Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all 13695 articles
Browse latest View live

የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ መጽሐፍ ጻፉ

$
0
0

ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)
fikresilase wegderese new book cover ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት በታኅሣሥ 16, 2006 ዓ/ም (Dec. 25, 2013) የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስን ‘እኛና አብዮቱ’ የሚል መጽሃፍ ለገበያ እንደሚያበቃ አስታወቀ። ሻምበል ፍቅረሥላሴ እንደ ደርግ አባልነታቸው በጋራ ያመኑበትን፣ የተማከሩትን፣ የወሰኑትን፣ የሰሩትን፣ የገጠማቸውንና በቅርብ በዓይን ምስክርነት ያዩትን ተንትነው በ‘እኛና አብዮቱ’ ያስነብቡናል። የራሳቸውን ዕይታ ያካፍሉናል።

ልጅ ሆነን አንድ አባባል እሰማ ነበር።”አበላል እንደ ደርግ አባል። አለባበስ እንደ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ!” – የሚል። በተለይ በኔ ትውልድ ያለን ሰዎች፣ ከዚህ ውጭ ስለኝህ ሰው የምናውቀው ብዙም ነገር አልነበረም። ግና እኝህ ሰው በልባቸው መክሊት ለአመታት የቋጠሩትን መረጃ ጀባ ሲሉን፤”… አጻጻፍም እንደ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ” የሚያሰኝ ሆኖ አገኘሁት።

ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ለአስራ አምስት ዓመታት አብዮቱን ሲመሩ ቆይተው ወደ መጨረሻው ከሥልጣን በጡረታ ስም እንዲሰናበቱ ተደርገዋል። ደርግን በጣለው በወያኔ መንግሥትም ለ፳ ዓመታት ታስረው፣ የሞት ፍርድ የተበየነባቸውና በመጨረሻ ፍርዱ ወደ ዕድሜ ልክ ተዛውሮላቸው ከእሥር ቤት በአመክሮ የወጡ ግለሰብ ናቸው።

ጸሃፊው በድራማ መልክ በመጽሃፋቸው ካሰፈሩዋቸው እውነታዎችና ግለ-ሂሶች ውስጥ አንዳንዶቹን ለአንባቢያን ማካፈሉ አይከፋም። ደርጎች መፈንቅለ መንግስት አድርገው ሲያበቁ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘንድ ቀርበው ከንጉሱ የገጠማቸውን አስገራሚ ምላሽ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ በመጽሃፋቸው እንዲህ ሲሉ አስፍረዋል።

የፖለቲካ እሥረኞች በሙሉ እንዲፊቱ የሚለው ጥያቄ እንደተነበበ ንጉሡ ጣልቃ ገብተው “ለመሆኑ የፖለቲካ እሥረኞቹ እነማን ናቸው?” የሚል ጥያቄ አቀረቡ። “በእርግጥ የምናውቃቸው የፖለቲካ እሥረኞች ባይኖሩም ማንኛውም የፖለቲካ እሥረኛ እንዲፈታ ነው የምንጠይቀው” አሉ ሻለቃ ተስፋዬ ገብረኪዳን። ንጉሡ ራሳቸውን ነቅነቅ አድርገው ጽሑፉን የሚያነበውን የደርግ አባል እየተመለከቱ “አልገባችሁም!” ብለው ዝም አሉ። በእርግጥም አልገባንም። ተማሪዎችና የተለየ ዓላማ የነበራቸው የተማሩ ሰዎች የሰነዘሩትን መፈክር ብቻ ነበር ይዘን ንጉሡ ፊት የቀረብነው። በፖለቲካ እሥረኝነት ስም በከፍተኛ ደረጃ ለጣሊያን ወራሪ መንግሥት በባንዳነት አድረው አገራችንን የወጉ፣ ለቅኝ ተገዥነትም የዳረጉትን እንደ ኃይለሥላሴ ጉግሳ ያሉ ወንጀለኞች የፖለቲካ እሥረኞች ተብለው ከግዞትና ከእሥር ቤት አስወጥተን እንደ ጀግና ራሳቸውን እንዲቆጥሩ አደረግናቸው።

የነ ጄነራል ተፈሪ በንቲ ጉዳይን አስመልክቶ የሰፈረው ታሪክ ደግሞ እንዲህ ይነበባል።

“በሊቀመንበርነት ስብሰባውን የሚመሩት ጄነራል ተፈሪ ‘የቋሚ ኮሚቴው’በዛሬው ቀን የሚወያይበትን ጉዳይ አስመልክቶ የመቶ አለቃ ዓለማየሁ የደርጉ ዋና ፀሐፊ ይገልጽልናል’ ብለው ስብሰባው መጀመሩን ካበሰሩ በኋላ ዓለማየሁ በአጀንዳው ላይ አጭር ገለጣ ማድረግ ሲጀምር ስልክ ተደወለ። ስልኩ ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ አጠገብ ስለነበር ወዲያው ቅጭል እንዳለ መነጋገሪያውን በማንሳት ሃሎ አሉ። ከሌላው ጫፍ ማን እንደደወለ አላወቀንም። በኋላ እንደታወቀው ሌ/ኮሎኔል ዳንኤል ነበር የደወለው። ምን እንደተነጋገሩ አልተሰማም። ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ ብቻ “እሺ እሺ” ብለው ስልኩን ዘጉት። ስልኩን እንደዘጉ “ይቅርታ ስልኩ የተደወለው ከጎንደር ነው። ጎንደር ውስጥ ችግር አለ። እናንተ ቀጥሉ” ብለው ከጀርባቸው ባለው በር በኩል ውልቅ አሉ። በዚህን ጊዜ ዓለማየሁና ሞገስ ጥርጣሬ የገባቸው መሰለ። ዓለማየሁ ንግግሩን አቋርጦ በመስኮት በኩል ውጭ ውጭዉን መመልከት ጀመረ። ዓይኖቹ አላርፍ አሉ። ግራና ቀኝ ይመለከታል። አጠገቡ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በጥርጣሬ ተመለከተ። ሻምበል ሞገስም በር በሩን ይመለከታል። ከአሁን አሁን አንድ ችግር ይከሰታል የሚል ፍርሃት ያደረበት ይመስላል። ሁሉም የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች ፈርተዋል። እንደፈሩት አልቀረም ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ ከወጡ ሁለት ደቂቃ እንኳን አልሞላም ከበስተጀርባ ባለው ኮሪደር የወታደሮችን እርምጃ ሰማን። ወታደሮች ሲንቀሳቀሱ በፊት ለፊታችን ባሉት መስኮቶች በኩል ተመለከትን። በዚህን ጊዜ ፍስሐ ደስታ “ተከብበናል” አለ። ወዲያው ሁለቱም በሮች በኃይል ተበረገዱ። ሁላችንም ደነገጥን፣ ቀልባችን ተገፈፈ፣ እጢአችንም የወደቀ መሰለን። ድርቅ ብለን በተቀመጥንበት ቀረን።…

ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ሰለ ልጅ ሚካኤልን አስተዋይነት ሲያስታውሱ እንዲህ የሚል ግለሂስም ያስነብቡናል።
እኛ በችኮላ ውሳኔ መስጠታችን፣ ሕዝቡን በደንብ አለማወቃችን፣ ሰፊ የሕዝብ አመራር ልምድ ማጣታችን፣ የአገርና የውጭውን ፖለቲካ ውስብሰባዊ ግንኙነት አለመገንዘባችን፣ የመንግሥትን አሠራር ደንብና ሥርዓት አለመረዳታችን፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጥመርታዊ ግንኙነትን መመልከት አለመቻላችን፣ የተለያየ ገንቢም ሆነ አፍራሽ ተልዕኮ ያላቸው ኃይሎች ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩብ ያለማጤናችን፣ በየዋህነትና በቅንነት ብቻ እንደምንሠራ በመገንዘባቸው ሊሆን ይችላል ልጅ ሚካኤል ከእኛ ጋር መቆየት የሚችሉት ለአጭር ጊዜ ብቻ እንደሚሆን የጠቆሙት…

በወቅቱ ስለ ህዝቡ የእርስ በርስ መጨካከንና መወነጃጀል ባሰፈሩት ክፍል ውስጥ እንዲህ የሚል ታሪክ እናገኛለን።

..የሥራ ዕድገት የተከለከለ፣ በሌብነትም ሆነ በስካር ወይም በሌላ ጥፋት የተቀጣ፣ በግል ጉዳይም ሆነ በመንግሥት ሥራ ከአለቃው ጋር የተጣላ፣ በአጋጣሚው ተጠቅሞ አዲስ ሹመት ወይንም ዕድገት ለማግኘት የሚፈልግ ሁሉ ጠቋሚ፣ ወንጃይ፣ ከሳሽ፣ ተበዳይ ነው።

የተወሰነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ሌላውን ለመጉዳት ብለው “ኢትዮጵያ ትቅደምን ይቃወማል፣ ከታሠሩት ባለሥልጣናት ወይም ሚኒስትሮች የቅርብ ዝምድና አለው። ስለሆነም ሥራ ይበድላል፣ ሠራተኛውን ያጉላላል፣ ውሳኔ አይሰጥም” በማለት አለቆቻቸውን የሚከሱ፣ የሚወነጅሉ በርካታ ናቸው። ለደርግ አባላት ቤታቸው ድረስ በመሄድ በማስረጃ የተደገፈ ቢሆንም ባይሆንም ተቆርቋሪ በመምሰል የክስ ማመልከቻ የሚያቀርቡም ነበሩ። እንታሠራለን ብለው በፍርሃት የተደበቁ ባለሥልጣናትን የቅርብ ዘመዶቻቸው ወይም አሽከሮቻቸው ወይም ጎረቤቶቻቸው ደርግ ጽሕፈት ቤት ድረስ በመምጣት ያጋልጧቸው ነበር። የመሥሪያ ቤቶችን ሰነዶች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ወይም ሰነዱን እንዳለ ከፋይሉ አውጥተው በማቅረብ “በመንግሥት ንብረት፣ ሀብት ወይንም ገንዘብ ላይ አላግባብ ተወስኗል” ብለው ጥቆማና መረጃ የሚያቀርቡም ነበሩ። ሠራተኞች አሠሪዎቻቸውን ይከሳሉ፣ ይወነጅላሉ። ገበሬዎች ለዘመናት በደል አደረሱብን የሚሏቸውን የአካባቢ ባለሥልጣናት ይወነጅላሉ። ውንጀላው በርካታ ነው።

አሽከሮች፣ ዘበኞች፣ ገረዶች… መረጃ ይሰጣሉ፣ ይጠቁማሉ። የተደበቀ የጦር መሣሪያ፣ የተደበቀ ገንዘብ፣ ወደሌላ ቦታ የተወሰደ ወይም የሸሸ ሀብት እንዳለም የሚጠቁሙን እነሱ ናቸው። በአንድ ቦታ በርከት ያሉ ሰዎች ተሰብስበው ምሽት ከአሳላፉ “ሲያድሙ ነበር” ብለው ከነስም ዝርዝራቸው መረጃውን ደርግ ጽሕፈት ቤት ድረስ ያመጣሉ። “እኛ እስከዛሬ የበይ ተመልካች ነበርን ዛሬ ዕድሜ ለእናንተ እንጀራ ሊወጣልን ነው! ከእናንተ ጎን ተሰልፈን አቆርቋዦቹን እንታገላለን! በማንኛውም ጊዜ ትዕዛዝ ብትሰጡን ለመፈጸም ዝግጁ ነን!” እያሉ ታማኝነታቸውንና ተባባሪነታቸውን የሚገልጡም ብዙዎች ነበሩ። በጣም የሚያስደንቀው አባቶቻቸውን፣ ልጆቻቸውን፣ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውን፣ ባሎቻቸውን፣ ሚስቶቻቸውን በመክሰስ፣ በመወንጀል፣ በማጋለጥ፣ በመጠቆም ብሎም በማሳሰር ጉዳት ያደረሱ በርካቶች መሆናቸው ነው።

እንግዲህ ስለ አዲሱ ‘እኛና አብዮቱ’ መጽሃፍ ይህንን ካልኩ ቀሪውን ለአንባቢ መተው ይበጃል። ሁሉም ሰው መጽሃፉን አንብቦ የራሱን ፍርድ ይስጥ።

ህይወት በሩጫ ትመሰላለች። የተፈጥሮ ህግጋት ነውና የሰው ልጅ እስትንፋሱ እስኪቋረጥ ይሮጣል። ከዚያም ሩጫውን ይጨርሳል። ሩጫውን ሳይጨርስ በልቡ ቋጥኝ የያዘውን እምቅ ቋጠሮ የሚተነፍስ ደግሞ እድለኛ ነው። በአንጻሩ ደግሞ በአእምሮው የቋጠረውን የእውቀት ምስጢር ሳያካፍል የሚያልፍ ሁሉ ያሳዝናል። ያለውን የወረወረ ንፉግ አይደለምና መንቀፍም ካለብን የሚወረውረውን ሳይሆን የማይወረውረውን ነው። መተቸት ካለብነም ሃሳቡን እንጂ ግለሰቡን ባይሆን ይመረጣል። በሃሳብ ላይ መወያየትና መተሻሸት ደግሞ አዋቂነት ነው።

በመጨረሻም የመጽሃፉ አርታኢ ኤልያስ ወንድሙ በመግቢያው ላይ ባሰፈረው መልእክት ጽሁፌን ልቋጭ።

የተማረ፣ ያወቀና ያደገ ትውልድና ዜጋ ምልክቱ የተጻፈን ማንበቡ፣ ያነበበውን ማብላላቱና ካነበበው ውስጥ ስንዴውን ከእንክርዳዱ መለየቱ ሲሆን፤ እራሱም አስተውሎና አገናዝቦ መጻፉ ደግሞ መማሩን ብቻ ሳይሆን መመራመሩንና ማወቁን የሚያሳይ ታላቅ ተግባር ነው። ለዚህም ደግሞ ግላዊ ነጻነት ያስፈልገዋልና ጫንቃው ላይ ያሉትን ግላዊና ታሪካዊ ቀንበሮች የሰበረ ነጻ ሰው መሆን ይጠበቅበታል። ትምህርትና ዕውቀት አስተዋይነትንና ጥልቀትን ከራስ በላይ ለትውልድ አሳቢነትን የሚያመለክት ታላቅ ኃላፊነት ነው። ለዚህም እንደ ትናንቱ ‘የተማረ ይግደለን’ ሳይሆን፤ የተማረ ያስተምረን፣ ያስተዳድረን ብሎም ይምራን በምንልበት ዘመን ከምናነብበው ውስጥ ያልተስማማንበትን በጨዋነት የመቃወም፣ የፈቀድነውን እንደ ስሜታችን የመደገፍና ተሳሳተ የምንለውን ለእርማት መጠቆም ግላዊ መብታችን ነው።…

* ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት ከዚህ በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምን፣ የቀድሞውን የህወሃት መሪ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን፣ የቀድሞውን የኢህአፓን አመራር አባል የዶ/ር መላኩ ገኝን፣ የቀድሞው ሚንስትር የአቶ ተካልኝ ገዳሙን መጽሃፍትና ከስልሳ በላይ የሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክና ጥናት ላይ ያተኮሩ መጽሃፍትን ማሳታሙ ይታወሳል። ‘እኛና አብዮቱ’ የሚለው ይህ አዲስ መጽሃፍ በwww.tsehaipublishers.com ድረገጽና በቀርቡ በየሱቁ አንደሚገኝ ከሎስ አንጀነሰ የደረሰን ዘገባ አስታውቋል። ሁላችንም ገዘተን እናንብብ።

