የአንድነት ፓርቲ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ላይ እየሆነ ያለው፣ ሕዝብ በይፋ እንዲያወቀው መደረግ አለበት ሲል፣ ለአማራዉ ክልል አስተዳዳሪ ደብዳቤ አስገባ። ፓርቲዉ የአገርን ሉዓላዊነት በተመለከተ በሚደረጉ እንቅስቅቅሴዎች ዙሪያ፣ በሌሎች የዉጭ ሜዲያዎች በስፋት እየተነገረ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ግን መደበቁ ትልቅ ችግር እንደሚፈጠር በማሳሰብ፣ ጉዳዩ በአስቸኳይ ምላሽ እንዲያገኝና ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ አሳስቧል።
ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለበት መልኩ በሚስጠር የሚደረግ ማናቸውም ስምምነቶች፣ ወደፊት ትልቅ ጣጣ እንዲሚያመጡ የገለጸዉ የአንድነት ደብዳቤ፣ «እያንዳንዱ ዉሳኔ በፍጹም ከሕዝብ ሊሸሸግ የማይገባ በመሆኑ ለሕዝብ ግልጽ እንዲሆን እየጠየቅን፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ማናቸዉም ችግር ተጠያቂዉ የፌደራልና የክልል መንግስት መሆአንቸውን ማሳወቅ እንወዳለን» ሲል ማስጠንቀቂያዉን አካቷል።
የአንድነት ፓርቲ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ዙሪያ ከሕዝብ ጋር ዉይይት የሚያደርግ ሲሆን ፣ አዲሱ የአንድነት አመራ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶት እንደሚከታተለዉም ለማወቅ ተችሏል።