Amharic News 1800 UTC –ሴፕቴምበር 11, 2013
ኢትዮጵያ ከ2ኛ የዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረች ሀገር ናት! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
ኢትዮጵያ ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ተከትሎ የተፈጠረች ሀገር ናት። ያም ሆነ ይህ ሌላ ሰው የፈልገው ሊል ይችላል ይህች ኢትዮጵያ በመባል የምትታወቀው ሀገር ግን ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ተከትሎ የመጣ የዓለም ሥርዓት ሥርዓቱ ራሱ በሚመርጣቸው ገዢዎች ይጠቀምባት ዘንድ የፈጠራት ኃይል ናት።
የጽሑፉ ሙሉ ይዘት ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ http://salsaywoyane.wordpress.com/
ይህ ጽሑፉ በጥቂቱ አድራሻቸው ከዚህ በታች ለሰፈረ ድረ ገጾች በሙሉ ተልከዋል::
Esat editor: editor@ethsat.com
addis voice: http://addisvoice.com/
addis dimts: abelewd@yahoo.com
ethiopiazare: ethiopiazare@gmail.com
Ecadf Ethiopia: sebastopol100@gmail.com
EMF ethioforum: media.emf@gmail.com
ETHIO MUNICH: webmaster@ethiomunich.com
Abugida: info@abugidainfo.com
Zehabesha: info@zehabesha.com
ethiomedia: editor@ethiomedia.com
ethiopian review: ethiopianreview8@gmail.com
ethiofreedom: info@ethiofreedom.com
ገድሎ ለቅሶ የሚደርሰው ሥርዓት ሞቶ ቀብር የምንወጣለት አዲስ አመት ይሁንልን!! – ዳኛቸው ቢያድግልኝ
መቸም የዘመን ዑደት ማለት አሮጌው አልፎ አዲሱ የሚተካበት፣ ዘር አፈር ቅሞ ወሀ ጠጥቶ በቅሎና አብቦ የሚያሸትበት መስከረም ማለትም አይደል? አዎ አዲስ ዘመናችን ምድሪቱ ጭጋግን ለብሳ፣ አራዊቱ ያጠራቀሙትን ስብ እያቀለጡ የሚኖሩበት፣ አእዋፍ ስደት የሚጀምሩበትና የሰው ልጅ አንደ በቆሎ በልብስ የሚጠቀለልበት የበረዶ ወቅት ባለመሆኑ እርግጥም አዲስ አመት ነው። በምንም መስፈርት በማንም መለኪያ ዘመን አቆጣጠራችን ለኛ ተገቢም ትክክልም ነው። አዲስ አመት ማለት ለኛ ለኢትዮጵያውያን ተስፋ ማለትም ነው። ታድያ ተስፋ ላይ ለቅሶና ቀብር እንዴት ርዕስ ሆነ ማለታችሁ አይቀርም። አዎ ሸፍጥ ሞቶ ሀቅ ቀብር ቢወጣና ለእውነት ኖረን ስለ ዕውነት ብናልፍ፤ በዚህ የአመታት ቅብብሎሽም እንደ አደይ አበባ ሁሉ የተስፋ ብስራት ቢያሸትልን ምን ይለናል? የሚል መንደርደርያ ነው የዚህን አይነት ርዕስ ያስመረጠኝ።
አዎ እነዚህ አዲሶቹ ገድሎ ቀብር ወጪዎች ‘ተረትና ማቅራራት’ የአማራ ነው እንዳለው አስተኳሻቸው ገድለው አያቅራሩም። በፊት በረሃ እያሉ እርግጥ ነው በአንድ ጥይት 10 ሰው መደዳውን እንደሚገድሉ ተራራው እንደሚንቀጠቀጥላቸው ነግረውን ነበር። ‘ፍሬንድሊ ፋየር’ የምትለውን ብልጥ ቃል መጠቀም የጀመሩት ግን ያኔ ‘ፍሬንዶቻቸውን’ እያጋደሙ ሲያርዱ ነበር። እድሜ ለገብረመድህን አርአያ አስገድሎ አሸርጦ ማልቀስን በሜጋ የፊልም ቅንብር ሀውዜን ላይ መተወናቸውን ነግሮናል። አተረፉበት ነው የሚባለው! ከበሩበት እንጂ ሸገር ይዞአቸው የገባው ሞት የሀውዜኑም አይደል?
ከዚያ በሁዋላ ያፈነገጠውን ሁሉ እርድ ያደርጉና ጉድ ተሰራን? ገዳዩን ለማግኘት የማንፈነቅለው ድንጋይ የለም ብለው አደባባይ ይምላሉ። በሁዋላ ግን የፈነቀሉትን ድንጋይ መቃብሩ ላይ ቆልለው ወሬውንም ያጠፉታል። አይንአውጣ ስለሆኑ ለቅሶ ሁሉ ይደርሳሉ። ስፍስፍ ብሎ የሚያለቅስና ሁዋላ አደጋ የሚያመጣ የሚመስላቸውን መንጥረው ለማባረር የሚጠቀሙበትም ይመስላል። ይህ ወንጀላቸው ወደ ህግ ባይመጣም እንኳ ሕሊናን መበጥበጡና ነገም ለኔ አይመለሱም የሚለው ፍርሀት መኖሩን ከሰዎቹ ፊት ማንበብ ይቻላል። ይህ ጥርጣሬና ፍርሃት ፊታቸውን አበላሽቶታል። የሆነ እርኩስ መንፈስ የተጠናወተው የሚመስል ቅብዝብዝ ዐይኖች አላቸው። የተሸበረ ፊት የሌለው ባለስልጣን እኮ የለም። አዎ የሰው ደም ያቅበዘብዛል። እነዚህ በጎደለ የተተኩ ከበረሀኞቹ በላይ በረሀኛ የሚመስሉትም ቶሎ የደለበ ግን መታረጃውን ያየ ሰንጋ መስለዋል የሚሉም አሉ።
አሁን በቀደም ሼክ ኑሩን መስዋዕት ሲያደርጓቸው ገድሎ አልቃሾቹ መስጊድ እንደጧፍ ሲነድ ቤተክርስትያን እንደ ደመራ ቦግ ሲል ሕዝቡ ሲተራረድና እነሱ ገላጋይ ሆነው ሲወጡ የሚያሳይ ባለቀለም ሕልም አይተው ነበር። ሕዝቡ ግን አረ ቀልዳችሁን አቁሙ ብለው ‘የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ’ የሚል የአማራ ተረት ተረተባቸው ሲባልም ሰምተናል። አዎና አርባ አመት ሙሉ ገድሎ ማልቀስ እንዴት ይቻላል? ማነው ስሙ አንድ አስለቃሽ ጋዜጠኛ ወደ ወሎ ሄዶ የ’አይዶል ሾው’ ቢሆን “ለዛሬው አልተሳካልህም” የሚያስብል ሳይጀመር ያለቀ ዘገባ አቅርቦ ነበር። ከዚህ የበለጠ ጭካኔ መቸም የለም። ለቅሶ ላይ መፈክር ሲያሰሙ እንዲውሉ አደረጋቸው። ውሸታቸው ወንዝ የመሻገር አቅም ስለሌለው ውሸቱን በውሸት ለመሸፈን አሁን መዘዙ ለሼኩም ልጅ አልቀረለት መታሰርና መጋዝ ውስጥ ወስጡን ሌላ ሞት መደገስ ሆነ። የሰለቸንም ይኸው ነው! ዘዴውም ጃጀ እንደ ተሰነጣጠቀ ሽክላ በድምጽ ሲፈርስም አየነው። አሁን አስተኳሹ ብቻ ሳይሆን ስርዐቱም ሞቱን በጸጋ ሊቀበል ይገባዋል።
ብዙ የለቅሶን ወሬ ወደ የመልካም ምኞት መግለጫ እንቀይረውና በሚቀጥለው አመት ገድሎን ለቅሶ የሚወጣው ጎጠኛና ወሮበላ ስርዐት ሞቶ ቀብር የምንወጣለት ይሁን ብለን እንመራረቅ። እንዲህ እያልን ምክርም እንምከር “ከነሱ ጋር በልቶ በሰላም ተኝቶ ማደር የለምና በቁልቋል የተመሰልክ ተላላ ሆይ ይህንን አጋም ተጠግተህ እድሜ ልክህን አታልቅስ።” ብለን።
የፍቅር አደይ አበባ የተነጠፈባት፣ የተስፋ ቀስተ ደመና የተዘረጋባት፤ ፍትህ፣ ነፃነትና እኩልነት መለያዋ የሆነች ውብ ኢትዮጵያ የመልካም አዲስ አመት ምኞታችን ትሁንልን እውነትም እናድርጋት።
በበዓል የረሃብ አድማ!! – ርዕዮት ምን ልትነግረን ነው?
ከዳዊት ሰለሞን (ጋዜጠኛ)
በብሄራዊ በዓላት ቀን በአብዛኛው ከወደ እስር ቤት የሚሰማው ዜና አስደሳች ነበር፡፡ይህንን አጼዎቹ ፣ሰው በላው የደርግ ስርዓትና ብሶት ወለደኝ ያለን ኢህአዴግ ሲያደርጉት ቆይተዋል፡፡በዘንድሮው አዲስ አመትም የመንግስትን ይቅርታ በማግኘት ከወዳጅ ዘመዶቻቸው የተቀላቀሉ ስለመኖራቸው ተሰምቷል፡፡በአዲሱ ዓመት ይቅርታ ከተቸራቸው እስረኞች መካከል ታዋቂ ፖለቲከኞች፣አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች አለመኖራቸው ተፈቺዎቹ በደረቅ ወንጀል ታስረው የነበሩ መሆናቸውን ለመናገር ብዙ መድከም አይጠይቅም፡፡
መንገስት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ሂሩት ክፍሌና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄር አቅርበውት ለነበረ የይቅርታ አቤቱታ የእምቢታ ምላሽ መስጠቱም ይቅርታ የሚገባውና የማይገባው በመንግስት ማውጫ ውስጥ ስለ መኖሩ ማሳያ ነው፡፡የይቅርታው ጉዳይ ለጊዜው ይዘግይልንና በጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ በበዓል ቀን ስለ ተፈጸመ ግፍ ላካፍላችሁ፡፡
ጋዜጠኛዋን በበዓሉ ዋዜማ ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ አምርተን ነበር፡፡በመጠየቂያ ሰዓት መድረስ የቻልን ቢሆንም ጥበቃዎቹ ‹‹ርዕዮት የምትጠየቀው በዋናው በር ሆኗል፡፡ስለዚህ ወደ ዋናው በር ሂዱ›› አሉን፡፡ዋናው በር ፈጣን ተራማጅ በ10 ደቂቃ የሚደርስበት በመሆኑ ሰዓቱ እንዳይረፍድና እንዳንከለከል በማለት መሮጥ ጀመርን፡፡
ዋናው በር ግብረ ገብነት አልያም ፖሊሳዊ ስነ ምግባር በዞረበት ለሰላምታ እንኳ አግኝቷቸው የማያውቁ የሚመስሉ ጠባቂዎች ‹‹በዚህ በኩል እስረኛ አይጠየቅም ሂዱ ››አሉን፡፡ግትር ብለን በዚህ በኩል ግቡ ተብለናል አልን፡፡ሰዓቱ እየሄደ ፖሊሶቹም በአቋማችን የበለጠ በመበሳጨት እየዛቱ ነው ፡፡በመካከሉ የርዕዮት ታናሽ እህት እስከዳር አለሙና እጮኛዋ ስለሺ ሀጎስ ከግቢው ውስጥ እየተጣደፉ ወጡ፡፡
ስለሺ አንገቱን አቀርቅሮ እጆቹን እያወናጨፈ ብቻውን ያወራል፣እስከዳርን በሙሉ አይን ማየት ያስፈራል፡፡ ፊቷ በርበሬ መስሎ በእንባ ጎርፍ እየታጠበች ነው፡፡አብሮኝ የነበረው ሰውና እኔ ለመግባት እናደርግ የነበረውን ትንቅንቅ በመተው ሁለቱን ለማጽናናት እና ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ መወትወቱን ተያያዝነው፡፡
ርዕዮት ቤተሰቦቿን እንዳገኘች‹‹ያለሁበት ሁኔታ አስቸጋሪ ነው፣ችግር ውስጥ ነኝ››ትላቸዋለች፡፡በዚህ ወቅት በዙሪያዋ የነበሩ ሴት ፖሊሶች ጋዜጠኛዋ ላይ በመጮህ ‹‹ስለ ራስሽ ብቻ አውሪ››ይሏታል፡፡
‹‹የነገረችን እኮ ስለ ራሷ ነው››የእስከዳር ምላሽ ነበር፡፡በዚህ መሃል በጊዜያዊነት የሴቶች ዞን ሃላፊ የሆነች ፖሊስ ‹‹እናንተ አቅማችሁ ጋዜጣ ላይ ነው ከፈለጋችሁ ሂዱና እንዳንጠይቃት ተከለከልን በሉ፡፡››በማለት በዚህ ቦታ ለመጥቀስ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የሚያቅበንን የስድብ መዓት በስለሺ ፣በርዕዮትና በእህቷ ላይ ታወርዳለች፡፡
ርዕዮት ሁኔታውን መቋቋም ተስኗት ሃላፊዋን ለምን እንዲህ አይነት በደል እንደምትፈጽምባት ለመጠየቅ ስትሞክር እየገፈታተሩ ወደ ውስጥ እንድትገባ በማድረግ እነ ስለሺን ግቢውን እንዲለቁ ያደርጋሉ፡፡
በንጋታው መስከረም 1/2006 ነው፡፡የመንግስት ሃላፊዎችና የሃይማኖት አባቶች የቴሌቭዥኑን መስኮት በአዲስ አመት ቀና መልዕክት አጨናንቀውታል፡፡አዲስ ቀን አዲስ ገጠመኝ እንደሚፈጥር ተስፋ ያደረጉት የርዕዮት ቤተሰቦች ከቃሊቲ አልቀሩም፡፡ነገር ግን የሰሙት ነገር በቀኑ እንጂ በአስተዳደሩ መካከል ለውጥ ወይም ዕድሳት አለመኖሩን ነው፡፡ለካ የአዲስ አመት በጎ መልእክት የሚያስተላልፉልን መሪዎቻችን ያሉት‹‹በድሮው ቀን ነው፡፡››
ርዕዮትን እንዲጠይቁ የተፈቀደላቸው ‹‹እናቷ፣አባቷና የነፍስ አባቷ ብቻ ናቸው››እነ ስለሺ ከቃሊቲ ሃላፊዎች ዛሬ ያደመጡት መንፈስ ሰባሪ ቃል ነው፡፡የህግ ባለሞያው አቶ አለሙ ጌቤቦ ድርጊቱ ህገ መንግስታዊ ጥሰት እንደሆነ በመግለጽ ቃሊቲ ደርሰው ልጃቸውን ሳይጠይቁ ተመልሰዋል፡፡ወላጅ እናቷ ያመጡትን ምግብ ለማስገባት ቢሞክሩም ርዕዮት በቃሊቲ የሴቶች ዞን ጊዜያዊ ሃላፊ እየደረሰባት የሚገኘውን ህገ ወጥ ድርጊት ለመቃወም የርሃብ አድማ በመጀመሯ እናት ያመጡትን ምግብ የሚቀበላቸው አላገኙም፡፡
ወዳጄ ስንቶቻችን ነን አዲሱ ዓመት በጾም ቀን ዋለ ብለን የተከፋን?ይህው እንግዲህ በዓሉን ርዕዮት በርሃብ አሳልፋዋለች፡፡
የርዕዮት የርሃብ አድማ መልእክቱ ግልጽ ነው፡፡አቅም ያላት በራሷ ላይ በመሆኑ ራሷን በመቅጣት ህገ ወጦችን እምቢ አለቻቸው በዚህ ሰላማዊውን ታጋይ ማህተመ ጋንዲን መሰለችው፡፡ሰዎቹ እየበሉ በርሷ ላይ የሚፈጽሙት በደል እየተራበች በምታስተላልፈው መልእክት የህሊና ርሃብተኞች መሆናቸውን ይነግራቸዋል፡፡
ከቃሊቲ ውጪ ያለንም ምግብ ወደ አፋችን ባስጠጋን ቁጥር ርዕዮት የቃሊቲ አጥር ሳይበግራት ትመጣብናለች፡፡በምግብ ብቻ በማይኖርባት አለም በምግብ ብቻ ለመኖር ለምናደርገው ከንቱ ሩጫም ርሃቧ ትልቅ ደወል ይሆንብናል፡፡
በአዲስ ዓመት አስገራሚ ዜና ከቃሊቲ – ‹‹ከአንድነት›› የሚል ጽሁፍ የሰፈረበት ኬክ ቃሊቲ እንዳይገባ ተደረገ – ፍኖተ ነጻነት
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራሮች እድሜ ልክ ተፈርዶበት በቅጣት ቤት የሚገኘውን ሰላማዊ ታጋይ አንዷለም አራጌን
‹‹እንኳን አደረሰህ አዲሱ ዓመት ፍጹም ነጻነትህን የምትቀዳጅበት እንዲሆን እንመኛለን እንታገላለንም››
በሚል ስሜት ተነሳስተው ኬክ በማስጋገር
‹‹ከአንድነት››
የሚል ጽሁፍ አጽፈውበታል፡፡
የአንዷለም ጠያቄዎች በሩን አልፈው የያዙትን ኬክ ለማስፈተሸ አስቀማሽ ጋር እንደደረሱ አስቀማሹ ኬኩንና የተጻፈበትን እየተመለከተ አንዴ ቆዮኝ ብሎ ጥሏቸው ሄደ፡፡ አስቀማሹ ሃፊዎቹን አስከትሎ መጣ ፡፡የሆነ ነገር ትከሻቸው ላይ የደረደሩ ሃላፊ ኮስተር ብለው
ኬኩ አይገባም እናንተ ግን መግባት ትችላላችሁ›
ይላሉ፡፡ የኬኩ በደል ምን እንደሆነ ሲጠይቁም
‹‹ከአንድነት››
ይላል አሏቸው፡፡
አንድነት በምርጫ ቦርድ እውቅና የተቸረው ቢሮ ያለው ሰላማዊ ፓርቲ ነው፡፡ አንዷለምንም እናንተ ሽብርተኛ በማለት አሰራችሁት እንጂ እስከሚታሰርበት ቀን ድረስ
የፓርቲው የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ ነበር፡፡››
ይሏቸዋል፡፡
ኬኩን አንድነት ከሚለው ውጪ ይዛችሁ መግባት ትችላላች ከዚህ ውጪ አናስተናግድም ሃላፊው ይላሉ፡፡ የአንድነት አመራሮች በበኩላቸው ኬኩ ህገ ወጥ ነገር እስካልሰፈረበት ድረስ አንድነት የሚለውን የፓርቲያችንን ስም አንፍቅም፡፡ ፍላጎታችሁ ሰላማዊውን ታጋይ እንዳንጠይቀው ለማድረግ በመሆኑ እኛም አንገባም በማለት ግቢውን ለቅቀው ወጥተውላቸዋል፡፡
በበዓል ቀን የርሃብ አድማ – ርዕዮት ምን ልትነግረን ነው? September 11, 2013
በብሄራዊ በዓላት ቀን በአብዛኛው ከወደ እስር ቤት የሚሰማው ዜና አስደሳች ነበር፡፡ይህንን አጼዎቹ ፣ሰው በላው የደርግ ስርዓትና ብሶት ወለደኝ ያለን ኢህአዴግ ሲያደርጉት ቆይተዋል፡፡ በዘንድሮው አዲስ አመትም የመንግስትን ይቅርታ በማግኘት ከወዳጅ ዘመዶቻቸው የተቀላቀሉ ስለመኖራቸው ተሰምቷል፡፡በአዲሱ ዓመት ይቅርታ ከተቸራቸው እስረኞች መካከል ታዋቂ ፖለቲከኞች፣አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች አለመኖራቸው ተፈቺዎቹ በደረቅ ወንጀል ታስረው የነበሩ መሆናቸውን ለመናገር ብዙ መድከም አይጠይቅም፡፡