መጽሃፉን አንብቤ እንደጨረስኩ በሂሳዊ ግምገማ እመለስበታለሁ።


የተሳካ ትርጉም ያለው – እንቅስቃሴ በሲቢሊቲ ሩም። ሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ 22.12.2013

sreate1ዕለቱ ሰንበት የተቀደሰ የተወደደ በፈጣሪው የተመረጠ ነበር። በዲኔግዲ አማክኝነት ሸገር የዘገበው የታልቅ ሚስጢር ዕውነተኛ ቀን ነበር 08.12.2013። በዚህ ሰዓት ነበር አባ መላ /አቶ ብርኃኑ ዳምጤ/ የሩሙ ባላቤት እጅግ በተመሰጠና ተቆርቆሪነቱ በአዬለ ሁኔታ በዕለቱ ስልኩን ፈልጎ ቃላቸውን በጀሯችን ያደረሰን። ስደት ደስታን የሚገፍ ሲሆን ያን ቀን ግን እውነተኛ ደስታ ነበር የተሰማኝ ከደስታም በላይ ሐሴት። በወቅቱ „ኢትዮጵያዊነት የታላቁን የሰላም አባት የኔልሰን ማንዴላ ህይወት የታደገ ታላቅ ሚስጢር …. አነጠረ።“ በሚል አንድ መታጥፍ ቢጤ ጽፌ ዘኃበሻም ታድጎኝ ለንባብ በቅቶ ነበር አመስግናለሁም።

አባ መላ ጥሩ ተናጋሪ ነው። ንግግር ሥነ – ጥበብ ነው። ጸጋም ነው። ተሰጥዖ። ሥጦታውም የማዳህኒዓለም ቢሆንም በክህሎት፤ በስልጠና ሥነ ደንቦችን በማጥናት ማሳደግ የሚቻል ጉልበታም ፊኖሚና ነው። ንግግር አድማጭን ወደ ተፈለገው አቅጣጫ የሚመራ የተዋጣለት መሪ ነው። ጥሩ ንግግር … በእጅ ያለ ወርቅ ነው። ጥሩ ንግግር ገዢ መሬት ላይ አለ አጥቂ ሰራዊት ነው። ይህን ለመልካም ተግባር ካዋሉት ውስጥ ዕውቅ የዓለማችን ሰዎች ውስጥ ኪንግ ማርቲን ሉተር፤ ፕሬዚዳንት አብርኃም ሊንከን፤ ማህተመ ጋንዲን ትናት፤ ዛሬ ደግሞ ፓኪስታናዊዋ የ16 ዓመቷ ታዳጊ ወጣት የታለቢና ጥቃት ሰለባ ሆና ከሞት የተረፈቸው ማላለ ለምሳሌነት ብናነሳ … ለጥፋት ደግሞ ጀርማናዊ አዶልፍ ሂትለር – ለናኒዝም፤ ሞሶሎኒ – ለፋሺዝም ተግባራዊነት ህዝብን በምዕላት ያንቀሳቀሱበት ታላቅ መሳሪያ ነው።

እኔ የአባ መላን የንግግር ጸጋ የማዬው ከዚህ አንጻር ነው። አባ መላ የተዋጣለት ተናጋሪነቱ ብቻ ሳይሆን የድምጹ ቃና ሳቢነት፤ እንዲሁም ሳቁ እራሱ ውበት አለው። ጥሩ ተናጋሪ ልብን ገዝቶ፤ ግርቶ ወደ ተፈለገው አቅጣጫ የመምራት ሞገዱ ሆነ አቅሙ መጠነ ሰፊ ነው። የአባ መላ የመታገስ አቅም፤ ኦዲዬንስ እንደ ባህሪው ለማስተናገድ ያለው ስልት፤ ከተረብ ጋር ይመቻል። የነፃነት ጉዞም ምልክት ነው – ለእኔ። የተመቸንና ያልተመቸን ኃሳብ አንዱ ለሌላው ቢጎረብጠውም አለስልሶ እውነትን አሸናፊ የማደረግ ኃይሉ ዓምድ ነው። አንድ ጊዜ እንደ ዋዛ „ከአባይ በፊት ሽሮ ይገደብ“ ሲል አዳምጥኩት። ይህ ቅኔ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ ወፈር ያለ ሽሮ ሰርቶ ለመብላት እንኳን ያልተቻለበት የተፋቀ ዘመን ስለመሆኑ እዬሳቀ ግን መንፈስን ሰርስሮ የገባ ሥነ – ቃላዊ አገላላጽ ነበር። ይህ አገላለጽ ህሊናን በአግባቡ የማዘጋጀት ስበቱ እጅግ ጠንካራና ረቂቅ ነው።

የታላቁ ሚስጢር ባላቤትና ባለውለታ የሆኑትን ትክሊላችን ካፒቴን ሻንበል ጉታ ዲንቃን ህይወት ከኢትዮጵያዊነት ሚስጢራዊ ተፈጥሮ ጋራ ከፍ ብሎ ዕውቅና እንዲያገኝ የነበረው ፍላጎትና ጉጉት ውስጡን ገልጦ ያሳይ ነበር ንግግሩ። ያን ቀን አባ መላ ዓዋጅም ዓወጆ ነበር  ከእንግዲህ አለ … “ልጅ የምትወልዱ ቤተሰቦች ልጆቻችሁን ጉታ ዲንቃ እያላችሁ ጥሩ“ አለ። የዛሬ ሳምንት ደግሞ „ ኢትዮጵያዊነት መሪ አገኘ ጉታ ዲንቃን“ አለን።

የካፒቴን ጉታ ዲንቃ ህልም ደቡብ አፍሪካ ሄዶ የምህረት፤ የትግል፤ የጽናት፤ የይበቃኛል አባት ከሆኑት ከኔልሰን ማንዴላ ቀብር ላይ መገኘት ስለነበር። የማይቻለውን ቻለ። በአራት ቀን ውስጥ ከኢትዮጵውያን የሚሰበሰበወን ገንዘብ ሳይጠብቅ የራሱን ገንዘብ የትኬት ምግዣ ልኮ። የኢሳትን ቲም፤ አርቲስት ታማኝ በዬነን፤ አቶ ነዓምን ዘለቀን በመያዝ በንዑድ ቅንነት ተግባሩን ጀመረ። በሩሙ ታዳሚዎች በመተማመን። ያው በፍቅር ስለሚያስተናግድ ለፍቅሩ የሚቻለውን ዋጋ ለመክፈል የቻሉ፣ በወቅቱ መልዕክቱን ያደመጡ፣ እንደ አቅማቸው ተባበሩት። ሀገር ውስጥም ደቡብ አፍሪካም የነበረውን ትብትቡን ቢሮክራሲ በታታሪንት ተቋቁሞ የዛሬ ሳምንት ዕለተ ቅዳሜ 14.12.2013 ዘውዳችን ሻንበል ጉታ ዲንቃ አውሮፕላን ውስጥ እንዳሉ ሲነገረን ፈነጠዝን። ዛሬ እኛነታችን፤ ማንነታችን ፈተና ላይ ወድቆ፤ ባለቤት አጥቶ ወገኖቻችን በዬተሰደደበት እያታነቁ በሚገደሉበት ወቅት አጋጣሚው የሰማይ ገድል ነበር። ሊያመልጠን አይገባም ነበር። በተባረኩ ወገኖችም አጋጣሚው እነሆ አፈራ። ቀሪው የሎቢ ተግባር ተጠናክሮ ከተሰራበት የበለጠ ትርፋማ መሆን ይቻላል። ኢትዮጵያዊነት የተከበረ ሰንደቅ ስለመሆኑ የዓለም ሚዲያ እንደመሰክር ማደረግ ይቻላል።

የተከበሩ ሻንበል ጉታ ዲንቃ ደቡብ አፍሪካ ከደረሱበት እስከ ተመለሱበት ድረስም የደቡብ አፍሪካ ጥቁር አንባሶች የኢትዮጵያዊነት ዓርማ ናቸውና አደራቸውን በተግባር አቅልመው ኢትዮጵያዊነትን ከፍ አደረጉልን። እግዚአብሄር ይስጣችሁ። በ2013 የአፍሪካ የእግር ኳስ ዋንጫ ወቅት ኢሮ ስፖርት ደቡብ አፍሪካ ላይ ስለሚገኙት ኢትዮጵውያን ልክ እንደ ሀገሩ ዜጋ ነበር በክብር ሲገልጻቸው የነበረው። ያኮራሉና! ኢሮ ስፖርት ስለ ኢትዮጵውያን የዘገበው እጅግ ነፍስን የሚገዛ ነበረ። ዛሬም ታሪካዊ ኃላፊነተቸውን በብቃት ተወጡ ሁነኛዎቻችን መካታና መመኪያዎቻችን ናቸው። ጠቅላላ ቃለ ምልልሱ፤ ምን እንደ ተሳማቸው ምስጋናው ሁሉም አለ …. ያልነባራችሁ ሲቢሊቲ ሩም እንሆ …. የ22.12.2013 የካፒቴን ሻንበል ጉታ ዲንቃ ቃለ ምልልስ በሲብሊቲ ሩም … „ፓን አፍሪካኒሰት የዘመኑ“ ይላቸዋል አባ መላ። በ አስር እጣታችን እንፈርማለን …. ጧፋችን ….

ማጠቃለያ …. አረሙ ወያኔ የምታሴሩትን የልዩነት ትብትብ ኢትዮጵውያን ፈተን አንድ ቀን ኢትዮጵያ ወደ ነበረችበት ክብር ትመለሳላች። በዚህ መልክ በትግባር፣ በመደማመጥ፣ ከተጋን አትጠራጠሩ የቀን ጉዳይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አሁንም የታሪካችን ሚስጢር አካል የሆኑት የጄ/ታደሰ ብሩ ልጆች ቤተሰቦች ይኖራሉ። እነሱን አፈለልጎ የተገባውን ክብር መስጠት የተገባ ነው። ከዚህ በተጨማሪም የማዲባ የቅርብ ጓደኛቸውና መምህራቸው የነበሩት ዛሬ ህመም ላይ ያሉት የኮ/ ፈቃደንም ጉዳይ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ራዲዮ ያደረገው ቃለ ምልልስ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎ ትውልዱ ታሪኩን በአግባቡ ይዘግበው ዘንድ ዝቅ ብዬ አሳስባለሁ። አክብሮታችን ፍለጋችን እኩል በተግባር ደምቆ መከናወን አለበት። ኢትዮጵያዊነትም ወደ ዘውዱ።

ዛሬ ደግሞ አባ መላ አዲስ ሃሳብ ይዞ መጥቷል ከትንሹ እንጀምር እያለን ነው። ወያኔ ለእርቅ ጠርቶ  እስርና ለበሸታ የዳረጋቸውን ጽኑ አቶ አበራ የማናአብ ከቤተሰባቸው ጋር አሜሪካን ሀገር የማቀላቀሉ የሎቢ ተግባር አብረን እንታደም ዘንድ አሳስቦናል። ወያኔ የሚጠላውን ስንፈጽም ወያኔን በቁሙ መግደል እንችላለን። ለነጻነት የአንድ ወጣት ዕድሜን ያሳለፉ፤ በሳንባ በሽታ የተጠቁ አካላችነን በአክብሮት ማገዝ በመርዳት ከጎን ተሰልፎ የድርሻን መወጣት ይገባል – ከትህትና ጋር። ቃለ ምልልሱ፤ ምን እንደ ተሳማቸው ምስጋናው ሁሉም አለ …. ያልነባራችሁ ሲቢሊቲ ሩም እንሆ …. የ22.12.2013 የካፒቴን ሻንበል ጉታ ዲንቃ ቃለ ምልልስ በሲብሊቲ ሩም … „ፓን አፍሪካኒሰት የዘመኑ“ ይላቸዋል አባ መላ። በ አስር እጣታችን እንፈርማለን …. ጧፋችን …. ልብል እኔ ደግሞ

 

ኢትዮጵያ ለዘለ ዓለም ትኑር!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ

 

ፍርድ ቤቱ አንድነት በኢቴቪ ላቀረበው ክስ ውሳኔ መስጠት ተስኖታል

$
0
0

ዳዊት ሰለሞን
መስከረም 3/2004 የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት ሀላETVፊ የሆነውን አንዷለም አራጌ፣የብሄራዊ ምክር ቤት አባሉን ናትናኤል መኮንንና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በቁጥጥር ስር መዋላቸው አይዘነጋም፡፡መንግስት ተጠርጣሪዎቹን ካሰረ በኋላ አሁን በህይወት የሌሉት መለስ ዜናዊ በፓርላማ‹‹ማስረጃም መረጃም አለን››በማለት እነአንዷለም ሽብርተኞች ስለመሆናቸው በድፍረት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ኢቴቪም ከጸረ ሽብር ግብረ ሀይል ጋር በመተባበር መለስ የፎከሩበትን መረጃና ማስረጃ ‹‹አኬልዳማ››በሚል ርዕስ ለማሳየት መዘጋጀቱን አታሞ መጎሰም ጀመረ፡፡አኬልዳማ ተጠርጣሪዎቹን ከፍርድ ቤት በፊት በሽብርተኝነት የወነጀለ፣ፓርቲውን ከሽብርተኛ ተቋማት ጋር ጋብቻ እንደፈጸመ አድርጎ በተራ ውንጀላ የፈረጀና የአንድነት አባላት ያልሆኑ ሰዎችን አባላት በማድረግ ያቀረበ የተለመደው ማጥላላት፣ሴራና ውሸት በመሆኑ ፓርቲው ለኢቴቪ አቤቱታ በማቅረብ እርምት እንዲወሰድ ይጠይቃል፡፡የኢቴቪ ቦርድ አመራሮች ግን ለዚህ ጆሮ አልነበራቸውምና፡፡በጥር 2004 ፓርቲው ክሱን አቀረበ፡፡
የፓርቲው ጠበቆች በቢፒአር መታየት ይገባዋል በማለት በፍጥነት እንዲታይላቸው ያቀረቡት ክስ እነሆ እስካሁን ድረስ ውሳኔ ሳያገኝ በድጋሜ ለጥር ወር ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡ለ20ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበው ክሱ በጥር ወር ሁለተኛ አመቱን ይደፍናል፡፡

የኢትዮ እስራኤላዉያን ህይወት

$
0
0
ኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያን ለዘመናት ወደናፈቋት እስራኤል በብዛት መሄድ ከጀመሩ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሆኗል። እስከዛሬም ወደመቶ ሰላሳ ሺህ የሚበልጡ እስራኤል እንደገቡ ይታመናል።…

221213 የዓለም ዜና 16:00 UTC

Amharic News 1800 UTC –ዲሴምበር 22, 2013

$
0
0
News, Radio Magazine or Mestawot…

ESAT Radio Dec 22

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን በዣንጥላና በምንጣፍ መለመንን ከልክላ በካሽ ርጅስተር ተጠቃሚ ልትሆን ነው

$
0
0

ቅዳሜ ዕለት የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንዘገበው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ በዣንጥላና በምንጣፍ መለመንን ከልክላ በካሽ ርጅስተር ልትጠቀም መሆኑን ዘግቧል። ጋዜጣው ጨምሮም ምእመናን ለቤ.ክ ሲሰጡ ደረሰኝ የሚጠይቁበት አሰራር ይኖራል ብሏል።

የአዲስ አድማስ ሙሉ ዘገባ እንደሚከተለው ነው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት የካሽ ሬጅስተር ማሽንን ለገቢ መሰብሰቢያነት ለመጠቀም የሚያስችላቸው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መኾኑ ተገለጸ፡፡

