ ነዉ።
በመሆኑም ኦሮሚያ ያለው የቁቤ ትዉልድ፣ በፌደራል መንግስት ዉስጥ ተቀጥሮ የመስራት አቅሙ ዜሮ ነዉ። እንደ ባህር ዳር፣ አዋሳ፣ ድሬደዋ፣ አዲስ አበባ በመሳሰሉ ታላላቅ ከተሞች ለመኖርና ለመስራት፣ ለመቀጠር በጣም ይቸገራል። በአጭሩ በኢኮኖሚ እንያድጉና እንዳይሻሻሉ ትልቅ ማነቆ ነው እየሆነባቸው ያለዉ ይህ የኦሮሚያ ክልል አሰራር። በሌሎቹ ክልል ካሉ ጋር ሲወዳደሩ ወደኋላ ቀርተዋል። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የኦነግ መሪዎች ልጆቻቸው በበርሊን ሚኒሴቶች …በመሳሰሉ ቦታዎች ናቸዉ። አማርኛም ባያወቁ፣ እንግሊዘኛ እስካወቁ ድረስ ችግር አያጋጥማቸዉም። የኦህደድ መሪዎች ልጆቻቸውን ሃሪፍ ትምህርት ቤቶች ነዉ በአዲስ አበባ የሚያተምሩት። ድሃዉና ምስኪኑ የኦርሚያ ተማሪ ግን፣ አጥር ታጥሮበት፣ በአጉል የኦሮሞ ብሄረተኘንት ስም እንዲተበተብ ተደርጎ ጉዳት እየደረሰብት ነዉ።
ይህ በኦሮሚያ የሚኖረው ወገናችን በኢኮኖሚ፣ በትምህርት ፖሊሲ ረገድ እየደረሰበት ካለው ግፍ በተጨማሪም፣ ኦነግ እየተባሉ በሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን እየታሰሩና እየተሰቃዩ ናቸው። ሕወሃት/ኢሃዴግ በአንድ በኩል እነሌንጮን ቀንደኛ ኦነጎችን እያባበለ፣ በሌላ በኩል የነሌኝቾ ደጋፊ ናችሁ እያሉ ሰላማዊ ዜጎችን ያስራል።
ታዲያ መፍትሄዊ ምንድን ነዉ ? አራት መፍትሄዎች አሉ፡
1. ኢትዮጵያዉያን አፋቸዉን በየትኛው ቋንቋ ነዉ የፈቱት የሚለዉን ጥያቄ ብንጠይቅ ፣ በአንደኝነት የሚቀመጠዉ ኦሮምኛ ነዉ። በበርካታ ዞኖች ከዘጠና በመቶ በላይ ኦሮምኛ የሚነገርባቸው ቦታዎች አሉ። 33.8 % የሚሆነው ሕዝባችን አንደኛ ቋንቋዉ አፋን ኦሮሞ ነዉ። 29.36% የሚሆነው ህዝብ አማርኛ አንደኛ ቋንቋዉ ነዉ። ሁለቱ ቋንቋዎች እንደ አንደኛ ቋንቋ የሚናገሩ 63.2% ይደርሳሉ። በመሆኑም ኦሮሞኛ ከአማርኛ ጎን የፌደራል ቋንቋ ቢሆን ትልቅ ጥቅም ይኖረዋል።
2. በሁሉም ክልሎችና ወረዳዎች፣ በአካባቢዉ ከሚነገረው ቋንቋ ጎን ለጎን፣ ተማሪዎች አማርኛ እንዲማሩ መደረግ አለበት። አማርኛ እንደ አንደኛ ቋንቋ 29.3% የሚሆነው ሕዝብ ይናገረዋል። እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ደግሞ፣ ከ30፣ 40 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ሊናገረው ይችላል ብዬ አስባለሁ።በመሆኑም አማርኛ ማወቅ ጥቅም አለው። ቋንቋ በአጠቃላይ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። አማርኛን መማር ኦሮሞኛን አይጎዳም። የኦሮሞ መሪ ነን የሚሉ ፖለቲከኞች፣ ለራሳቸው ልጆች እንዳሰቡት፣ ለተቀረዉም የኦሮሞ ልጅ ሊያስቡ ይገባል ባይ ነኝ።
3. የኦሮሚያ ክልል መንግስት አማርኛን ከኦሮሞኛ ጎን የሥራ ቋንቋ ማድረግ አለበት። ኦሮሞኛ የማይናገር በክልሉ አስተዳደር ዉስጥ የመስራት መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል። በኦሮሚያ 95% ነዋሪዉ ኦሮሞኛ የሚናገር ቢሆን፣ እሺ አንድ ነገር ነዉ። ግን ከ 15% በመቶ በላይ ሕዝብ አንደኛ ቋንቋም ኦሮሞኛ ባልሆነበት፣ «አፋን ኦሮሞ ብቻ ወይንም ሞት» ማለት ትልቅ ስህተት ነዉ። በክልሉ ዋና ከተማ አዳማ/ናዝሬት እንኳን ፣ አንድ አራተኛ ሕዝብ ብቻ ነው ኦሮሞኛ የሚናገረው።
4. ናዝሬት/አዳም እና ጂማ የመሳሰሉ እንደ አዲስ አበባና ድሬደዋ፣ ለጊዜዉ ቻርተር ከተማ ቢሆኑ መልካም ነዉ። (ለዘለኬታዉ፣ ለሁሉም በሚበጅ፣ የተለያዩ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባና በተጠና መልኩ ፣ፌደራል አወቃቀሩ እንደገና በአዲስ የሚዋቀርበትን ሁኔታ በመፈለግ ለብዙ ችግሮች መፍቴሄ ማግኘት ይቻላል)
ከላይ የዘረዘርኳቸዉ አሃዞች በኦፊሴል ከተመዘገበዉ የኢትይጵፕያ ሕዝብ ቆጠራ ሪፖርት ነዉ። በሚቀጥለው ጊዜ የቤኔሻንጉል ጉምዝ እና ሃረሪ ክልሎችን እንመለከታለን።
ገንዘቤ ዲባባ በ3000 ሺህ ሜትር ስቶክሆልም ላይ ዛሬ ያሸነፈችበት ቪድዮ
ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ – ግርማ ካሳ
ከበደ ካሳ የሚባሉ አፍቃሪ ኢሕአዴግ ግለሰብ “አንዳንድ ሰዎች «ብሄር ..?» ተብለው ሲጠየቁ «ኢትዮጵያዊ!!!…» እያሉ የሚመልሱት፣ የራሳቸዉን ማንነት የኢትዮጵያ ማንነት አድርገው ያስቀመጡና በራሳቸው ማንነት የሌሎቹን ለመጨፍለቅ የሚያልሙ – የቅዠት ታንኳ ቀዛፊዎች ናቸው…. ተዛብታችሁ ሌላንም ለማዛባት ለምትፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጂ ብሄር አይደልም። ኢትዮጵያ ሃገር እንጂ የአንድ ሕብረተሰብ ክፍል መለያ አይደለም።” የሚል አባባል ፌስቡክ ላይ ለጥፈው አነበብኩ።
በአንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ሕገ መንግስቱ እንዲህ ይላል ፡
“በዚህ ሕገ መንግስት ዉስጥ «ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸዉን ባህርይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነዉ። ሰፋ ያላ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልዉና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የስነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛዉ በተያያዘ መልክአ ምድር የሚኖሩ ናቸው»
እንግዲህ እዚህ ላይ እናስተዉል። ለብሄር የተሰጠው ትርጉምና ለብሄረሰብ የተሰጠው ትርጉም አንድ አይነት ነዉ። በአጭሩ ብሄር ማለት ብሄረሰብ ማለት ነዉ በሕገ መንግስቱ መሰረት።
ብሄር በእንግሊዘኛ ኔሽንስ ማለት ነዉ። «ዩናይትድ ኔሽንስ» ስንል የተባበሩት መንግስታት (የተባባሩት አገሮች ማለታችን ነዉ) ። እንደሚገባኝ ኢትዮጵያ እንጂ፣ ኦሮሞ፣ ወይንም፣ ትግሬ ወይንም ወላይታ የተባበሩት መንግስታት አባል አይደሉም።
«ብሄር» የሚለዉን ቃል የመጀመሪያ አመጣጥ ስንመለከት ፣ ከግእዝ የተወሰደ እንደሆነ እንረዳለን። ትርጉሙም በግእዝ አገር ማለት ነዉ።
ስለዚህ ኢሕአዴግን እና ኦነግ በሕገ መንግስቱ ብሄር የሚለዉን ቃል ያኔ የወሸቁት፣ ኢትዮጵያን እንደ አንዲት አገር ሳይሆን የተለያዩ የአገሮች ስብሰብ እንደሆነች ለማሳየት፣ በፈለጉ ጊዜ ደግሞ ከኢትዮጵያ ለመለየት አማራጭ እንዲኖራቸው ከመፈለግ የተነሳ ነዉ።
ፕሮፌሰር ተኮላ ሃጎስ ደግሞ ብሄር ብሄረሰብና ሕዝብ የሚለውን ለምን ሕገ መንግስቱ ዉስጥ እንደገባም ሲጽፉ የሚከተለዉን ነበር ያሉት፡
“The phrase “the nations, nationalities and peoples” thus found in the Ethiopian Constitution is a legacy from the writings of immature and juvenile diatribe of badly educated and socially disfranchised and radicalized students of Haile Selassie I University of the 1970s. It is the ersatz voice of Meles Zenawi forcing himself through the 1995 Constitution on the People of Ethiopia his narrow and ignoramus ideas on the history of Ethiopia and the process of nation building”
ስለዚህ «ብሄርህ ምንድን ነዉ ?» ተብሎ አንድ ሰው ሲጠየቅ «ኢትዮጵያዊነት» ብሎ ከመለሰ፣ በትክክለኛዉ የግእዝ አተርጓጎም እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ብሄር የሚለው ቃል ያለው አጠቃቀም አንጻር፣ ትክክለኛ መልስ ነዉ።
«ብሄረሰብህስ ምንድን ነዉ ? » የሚል ጥያቄ ቢነሳስ ?