መንገስት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ሂሩት ክፍሌና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄር አቅርበውት ለነበረ የይቅርታ አቤቱታ የእምቢታ ምላሽ መስጠቱም ይቅርታ የሚገባውና የማይገባው በመንግስት ማውጫ ውስጥ ስለ መኖሩ ማሳያ ነው፡፡የይቅርታው ጉዳይ ለጊዜው ይዘግይልንና በጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ በበዓል ቀን ስለ ተፈጸመ ግፍ ላካፍላችሁ፡፡ ጋዜጠኛዋን በበዓሉ ዋዜማ ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ አምርተን ነበር፡፡በመጠየቂያ ሰዓት መድረስ የቻልን ቢሆንም ጥበቃዎቹ
‹‹ርዕዮት የምትጠየቀው በዋናው በር ሆኗል፡፡ስለዚህ ወደ ዋናው በር ሂዱ››
አሉን፡፡ዋናው በር ፈጣን ተራማጅ በ10 ደቂቃ የሚደርስበት በመሆኑ ሰዓቱ እንዳይረፍድና እንዳንከለከል በማለት መሮጥ ጀመርን፡፡
ዋናው በር ግብረ ገብነት አልያም ፖሊሳዊ ስነ ምግባር በዞረበት ለሰላምታ እንኳ አግኝቷቸው የማያውቁ የሚመስሉ ጠባቂዎች
‹‹በዚህ በኩል እስረኛ አይጠየቅም ሂዱ ››
አሉን፡፡ ግትር ብለን በዚህ በኩል ግቡ ተብለናል አልን፡፡ሰዓቱ እየሄደ ፖሊሶቹም በአቋማችን የበለጠ በመበሳጨት እየዛቱ ነው ፡፡በመካከሉ የርዕዮት ታናሽ እህት እስከዳር አለሙና እጮኛዋ ስለሺ ሀጎስ ከግቢው ውስጥ እየተጣደፉ ወጡ፡፡ ስለሺ አንገቱን አቀርቅሮ እጆቹን እያወናጨፈ ብቻውን ያወራል፣እስከዳርን በሙሉ አይን ማየት ያስፈራል፡፡ ፊቷ በርበሬ መስሎ በእንባ ጎርፍ እየታጠበች ነው፡፡አብሮኝ የነበረው ሰውና እኔ ለመግባት እናደርግ የነበረውን ትንቅንቅ በመተው ሁለቱን ለማጽናናት እና ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ መወትወቱን ተያያዝነው፡፡
ርዕዮት ቤተሰቦቿን እንዳገኘች
‹‹ያለሁበት ሁኔታ አስቸጋሪ ነው፣ችግር ውስጥ ነኝ››
ትላቸዋለች፡፡በዚህ ወቅት በዙሪያዋ የነበሩ ሴት ፖሊሶች ጋዜጠኛዋ ላይ በመጮህ
‹‹ስለ ራስሽ ብቻ አውሪ››
ይሏታል፡፡
‹‹የነገረችን እኮ ስለ ራሷ ነው››
የእስከዳር ምላሽ ነበር፡፡ በዚህ መሃል በጊዜያዊነት የሴቶች ዞን ሃላፊ የሆነች ፖሊስ
‹‹እናንተ አቅማችሁ ጋዜጣ ላይ ነው ከፈለጋችሁ ሂዱና እንዳንጠይቃት ተከለከልን በሉ፡፡››
በማለት በዚህ ቦታ ለመጥቀስ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የሚያቅበንን የስድብ መዓት በስለሺ ፣በርዕዮትና በእህቷ ላይ ታወርዳለች፡፡
ርዕዮት ሁኔታውን መቋቋም ተስኗት ሃላፊዋን ለምን እንዲህ አይነት በደል እንደምትፈጽምባት ለመጠየቅ ስትሞክር እየገፈታተሩ ወደ ውስጥ እንድትገባ በማድረግ እነ ስለሺን ግቢውን እንዲለቁ ያደርጋሉ፡፡
በንጋታው መስከረም 1/2006 ነው፡፡የመንግስት ሃላፊዎችና የሃይማኖት አባቶች የቴሌቭዥኑን መስኮት በአዲስ አመት ቀና መልዕክት አጨናንቀውታል፡፡አዲስ ቀን አዲስ ገጠመኝ እንደሚፈጥር ተስፋ ያደረጉት የርዕዮት ቤተሰቦች ከቃሊቲ አልቀሩም፡፡ነገር ግን የሰሙት ነገር በቀኑ እንጂ በአስተዳደሩ መካከል ለውጥ ወይም ዕድሳት አለመኖሩን ነው፡፡ለካ የአዲስ አመት በጎ መልእክት የሚያስተላልፉልን መሪዎቻችን ያሉት
‹‹በድሮው ቀን ነው፡፡››
ርዕዮትን እንዲጠይቁ የተፈቀደላቸው
‹እናቷ፣አባቷና የነፍስ አባቷ ብቻ ናቸው››
እነ ስለሺ ከቃሊቲ ሃላፊዎች ዛሬ ያደመጡት መንፈስ ሰባሪ ቃል ነው፡፡ የህግ ባለሞያው አቶ አለሙ ጌቤቦ ድርጊቱ ህገ መንግስታዊ ጥሰት እንደሆነ በመግለጽ ቃሊቲ ደርሰው ልጃቸውን ሳይጠይቁ ተመልሰዋል፡፡ወላጅ እናቷ ያመጡትን ምግብ ለማስገባት ቢሞክሩም ርዕዮት በቃሊቲ የሴቶች ዞን ጊዜያዊ ሃላፊ እየደረሰባት የሚገኘውን ህገ ወጥ ድርጊት ለመቃወም የርሃብ አድማ በመጀመሯ እናት ያመጡትን ምግብ የሚቀበላቸው አላገኙም፡፡
ወዳጄ ስንቶቻችን ነን አዲሱ ዓመት በጾም ቀን ዋለ ብለን የተከፋን?ይህው እንግዲህ በዓሉን ርዕዮት በርሃብ አሳልፋዋለች፡፡
የርዕዮት የርሃብ አድማ መልእክቱ ግልጽ ነው፡፡አቅም ያላት በራሷ ላይ በመሆኑ ራሷን በመቅጣት ህገ ወጦችን እምቢ አለቻቸው በዚህ ሰላማዊውን ታጋይ ማህተመ ጋንዲን መሰለችው፡፡ሰዎቹ እየበሉ በርሷ ላይ የሚፈጽሙት በደል እየተራበች በምታስተላልፈው መልእክት የህሊና ርሃብተኞች መሆናቸውን ይነግራቸዋል፡፡
ከቃሊቲ ውጪ ያለንም ምግብ ወደ አፋችን ባስጠጋን ቁጥር ርዕዮት የቃሊቲ አጥር ሳይበግራት ትመጣብናለች፡፡በምግብ ብቻ በማይኖርባት አለም በምግብ ብቻ ለመኖር ለምናደርገው ከንቱ ሩጫም ርሃቧ ትልቅ ደወል ይሆንብናል፡፡
ESAT Radio: Sep 11
ገድሎ ለቅሶ የሚደርሰው ስርዐት ሞቶ ቀብር የምንወጣለት አዲስ አመት ይሁልን
መቸም የዘመን ዑደት ማለት አሮጌው አልፎ አዲሱ የሚተካበት፣ ዘር አፈር ቅሞ ወሀ ጠጥቶ በቅሎና አብቦ የሚያሸትበት መስከረም ማለትም አይደል? አዎ አዲስ ዘመናችን ምድሪቱ ጭጋግን ለብሳ፣ አራዊቱ ያጠራቀሙትን ስብ እያቀለጡ የሚኖሩበት፣ አእዋፍ ስደት የሚጀምሩበትና የሰው ልጅ አንደ በቆሎ በልብስ የሚጠቀለልበት የበረዶ ወቅት ባለመሆኑ እርግጥም አዲስ አመት ነው። በምንም መስፈርት በማንም መለኪያ ዘመን አቆጣጠራችን ለኛ ተገቢም ትክክልም ነው። አዲስ አመት ማለት ለኛ ለኢትዮጵያውያን ተስፋ ማለትም ነው።
ታድያ ተስፋ ላይ ለቅሶና ቀብር እንዴት ርዕስ ሆነ ማለታችሁ አይቀርም። አዎ ሸፍጥ ሞቶ ሀቅ ቀብር ቢወጣና ለእውነት ኖረን ስለ ዕውነት ብናልፍ፤ በዚህ የአመታት ቅብብሎሽም እንደ አደይ አበባ ሁሉ የተስፋ ብስራት ቢያሸትልን ምን ይለናል? የሚል መንደርደርያ ነው የዚህን አይነት ርዕስ ያስመረጠኝ። አዎ እነዚህ አዲሶቹ ገድሎ ቀብር ወጪዎች ‘ተረትና ማቅራራት’ የአማራ ነው እንዳለው አስተኳሻቸው ገድለው አያቅራሩም። በፊት በረሃ እያሉ እርግጥ ነው በአንድ ጥይት 10 ሰው መደዳውን እንደሚገድሉ ተራራው እንደሚንቀጠቀጥላቸው ነግረውን ነበር። ‘ፍሬንድሊ ፋየር’ የምትለውን ብልጥ ቃል መጠቀም የጀመሩት ግን ያኔ ‘ፍሬንዶቻቸውን’ እያጋደሙ ሲያርዱ ነበር። እድሜ ለገብረመድህን አርአያ አስገድሎ አሸርጦ ማልቀስን በሜጋ የፊልም ቅንብር ሀውዜን ላይ መተወናቸውን ነግሮናል። አተረፉበት ነው የሚባለው! ከበሩበት እንጂ ሸገር ይዞአቸው የገባው ሞት የሀውዜኑም አይደል? ከዚያ በሁዋላ ያፈነገጠውን ሁሉ እርድ ያደርጉና ጉድ ተሰራን? ገዳዩን ለማግኘት የማንፈነቅለው ድንጋይ የለም ብለው አደባባይ ይምላሉ።
በሁዋላ ግን የፈነቀሉትን ድንጋይ መቃብሩ ላይ ቆልለው ወሬውንም ያጠፉታል። አይንአውጣ ስለሆኑ ለቅሶ ሁሉ ይደርሳሉ። ስፍስፍ ብሎ የሚያለቅስና ሁዋላ አደጋ የሚያመጣ የሚመስላቸውን መንጥረው ለማባረር የሚጠቀሙበትም ይመስላል። ይህ ወንጀላቸው ወደ ህግ ባይመጣም እንኳ ሕሊናን መበጥበጡና ነገም ለኔ አይመለሱም የሚለው ፍርሀት መኖሩን ከሰዎቹ ፊት ማንበብ ይቻላል። ይህ ጥርጣሬና ፍርሃት ፊታቸውን አበላሽቶታል።
የሆነ እርኩስ መንፈስ የተጠናወተው የሚመስል ቅብዝብዝ ዐይኖች አላቸው። የተሸበረ ፊ የሌለው ባለስልጣን እኮ የለም። አዎ የሰው ደም ያቅበዘብዛል። እነዚህ በጎደለ የተተኩ ከበረሀኞቹ በላይ በረሀኛ የሚመስሉትም ቶሎ የደለበ ግን መታረጃውን ያየ ሰንጋ መስለዋል የሚሉም አሉ። አሁን በቀደም ሼክ ኑሩን መስዋዕት ሲያደርጓቸው ገድሎ አልቃሾቹ መስጊድ እንደጧፍ ሲነድ ቤተክርስትያን እንደ ደመራ ቦግ ሲል ሕዝቡ ሲተራረድና እነሱ ገላጋይ ሆነው ሲወጡ የሚያሳይ ባለቀለም ሕልም አይተው ነበር። ሕዝቡ ግን አረ ቀልዳችሁን አቁሙ ብለው ‘የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ’ የሚል የአማራ ተረት ተረተባቸው ሲባልም ሰምተናል። አዎና አርባ አመት ሙሉ ገድሎ ማልቀስ እንዴት ይቻላል? ማነው ስሙ አንድ አስለቃሽ ጋዜጠኛ ወደ ወሎ ሄዶ የ’አይዶል ሾው’ ቢሆን “ለዛሬው አልተሳካልህም” የሚያስብል ሳይጀመር ያለቀ ዘገባ አቅርቦ ነበር። ከዚህ የበለጠ ጭካኔ መቸም የለም።
ለቅሶ ላይ መፈክር ሲያሰሙ እንዲውሉ አደረጋቸው። ውሸታቸው ወንዝ የመሻገር አቅም ስለሌለው ውሸቱን በውሸት ለመሸፈን አሁን መዘዙ ለሼኩም ልጅ አልቀረለት መታሰርና መጋዝ ውስጥ ወስጡን ሌላ ሞት መደገስ ሆነ። የሰለቸንም ይኸው ነው! ዘዴውም ጃጀ እንደ ተሰነጣጠቀ ሽክላ በድምጽ ሲፈርስም አየነው። አሁን አስተኳሹ ብቻ ሳይሆን ስርዐቱም ሞቱን በጸጋ ሊቀበል ይገባዋል። ብዙ የለቅሶን ወሬ ወደ የመልካም ምኞት መግለጫ እንቀይረውና በሚቀጥለው አመት ገድሎን ለቅሶ የሚወጣው ጎጠኛና ወሮበላ ስርዐት ሞቶ ቀብር የምንወጣለት ይሁን ብለን እንመራረቅ። እንዲህ እያልን ምክርም እንምከር “ከነሱ ጋር በልቶ በሰላም ተኝቶ ማደር የለምና በቁልቋል የተመሰልክ ተላላ ሆይ ይህንን አጋም ተጠግተህ እድሜ ልክህን አታልቅስ።” ብለን። የፍቅር አደይ አበባ የተነጠፈባት፣ የተስፋ ቀስተ ደመና የተዘረጋባት፤ ፍትህ፣ ነፃነትና እኩልነት መለያዋ የሆነች ውብ ኢትዮጵያ የመልካም አዲስ አመት ምኞታችን ትሁንልን እውነትም እናድርጋት።
ዳኛቸው ቢያድግልኝ
biyadegelgne@hotmail.com
የአርቲስት ሻምበል በላይነህ አገራዊ ስራዎች አርአያነት – “ወጣቱ አንበሳ ላገርህ ተነሳ…” (ከሉሉ ከበደ)
ውድ ኢትዮጵያን ወገኖቼ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ። እዲሱ አመት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ብስራት ይዞ የሚመጣ ይሁን። ያለምንም ደም መፋሰስ ይህ ዘረኛ የወያኔ ገዢ ቡድን መቃብር ገብቶ፤ ዘረኝነት፤ ጎጠኝነትና በታኝነት ከምድራችን ጠፍቶ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተፋቅሮ ተከባብሮ፤ ሲያጠፉ የሚቀጣቸውን የሚሽራቸውን፤ ሲያለሙ የሚሾማችውን የሚሸልማቸውን መሪዎች በድምጹ መርጦ፤ የሚኖርበት፤ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከዘር ማንነቱ በፊት በኢትዮጵያ ሲምል ሲገዘት የምናይበት፤ ዜጎች ሁሉ ለሀገሬ፤….. ለወገኔ.. እያሉ ሲተጉ፤ ለጋራ እድገትና ብልጽግና ሲጓጉ….አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ እያሉ አንዳቸው ላንዳቸው ሲሞቱ የምናይበት የተአምር ዘመን ይሁንልን,….ዘረኞች ለአንዴና ለመጨረሻ የሚጠፉበት ዘመን ይሁንልን….2006. አሜን!
አርቲስቶች የተሰጥኦና የህዝብ ሁለንተናዊ ባህልና ወግ፤ እናም የህዝብ ድጋፍና አድናቆት ውጤቶች እንደ መሆናቸው፤ ስራዎቻቸው ሁሉ የህብረተሰብ ህይወት ነጸብራቆች የመሆን ተፈጥሮአዊ ግዴታ አለባቸው። ሰላምና ጦርነት፤ ድልና ሽትንፈት፤ ደስታና ሀዘን፤ ፍቅርና ጥላቻ ምን ጊዜም ከሰው ልጅ ጋር የሚኖሩ ክስተቶች በመሆናቸው፤ ሰውም በጥብበ ስራዎቹ ውስጥ እነዚህን ባህሪያት እያንጸባረቀ፤ ይማማርባቸዋል። ይዝናናባቸዋል። ያስተላልፋቸዋል። ለሚከታተል ትውልድ የታሪክ መንገሪያም ያደርጋቸዋል ።
ጥበብ የአንድ ህብረተሰብ የስልጣኔ፤ የባህል፤ የሳይንስ፤ የፖለቲካ፤ የሁለንተናዊ እድገት ነጸብራቅና ማሳያም ነው። ጭቆናን ለመታገል፤ ፍትህ ርትእ እንዲሰፍን ህዝብን መቀስቀሻና ማስተማሪያ መሳርያም ነው። ትያትር፤ ስነጽሁፍ፤ ሙዚቃ፤ወዘተ…የህዝብን ንቃተ ህሊናና ታሪካዊ ሁለንተናዊ እውቀት እንደሚያጎለብቱ የሚያጠያይቅ ነገር የለውም።
በሀገራችን የወኔ ስራት ከሰፈነ ያልፉት ሀያ ሁለት አመታት ወዲህ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች አድሎን፤ ዘረኛነትን፤ የመብት ረገጣን በመታገል ረገድ ማን ምን አስተዋጾ አበረከተ ብለን የመረመርን እንደሆን፤ የተወሰኑ ጠንካራ አርቲስቶች እንዳሉን ብናውቅም፤ አሰሩትም ፤አንገላቱትም፤ ሰደቡትም አዋረዱት፤ ስለመከረኛው የኢትዮጵያ ህዝብ አለቀሰ አንጎራጎረ፤ መከረ አስተማረ፤ አጽናና እንጂ ለወያኔ ስራት አድሮ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ማይክራፎን አልሆነም። የሚወዳት ሀገሩንም ጥሎ አልሄደም….ማን?… ሀዋርያውን ብላቴና ቴዲ አፍሮን ዙፋኑ ላይ እናስቀምጠዋልን።
አርቲሥቶች ህዝባዊ ሀላፊነት አለባቸው። ይህም ማለት በጥበብ ስራዎቻቸው የሚያገለግሉትን ህብረተሰብ የሞያ ስነምግባርን በጠበቀ መልኩ፤ ማህበራዊ፤ ባህላዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ከባቢያዊ ብሎም ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ህጸጾችን እያፈነፈኑ፤ ነቅሰው እያወጡ፤ በብሩሽ በዜማ በግጥም እያዋዙ ማዝናናት፤ ህብረተሰብን ማስተማር፤ ማንቃት፤ የሞራልና የዜግነት ግዴታ ሊሆንባቸውም ይገባል።
አርቲስት በአድናቂዎቹ ልብ ውስጥ የዘራው ፍሬ በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ውጤት ማፍራቱ አይቀርም። የህውሀት ካድሬዎች ፖለቲካ አስተምረው፤ አንቅተው፤ ካሸፈቱት የትግራይ ወጣት፤ በዘፈን በጭፈራና በቀረርቶ የሸፈተው ሳይበለጥ አይቀርም።
ተወዳጅ አርቲስቶች ከአንድ ጠንካራ ፖለቲከኛ የበለጠ ድምጣቸው በአድናዊዎቻቸው ዘንድ ይሰማል።
ክቡር ለሆነው የሰው ልጅ ሰባዊ መብትና ነጻነት ጥብቅና የቆሙ የጥበብ ሰዎች እንደ ነጻ አውጭ አርበኛ ሲሞገሱ፤ ሲወደሱና ሲመለኩ ይኖራሉ።
በሌላ መልኩ አድርባይ ፤ እበላባይ አርቲስቶችን፤ አንባ ገነኖች፤ ህዝብን በዜማና በጥበብ እንዲያደነዝዙላቸው ማበረታታት ማስገደድም የተለመደ ነው። እንዲመለኩ እንዲዘመርላቸው፤ መልካቸው አምሮ እንዲሳልላቸው፤ የሚገዟት አገር በምስላቸው እንድትሸፈን ያስደርጋሉ። የተለመደ ነው። የመለስ ዜናዊ ፎቶ ከዚያች ቅዱስ ምድራችን ተለቅሞ ይልቆ ይሆን?
