ነብዩሲራክ
ትናንት እንደ ቀልድ ...
በያዝነው የፈረንጆች 2013 ዓም በወርሃ መጋቢት አጋማሽ የሳውዲ አረቢያ መንግስት " ህጋዊ ሰነድ ያልያዙትን አስወጣለሁ !" ብላ አወ ች ። ቀጠለና አፈሳ አሰሳው ተከተለ! አስፈሪው ያ ክፉ የጭንቅ ቀን በሳውዲው ንጉስ ሌላ የምህረት አዋጅ ተተክቶ ህገ ወጥ የተባሉትን ህጋዊ በሚያደርግ ህግ ተተካና የምህረቱ አዋጅ በያዝነው ህዳር መባቻ እንደሚያልቅ በተጠቆመው አዲስ የምህረት አዋጅ ተተካ !