አንድ መርሳት የሌለብን ነገር አለ። አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የተደባለቀ ነዉ። ሰሜን ጎንደና ሰሜን ወሎ ከሄዳችሁ ትግሪኛ ተናጋሪዉና አማርኛ ተናጋሪዉ ተደበላልቋል። ኦሮሚያ ዉስጥ በሸዋ፣ በሰሜን እና በምስራቅ ወለጋ..፣ አማራዉ ክልል ደግሞ በወሎ ፣ ኦሮሞኛ ተናጋሪው ከአማርኛ ተናጋሪው ተደባልቋል። በምስራቅ ሃረርጌና በባሌ ደግሞ ሶማሌዉና ኦሮሞዉ የተደባለቀበትም ሁኔታ አለ። በደቡብ ክልል ከሄድን፣ ወላይታዉ ከሲዳማው፣ ከንባታዉ ከሃዲያዉ …ሁሉም ተበራርዟል። ስለዚህ በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የብዙ ብሄረሰቦች ድብልቅ ናቸው። በመሆኑም «ብሄረሰብህ ምንድን ነዉ?» ተብለው ሲጠየቁ እዚም እዚያም በመሆናቸው፣ ለመመለስ ይቸግራቸዋል። ስለዚህ በአጭሩ በብሄረሰባቸው ወይንም ዘራቸው ሳይሆን በኢትዮጵያዊነታቸው መለየትን ይመርጣሉ። ከነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነኝ።
አቶ ከበደ፣ ኢትዮጵያዊያን፣ ብሄራችን ኢትዮጵያዊነት ነው ማለታቸው፣ የሌሎችን ማንነት ለመጨፍለቅ እንደመሞከር አድርገውም ወስደዉታል። አንድ ሰው «ኦሮሞ ነኝ፣ ትግሬ ነኝ ወዘተረፈ » የማለት መብቱ ከተከበረለት፣ ሌላው «አይ እኔ በዘሬ መለየት አልፈልግም፣ በኢትዮጵያዊነቴ ነዉ መለየት የምፈልገው » ካለ የርሱስ መብት ለምን አይከበርለትም ? ኦሮሞ፣ ወይም ትግሬ ፣ ወይም አማራ ያለመባል መብቱ መጠበቅ የለበትምን?
በኢሕአዴግ መንግስት፣ ይሄ መሰረታዊ መብት እየተጠበቀ አይደለም። እያንዳንዱ ዜጋ፣ እነርሱ ብሄር ብሄረሰብ የሚሉት አንዱ የዘር ሳጥን ዉስጥ መግባት አለበት። ያ ካልሆነ መታወቂያ እንኳ ማግኘት አይቻልም።
እንግዲህ ይሄንን ነዉ የምንቃወመው። «ለአገራችን የሚያዋጣዉ ዘር ላይ ማተኮር ሳይሆን፣ሥራ ላይ ማተኮር ነዉ። መመዘን ያለብን በዘራችን ሳይሆን በስራችን መሆን አለበት» እያልን ነዉ።
አፋን ኦሮሞ፣ ትግሪኛ፣ ጉራጌኛ፣ ሃምባሻ፣ ቆጮ ….በተለያዩ የአገራችን ግዛቶች ያሉ የተለያዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎችን ፣ ምግቦች …ሁሉም «ኢትዮጵያዊነት» ናቸው። ሁሉም የኢትዮጵያ መገለጫዎች ናቸው። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ አይደለችም። የተለያዩ ባህሎችን ፣ ቋንቋዎች፣ በአጭሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች ያሉባት አገር ናት። ቢራቢሮዎችና አበባዎች የተለያዩ ቀለማቶቻቸው ዉበታቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ዉበቷ ብሄረሰቦቿ ናቸው።
ግርማ ጌታቸዉ ካሳ
ዘብሄረ ኢትዮጵያ ( የዶር ፍቅሬ ቶሎሳን አባባል ልዋስና)
የኦህደድ እና ኦነግ ፖለቲካ «ኦሮሞዉን» ጎድቷል – አማኑኤል ዘሰላም
የኢትዮጵያ ፈዴራል ሕገ መንግስት አንቀጽ 46 «ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ የማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት ነዉ» ይላል። አንቀጽ 47 ደግሞ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሩፑብሊክ አባላት የሆኑቱን ክልሎች ይዘረዝራቸዋል። እነርሱም የትግራይ፣ የአፋር ፣ የአማራ፣ የሱማሌ፣ የቤኔሻንጉል/ጉሙዝ፣ የደቡብ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች እና የሃረሪ ሕዝብ ክልሎች ናቸው።
የዚህን የፌደራል ክልልን በተመለከተ በክልሎች እየታዩ ያሉትን አንዳንድ ሁኔታዎች ለማሳየት እንሞክራለን። ከትልቁ ክልል ኦሮሚያ እንጀምር።
ኦሮምኛ የማይናገሩትን የማግለል ዘረኛ አሰራር
ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ ሃያ ዞኖች አሉ። ሶስቱ «ልዩ ዞኖች» ይባላሉ። ናዝሬት/አዳማን ያካተተ፣ የአዳም ልዩ ዞን፣ ጂማን ያካተተው፣ የጂማ ልዩ ዞን እና የቡራዮ ልዩ ዞን ናቸው። በነዚህ ዞኖች የመጀመሪያ ቋንቋቸው አፋን ኦሮሞ የሆኑቱ ቁጥራቸው ከ45 በመቶ በታች ነዉ። በአዳማ 26%፣ በጂማ 39% እና በቡራዮ 44% ናቸው።
በአሥራ ሶስቱ ሌሎች የኦሮሚያ ዞኖች አፋን ኦሮሞ የመጀመሪያ ቋንቋቸው የሆኑ ከ90 % በታች ናቸው። እነዚህም ምስራቅ ሸዋ ( 69%)፣ ጉጂ (77%) ፣ አርሲ ( 81%)፣ ሰሜን ሸዋ ( 82%)፣ ደቡብ ምስራቅ ሸዋ (84%)፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ (85%) ፣ ምእራብ አርሲ (87%)፣ ምስራቅ ወለጋ ( 88%) ፣ ምእራብ ሃረርጌ (89 %)፣ ኢሊባቡር (90%) ፣ ጂማ – የጅማ ከተማ አካባቢ ( 90%)፣ ባሌ (90%)፣ ቦረና (90%) ናቸው። እንግዲህ ከሃያ የኦሮሚያ ዞኖች፣ በአሥራ ስድስቱ፣ ምን ያህል አፋን ኦሮሞ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያን በስፋት እንዳሉ እያየን ነዉ። በአራት የኦሮሚያ ዞኖች፣ በአፋን ኦሮሞ አፋቸዉን የፈቱ፣ ከዘጣና ሶስት በመቶ በላይ ናቸው። እነርሱም ምእራብ ወለጋ (97%) ፣ ምእራብ ሸዋ (93%)፣ ምስራቅ ሃረርጌ፣ (94%)፣ ቀለም ወለጋ ( 94%) ናቸው።