ዘመኑን ያልዋጀውንና ጥራት የጎደለውን፣ ለሙስናና ብክነት የተጋለጠውን የቤተ ክርስቲያኒቱን የፋይናንስ አሠራርና ቁጥጥር ችግር ግልጽነት፣ ወጥነት፣ ተቀባይነትና ተጠያቂነት ባለው የፋይናንስ አያያዝ ሥርዐት ለመቅረፍና ለማድረቅ ያስችላል፤ በሚል በቀረበው የሀገረ ስብከቱ የሒሳብ አያያዝ ፖሊሲና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ ረቂቅ ላይ እንደተጠቀሰው÷ በማንኛውም መንገድ የተሰበሰበ ገቢ ገንዘብ ሕጋዊ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወዲያውኑ ሊቆረጥለት የሚገባ ሲኾን ይህም በዋናነት በካሽ ሬጅስትር ማሽን እንደሚከናወን ተመልክቷል፡፡
bole_church_ethiopia-300x225 (1)
የሀ/ስብከቱ አብያተ ክርስቲያናት የካሽ ሬጅስተር ማሽን ተጠቃሚ መኾናቸው በገቢ ሒሳብ አሠራርና ቁጥጥር እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመከላከል ያስችላል፡፡ በጥናቱ ላይ በመነሻነት ከተዘረዘሩት ችግሮች ለመረዳት እንደሚቻለው በዕለት ገቢዎችና ደረሰኝ አጠቃቀም ረገድ፡- የቤተ ክርስቲያኒቱን የገንዘብ ገቢ ሰነዶች በሕገ ወጥ መንገድ አሳትሞ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ለግል ገንዘብ ይሰበሰባል፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የተከለከለ ደረሰኝ ጥቅም ላይ የሚውልበት አጋጣሚ ታይቷል፤ ከደረሰኙ በበራሪው/ለከፋዩ ከሚሰጠው/ የተለየ መጠን በቀሪው ላይ መጻፍና የግል ጥቅምን ማካበት ይዘወተራል፤ በዘወትርና በክብረ በዓላት በርካታ ገንዘብ ገቢ ቢኾንም በዕለቱ ወደ ባንክ ያለማስገባት ኹኔታ አለ፤ ምእመናን ለሚከፍሉትና ለሚሰጡት ገንዘብ ከመተማመን አንጻር ደረሰኝ የመቀበል ልማድ የለሌላቸው መኾኑን እንደክፍተት በመጠቀም ለቤተ ክርስቲያን የመጣው ገንዘብ ‹‹በየመንገዱ እየተንጠባጠበ ወፎች የሚለቃቅሙት ይበዛል፤›› በሥራ ላይ ያልዋሉ የገንዘብ ገቢና ወጪ ሰነዶች (ሞዴላሞዴሎች ሴሪ ንምራ ቁጥር) መሠረታዊ ችግር ተጠንቶ መፍትሔ አልተሰጠም፡፡

በንግሥ፣ በወርኃዊ በዓላትና በዕለተ ሰንበት በሙዳየ ምጽዋት ሳይኾን በተዘረጋ ጨርቅ ላይ የሚሰበሰብ ገንዘብ መኖሩን የሚጠቅሰው ጥናቱ÷ በዚህ መልክ የተሰበሰበው ገንዘብ ሀ/ስብከቱ በታኅሣሥ፣ 2003 ዓ.ም. ባስተላለፈው የገንዘብ ቆጠራ፣ የንብረት አመዘጋገብና አጠባበቅ የሥራ መመሪያ መሠረት የምእመናንና ካህናት ሰበካ ጉባኤ ተወካዮች በሙሉ በተገኙበት ቆጠራ የማይካሄድበትና በተወሰነ መልኩም ሙሉ ገንዘቡ ገቢ የማይደረግበት ኹኔታ በመኖሩ አሠራሩ ለብኩንነት፣ ሐሜትና አሉባልታ መጋለጡን ገልጧል፡፡ በንግሥ በዓላት ወቅት ጥላ ዘቅዝቀው የሚለምኑ ሰዎች ኹሉም ስለማይታወቁ የተኣማኒነት ችግር አለ፡፡ በስእለትና በሙዳየ ምጽዋት በውጭ ምንዛሬ የሚገቡ የውጭ ሀገር ገንዘቦች በመመሪያው መሠረት በዕለቱ የባንክ ምንዛሬ ወደ ብር እየተቀየሩ በተገቢው መንገድ ገቢ አለመኾናቸው፣ በምትኩ ቅያሬው ወጥነት ያለውና ለብኩንነት የተጋለጠ እንደኾነም ተዘግቧል፡፡

በቃለ ዐዋዲ ድንጋጌው የተመለከተውንና በዝርዝር የሥራ መመሪያ የተላለፈውን የገቢ አሰባሰብ በተሻለ አሠራር ያጠናክራል የተባለው በፖሊሲና መመሪያ ረቂቁ የሒሳብ ሰነዶች አያያዝ፣ ምዝገባና አወጋገድ መሠረት÷ ለሒሳብ ሥራ የሚያገለግሉ ደረሰኞችና ቫውቸሮች የዋና ተጠቃሚውን ተቋም ስም ይዘው በሀገረ ስብከቱ ምስጢራዊ ኮድ ይዘው ይታተማሉ፤ የማሳተም ሓላፊነቱም የሀገረ ስብከቱ የፋይናንስና በጀት ዋና ክፍል ሲኾን ይህም በዋና ሥራ አስኪያጁ ፈቃጅነት የሚከናወን ይኾናል፡፡Cash register machine

በማንኛውም መንገድ የተሰበሰበ ገቢ ሕጋዊ የገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወዲያውኑ ሊቆረጥለት ይገባል፤ ይህም በዋናነት በካሽ ሬጅስተር ማሽን ተፈጻሚ ይኾናል፤ የገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ከገንዘብ ሰብሳቢ ውጭ መያዝና መጠቀም አይቻልም፡፡ ማንኛውም የገንዘብ ስጦታ በገንዘብ ያዡ በኩል መሰጠት ይኖርበታል፤ ስጦታው እንደተበረከተም ወዲያውኑ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ሊቆረጥለት ይገባል፡፡ በዐይነት የሚሰጥ ስጦታ በግዥ፣ ሽያጭና ንብረት አስተዳደር ፖሊሲና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ መሠረት በተተመነለት ዋጋ ይመዘገባል፡፡
cash rigestor
ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ውጭ በሙዳየ ምጽዋት ሣጥን ገንዘብ መሰብሰብ አይቻልም፤ ቋሚ ሙዳየ ምጽዋት በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን የሚቀመጥበት ቦታ ተጠንቶ በሰበካ ጉባኤው መጽድቅ አለበት፤ ለቆጠራ ካልኾነ በቀር ከተቀመጠበት ማንቀሳቀስ አይቻልም፤ በትከሻና ተይዘው የሚዞሩ ሙዳየ ምጽዋት ሣጥኖች ሙሉ መረጃ ተመዝግቦ ይያዛል፡፡ የሙዳየ ምጽዋት ቆጠራ በሚካሄድበት ወቅት ሣጥኖቹ ከመከፈታቸው በፊት ሁሉም ቆጣሪዎች የቁልፍ ካዝናውና የቁልፍ ሣጥኖች፣ የሣጥኖቹን ብዛትና እሽጋቸው አለመከፈቱን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፤ የተቆጠረ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ወዲያውኑ ካልተቻለ ከሌላ ገንዘብ ጋራ ሳይቀላቀል በበነጋው ወደ ባንክ አካውንት መግባት አለበት፤ ዣንጥላን፣ ምንጣፍንና የመሳሰሉትን በመጠቀም ገንዘብ መሰብሰብ ፈጽሞ የተከለከለ ይኾናል፡፡

[የሀገረ ስብከቱ የመዋቅርና አደረጃጀት ሰነድ አካል የኾነው የሒሳብ አያያዝ ፖሊሲና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ ጥናት ረቂቅ እንደሚያትተው÷ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት፣ የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች፣ የልማትና በጎ አድራጎት ተቋማት፣ ደረጃ አንድ እና ሁለት የኾኑ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በኮምፒዩተር የታገዘ የሒሳብ አያያዝ ዘዴን/ሥርዐት እንዲከተሉ ይደረጋል፡፡ የሒሳብ አያያዝ ዘዴውም የሁለትዮሽ የሒሳብ አያያዝ ዘዴ(Double entry system) ሲኾን በአክሩዋል ቤዝስ ከሚጠቀሙት ከልማት ተቋማት በስተቀር የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ ያሉ ሌሎች ተቋማት በጥሬ ገንዘብ ላይ የተመሠረተ፣ ገቢንና ተከፋይን በታሳቢነት በሚያስላው የሒሳብ አያያዝ ዘዴ(Modified cash bases) እንዲከተሉ ለማድረግ መታቀዱ ተገልጦአል፡፡ በኮምፒዩተር የሚታገዘው የሒሳብ አያያዝ ሶፍትዌርም በሀገረ ስብከቱ ተመርጦ የተዘጋጀው እንደሚኾን ታውቋል፡፡

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ዘመናዊው የፋይናንስ ሞያ በጥምረት ሥራ ላይ ለሚውልበት ለዚህ አሠራር ተፈጻሚነት÷ ከሀገረ ስብከቱ፣ ከክፍለ ከተማ ጽ/ቤቶችና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ተመርጠው ለተውጣጡና ለሚመለከታቸው የሒሳብና የቁጥጥር ሓላፊዎችና ሠራተኞች ሥልጠና እንደሚሰጥ የተጠቆመ ሲኾን የሀገረ ስብከቱ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ዶኩመንቴሽን ዋና ክፍል በማእከል ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው የመሠረተ - ቴክኖሎጂው ዝርጋታ በሚተገበርባቸው ተቋማትና አብያተ ክርስቲያናትም በግልጽ የፕሮጀክት አሠራር እንደሚፈጸም ተገልጧል፡፡]
ዘመናዊው የፋይናንስ አሠራር በሀገረ ስብከቱ ተቋማትና አብያተ ክርስቲያናት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲኾንም በተጭበረበሩ ደረሰኞችና በማይታወቁ የገንዘብ አሰባሰቦች የግል ጥቅምን ማካበት በመከላከል ለክትትልና ቁጥጥር አመች ለማድረግ እንደሚያበቃ ተመልክቷል፡፡ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት፣ በልማትና በጎ አድራጎት ተቋማቱ እንዲሁም በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ የሚዘጋጁ የፋይናንስ ሪፖርቶች ግልጽነት፣ ወቅታዊነትና ተኣማኒነት/ተቀባይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ፣ ሀገረ ስብከቱ በሚሰበሰበው የኻያ በመቶ ፈሰስና ከአብያተ ክርስቲያናቱ በቅጽ ተሞልቶ በሚላከው ሒሳብ መካከል በየዓመቱ የሚያጋጥመውን ልዩነት ለማስወገድ እንደሚያስችል ተገልጧል፡፡

ይህም በሒደት ከፍተኛ የሀብት ክምችት የሚገኝበት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በፋይናንስ አሠራሩና መልካም አስተዳደሩ የሁሉም አህጉረ ስብከት ሞዴል በመኾን ቤተ ክርስቲያኒቱ በመንበረ ፓትርያርክ ደረጃ ማእከላዊ የፋይናንስና በጀት አስተዳደር ይኖራት ዘንድ መሠረት ለመጣል፣ የካህናቷን ኑሮ በማሳደግና በማሻሻል ሐዋርያ ተልእኮዋን ለማጠናከር ከፍተኛ አቅም የምትፈጥርበት መሠረት ለመጣል እንደሚያስችላት ታምኖበታል፡፡


በሳዑዲ አረቢያ ዛሬ የተነሳው የሸሜሲ መጠለያ ሁከት እልባት ሳያገኝ ቀረ

$
0
0

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በፌስቡክ ገጹ እንደዘገበው፦
የዛሬው የሽሜሲ መጠለያ ሁከት …

የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ” ህጋዊ ሰነድ የማታሟሉ ወደ ሃገር ቤት ግቡ! ” ያወጣውን ተደጋጋሚ መረጃ ተከትሎ ከአምስት ቀናት ጅምሮ ወደ ሽሜሲ መጠለያ በአስር አውቶቡስ በላይ ሆነው የገቡ ኢትዮጵያውያን ሜዳ ላይ ተጥለው ለከፋ መጉላላት መዳረጋቸው ገልጸዋል። አኒሁ ቅሬታ አቅራቢ ዜጎች በማከልም የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ዛሬ ጠዋት ሊያነጋግሯቸው የመጡ ቢሆንም ” ተረጋጉ እንመለሳለን !” ብልዋቸው መፍትሄ ሳይሰጧቸው እንደሄዱ ገልጸውልኛል። የሃላፊዎች ሙሉ ቀን መጥፋት ያበሳጫቸው ነዋሪዎች ዛሬ ከቀትር በኋላ በነፍሰ ጡር ፣ በህጻናት ላይ እያደረሰ ያለውን መንገላታት እየጎዳቸው መሆኑን በመግለጽ ለሳውዲ ሃላፊዎችን መፍትሔ ቢጠይቁም ” መፍትሄው በእናንተ ሃላፊዎች እጅ እንጅ ፣ በእኛ እጅ አይደለም! ” በማለት እንደመለሱልቸው እና ነዋሪው በብስጭት አስወጡን በሚል ወደ በሮች ቢጠጋም በወታደሮች መከልከላቸው በምሬት ገልጸውልኛል። ለሶስት ሰአታት በመጠለያው ውስጥ በተከሰተው ተቃውሞ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ወደ ቦታው በመሄድ ነዋሪውን አለማረጋጋታቸውን ብዙዎችን አሳዝኗል ።

(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)


ዛሬ በሽሜሲ መጠለያ የተነሳው ግርግር መንስኤነት በጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች እና በሳውዲ የመጠለያው ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር በተከሰተ አለመግባባት እንደሆነ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረጉት ሙከራ ለመረዳት ችያለሁ! የአለመግባባቱ ምንጭም መኖሪያ ፍቃዳቸውን ጥለው ወደ ሃገር የሚገቡ ዜጎችን ሰነድ ማጓተት ተከትሎ የቆንስል ሃላፊዎች ” ወደ ሃገር መግባት የሚፈልጉ ዜጎቻችን የመውጫ ሰነድ እስካልተሰጠ ድረስ ሰነድ አንሰራም!” አስገዳጅና ጠቃሚ መከራከሪያ በማቅረባቸው እንደሆነ ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ! ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ስልክ በመደወል ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም ።

የሽሜሲ ተቃውሞ እልባት ሳያገኝ በዚህ መልኩ ከቀጠለ እና ነዋሪዎች በሁኔታው ተማረው በሚወስዱት ተቃውሞ ለረብሻና ሁከት ሰበብ እንዳይሆን ሊታሰብበት የሚገባ ሲሆን ነዋሪውም ምግብና ውሃ በአግባቡ እስከ ቀረበ ድረስ ጉዳዩን በትዕግስት ሊጠባበቁ እንደሚገባ ይመከራል! በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ሃገር እንግባ በሚል በግላቸው ወደ ሽሜሲ መጠለያ የሄዱት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም በመጠለያው በት በመጉላላት ላይ መሆናቸውን ገልጸውልኛል። አቤቱታቸውን በተደጋጋሚ ያቀረቡልኝ ነዋሪዎች እኔን ሳይቀር “ድምጻችን አታፍንብን ፣ ለአለም አሰማልን! “ሲሉ ሃይለ ቃልን ጨምረው ወቅሰውኛል !