ወያኔ ወደ ስልጣን የመጣ የመጀመሪያዎቹ አመታት እንደነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች በርካታ አርቲስቶች ማለት ይቻላል፤ የአንድነትን ጥቅም፤ በዘር የመከፋፈልን ጉዳት፤ በዜማዎቻቸው ለማስገንዘብ ሞክረዋል። ከፊሎቹ ከልባቸው በራሳቸው ሰብእና ውስጥ ካላቸው ኢትዮጵያዊ ስሜት ተነስተው እንደቴዲ አፍሮ አይነቶቹ በሀገራቸውና በህዝባቸው ጉዳይ ላይ የማይናወጥ ጠንካራ ወገንተኝነት እንደያዙ ዘልቀዋል።
አንዳንዶች ደግሞ በወቅታዊ የህዝብ ብሶት ላይ ያተኮረ ስራ ማቅረብ ገበያ ያስገኛል ብለው በማመንም ሊሆን ይችላል፤ የህዝቡን ብሶት የሚኮረኩሩ ስራዎችን አቅርበው የተቸራቸው ድጋፍና ጭብጭባ ሳያባራ፤ ሶስት መቶ ሰላሳ ዲግሪ ተሽከርክረው፤ በአንዲት ቀን ጀንበር ወደ ካድሬነት የተለወጡ አሉ። ሰለሞን ተካልኝ ተገፋን ሲል በዘመረበት አፉ ነው ስለመለስ ዜናዊ ቅንድብ ማማር ማላዘን የጀመረው።
ገናናዋ የደቡብ አፍሪካ ተወላጅ ማሪያ ማኬባ እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር 1963 ዓ ም ለተባበሩት መንግታት ድርጅት የደቡብ አፍሪካው የነጮች መንግስት ያሰፈነው የአፓርታይድ ስራት፤ በሀገሬው ተወላጅ ላይ እያደረሰ የነበረውን ስቃይ በመመስክሯ ነበር የገዛ አገሯን የዜግነት መብት ገፏት፤ ካገሯ እንድትሰደድ ያደረጋት አፓርታይድ። ማሪያ ለስርአቱ ያጎበደደችበት ጊዜ አልነበረም። በዜማዎቿ ህዝቡ ለነጻነቱ እንዲታገል ታበረታታ ትቀሰቅስ ነበር።
ከዚያ በኋላ ለሰላሳ አመታት በኖረችበት የስደት ዓለም፤ በዜማዎቿ ፤ በንግግሮቿ፤ አፓርታይድ ምን አይነት ስራት እንደሆነ፤ በደቡብ አፍሪካ ህዝብ ላይ ምን አይነት ግፍ እንደሚፈጸም ስትነግር፤ የደቡብ አፍሪካውያንን ባህሎችና ልምዶች ስታስተዋውቅ ኖረች።
ቁጥራቸው በቀላል የማይገመት ኢትዮጵያን አርቲስቶች ሀገራቸውን ጥለው በውጭው ዓለም ለመኖር ሲወስኑ ጥቂቱ፤ የስራቱን እኩይ ተግባራት እየኮነኑ የህዝባቸውን መከራና ስቃይ በማስተጋባታቸው የዘረኛው ህውሀት ቡድን ሰለባ በመሆናቸው ለስደት ተዳርዋል። ከነዚህም ታማኝ በየነ በዋናነት ይጠቀሳል። ሌሎችም የተሻለ ህይወትና ኑሮ ፍለጋ ያተርፈናል ወዳሉት አህጉር ተሰደዋል። ይሁንና እነዚህ አርቲስቶች ሀሳብን እንደልብ መግለጽ በሚቻልበት ሀገር ውስጥ የመኖራቸውን ያህል ኢትዮጵያ ውስጥ እየደረሰ ያለውን ሁለንተናዊ ጥፋትና የሰብአዊ መብት ረገጣ፤ በጥበብ ስራዎቻቸው በመዋጋት ረገድ የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ ነው ወይ?
ከቅርብ አመታት ወዲህ ሀገር ቤት ያሉ አርቲስቶች እጅግ በሚያሳፍርና ለማመን በሚያዳግት መልኩ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ክደው፤ የወያኔ የፕሮጋንዳ እቃና አጫፋሪ ሆነው፤ የገዛ ሀገሩን ባንዲራውንና ወገኑን ክዶ፤ ስለ ዲሞክራሲ የተናገረውን፤ ስለመብት የተናገረውን፤ የጻፈውን ሁሉ በመጨፍጨፍና ወህኒ በማጋዝ አለም አቀፍ ዝና ላተረፈው መለስ ዜናዊ ፤ የወርቅ ብእር ሽልማት መስጠት ፤ የኢትዮጵያን መፍረስና የአንድን ዘር የበላይነት ተቀብሎ፤ በሎሌነት ለማደር ከመዘጋጀት ውጭ ምንም አይነት መልእክት ያለው ተግባር አልነበረም። ስመጥሩና እጅግ ተወዳጅ የነበሩ አርቲስቶች ዛሬ ወደ ነፈሰበት አዘንብለው፤ ስለወያኔ ስራት ና መሪዎች መልካምነት የምስክርነት ቃላቸውን ሲሰጡ መስማት ጥበብ በኢትዮጵያ ውስጥ መዝቀጧንና ተጠባቢውም በአድርባይነትና እበላባይነት ሰብእና ውስጥ መስጠሙን ያመለክታል።
በራሱ ሩጫና ጥረት የሚተዳደር አዝማሪ የህዝብ ግጥም እየተቀበለ ዜጎችን ማዝናናት ያልቻለበት ደረጃ ላይ መደረሱ፤ ያስደነግጣል። ልማታዊ ግጥም እንጂ መቀበል አለመቻሉ፤ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ምን ያህል አካሉንም ህሊናውንም እንደገዛው አመላካች ነው። ይህ ቡድን እምን ድረስ ዝቅ ብሎ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመቆጣጠረ እየሞከረ እንዳለ የሚያስገነዝብ ሁኔታ ነው።
ሀተታውን እዚሁ ላይ ላቁመውና ዋናው የርእሴ ጉዳይ ወደ ሆነው እንደ ማሪያ ማኬባ በተሰደደበት የባእድ አገር ፤ በሚያውቅበትና በሚችለው ሙያው እናት ሀገር ኢትዮጵያን የወረራት ህውሀት ዘረኛ አስተዳደር በሀገርና በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን አደጋና ጥፋት በዜማው እየነገረ፤ እየመከረ፤ የሚበጀውን እያመለከተ ትግሎን ስለተያያዘው አርቲስት ሻንበል በላይነህ ስራዎች ላወሳ እሻለሁ።
ውድ አንባቢያን አርቲስቱ ባልፉት አመታት የተጫወታቸውን በርካታ ቀስቃሽ ዜማዎች ሁሉ በዚህ አጭር ጽሁፍ ውስጥ አካቶ ለማመላከት አይቻለኝም ። ለዛሬ በቅርቡ ካወጣቸው ሲዲዎች “ በቁም እንዋደድ እናም ሀይለስላሴ” የሚል መጠሪያ ከሰጣቸው ሁለት አልበሞቹ ውስጥ በሀገራችን ባለው ወቅታዊ እውነታ ላይ ያጠነጠኑ ቀስቃሽ ግጥሞቹን፤ ከየዘፈኑ የተወሰኑ ስንኞች እያወጣሁ ያሰውን ሁኔታ እንዴት ቁልጭ አድርጎ እንዳስቀመጠው ለማመላከት እሞክራለሁ፤ ሌሎች አርቲስቶቻችንም ወቅታዊውን ሁለገብ ትግል ለማገዝ በዜማዎቻቸው ህዝቡን ለነጻነት ማነሳሳት እንዲጀምሩ ጥሪ ለማቅረብ እሻለሁ። ከንግዲህ ኢትዮጵያውያን በሚችሉት ሁሉ ወደ ትግሉ በመቀላቀል የወያኔን ስርአት እስትንፋስ ማሳጠር ግድ ይላል።
ይሰማ ድምጻችን…. ግጥም አይገልጥም፤ ዜማ..ሻንበል በላይነህ
….እኛ አንበተንም፤ እኛ አንበተንም፤ ሙስሊም ክርስቲያኑ ልዩነት የለንም።
ዛሬም ቢሆን እንደበፊታችን፤ ተጠናክሮ ይህ አንድነታችን፤
ሙስሊም ክርስቲያኑ በለቅሶም በሰርጉም፤ አብረን እንኖራለ በክፉም በደጉም። …..
አዎ!.. “..ተነሱ ውጡና እስላም ወንድሞቻችሁን ስደቡ፤ እርገሙ፤ መንግስት ሊሆኑባችሁና ሊያጠፏችሁ ነው “ እያለ የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች እያስፈራራና እየዛተ አደባባይ የሚያወጣ፤ በመንግስት ቅርጽ መደራጀት የቻለ የወንጀለኞች ቡድን፤ ምናልባትም በዛሬዪቱ አለማችን በአይነቱ የተለየ የሆነ፤ መንግስት የሚመስል የወንጀለኞች ቡድን ፤ ሀገር በተቆጣጠረበት፤ ሻንበል በላይነህ በምርዋ ድምጹ በጣፋጭ ዜማው ያንቆረቆረልን መልእክት ህዝባዊ እንጉርጉሮ መሆን ያለበትና ሁሉም ኢትዮዝፕያዊ ሊያንጉራጉረው የሚገባ የሙስሊም ክርስቲያኑን መተላለቅ ለሚናፍቀው ወያኔ ጠንካራ ምላሽ ነው።
ህዝበክርስቲያን፡ መስሊሙ፤
ሁሌም በውኑ፡ በህልሙ፤
ያስባል ስለሰላሙ ….
ችግሩ የኢትዮጵያን ህዝብ ከማሸበር ተግባሩ ያልታቀበው የወያኔ ቡድን ነው እንጂ፤ ህዝቡ ስለሰላሙ ያስባል። በአስራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን ግራኝ አህመድ ሙስሊሙን ይዞ ያን ያክል ጥፋት ሲያደርስ፤ ሙስሊሙን የድጋፍና የሀይል ምንጭ አድርጎት ለራሱ የመንግስትነትን ስልጣን ለመቀዳጅት ተዋጋ እንጂ፤ ነብዩ ሙሀመድ ያላዘዙትን፤ እስልምናን በሰይፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊያስፋፋ አልነበረም ጦርነቱ ፤ “አህባሽ የሚባለውን እስልምና ፤ እኔ ያመጣሁልህን ተቀበል ፤ ለሺዎች ዘመናት ይዘህ የተጓዝከውን እምነትህን ጣል” እያለ በኢትዮጵያዊው ሙስሊም ላይ ከጂሀድ ያልተናነስ ስራ እየሰራ ያለው ወያኔ ነው። ማሰር መግደል። ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ክርስቲያን ወንድሞቹን ያሸ በረበት ዘመን የለም። አርቲስቶቻችን እንደሻንበል በላይነህ በዜማቸው ደግመው ደጋግመው ሊናገሩት የሚገባ እውነታ ነው።
አማራ… ግጥም፤ አይገልጽም። ዜማ፤ የህዝብ…
……ምነው ምን በደለ ደጉ ያገሬ ሰው፤ አረ የሰው ያለህ ፡አረሰው፡ አረ ሰው። እሳት ቢያንቀላፋ ገለባ ጎበኘው፤ ዘመን አረጀና ይሄ ቀን አገኘው። ከባህር ይሰፋል አማራ ማለት፤ ያንድነት ሀረግ ነው ኢትዮጵያዊነት ……
በፋሸሽት ወረራ ዘመን ተፈጸመ ያልተባለ ግፍ፤ አማሮች እስከወዲያኛው እንዲጠፉ፤ በሽታ ገብቷል ብለው የወያኔ ጤና ጥበቃ ሀላፊዎች ወጣት የአማራ ታዳጊዎችን በክትባት ዘመቻ እንዳይወልዱ ያመከነ አውሬ ቡድን የጁን ማግኘት አለበት። ይህ በጥይት ተጨፍጭፎ አላልቅ ያለ ህዝብ፤ እንደሌሎቹ ኢትዮጵያውያን እንደኦሮሞው፤ እንደትግሬው፤ እንደአፋሩ እንደ ደቡቡ እንደ ሁሉም….. ደሙን እያፈሰሰ ፤ ኢትዮጵያን ሲያቀና ዳር ድንበር ሲያስከብር ኖረ እንጂ፤ ወያኔ ሻእቢአና መሰሎቻቸው እንደሚያወሩት ተረት፤ ሌሎቹን ሲገዛና ሲጨቁን አልኖረም። ይልቁን ከማንም በክፋ መልኩ ሲረገጥ ነው የምናየው። የጎጃምን ድሀ አርሶ አደር፤ ከትግራይ ደሀ አርሶ አደር፤ የትግራይን ድሀ አርሶ አደር፤ ከሀረርጌ ድሀ አርሶ አደር ባጠቃላይ የኢትዮጵያን ድሀ ህዝብ አንዱን ካንዱ የተለየ የሚያደርገው የትኛው ኑሮው ነውና ነው አማራው ተለይቶ እንዲጠፋ የተፈረደበት? የህውሀት በሽተኞች አማራውን የበቀል ኢላማ ያደረጉበት ምክንያት እንደሎሎቹ ሁሉ ለኢትዮጵያ ቀናኢ በመሆኑ ነው። ወያኔ አማራን በማጥፋት ኢትዮጵያን የሚያጠፋ ሊመስለው ይችል ይሆናል፤ ግና ለኢትዮጵያ ደሙን ያፈሰሰላት ከሰሜን ምጽዋ ጫፍ እስከ ደቡብ ዶሎ፤ ከምስራቅ ፌርፌር ጫፍ እስከ ምእራብ ኢሎባቡር ጫፍ ያለ ህዝብ ሁሉ ነው። አሁንም ከወያኔ የማጥፋት ዘመቻ ያድናታል። ኢትዮጵያን ይታደጋታል።
ዘንድሮ… ግጥም፤ ተስፋዬ ለማ። ዜማ፤ ተስፋዬ ለማ
……ህጻናት ሲሸጡ ወተው በማደጎ፤ ያለቅሳል ባመቱ ወላጅ አደግድጎ…. ሻንበል በላይነህ በዜማው የነገረን የምናየው ነገር ነው። በማደጎ ስም ህጻናቶቻችንን እየቸበቸበ ያለው ወያኔ ህጻናቱ ካገር ከወጡ በሗላ የት ወደቁ ያለበት ጊዜ የለውም። በስርቆትና በዘረፋ ስለተጠመደ ስለዜጎች የሚያስብበት ገዜ የለውም። ሽያጩ ግን በስፋት እንደቀጠለ ነው። በየ አለሙ ያሉት ኢምባሲዎቹም ድለላውናንና ዶላር ማቀባበሉን እንጂ ስለኢትዮጵያውያን መብትም ሆነ ህይወት የሚያገባቸው ነገር የለም። ዓለም ደቻሳ ቤይሩት ወያኔ ኢንባሲ ፊት ለፊት ነበር ኡ ኡ እያለች በባእድ ጫማ ስትረገጥ መሬት ለመሬት ስትጎተት በዚያው የራሷን ህይወት ያጠፋችው። የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተብሎ ወያኔዎች እዚያው ነበር አድፍጠው በዚያች ኢትዮጵያዊ ድሀ ላይ ይደርስ የነበረውን የሚመለከቱት። እነዚህን ነው ሀያ ሁለት አመት ተሸክመን የተቀመጥነው።
…..ጥያቄ ባነሳ መብቱን ያስከበረ፤ ጸረ ሰላም ሲሉት በህግ ሽብር፤ እውነቱን አውጥቶ ስለተናገረ፤ ስንቱ ጋዜጠኛ እስር ቤት ታጎረ… ዘንድሮ
ፍርሀት አሽነፈን…. ግጥም፤ ተስፋዬ ለማ። ዜማ፤ ተስፋዬ ለማ
….ፍራት አሽመድምዶን ጥሎን ባደባባይ፤ ክፉንም ደጉንም ሁነናል ተቀባይ፤ የቆረቆረንን ምቹ ስናስመስል፤ ስንጨስ እንኖራልን ስንጠቁር ስንከስል……
አዎ .. ኢትዮጵያውያን በባህላችንም በተፈጥሮአችንም፤ ለህግ የመገዛት፤ የማክበር፤ በይሉኝታ መገዛት መፍራት፤ ስለሚያጠቃን፤ አንዳንድ ጌዜ ስንገፋና መብታችን ሲገፈፍ፤ ይህ ተፈጥሮ ከልክ ያለፈ ትግስት እንዲኖረን ያደረገ ይመስላል። ለዚህ ስርአት ያሳየነው ከልክ ያለፈ ትግስት ፍርሀት ነው የሚመስለው። አርቲስት ሻንበል በበላይነህ ምናልባትም ይህንኑ ታዝቦ ሳይሆን አልቀረም በዜማው እየነገረን ያለው። ሆድ ይፍጀው ወይም የባሰ አታምጣ እያልን ይኸው ሀያ ሁለት አመታት ጉዳት ተሸካሚዎች ሆነን በዚያው ጉዞ ቀጥሏል።
….. በጥቅም ሲፈረድ፤ በወገን ሲሰራ፤ አይተን እያለፍን ስንጠብቅ ወር ተራ፤ ፍርሀት እንደውሀ ወኔያችን አፍሶት፤ ይዘን ኖራለን የማይወጣ ብሶት…