አሁን በሥራ ላይ እየተተገበረ ያለው የኦሮሚያ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ 33 «በክልሉ ዉስጥ ነዋሪ የሆኑና የክልሉን የሥራ ቋንቋ የሚያውቅ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በማንኛዉም የክልሉ መንግስታዊ ወይም ሕዝባዊ ሥራ ተመርጦ ወይም ተቀጥሮ የመስራት መብት አለዉ።» ይላል። አንቀጽ 5 ደግሞ « ኦሮምኛ የክልሉ መንግስት የሥራ ቋንቋ ይሆናል። የሚጻፈዉም በላቲን ፊደል ነው» ይላል።
74% የአዳማ፣ 61% የጂማ ከተማ ፣ 56% የቡራዩ ዞን፣ 31% የምስራቅ ሸዋ ዞን፣ 23% የጉጂ ዞን ፣ 25% የሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን፣ 23% የምእራብ አርሲ ዞን … ነዋሪዎች የመጀመሪያ ቋንቋቸው አፋን ኦሮሞ ባላመሆኑ፣ አፋን ኦሮሞ ካልተማሩ በቀር፣ የመመረጥ፣ በኦሮሚያ ክልል የመስራት መብት የላቸውም። ይህም አማርኛና ሌሎች ቋንቋዎች የሚናገሩ፣ በኦሮምያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን እንደ ሁለተኛና ሶስተኛ ዜጋ እንዲቆጠሩ የሚያደርግ ነዉ። በብሄረሰብ መብት ስም የግልሰበ መብት እየተረገጠ ነዉ።
«ኦሮሚያ ፈርስት» የሚል እንቅስቃሴን የሚመራው ጃዋር ሞሃመድ፣ አንድ ወቅት «Ethiopians Out from Oromia» የሚል መፈክር ያሰማበትን ቪዲዮ ተመልክቻለሁ። ጃዋር በአጭሩ አነጋገር፣ ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ብቻ እንደሆነችና ሌሎች «ኦሮሞ» ያልሆኑ፣ በኦሮሚያ ዉስጥ እንግዶች፣ ኦሮሞዎች ሲፈቅዱላቸው ብቻ ሊኖሩ የሚችሉ እንደሆኑ ነው የነገረን። ይህ የጃዋር አባባል፣ ብዙዎችን እንዳስገረመ ተመልክቻለሁ። ነገር ግን አንድ የዘነጋነው ነገር ቢኖር፣ ይህ የጃዋር አባባል ፣ ጃዋር የፈጠረዉ ሳይሆን በኦሮሚያ በአሁኑ ሕግ መንግስት፣ በሰነድ የተቀመጠ እንደሆነ ነዉ።ይህ አይነቱን ዘረኛ የጃዋር አባባል፣ የኦሮሚያ ክልል «ሕግ» ይደግፈዋል። ስለዚህ ትኩረታችንን ከጃዋር አዙረን ወደ ኦሕደድ/ኢሕአዴግ እንዲሁም ኦነግ ማዞር አለብን።
የኦሮሚያ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ ስምንት «የኦሮሞ ሕዝብ የክልሉ የበላይ ስልጣን ባለቤት ሲሆን ..» ሲል የኦሮሚያ ባለቤት «ኦሮሞው» ብቻ እንደሆነ ነው ያስቀመጠው።
ኦሮምኛ ተናጋሪው በኢኮኖሚ እንዲጎዳ ያደረገ ጎጂ ፖለቲካ
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ፖሊሲን ካየን ደግሞ፣ አዲስ አበባ አካባቢ ያሉ እንደ አዳማ/ናዝሬት ያሉ ቦታዎች ሕዝቡ ተቃዉሞ ስላስነሳ፣ በዚያ ተማሪዎች አማርኛም ከአፋን አፋን ኦሮሞ ጎን ለጎን እንዲማሩ ከመደረጉ በስተቀር፣ በኦሮሚያ የሚኖሩ ተማሪዎች አማርኛ እንዲማሩ አይደረግም። አማርኛ ማንበብና መጻፍ አይችሉም።
አንድ የግል ባለሃብት ከአዲስ አበባ ሄዶ አንድ ኩባንያ በአንድ የኦሮሚያ ከተማ ይመሰርታል። ሰራተኞች ቀጥሮ ያሰራል። ሰራተኞቹ ስራቸዉን በተመለከተ፣ ሪፖርት ማቅርብ ሲጠበቅባቸው ሪፖርት ሳያቀርቡ ይቀራሉ። አለቃቸው ያስጠራቸዉና ይጠይቃቸዋል። ሪፖርታቸውን በቃል ያቀርቡለታል። «እሺ በፋይል እንዲቀመጥ በጽሁፍ አምጡልኝ» ሲላቸው፣ ማንገራገር ጀመሩ። «ጌታዬ እኛ አማርኛ መጻፍ አንችልም። በቁቤ እንጻፈዉና ከፈለጉ ያስተርጉሙት፤ ወይም እኛ አስተርጉመን እንመጣለን» ይሉታል። ሰዎዬዉ ባንድ በኩል ቢናደድም፣ በሌላ በኩል አዘነ። ቢዝነስ ነዉና፣ ለስራው ብቃት ከሌላቸው ሰራተኞቹ ማባረር ግድ ሆነበት።
አማርኛን የመጥላት የኦህደድ እና ኦነግ ፖለቲካ ፣ ዜጎች አፋን ኦሮሞን ያዉም በቁቤ ብቻ እንዲማሩ በማድረግ፣ ትልቅ የኢኮኖሚ ጉዳት በ«ኦሮሞዎች» ላይ አድርሷል። እዚህ ላይ «ብቻ» የሚለውን ቃል እናስምርበት። በትግራይ ከአንደኛ ክፍል ጀመሮ ከትግሪኛ ጎን አማርኛ እንዲማሩ ይደረጋል። የኦሕደድ ባለስልጣናት እነ አባ ዱላ ገመዳ፣ ኩማ ደመቅሳ የመሳሰሉት ልጆቻቸዉን የሚያስተምሩት በአዲስ አበባ ሃሪፍ ትምህርት ቤቶች ነዉ። ሃብታም የሆኑና አቅሙ ያላቸው ልጆቻቸውን ወደ አዲስ አበባ እየላኩ ያስተምራሉ። ለምን ቁቤ ብቻ ተምረው ልጆቻቸው የትም እንደማይደርሱ ስለሚያወቁ።
የግል ኢንቨስተሮች የሥራ ቋንቋቸው በኦሮሚያም ሳይቀር በብዛት አማርኛ ነዉ። በናዝሬት፣ በጂማ በመሳሰሉት ቦታዎች ሂዱ፣ የንግድ ተቋማት፣ የግል መስሪያ ቤቶች .. የሚጠቀሙት አማርኛን ነዉ። ከክልል መንግስት ጋር አንዳንድ ደብዳቤዎች መላላክ ካስፈለገ ፣ የክልሉን የአፋን ኦሮሞ ብቻ ፖሊስ ሕግን ለማክበር ፣ ተርጓሚ ይቀጥራሉ።
በኢትዮጵያ ካሉ 9 ክልሎች በአራቱ (አማራዉ፣ ደቡብ፣ ጋምቤላና ቤኔሻንጉል ጉሙዝ) ክልሎች፣ እንዲሁም በአገሪቷ መዲና አዲስ አበባ፣ በድሬደዋ የሥራ ቋንቋ አማርኛ ነው። የፌደራልም ቋንቋ አማርኛ ነዉ።
በመሆኑም ኦሮሚያ ያለው የቁቤ ትዉልድ፣ በፌደራል መንግስት ዉስጥ ተቀጥሮ የመስራት አቅሙ ዜሮ ነዉ። እንደ ባህር ዳር፣ አዋሳ፣ ድሬደዋ፣ አዲስ አበባ በመሳሰሉ ታላላቅ ከተሞች ለመኖርና ለመስራት፣ ለመቀጠር በጣም ይቸገራል። በአጭሩ፣ ይህ የኦሮሚያ ክልል አሰራር፣ የኦሮሚያ ተማሪዎች፣ በኢኮኖሚ እንያድጉና እንዳይሻሻሉ ትልቅ ማነቆ ነው እየሆነባቸው ያለዉ። በሌሎቹ ክልል ካሉ ጋር ሲወዳደሩ ወደኋላ ቀርተዋል። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የኦነግ መሪዎች ልጆቻቸው በበርሊን፣ ሚኒሶታ …በመሳሰሉ ቦታዎች እያስተማሩ ነዉ። አማርኛም ባያወቁ፣ እንግሊዘኛ እስካወቁ ድረስ ችግር አያጋጥማቸዉም። የኦህደድ መሪዎች ልጆቻቸውን ሃሪፍ ትምህርት ቤቶች ነዉ በአዲስ አበባ የሚያተምሩት። ድሃዉና ምስኪኑ የኦርሚያ ተማሪ ግን፣ አጥር ታጥሮበት፣ በአጉል የኦሮሞ ብሄረተኘንት ስም እንዲተበተብ ተደርጎ ጉዳት እየደረሰበት ነዉ።