ቸር ያሰማን

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለዳግመኛ ክህደት እንዳይደረግ ሲሉ የቀድሞ አየር ኃይል አባላት ወቅታዊ ጽሁፍ በተኑ

$
0
0

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በመመርኮስ “በደም የተገነባ ተቋም” በሚል በበተኑት ጽሁፍ የአየር ኃይል ለዳግመኛ ክህደት እንዳይበተን ሲሉ አሳስበዋል። ለዘ-ሐበሻ የደረሰው የቀድሞው አየር ኃይል አባላት ጽሁፍ እንደሚከተለው ተስተናግዷል።
ethiopian airforce
በደም የተገነባ ተቋም
የኢትዮጵያ አየር ኃይል
(ለዳግመኛ ክህደት እንዳይዳረግ)

ግንቦት 83/91 ላይ የኢትዮጵያ ሰማይ ክፉኛ በሃዘን ሲመታ ፣ ደመናው ሲጠለሽ ፤ ወንዞች መደፈራረስ ሲጀምሩ፤ የሰውን ልብ ባር ባር ሲለው …….. የክፉው ቀን ጅማሮ ፣ የውርደት ሃሌታ ፣ የሃገር አልባነት ስሜትና የዜግነት ውርደት ደጃፍ ላይ መውደቃችን እውነት ነበር ።
ውርስ ከአባት ወደ ልጅ ሊተላለፍ ካልቻለ ፤ አባት የጀመረውን ልጅ ካልቋጨው ፤ አዲስ መንግስት ሲቀየር የድሮውን በጐ ነገር ሁሉ ብትንትኑን አውጥቶ ካጠፋ ፤ የትውልድ ቅብብሎሽ ገደል ገባ ማለት አይደል ? እናም በአገሬ ምድር ላይ የእርግማን ዘመን ያኔ “ በ1991 “ “ ሀ “ ብሎ ጀመረ ።
ሌባው ከሳሽ … ቀማኛው ፈራጅ የሆነበት ፤ አባት ተቀምጦ ልጅ የሁሉ ነገር አዛዥ ሲሆን ፤ አህያ ወደ ሊጥ … ውሻም ወደ ግጦሽ ከተሰማራ …. እነሆ ዘመነ ብልሹ ላይ መድረሱን ያልተረዳ ካለ … እሱ ባይፈጠር …. እናቱ ሆድ ውስጥ ውሃ ሆኖ ቢቀር ይሻለው ነበር ።

ሙሉውን ዘገባ በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ዝነኛው አርቲስት ቴዎድሮስ ምትኩ አረፈ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) አርብ ሴፕቴምበር 7 ቀን 2013 ታዋቂው የሙዚቃ ሰው ቴዲ (ቴዎድሮስ) ምትኩ በሜሪላንድ ግዛት ሆስፒታል መግባቱ ተገለጸ በሚል ዘ-ሐበሻ ዘግባ ነበር። ይህ ዜና እንደተሰማም በርካታ የኢትዮጵያ ሙዚቃ አፍቃሪያን ይህን ዝነኛ አርቲስት ፈጣሪ ምህረቱን እንዲሰጠው ሲጸልዩ ቆይተው ድምጻዊው ከሆስፒታል ተሽሎት ወጣ።

ሆኖም ግን ዛሬ ጠዋት ዲሴምበር 22 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡06 ላይ ኢትዮጵያውያንን ከ1960ዎቹ ጀምሮ ሲያዝናና የነበረው ቴዎድሮስ ምትኩ ማረፉ ተሰምቷል። የድምጻዊው የቀብር ቦታ እና የፍትሃት ሁኔታው ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ባይሰማም፤ የፊታችን ማክሰኞ ሊሆን ይችላል የሚል መረጃ ግን ለዘ-ሐበሻ ደርሷል። ሁኔታውን ተከታትለን እንዘግባለን።

ዝነኛው ቴዎድሮስ ምትኩ የጥላሁን ገሰሰ ባለቤት እህት ከሆነችው ወ/ሮ መአዛ በዙ ጋር ላለፉት 22 ዓመታት በትዳር ዓለም ቆይቷል።

ዘ-ሐበሻ በዚህ ታዋቂ የሳክስፎን ባለሙያ የተሰማትን ሃዘን እየገለጸች ታዋቂው ጸሐፊ ዳግላስ ጴጥሮስ እንደ አርቲስት ቴዎድሮስ ምትኩ ያሉ ዝነኞችን ለማስታወስ የጻፈውን ለግንዛቤ አስተናግዳለች።
ከዳግላስ ጴጥሮስ
የአንድ ጐልማሳ ዕድሜን ያህል ወደ ኋላ ዞር እንድንል የዛሬው ርዕሰ ጉዳዬ ትዝታ ይቀሰቅሳል – ከ1960ዎቹ ዓመታት በፊት፡፡ በእነዚያ ዓመታት ውስጥ በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ በድንቅ ባህልነቱ የሚጠቀስ አንድ ጥበብ በተለየ ሁኔታ አብቦ ነበር፡፡ ያውም የሙዚቃ ጥበብ፡፡
ይሁን እንጂ ይህን መሰሉ ባህል ከዘመን ዘመን የሚሸጋገር ፍሬ እንዳያፈራ «የሥርዓቶች ዋግ መትቶት» በአበባ ብቻ ሊቀር ግድ ሆኗል፡፡ በጭንገፋ ተመትቶ «ግባ መሬቱ» የተፈፀመው ይህ የጥበብ ቡቃያ ፍሬው ከትውልድ ትውልድ እንዳይተላለፍ በእሸትነቱ ስለ ተቀጨ እነሆ የዛሬው ጥበብ ነክ ችግራችን ገዝፎና ሥር ሰዶ «ለወይነዶ!» ቁጭት ዳርጎናል፡፡
ዝነኛው አርቲስት ቴዎድሮስ ምትኩ አረፈ
«ዛሬ» የሚለው ቃል በጽሑፌ ውስጥ መደጋገሙ አለብልሃት አይደለምና አንባብያን እንድትታገሱኝ በመቅድም አቤቱታ እማፀናለሁ፡፡
እናም የዛሬን አያድርገውና ለልዩ ልዩ ሕዝባዊ ክብረ በዓላት በመዲናችን አዲስ አበባና በዋና ዋና የሀገራችን ከተሞች በዓላቱን የሚያደምቁት የማርች ባንድ (በተለምዶ ማርሽ ባንድ የሚባለው) ሙዚቀኞች ከወታደራዊ ክፍሎች የተገኙት ብቻ አልነበሩም፡፡ ከእነርሱ ባልተናነሰ ደረጃ ያውም በተሟላ ዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ተደራጅተውና ማራኪ የደንብ ልብስ ለብሰው ጥዑም ዜማቸውን ለሕዝብ የሚያቀርቡ የትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንዶች ያበቡበት ወቅት ነበር፡፡ ወጣትነት በለገሳቸው መለሎ ቁመት እየተውረገረጉ የተመልካችን ቀልብ ይስቡ የነበሩት እኒያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ታዳጊ የሙዚቃ ጠበብት ዘግይቶ በተፈጠረው ትውልድ ይዘነጉ ካልሆነ በስተቀር በታሪክ መዝገብ ውስጥ ግን ህያው እንደሆኑ መቆየታቸውን የሚደልዝ የተሟጋች ብዕር አይኖርም፡፡
ዳግማዊ ምኒልክን፣ ኰከበ ጽባሕን፣ የደሴው ወ/ሮ ስሂንና የናዝሬቱን አፄ ገላውዲዎስ ትምህርት ቤቶች ብቻ ለጊዜው በክብር ልዘክር፡፡ እነዚያ ትምህርት ቤቶች የነበራቸው የሙዚቃ ባንዶች (ኦርኬስትራና ማርቺንግ ባንድ) በወቅቱ ለተደረሰበት የሙዚቃ ዕድገት ከፍታ ብቻ ሳይሆን በእነዚያ የሙዚቃ ባንዶች ውስጥ ተፈጥረው፣ አድገውና በጥበቡ ተራቅቀው ከሙዚቃ ጋር ነፍስና ሥጋቸው እንደተቆራኘ የሚገኙ ባለሙያዎች ቁጥር ቀላል የሚሰኝ አይደለም፡፡ ሌሎቹን ጥበባት ወቅትና ጊዜ ሲፈቅድ አስታውሳቸዋለሁ፡፡
«ክርስቶስ ለሥጋው አደላ” እንዲሉ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ዕውቀት የተጐነጨበትን የዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንድ የሚያስታውሰው በትልቅ አክብሮት ነው፡፡ ልዩ ልዩ ክበረ በዓላት ሲመጡ አዲስ የሙዚቃ ቅንብር ለመፍጠር ቀን ከሌት ይደረግ የነበረው ኃላፊነት የተሞላበት የተማሪ ጓደኞቹ የሸብ ረብ ዝግጅት አስደናቂ የሚሰኝ ብቻ ሳይሆን ከግምት በላይ ሊነገርለት የሚገባ ነው፡፡ በወርቃማ ጐፈርና በቀይና ቢጫ ቀለማት የተዋበው የተማሪዎቹ የሙዚቃ ባንድ ገና የትምህርት ቤቱን በር አልፎ ወደ ዋናው የአራት ኪሎ አውራ ጐዳና ሲገባ በዕልልታ ይቀርብለት የነበረው የሕዝብ አቀባበል ወደር አልነበረውም፡፡ በዚህ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንዶች ውስጥ ያገለግሉ የነበሩት የያን ጊዜዎቹ ተማሪዎች በኋለኞቹ የጉልምስና ዕድሜያቸው ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ዕድገት የተጫወቱት ሚና እንዲህ በዋዛ በቀላል የሃሳብ ጥቅሻ የሚታለፍ ስላይደለ ጥቂቶቹን ብቻ ለአብነት በመጥቀስ ዝርዝሩን በይደር ማስተላለፉ ይበጃል፡፡

