Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

መንግስት ስለምን በሐይማኖት ጉዳዬች ጣልቃ ይገባል?

$
0
0

ከቴዎድሮስ ጌታቸው
በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በሐይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ እንደሚገባ የተለያዩ እምነት በሚከተሉ ግለሰቦች እና ቡድኖች ሲከሰስ እና ሲወቀስ መኖሩ እውነት ነው። በርግጥ እገዛዙ በሐይማኖት ጉዳዬች እጁን ብቻ ሳይሆን እግሩንም ሊያስገባ እንደሚችል ከባህሪው በመነሳት መገመት ብዙም የሚከብድ አይደለም ። ከሞላ ጎደልም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ሐይማኖቶች ውስጥ በመግባት ገብቶም በመቆጣጠር ተቆጣጥሮም ወደ ፈለገው አቅጣጫ እየነዳ ወይም ለመንዳት እየሞከረ ለመሆኑ ከራሳቸው ከአማኞቹ ጀምሮ የራሱ የመንግስት እንቅስቃሴ ብዙ ጠቌሚ ነገሮች ማየት ይቻላል።
የሐይማኖት ነጻነት ተከብራል መንግስትና ሐይማኖት አልጋ ለይተዋል እያለ በተገኝው አጋጣሚ የሚነዘንዘን መንግስት በምን ምክንያት ነው ታዲያ በሐይማኖት ጉዳዮች ላይ ብቅ ጥልቅ ያበዛው ለሚሉ ጥያቄዎች መልሳቸው ብዙም አወዛጋቢ አይደለም አወዛጋቢው ጉዳይ ይሄንን ጣልቃ ገብነት በምን አይነት መንገድ ነው ማቆም የሚቻለው ወይም እንዴት ይፈታል የሚለው ነጥብ ነው።
ኢትዮጵያ ከሶስቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች ጋር ታሪካዊ ትስስር ያላት ሐገር ስትሆን ሃይማኖቶቹ በበኩላቸው ደግሞ የራሳቸው አስገራሚ የእርስ በእርስ ግንኙነት ይዘዋል፤ ለብዙ ዘመናትም ሐይማኖቶቹ ጐን ለጐን በሰላም ለመኖር እንደቻሉ ብዙ ተብሏል ተጽፎዋል፤ ሌሎች ሐገሮች ጋር የሌሉ ወይም የማይታሰቡ ትስስሮች ነበሩን አሉንም መሐመድ ሰልማን «ሼ-መንደፈር በመርካቶ» በሚለው መጣጥፉ ከነዚህ ልዩ ትስስሮች ውስጥ አንዱን እንዲህ ሲል በሚገርም ምልከታው ገልጾታል
«…….በአንዋር መስጊድ እና በቅዱስ ራጉዔል ቤተክርስቲያን አጥሮች መካከል ያለው ርቀት አንድ መኪናን ብቻ ማሳለፍ የሚያስችል ነው። በእነዚህ የአምልኮ ስፍራዎች የሚገኘው ሕዝብ ደግሞ አጥሮቹን አልፎ የሚፈስ ነው። በመኾኑም ምዕመናኑ በዐቢይ የጸሎት ወቅቶች በዙርያቸው የሚገኙትን የተሽከርካሪ ጎዳናዎችን ለመጠቀም ይገደዳሉ፡፡
በተለይም አንዋር መስጊድ በረመዳን የጁምዐ ስግደት የምዕመናኑ ቁ|ጥር በአራት እና አምስት እጥፍ ስለሚጨምር የመርካቶን ሲሶ በጸሎት ስፍራነት ለመጠቀም ይገደዳል፡፡ በደቡብ በኩል እስከ “ሲኒማ ራስ”፣ በምዕራብ እስከ “ጣና ገበያ” አንዳንዴም እስከ “ምዕራብ ሆቴል”፣ በሰሜን እስከ “ጎጃም በረንዳ” እንዲሁም በምሥራቅ እስከ አሜሪካን ግቢ ድረስ ይዘልቃል፡፡ ይህ ኹኔታ ከሚፈጥራቸው አስገራሚ ትዕይንቶች አንዱ ሰጋጆቹ የራጉዔልን ዙርያ አጥር ለመጠቀም መገደዳቸው ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ነጠላ እና አባያ፣ ጥምጣም እና ጀለቢያ ባይፈቅዱትም ትከሻ ለትከሻ፣ መሳ ለመሳ ለመቆም ይገደዳሉ፡፡