ይህ በኦሮሚያ የሚኖሩት ወገናችን በኢኮኖሚ፣ በትምህርት ፖሊሲ ረገድ እየደረሰባቸው ካለው ግፍ በተጨማሪም፣ ኦነግ እየተባሉ በሺሆች የሚቆጠሩ እየታሰሩና እየተሰቃዩ ናቸው። ሕወሃት/ኢሃዴግ በአንድ በኩል እነሌንጮን፣ ቀንደኛ ኦነጎችን፣ እያባበለና እያቀፈ፣ በሌላ በኩል የነሌንጮ ደጋፊ ናችሁ እያለ ሰላማዊ ዜጎችን ያስራል።
ታዲያ መፍትሄዊ ምንድን ነዉ ? አራት ነጥቦች ላስቀምጥ፡
1. ኢትዮጵያዉያን አፋቸዉን በየትኛው ቋንቋ ነዉ የፈቱት የሚለዉን ጥያቄ ብንጠይቅ ፣ በአንደኝነት የሚቀመጠዉ ኦሮምኛ ነዉ። በበርካታ ዞኖች ከዘጠና በመቶ በላይ ኦሮምኛ የሚነገርባቸው ቦታዎች አሉ። 33.8 % የሚሆነው ሕዝባችን አንደኛ ቋንቋዉ አፋን ኦሮሞ ነዉ። 29.36% የሚሆነው ህዝብ አማርኛ አንደኛ ቋንቋዉ እንደመሆኑ፣ አማርኛን ወይንም ኦሮምኛን እንደ አንደኛ ቋንቋ የሚናገሩ 63.2% ይደርሳሉ። በመሆኑም ኦሮሞኛ ከአማርኛ ጎን የፌደራል ቋንቋ ቢሆን ትልቅ ጥቅም ይኖረዋል። ቢያንስ አማርኛ ፊደል የማያነበው፣ የጠፋው አንዱ የቁቤ ትዉልድ በፌደራል መሥሪያ ቤቶች የመስራት እድል ያጋጥመዋል።
2. በሁሉም ክልሎችና ወረዳዎች፣ በአካባቢዉ ከሚነገረው ቋንቋ ጎን ለጎን፣ ተማሪዎች አማርኛ እንዲማሩ መደረግ አለበት። አማርኛ እንደ አንደኛ ቋንቋ 29.3% የሚሆነው ሕዝብ ይናገረዋል። እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ደግሞ፣ ከ30፣ 40 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ሊናገረው ይችላል ብዬ አስባለሁ።በመሆኑም አማርኛ ማወቅ ጥቅም አለው። ቋንቋ በአጠቃላይ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። አማርኛን መማር ኦሮሞኛን አይጎዳም። የኦሮሞ መሪ ነን የሚሉ ፖለቲከኞች፣ ለራሳቸው ልጆች እንዳሰቡት፣ ለተቀረዉም የኦሮሞ ልጅ ሊያስቡ ይገባል ባይ ነኝ።
እነርሱ አቀላጥፈው አማርኛ መናገር፣ ማንበብ መጻፍ እንደሚችሉትም ሌላዉን እነርሱ ታገኙትን እድል ማሳጣት የለባቸውም። እስቲ አስቡት አሁን አባ ዱላ አማርኛ መጻፍና ማንበብ ባይችል ኖሮ የፓርላማ አፈጉባኤ ይሆን ነበር ? ዶር ነጋሶ ፕሬዘዳነት መሆን ይችሉ ነበር ? እያልን ያለነዉ እኮ የኦሮሞ ወጣት፣ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፣ አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ ዶር ዲማ ነግዎ፣ ጀነራል ከማል ገልቹ ፣ ዶር መራራ ጉዲና ያገኙት እድል ያግኙ ነዉ። አፋን ኦሮሞም ይማሩ፤ አማርኛም ይማሩ።
3. የኦሮሚያ ክልል መንግስት አማርኛን ከኦሮሞኛ ጎን የሥራ ቋንቋ ማድረግ አለበት። ኦሮሞኛ የማይናገር በክልሉ አስተዳደር ዉስጥ የመስራት መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል። በኦሮሚያ 95% ነዋሪዉ ኦሮሞኛ የሚናገር ቢሆን፣ እሺ አንድ ነገር ነዉ። ግን ከ 15% በመቶ በላይ ሕዝብ አንደኛ ቋንቋም ኦሮሞኛ ባልሆነበት፣ «አፋን ኦሮሞ ብቻ ወይንም ሞት» ማለት ትልቅ ስህተት ነዉ። ዘረኝነትም ነዉ። በክልሉ ዋና ከተማ አዳማ/ናዝሬት እንኳን ፣ አንድ አራተኛ ሕዝብ ብቻ ነው ኦሮሞኛ የሚናገረው።
4. ናዝሬት/አዳም እና ጂማ የመሳሰሉ እንደ አዲስ አበባና ድሬደዋ፣ ለጊዜዉ ቻርተር ከተማ ቢሆኑ መልካም ነዉ። (ለዘለኬታዉ፣ ለሁሉም በሚበጅ፣ የተለያዩ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባና በተጠና መልኩ ፣ፌደራል አወቃቀሩ እንደገና በአዲስ የሚዋቀርበትን ሁኔታ በመፈለግ ለብዙ ችግሮች መፍቴሄ ማግኘት ይቻላል)
ከላይ የዘረዘርኳቸዉ አሃዞች በኦፊሴል ከተመዘገበዉ የኢትይጵፕያ ሕዝብ ቆጠራ ሪፖርት ነዉ። በሚቀጥለው ጊዜ የቤኔሻንጉል ጉምዝ እና ሃረሪ ክልሎችን እንመለከታለን።
[የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] የፍርድ ቤቱ ውሎ ይህን ይመስል ነበር – ከቤዛ ለኩሉ ሰንበት ት/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ከሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የቤዛ ኩሉ የሰንበት ትምህርት ቤት ለሕዝብ ያወጣው መረጃ ለዘ-ሐበሻ ደርሷል። የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሕዝብ ግንኙነት ያሰራጨው ዜና እንደወረደ ይኸው፦
የቤተክርስቲያን ውሎ በጲላጦስ አደባባይ
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን
ዛሬ ቤተክርስቲያናችን በጲላጦስ አደባባይ ላይ እንደምትቆም ስላወቃቸሁ ግማሾቻችሁ በአካል በመገኘት፤ አብዛኞቻችሁ ድግሞ ካላችሁበት ቦታ “እለት እለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሃሳብ ነው” እንዳለ ቅዱሱ ሐዋርያ (ቆሮ ፲፩፡፳፰) ( በፀሎትና እንባ ቀኑን ለቤተክርስቲያን ድል የሆን ዘንድ ፀልያችኋል አልቅሳችኋል።
የእግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን ውሳኔው ይህን ይመስል ነበር……
፬ቱ የቦርድ አባላት (አቶ ጥበቡ፤ ቀስስ አዲስ፤ ወ/ሮ ደብረ ወርቅና አቶ አዳም) የቤተክርስቲያን አስተዳደሩን የከሰሱት በነዚህ ነጥቦች ዙሪያ ነበር…
1- – የሕዝቡን ውሳኔ አንቀበልም አሉ
2-ያለ ሊቀ መንበርና ም/ሊመንበር ፍቃድ ያደረጉት የ January 23, 2014 ስብሰባ ሕጋዊ አይደለም
3- አቶ ጥበቡን ከሊቀመንበርነት አወረዱ
እነሱ ዳኛዋ እንድትወስን የፈለጉት….