ወደ ኰከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት እስኪዛወር ድረስ የዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ማርቺንግ ባንድ ታንቡር መች የነበረው የሙዚቃው ሊቅ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደና በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ውስጥ ከከፍተኛ የሥራ መሪነት እስከ መምህርነት እያገለገለ የሚገኘው አቶ ሰሎሞን ሉሉን ብቻ ለአብነት አስታውሼ ልልፍ፡፡ አቶ ሰሎሞን ሉሉ አሁን በሥራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ መዝሙር የዜማ ደራሲ እንደሆነም ማስታወሱ አስፈላጊ ነው፡፡
እኒህን መሰል ጐምቱ የሙዚቃ ጠበብት ተኰትኩተው ያደጉት በአንጋፋው የዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንድ ውስጥ ነው፡፡ እኒህንና ሌሎች በርካታ ወጣቶችን ሲያሰለጥኑ የነበሩት አቶ ዘውዱና አቶ መብራቱም የማይዘነጉ የጥበቡ ፊታውራሪዎች ነበሩ፡፡
የኰከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንድም ልክ እንደ ትምህርት ቤቱ ስም ሁሉ በወቅቱ የፈካ አጥቢያ ኰከብ ነበር፡፡ በዚያ የሙዚቃ ባንድ ውስጥ አድገው የወጡት ወጣቶችም በሀገራችን የሙዚቃና የቴአትር ጥበብ ላይ ያሳረፉት በጐ አሻራ ሊዘነጋ ከቶውንም አይችልም፡፡ ጥቂቱቹን ልዘክር፡፡ የትምህርት ቤቱ ዘንግ ወርዋሪ፣ ትራንፔት ተጫዋችና ድምፃዊ የነበረው ዓለሙ ገብረአብ እንዴት ይረሳል፡፡ ዓለሙ ገብረአብ ሕይወቱ እስካለፈ ጊዜ ድረስ የብሔራዊ ቴአትር ቤት ፈርጥ ተዋናይ ነበር፡፡
ዛሬ በውጭ ሀገራት ኑሮአቸውን የመሠረቱት ዝነኞቹ የሙዚቃ ባለሙያ ወንድማማቾቹ ተሾመ ምትኩና ቴዎድሮስ ምትኩ የኰከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንድ አባላት ነበሩ፡፡ በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ከዲሬክተርነት እስከ መምህርነት የዘለቀው አቶ ተክለ ዮሐንስ ዝቄ የዚሁ ትምህርት ቤት ፍሬ ነው፡፡ ታምራት ፈረንጅ፣ ተስፋዬ መኰንን፣ ታምራት ሎቴ፣ ሞገስ ሀብቴ ብዙዎቹ በሕይወት ባይኖሩም በተነደፉበት የሙዚቃ ፍቅር እስከ መጨረሻ የዘለቁት የኰከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት ባንድ ከጥበቡ ፍቅር ጋር ስላቆራኛቸው ነበር፡፡ የእነዚህ ወጣቶች አሠልጣኝ የነበሩት አቶ ማሞ ደምሴና አቶ ጌታነህ ታደሰም አይዘነጉም፡፡ በምሥረታውና በማጠናከሩ ሂደት ላይ የጐላ ድርሻ የነበራቸው ዳኒሻዊውን ፓል ባንክ ሃንሰንን የመሳሰሉ የውጭ ሀገር መምህራንን ለጊዜው በማስታወስ ብቻ እናልፋቸዋለን፡፡
የዝነኛው የደሴው ወ/ሮ ስሂን ትምህርት ቤት የወጣቶች ፖለቲካዊና ሁለገብ ገናና ተሳትፎ በታሪክ የከበረ ቦታ እንዳለው አይደለም የሰው ምስክርነት ሣር ቅጠሉም ቢሆን እኔ ልናገር ብሎ ለዋቢነት መሽቀዳደሙ አይቀርም፡፡ በተለይ ግን የወ/ሮ ስሂን ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንድ በወቅቱ የነበሩትን ወታደራዊ የሙዚቃ ባንዶችን ብቃት በከፍተኛ ሁኔታ ይፈታተን እንደነበር ዕድሜውን የታደሉት ሁሉ የሚያስታውሱት ነው፡፡
የናዝሬቱ ዓፄ ገላውዲዎስ፣ የሐረሮቹ መድኃኒዓለም ትምህርት ቤት እና የመምህራን ማሠልጠኛ ተቋም የሙዚቃ ባንዶችም የነበራቸው ዝና እንዲሁ በጥቂት ቃላት እየታወሰ የሚታለፍ ባይሆንም ዝርዝሩን ለታሪክ ጸሐፍት በመተው ለዝክር ያህል ስማቸውን አስታውሰን እናልፋለን፡፡ የአዲስ አበባዎቹን መድኃኒዓለም ትምህርት ቤትና ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤትን በተመለከተ ግን ንባቤና መረጃዬ ስላልዳበረ እንዲህ ነበሩ ለማለት ድፍረት አጥቻለሁ፡፡ እነዚህን ሁለት ትምህርት ቤቶች በተመለከተ አዋቂዎች ቢያስተምሩን ነበርኩበት ባዮች ቢያሳውቁን ለዕውቀታችን በእጅጉ ይጠቅመናል፤ ከስህተትም ይታደገናል፡፡ መድኃኒዓለም ትምህርት ቤትን ካነሳሁ አይቀር ብዕረ መንገዴን በትምህርት ቤቱ ዋና መግቢያ ላይ ይነበብ የነበረውንና በፍፁም ከህሊናዬ ሊወጣ የማይችለውን ጥቅስ አስታውሼ ልለፍ፤ «ከዚህ ከማይሞተው የሰው ልጅ ማደጊያ ሥፍራ ግቡ» የሚለውን፡፡ ዛሬስ ያ ጥቅስ በቦታው ይገኝ ይሆን?
በውስን የጋዜጣ ገጽ ግዙፍ ሃሳቦችን ማስተናገድ ፈተናው የትዬለሌ መሆኑን አንባቢያን እንደሚረዱት ተስፋ በማድረግ ወደ ማጠቃለያው ሃሳብ ብዕሬን በፍጥነት ማንደርደሩን መርጫለሁ፡፡
ዛሬን ከቀዳሚ ዘመናት ጋር እያስተያዩ ይህ ጐደለ ይህ ሞላ ማለቱ አግባብ ባይሆንም ትናንትን ከዛሬ ጋር እያነፃፀሩ መልካሙን ማስታወሱ ግን ተገቢነት ይኖረዋል፡፡ ለምን ቢሉ፤ «ብልህ ከትናንት ይማራል፣ ሞኝ ግን ዕለት በዕለት ይሳሳታል» እንዲሉ መሆኑ ነው፡፡
ከላይ በተዘረዘሩት ትምህርት ቤቶች የሙዚቃ ባንድ ውስጥ አባላት የነበሩት ወጣት ተማሪዎች ትምህርት ቤታቸውን ከተሰናበቱ በኋላ ምን ሠሩ? ምን ፈፀሙ? ዛሬስ የት ናቸው? ተገቢ ጥያቄዎች ናቸው፡፡
በታዳጊነት ዕድሜ ከመደበኛው ትምህርታቸው ጐን ለጐን በሙዚቃ ፍቅር የወደቁት እኒያ ወጣቶች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአሸናፊነት ተወጥተው በልዩ ልዩ ሙያቸው ለሀገራቸው ኩራት እንደነበሩና እንደሆኑ ሥራቸውና ስማቸው ምስክር ነው፡፡
ለአብነት ያህልም በዘመኑ ዝነኛ ባንድ የነበረውን «ሶል ኤኰስ» በመባል ይታወቅ የነበረውን ባንድ የመሠረቱት በኰከበ ጽባሕ የሙዚቃ ባንድ ውስጥ የነበሩት ተስፋዬ (ሆዶ) መኰንን (ከበሮ መቺ)፣ ታምራት ፈረንጅ (ትራምፔት ተጫዋችና ድምፃዊ)፣ ተክለ ዮሐንስ ዝቄ (ትራምፔት)፣ ተሾመ ምትኩ (ጋራ ሥር ነው ቤትሽ፣ ሞት አደላድሎን፣ ሃሳቤን የመሳሰሉት ዝነኛ ዜማዎቹ ይጠቀሳሉ) እና ቴዎድሮስ ምትኩ (ሳክሲፎኒስት) የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህ የኰከበ ጽባሕ ፍሬዎች ከሶል ኤኰስ በፊትም ዙላ ባንድን መሥርተው ነበር፡፡ «ሶል ኤኰስ» ባንድን ወደ «አይቤክስ ባንድ» ከዚያም «ሮሃ ባንድ» ወዘተ. እየተባለ የስም ሽግግር በሚደረግበት ጊዜ ሁሉ እነዚያ ወጣቶች በንቃት ተሳታፊ ነበሩ፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩት ብዙዎቹ የትምህርት ቤቶቹ የሙዚቃ ባንድ አባላት በሀገራችን የሙዚቃ ጥበብ ውስጥ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ዛሬም ድረስ የደበዘዘ አይደለም፡፡ እንዲያውም ብዙ ታላላቅ የጥበቡ ሰዎችን አሁን ድረስ ለደረሱበት ደረጃ መሠረት የሆናቸውን መደላድል ጥቀሱ ቢባሉ ያለጥርጥር ምሥጋና የሚያቀርቡት ላሳደጋቸው የየትምህርት ቤቱ የሙዚቃ ባንድ እንደሆነ መገመት አይገድም፡፡
ይህ ታላቅ የጥበብ መክሊት በዛሬዎቹ ትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ አለወይ? ርግጥ የዕውቀትና የጥበብ ሁሉ መፍለቂያው ትምህርት ቤት መሆኑ መስካሪ አያሻውም፡፡ ግን ግን በየትምህርት ቤቱ ለዛሬውም ሆነ ለነገው ሙዚቃችን መሠረት ሊሆን የሚችል ሥራ እየተሠራ ነው? ከመደበኛው ሥርዓተ ትምህርት ጐን ለጎን ለሙዚቃ ጥበብ እየተሠጠ ያለው ትኩረት ምን ያህል ነው? የትምህርት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን «የተቀበረውን ውጤታማ መክሊት» ቆፍሮ ለማውጣት ምን እየሠራ ይሆን? ዳግማዊ ምኒልክ፣ ኰከበ ጽባሕ፣ ወ/ሮ ስሂን … ትምህርት ቤቶችስ «ነበር» ታሪካቸውን ማደስ አይገባቸውምን? የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወድቋል ወይም ተነስቷል እያልን መከራከራችን ብቻ በራሱ በቂ ይሆናልን? ምን ያህሉን መክሊቶቻችንስ አርቀን በመቆፈር ያለማስተዋል ቋጥኝ ጭነንባቸው ቀበርናቸው ይሆን? እንወያይበት፣ እንምከርበት፡፡ ከንባቤ ጎን ለጎን ለዚህ ጽሑፍ በቂ ግብዓት በመስጠት የተባበሩኝን አርቲስት እሸቱ ጥሩነህ፣ ደራሲና ሃያሲ አስፋው ዳምጤና አቶ ተክለዮሐንስ ዝቄን ክብረት ይስጥልኝ በማለት በአንባቢያን ስም የማመሰግነው በታላቅ አክብሮት ነው፡፡ ሰላም፡፡

የአማራ ዴ/ኃ/ን ለሱዳን ተላልፎ በተሰጠው መሬት ዙሪያ “ዳሩ ካልተጠበቀ መሃሉ ዳር ይሆናል” የሚል መግለጫ አወጣ

$
0
0

Amara Democratic Force
ጋዜጣዊ መግለጫ 

“ዳሩ ካልተጠበቀ መሃሉ ዳር ይሆናል”!!

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የተሰጠ መግለጫ

ታህሣሥ 10 ቀን 2006 ዓ.ም.

በዓለም ላይ እስከአሁን የተከሰቱ መንግሥታት (ቅኝ ገዥዎችን ጨምሮ) ጨቋኝ (አምባገነን)፣ በዝበዥ፣ ዘራፊ (በሙስና የተዘፈቀ) … ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። አሁን ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ እንዳለው የትግሬ ዘረኛ ቡድን የሚገዛትን ሀገርና ሕዝብ የሚጠላና ሀገሩንም ለማጥፋት 24 ሰዓት የሚሠራ መንግሥት ግን እስከ አሁን በታሪክ አልታየም። ወደፊትም ከወያኔ በስተቀር የሚገዛትን ሀገር፣ ታሪኳንና ሕዝቧን የሚጠላና ሆን ብሎ ለማጥፋትም ቀን – ተሌት የሚጥር መንግሥት በምድር ላይ ይከሰታል ብለን አናምንም። ይህ የትግሬ ዘረኛ ቡድን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን መጥላቱን የሚያሳይ የድርጊቱን ሥንክሣር መዘርዘር ቢቻልም፣ በአሁኑ ሰዓት የተከሰቱ ሁለት ታላላቅ ብሔራዊ ጉዳዮችን ብቻ እንኳ ብናይ ዘረኛው ቡድን ምን ያህል የሚገዛትን ሀገርና ሕዝቧን አምርሮ እንደሚጠላ ፍንትው አድርገው ያሳያሉ፦

  1. በሣዑዲ አረቢያ የወገኖቻችን ደም  በግፍ ሲፈስስ፣ እህቶቻችን ያለርህራሄ በቡድን ሲደፈሩ፣ በ21ኛው ክ/ዘመን በሰው ልጅ ላይ የፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ ኢሰብአዊ ግፍ ሲፈፀምባቸውና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ላይ ብሔራዊ ውርደት ሲደርስ የትግሬው ዘረኛ ቡድን “የሣዑዲ አረቢያ መንግሥት በሀገሩ ላይ ይህንን ማድረግ መብቱ ነው” ነበር ያለው።
  2. በዚህ ሰቅጣጭ ሐዘን ውስጥ ተውጠንና በስቃይ ላይ ያሉ ወገኖቻችንን ለመርዳት ላይ ታች በምንልበት ጊዜ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ታጥቆ የተነሳው የትግሬው ዘረኛ ቡድን አባቶቻችን ደማቸውን በማፍሰስና አጥንታቸውን በመከስከስ ጠብቀው ያቆዩትን 1600 ኪ/ሜ ርዝመትና ከ20-60 ኪ/ሜ ወደ ኢትዮጵያ ጥልቆ የሚገባውን ከሱዳን የሚያዋስነውን ድንበራችንን በሕገወጥነት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ፈርሞ ለሱዳን አስረከበ። ምንም እንኳን በሚስጥር ሊይዘው ቢሞክርም የድንምበር ማካለሉ ከጥር ወር 2006 እስከ መስከረም 2007 ችካል በመቸከል እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) ይህንን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ የሚደረግ ሕገወጥ የድንበር ክለላ አጥብቆ መቃወምና ማውገዝ ብቻ ሳይሆን እንዳባቶቹ ደሙን አፍስሶና አጥንቱን ከስክሶ ታሪካዊ ድንበሩን ለማስከበር ቆርጦ ተነስቷል። ባንዳ የባንዳ ልጆች ከአባቶቻቸው የወረሱትን ሀገር የማጥፋትና የመሸጥ ውርስ ተግባራዊ ሲያደርጉ እኛ የአርበኛ ልጆች ነን የመንል ይህንን ደባ ዝም ብለን ብንመለከት ድንበር ላይ የተከሰከሰው የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይዎጋናል። በመሆኑም በአካባቢው ያላችሁ ታጋይ ኃይሎችና የገፈቱ ቀማሽ የሆንከው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በርስቱና በሚስቱ ያልሞተ ወንድ ልጅ ወንድ አይደለምና ወንድ ልጅ ነኝ ያልክ ሁሉ ተባበረን፣ ከዚህ በላይ የሞት ሞት የለምና።

አዴኃን ይህንን ድርጊት አምርሮ የሚቃወመው እንዲያው በጭፍኑ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ሕጋዊ የሆነ ድንበር አይኑራት ብሎ አይደለም። የድንበር ስምምነቱ ኢትዮጵያን ጎድቶ ሱዳንን የሚጠቅም፣ ከ110 ዓመታት በፊት የፈረሰና ሕጋዊ ያልሆነ ውልን መሠረት ያደረገ፣ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናት ያደረጉ ኢትዮጵያውያንን ጥናትና ውትወታ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ  ሕዝብ ጀርባ በደባና በሕገወጥነት የተፈረመ ውል በመሆኑ እንጅ።

በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናት ያደረገው የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴና ከዚያ በፊትም ጥናት ያደረጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሑራን እንደሚሉን ከሆነ ይህ ዛሬ የትግሬው ዘረኛ ቡድን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ለተፈራረመው ውል ዋቢ የሚያደርገው ውል በዳግማዊ አፄ ምኒልክና በጊዜው የሱዳን ቅኝ ገዥ በነበረችው እንግሊዝ መካከል የተፈረመው እ.አ.አ 1902 ነበር። አፄ ምኒልክ ይህንን ውል የፈረሙት በኃይል ተገድደውና በይዞታቸው ሥር የነበሩ ብዙ መሬቶችን ለቀው ነበር። በዓመቱ በ1903 የእንግሊዙ የጦር መኮንን ሻለቃ ጉዊን ድንበሩን ከስምምነቱ ውጭ ብቻውን ሄዶ ከመከለሉም በላይ አፄ ምኒልክ ተገድደውም ቢሆን የፈረሙትን ካርታ አዛብቶ ኢትዮጵያን እየጎዳ ችካል ቸከለ። ይህንንም ሻለቃ ጉዊን ከተሰጠው ሥልጣን በላይ ሄዶ መሥመሩን በማዛባት ከኢትዮጵያ መሬት እንደወሰደ በራሱ ሪፖረት ላይ በግልፅ ሳይደብቅ ጽፏል። እንግሊዞችም በ1902 የተፈረመበትን ካርታ ጥለው በችካሉ መሠረት በ1903 አዲስ ካርታ በመሥራት እነርሱ ከፈረሙበት በኋላ አፄ ምኒልክን ለማስፈረም ቢሞክሩም ከስምምነት ውጭ ለተቸከለው የጉዊን ክለላ ዕውቅና በመንፈግ ሳይፈርሙበት ቀርተዋል። የትግሬው ዘረኛ ቡድን አፄ ምኒልክ፣ አፄ ኃይለሥላሴና ደርግ የጉዊንን መሥመር ተቀብለዋል እያለ የሚያላዝነው ይህንን የመሰለውን ሐቅ በመካድ ነው። ይህንንም ዓይን ያወጣ የወያኔን ቅጥፈት አዴኃን ብቻ ሳይሆን ሰኞ 19 ኖቬምበር 2007 (እ.አ.አ.) ሱዳን ትሪቢዩን የተባለ ጋዜጣም “ድንበሩን አስመልክቶ የሱዳን መንግሥት ከቀደምት የኢትዮጵያ መንግሥታት ጋር የነበረው ግንኙነት ቀና አልነበረም። በድንበሩ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር የመጀመሪያው ፈቃደኛ መንግሥት ገዥው የኢሕአዴግ መንግሥት ብቻ ነው” በማለት መሥክሮበታል።

ጥሪ፦     

ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራትም ጭምር፣ ይህ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ በሀገር ከሃዲው የትግሬ ዘረኛ ቡድ ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከወለጋና ከኢሊባቡር ክፍለ ሀገሮች ተቆርሶ ለሱዳን የሚሰጠው ለም መሬት የክፍለ ሀገራት ተወላጆቹ መሬት ብቻ አይደለም፤ የአንተም የኢትዮጵያዊው መሬት እንጅ። በመሆኑም አዴኃን ይህንን በባንዳ ልጆች የተጋረጥብንን ኢትዮጵያን የማጥፋት ታላቅ አደጋ ለመቀልበስ ስንል ያሉንን ጥቃቅን ልዩነቶች ወደጎን በመተው፣ ከምንጊዜውም በላይ እጅ ለእጅ ተያይዘንና ያለንን አቅም ሁሉ አስተባብረን በመነሳት የዜግነት ግዴታችን እንድንወጣ አስቸኳይ ጥሪውን ያስተላልፋል። “ዳሩ ክልተጠበቀ፣ መሀሉ ዳር ይሆናል” እንደሚባለው የትግሬውን ዘረኛ ቡድን በተባበረ ክንድ ዛሬውኑ ካላስወገድነው በስተቀር እናት ሀገራችን ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዕኩይ ተልዕኮው የድንበር መሬቶችን እየቆረሰ ለጎረቤት ሀገራት በመስጠት ብቻ ያቆማል ብሎ ማሰብ ፍፁም የዋህነት ነው።

ለመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ኃይልና የኢሕአዴግ ደጋፊዎች፣ እናንተ የምትደግፉት ሀገር አጥፊው የትግሬ ዘረኛ ቡድን አባቶቻችን ደረታቸውን ለጦር፣ እግራቸውን ለጠጠር ሰጥተው በደማቸው ያቆዩአትን ይህችን ጥንታዊትና ታሪካዊት ሀገራችንን እያጠፋት እንደሆነ ለእናነተ የተሠወረ አይደለም። ይህንን ሀገር የማጥፋት ወንጀል የሚፈፅመው ደግሞ እናንተን በመሣሪያነት በመጠቀም ስለሆነ ይህንን ተገንዝባችሁ አሁኑኑ ከሕዝባችንና አደጋውን ለመቀልበስ ከሚታገሉ ኃይሎች ጎን በመቆም ሀገራችሁን እንድትታደጉ ስናሳስብ፣ ጥሪያችን ችላ በማለት ለሀገር አጥፊው ቡድን ተባባሪነታችሁን ከቀጠላችሁበት ግን ታሪክና ሕዝብ ይቅር እንደማይላችሁ በጥብቅ ልናስጠነቅቃችሁ እንወዳለን።

ለብአዴን አባላት፦ “እሣት አመድ ይወልዳል” እንደተባለው ካልሆነ በስተቀር፣ አባቶቻችሁ ኢትዮጵያን ከሚያጠፋ ጠላት ጋር ተባብረው እናት ሀገራቸውን አላጠፉም፤ ይልቁንም ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው የታፈረችና አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለእናንተ አስረከቧችሁ እንጅ። እናንተ ግን የጀግኖች አባቶቻችሁ የባሕሪ ልጆች መሆን አቅቷችሁና አደራቸውን በልታችሁ ኢትዮጵያን ለማፈራረስና አማራን ለማጥፋት ቆርጦ ለተነሳው የትግሬ ዘረኛ ቡድን አሽከር ሆናችሁ እናት ሀገራችሁንና ወገናችሁን እያጠፋችሁ ነው። “ለእንጀራየ፣ ለልጆቼና ለቤተሰቦቼ ስል ወይም ተገድጀ ነው ይህንን የማደርገው” የሚለው ውሃ የማይቋጥር ምክንያት እንደማያዋጣችሁ አውቃችሁ የጋራ ሀገራችንንና ወገናችንን ለመታደግ አብራችሁት እንደትቆሙ አዴኃን ከልብ የመነጨ የሀገር አድን ጥሪ ያቀርብላችኋል።

ወንድም ለሆነው የሱዳን ሕዝብ፦ የኢትዮጵያና የሱዳን ሕዝብ ለብዙ ሺህ ዘመናት ከአንድ ወንዝ ከተቀዳ ውሃ እየጠጣ፣ በመከባበር ላይ በተመሠረተና በመልካም ጉርብትና አንዱ ለሌላው የችግር ጊዜ ደራሽ ሆኖ የኖረ ወንድማማች ሕዝብ ነው። ነገር ግን ዛሬ የትግሬው ዘረኛ ቡድን በሀገር ውስጥ የሚገኙ ነገዶችን እርስ በእርሳቸው ከማናከስ አልፎ የኢትዮጵያን ሕዝብ በተለይም የአማራውን ነገድ ወንድም ከሆነው የሱዳን ሕዝብም ለማናከስ ቆርጦ የተነሳ በመሆኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕውቅና ውጭ የተፈረመን የድንበር ስምምነት እንዳይቀበል በጥብቅ እናሳስባለን።

በመጨረሻም የዓለም ምንግሥታትና ዓለም – አቀፍ ሠላም ወዳድ ሕብረተሰብም የወያኔ ዘረኛ ቡድን ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ፈፅሞ እንደማይወክልና አሁን ከሱዳን መንግሥት ጋር በድብቅ የተፈራረመውንም የድንበር ስምምነት ንቅናቄያችን አዴኃን እና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማያውቁት ተገንዝበው ስምምነቱ አሁንም ይሁን ወደፊት በሁለቱ ሀገራት ሕዝብ መካከል የሚፈጠረውን ቀውስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለስምምነቱ ዕውቅና እንዳይሰጡና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ይህንን ሤራ እንዲቃወሙ አዴኃን ጥሪውን ያስተላልፋል።

በደም የተረከብናትን ሀገር በደም እንጠብቃታለን!!

 

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ

የኢህአዴግ አዲሱ አሰላለፍ ፪ – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

samora and azeb

በድህረ-መለስ ኢትዮጵያ የፖለቲካው ሥልጣን በስርዓቱ ልሂቃን መካከል ከሚደረገው የኃይል መተናነቅ አንጻር፣ ዛሬም ከመፈራረቅ ጣጣው የተላቀቀ የማይመስልባቸው ምልክቶች መታየታቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ከአራት ወር በፊት በዚህ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ባቀረብኩት ፅሁፍ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው ክፍፍል የትኛው ቡድን የበለጠ ጉልበት አግኝቶ በአሸናፊነት መውጣት እንደቻለ ከገለፅኩ በኋላ ፅሁፉን የቋጨሁት እንዲህ በማለት ነበር፡- ‹‹የፓርቲው የታሪክ ድርሳን እንደሚነግረን ‹ይሆናሉ› የተባሉት ተቀልብሰው፣ ባልተጠበቁ ሁነቶች (የኃይል መገለባበጥ ተከስቶ) ፖለቲካው የሚመራበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አያስፈልግም፡፡››

እነሆ በዚህ ፅሁፍ ደግሞ በቅርቡ በተጨባጭ የታዩትን አዳዲስ ኩነቶች እና ይህንኑ ተከትለው ሊመጡ ይችላሉ ብዬ የምገምታቸውን ‹የቢሆን ዕድሎች› (Scenarios) ለማየት እሞክራለሁ፡፡
ሰላም የራቀው-ኢህአዴግ
በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ዛሬም ድረስ ሙሉ በሙሉ የተረጋጋ ፖለቲካ አልሰፈነም፤ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ፣ ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎችን ጠቅልሎ ይዞ በነበረው በቀድሞ ሊቀ-መንበሩ ህልፈት ሳቢያ የተፈጠረው የአመራር ክፍተት እና እርሱን ሊተካ የሚችል መሪ ማግኘት ባለመቻሉ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎችም በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ከሕግ ይልቅ የጠመንጃ ኃይልና የግለሰብ አምባገነናዊነት በገነነበት ሀገር ‹የማይገመቱ ክስተቶች› (Unpredictable Event) ማምጣታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡

የሆነው ሆኖ በዚህ አጀንዳ ለመመልከት የምሞክረው ጉዳይ፣ በአሁኑ ጊዜ ሀገር እየመራ ያለው ኃይል ለሁለት የተከፈለ ቢሆንም፣ በአንፃራዊነት በጥምር የሚሰራ መሆኑን በማስረገጥ ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቡድኖች የጉልበት ምንጭም የታጠቀውን ኃይል በመቆጣጠር እና የፖለቲካውን ሥልጣን በመያዝ ላይ የተመሰረተ ነው፤ ይኸውም ሠራዊቱ እና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሙሉ በሙሉ በህወሓት ሰዎች ሲንቀሳቀሱ፣ ፖለቲካውን ደግሞ የብአዴን መሪዎች፣ ከተወሰኑ የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት ጋር ተባብረው መያዛቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች መኖራቸው ነው፡፡

የህወሓት ኃይል

ህወሓት የቀድሞው ፍፁማዊ የበላይነቱን ለመመለስ ዋና ችግር የሆነበት በውስጡ ለተፈጠረው መከፋፈል እስካሁን መፍትሄው ተለይቶ አለመታወቁ ነው፤ ከዚህ ቀደም በዚሁ መፅሄት፣ አንዱ ኃይል የተሻለ ጉልበት በማግኘቱ ሌላኛውን (እነአዜብ መስፍንን ጨምሮ አባይ ወልዱና ቴዎድሮስ ሀጎስን የመሳሰሉ ከፍተኛ ካድሬዎች የተሰባሰቡበትን) በመብለጥ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እንቅስቃሴያቸውን መገደቡ ተሳክቶለት እንደነበረ ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ ይህ ክፍፍል ምንም እንኳ እንደ 1993ቱ ከፓርቲ እስከ ማስወጣት የሚደርስ አለመሆኑ ቢታወቅም፣ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ጌታቸው አሰፋ የተሰለፉበት ቡድን ተፅእኖ ፈጣሪ ሆኖ መውጣት ችሏል፤ ይህም ሆኖ ውስጥ ውስጡን የሚገመደው ተንኮልም ሆነ ሽኩቻ ገና መቋጫ አለማግኘቱ ግልፅ ነው፡፡
በዚህ ፅሁፍ ጠመንጃ የታጠቀውን ክፍል ‹የህወሓት ኃይል› እያልኩ የምገልፀበት ዓብይ ምክንያት፣ በጄነራል ሳሞራ የኑስ ኤታ ማዦር ሹምነት የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት እና በማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጌታቸው አሰፋ ስር ያለው የደህንነት ኃይል ለሚደግፉት ቡድን መጠናከር እያበረከቱት ያለውን አስተዋፅኦ ከግምት በመክተት ነው፡፡ ሁለቱም ሰዎች ለመለስ ፍፁም ታማኝ የነበሩ ቢሆንም፣ ከህልፈቱ በኋላ እንደእርሱ ተጭኖ ሊቆጣጠራቸው የሚችል ጉልበታም ህወሓትን ጨምሮ በሁሉም የግንባሩ አባል ፓርቲ ውስጥ አለመኖሩ፣ በፖለቲካው ‹ቼዝ› የ‹ዘመነ መሳፍንቱ›ን ሚካኤል ስሁል አይነት ሚና እንዲጫወቱ አስችሏቸዋል፤ ሁለቱም ከስራቸው የነበሩትንና ‹ስልጣን ሊጋፉ ይችላሉ› ብለው የጠረጠሯቸውን ባልደረቦቻቸውን አስቀድሞ ገለል ማድረጉ ከሞላ ጎደል የተሳካላቸው ይመስለኛል፡፡
በተለይም ጌታቸው አሰፋ ከራሱ ወንበር አልፎ ከእነአዜብ መስፍንና አባይ ወልዱ ጋር በመተባበር አንድ ቀን በጠቅላላው የመንግስት የሥልጣን እርከን ላይ ‹ናቡቴ ሊሆን ይችላል› የሚል ስጋት ያሳደረበትን እና ‹መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድመው በእርሱ ቦታ ሊተካው ነበር› እየተባለ የሚነገርለትን የመረጃ ኃላፊ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና የሚወነጀልበትን መንገድ አመቻችቶ ለእስር ባይዳርገው ኖሮ ‹‹ለቁርስ ያሰቡንን…›› አይነት ታሪክ ራሱን መድገሙ አይቀሬ ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡
ጄነራል ሳሞራ የኑስ በበኩሉ ተቀናቃኙ አድርጎ ይመለከታቸው የነበረው ሶስቱ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ ወልደስላሴ ‹ፍንቀላ መሳይ ነገር ሊሞክሩ ይችላሉ› ተብለው አይደለም፡፡ የእነርሱ የመጀመሪያው ችግር ከወታደራዊ ዲሲፕሊን በማፈንገጥ አለቃቸውን አለማክበራቸው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሳሞራ ‹በየትኛውም ምክንያት ከኃላፊነቴ ብነሳ የቆየ ፋይል አገላብጠው አደጋ ላይ ሊጥሉኝ ይችላሉ› በሚል ስለሚጠረጥራቸው ነው፡፡ እነዚህ መኮንኖች የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል ሰዓረ መኮንን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መልካም ግንኙነታቸው እንደቀድሞው እንዳልሆነ የሚነገረው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል አበባው ታደሰ እና የአየር ኃይሉ አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሞላ ኃይለማርያም ናቸው፡፡ እናም ሰዓረ እና አበባው በቀጥታ ሠራዊት ከሚያዙበት ቦታ ተነስተው በመከላከያ ሚኒስትር ውስጥ በቢሮ ስራ ላይ ሲመደቡ፣ ሞላም ከነበረበት ኃላፊነት አኳያ ብዙም ይመጥነዋል የማይባል የቢሮ ስራ ተሰጥቶታል፤ በእርሱም ቦታ ሜጀር ጄነራል አደም መሀመድ ተተክቷል፡፡ የሳሞራ እና የሞላ ልዩነት በመለስ ዘመንም በአደባባይ የሚታወቅ እንደነበረ ሰምቻለሁ፡፡
Samora (2)
ለጉዳዩ ቅርብ ከሆነ የመረጃ ምንጬ እንዳረጋገጥኩት የአስተዳደር ዘይቤውን በማኪያቬሊያዊ አስተሳሰብ (ከፋፍለህ ግዛ) የሚያሳልጠው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ለሞላ ትዕዛዝ የሚሰጠውም ሆነ ማንኛውንም ጉዳይ በተመለከተ የሚያነጋግረው የዕዝ ተዋረዱን ጠብቆ በኤታ ማዦሩ በኩል ሳይሆን፣ በቀጥታ በመገናኘት መሆኑ፣ አየር ኃይሉን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገነጠለ አስመስሎት ነበር፤ ይህ ሁኔታም በሁለቱ መኮንኖች መካከል ያለው ግንኙነት የሥልጣን ተዋረድን የጠበቀ እንዳይሆን በማሰናከሉ በጄነራሉ ላይ ደፍሮ የማይናገረው ቅሬታ ሊያሳድርበት ችሏል፤ ከመለስ ህልፈት በኋላም ሳሞራ ሂደቱን ለማስተካከል መሞከሩ፣ በየግምገማው ላይ እስከ መዘላለፍ አድርሷቸው ነበር (በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ እንደ ጦር ኃይሎች አዛዥነቱ፣ ከጄነራሎቹ ጋር መደበኛ /Official/ በሆነ መንገድ ትውውቅ አላደረገም፤ እነዚህ ሶስት ጄነራሎችም ለዚህ አይነቱ የአሰራር መፋለስ ጥፋተኛ የሚያደርጉት አለቃቸውን ሳሞራ የኑስን ነው፤ ከምንጮቼ እንደሰማሁት ከሆነም ከወራት በፊት ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኘበት ‹ጎልፍ ክለብ› በሚባለው የጄነራሎቹ መዝናኛ በተዘጋጀ ፕሮግራም ማጠናቀቂያ ላይ ሳሞራ አንድ ጠረጴዛ ከበው ወደ
ተቀመጡት እነዚህ ጄነራሎች ጋ ሄዶ ‹ኑ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ላስተዋውቃችሁ› ማለቱን እና እነርሱም በጥያቄው ተበሳጭተው ቢሮ ያላቸው መሆኑን እና ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ መተዋወቅ እንደነበረባቸው በኃይለ ቃል መመለሳቸውን ነው)