መለስ ስብሀት ሰራሹ የወያኔ ገዢ ቡድን ወደስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በመንግስቱም ሆነ በግላ ተቋማት፤ ያሻውን ሲሰራ ስንቱን ሺህ ሰራተኛ በገፍና በግፍ እያባረረ የወደደውን የራሱን ምልምል እስከ አሁን ድረስ ሲሰገስግ፤ ሁሉም ተራው ሲደርስ ሜዳ ላይ እየተጣለ ከማልቀስ በቀር ዛሬ በወገኔ ላይ የደረሰ ነገ በኔ ነው ብሎ አምርሮ ስራቱን ለመዋጋት የተነሳ እስካሁን የለም።
የቀድሞው ሰራዊት….. ግጥም ይልማ ገብረአብ። ዜማ ሻምበል በላይነህ ….ጊዜ ተለውጦ ቀን እስከሚከዳው፤ አንጠፍጥፎ ቀምሶ ውሀውን ከኮዳው፤ ያገር መሰረቱ ህብረቱ እንዳይናድ፤ ኑሮውን አድርጎ በቀበሮ ጉርጓድ፤ ታግሎ ወድቆልናል ስላንድነታችን፤ ውለታው ይዘከር የሰራዊታችን። ሳያጓድል ያባት አደራ፤ ያስጠበቀ ያገር ባንዲራ፤ እንዳናጣ የባህር በር፤ ነፍሱን ከፍሏል ለኛ ክብር……
የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታ እንደሚባለው ; የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጦርሰራዊት መበተኑ ሳያንሰው ፤ ለወያኔ የፕሮፓጋንዳ ሰለባ እንደሆነ እስካሁን በመቆየቱ እድሜ ልኩን ሲዘመርለትና ሲሞገስ ሊኖር የሚገባው ጀግና ሰራዊት፤ ባልፉት ሀያ ሁለት አመታት እንደዋዛ ተዘንግቶ ቆይቶ ነበር። ሻንበል በላይነህ ምስጋና ይድረሰውና ዛሬም እንደትናንቱ የዚያን ክቡር ሰራዊት ገድል አንስቷል። ይበል የሚያሰኝ ነው። የኢትዮጵያን ሰራዊት ሀያል ክንድ አጣጥመው የሚያውቁት ገንጣይና አስገንጣይ እንዳላሸነፉት ልቦናቸው ያውቀዋል። ሰራዊቱን በአካልና በሞራል ከውስጥ ይገልላቸው የነበረው መንግስቱ ሀይለማርያም ባለውለታቸው ነው። በዚያ በውሸት ፕሮፓጋንዳቸው እውነት ለዲሞክራሲና ለእኩልነት የሚዋጉ መስሎት በገፍ እየሄድ ሲቀላቀላቸው፤ ያልተቀላቀለውም መሳሪያውን አውርዶ ባዶ እጁን የቆመ ወታደር በመትረየስ እያጨዱ ነበር ተሯሩጠው ድፍን ኢትዮጵያን እንደ ወባ ትንኝ የወረሯት። መልካሙ ነገር ኢትዮጵያውያን ጀግኖቻችንን መሸለም መጀምራቸው ነው። ያየር ሀይል፤ የምድር ጦር የባህር ሀይል ጀግኖቻችን አሁንም ሊዘፈንላቸው ሊሸለሙና ሊወደሱ ይገባል።
ታሪክ ይፍረደን፤ ግጥም፤ ተስፋዬ ለማ። ዜማ፤ ተስፋዬ ለማ
…የነበረው ቀርቶ ያልነበረው ሆነ፤ የሰራነው ሁሉ እንደቀልድ ባከነ….. ……… .የራሳችን ቋንቋ የራሳችን ፊደል፤ የራሳችን እምነት የራሳችን ባህል፤ የነሉሲ ሀገር፤ የሰው ልጅ መገኛ፤ በራሱ የተሟላ ማን ነበር እንደኛ……
እርግጥ ነው። በራሱ የተሟላ እንደኛ ማንም አልነበረም:: ምን ያደርጋል፤ በመካከላችን የበቀሉ፤ በዚችው ምድር ላይ የተፈለፈሉ፤ ለራሳቸው ታሪክ ባእድ ሆነው፤ አባቶቻቸው የባእድ ጠላት አሽከሮችና ባንዳዎች፤ ያ ጠላት በወላጆቻቸው እአምሮ ውስጥ ባሰረጸው እኩይ አስተሳሰብ ተኮትኩተው ያደጉ፤ ጊዜ ለነሱ አድልታ ኢትዮጵያ እጃቸው ላይ ወደቀች። በማግስቱም … የአድዋው ታሪክ ለአማራው፤ ለደቡቡ ምኑ ነው፤ የኢትዮጵያ ባንዲራ ጨርቅ ነው፤ እንኳን ከትግራይ ተወለድኩ፤ የሚል ሰው መሪ ተብሎ ባደባባይ የሚናገር፤ ሚኒሊክ ቤተ መንግስት መኖር የቻለ አጥፊ አየን። መልካሙ ነገር እግዚአብሄር ባጭር አስቀረው። የጀግኖቻችን ሀውልቶች ፈረሱ። በባንዳ ልጆች ስም ተተኩ። በዘመናት አብሮ መኖር የተገነባ የደምና የስጋ ውህደት እንዲለያይ የዘር አጥር ግርግዳ የሚገነቡ፤ በስጋ ፤ ኢትዮጵያውያን፤ በመንፈስና በገቢር ባእዳን የሆኑ ገዢዎችን ለማስተናገድ በቃን። የሻምበል በላይነህ ዜማ ይህንን ነው ልብ ብሎ ለሰማ የሚነግረው።
ኢትዮጵያ…. ግጥም፤ ይልማ ገብረአብ። ዜማ፤ ይልማ ገብረአብ
…….ኢትዮጵያ ህይወታችን፤ ኢትይጵያ ኩራታችን፤ ኢትዮጵያ እምነታችን፤ ያገር ፍቅር ጽናት የምንማርብሽ፤ በፈጠርሽው ትውልድ ይመርብሽ፤ ዛሬም ትላንትም የምልሽ ህይወቴ፤ ውዳሴ ነሽ ለኔ የዘላለም ሀብቴ…. ከዳሽ በሞትሽ ለማትረፍ፤ በሚኒሊክ ጅራፍ ልገረፍ….
ውድ አንባቢያን እነዚህ ሁሉ መልክቶች ሻንበል በላይነህ በቁም እንዋደድ በሚለው አልበሙ ውስጥ ያካተታቸው ስራዎቹ ናቸው። ሀይለስላሴ የሚል ርእስ የተሰጠው ሲዲም ብዙ ታሪካዊና ወቅታዊ መል እክቶች አሉት፤ በተለይም በከፍጠኛ ሁኔታ ወጣቶችን ለትግል የሚያነቃቃ መልእክቶችም አሉ። እራሱን ማዳመጡ የተሻለ ነው። የሻንበል በላይነህ ስራዎች ለአርቲስቶቻችን በአርአያነት የሚጠቀሱ ናቸው። ተመሳሳይ ስራዎች ከየአቅጣጫው ብቅብቅ ቢሉ የህዝባችንን ንቃት እጥፍ ድርብ ያሳድጉታል። ሻንበልም የነጻነት ቀን እስከሚመጣ በያዘው መንግድ እንደሚጓዝና ሌሎችንም እንደሚያስከትል ተስፋ አደርጋለሁ።
ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር
lkebede10@gmail.com
“ ወጣቱ አንበሳ ላገርህ ተነሳ…” የአርቲስት ሻምበል በላይነህ አገራዊ ስራዎች አርአያነት – (ሉሉ ከበደ)
ውድ ኢትዮጵያን ወገኖቼ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ። እዲሱ አመት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ብስራት ይዞ የሚመጣ ይሁን። ያለምንም ደም መፋሰስ ይህ ዘረኛ የወያኔ ገዢ ቡድን መቃብር ገብቶ፤ ዘረኝነት፤ ጎጠኝነትና በታኝነት ከምድራችን ጠፍቶ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተፋቅሮ ተከባብሮ፤ ሲያጠፉ የሚቀጣቸውን የሚሽራቸውን፤ ሲያለሙ የሚሾማችውን የሚሸልማቸውን መሪዎች በድምጹ መርጦ፤ የሚኖርበት፤ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከዘር ማንነቱ በፊት በኢትዮጵያ ሲምል ሲገዘት የምናይበት፤ ዜጎች ሁሉ ለሀገሬ፤….. ለወገኔ.. እያሉ ሲተጉ፤ ለጋራ እድገትና ብልጽግና ሲጓጉ….አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ እያሉ አንዳቸው ላንዳቸው ሲሞቱ የምናይበት የተአምር ዘመን ይሁንልን,….ዘረኞች ለአንዴና ለመጨረሻ የሚጠፉበት ዘመን ይሁንልን….2006. አሜን!
አርቲስቶች የተሰጥኦና የህዝብ ሁለንተናዊ ባህልና ወግ፤ እናም የህዝብ ድጋፍና አድናቆት ውጤቶች እንደ መሆናቸው፤ ስራዎቻቸው ሁሉ የህብረተሰብ ህይወት ነጸብራቆች የመሆን ተፈጥሮአዊ ግዴታ አለባቸው። ሰላምና ጦርነት፤ ድልና ሽትንፈት፤ ደስታና ሀዘን፤ ፍቅርና ጥላቻ ምን ጊዜም ከሰው ልጅ ጋር የሚኖሩ ክስተቶች በመሆናቸው፤ ሰውም በጥብበ ስራዎቹ ውስጥ እነዚህን ባህሪያት እያንጸባረቀ፤ ይማማርባቸዋል። ይዝናናባቸዋል። ያስተላልፋቸዋል። ለሚከታተል ትውልድ የታሪክ መንገሪያም ያደርጋቸዋል ።
ጥበብ የአንድ ህብረተሰብ የስልጣኔ፤ የባህል፤ የሳይንስ፤ የፖለቲካ፤ የሁለንተናዊ እድገት ነጸብራቅና ማሳያም ነው። ጭቆናን ለመታገል፤ ፍትህ ርትእ እንዲሰፍን ህዝብን መቀስቀሻና ማስተማሪያ መሳርያም ነው። ትያትር፤ ስነጽሁፍ፤ ሙዚቃ፤ወዘተ…የህዝብን ንቃተ ህሊናና ታሪካዊ ሁለንተናዊ እውቀት እንደሚያጎለብቱ የሚያጠያይቅ ነገር የለውም።
በሀገራችን የወኔ ስራት ከሰፈነ ያልፉት ሀያ ሁለት አመታት ወዲህ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች አድሎን፤ ዘረኛነትን፤ የመብት ረገጣን በመታገል ረገድ ማን ምን አስተዋጾ አበረከተ ብለን የመረመርን እንደሆን፤ የተወሰኑ ጠንካራ አርቲስቶች እንዳሉን ብናውቅም፤ አሰሩትም ፤አንገላቱትም፤ ሰደቡትም አዋረዱት፤ ስለመከረኛው የኢትዮጵያ ህዝብ አለቀሰ አንጎራጎረ፤ መከረ አስተማረ፤ አጽናና እንጂ ለወያኔ ስራት አድሮ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ማይክራፎን አልሆነም። የሚወዳት ሀገሩንም ጥሎ አልሄደም….ማን?… ሀዋርያውን ብላቴና ቴዲ አፍሮን ዙፋኑ ላይ እናስቀምጠዋልን።
አርቲሥቶች ህዝባዊ ሀላፊነት አለባቸው። ይህም ማለት በጥበብ ስራዎቻቸው የሚያገለግሉትን ህብረተሰብ የሞያ ስነምግባርን በጠበቀ መልኩ፤ ማህበራዊ፤ ባህላዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ከባቢያዊ ብሎም ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ህጸጾችን እያፈነፈኑ፤ ነቅሰው እያወጡ፤ በብሩሽ በዜማ በግጥም እያዋዙ ማዝናናት፤ ህብረተሰብን ማስተማር፤ ማንቃት፤ የሞራልና የዜግነት ግዴታ ሊሆንባቸውም ይገባል።
አርቲስት በአድናቂዎቹ ልብ ውስጥ የዘራው ፍሬ በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ውጤት ማፍራቱ አይቀርም። የህውሀት ካድሬዎች ፖለቲካ አስተምረው፤ አንቅተው፤ ካሸፈቱት የትግራይ ወጣት፤ በዘፈን በጭፈራና በቀረርቶ የሸፈተው ሳይበለጥ አይቀርም።
ተወዳጅ አርቲስቶች ከአንድ ጠንካራ ፖለቲከኛ የበለጠ ድምጣቸው በአድናዊዎቻቸው ዘንድ ይሰማል። ክቡር ለሆነው የሰው ልጅ ሰባዊ መብትና ነጻነት ጥብቅና የቆሙ የጥበብ ሰዎች እንደ ነጻ አውጭ አርበኛ ሲሞገሱ፤ ሲወደሱና ሲመለኩ ይኖራሉ።በሌላ መልኩ አድርባይ ፤ እበላባይ አርቲስቶችን፤ አንባ ገነኖች፤ ህዝብን በዜማና በጥበብ እንዲያደነዝዙላቸው ማበረታታት ማስገደድም የተለመደ ነው። እንዲመለኩ እንዲዘመርላቸው፤ መልካቸው አምሮ እንዲሳልላቸው፤ የሚገዟት አገር በምስላቸው እንድትሸፈን ያስደርጋሉ። የተለመደ ነው። የመለስ ዜናዊ ፎቶ ከዚያች ቅዱስ ምድራችን ተለቅሞ ይልቆ ይሆን?
ወያኔ ወደ ስልጣን የመጣ የመጀመሪያዎቹ አመታት እንደነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች በርካታ አርቲስቶች ማለት ይቻላል፤ የአንድነትን ጥቅም፤ በዘር የመከፋፈልን ጉዳት፤ በዜማዎቻቸው ለማስገንዘብ ሞክረዋል። ከፊሎቹ ከልባቸው በራሳቸው ሰብእና ውስጥ ካላቸው ኢትዮጵያዊ ስሜት ተነስተው እንደቴዲ አፍሮ አይነቶቹ በሀገራቸውና በህዝባቸው ጉዳይ ላይ የማይናወጥ ጠንካራ ወገንተኝነት እንደያዙ ዘልቀዋል።
አንዳንዶች ደግሞ በወቅታዊ የህዝብ ብሶት ላይ ያተኮረ ስራ ማቅረብ ገበያ ያስገኛል ብለው በማመንም ሊሆን ይችላል፤ የህዝቡን ብሶት የሚኮረኩሩ ስራዎችን አቅርበው የተቸራቸው ድጋፍና ጭብጭባ ሳያባራ፤ ሶስት መቶ ሰላሳ ዲግሪ ተሽከርክረው፤ በአንዲት ቀን ጀንበር ወደ ካድሬነት የተለወጡ አሉ። ሰለሞን ተካልኝ ተገፋን ሲል በዘመረበት አፉ ነው ስለመለስ ዜናዊ ቅንድብ ማማር ማላዘን የጀመረው።
ገናናዋ የደቡብ አፍሪካ ተወላጅ ማሪያ ማኬባ እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር 1963 ዓ ም ለተባበሩት መንግታት ድርጅት የደቡብ አፍሪካው የነጮች መንግስት ያሰፈነው የአፓርታይድ ስራት፤ በሀገሬው ተወላጅ ላይ እያደረሰ የነበረውን ስቃይ በመመስክሯ ነበር የገዛ አገሯን የዜግነት መብት ገፏት፤ ካገሯ እንድትሰደድ ያደረጋት አፓርታይድ። ማሪያ ለስርአቱ ያጎበደደችበት ጊዜ አልነበረም። በዜማዎቿ ህዝቡ ለነጻነቱ እንዲታገል ታበረታታ ትቀሰቅስ ነበር።ከዚያ በኋላ ለሰላሳ አመታት በኖረችበት የስደት ዓለም፤ በዜማዎቿ ፤ በንግግሮቿ፤ አፓርታይድ ምን አይነት ስራት እንደሆነ፤ በደቡብ አፍሪካ ህዝብ ላይ ምን አይነት ግፍ እንደሚፈጸም ስትነግር፤ የደቡብ አፍሪካውያንን ባህሎችና ልምዶች ስታስተዋውቅ ኖረች።ቁጥራቸው በቀላል የማይገመት ኢትዮጵያን አርቲስቶች ሀገራቸውን ጥለው በውጭው ዓለም ለመኖር ሲወስኑ ጥቂቱ፤ የስራቱን እኩይ ተግባራት እየኮነኑ የህዝባቸውን መከራና ስቃይ በማስተጋባታቸው የዘረኛው ህውሀት ቡድን ሰለባ በመሆናቸው ለስደት ተዳርዋል። ከነዚህም ታማኝ በየነ በዋናነት ይጠቀሳል። ሌሎችም የተሻለ ህይወትና ኑሮ ፍለጋ ያተርፈናል ወዳሉት አህጉር ተሰደዋል። ይሁንና እነዚህ አርቲስቶች ሀሳብን እንደልብ መግለጽ በሚቻልበት ሀገር ውስጥ የመኖራቸውን ያህል ኢትዮጵያ ውስጥ እየደረሰ ያለውን ሁለንተናዊ ጥፋትና የሰብአዊ መብት ረገጣ፤ በጥበብ ስራዎቻቸው በመዋጋት ረገድ የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ ነው ወይ?