1- በ ጃንወሪ 23 የተጠራው የቦርድ ስብሰባ ኢ-ሕጋዊ አይደለም ዳኛዋ እንድትል
2- ምንም አይነት ስብሰባ እስከ ፌብ 23 ቦርዱ እንዳያደርግ፡ ለጊዜው እንዲታገድ (Temporary injunction)
3- ፍራቻቸው– ብር ያዘዋውርሉ፡
ይህንን ሁሉ ክስ ዳኛዋ ከአዳመጠች በኋላ ያቀረቡትን ሁሉ ክስ ውድቅ አድርጋለች። ስለዚህ በ ጃንዋሪ 23 የተደረገውን የቦርድ ስበሰባ ሕጋዊነቱን ዳኛዋ አስድቃለች። ነገር ግን እንደ መተዳደሪያ ደንቡ መሠረት (by law) ጠቅላላ ጉባዔ ሲጠራ የአቶ ጥበቡን ከሥልጣን መውረድና የአቶ ይመርን ሊቀመንበርነት ጠቅላላ ጉባዔው ያፀድቃል። እሰከዛ ድረስ አቶ ይመር ሕጋዊው ሊቀመንበር ናቸው። አቶ ጥበቡ በቦርድ ስብሰባ መሳተፍ አይችሉም። ባንኩኑም ቦርዱ unfreeze አድርጎ መደበኛ አገልግሎቱን ይቀጥላል።
-የ፬ቱ ካሳሾች ጠበቃ፤ ቀሲስ አዲስ ወደፊት የሚጠራውን ስብሰባ እንዲመራ ጥያቄ (recommendation) አቅርበዋል። ቦርዱም ለስብሰባ ሲቀመጥ ይወያይበታል።
የፌብ 23 ጠቅላላ ጉባዔ ይኑር አይኑር ወይንም ወደፊት ይራዘም የሚወስኑት ቦርዱ ነው እንጂ አቶ ጥበቡ በቦርድ ስብሰባ ምንም ተሳትፎ ከአሁን በኋላ አይኖራቸውም።
- March 10 2014 የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተይዟል
እንግዲህ ቅድስት ቤተክርስቲያን በራሷ ልጆች ተጎትታ በዛሬው አማኑኤል ቀን (ጥር 28. 2006 ዓ/ም) የፍርድ ቤት ውሎዋ በአጭሩ ይህን ይመስል ነበር።
በእግዚአብሔርም ክብርም ተስፋ እንመካለን። የህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን በመከራችን ደግሞ እንመካለን በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። (ሮሜ ፭፡፪-፭)
ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥
2ቆላስይስ 3፡23
ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ
- ግርማ ካሳ
ከበደ ካሳ የሚባሉ አፍቃሪ ኢሕአዴግ ግለሰብ “አንዳንድ ሰዎች «ብሄር ..?» ተብለው ሲጠየቁ «ኢትዮጵያዊ!!!…» እያሉ የሚመልሱት፣ የራሳቸዉን ማንነት የኢትዮጵያ ማንነት አድርገው ያስቀመጡና በራሳቸው ማንነት የሌሎቹን ለመጨፍለቅ የሚያልሙ – የቅዠት ታንኳ ቀዛፊዎች ናቸው…. ተዛብታችሁ ሌላንም ለማዛባት ለምትፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጂ ብሄር አይደልም። ኢትዮጵያ ሃገር እንጂ የአንድ ሕብረተሰብ ክፍል መለያ አይደለም።” የሚል አባባል ፌስቡክ ላይ ለጥፈው አነበብኩ።
በአንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ሕገ መንግስቱ እንዲህ ይላል ፡
“በዚህ ሕገ መንግስት ዉስጥ «ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸዉን ባህርይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነዉ። ሰፋ ያላ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልዉና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የስነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛዉ በተያያዘ መልክአ ምድር የሚኖሩ ናቸው»
እንግዲህ እዚህ ላይ እናስተዉል። ለብሄር የተሰጠው ትርጉምና ለብሄረሰብ የተሰጠው ትርጉም አንድ አይነት ነዉ። በአጭሩ ብሄር ማለት ብሄረሰብ ማለት ነዉ በሕገ መንግስቱ መሰረት።
ብሄር በእንግሊዘኛ ኔሽንስ ማለት ነዉ። «ዩናይትድ ኔሽንስ» ስንል የተባበሩት መንግስታት (የተባባሩት አገሮች ማለታችን ነዉ) ። እንደሚገባኝ ኢትዮጵያ እንጂ፣ ኦሮሞ፣ ወይንም፣ ትግሬ ወይንም ወላይታ የተባበሩት መንግስታት አባል አይደሉም።
«ብሄር» የሚለዉን ቃል የመጀመሪያ አመጣጥ ስንመለከት ፣ ከግእዝ የተወሰደ እንደሆነ እንረዳለን። ትርጉሙም በግእዝ አገር ማለት ነዉ።
ስለዚህ ኢሕአዴግን እና ኦነግ በሕገ መንግስቱ ብሄር የሚለዉን ቃል ያኔ የወሸቁት፣ ኢትዮጵያን እንደ አንዲት አገር ሳይሆን የተለያዩ የአገሮች ስብሰብ እንደሆነች ለማሳየት፣ በፈለጉ ጊዜ ደግሞ ከኢትዮጵያ ለመለየት አማራጭ እንዲኖራቸው ከመፈለግ የተነሳ ነዉ።
ፕሮፌሰር ተኮላ ሃጎስ ደግሞ ብሄር ብሄረሰብና ሕዝብ የሚለውን ለምን ሕገ መንግስቱ ዉስጥ እንደገባም ሲጽፉ የሚከተለዉን ነበር ያሉት፡
“The phrase “the nations, nationalities and peoples” thus found in the Ethiopian Constitution is a legacy from the writings of immature and juvenile diatribe of badly educated and socially disfranchised and radicalized students of Haile Selassie I University of the 1970s. It is the ersatz voice of Meles Zenawi forcing himself through the 1995 Constitution on the People of Ethiopia his narrow and ignoramus ideas on the history of Ethiopia and the process of nation building”
ስለዚህ «ብሄርህ ምንድን ነዉ ?» ተብሎ አንድ ሰው ሲጠየቅ «ኢትዮጵያዊነት» ብሎ ከመለሰ፣ በትክክለኛዉ የግእዝ አተርጓጎም እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ብሄር የሚለው ቃል ያለው አጠቃቀም አንጻር፣ ትክክለኛ መልስ ነዉ።
«ብሄረሰብህስ ምንድን ነዉ ? » የሚል ጥያቄ ቢነሳስ ?
አንድ መርሳት የሌለብን ነገር አለ። አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የተደባለቀ ነዉ። ሰሜን ጎንደና ሰሜን ወሎ ከሄዳችሁ ትግሪኛ ተናጋሪዉና አማርኛ ተናጋሪዉ ተደበላልቋል። ኦሮሚያ ዉስጥ በሸዋ፣ በሰሜን እና በምስራቅ ወለጋ..፣ አማራዉ ክልል ደግሞ በወሎ ፣ ኦሮሞኛ ተናጋሪው ከአማርኛ ተናጋሪው ተደባልቋል። በምስራቅ ሃረርጌና በባሌ ደግሞ ሶማሌዉና ኦሮሞዉ የተደባለቀበትም ሁኔታ አለ። በደቡብ ክልል ከሄድን፣ ወላይታዉ ከሲዳማው፣ ከንባታዉ ከሃዲያዉ …ሁሉም ተበራርዟል። ስለዚህ በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የብዙ ብሄረሰቦች ድብልቅ ናቸው። በመሆኑም «ብሄረሰብህ ምንድን ነዉ?» ተብለው ሲጠየቁ እዚም እዚያም በመሆናቸው፣ ለመመለስ ይቸግራቸዋል። ስለዚህ በአጭሩ በብሄረሰባቸው ወይንም ዘራቸው ሳይሆን በኢትዮጵያዊነታቸው መለየትን ይመርጣሉ። ከነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነኝ።
አቶ ከበደ፣ ኢትዮጵያዊያን፣ ብሄራችን ኢትዮጵያዊነት ነው ማለታቸው፣ የሌሎችን ማንነት ለመጨፍለቅ እንደመሞከር አድርገውም ወስደዉታል። አንድ ሰው «ኦሮሞ ነኝ፣ ትግሬ ነኝ ወዘተረፈ » የማለት መብቱ ከተከበረለት፣ ሌላው «አይ እኔ በዘሬ መለየት አልፈልግም፣ በኢትዮጵያዊነቴ ነዉ መለየት የምፈልገው » ካለ የርሱስ መብት ለምን አይከበርለትም ? ኦሮሞ፣ ወይም ትግሬ ፣ ወይም አማራ ያለመባል መብቱ መጠበቅ የለበትምን?
በኢሕአዴግ መንግስት፣ ይሄ መሰረታዊ መብት እየተጠበቀ አይደለም። እያንዳንዱ ዜጋ፣ እነርሱ ብሄር ብሄረሰብ የሚሉት አንዱ የዘር ሳጥን ዉስጥ መግባት አለበት። ያ ካልሆነ መታወቂያ እንኳ ማግኘት አይቻልም።
እንግዲህ ይሄንን ነዉ የምንቃወመው። «ለአገራችን የሚያዋጣዉ ዘር ላይ ማተኮር ሳይሆን፣ሥራ ላይ ማተኮር ነዉ። መመዘን ያለብን በዘራችን ሳይሆን በስራችን መሆን አለበት» እያልን ነዉ።
አፋን ኦሮሞ፣ ትግሪኛ፣ ጉራጌኛ፣ ሃምባሻ፣ ቆጮ ….በተለያዩ የአገራችን ግዛቶች ያሉ የተለያዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎችን ፣ ምግቦች …ሁሉም «ኢትዮጵያዊነት» ናቸው። ሁሉም የኢትዮጵያ መገለጫዎች ናቸው። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ አይደለችም። የተለያዩ ባህሎችን ፣ ቋንቋዎች፣ በአጭሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች ያሉባት አገር ናት። ቢራቢሮዎችና አበባዎች የተለያዩ ቀለማቶቻቸው ዉበታቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ዉበቷ ብሄረሰቦቿ ናቸው።
ግርማ ጌታቸዉ ካሳ
ዘብሄረ ኢትዮጵያ ( የዶር ፍቅሬ ቶሎሳን አባባል ልዋስና)
“ስለአጼ ቴዎድሮስ እና አጼዮሐንስ መዝፈን የሚቻለው እነርሱ የሞቱለትን መሬት አሳልፈን ካልሰጠን ነው” – ኢንጂነር ይልቃል (ቪድዮ)
ኢ.ኤም.ኤፍ – የግንቦት 7 የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ – ያሬድ ኃይለማርያም
ኢ.ኤም.ኤፍ – የግንቦት 7 የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ – ያሬድ ኃይለማርያም
አቶ አስራት ጣሴ ታሰሩ
(ዘ-ሐበሻ) የኢሕአዴግ አስተዳደር ለፕሮፓጋዳና ዜጎችን ለማስፈራሪያ የሠራውን “አኬልዳማ” ዶክመንታሪ ፊልም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከታየ በኋላ በፊልሙ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል፤ መንግስትንም ዘልፈዋል በሚል የተከሰሱት የአንድነት ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ አስራት ጣሴ ታሠሩ።
ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በፊልሙ ላይ የተሰማቸውን አስተያየት ሰጥተዋል የሚባሉት አቶ አስራት በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ አስተያየታቸውን በመስጠታቸውና በዚህ ጽሑፍ ላይም መንግስት ላይ ዘለፋ አዘል ቃላት ተጠቅመዋል በሚል ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ የተላለፈባቸው ሲሆን፤ በዚህም መሠረት ዛሬ ፌብሩዋሪ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቢቀርቡም፤ የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤቱም ለ7 ቀናት ያህል ታሰረው በቀጣይ ሳምንት እንዲቀርቡ የ እስር ት ዕዛዝ በማስተላለፉ አቶ አስራት ጣሴ ወህኒ ወርደዋል።
የዘ-ሐበሻ የአንባቢያን አስተያየት ይጠበቃል።
የብዕር ዕጢ – መናጢ
ከሥርጉተ ሥላሴ 07.02.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
ዛሬ ልተርብ ሳይሆን ከልብ ሆነን በጎርባጣ መንገዶች ሊያስጉዙን የሚሽቱትን ፈንጋጣ ስሜቶች ከልብ ሆነን ባትኩሮት እንመረምር ዘንድ ፈለግሁኝ። ብላሽ – ዬቀለም ብዕር …. ሲባዛ መንፈስን ይበጥሳል ሲያንሰ ይሸረሽራል። ለመሆኑ ማንና ምን እንዲመራን እንፍቅዳለን? ናፍቆታችንስ ምንድን ነው?!