የሳሞራ የኑስ እና ሰዓረ መኮንን መነቋቆር ከትግሉ ዘመን ጀምሮ የመጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ሳሞራ ከማንም በላይ የሚፎካከረውም ሆነ መበለጥ የማይፈልገው በሟቹ ጄነራል ኃየሎም አርአያ እንደ ነበር የቀድሞ ጓዶቻቸው ያስታውሳሉ፤ ይህ ሁኔታ ዛሬም ድረስ በስራ ላይ ያሉ መኮንኖችን ‹የሳሞራ› ወይም ‹የኃየሎም ተከታይ› በማለት መከፋፈሉ በጓዶቻቸው እና በፓርቲው መሪዎች አካባቢ የሚታወቅ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለማዕረግ እድገት የተለየ የድጋፍ አስተያየት የሚያገኙት በዛን ዘመን ‹የሳሞራ ተከታይ› የሚባሉት እየተመረጡ እንደነበረ በወሬ ደረጃ ይናፈሳል (በነገራችን ላይ ጄነራል ሳሞራ ከጤንነት ጋር በተያያዘ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጡረታ ይሰናበታል በተባለበት ጉዳይ ላይ እያንገራገረ እንደሆነ ከመከላከያ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፤ እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ ‹ለእኔ በጎ አመለካከት የላቸውም› በሚል የሚጠራጠራቸው ጄነራሎች በሥራ ላይ እያሉ የእሱ ጡረታ መውጣት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ያደሩ የሙስና ካርዶች የሚመዘዙበትን ዕድል ያሰፋዋል የሚል ነው፤ በተለይም በግዙፍ የቢዝነስ ሥራዎች ላይ በታላቅ ተፎካካሪነት እየተሳተፈ የሚገኘው ‹መቴክ› ምንም እንኳ ማረጋገጫዎች ባይቀርቡበትም በመከላከያ ሥር ከነበረበት ዘመን እስከ 2002 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ከግዥዎች ጋር ተያይዘው የሚነሱ በርካታ የሙስና ሁኔታዎች በመኖራቸው ነው፡፡
መቴክ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ በአዋጅ የልማት ድርጅት እንዲሆን ቢደረግም፣ ዛሬም ዳይሬክተሩ የሠራዊቱ አባል ብርጋዴር ጄነራል ክንፈ ሲሆን፣ መከላከያ ደሞዝ የሚከፍላቸው ጥቂት የማይባሉ ሠራተኞችንም እንዳቀፈ ይታወቃል፡፡ እናም ሳሞራ ሃሳቡ ከተሳካለት ለጥቂት ተጨማሪ ዓመታት በሥልጣኑ ላይ ሲቀጥል፣ አሊያም ‹የወንድ በር› ለማግኘት በትግሉ ዘመን የእርሱ ሰልጣኝ እንደነበረ የሚነገርለትን እና በቅርቡ ብቸኛው ከሜጀር ወደ ሌፍተናት ጄነራል ማዕረግ ያደገው ዮሀንስ ገ/መስቀል እንዲተካው መንገድ ጠረጋውን ማመቻቸቱ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ ይመስለኛል)
samora
ይህም ሆኖ የተኮረኮርን ያህል የምንስቀው ጄነራል ሳሞራ የኑስ በቅርቡ ለታተመው ‹‹ህብረ ብሔር›› መፅሄት ሙስና ለሠራዊቱ አደገኛ መሆኑን እንዲህ በማለት መግለፁን ስናነብ ነው፡-
‹‹ሙስና ሠራዊቱን ሊያበላሸው ይችላል፡፡ ሙስና ፀረ-ልማት ነው፤ ሠራዊቱን ሊበትነው እና ሕዝባዊ ባህሪውን እንዲያጠፋ ሊያደርገው ይችላል፤ አንድ ሠራዊት ሠራዊት ነው የሚባለው እንደ ወታደር እንደ አንድ አካል ሲያስብ እንጂ ለግሉ ሲያስብ አይደለም፡፡ …በአጠቃላይ (ሠራዊቱ) በዚህ ነው የሚፈርሰው፡፡››
መቼም ጄነራሉ ይህንን የተናገረው እራሱን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ እንግሊዝ ንጉሳውያን ቤተሰቦች በተንጣለለ ቪላ ቤት ውስጥ፣ የተቀማጠለ ኑሮ መኖራቸውን ረስቶት አይመስለኝም፤ ‹ይህ የተንዛዛ ወጪያቸውም የሚሸፈነው ከደሞዛቸው በሚያገኙት ገቢ ነው› ብሎ ቧልት መሳይ ክርክር ሊያመጣ አይችልም፡፡ ይሁንና እታች ያለው ጭቁን የኢትዮጵያ ሠራዊት ምንም እንኳ በአለቆቹ ‹ቴክሳስ›ነት ላይ ለመቆጣት ባይደፍርም፣ እንደማንኛውም ዜጋ ለኑሮ ውድነትና አስከፊ ድህነት የተጋለጠ መሆኑን መካድ አይቻልም፡፡
የሆነው ሆኖ ተሰሚነታቸው እየተቀዛቀዘ የመጣው አቦይ ስብሃት ነጋ ከወራት በፊት ለ‹‹ውራይና›› መፅሔት ‹‹ህወሓት ትንሳኤ ያስፈልገዋል›› በማለት የሰጡትን ምክር ተከትሎ፣ ጄነራል ሳሞራ እና አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ከድርጅቱ ምክትል ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ጋር በመተባበር ህወሓትን ለማጠናከር እና በፖለቲካ ውስጥ የነበረውን የአንበሳውን ድርሻ ለማስከበር (ጉዳዩን ከለጠጥነው ደግሞ ‹ለማስመለስ›) እየሰሩ እንደሆነ ይነገራል (በነገራችን ላይ የሳሞራና ጌታቸው ተፅእኖ መጨመሩን ለመረዳት፣ መከላከያ ‹አገራዊ ጥቅምንና ደህንነትን ለመከላከል› በሚል ‹እጅግ ጥብቅ ሚስጢር ብሎ የሰየማቸውን የሰው ኃይል ፕሮፋይል፣ የሒሳብ መዝገቦችና ሰነዶች እና የክፍያ ማስረጃዎች ለማንም አካል እንዳይገለፅ› የሚያስችለውን ስልጣን፣ ደህንነቱ ደግሞ በስራ ላይ የሚፈፅማቸው ማንኛውም ጉዳዮች ወደፊት በህግ እንዳይጠይቅ እስከ መከላከል የሚደርሰውን አዲስ የተዘጋጁትን አዋጆች ማንበቡ በቂ ነው፡፡ በርግጥ እነዚህ ባለሥልጣናት እንዲህ ባለ ተመሳሳይ መንገድ እንዲጓዙ ያስተሳሰራቸው አንዱ ጉዳይ ‹ህወሓት ተዳከመ፣ ተሸነፈ፣ አበቃለት…› የሚለው የካድሬውና ደጋፊው ቁጭት እንጂ ወትሮም መልካም ግንኙነት ኖሯቸው አይመስለኝም)

ለማንኛውም በጥቅሉ ሲታይ የህወሓት ትልቁ ችግር ተብሎ በአመራር አባላቱ የሚጠቀሰው ‹በዚህ ወቅት ወደፊት መምጣት የሚችሉ ጠንካራ ቴክኖክራቶችን አለማፍራቱ፣ ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግለትን የታጠቀውን ኃይል ተጠቅሞ የፖለቲካ ልዩነቱን ጨፍልቆ በአሸናፊነት ይዞት መውጣት የሚችል መሪ እንዳይኖረው አደረገ› የሚል ነው፡፡ በርካታ የላይኛ እና የታችኛው ካድሬዎችም ‹ለእንዲህ አይነቱ ክፉ ጊዜ ድርጅቱ የሚያስፈልገው፣ በትግሉ ዘመን ልምድ ያካበተ ታጋይ ብቻ ነው› የሚል አቋም እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ስርዓቱ ከሚያራምደው ርዕዮተ-ዓለም ጋር ጠንካራ ትውውቅ ያሌለውን እና የትግሉን ዘመን በአሜሪካን ሀገር በማሳለፉ ‹የምዕራባውያን ድጋፍ አለው› ለሚባለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚሰጡት ዝቅተኛ አመለካከት መግፍኤም ይኸው ይመስለኛል፡፡
ለነገሩ እርሱም ቢሆን በጠንካራ ድርጅታዊ ዲሲፕሊን ካለመታነፁ እና መሰል ጉዳዮች ጋር በሚያያዙ ምክንያቶች ለትንፋሽ ጊዜ የማይሰጠውን የድርጅት ሊቀ-መንበርነትንም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ የሚወራውን ያህል ይፈልገዋል ብሎ መደምደሙ አስቸጋሪ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ከዚህ ይልቅ በተፈጥሮ ከታደለው የተግባቢነት ባህሪው አኳያ እንደ ሕዝብ ግንኙነት የመሳሰለ ብዙም የማያጨናንቅ ሥራን ይመርጣል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከሰለጠነበት ሙያ ጋር የቀጥታ ተያያዥነት ያለውን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሚመራበት ዘመን፣ ከውጭ ሀገር በርካታ የተቋረጡ ፈንዶችን እንደገና ለማስለቀቅ መቻሉ እንደ ታላቅ ስኬት የሚወራለት፤ አልፎ ተርፎም ‹ወባን ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት ብርቱ ትግል አደረገ› ተብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሳይቀር እስከ መሸለም የደረሰው እዚህ መስሪያ ቤት እያለ እንደሆነም ይታወቃል፡፡

ትንቅንቅ

ትንቅንቅ


በሌላ በኩል ደግሞ በፓርቲውም ሆነ በመንግስት አስተዳደር ከህወሓት ሰዎች ትልቁን ስልጣን የያዘው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከምዕራባውያን ጋር የቆየ ቀረቤታ እንዳለው ሰምቻለሁ፤ እንደሚታወሰው ደብረፅዮን ከክፍፍሉ በፊት (የደህንነት መስሪያ ቤቱ እንዲህ እንደ ዛሬው እጅግ ዘመናዊ በሆነው የቻይና ቴክኖሎጂ ሳይጥለቀለቅ) ከነበረው ከፍተኛ የሥልጣን ቦታ ላይ ተነስቶ፣ ቁልቁል ወርዶ በሁመራ በአንድ ዞን እንዲሰራ የተመደበው (ሁላችንም ስንገምት እንደነበረው) የአንጃው አባል ወይም ደጋፊ ሆኖ አይደለም፤ ይልቁንም የእነስዬ-ተወልደ ቡድን በመባል የሚታወቀው (‹አፈንጋጩ› ኃይል) ደብረፅዮንን በሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድ ወኪልነት የመክሰሱ ጉዳይ የድርጅቱን በርካታ አባላት ቀልብ በመሳቡ፣ መለስ ይህንን ተከትሎ ከሚመጣበት አደጋ ራሱን ለመከላከል የወሰደው እርምጃ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት እስከ 1998 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በሁመራና ራያ አካባቢዎች በዞን ደረጃ ለማገልገል ተገዷል፡፡ እናም እርሱን የምዕራቡ ዓለም ፊት-አውራሪ አሜሪካና ሸሪኮቿ ወዳጅ ነው የሚያስብለው በቀድሞ መስሪያ ቤቱ በኩል በነበረው ግንኙነት ይመስለኛል።

የፖለቲካውን መዘውር የጨበጠው ኃይል

የዚህ ቡድን አምበል እንደ ድርጅት ብአዴን ቢሆንም፣ በቋሚ ተሰላፊነት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ሙክታር ከድር እና ሬድዋን ሁሴን እንደሚገኙበት ይነገራል፤ ለብአዴን ‹በተሻለ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ለመገኘቱ መደላድል ፈጥሮለታል› የሚለውን ሙግት ምክንያታዊ የሚያደርገው ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ በረከት ስምዖን፣ የኢህአዴግን የካድሬ ማሰልጠኛ ማዕከል በዳይሬክተርነት የሚመራው አዲሱ ለገሰ፣ ደርቦ ይዞት የነበረውን የትምህርት ሚኒስትርነት ለሽፈራው ደሳለኝ በመልቀቅ፣ በአሁኑ ወቅት ሙሉ የስራ ጊዜውን በግንባሩ ፅ/ቤት የሚያውለው ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤው ካሳ ተክለብርሃን የያዙት ሥልጣን ያለውን የፖለቲካ አቅም መመዘኑ ይመስለኛል፡፡ በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥም ከሳሞራ አንድ እርከን ዝቅ ባለ ሥልጣን ከሌሎች ሁለት ጄነራሎች ጋር የሚገኘው አበባው ታደሰ እንደ ቀድሞው በዕዝ አዛዥነቱ (በቀጥታ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማንቀሳቀስ የሚችልበት) ላይ ቢሆን ኖሮ ጥንካሬውን የተሟላ ማድረጉ አይቀሬ እንደነበረ መገመት ይቻላል፡፡

ከዚህ ሌላ ለእነበረከት ቡድን ተጨማሪ የፖለቲካ ጉልበት እየሆናቸው ያለው የኃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ እና በአባዱላ ገመዳ አፈ-ጉባኤነት የሚመራው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው፡፡ አባዱላ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ለማቅረብም ሆነ ለመታዘዝ ፍቃደኛ ያልሆኑ አንዳንድ ባለስልጣናት፣ በውስጥ መስመር በሚተላለፍለት ‹ጥቅሻ› በምክር ቤቱ በኩል የሚመለከተው የቋሚ ኮሚቴ አባላት አስጠርቶ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚገመግምበት ስልት እየተገበረ ነው፡፡ በአናቱም ምን ጊዜም የሳምንቱን የሥራ መጨረሻ ቀን አርብን ጠብቆ የሚሰበሰበው የሚኒስትሮች ም/ቤትን ከሞላ ጎደል ይህ ቡድን እየጠቀመበት ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ሚኒስትሮቹ በሚገናኙበት አብዛኛውን ሰዓት ሳይግባቡ (በጭቅጭቅ) ማሳለፋቸው ይነገራል፤ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በአቶ መለስ ዘመን ም/ቤቱ የሚሰበሰበው የተለያዩ አጀንዳዎችን ለማቅረብ እና በቀረበው አጀንዳ ላይ ለመከራከር (ለመመካከር) ሳይሆን፣ መለስ ወስኖ የመጣበትን የሥራ ድርሻ ተቀብሎ ለመበተንና ሪፖርት ለመስማት የነበረው አሰራር፣ ዛሬ ተቀይሮ በርካታ የተነቃቁ ሚኒስትሮች የየራሳቸው ሃሳብ ተቀባይነት እንዲያገኝ (ለማንፀባረቅ) የሚታገሉበት መድረክ ወደ መሆን በመሸጋገሩ ነው፡፡ ይህም ሁናቴ ዋናውን የመንግስት ሥራ የመገምገም እና የማስፈፀም አቅምን ሳይቀር ከሚኒስትሮች ም/ቤት ወደ ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አሻግሮታል የሚያስብሉ ማሳያዎች አሉ፡፡ ይሁንና በዚህስብሰባ ላይም ቢሆን ደፈር ብሎ ከበረከት ስምዖን እና አባይ ፀሀዬ የተሻለ አዳዲስ ሃሳብ የሚያቀርብ ባለሥልጣን እንደሌለ ሰምቻለሁ (በነገራችን ላይ ምክንያቱን ባላውቅም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ› ተደርገው የተሾሙት በረከት ስምዖን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ኩማ ደመቅሳ እና ዶ/ር ካሱ ኢላላ የሥራ ቦታቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ሳይሆን መገናኛ አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንፃ ላይ ነው፡፡ የተሰጣቸው ኃላፊነት ኃይለማርያምን በቅርብ እንዲያገኙ ከማስገደዱ እና በግልፅ ከሚታወቀው የአማካሪ አስፈላጊነት አኳያ ካየነው ግን ግራ የሚያጋባ ይመስለኛል)

አቶ አባይ ጸሐዬ

አቶ አባይ ጸሐዬ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ…

ኃይለማርያም ደሳለኝ ይህንን ቦታ ከያዘ በኋላ፣ ብዙዎች በስልጣኑ የማዘዝ አቅሙ ላይ አመኔታ እንደሌላቸው (አንጋፋ ታጋዮች እንደ ‹አሻንጉሊት› ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ) ደጋግመው መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ በግልባጩ ‹አፈንግጦ ለመውጣት መሞከሩ አይቀሬ ነው› የሚሉ ግምቶች ነበሩ፡፡ በርግጥ እነዚህ መላ-ምቶች ዛሬም ድረስ እልባት ባያገኙም፣ እዚህ ጋ ያልጠቀስኳቸው አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ያሳያቸው ወጣ ያሉ አቋሞቹን ሳስተውል ግን፣ አሁን ያለው አሰላለፍ (የአነበረከት እና አባዱላ ፖለቲካዊ መጠናከር) ለእርሱም የተረፈው ይመስለኛል፡፡ እንዲሁም ከቤንች ማጂ የተባረሩ አማርኛ ተናጋሪዎችን አስመልክቶ በድርጅቱ ውስጥ ባልተለመደ መልኩ ‹አጥፊዎቹ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ› ከማለት አንስቶ (በነገራችን ላይ በአማካሪ ብዛት እንዲከበብ ካደረገው ምክንያት አንዱ ጓዶቹ በዚህ ንግግሩ መበሳጨታቸው ነው) በቅርቡ ህወሓትን ለመሸምገል በተዘጋጀ መድረክ ላይ ‹ሁኔታዎች እንዲህ እየተካረሩ ከሄዱ ወደ ማሰሩ መግባታችን አይቀርም› በማለት ማስፈራራቱ እና በቴዎድሮስ አድህኖም የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ የመቆጣቱ ጉዳይ ድረስ የሚካተቱ እውነታዎች ሰውየው የራሱን መንገድ ለመከተል እየሞከረ መሆኑን ያሳያሉ ብዬ አስባለሁ፡፡

የሆነው ሆኖ እነዚህ ሁናቴዎች የፖለቲካውን ጉልበት ሙሉ በሙሉ በብአዴንና በተባባሪነት በጠቀስኳቸው የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት አካባቢ ቢያከማቻቸውም፣ በማንኛውም ሰዓት ያሻውን ማድረግ የሚችለው የታጠቀው ኃይል ደግሞ ከህወሓት ጎን እንደተሰለፈ ይገኛል፡፡ መጪውን ጊዜም አዲስ ክስተት እንድንጠብቅ ገፊ ምክንያት ይህ አይነቱ የኃይል አሰላለፍ ይመስለኛል፡፡

ምን እንጠብቅ?