ከቅርብ አመታት ወዲህ ሀገር ቤት ያሉ አርቲስቶች እጅግ በሚያሳፍርና ለማመን በሚያዳግት መልኩ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ክደው፤ የወያኔ የፕሮጋንዳ እቃና አጫፋሪ ሆነው፤ የገዛ ሀገሩን ባንዲራውንና ወገኑን ክዶ፤ ስለ ዲሞክራሲ የተናገረውን፤ ስለመብት የተናገረውን፤ የጻፈውን ሁሉ በመጨፍጨፍና ወህኒ በማጋዝ አለም አቀፍ ዝና ላተረፈው መለስ ዜናዊ ፤ የወርቅ ብእር ሽልማት መስጠት ፤ የኢትዮጵያን መፍረስና የአንድን ዘር የበላይነት ተቀብሎ፤ በሎሌነት ለማደር ከመዘጋጀት ውጭ ምንም አይነት መልእክት ያለው ተግባር አልነበረም። ስመጥሩና እጅግ ተወዳጅ የነበሩ አርቲስቶች ዛሬ ወደ ነፈሰበት አዘንብለው፤ ስለወያኔ ስራት ና መሪዎች መልካምነት የምስክርነት ቃላቸውን ሲሰጡ መስማት ጥበብ በኢትዮጵያ ውስጥ መዝቀጧንና ተጠባቢውም በአድርባይነትና እበላባይነት ሰብእና ውስጥ መስጠሙን ያመለክታል።
በራሱ ሩጫና ጥረት የሚተዳደር አዝማሪ የህዝብ ግጥም እየተቀበለ ዜጎችን ማዝናናት ያልቻለበት ደረጃ ላይ መደረሱ፤ ያስደነግጣል። ልማታዊ ግጥም እንጂ መቀበል አለመቻሉ፤ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ምን ያህል አካሉንም ህሊናውንም እንደገዛው አመላካች ነው። ይህ ቡድን እምን ድረስ ዝቅ ብሎ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመቆጣጠረ እየሞከረ እንዳለ የሚያስገነዝብ ሁኔታ ነው። ሀተታውን እዚሁ ላይ ላቁመውና ዋናው የርእሴ ጉዳይ ወደ ሆነው እንደ ማሪያ ማኬባ በተሰደደበት የባእድ አገር ፤ በሚያውቅበትና በሚችለው ሙያው እናት ሀገር ኢትዮጵያን የወረራት ህውሀት ዘረኛ አስተዳደር በሀገርና በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን አደጋና ጥፋት በዜማው እየነገረ፤ እየመከረ፤ የሚበጀውን እያመለከተ ትግሎን ስለተያያዘው አርቲስት ሻንበል በላይነህ ስራዎች ላወሳ እሻለሁ።
ውድ አንባቢያን አርቲስቱ ባልፉት አመታት የተጫወታቸውን በርካታ ቀስቃሽ ዜማዎች ሁሉ በዚህ አጭር ጽሁፍ ውስጥ አካቶ ለማመላከት አይቻለኝም ። ለዛሬ በቅርቡ ካወጣቸው ሲዲዎች “ በቁም እንዋደድ እናም ሀይለስላሴ” የሚል መጠሪያ ከሰጣቸው ሁለት አልበሞቹ ውስጥ በሀገራችን ባለው ወቅታዊ እውነታ ላይ ያጠነጠኑ ቀስቃሽ ግጥሞቹን፤ ከየዘፈኑ የተወሰኑ ስንኞች እያወጣሁ ያሰውን ሁኔታ እንዴት ቁልጭ አድርጎ እንዳስቀመጠው ለማመላከት እሞክራለሁ፤ ሌሎች አርቲስቶቻችንም ወቅታዊውን ሁለገብ ትግል ለማገዝ በዜማዎቻቸው ህዝቡን ለነጻነት ማነሳሳት እንዲጀምሩ ጥሪ ለማቅረብ እሻለሁ። ከንግዲህ ኢትዮጵያውያን በሚችሉት ሁሉ ወደ ትግሉ በመቀላቀል የወያኔን ስርአት እስትንፋስ ማሳጠር ግድ ይላል።
ይሰማ ድምጻችን….
ግጥም አይገልጥም፤ ዜማ..ሻንበል በላይነህ
….እኛ አንበተንም፤ እኛ አንበተንም፤
ሙስሊም ክርስቲያኑ ልዩነት የለንም።
ዛሬም ቢሆን እንደበፊታችን፤
ተጠናክሮ ይህ አንድነታችን፤
ሙስሊም ክርስቲያኑ በለቅሶም በሰርጉም፤
አብረን እንኖራለ በክፉም በደጉም። …..
አዎ!.. “..ተነሱ ውጡና እስላም ወንድሞቻችሁን ስደቡ፤ እርገሙ፤ መንግስት ሊሆኑባችሁና ሊያጠፏችሁ ነው “ እያለ የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች እያስፈራራና እየዛተ አደባባይ የሚያወጣ፤ በመንግስት ቅርጽ መደራጀት የቻለ የወንጀለኞች ቡድን፤ ምናልባትም በዛሬዪቱ አለማችን በአይነቱ የተለየ የሆነ፤ መንግስት የሚመስል የወንጀለኞች ቡድን ፤ ሀገር በተቆጣጠረበት፤ ሻንበል በላይነህ በምርዋ ድምጹ በጣፋጭ ዜማው ያንቆረቆረልን መልእክት ህዝባዊ እንጉርጉሮ መሆን ያለበትና ሁሉም ኢትዮዝፕያዊ ሊያንጉራጉረው የሚገባ የሙስሊም ክርስቲያኑን መተላለቅ ለሚናፍቀው ወያኔ ጠንካራ ምላሽ ነው።
ህዝበክርስቲያን፡ መስሊሙ፤
ሁሌም በውኑ፡ በህልሙ፤
ያስባል ስለሰላሙ ….
ችግሩ የኢትዮጵያን ህዝብ ከማሸበር ተግባሩ ያልታቀበው የወያኔ ቡድን ነው እንጂ፤ ህዝቡ ስለሰላሙ ያስባል። በአስራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን ግራኝ አህመድ ሙስሊሙን ይዞ ያን ያክል ጥፋት ሲያደርስ፤ ሙስሊሙን የድጋፍና የሀይል ምንጭ አድርጎት ለራሱ የመንግስትነትን ስልጣን ለመቀዳጅት ተዋጋ እንጂ፤ ነብዩ ሙሀመድ ያላዘዙትን፤ እስልምናን በሰይፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊያስፋፋ አልነበረም ጦርነቱ ፤ “አህባሽ የሚባለውን እስልምና ፤ እኔ ያመጣሁልህን ተቀበል ፤ ለሺዎች ዘመናት ይዘህ የተጓዝከውን እምነትህን ጣል” እያለ በኢትዮጵያዊው ሙስሊም ላይ ከጂሀድ ያልተናነስ ስራ እየሰራ ያለው ወያኔ ነው። ማሰር መግደል። ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ክርስቲያን ወንድሞቹን ያሸ በረበት ዘመን የለም። አርቲስቶቻችን እንደሻንበል በላይነህ በዜማቸው ደግመው ደጋግመው ሊናገሩት የሚገባ እውነታ ነው።
አማራ…
ግጥም፤ አይገልጽም። ዜማ፤ የህዝብ…
……ምነው ምን በደለ ደጉ ያገሬ ሰው፤
አረ የሰው ያለህ ፡አረሰው፡ አረ ሰው።
እሳት ቢያንቀላፋ ገለባ ጎበኘው፤
ዘመን አረጀና ይሄ ቀን አገኘው።
ከባህር ይሰፋል አማራ ማለት፤
ያንድነት ሀረግ ነው ኢትዮጵያዊነት ……
በፋሸሽት ወረራ ዘመን ተፈጸመ ያልተባለ ግፍ፤ አማሮች እስከወዲያኛው እንዲጠፉ፤ በሽታ ገብቷል ብለው የወያኔ ጤና ጥበቃ ሀላፊዎች ወጣት የአማራ ታዳጊዎችን በክትባት ዘመቻ እንዳይወልዱ ያመከነ አውሬ ቡድን የጁን ማግኘት አለበት። ይህ በጥይት ተጨፍጭፎ አላልቅ ያለ ህዝብ፤ እንደሌሎቹ ኢትዮጵያውያን እንደኦሮሞው፤ እንደትግሬው፤ እንደአፋሩ እንደ ደቡቡ እንደ ሁሉም….. ደሙን እያፈሰሰ ፤ ኢትዮጵያን ሲያቀና ዳር ድንበር ሲያስከብር ኖረ እንጂ፤ ወያኔ ሻእቢአና መሰሎቻቸው እንደሚያወሩት ተረት፤ ሌሎቹን ሲገዛና ሲጨቁን አልኖረም። ይልቁን ከማንም በክፋ መልኩ ሲረገጥ ነው የምናየው። የጎጃምን ድሀ አርሶ አደር፤ ከትግራይ ደሀ አርሶ አደር፤ የትግራይን ድሀ አርሶ አደር፤ ከሀረርጌ ድሀ አርሶ አደር ባጠቃላይ የኢትዮጵያን ድሀ ህዝብ አንዱን ካንዱ የተለየ የሚያደርገው የትኛው ኑሮው ነውና ነው አማራው ተለይቶ እንዲጠፋ የተፈረደበት? የህውሀት በሽተኞች አማራውን የበቀል ኢላማ ያደረጉበት ምክንያት እንደሎሎቹ ሁሉ ለኢትዮጵያ ቀናኢ በመሆኑ ነው። ወያኔ አማራን በማጥፋት ኢትዮጵያን የሚያጠፋ ሊመስለው ይችል ይሆናል፤ ግና ለኢትዮጵያ ደሙን ያፈሰሰላት ከሰሜን ምጽዋ ጫፍ እስከ ደቡብ ዶሎ፤ ከምስራቅ ፌርፌር ጫፍ እስከ ምእራብ ኢሎባቡር ጫፍ ያለ ህዝብ ሁሉ ነው። አሁንም ከወያኔ የማጥፋት ዘመቻ ያድናታል። ኢትዮጵያን ይታደጋታል።
ዘንድሮ…
ግጥም፤ ተስፋዬ ለማ። ዜማ፤ ተስፋዬ ለማ
……ህጻናት ሲሸጡ ወተው በማደጎ፤
ያለቅሳል ባመቱ ወላጅ አደግድጎ….
ሻንበል በላይነህ በዜማው የነገረን የምናየው ነገር ነው። በማደጎ ስም ህጻናቶቻችንን እየቸበቸበ ያለው ወያኔ ህጻናቱ ካገር ከወጡ በሗላ የት ወደቁ ያለበት ጊዜ የለውም። በስርቆትና በዘረፋ ስለተጠመደ ስለዜጎች የሚያስብበት ገዜ የለውም። ሽያጩ ግን በስፋት እንደቀጠለ ነው። በየ አለሙ ያሉት ኢምባሲዎቹም ድለላውናንና ዶላር ማቀባበሉን እንጂ ስለኢትዮጵያውያን መብትም ሆነ ህይወት የሚያገባቸው ነገር የለም። ዓለም ደቻሳ ቤይሩት ወያኔ ኢንባሲ ፊት ለፊት ነበር ኡ ኡ እያለች በባእድ ጫማ ስትረገጥ መሬት ለመሬት ስትጎተት በዚያው የራሷን ህይወት ያጠፋችው። የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተብሎ ወያኔዎች እዚያው ነበር አድፍጠው በዚያች ኢትዮጵያዊ ድሀ ላይ ይደርስ የነበረውን የሚመለከቱት። እነዚህን ነው ሀያ ሁለት አመት ተሸክመን የተቀመጥነው።
…..ጥያቄ ባነሳ መብቱን ያስከበረ፤
ጸረ ሰላም ሲሉት በህግ ሽብር፤
እውነቱን አውጥቶ ስለተናገረ፤
ስንቱ ጋዜጠኛ እስር ቤት ታጎረ… ዘንድሮ
ፍርሀት አሽነፈን….
ግጥም፤ ተስፋዬ ለማ። ዜማ፤ ተስፋዬ ለማ
….ፍራት አሽመድምዶን ጥሎን ባደባባይ፤
ክፉንም ደጉንም ሁነናል ተቀባይ፤
የቆረቆረንን ምቹ ስናስመስል፤
ስንጨስ እንኖራልን ስንጠቁር ስንከስል……
አዎ .. ኢትዮጵያውያን በባህላችንም በተፈጥሮአችንም፤ ለህግ የመገዛት፤ የማክበር፤ በይሉኝታ መገዛት መፍራት፤ ስለሚያጠቃን፤ አንዳንድ ጌዜ ስንገፋና መብታችን ሲገፈፍ፤ ይህ ተፈጥሮ ከልክ ያለፈ ትግስት እንዲኖረን ያደረገ ይመስላል። ለዚህ ስርአት ያሳየነው ከልክ ያለፈ ትግስት ፍርሀት ነው የሚመስለው። አርቲስት ሻንበል በበላይነህ ምናልባትም ይህንኑ ታዝቦ ሳይሆን አልቀረም በዜማው እየነገረን ያለው። ሆድ ይፍጀው ወይም የባሰ አታምጣ እያልን ይኸው ሀያ ሁለት አመታት ጉዳት ተሸካሚዎች ሆነን በዚያው ጉዞ ቀጥሏል።
….. በጥቅም ሲፈረድ፤ በወገን ሲሰራ፤
አይተን እያለፍን ስንጠብቅ ወር ተራ፤
ፍርሀት እንደውሀ ወኔያችን አፍሶት፤
ይዘን ኖራለን የማይወጣ ብሶት…
መለስ ስብሀት ሰራሹ የወያኔ ገዢ ቡድን ወደስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በመንግስቱም ሆነ በግላ ተቋማት፤ ያሻውን ሲሰራ ስንቱን ሺህ ሰራተኛ በገፍና በግፍ እያባረረ የወደደውን የራሱን ምልምል እስከ አሁን ድረስ ሲሰገስግ፤ ሁሉም ተራው ሲደርስ ሜዳ ላይ እየተጣለ ከማልቀስ በቀር ዛሬ በወገኔ ላይ የደረሰ ነገ በኔ ነው ብሎ አምርሮ ስራቱን ለመዋጋት የተነሳ እስካሁን የለም።
የቀድሞው ሰራዊት…..
ግጥም ይልማ ገብረአብ። ዜማ ሻምበል በላይነህ
….ጊዜ ተለውጦ ቀን እስከሚከዳው፤
አንጠፍጥፎ ቀምሶ ውሀውን ከኮዳው፤
ያገር መሰረቱ ህብረቱ እንዳይናድ፤
ኑሮውን አድርጎ በቀበሮ ጉርጓድ፤
ታግሎ ወድቆልናል ስላንድነታችን፤
ውለታው ይዘከር የሰራዊታችን።
ሳያጓድል ያባት አደራ፤ ያስጠበቀ ያገር ባንዲራ፤
እንዳናጣ የባህር በር፤ ነፍሱን ከፍሏል ለኛ ክብር……
የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታ እንደሚባለው ; የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጦርሰራዊት መበተኑ ሳያንሰው ፤ ለወያኔ የፕሮፓጋንዳ ሰለባ እንደሆነ እስካሁን በመቆየቱ እድሜ ልኩን ሲዘመርለትና ሲሞገስ ሊኖር የሚገባው ጀግና ሰራዊት፤ ባልፉት ሀያ ሁለት አመታት እንደዋዛ ተዘንግቶ ቆይቶ ነበር። ሻንበል በላይነህ ምስጋና ይድረሰውና ዛሬም እንደትናንቱ የዚያን ክቡር ሰራዊት ገድል አንስቷል። ይበል የሚያሰኝ ነው። የኢትዮጵያን ሰራዊት ሀያል ክንድ አጣጥመው የሚያውቁት ገንጣይና አስገንጣይ እንዳላሸነፉት ልቦናቸው ያውቀዋል። ሰራዊቱን በአካልና በሞራል ከውስጥ ይገልላቸው የነበረው መንግስቱ ሀይለማርያም ባለውለታቸው ነው። በዚያ በውሸት ፕሮፓጋንዳቸው እውነት ለዲሞክራሲና ለእኩልነት የሚዋጉ መስሎት በገፍ እየሄድ ሲቀላቀላቸው፤ ያልተቀላቀለውም መሳሪያውን አውርዶ ባዶ እጁን የቆመ ወታደር በመትረየስ እያጨዱ ነበር ተሯሩጠው ድፍን ኢትዮጵያን እንደ ወባ ትንኝ የወረሯት። መልካሙ ነገር ኢትዮጵያውያን ጀግኖቻችንን መሸለም መጀምራቸው ነው። ያየር ሀይል፤ የምድር ጦር የባህር ሀይል ጀግኖቻችን አሁንም ሊዘፈንላቸው ሊሸለሙና ሊወደሱ ይገባል።
ታሪክ ይፍረደን፤
ግጥም፤ ተስፋዬ ለማ። ዜማ፤ ተስፋዬ ለማ
…የነበረው ቀርቶ ያልነበረው ሆነ፤
የሰራነው ሁሉ እንደቀልድ ባከነ…..
……….የራሳችን ቋንቋ የራሳችን ፊደል፤
የራሳችን እምነት የራሳችን ባህል፤
የነሉሲ ሀገር፤ የሰው ልጅ መገኛ፤
በራሱ የተሟላ ማን ነበር እንደኛ……
እርግጥ ነው። በራሱ የተሟላ እንደኛ ማንም አልነበረም:: ምን ያደርጋል፤ በመካከላችን የበቀሉ፤ በዚችው ምድር ላይ የተፈለፈሉ፤ ለራሳቸው ታሪክ ባእድ ሆነው፤ አባቶቻቸው የባእድ ጠላት አሽከሮችና ባንዳዎች፤ ያ ጠላት በወላጆቻቸው እአምሮ ውስጥ ባሰረጸው እኩይ አስተሳሰብ ተኮትኩተው ያደጉ፤ ጊዜ ለነሱ አድልታ ኢትዮጵያ እጃቸው ላይ ወደቀች። በማግስቱም … የአድዋው ታሪክ ለአማራው፤ ለደቡቡ ምኑ ነው፤ የኢትዮጵያ ባንዲራ ጨርቅ ነው፤ እንኳን ከትግራይ ተወለድኩ፤ የሚል ሰው መሪ ተብሎ ባደባባይ የሚናገር፤ ሚኒሊክ ቤተ መንግስት መኖር የቻለ አጥፊ አየን። መልካሙ ነገር እግዚአብሄር ባጭር አስቀረው። የጀግኖቻችን ሀውልቶች ፈረሱ። በባንዳ ልጆች ስም ተተኩ። በዘመናት አብሮ መኖር የተገነባ የደምና የስጋ ውህደት እንዲለያይ የዘር አጥር ግርግዳ የሚገነቡ፤ በስጋ ፤ ኢትዮጵያውያን፤ በመንፈስና በገቢር ባእዳን የሆኑ ገዢዎችን ለማስተናገድ በቃን። የሻምበል በላይነህ ዜማ ይህንን ነው ልብ ብሎ ለሰማ የሚነግረው።
ኢትዮጵያ….
ግጥም፤ ይልማ ገብረአብ። ዜማ፤ ይልማ ገብረአብ
…….ኢትዮጵያ ህይወታችን፤
ኢትይጵያ ኩራታችን፤
ኢትዮጵያ እምነታችን፤
ያገር ፍቅር ጽናት የምንማርብሽ፤
በፈጠርሽው ትውልድ ይመርብሽ፤
ዛሬም ትላንትም የምልሽ ህይወቴ፤
ውዳሴ ነሽ ለኔ የዘላለም ሀብቴ….
ከዳሽ በሞትሽ ለማትረፍ፤
በሚኒሊክ ጅራፍ ልገረፍ….
ውድ አንባቢያን እነዚህ ሁሉ መልክቶች ሻንበል በላይነህ በቁም እንዋደድ በሚለው አልበሙ ውስጥ ያካተታቸው ስራዎቹ ናቸው። ሀይለስላሴ የሚል ርእስ የተሰጠው ሲዲም ብዙ ታሪካዊና ወቅታዊ መል እክቶች አሉት፤ በተለይም በከፍጠኛ ሁኔታ ወጣቶችን ለትግል የሚያነቃቃ መልእክቶችም አሉ። እራሱን ማዳመጡ የተሻለ ነው። የሻንበል በላይነህ ስራዎች ለአርቲስቶቻችን በአርአያነት የሚጠቀሱ ናቸው። ተመሳሳይ ስራዎች ከየአቅጣጫው ብቅብቅ ቢሉ የህዝባችንን ንቃት እጥፍ ድርብ ያሳድጉታል። ሻንበልም የነጻነት ቀን እስከሚመጣ በያዘው መንግድ እንደሚጓዝና ሌሎችንም እንደሚያስከትል ተስፋ አደርጋለሁ።
ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!!
አንዱአለም አራጌ (የአንድነት ምክትል ሊቀመንበር) በኢሳት ሬዲዮና ቲቪ የ2006 የዓመቱ ምርጥ ኢትዮጵያዊ እና ዘሐበሻ ድህረ ገጽ የ2006 የዓመቱ ምርጥ ሰው ተብሎ ተሰየመ!!! ይገባዋል!!