ህም! ቀዶ ጥገና ማድረግ ሽው አለኝ። ዖዬ! በምኞት ቀረ እንጂ የወጣልኝ የባይወሎጂና የኬሚስትሪ ትጉህ ተማሪ ነበርኩኝ። ያ .. ቢቀር ደግሞ ቢያንስ በደም ውስጥ የመርዝ መስኖ ቦይ ለከፈተ ባለ ዕጢ ብዕረ- በዝውውሩ ላይ ማዕቀብ ጥሎ ወደ ሆስፒታል ጎራ በማደረግ የተበከለውን ደም አጣርቶ በንጡህ ደም መተካት ግድ ይላል። የትውልዱ ንጹህ መንፈስ እጅ የሚያነሳ ወደርየለሽ ቅዱስ መንፈስ ሆኖ፤ የባለ ዕጢዋ ግን በካይ ሆነብን። ስለሆነም ግራ ቀኙን በንጽጽር በማቅረብ ለስሜታችንና ለፍላጎታችን የራቀውን ገፍቶ፤ የቀረበውን ማጣጣም ሸጋ ነው። ለነገሩ ባለ ዕጢዋ ብዕር ድሃ አይደለችም ምን አጥታ ዲታ ናት። መልክ ጥፉም አይደለችም ደም- ግቡ ናት። ነገር ግን ጣል ጣል የምታደርጋቸው ማላታይሎች ነገ ከመምጥቱ ቀድማ ችግር ጠሪ በመሆኑ ትፈተሽ፤ ትበርበር ተብሎ ብይን ተላላፈባት — እንዲህ ከወደ ሲዊዘርላንድ …..
የአንዷለም አራጌ የውሳኔ አሁንም ቀጠሮ ተራዘመ፤ ኢሕአዴግ 4 የአንድነት አመራሮችን ሊያስር መሆኑ ተሰማ
(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያውያን ዘንድ የዓመቱ ምርጥ ሰው በሚል የተሰየመው ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ በካንጋሮው ፍርድ ቤት ዕድሜ ልክ ዕስራት እየተፈርደበት መሆኑ ይታወሳል። ወጣቱ ፖለቲከኛ ለሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ለውሳኔ ከተቀጠረ በኋላ አሁንም እንደዚህ ቀደሙ ቀጠሮው መራዘሙን የዜና ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ጠቁመዋል።
አቶ አንዷለም አራጌ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ወህኒ እየተሰቃየ ቢሆንም “የእኔን መታሰር ተቃዋሚዎች ሊጠቀሙበት አልቻሉም” ሲል መናገሩ አይዘነጋም። ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረብ የነበረበት አንዷለም በዳኞች የተለመደ ምክንያት ቀጠሮው ለመጋቢት 8 ቀን 2006 እንዲተላለፍ ተወስኗል። ዛሬ አንዷለም ላይ ምን ይወሰን ይሆን የሚለውን ለማየት በርካታ ሰዎች ስድስት ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ታድመው እንደነበርም የደረሰን መረጃ ያመልከታል።
የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘጋቢ ነብዩ ሃይሉ እንደዘገበው ኢህአዴግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱ ተጋለጠ። በዘገባው መሠረት ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ 4 አመራሮችና አባላት እንዲታሰሩ ኢህአዴግ ወስኗል፤ የክስ ቅድመሁኔታዎች በፍርድ ቤት መጠናቀቃቸውን ታውቋል፡፡
የፍትህ ሚ/ር ምንጮች እንዳስታወቁት በኢህአዴግ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ክስ እንዲከፈትባቸውና እንዲታሰሩ የተወሰኑት የአንድነት አባላት በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም የመጀመሪያው ዙር ክስና እስር በ4 አመራሮችና አባላት ላይ ያነጣጠረ ነው ይላል የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘገባ።
“የደወሉላቸውንደንበኛማግኘትአይችሉም”
የኢትዮ-ቴሌኮሟ ቅርፀ-ድምፅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰሞኑን "የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም" ትላለች። ዛሬ (ጥር 29/2006) ግን ማለዳውን ሙሉ ስልኮች ሁሉ "ዝም፣ ጭጭ" ብለው ነው ያረፈዱት። አዲስ አበባን ከስሪ-ጂ (ሦስተኛው ትውልድ የስልክ በይነመረብ ግንኙነት አቅም) ወደ ፎር-ጂ (አራተኛው ትውልድ አቅም) ለማሳደግ፣ ሌሎቹን ክልሎች ደግሞ ወደ ሦስት ትውልድ ለማሳደግ ሥራዎች እየተጣደፉ እንደሆነ በሚደሰኮርበት በዚህ ሰዓት ኔትዎርኩ እንደ ክሪስማስ ዛፍ ብልጭ ድርግም ይል ገብቷል።
በነገራችን ላይ እኛ 1·1% የኢንተርኔት ፔኔትሬሽን (ተዳራሽነት) ላይ ቁጭ ብለን 28% ደረስኩ ብላ እንቁልልጭ የምትለን ኬንያ፣ በሁሉም ቴሌኮም ድርጅቶቿ የሚቀርቡት የስልክ አገልግሎቶች ከ3ጂ በላይ ናቸው። (Keeping up with the Joneses has become mission impossible).
ምትሐተ-ኢትዮቴሌኮም
ዛሬ የገጠመኝ ደግሞ ለየት ይላል። ሌላ ሰው'ጋ እደውላለሁ ብዬ አብሮኝ ያለው ሰው'ጋ ደወልኩ፤ ቢጠራም አይነሳም። ምንድን ነው ነገሩ ብዬ ስመለከተው የደወልኩት አብሮኝ ያለው ሰው'ጋ ነው። "እንዴ የደወልኩት ላንተ ነው፤ አንተ ደግሞ አይሰማህም እንዴ?" ብዬ ሌላኛው ስልክ ላይ መደወሌን ቀጠልኩ። እሱ ደግሞ ኧረ እኔ'ጋ አልደወልክም ብሎ ስልኩን ሲያሳየኝ እኔ ከሌላኛው ሰው'ጋ ማውራት ጀምሬ ነበር። ከዚያ አብሮኝ ያለው ሰው የስልኩን ስክሪን ዓይኔ ላይ አምጥቶ ደቀነው። "befeqe is calling..." ይላል። "ኧረ እኔ ከሌላ ሰው'ጋ እያወራሁ ነው!" አብሮኝ ያለው ሰው ስልኩን ሊያነሳ ሲሞክር እምቢ አለው። ሁኔታውን 'ምትሐተ-ኢትዮቴሌኮም' ብለነዋል።
ስልኮቹ በተመሳሳይ ሰዓት ካልተገናኙ (synchronized ካልሆኑ) ማውራት አይቻልም። እንዲህ ዓይነቱ መቀዣበር የሚፈጠረው ስልኮች ሲጠለፉ ነው። ኢትዮቴሌኮም (ወይም ወዳጆቹ) ስልኬን አይጠልፉም ብዬ ባልጠረጥርም የሁሉንም ሰው ስልክ ይጠልፋሉ ብሎ መጠርጠር ይከብደኛል። ፍላጎቱ ቢኖራቸውም አቅም ያንሳቸዋል። የኔትዎርኩ ችግር ደግሞ ባገር የመጣ ነው።
ጠለፋና ማስፋፋት
ሑዋዌይ በአሜሪካ የደኅንነት ቢሮ የጠለፋ ሶፍትዌሮችን እና ሀርድዌሮችን ይጠቀማል በሚል ከገበያ አግዶታል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ከዜድቲኢ ጋር አብሮ የሚሠራው የቢሊዮን ዶላር የኔትዎርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሸልሞታል። ለኛ መንግሥት መሪዎች የአሜሪካው ዜና የምስራች ነው። እንዲያውም ሳስበው ዶ/ር ደብረፅዮን የሑዋዌይን ኃላፊ "እስኪ የሚወራባችሁን ነገር እኛ ላይ ተግብሯትና ይህን ሕዝብ ሲያወራ እንስማው" የሚሉት ይመስለኛል።
ግሎባል ኢንተርኔት ሴኩሪቲ በሪፖርቱ እንደነገረን ተንቀሳቃሽ ስልኮች በኢትዮጵያ ከ3% (እ.ኤ.አ. በ2008) ወደ 18% በ2012 ተዳርሷል። እድገቱ ሸጋ ነው፤ ከጎረቤቶቻችን አንፃር ካላየነው ማለቴ ነው። ከነዚህ ወስጥም ኢንተርኔት የሚሠሩት ስልኮች 6·2% ብቻዎቹ ናቸው።
እንደ ትራንስፎርሜሽን እና ዕድገቱ ዕቅዱ ከሆነ ግን 40 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ተንቀሳቃሽ ይኖራቸዋል። ዶ/ር ደብረፅዮን እንደነገሩን ደግሞ ሌሎች 16 ሚሊዮን የሚደርሱ 3 እና 4ጂ የሚሠሩ ስልኮች ሲጨመሩ 56 እናዳርሳቸዋለን ተብሏል። ማስፋፊያው ሲጨረስ 85% ሕዝቡን የሚያዳርስ የተንቀሳቃሽ ስልክ እናቀርባለን ተብሎ ታቅዷል። 'See Separate' የተባለ ድርጅት ግን በ2015 እ.ኤ.አ. ቁጥሩ 99·6 ሚሊዮን ይደርሳል ከተባለው ሕዝባችን ውስጥ 34·2 ሚሊዮን የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ብቻ እንደሚኖሩ (ከዕቅዱ'ጋ ሲነፃፀር 22 ሚሊዮን ያነሰ እንደሚሆን) በሒደቱ (projection) ገምቷል።
የታቀደው ግብ ቢመ'ታ መልካም ነበር። ግን ከታቀደው በታች ተፈፅሞም፣ ጥራቱ ተጓድሎም እንዴት ይሆናል? እስከዛሬ በሁሉም ዘርፎች ላይ የዘገየንባቸው ነገሮች ላይ ከሚሰጡ እልፍ ሰበቦች ውስጥ 'በተዳራሽነት ብዛት ላይ ስናተኩር ጥራት አመለጠን' የሚለው ይገኝበታል። ሁለቱም ላይ ካላተኮርን ሌላ ምን ላይ አተኩረናል ሊባል ነው?