ከረጅሙ የፓርቲ ፖለቲካና መንግስታዊ መንገራገጮች በኋላ፣ የሁለቱንም የኃይል መሰረቶች ጠቅልሎ በመዳፉ ሥር የከተተው መለስ ዜናዊ በሞተ ማግስት ‹የኃይል መገዳደሮች ሊከሰቱ ይችላሉ› የሚለው የብዙዎቹ ግምት ነበር፤ ከወራት በፊት አስነብቤ በነበረው ከላይ በተጠቀሰው ፅሁፍም ግምቶቹ እውን መሆን እንደ ጀመሩ ማሳያዎች ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ ራሳቸውን ያቧደኑት ኃይሎች ዋነኛ ግብ ከሥልጣን የሚነሱ ጥቅሞችና አነስተኛ የየራሳቸው ፓርቲ ፍላጎቶች የፈጠሩት በመሆኑ፣ እንደ ሟቹ ደመ-ቀዝቃዛ አምባገነን አይነት በጠንካራ መዳፍ ሥር የሚያሰባስባቸው ባለመገኘቱ በየጊዜው የኃይል መሸጋሸጎች ሊከሰቱ እንዲችሉ አድርጓቸዋል፤ አሁንም እየተስተዋለ ያለው ይኸው እውነታ ነው፡፡ በዚህ አውድ ላይ ቆመን ሊፈጠሩ የሚችሉ የቢሆን ሃሳቦችን ስናስቀምጥም በጠረጴዛው ላይ የምናገኘው ሁለት ዕድሎችን ይመስለኛል፡፡

የመጀመሪያ ሲናሪዮ የሚሆነው ከላይ የጠቀስኩት ቡድንተኝነት እንዳለ ሊቀጥል ይችላል የሚል ነው፤ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ባለኝ መረጃዎች መሰረት የፖለቲካውን መስመር የያዘው ቡድን መሪ አባላት፣ አሁን ያላቸውን መንግስታዊ ሥልጣን ጠብቀው መቆየትን መሰረታዊ መሰባሰቢያ አጀንዳ ማድረጋቸው ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሳሞራና ጌታቸው ጥምረት ህወሓትን ወደ ቀደመው ዘመኑ ለመመለስ ቢሻም፣ ሊሄድበት የሚችልበት መንገድ አደገኛ መሆኑ (ወታደራዊ ላዕላይ መዋቅሩንና የደህንነት ኃይሉን ከመያዙ አኳያ) ሁኔታዎችን ባሉበት ይዞ መቀጠልን በትርፍ-ኪሳራ ስሌት የተሻለ አማራጭ አድርጎ ይወስደዋል ብዬ አስባለሁ፡፡
ሁለተኛው የቢሆን ዕድል፣ ዳግመኛ የኃይል መሸጋሸግ ሊፈጠር መቻሉ ነው፤ ሰዎቹ ጥቅመኛ በመሆናቸው የቋንቋ ተናጋሪነት ልዩነቶቻቸውንና የኋላ የመቆራቆስ ታሪኮቻቸውን ተሻግረው፣ አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር ሌላ መልክ ያለው ስብስብ ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆናል፤ ይህ አይነቱ አዲስ የኃይል አሰላለፍም፣ ከቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በፊት በማይታወቀው ተሰዊና ሰዊ ሊጠናቀቅም ይችላል፡፡
በመጨረሻም ምንም ይፈጠር ምን፤ እኛን ሊያግባባን የሚገባው ጭብጥ፣ የትኛውም ቡድን በግንባሩ ውስጥ ቢነሳ፣ የማዕከላዊ መንግስቱን ህልውና ወደሚበታትን ሂደት መግባቱ ሊሰካለት አለመቻሉ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ መልኩ ሄዶ የሚጣሉበትን ጠረጴዛ መስበሩ ምን እንደሚያስከትል ያውቁታልና ወደዚህ ምዕራፍ እንደማይሻገሩ አምናለሁ፡፡ ይሁንና ከፓርቲው ዝግነት እና ከፖለቲከኞቹ አቋም የለሽነት አንፃር አሁንም ሆነ በቀጣይ ጊዜያት ከማንም ግምት ውጪ ያሉ ክስተቶች እንደ ደራሽ ውሃ ድንገት ሳይታሰብ ግንባሩን ሊያተራምሱት ይችላሉ ብሎ መገመቱ አግባብ ይመስለኛል፡፡

ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ጻፉ

$
0
0
ክንፉአሰፋ

New book by Fkreselase Wegderesፀሃይ አሳታሚ ድርጅት በታኅሣሥ 16, 2006 ዓ/ም (Dec. 25, 2013)  የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስን ‘እኛና አብዮቱ’ የሚል መጽሃፍ  ለገበያ እንደሚያበቃ አስታወቀ። ሻምበል ፍቅረሥላሴ እንደ ደርግ አባልነታቸው በጋራ ያመኑበትን፣ የተማከሩትን፣ የወሰኑትን፣ የሰሩትን፣ የገጠማቸውንና በቅርብ በዓይን ምስክርነት ያዩትን ተንትነው በ‘እኛና አብዮቱ’ ያስነብቡናል። የራሳቸውን ዕይታ ያካፍሉናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመካከለኛው አፍሪቃ ሪፐብሊክ ቀውስ

$
0
0
የተቀሰቀሰው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ካልተደረገ ሀገሪቱ ወደ አስከፊ የእርስ በእርስ ጦርነት ልታመራ የምትችል መሆኑን በርካታ የዓለም ዓቀፍ የሠብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችና የመንግሥታቱ ድርጅት ጽ/ቤት በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው።…

ቤት የፈረሰባቸው አባወራዎች ቅሬታ

$
0
0
በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ በመድሐኔዓለም ቤተክርስትያን ጀርባ ቤቶችና የመንገድ ሱቆች እየፈረሱ በመሆኑ ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎች በቂ ጊዜ ሳይሰጠን ተፈናቀልን ሲሉ ያማርራሉ።…

የትምባሆ ፍላጎት መቀነስና የአቅርቦት ቁጥጥር ሥርዓት አገራት እንዲዘረጉ የሚያስገድደውን ዓለምአቀፉ የትምባሆ ቁጥጥር ኮንቬንሽን ረቂቅ አዋጅ በፓርላማ ሊጸድቅ ነው፡፡

$
0
0

፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ /  ኢሳት ዜና :- ፓርላማው እ.ኤ.አ በ2003 በጄኔቭ የወጣው ኣለምአቀፍ የጤና ድርጅት የትምባሆ ቁጥጥር ኢትዮጽያ ፈራሚ አገር የነበረች ሲሆን ይህንን ለማጽደቅ ረቂቅ ሕግ በዛሬው ዕለት ለፓርላማው ቀርቦለት በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በሃላ ለሚመለከተው ኮሚቴ መርቶታል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ላይ በኢትዮጽያ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል 8በመቶ ያህሉ የትምባሆ ምርቶችን እንደሚጠቀሙ ጥናቶችን ጠቅሶ አስቀምጧል፡፡ በተጨማሪም ወደ 41 በመቶ ያህል ወጣቶች ደግሞ ትምባሆ በሚጨስበት አካባቢ ውስጥ የሚያዘውትሩ በመሆናቸው ለጤና ችግሮች ተጋላጭ መሆናቸውን ይጠቁማል፡፡ ይህ ኮንቬንሽን ኢትዮጽያ መቀበልዋ በተለይ ከትምባሆ ጋር በቀጥታ የተያያዙ የጤናና ማህበራዊ ቀውሶችን ለመታደግ ያስችላል ተብሎአል፡፡

ኮንቬሽኑ የትምባሆ ቁጥጥር ስትራቴጂዎች በዋንኛነት የትምባሆ ፍላጎትን እና አቅርቦትን ላይ ያነጣጠሩ እንዲሆኑ ያስገድዳል፡፡ በኮንቬሽኑ ክፍል ሶስት ደግሞ የተለየ የፍላጎት መቀነሻ ዘዴዎች ማለትም የዋጋና የግብር እንዲሁም ዋጋ ነክ ያልሆኑ የትምባሆ መቀነሻ ስልቶች እንዲተገበሩ ያዛል፡፡

ይህ ኮንቬንሽን በተለይ ሲጋራና የሲጋራ ውጤቶችን በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች፣ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች፣በምግብ ቤቶች፣በት/ቤቶችና በመመሳሰሉት ስፍራዎች መጠቀም ስለሚከለክል ኢትዮጽያም ይህን ተግባራዊ እንደምታደርግ ይጠበቃል፡፡

70 ድርጅቶች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተከሰሱ

$
0
0

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ፋና እንደዘገበው በአዲስ አበባ በግሉ ዘርፍ ከተሰማሩ 470 ቀጣሪ ድርጅቶች መካከል 70 ዎቹ ሰዎችን በህወጥ መንገድ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን ያዘዋውራሉ ተብሎ ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የሰራተኛና የማህበራዊ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት ኤፍሬም ግዛው ፣ በድርጅቶች ላይ ክስ ለመመስረት አስፈላጊው መረጃ ሁሉ ተሰብስቧል።

የአዲስ አበባ መስተዳድር በበኩሉ እርምጃው በሌሎች ድርጅቶችም ላይ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ታገዱ የተባሉት ድርጅቶች በስም አልተጠቀሱም። አስተያየቱን የተጠየቀው የአዲስ አበባው ዘጋቢ መንግስት በሳውድ አረቢያ የተከሰተውን ችግር ተከትሎ እርምጃ እየወሰደ ቢመስልም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ በ70 ድርጅቶች ላይ ምርመራ አድርጎና ማስረጃ ሰብስቦ ለመጨረስ የሚችል አይመስለኝም ብሎአል።  የገዢው ፓርቲ ኩባንያዎች የማይፈልጉዋቸውን ድርጅቶች ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ እንዲህ አይነቱን ዘዴ ሊጠቀሙ እንደሚችልም ያለውን ስጋት ገልጿል። 

ኦብነግ ከመንግስት ሀይሎች ጋር መዋጋቱ ተዘገበ

$
0
0

፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ /  ኢሳት ዜና :- ኦጋዴን ፕሬስ እንደዘገበው የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ከመከላከያ ሰራዊት እና ከልዩ ሚሊሺያዎች ጋር ባደረገው የተኩስ ልውውጥ 70 የኢትዮጵያ ወታደሮች እንደተገደሉ በእርሱ ወገንም የተወሰኑ ታጣቂዎች እንደሞቱ ገልጿል። እንደ ጋዜጣው ዘገባ 3  የመንግስት ወታደራዊ አዛዦችም ተገድለዋል። መንግስት አስተያየተቱን ባይሰጥም ልዩ ሚሊሺያ የሚባለው ሀይል የኦብነግን ወታደራዊ አዛዥ መግደሉን ለጋዜጣው እንደገለጹለት ተዘግቧል። በደጋሀቡር፣ ኮራሄና ፊክ ዞኖች በርካታ ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውም ተዘግቧል።

በአካባቢው ስላለው ግጭት የአለማቀፍም የመገናኛ ብዙሀንም ሆነ የሲቪክ ድርጅቶች ተንቀሳቅሰው መዘገብ አይችሉም። በክልልሉ ውስጥ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ መሆኑ ይታወቃል።

መንግስት በቅርቡ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን በክልሉ ማክበሩ ይታወቃል።

ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤቱን እንዲለቅ ትእዛዝና ማስጠንቀቂያ ተሰጠው::‪

$
0
0

፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ /  ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ ግንፍሌ አከባቢ የሚገኘውን እና በጽ/ቤትነት የሚጠቀምበትን ቢሮ  በአስቸኳይ እንዲለቅ  ትዕዛዝ ደረሰው።

በዛሬው እለት ከሰኣት  በኋላ አቶ ሄኖክ የተባሉ አከራዩ ከአራት ግለሰቦች ጋር በመምጣት ፦”ቤቱን ለነዚህ ግለሰቦች ስለሸጥኩላቸው እንድትለቁላቸው” ሲሉ ከውል ውጪ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

ቤቱን ገዛሁት የሚለው  ግለሰብ በበኩሉ፦”ቤቱን የኔ  ስለሆነ በአስቸኳይ እንድትለቁልኝ፣ ካልሆነ የራሴን እርምጃ እወስዳለሁ” ሲል አመራሮቹ ላይ ዝቷል::

ይህ ግለሰብ በማይመለከተው ጉዳይ በመግባት፦” ከዚህ በፊትም ልቀቁ ተብላችሁ በተደጋጋሚ እንደተነገራችሁ መረጃው አለኝ፤ በቶሎ የማትለቁ ከሆነ እርምጃ ይወሰድባችሁዋል” በማለት በአመራሮቹ ላይ ቁጣ የተቀላቀለበት ዛቻ በመዛት ሄዷል:;

ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ቀደም በመነን አከባቢ ተከራይቶት የነበረውን ጽ/ቤት ገና ሳይገባበት በዝግጅት ላይ እንዳለ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና እና ቅጥረኞች በተቀናጀ አፈናና ሀይል የተቀላቀለበት እርምጃ ቢሮውን እንዳስለቀቁት ይታወቃል::

ቀደም ሲል ከሰማያዊ ፓርቲ የተነጠቀውን ቢሮ  የወሰደው ካድሬም፤ ፔንሲዎን ከፍቶ እየነገደበት እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ ፓርቲያቸውን በውጪ አገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በማስተዋወቅ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

Viewing all 13695 articles
Browse latest View live


Latest Images

<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>