የአስተሳሰብ እንጅ የዓመት አዲስና አሮጌ የለውም!
በአዲስ ዓመት የኃይማኖት፣ የፖለቲካ አስተሳሰብ፣ የብሔር ልዩነትቶች፣ ድህነት፣ ሁከት፣ ጦርነት፣ ስደት፣ ምቀኝነት፣ ጭንቀትና ልመና ተወግደው ሰላም፣ ጤና፣ ህብረት፣ እኩልነት፣ ነጻነት፣ ብልጽግና፣ ዕድገት፣ ለውጥና ደስታ አዲስ ይሆንለት ዘንድ ተስፋ የማያደርግና የማይመኝ የለም። በምኞት የሚሆን ነገር የለም እንጅ ቢሆን እኔም ደስ ባለኝ። በእርግጥ አዲስ መንፈስ/አዲስ ህልም አዲስ ዓመት እየተባለ ከሚከበረው በዓል ጋር ምንም ግኑኝነት የለውም። ይህ ብቻም አይደለም አርጅቶ የሚያልፍ አዲስ ሆኖ የሚወልድ ዘመን የለም። እንደ ሣር እንደ ዱር አበባም እንዲሁ አብቦ ነፋስ በነፈሰበት ጊዜም የሚያልፈው የሰው ልጅ ብቻ ነው (መዝሙረ ዳዊት 103፥ 15)። ዓመት “ስለ ሄድ” ዓመት “ስለ ስለመጣ” የሚለወጥ አንዳች ነገር የለም። ቁልፉ/መፍትሔው ያለው ኮንትራታችን ጨርሰን እስክንሸበለል ድረስ አንዱን ‘እየሸኘን” ሌላውን “እየተቀበልን” በምንገኘው በእኔና በእናንተ እጅ ነው ያለው። እውነቱን ለመናገር አንዱ እየተቀበለ አንዱን የሚሸኝ ዘመን እንጅ ሰው ዘመን ተቀብሎ ዘመንን አይሸንም። የአቅጣጫ ለውጥ ለማድረግ ቆርጠው የተነሱ እንደሆነ ከዓመት “መባቻ” ሆነ ከዓመት “መጨረሻ” ምንም የሚያገናኝ ዓመትም የምያስጠብቅ አንዳች ምክንያት የለንም። አይመስሎትም?
እኔ እስከማቀው ድረስ ለበሽታቸው መድኃኒት ፍለጋ ወደ ቤተ ሳይዳ የማጥመቂያ ስፍራ ይወርዱና የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ ይንቦጫረቁ የነበሩ የኢየሩሳሌም ዕውሮች፣ አንካሶች፣ ሰውነታቸውም የሰለለ ነው። የእርስዎስ? ከሰው በታች ያደረገን የአእምሮ ፈውስ ያስፈልገናል ነው የምሎት።
ሙሉ የጽሑፉ ይዘት ለማንበብ የሚቀጥለውን ሊንክ ይጫኑ
http://salsaywoyane.wordpress.com/
“ወጣቱ አንበሳ ላገርህ ተነሳ…”
Normal 0 false false false MicrosoftInternetExplorer4
/* Style Definitions */ table.MsoNormalTable {mso-style-name:"Table Normal"; mso-tstyle-rowband-size:0; mso-tstyle-colband-size:0; mso-style-noshow:yes; mso-style-parent:""; mso-padding-alt:0cm 5.4pt 0cm 5.4pt; mso-para-margin:0cm; mso-para-margin-bottom:.0001pt; mso-pagination:widow-orphan; font-size:10.0pt; font-family:"Times New Roman"; mso-fareast-font-family:"Times New Roman"; mso-ansi-language:#0400; mso-fareast-language:#0400; mso-bidi-language:#0400;}
የአርቲስት ሻምበል በላይነህ አገራዊ ስራዎች አርአያነት
(ሉሉ ከበደ -ጋዜጠኛና ደራሲ)
ውድ ኢትዮጵያን ወገኖቼ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ። እዲሱ አመት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ብስራት ይዞ የሚመጣ ይሁን። ያለምንም ደም መፋሰስ ይህ ዘረኛ የወያኔ ገዢ ቡድን መቃብር ገብቶ፤ ዘረኝነት፤ ጎጠኝነትና በታኝነት ከምድራችን ጠፍቶ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተፋቅሮ ተከባብሮ፤ ሲያጠፉ የሚቀጣቸውን የሚሽራቸውን፤ ሲያለሙ የሚሾማችውን የሚሸልማቸውን መሪዎች በድምጹ መርጦ፤ የሚኖርበት፤ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከዘር ማንነቱ በፊት በኢትዮጵያ ሲምል ሲገዘት የምናይበት፤ ዜጎች ሁሉ ለሀገሬ፤..... ለወገኔ.. እያሉ ሲተጉ፤ ለጋራ እድገትና ብልጽግና ሲጓጉ....አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ እያሉ አንዳቸው ላንዳቸው ሲሞቱ የምናይበት የተአምር ዘመን ይሁንልን,....ዘረኞች ለአንዴና ለመጨረሻ የሚጠፉበት ዘመን ይሁንልን....2006. አሜን!
“ኢትዮጵያከ2ኛየዓለምጦርነትበኋላየተፈጠረችሀገርናት!”
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
የባሰ አታምጣ! ነው የሚባለው። መቼም የኤርትራ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋዜጣዊ መገለጫ በሰጡ ቁጥር ግርግር ሳይፈጥሩ፤ ጎረበት አገር በውስጠ ወይራ ሳይጎነትሉ፤ ምዕራባውያን መንግሥታት ግልጽና በማያሻማ ቋንቋ ሳይወርፉና ሳይዘነጥሉ፤ ብዙሐን ፈገግ ሳያሰኙ፤ በአንጻሩ ደግሞ የተማረውን ክፍል ሳያስለቅሱና እርር ድብን እስኪል ድረስ ሳያደርጉ አልፉ ማለት ዘበት ነው።
የመቅደላው ዮሐንስ እሸቴ በሎንዶን
ይመኩ ታምራት ከሎንዶን
መቶ አርባ-አምስት ዓመት ያስቆጠረውን መቅደላን ስናነሳ መቼም ዓፄ ቴዎድሮስና ታላቁ ጀብዷቸው፤ ሮበርት ናፒዬር እና እንግሊዞች በሀገራችን ላይ ያካሄዱት ከ'ግዳጅ ወሲብ' ጋር የማይተናነስ ደፈራ እና ብዝበዛ፣ የነደጃች ካሣ ምርጫ ሴራ፤ የልጅ ዓለማየሁ መሰደድና በለጋ ዕድሜው ከሀገርና ከዘመድ ተለይቶ ሳለ የሕይወቱ በአጭሩ መቀጠፍ፣ ወ.ዘ.ተ. ይታወሱናል። ስለዚያ ወቅት ታሪክ በጥልቀት ለሚያጠና፣ አያሌ መጻሕፍትና ማስታወቻዎች፤ አብዛኞቹ በነጮቹ፣ አንዳንድም በኛው ሰዎች ተጽፈው በታሪክ ማኅደር ውስጥ ይገኛሉ።
ወቅታዊ የቴሌ-ኮንፍረንስ ስብሰባ ግብዣ – ጋባዥ፥ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት የሰሜን አሜሪካ ግብረ ኃይል – ተጋባዥ፥ ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች እና የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ዜጎች
ጋባዥ፥ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት የሰሜን አሜሪካ ግብረ ኃይል
ተጋባዥ፥ ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች እና የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ዜጎች
በስብሰባው ላይ የሚገኙት እንግዶች፥
1)የተከበሩ አቶ ተክሌ በቀለ – የአንድነት ፓርቲ ትሬዠረር
2)አቶ ሀብታሙ አያሌው – የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ምክትል ሃላፊ
3)የሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች ተወካይ
እንደሚታወቀው ላለፉት ሦስት ወራት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከገዢው ፓርቲ ያጋጠሙትን እንቅፋቶች በሰላም እየተራመደ በጎንደር፣ በደሴ፣ በባህርዳር፣ በአርባ ምንጭ፣ በጅንካ፣ በፍቼ፣ አዳማ ከተሞች ሕዝቡን ያሳተፉ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች አከናውኗል፡፡ አንድነት የጀመረውን ይኽን ሕዝባዊ ሰላማዊ ንቅናቄ የመጀመሪያ ምዕራፍ ከሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በሚያካሂደው ህዝባዊ ሰልፍ እንደሚያጠናቅቅ ለመንግስት ቀደም ብሎ አስታውቋል። ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስፈልገው ከ24 ሰአቶች ቀደም ብሎ ለመንግስት ማሳወቅ እንጂ ማስፈቀድ እንዳልሆነ ህገ-መንግስቱ እንደሚደነግግ ቢታወቅም አንድነት ግን ከነሐሴ 21 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ መንግስት እንዲያውቅ በማድረጉ ሰልፉ በታቀደው ቀን መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠኋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ይደረጋል፡፡
ስለዚህ እሁድ መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም. (September 15, 2013) በአዲስ አበባ በሚካሄደው የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ሰላማዊ ሰልፍ እና በቀጣዩ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ሰላማዊ ትግላችን ቀጣይ ምዕራፎች ላይ ከፍ ብለው የተጠቀሱት እንግዶች በቴሌ-ኮንፍረንስ ከኢትዮጵያውያን ጋር አሳብ ስለሚለዋወጡ የውይይቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የሰሜን አሜሪካ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ግብረ ኃይል በአክብሮት ጋብዞዎታል።
በዚኽ ቴሌ-ኮንፍረንስ ከተጋበዙት ሚዲያዎች ውስጥ ጥቂቶቹ፥
1) ፓልቶክ ሚዲያዎች፥ ቃሌ፣ ሲቪሊቲ እና ኢትዮጵያዊ ከረንት አፌርስ
2) ሪዲዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶች፥ የአሜሪካ ድምጽ (አማርኛ፣ ትግሪኛ እና ኦሮምኛ ፕሮግራሞች)፣ ኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ፣ የጀርመን ሬዲዮ ጣቢያ፣ የዲሲ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ሬዲዮኖች በሰሜን አሜሪካ በሙሉ
3)ድረገጾች፥ ዘሐበሻ፣ ኢትዮሚዲያ፣ ኢትዮሚዲያ ፎረም፣ አቦጊዳ፣ ኢትዮጵያዊ ሪቪው፣ አውራምባ ታይምስ፣ ኢትዮጵያዊ ከረንት አፌርስ ፎረም እና ሌሎች
ቴሌ-ኮንፍረንሱ የሚደረገበት ቀን እና ሰዓት፥
ቀን፥ ቅዳሜ መስከረም 4 ቀን 2006 ዓ.ም. (Saturday, September 14, 2013)
ሰዓት፥ ከቀኑ 1፡00 ሰዓት (1:00 PM Eastern Time)
በቴሌ-ኮንፍረንሱ ለመሳተፍ፥ (267) 507-0240 ይደውሉ እና 20-18-20 ኮድ ይጠቀሙ
የደርብ ከፈለኝ አስተያየት በእኔ እይታ – መሠረት ከቴክሳስ
‘አህያውን ፈርቶ ዳውላውን’ በሚል ርእስ በተክለሚካኤል ላይ የስድብ ውርጅብኝ ያወረዱት ደርብ ከፈለኝን ሳስብ በእኛ በኢትዮጵያውያን ውስጥ በብዙ ሰዎች ዘንድ የማየው በሽታ ታወሰኝ። ይኸውም ታዋቂን፣ሀብታምን፣ባለስልጣንን እንደው ብቻ በማናቸውም መልኩ በማህበረሰቡ አይን ውስጥ የገባን ሰው ማሞካሽት፤ ቢሳሳት እንኳን ስህተቱን ስህተት ነው ብሎ ደፍሮ ከማረም ግለሰቡ ከተናገረው ይዘት ጋር በማይገናኝ ሁኔታ አቃንቶ እንዲህ ለማለት ፈልጎ እኮ ነው ብለው የሚሉ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ። እንዲህ አይነት ሰዎች ከባለ ጉዳዩ በላይ ተቆርቋሪ ሆነው ከስህተቱ እንዳይማር መንገድ የሚዘጉ፣እንደዚያ አይነት ሰው ስህተት ቢፈጽም እንኳን ይቅርታ መጠየቅ የማይገባው መሆኑን እስከመግለጽ ይደርሳሉ።
ይህን መሰል አንድ እውነተኛ ታሪክ ላጫውታችሁ። በአሜሪካን አገር ውስጥ አንድ የአበሻው ብዛት ከሁለት ሺህ አይበልጥባትም በምትባል ከተማ ውስጥ አበሾች ተሰባስበው ቤተክርስቲያን ይተክላሉ። ቤተክርስቲያኗም የምትተዳደረው አቡነ ይስሐቅ በሚባሉት ጳጳስ ስር ነበር። አቡነ ይስሐቅ ነፍሳቸውን እግዚአብሔር በገነት ያኑርልንና በዘመናቸው የኢትዮጵያን ቋንቋ የማይናገሩ ህዝቦችን አስተምረው የእኛን ኦርቶዶከስ እምነት አለማቀፋዊ ይዘት ያላበሱ ትልቅ አባት ነበሩ። እሳቸው ከሞቱ በሁዋላ ቤተክርስቲያኗ ከአገር ውስጥም ከውጨውም ሲኖዶስ ሳትሆን ከምእመናን በተውጣጡ የቦርድ አባላት እየተመራች ባለችበት ሁኔታ ውስጥ የቤተክርስቲያኗ ካህን ምእመኑን ለመከፋፈል እራሳቸውን አንዴ የወሎ ሰው ነኝ ብለው ወሎዬውን ሲሰብኩ ሌላኛውን ጎጃሜነኝ ሲሉ ሌላውንም ሌላ እያሉ ምእመኑን እየፈተሹ ባሉበት ሂደት ውስጥ አንድ ቀን ያልታሰበ ዱብዳ ተፈጠረ ። ይኸውም ካህኑ ከአራት አባት ምአመናን ጋር የቆመችውን ሴት የተናገሩትን ለመድገም በሚያሸማቅቅ ቃላት ዘለፉዋት። መንፈሳዊው አባት ሲሳደቡ ምእመን አባቶች ቆመው ታዘቡ። በትዝብት ማለፉ አስተማሪነት የለውም በሚል በአደባባይ በደፈናው ስህተት መፈጸማቸውን አምነው ይህቺን ሴት በቤተመቅደስ ቆመው ይቅርታ እንዲጠይቁ ከ4ምእመናን ሶስቱ ጠየቁ። አራተኛው ግን ይህ ነገር በእኛው መሀል ይቅር፣ ሴትየዋን እኛ ይቅርታ ጠይቀን ለሌላም ሰው እንዳትናገር እናግባባት በሚል አቋም ይይዛሉ። የተቀሩት ሶስቱ ግን ይህ በተአምር አይደረግም ብለው ጉዳዩን ምእመኑ ፊት ይዘውት ቀረቡ። ብዙዉ ምእመን ካህን ቢያጠፋ እግዜር ይጠይቀው እንጂ ሰው ምን አገባው ባይ ሆነና ለካህኑ የቆመው ሰው ጉልበት አገኘ። እነኝህኞቹ እውነትን ይዘው ካህኑን ሞገቱዋቸው። ካህኑም ስለ እውነት ስንት ነገር እያስተማሩ ፊትለፊታቸው እውነት ሲያፈጥባቸው አልቻሉምና ልክናችሁ ልጆቼ ብለው ለይቅርታ ንስሀቸውን መናዘዝ ሲጀምሩ ከአራቱ አንዱ የሆነው ሰው ‘ልጅ እንጂ አባት ይቅርታ እንዴት ይጠይቃል’ በማለት ሌላውን ምአመን ምን ዝም ትላላችሁ በማለት ሲያነሳሳ ካህኑም ወዲያው ሀሳባቸውን ገልብጠው ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ጉባኤው በብጥብጥ ተበተነ። ይህቺ አጋጣሚ ለካህኑ የትልቌ እድል በር ከፈተችና ለእውነት ሲሙዋገቱ የነበሩት ምእመናንና ተከታዮቻቸው ሲቀሩ የተቀሩትን ይዘው ቤተክርስቲያኗን ለአባ ጳውሎሱ ሲኖዶስ የእጅ መንሻ አድርገው በማቅረብ እሳቸውም የጳጳስነት ሹመታቸውን በማግኘት ሂደቱ ተጠናቀቀ።
መቼም ይሄ ጥፋት ህሊና ለአለው ሁሌም ሲያሳፍር የሚኖር ነው። ዛሬ በዚያ አካባቢ ለአንድ ቤተክርስቲያን የማይበቃ ህዝብ በአለበት፣ ሁለት ቤተክርስቲያን ተሰርቶ ሰዉም ቂም ቋጠሮ ያንን ክፉ ቀን በሁለቱም ወገን የማይረሱት ታሪክ ሆኖ ተቀምጧል። የያኔው ቄስ የዛሬው ጳጳስ እድሜ ሰጥቷቸው ይህን ማስተዋል ከቻሉ የህሊና ቁስል እንደሚሆንባቸው አልጠራጠርም። የእሳቸው ተቆርቋሪ ነኝ ብሎ ትልቅ ስህተት ውስጥ የጨመራቸውን ሰው ግን ያ ሰይጣን ባያሳስተኝ ኖሮ እኮ እንደሚሉ አሁንም በድጋሚ አልጠራጠርም። ሰውየው ካህን ተሳስቷል ከሚለው ሃሳብ ተሻግሮ ይቅርተቀ ይጠይቅ የሚለው ሃሳብ አሳፋሪ አድርጎ በውስጡ በማመኑና እምነቱን ከእራሱ አልፎ ለሌሎችና ባለጉዳዩንም የሃሳቡ ተጋሪ በማድረጉ እራሱ መሳሳቱ ሳይበቃው ካህኑንና ሌሎችንም ከእውነት ጋር አጣልቱዋቸው ለብዙዎች የተረፈ የታሪክ ጠባሳ ጥሎ አልፉዋል። ደርብ ከፈለኝ በጽሁፎት ላይ ማጋነን ባይሆንብኝ ከ90 በመቶ በላይ ትችቱ ተክለሚካኤልን መዝለፍ ነው። አንባቢም ሆነ ተተቺ እንዲሁም ተቺ እርሶ ትችቱን ስር በያዘና በጥሩ ምክንያቶች የእራስዎትን እይታ ቢሰጡ መልካም ነበር። መቼም ዶ/ር ብርሃኑ እንደቄሱ ደጋፊ ከአገኘሁ ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ የእርስዎ ደጋፊ ሊሆን እንደማይችል እገምታለሁ። የእኔ ጽሁፍ አላማ በተክሌ ጽሁፍ አስተያየት ለመስጠት ባይሆንም ዶ/ር ብርሃኑ ግን የተክሌ ሀሳብ የእሱ ብቻ አለመሆኑን ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስባለሁ። ባለራዕዩ፣ ምሁሩ ፣ የምርጫ 97 ሞተሩ፣የእስርቤቱ ታሪክ ጸሐፊው እንዲሁም የግንቦት 7 ፈጣሪው ብርሃኑ እንደ ሰው ለፍጹምነት ሲሮጥ ያልፋል እንጂ ፍጹም አይደለም። እንደ ሰው የሚጎለውን ፊትለፈት ነግረነው አድመጭ መሪያችን እንዲሆን ማድረግ ይኖርብናል። መተቸትን ዛሬ በቅርብ ሆኖ ካላስለመድነው ነገ ስልጣን የመያዝ አጋጣሚው ቢፈጠርና አውሬ ሆኖ ቢበላን ጥፋቱ የእኛ እንጂ የእሱ አይሆንም። ለማንኛውም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እባክህን አስተያትህን ስጠን። ካልሆነ ግን ኢሳት ላይ ጠይቁት ከተባለ ይህቺ ጥያቄ የእኔ ናት።
መሠረት ከቴክሳስ
ሕዝብን የሚያሸብር ሥርዓትና የህዝቡ መከራ -አበራ ሽፈራው /ከጀርመን/
አበራ ሽፈራው /ከጀርመን/
ዛሬ አለማችን በከፍተኛ ስልጣኔ ላይ ትገኛለች። በዚህም ስልጣኔ ውስጥ በኢንተርኔትና ተያያዥ የመገናኛ ዘዴዎች ተጠቅሞ የሰው ልጅ የሚፈልገውን መረጃ መፈልግ፣ማግኘት፣መለዋወጥና ማሳወቅም ሆነ ማወቅ የሚችልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።
ጊዜው ለውሸታሞች ፣ ለአታላዬች፣ ለግፈኞች እና ለበዝባዦች የሚመች አይደልም፤ ዓለም መድረስ ወደሚፈልግበት እየሔደ ነው፤ጊዜው ወደፊት መሄድን እንጂ እንደኃለኛው ዘመን ማሰብን አይፈቅድም፤ ስለዚሀ ከጊዜው ጋር አብሮ መሄድ ካልሆነም ውሸታሞች ውሸታቸውን ሊድብቁ የሚችሉብትን አዳዲስ መሳሪያዎችን መፈብረክ ይጠይቃል።አለመታደል ሆነና ህወሓቶች ስለእነሱና ስለተግባራቸው ማንም የሚያውቅ አይመስላቸውም። ትልቁ የሚያውቁትም ቃታን እየሳቡ ሰውን መግደል ብቻ መሆኑን ድርጊታቸው እያሳየን ነው፤ በዚህም ድርጊታቸው እንደ ትልቅ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እራሳቸውን ከመሪዎቻቸው ጀምሮ ሲያጋንኑ፣ ከበሮ ሲያስደልቁ ኖርዋል አሁንም በሰብዓዊ ፍጥረት ላይ ግድያን መፈጸም፣መስረቅ፣መንጠቅ፣ማሸማቀቅ፣እያሰሩ ማሰቃየት፣በአጠቃላይ ግፍን መፈጸምና ማሸበር እንደትልቅ ሙያና ተግባር ተያይዘውታል።
ህወሃት /TPLF/ እ.ኤ.አ ከ1976-1991 በሰው ልጆች ላይ በፈጸማችው የሽብር ወንጀሎችና ጥቃቶች በአሸባሪነት ተመዝግቦ የነበረ ቡድንም ነበር። ህወሓት ሽብርን ለመፈጸም ለ39 ዓመታት ያካበተው ልምድ ቢኖረውም ከዚህ በላይ መሽበር ግን የህዝቡ ግዴታ ሊሆን አይግባም።
ህወሓት ዛሬ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልን ሽብር፣የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄን ሽብር፣ጋዜጠኝነትን ሽብር፣መደራጀትን ሽብር ፣ሃሳብን በነጻነት መግልጽን ሽብር በማለት ህዝብን ሲያሸብር ሲታይ ህወሓት ስሙንና ተግባሩን ለሌላ ለመስጠት የፈለገ ይመስላል።
በየጊዜዉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅት አማካኝንት የሚነዙትን ፕሮፓጋንዳ ላየና ለሰማ ሁሉ ሽብርተኝነት ህወሃትን ያስመረረው ይመስላል። ይልቁንም የኢትዮጵያ ህዝብ በህወሃት መሸበሩንና መማረሩን፤ የሽብርተኝንት ታሪክም የህወሓት የራሱ የ39 ዓመታት ታሪክ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ እንደልሆነ ለህወሓት ለራሱ ሊነገረው ይገባል።
- 1. ህወሓት መንግስት ከመሆኑ በፊት የፈጸማቸው የሽብር ተግባራት ምን ነበሩ ?