ከሁሉም ግን ስጋቴ የደወሉላቸውን ደንበኛ ማግኘት፣ በፈለጉት ጊዜ የማይችሉ 56 ሚሊዮን የስልክ ደምበኞች እንዳናፈራ እሰጋለሁ።
አቡጊዳ – አመራር አባልና የቀድሞ ዋና ጸሃፊ አቶ አስራት ጣሤ ታሰሩ
የአንድነት ፓርቲ ለበርካታ አመታት በዋና ጸሃፊነት ያገለገሉት አቶ አስራት ጣሴ መታሰራቸዉን የአንድነት ፓርቲ ሚሊየም ድምጽ፡ለነጻነት ፌስቡ ገጽ ዘገበ።
«የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ፣ በክስ ሂደት ላይ የነበረው የአኬልዳማ ዶክመንተሪ በድጋሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መታየቱን ተከትሎ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ከፃፉት አስተያየት ጋር በተያያዘ “ዘለፋ አዘል ጽሑፍ” ጽፈዋል በሚል ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ በተላለፈባቸው መሰረት በዛሬው እለት በፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የተገኙ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ለ7 ቀን ታስረው በቀጣዩ ሳምንት እንዲቀርቡ በማለት የእስር ትዕዛዝ ወስኖባቸዋል » በሚል ነበር ዘገባው የቀረበዉ።
በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶ ነጻነት እንደሌላዉ የሚታእቅ ሲሆን፣ በአቶ አሥራት ጣሴ ላይም ሆነ በሌሎች የተቃዋሚ አመራር አባላት ላይ እየታዩ ያሉ ጥቃቶች፣ፍርድ ቤት ወለድ ሳይሆኑ፣ ሆን ተብሎ አንድነትን ለማዳከም ከኢሕአዴግ ጽ/ቤት በመጣ መመሪያ መሰረት መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ።
በሦስት የመንግስት ተቋማት ላይ አንድነት ፓርቲ ክስ መሰረተ – በአሸናፊ ደምሴ
ሕገ-መንግሥቱ የሚፈቅድልኝን ሰላማዊ ሰልፍ እንዳላካሂድ ከልክለውኛል፤ አባላቶቼን ያለአግባብ በማንገላታት አስረውብኛል፤ ቅስቀሳ እንዳላካሂድ አግደውኛልና ድምፅ ማጉያዎቼን ቀምተውኛል ሲል አንድነት ለዴሞክራሲ ለፍትህና ፓርቲ (አንድነት) በሶስት የመንግስት ተቋማት ላይ ክስ መሰረተ። ፓርቲው በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ፍትሃ ብሔር ችሎት ላይ ክስ የመሰረተባቸው ተቋማት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መሆናቸውን በክስ መዝገቡ ተገልጿል።
ፓርቲው የዘወትር ፖለቲካዊ ስራዎቹን እንዳላያካሂድ መስተጓጉል ተፈጥሮብኛል በማለቱ ክሱ መዘጋጀቱን ለሰንደቅ ያስረዱት የሕግ ባለሙያው አቶ ተማም አባቡልጉ፤ በክስ ዝርዝሩ ውስጥ ፓርቲው በመስቀል አደባባይ የጠራው ሰልፍ እንዳይካሄድ ከመደረጉም በተጨማሪ የቅስቀሳ እገዳ፣ የአባላት መታሰርና የቁሳቁስ መነጠቅ ሁሉ ስለማጋጠሙ በክሱ ውስጥ በዝርዝር ተካቷል ብለዋል።
በከተማዋ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ከፈቃድ ሰጪ አካላት ፈቃድ መገኘት አለበት ቢባል እንኳን ተቋማት የተከተሉት አካሄድ አግባብነት የሌለውና ከሕግም ውጪ በመሆኑ ይህን ለመጠየቅ ክስ መስርተናል ብለዋል። የመንግሥት አካላቱን የሰልፍ እገዳ ተከትሎ አንድነት ፓርቲ ዘጠኝ የሚደርሱ አማራጭ የሰልፍ ቦታዎች ቢያቀርብም አንዱንም ሳይቀበሉ በራሳቸው ምርጫ ጃንሜዳ ላይ ሰልፍ እንዲካሄድ መፍቀዳቸው በሕጉ ላይ ከሰፈረውና ማንኛውም ዓይነት ሰላማዊ ሰልፍ ከጦር ካምፕ በ50 ሜትር ርቀት ላይ መካሄድ አለበት ከሚለው መመሪያ ጋር የማይጣጣም ነው ብለዋል።
ይህም በመሆኑ አንድነት ፓርቲ የመንግስት ተቋማት በጣምራ በመሆን ሕዝብን ለመቀስቀስ የሚደረገውን ጥረት ስልታዊ በሆነ መንገድ አስተጓጉለውብኛል ይላል።
በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተመሰረተባቸውን ክስ አስመልክተው በችሎት በመገኘት የሚሰጡትን መልስ ለማድመጥ ለየካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
አቶ በቀለ ገርባ የእሥር ጊዜያቸውን ቢጨርሱም ሊፈቱ አልቻሉም በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የእስር ጊዜያቸውን ቢጨርሱም ኣመክሮ መከልከላቸው ተሰማ። ህክምናም እያገኙ ኣይደለም ተብሏል። የኮንግረሱ ዋ/ጸኃፊ ለዶቸቬሌ እንደ ነገሩት ከሆነ አቶ በቀለ ገርባ የ 3 ዓመት ከ 7 ወር የእስር ጊዜያቸውን ኣጠናቀው መለቀቅ የነበረባቸው ባለፈው ጥር 11 ቀን ነበር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሺን በበኩሉ የዚህ ኣይነት ቅሬታ እስከኣሁን እንዳልደረሰው ኣስታውቋል። ቀድሞ በዶ/ር መረራ ጉዲና ይመራ የነበረው የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ (ኦህኮ) እና ያኔ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ይመራ የነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፈዲን) ተዋህደው የፈጠሩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር ነበሩ፤ አቶ በቀለ ገርባ። በያዙት ኃላፊነትም ያለ ኣግባብ የታሰሩ ኦሮሞዎችን ጉዳይ እየተከታተሉ ለዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾች እና ለሚመለከታቸው ሁሉ ያሳውቁም ነበር። ይኸው ተግባራቸው ያላስደሰተው የኢትዮጵያ መንግስት ታዲያ የኮንግረሱ ዋ/ጸኃፊ አቶ በቀለ ነጋ እንደሚሉት ኣሸባሪ በሚለው ድርጅት ስም ወንጅሎ ኣስፈረደባቸው። የተፈረደባቸው ስምንት ዓመት ሲሆን በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ወደ 3 ዓመት ከ 7 ወር ተሻሽሎላቸው ነበር ዝዋይ እስር ቤት የከረሙት። አቶ በቀለ ገርባ ከዝዋይ እስር ቤት ጀምሮ ኣሁን በሚገኙበት የቃሊቲ ወ/ቤትም ታመው ህክምና እንዳላገኙም ነው እየተነገረ ያለው። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሺን ሊቀመንበር የሆኑት አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ግን የዚህ ኣይነት አቤቶታ እስከ ኣሁን ኣልደረሰንም ባይ ናቸው። ከኢትዮጵያ መንግስት ወከባና እስራት ሸሽተን በጎረቤት ኣገር እንገኛለን ከሚሉት የኦሮሞ ተወላጆች መካከል ኣንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ስደተኛ በበኩላቸው ከአቶ በቀለ ገርባ በባሰ ሁኔታ ህክምና ተነፍገው የሞቱ የኦሮሞ እስረኞችም ኣሉ ሲሉ ኣንዳንዶቹን ጠቃቅሷል። ከዚሁ በመነሳ የኢትዮጵያ እስር ቤቶች የስራ ቐንቐ ኦሮምኛ ሆኗል እስከማለትም ተደርሷል። የሰብዓዊ መብት ኮሚሺን ሊቀመንበሩ አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ግን ሊደንቀን ኣይገባም ይላሉ። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበሩ፤ አቶ በቀለ ገርባ፤ በተፈረደባቸው ዕለት የፍርድ ማቅለያ ኣስተያየት ይሰጡ ዘንድ እድል ቢሰጣቸውም «ሳላጠፋ የፈረደብኝን ፍ/ቤት ይቅርታ ኣልጠይቅም። ይቅርታ መጠየቅ ካለብኝ የሚጠበቅብኝን ያህል ካልሰራሁለት የኦሮሞን ህዝብ ነው ይቅርታ እምጠይቀው» ሲሉ ችሎቱ ፊት ቆመው መናገራቸው አይዘነጋም። ጃፈር ዓሊ ተክሌ የኋላ
በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የእስር ጊዜያቸውን ቢጨርሱም ኣመክሮ መከልከላቸው ተሰማ። ህክምናም እያገኙ ኣይደለም ተብሏል። የኮንግረሱ ዋ/ጸኃፊ ለዶቸቬሌ እንደ ነገሩት ከሆነ አቶ በቀለ ገርባ የ 3 ዓመት ከ 7 ወር የእስር ጊዜያቸውን ኣጠናቀው መለቀቅ የነበረባቸው ባለፈው ጥር 11 ቀን ነበር::
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሺን በበኩሉ የዚህ ኣይነት ቅሬታ እስከኣሁን እንዳልደረሰው ኣስታውቋል።
ቀድሞ በዶ/ር መረራ ጉዲና ይመራ የነበረው የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ (ኦህኮ) እና ያኔ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ይመራ የነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፈዲን) ተዋህደው የፈጠሩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር ነበሩ፤ አቶ በቀለ ገርባ። በያዙት ኃላፊነትም ያለ ኣግባብ የታሰሩ ኦሮሞዎችን ጉዳይ እየተከታተሉ ለዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾች እና ለሚመለከታቸው ሁሉ ያሳውቁም ነበር። ይኸው ተግባራቸው ያላስደሰተው የኢትዮጵያ መንግስት ታዲያ የኮንግረሱ ዋ/ጸኃፊ አቶ በቀለ ነጋ እንደሚሉት ኣሸባሪ በሚለው ድርጅት ስም ወንጅሎ ኣስፈረደባቸው። የተፈረደባቸው ስምንት ዓመት ሲሆን በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ወደ 3 ዓመት ከ 7 ወር ተሻሽሎላቸው ነበር ዝዋይ እስር ቤት የከረሙት።
አቶ በቀለ ገርባ ከዝዋይ እስር ቤት ጀምሮ ኣሁን በሚገኙበት የቃሊቲ ወ/ቤትም ታመው ህክምና እንዳላገኙም ነው እየተነገረ ያለው። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሺን ሊቀመንበር የሆኑት አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ግን የዚህ ኣይነት አቤቶታ እስከ ኣሁን ኣልደረሰንም ባይ ናቸው።
ከኢትዮጵያ መንግስት ወከባና እስራት ሸሽተን በጎረቤት ኣገር እንገኛለን ከሚሉት የኦሮሞ ተወላጆች መካከል ኣንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ስደተኛ በበኩላቸው ከአቶ በቀለ ገርባ በባሰ ሁኔታ ህክምና ተነፍገው የሞቱ የኦሮሞ እስረኞችም ኣሉ ሲሉ ኣንዳንዶቹን ጠቃቅሷል። ከዚሁ በመነሳ የኢትዮጵያ እስር ቤቶች የስራ ቐንቐ ኦሮምኛ ሆኗል እስከማለትም ተደርሷል። የሰብዓዊ መብት ኮሚሺን ሊቀመንበሩ አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ግን ሊደንቀን ኣይገባም ይላሉ።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበሩ፤ አቶ በቀለ ገርባ፤ በተፈረደባቸው ዕለት የፍርድ ማቅለያ ኣስተያየት ይሰጡ ዘንድ እድል ቢሰጣቸውም «ሳላጠፋ የፈረደብኝን ፍ/ቤት ይቅርታ ኣልጠይቅም። ይቅርታ መጠየቅ ካለብኝ የሚጠበቅብኝን ያህል ካልሰራሁለት የኦሮሞን ህዝብ ነው ይቅርታ እምጠይቀው» ሲሉ ችሎቱ ፊት ቆመው መናገራቸው አይዘነጋም።
ጃፈር ዓሊ
ተክሌ የኋላ
አቡጊዳ – ኢሕአዴግ የአንድነት መሪዎች ለማሰር እየተዘጋጀ እንደሆነ ተዘገበ
የአንድነት ልሳ የሆነዉ ፍኖት ነጻነት፣ ሰበር ዜና ብሎ እንደዘገበዉ፣ ኢሕአዴግ አቶ ዳን ኤል ተፈራን ጨምሮ በርካታ የአመራር አባላትን ለማሰር እየትዘጋጀ እንደሆነ፣ በፍትህ ሚኒስቴር ያሉትን ምንጮች በመግለጽ ዘግቧል።
« አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱን የፍትህ ሚ/ር ምንጮች አጋለጡ፡፡ ምንጮቹ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት በኢህአዴግ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ክስ እንዲከፈትባቸውና እንዲታሰሩ የተወሰኑት የአንድነት አባላት በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም የመጀመሪያው ዙር ክስና እስር በ4 አመራሮችና አባላት ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡» ሲል የዘገበው ፍኖት፣ የክስ ቅድመሁኔታዎች በፍርድ ቤት መጠናቀቃቸውን ገልጿል።
አንድነት መግለጫ – የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የማድረግ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!!!
የዩክሬንን የውስጥ ቀውስ አስመልክቶ የ አሜሪካ ባለስልጣናት የአውሮፓ ህብረትን ሲዘልፉ የሚደመጡበት የስልክ ምልልስ አፈትልኮ ወጣ።
ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩናይትድ ስቴስት ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት ምክትል ሴክሬታሪ ቪክቶሪያ ኑላንድ- በዩክሬን ከ አሜሪካ አምባሳደር ጋር ስለ ዩክሬን ግጭት በስልክ ያወሩት ወሬ ተጠልፎ በድረ ገፆች መለጠፉ አሜሪካን ማሳፈሩን ዘገባዎች አመልክተዋል።
ቪክቶሪያ ኑላንድ በዙሁ የስልክ ምልልስ ላይ ስለዩክሬን ግጭት ሲያወሩ የአውሮፓ ህብረትን ሲወቅሱና በወረደ ቃላት ሲዘልፉ ይሰማሉ። በሁኔታው የደነገጠችው አሜሪካ ፦”ቪክቶሪያ ኑላንድ ለተናገሩት ነገር ይቅርታ ጠይቀዋል” ስትል ፈጥና አስተባብላለች።
በዩክሬን የተቀሰቀሰው ያለመረጋጋት ያከትም ዘንድ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት የሀገሪቱን ፓርቲዎችን ለማስማማት ጣልቃ መግባታቸው ይታወቃል።
ባለፈው ህዳርወር መጨረሻ ላይ ፕሬዚዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች ከአውሮፓ ህብረት ጋር የትብብርና የንግድ ስምምነት ለመፈረም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ በዩክሬን የተነሳው ህዝባዊ አመጽ እስካሁን ሊበርድ አልቻለም።
ዩክሬን ስምምነቱን እንዳትፈርም ጣልቃ ገብታ ጫና የፈጠረችው ሩሲያ ናት ።ሩሲያ በበኩሏ አሜሪካንና የአውሮፓ ህብረትን በጣልቃ ገብነት ትወነጅላለች። የአሁኑ የስልክ ጠለፋ በሩሲያ ሳይካሄድ እንዳልቀረ አሜሪካ እየገለጸች ነው።