ሀ. ህወሓት አሸባሪ ድርጅት የነበረና የተመዘገበም መሆኑ፡-
በዩ.ኤስ.ኤ አሜሪካ በአገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት አማካኝንት በሜሪላንድ ዩንቨርስቲ በአለም አቀፍ ደረጃ የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴና ድርጊታቸውን የሚመዘግበውና የሚተነትነው የመረጃ ማዕከል ማለትም The National Consortium for the study of Terrorism and Responses to Terrorism/START/ ለመረጃ መሰብሰቢያ ባዘጋጀው ዳታ ቤዝ ወይም GTD/Global Terrorism Data Base/ ክፍት በሆነው የመረጃ ፍልሰቱ ውስጥ እ.ኤ.አ ከ1976-1991 ድረስ አሥር/10/ ልዩ ልዩ የሽብር ጥቃቶች በህወሓት/TPLF/ መፈጸማቸውን መዝግባል፤ በነዚህ የሽብር ድርጊቶቹ ህወሓት አሸባሪ ድርጅት ተደርጎ ተመዝግባል። ይህ የመረጃ ማዕከል ህወሓት የፈጸማቸውን የሽብር ድርጊቶች የዘረዘረ ሲሆን በዚህ መረጃ ላይ ድርጊቱ የተፈጸመበት ቀን፣ ቦታ፣የአደጋው ብዛት፣ የአደጋው አይነት፣የተጠቀማቸውን የመሳሪያ ዓይነት ለመመዝገብ ሞክሯል፤በዚህ መረጃ መሰረት በራያ ቆቦ፣በትግራይ ቦታዎች፣በላሊበላ፣በጅሬ፣በኮረም፣በወርቅ አምባ፣በአክሱምና በሌሎች ቦታዎችም የሽብር ድርጊቱ የተፈጸመ መሆኑን ጽፋል፤በነዚህም ጥቃቶች የሃይማኖት ተቃማትና መሪዎች፣በግለሰብ ህይወት እና ንብረት ላይ፣ በመንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ፣በንግድ ተቃማት ላይ ፣በጋዜጠኞች እና ሚዲያዎች ላይ ሽብሩ መፈጸሙን ዘርዝሯል። ስለዚህ ህወሓት አሸባሪ ድርጅት እንደነበረና ተግባሩም ሽብር እንደነበረ ለማወቅ ይቻላል። ለበለጠ መረጃ http://www.start.umd.edu/start/ ይመልከቱ።
ለ. ህወሓት ልዩ ልዩ ሽብሮችን ሲፈጽም እንደነበረ አባሎቹ የነበሩ መመስከራቸው፡-
የህወሃትን እኩይ ተግባር በማጋለጥ የሚታወቁት አቶ ገብረመድህን አርአያ ስለ ህወሓት ያለፈው ታሪክ ላይ በጻፋቸው ጽሁፎች ላይ ህወሓት ግልጽ አሸባሪ መሆኑን በተደጋጋሚ ከመግለጻቸውም በላይ አሁንም ካዩትና ከሰሙት እዉነታዎች ተነስተዉ ይህንን አሽባሪ ድርጅት እያጋለጡም ይገኛሉ።
ህወሓት ከምስረታው ጀምሮ የተነሳው የራሱን የህወሓትንና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ለማስጠብቅ ሳይሆን ጥቂቶች በስውር ይዘዉት የተነሱትን ስውር የዘረኝነት፣የብዝበዛና የጭቆና ዕቅዶቻቸውን ከግብ ለማድረስ እንደህነ ተግባራቸው ያሳየና፤ ይህንንም ግባቸውን ለመፈጸም የትኛውንም ሽብር ከመፈጸማቸው ጋር ተያይዞ ህወሓቶች በዓለም ከሚታወቁ የሽብርተኛ ቡድን ተርታ ተሰልፈው የነበረ ቢሆንም ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት ጋርና ከደርግ መንግስት መንኮታኮት ጋር ተያይዞ አገራችን በአሸባሪዎች እጅ ወደቀች፤ ደርግና ባለማሎቹም እንዲሁም ዋና ዋናዎቹም የዓለም መንግስታትም ህዝቡንና አገራችንን አሳልፈው ለሽብርተኞች ሰጡ ። ይለወጣል ብለው ብዙዎች ቢጠብቁትም ተግባሩ ያለቀቀው ህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ከሆነም በኃላ ከቡድናዊ ሽብርተኝንት ወደ መንግስታዊ ሽብርተኝነት ተሸጋገረ።
- 2. የህወሓት/ኢህአዴግ የመንግስት ስልጣን ከያዘ በኃላ ወደ መንግስታዊ ሽብርተኝነት መቀየር /State Terrorisim/
ሀ . ለመሆኑ የመንግስት ሽብርተኝንት/ State Terrorisim/ ምንድ ነው?
ጸሃፊዎች የሽብርተኝነት መሰረታዊ ዓላማ ሽብርተኞቹ የሚፈልጉትን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ሃይማኖታዊ ግቦችን ተግባራዊ ለማድረግ ልዩ ልዩ መንገዶችን ተጠቅመው በህዝቦች ላይ ከሚገባው በላይ ፍርሃትን በመፍጠርና በማስገደድ ዓላማቸውን ከግብ ማድረስ እንደሆነ ይገልጻሉ።
በ acadamia.org ላይ የመንግስት ሽብርተኝነትን እንደዚህ ጽፎታል፡- State terror refers to the use or threat of violence by the state or its agent or supporters,particularly against civilian individuals and population,as a means of poletical intimidation and control.
የፖለቲካ የበላይነትን ለመያዝና ጫናን ለመፍጠር በተለይም በሰላማዊ ግለሰቦችና ህዝቦች ላይ ተገቢ ያልሆነን ጥቃትን በራሱ በመንግስት፣በተወካዮቹና በደጋፊዎቹ ሲፈጸም ይህንን ጥቃት መንግስታዊ ሽብር ብሎታል።
እንግዲህ ህወሓት/ኢህአዴግ ምንም እንካን የመንግስትን ሥልጣን የያዘ ቢሆንም ሌሎች አሸባሪ ድርጅቶች የሚፈጽማቸውን ተግባራት በግልጽና በአደባባይ ይፈጽማል። ከነዚህም ውስጥ ፍንዳታን ይፈጽማል ፣ያፍናል፣ህጋዊ ያልሆኑ እስራትን ይፈጽማል፣በሰብዓዊ ፍጥረት ላይ የማይፈጸሙ ድብደባዎችን፣ በወንዶችም ሆነ በሴቶች የመራቢያ ብልቶች ላይ አደጋን ማድረስ፣አካለ ስንኩል ማድረግ፣ ቤተሰቦች እንዲለያዩ ማድረግ፣ ስውርና የአደባባይ ላይ ግድያዎችንና ሌሎችም ተግባሮችን ይፈጽማል።ከዚህም ድርጊቱ አንጽር ህወሓት/ኢህአዴግ ከአሸባሪነት መገለጫዎች የዘለሉ ተግባሮችን የሚፈጽም ቡድን መሆኑን ያሳያል።
ህወሓት/ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን የሽብር ጥቃቶችን ኢትዮጵያውያን በግልጽ የሚያውቁት ጉዳይ መሆኑ ፣የልዩ ልዩ ሃገራት መንግስታትና በኢትዮጵያ የሚኖሩ የልዩ ልዩ ሃገራት አምባሳደሮችም ሳይቅሩ በግልጽ የሚያውቁት መሆኑና ይህንንም የሚያግዙ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ መሆናቸው፤በተለይም የዩ.ኤስ.ኤ አሜሪካንና ሌሎችንም መረጃዎችን በመሰብሰብ እና በማጋለጥ የሚታወቀው ዊኪሊክስ ይፋ ባደረጋቸው መረጃዎች መሰረት እነዚህ እውነታዎች ግልጽ እየሆኑ መምጣታቸውና በተለይም ህወሓት የራሱን የሽብርን ጥቃት ለመፈጸም እንዲያግዘው ኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር ጥቃት እንዳለ ለማስመሰል ሲጠቀምባቸው የነበሩትን የማታለያ እንቅስቃሴዎች ማለትም የሽብር መሳሪያዎችን በራሱ ወታደሮችና የደህንነት ሰዎች በልዩ ልዩ ቦታዎች በማስቀመጥ መልሶ በራሱ የደህንነት ሰዎች እንደተገኙ በማስመሰል ያደርገዉ የነበረውን ተግባር አጋልጧል፤ እነዚህም ድርጊቶቹ አስቀድሞም ብዙዎች የነበራቸውን ጥርጣሬም አጠናክሮታል።
ለ. ህወሓትኢህአዴግ የፈጸማቸው የሽብር ጥቃቶችስ ምንድ ናቸው?
ህወሓት/ኢህአዴግ የመንግስትን ሥልጣን ከያዘ በኃላ መጠነ ሰፊ የሽብር ጥቃቶችን በህዝቡ ላይ በተለያዩ ጊዜያትና ቦታ የፈጸመ ሲሆን ዋና ዋናዎቹን በጥቂቱ እንመልከት፡-
- በወልቃሪት ጠገዴ ህዝቦች ላይ የተፈጸሙት የዘር ማጥፋት ዘመቻና የዚህንም ህዝብ ህልዉና በማጥፋት የራሱን መስፋፋት ከግብ ለማድረስ በህዝቡና በትውልዱ ላይ የተወሰደዉ የዘር ማጥፋት ተግባር እጅግ ዘግናኝ ተግባር የሆነና ጉዳዩ ገና መፍትሄ ያልተገኘለት ይልቁንም ገና ብዙ ቀውስን ሊፈጥር የሚችል ተግባር መሆኑም እራሱም ህወሃትም ያልተረዳው ግፍ ነዉ።ለበለጠ መረጃ http://ethio-wolqait.blogspot.de/. እና ሌሎችንም ተያያዥ ጽሁፎችን ይመልከቱ::
- በጋምቤላ በአኟኮች ላይ እ.ኤ.አ በዲሴምበር 13/2003 በጋምቤላ ከተማ የተደረገው የጅምላ ግድያ/Gonocide/ 424 ስዎችን በጅምላ በመግደል ታሪክ የማይረሳው የመንግስት ሽብር የተፈጸመ ሲሆን ብዙዎችም አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ተደርገዋል፣የአኟክ ሴቶች በወታደሮች ተደፍረዋል፣በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ወድመዋል፣የሚመገቡአቸው ምግቦችና የቤት እንሥሣቶችም እንዲወድሙ ተደርጓል።ይህ ሽብር ህወሓት በዚህ ክልል ውስጥ ለመስፋፋት ብሎ በህዝብ ላይ የተፈጸመ ግልጽ ሽብር ነው።ለዚሀም ድምዳሜ ላይ ያደረሰኝ ጉዳይ አብዛኛው የጋምቤላ ሰፋፊ መሬቶች በህወሃቶችና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ቁጥጥር ውስጥ መሆኑና እየተበዘበዘ መሆኑ ነው። በዚሁ ክልል ስለተፈጸመው ጅምላ ግድያና ህወሓት በዚሁ ክልል ስለሚፈጽማቸው የሃብት ብዝበዛ ለማውቅ ከፈለጉ የአኟክ የፍትህ ካውንስልን ዌብ ሳይት “http://www.anuakjustice.org/” ይመልከቱ።
- የሲዳማ ህዝቦች ሰላማዊ ጥያቄዎች በማንሳታቸው እና ህገ-መንግስታዊ መብቶቻቸውን ተግባራዊ ለማድረግ በመነሳታቸው ብቻ ከ 11 ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ ሜይ 24/ 2002 በአዋሳና አካባቢው ከ100 በላይ የሲዳማ ተወላጆችን በጅምላ በመግደልና ከ250-300 የሚሆኑትን በማቁሰል የተፈጸመው ዘግናኝ ሽብር ለታሪክ የማይረሳና የህወሓትን ግልጽ ሽብርተኝነት የሚያሳይ ሌላው ሀቅ ነው። ለበለጠ መረጃ http://sidamaliberation-front.org/ ይመልከቱ።
- በኢትዮጵያ አቆጣጥር ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኃላ በህዝብ ምርጫ የተሸነፈው ህወሓት/ኢህአዴግ ከህጻናት እስከ አዋቂ በጠራራ ጸሃይ በመቶዎች የሚቆጠሩትን ንጹሃን ግንባር ግንባራቸውን ብሎ በመግደል፣ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩትን አካለ ስንኩል በማድረግ፣በሽዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ በእሥር ቤቶች ውስጥ በማሰርና በማሰቃየት በኢትዮጵያ ህዝብና በዓለም ማህበረሰብ ፊት ግልጽ ሽብር የፈጸመ ቡድን መሆኑ የቅርብ ግዜ እውነታዎች ናቸው።
- በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ውስጥ በተወሰኑ በኦሮሞና በትግራይ ተማሪዎች መካከል በተደረግ ግጭት ግልጽ በሆነ መድሎና በማን አለብኝነት በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ከትምህርት ገበታቸው እንዲባረሩ ተወስኖ የነበረውን ውሳኔ ሰንመለከት እጅግ የሚያሳዝን ተግባር መሆኑና ድርጊቱ በአዲሱ ትውልድም ላይ የተቃጣ ሽብር ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያውያን በአገራችን በግልጽ መድሎ ውስጥ መሆናችንን ያሳያል።
- በኦሮሞ ህዝቦች ውስጥ የሚደረጉትን ትግሎች በሙሉ ከኦነግ ጋር በማያያዝ የኦሮሞ ህዝቦች በእስር ቤቶች ውስጥ እንዲማቅቁ መደረጉና አብዛኛው የአገሪቷ እስር ቤቶች ኦሮሚኛ የሚነገርባቸው እስከ መሆን መድረሳቸውን ከፖለቲከኞች አፍ መስማታችን እጅግ ከባድ ችግሮች በህዝቡ ላይ መኖራቸውንና በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሽብር እየተፈጸመ መሆኑን ያሳየናል።
- ህወሓት/ኢህአዴግ ሊፈጽመው የሚፈልገውን ሽብር በሽብር ህግ ድጋፍ እንዲደረግለት በህዝቡ ሳይሆን ለህወሓት የብዝበዛና የጭቆና መሳሪያነት በሚያገለግለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካኝነት አጽድቆ የሽብር ጥቃቱን እየፈጸመ ሲሆን በዚህ ጥቃትም ልዩ ልዩ አካላት የህወሓት የሽብር ጥቃት ስለባዎች ሆነዋል። በዚህም ውስጥ ጋዜጠኞች፣የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ የነጻነት ተማጋቾችና ልዩ ልዩ ግለሰቦች በሙሉ በዚሁ ጥቃት ውስጥ ወድቀዋል።
ከጋዜጠኞች መካከልም፡- ርዮት አለሙ፣ውብሸት ታዮ፣እስክንድር ነጋ፣ በተለያዩ ጊዜያት በፍርድ ቤት የሚመላለሰው ተመስገን ደሳልኝ እና ሌሎችም ከሃገር ውስጥ ፣ የስውዲን ጋዜጠኞች ጀሃን ፕርሰን/Johan person/ እና ማርቲን ሽብዮ/Martin Schibbye/ ከውጭ ይገኙባቸዋል።
ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላትም ውስጥ አንዱዓለም አራጌ ፣በቀለ ገርባ፣ኦርባና ሌሊሳና ሌሎች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በእሥር ቤቶች የሚማቅቁ ይጠቀሳሉ።
በተለይም ተዋቂ ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት ሰበብ አስሮ ሌሎች በአገራቸው በሚደረገው የነጻነት እንቅስቃሴ ላይ ምንም እንዳይናገሩ በማድረግ በነጻው ሚድያ ላይ ግልጽ የመንግስት ሽብር እንዳለ ሁሉም የሚያውቀውና እ. ኤ. አ ከ2007-2012 ድረስ ብቻ 49 የሚሆኑ ጋዜጠኞች በዚህ የህወሓት የሽብርተኝነትን ድርጊት በመፍራትና በግዳጅ ከሃገር መሰደዳቸውን ለጋዜጠኞች መብት የሚከራከረው ሲፒጄ/Commitee to Prtect Jornalists / በተለያዩ ጊዜያት ገልጸዋል፤በዚህም ምክንያት አገራችን ለጋዜጠኞች ህይወት አደገኛ አገር መሆናንና ከሱማሊያና ከኢራቅ ቀጥላ ለጋዜጠኞች የስደት ምክንያት በመሆን ታዋቂ ሆናለች ።
- በተለያዩ ጊዜያት በአፋር፣በሶማሊያና በጋምቤላ ክልሎች የህወሓት የመሬት መስፋፋትን ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የእነዚህን ህዝቦች የመሬት ሃብት ተጠቃሚነትን በመንጠቅ የህወሓት የብዝበዛ ቡድን አባላትና ጀሌዎቻቸው በህዝቦች ህይወት ላይ ተደጋጋሚ አደጋ በመፍጠርና በማፈናቀል አስከፊ ተግባር እየተፈጸመ ያለው በዚሁ ተስፋፊ የህወሓት/ኢህአዴግ ቡድን አሸባሪነት መሆኑም ሊሰመርበት ይገባል።
- በአማራ ተወላጆች ላይ ከደቡብ ከጉራፈርዳ፣ከቤንሻንጉል ጉምዝና ከሌሎችም ክልሎች በማፈናቀል፣መሬት በመንጠቅና በማሳደድ የዘር ማጽዳትን ተግባርን የሚያቅደው እራሱ ህወሓት መሆኑንና ከትግሉ ጀምሮ ይዞት የመጣው በማኔፌስቶውም ላይ በግልጽ ያስቀመጠውና እየተገበረ ያለው ተግባር ነዉ፤በዚህም ብዙ ጭቁን አማሮች የሚከላከልላቸው አጥተው የዚሁ የሽብር ጥቃት ሰለባ ሆነው ተቀምጠዋል።
- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በተለይም ከአንድ ዓመት ወዲህ በሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የሚፈጸመው የአደባባይ ላይ ድብድባ፣እስራትና ግድያዎች የህወሓት/ኢህአዴግ ሌላው ህዝብን የማሽበር ተግባሩ አካል እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል።
- በሃገር ውስጥ ባሉ ሰላማዊ ትግልን አማራጭ ትግል በማድረግና ህግን ተከትለው የሚታገሉትን የተቀዋሚ ፓርቲዎች አመራርና አባላት ላይም እየደረሰ ያለው ወከባና እንግልት ሰላማዊ ትግሉን እጅግ መራራ አድርጎታል፤ለዚህም ማስረጃ ይሆን ዘንድ በቅርቡ በሰማያዊ ፓርቲ ላይና በአንድነት ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ ህወሓት/ኢህአዴግ በፍጹም ማን አለብኝነት መቀጠሉንና ሰላማዊ ትግሎችንም ጭምር ለማጥፋት መቀጠሉ ይህ ሥርዓት በግልጽ በመንግስታዊ ሽብርተኝነት መቀጠሉን ግልጽ አድርጎልናል።
- 3. ህወሓት/ኢህአዴግ የሽብር ጥቃትን ለምን ይፈጽማል ?
ህወሓት/ኢህአዴግ በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰና ለእውነተኛ ዲሞክራሲና ፍትህ የቆመ ቡድን ሳይሆን በጥቂቶች ጠባብና ዘረኞች የተዋቀረ የማፍያ ቡድን መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያውቃል። የህወሓት ዓላማና ግብ በእርግጥም የነጻነትና የዲሞክራሲ ሳይሆን ጥቂቶች የአገሪቷን ወታደራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መዋቅሮችን በሙሉ ተቆጣጥረው ለዓመታት የተመኙትን የኢኮኖሚና የመሬት መስፋፋትን ዕውን ለማድረግ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አካልና፤በኢትዮጵያ ህዝብ ደምና ሀብት ለመክበር በሚቋምጡና በሚተገብሩ የህወሓት መሪዎችና ጀሌዎቻቸው አማካኝነት ይህንን ስውር ተግባር ለማስፈጸም የሚፈጸም የሽብር ተግባር ነው።
የዚህን እውነታዎች ለማወቅ ለሚፈልጉ ሁሉ አሁን በተጨባጭ የሚታየውን እውነታን ማየት ይቻላል።አጠቃላይ የኢኮኖሚው ክፍል በሙሉ ማለት ይቻላል በህወሓት ቁጥጥር ስር መውደቁና፤ የህወሓት የንግድ ድርጅቶች ሙሉውን የአገሪቷን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ለመቆጣጠር ሩጫ ላይ መሆናቸውና፤ እነዚህን ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ የመንግስት መዋቅሮች በእነዚሁ በህወሓት ሰዎች እጅ ቁጥጥር ስር መዉደቁ ግልጽ ማስረጃ ሆኖ ይገኛል፤ለምሳሌ ኢፈርት በሁሉም የአገሪቷ የንግድ ሴክተሮች ተጽዕኖን እንዲፈጥርና ሌሎችን ከገበያ ውጭ እንዲሆኑ የሚያደርገው እንቅስቃሴና በብሄራዊ ባንክ፣በግሙሩክ፣በአየር መንገድ፣በአገር ዉስጥ ገቢ መስሪያ ቤቶች፣በወታደራዊ ተቋማት፣በፖሊስና ደህንነት መስሪያ ቤቶች ተሰግስገው አገሪቷን ለመበዝበዝ የሚያስችሉአቸውን ሁኔታዎች በቁጥጥር ውስጥ ያስገቡ በመሆኑ፤ ይህንን ብዝበዛ የሚቃወምም ሆነ የሚነካ ሃይል በሙሉ የጥቅሞቹ ተቀናቃኝ አድርጎ በመቁጠሩና፤ ይህንን የህወሓትን ቡድን ስውር ዓላማን ለማስፈጸመ መንግስታዊ ሽብርን አንዱ አማራጭ አድርገው የያዙት መሆኑ፤ ህወሓትን የሚያሳስበው የፍትህና የዲሞክራሲ ጉዳይ ሳይሆን ይህንን የብዝበዛ መዋቅራቸውን የሚነካ ሃይል ሁሉ በአሸባሪነት በመፈረጅ የብዝበዛ ተግባራቸውን ከግብ ለማድረስ የመንግስት ሽብርተኝነትን እያቀጣጠሉ መሆኑ ነው።
- የህወሓት/ ኢህአዴግ የሽብር ተግባራት በህዝቡ ላይ የፈጠራቸው ችግሮች ምንድን ናቸው ?
የህወሓት/ኢህአዴግ ቡድን በሚፈጥራቸው የሽብር ተግባራት የተነሱ በህዝቡና በአገሪቷ ላይ የፈጠሩት ተጽዕኖዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
- በህዝቡ ላይ ፍርሃት መንገሱና በብዙዎች ላይ የስለልቦናም ችግር ያስከተለ መሆኑ፤
- ስደትና በስደትም የተነሳ ወጣቶች በጎረቤት አገራትና በየበረሃው ለሞት መዳረጋቸው፤
- እስራትና ሞት፤
- ግልጽ የህወሓትንና የጥቅም ተጋሪዎቻቸውን ልዩ ልዩ ብዝበዛዎችን ከፍርሃት የተነሳ በዝምታ ማየት፤
- በህዝቡ ላይ ሰብዓዊ ጥሰቶች በብዛት እየተፈሰሙ መምጣታቸው፤
- የመሬትና የተፈጥሮ ሃብቶች ብዝበዛ መቀጠሉ፤
- የሃገሪቷ ሃብቶች በጥቂቶች እጅ እየወደቁ መምጣታቸው፤
- ህዝቡ መብቶቹን እንዳይጠይቅ መገደዱ፤
- የስራና የትምህርት እድሎች መድሎዎች መፈጠራቸው ይህንንም መድሎ በዝምታ ለመቀበል መገደድ፤
- የስራና የመኖሪያ ቦታዎች ችግር መፈጠሩ፤
- የሙስና መስፋፋት መባባሱ፤
- የህግ የበላይነት ቀርቶ የህግ መድሎ መፈጠሩ፤
- ግልጽ የንግድና የስራ ቦታዎች መድሎ መኖሩ፤
- ህዝቡ ከተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እንዳይቀላቀልና መብቶቹን እንዳያስከብር መሆኑ፤
- በንሮ ውድነት መማቀቅ፤
- ህዝቡ በሃገሩ ላይ የበይ ተመልካች መሆኑ፤
- የንብረት መነጠቅ ችግሮች መደራረብና ሌሎችም:-
- 5. ከፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ከስቪክ ማህበራትና ከኢትዮጵያ ህዝብ አጠቃላይ ምን ይጠበቃል ?
ህወሓት/ኢህአዴግና የጥቅም ተጋሪዎቹ ይዘው የተነሱትን የኢኮኖሚ፣የንግድና የመሬት መስፋፋት ከግብ ለማድረስ በሚያደርጉት የብዝበዛና የዝርፊያ እንቅስያሴ ዉስጥ ማናቸውንም ሰላማዊና ህጋዊ ትግሎች ሳይቀሩ በሽብርተኝነት ሰበብ መግደል፣ማሰር፣ማሳደድ፣ማሸማቀቅና ማስፈራራት የህወሓት የየዕለት ተግባር ሆኗል። ይሁንና ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ እራሳችን ለመታገል ካልቆረጥንና መሰዋዕትነትን ለመክፈል ካልተነሳን ችግሩ ማብቂያ እንደማይኖረው ሊሰመርበት ይገባል።
በሃገራችን ታሪክ ህዝብንና አገርን በማሽበር በኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን በዓለም የሽብርተኝነት መዛግብት ውስጥ የተመዘገበውን ይህንን ሽብርተኛን የህወሓትን ቡድን ከድርጊታቸው እንዲያቆሙ ማድረግ ወይም እራስን የመከላከል ተፈጥሮአዊና ህጋዊ መብቶችን ተጠቅሞ ወደ መከላከል መግባት፣ የህወሓት ፍጹም አምባገነንነት እንዲያበቃና የአገራችንና የህዝቦቻ ነጻነት እንዲረጋግጥ ማድረግ ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም።
በእርግጥም ህዝብን በማሸበር ህወሓት ለዓመታት በህዝቦች መብቶችና ህይወት ላይ የሚፈጽማቸው የሽብር ጥቃቶች እንዲያበቁ አስፈላጊዉ ሁሉ ባለመደረጉ ዛሬ ህዝባችን በመከራ ውስጥ መሆኑ ለሁሉም የተሰወረ አይደለም።ትግሉ አሁን የመንግስት ስልጣን ይዘው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ግፍን ከሚፈጽሙ የመንግስት ሽብርተኞች ጋር እንጂ ከህገ መንግስት ጋር አይደለም፤ህግ በትክክል እየተጣሰ ያለው በእነዚህ እኩይ ተግባርን በሚፈጽሙ የህወሓት/ኢህአዴግ በዝባዥ ሥርዓትና የሥርዓቱ መሪዎች ነው፤ ይህንን አስከፊ ሥርዓት ለማስወገድ መነሳት፣ መታገልና አስፈላጊውን መስዋዕትነት ከፍሎ በድል ማጠናቅቀ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።
በሃገራችን የበይ ተመልካች ሆነን መቀጠል ያብቃ፤ጥቂቶች ብዙሃኑን የሚዘርፉበትና የሚጨቁንበት ሊያበቃ ይገባል፤የተወለድንባቸውና ያደግንባቸው ቦታዎች የራሳችን እስር ቤቶች ሊሆኑ አይገባም፤ወታደሩ፣ፖሊሱና የደህንነት ሀይሉ ኢትዮጵያውያንን የሚወክል መሆን ይኖርበታል እንጂ ለጥቂት ዘረኞች ቅጥረኛ ሆኖ የሚያገለገለበት ጊዜ ሊያበቃ ይገባል።
ህወሓት/ኢህአዴግን መታገልና ማስወገድ የተቀዋሚ ፓርቲዎች፣የስቪክ ማህበራት፣ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችና ለእውነት የቆሙ ጋዜጠኞች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ሁሉ ትግል ሊሆን ይገባል።
ለዚህም ይረዳ ዘንድ የሚከተሉት ሁኔታዎችን ማየት ይኖርብናል ብዮ አስባለሁ፡-
- ነጻነቱን የተነጠቀዉ ሁሉም መሆኑና ነጻነቱን ማስመለስ የሁሉም መሆኑ፤ ስለሆነም ትግሉም የሁሉንም ተሳትፎና መስዋዕትነትን የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም በመረጠዉ የትግል መንገድ ወደ ትግሉ መቀላቀል ይጠበቅበታል።ድልን የሚጠብቅ ሁሉ የትግሉም አካል ሊሆን ይገባል፤
- የህዝቦች መቀራረብና በጋራ ጠላት ላይ የጋራ ትግልን ማፋጠን ለነገ የማይባል መሆኑ፤
- የተማሩና የህዝባቸው ሮሮ የሚሰማቸው ሁሉ ዛሬ ህዝቡ የሚፈልጋቸው በመሆኑ ያስተማራቸውን ህዝብ ለማገልግል የሚቆርጡበት ጊዜ መሆኑ፤
- የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነቶችን በማጥበብና ለትዉልዱ በማሰብ በጋራ ጠላት ላይ በጋራ መነሳት መቻልና ለህዝቡ የትግል ፍላጎት መዳረሻ ሊሆኑና ሊያታግሉ ይገባል፤
- የስቪክ ማህበራትም ያላቸዉን ትስስር በማጠናከር ትግሉን ማገዝ ይኖርባቸዋል፤
- አዲሱ ትውልድም ለራሱ ሲል ወደ ትግሉ መቀላቀል ይኖርብታል፤
- በውጭ የሚገኙም የዚህን ዘረኛና አሸባሪ መንግስታዊ ቡድን ተግባር በማጋለጥና በዲፕሎማሲው ዘርፍ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ በማድረግ ዕርቃኑን ማስቀረትና አገራትና መሪዎቻቸው ከተጨቆነው ህዝብ ጋር እንዲወግኑ ጥረት ማድረግ፤
- በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል፣ በስቪክ ማህበራት መካከል፣ በሰብዓዊ ድርጅቶች መካከል በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉት የእርስ በእርስ ግንኙነቱን በአህጉራት መካከልና በዓለም አቀፍ ደረጃ በማጠናከር የህወሓትን የመከፋፈል አቅምን መስበር መቻል፤
- በውጭ ያሉ ምሁራንም የተለያዩ ሙያዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ማበረታታትና ተነሳሽነት መፍጠር፤
- የህወሓት የንግድ ድርጅቶች ምርቶችን ባለመግዛትና የንግድ አገልግሎቶቹን ባለመጠቀም ጭምር የህወሓትን የብዝበዛ መስመሮች መዝጋትና
- ልዩ ልዩ ትግሎችን በሃገር ውስጥና በውጭ ማቀጣጠልና ተግባራዊ ማድረግ ግድ ይላል።
እነዚህንና ሌሎች ተግባራትን በመፈጸም ይህንን ሽብርተኛ ቡድን ከሃገራችንና ከህዝባችን ላይ ማንሳት ይጠበቅብናል።
- 6. ማጠቃለያ
ከላይ ከተዘረዘሩትም ሆኑ ሌሎች በዚህ ጽሑፍ ካልተጠቀሱ የህወሓት/ኢህአዴግ ተግባራት ስንነሳ ግዜው መሰባሰባችንን ይጠይቃል። ከራሳችን ይልቅ ለደሃው ህዝባችን ልናስብና የመከራውን ግዜ ልናሳጥር የሚገባን ሰዓት ላይ ነው ያለነው፤ ስልሆነም አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅበናል።
ህወሓት/ኢህአዴግ በሰላማዊ ትግል ላይ ባሉ የሰላማዊ ትግል አራማጅ ፓርቲዎች ላይም ሳይቀር መንግስታዊ ሽብርን ቀጥሏል። ይህንን የፓርቲዎችን ትግል ማገዝና ችግራቸውን መጋራት ለነገ የሚባል ሳይሆን ዛሬ የሚተገበር ተግባር ነዉ። በሩቁ ሆኖ ፓርቲዎቹ ብቻቸውን እንዲታገሉ መፈልግ ትግሉን ይጎዳዋል እንጂ አይጠቅመዉም፤ ስለሆነም ትግሎችን መደገፍና ከውጤት ላይ ማድረስ የሁሉም ተጠቂ ሁሉ ሃላፊነት ነው ።
በመጨረሻም አንድ ነገርን ሳልል አላልፍም ይኽውም ትግሎቻቸን ግቦቻቸውን እውን የሚያደርጉ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችንና አስተሳሰቦችንና ፖሊሲዎቻቸውን ማየት ይኖርባቸዋል ፤ እነዚህም ቢሆኑ የብዙሃኑን ተሳትፎ ይጠይቃሉ ። ይኽንን ያልኩባቸው ምክንያቶችን ለመመልከት ያህል በዓለማችን እንደሚታየው አብዛኞች ትግሎች ግባቸውን እንዲስቱ የሚደረጉበት አጋጣሚዎች ተፈጥረዋል፤ ትግሎች በልዩ ልዩ ምክንያት በድሎቹ ዋዜማና አስቀድሞ የራሳቸው ስውር ግብ ባላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች እጅ በመውደቃቸው ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለባቸው ትግሎች ግቦቻቸውን እየሳቱ ሌሎች ትግሎችን የሚጠይቁበት ሁኔታዎች ታይተዋል።ለምሳሌም በሃገራችን የተደረጉት የተማሪዎች ትግል በደርግ እጅ መውደቅና የኢህአዴግ ትግል በጥቂቶች የህወሓቶች እጅ መውደቁ፣አሁን በአረቡ ዓለም የሚደረጉ ትግሎችንም ስንመለከት ደግሞ እንዲሁ ብዙ መስዋዕትነት ከተከፈለባቸው በኃላ ባልታሰቡና ወይም ያልተጠበቀ ግብ ባላቸው እጅ እየወደቁ ሌላ ተጨማሪ መከራን ሲፈጥሩ ተስተውላል፤ስልሆነም ትግሎች ግቦቻቸውን የሚተገብሩ ሰዎችንና ቡድኖችን ማንነት ማወቅ ይኖርባቸዋል ለዚህም የብዙሃኑ ተሳትፎዎች ወሳኝነት ይኖረቸዋል።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ።
aberashiferaw.wordpress.com