ዘወትር ምሽት በረመዳን ወር የሚሰገደው የ‹‹ተራዊህ›› ስግደት ዘለግ ያለ ሰዓትን ይወስዳል፡፡ አማኞች መኪናዎቻቸውን በሁለቱም የእምነት ስፍራዎች ዙርያ እየኮለኮሉ ያቆሟቸዋል፡፡ ሶላት ሲሰግዱም የራጉዔልን አጥር ተደግፈው ጭምር ነው፡፡ መስገጃዎቻቸው የራጉዔልን ሕንፃ በረንዳዎች ጭምር አካሎ ይይዛል፡፡ ዘወትር ምሽት ይህንን አስገራሚ ክስተት ባስተዋልኹ ቁጥር በካሜራ ቀርጾ ለማስቀረት ይዳዳኛል፤ ተሳክቶልኝ ባያውቅም።
የጁምዐ ስግደት ላይ ሃይማኖታዊ ዲስኩር (ኹጥባ) በአሰጋጁ (ኢማሙ) አማካኝነት ይቀርባል። አንዳንድ ጊዜ በተመሳሳይ ከራጉዔል የቅዳሴ ዜማ ይለቀቃል፡፡ ከሁለቱም ጎረቤት የእምነት ስፍራዎች በድምፅ ማጉያ የሚስተጋቡት ድምፆች እርስ በርስ ስለሚራበሹ ምእመናኑ ሁለቱንም ከማዳመጥ ውጭ ምርጫ ያጣሉ። ከሁለቱም ጎራ ያሉ አማኞች ይህ ኹኔታ የሚፈጥርባቸውን እውነተኛ ስሜት ባላውቅም ለእኔ ግን ትርጉሙ የትየለሌ ይኾንብኛል፡፡ በዐረብኛ እና በግዕዝ ወደ አምላክ የሚተላለፉ ተማጽኖዎች፡፡
የቅዱስ ራጉዔል ቤተክርስቲያን እንደ ብዙዎቹ አቻዎቹ አጥሩን አስታኮ ያስገነባው ግዙፍ ሕንፃ ፎቁ ለደብረ ኀይል ቅዱሰ ራጉዔል ትምህርት ቤትነት ሲያገለግል ምድሩ ላይ ያሉት ቤቶች ደግሞ የንግድ ቤት ኾነው ያገለግላሉ። በእነዚህ ሱቆች በአመዛኙ የሞባይል መለዋወጫዎች፣ በስተ ምዕራብ ባሉት ሱቆች ሻንጣ እና ብርድ ልብስ፣ ኦርቶዶክስ ዘ-ተዋህዶ መዝሙር ቤቶች እና በስተ ምሥራቅ ባሉት ሱቆቹ ደግሞ ኢስላማዊ ቁሳቁሶች የሚሸጡባቸው ናቸው፡፡ በዚሁ ሕንፃ ላይ የሚገኘው ዘመናዊው “ሄኒ-ፔኒ ካፌ” ለረመዳን ኢስላማዊ ምግብ እና መጠጦችን ያቀርባል፡፡ ይህ የቅዱስ ራጉዔል ሕንፃ የአርክቴክት ዲዛይኑ የመስቀል ቅርጽ እንዲኖረው ተደርጎ የተሠራ ነው። ኾኖም በሥሩ ከሚገኙት ሱቆች ውስጥ አባያ ( ሙስሊም ሴቶች የሚለብሱት ቀሚስ)፣ ኒቃብ (ፊትን በከፊል የሚሸፍን)፣ ሂጃብ (ጸጉርን የሚሸፍን)፣ ቡርቃ (ከዐይን በስተቀር መላ ሰውነትን የሚሸፍን) እንዲሁም ጀለቢያ እና መስገጃዎች ይሸጡበታል፡፡ ይህ ኹነት ለአንዳንዶች ከቢዝነስ ፍልስፍና ከፍ ያላለ ትርጉም ሊኾን ይችላል፡፡ ለእኔ ግን ከዚያም የላቀ ትርጉም አለው።
ድህነታችን እና ባህላችን ተጋግዘው የፈጠሩት ጥብቅ ጉርብትና ማኅበራዊ ሕይወታችንን ይጫኑታል፡፡ ይህ ኹኔታ በሃይማኖት መሥመሮችም የሚገለጥበት ጊዜ አለ። እናቴ እነ መምሬ ቤት ጠበል ቅመሱ ሲባል ከመሄድ አትቦዝንም። ከክርስቲያን አብሮ አደጎቼ ጋራ የነበረን ወዳጅነት አንድ ጊዜም ቢኾን በሃይማኖት ስሜት የተቀኘበት ወቅት ትዝ አይለኝም። አንዳንድ ጓደኞቼ አሁንም ድረስ የኢስላም አቡጊዳ የኾኑትን የዐረብኛ ፊደላትን እና ጥቂት የቁርዐን አንቀጾችን በቃላቸው ማነብነብ እንደሚችሉ አስተውያለኹ፤ እንደ እኔ ከሙስሊም ቤተሰብ ለወጡ ብዙ ዜጎች ቄስ ትምህርት ቤት ሙዋዕለ-ሕፃናት እንጂ የክርስትያን ተቋም ኾኖ ተሰምቶን አያውቅም………..» ይለናል
Lalibela Lalibela the famous and ancient for its churches

bilall
Negash Mosque (Ancient Mosque in Ethiopia)

ይሁንና አገዛዙ እነዚህንና እነዚህን መሰል ልዩ ግንኙነቶች በከፋፈለህ ግዛው የተለመደ የአንባገነኖች መመሪያ በማዳከም ሃይማኖቶቹን ወደ ባላንጣነት የመቀየር ፍላጐት በመያዙ እነዚህ እሴቶች ቀስ በቀስ በመሸርሸርና በመደብዘዝ ላይ ይገኛሉ።
ሲጀመር በተለያየ እምነቶች መካከል ያለውን ልዩነት በማክረር እርስ በእርሳቸው እንዲጠባበቁ ብሎም በጠላትነት እንዲተያዩ በማድረግ ሐይላቸው እላያቸው ላይ ቁጭ ብሎ የሚጫናቸው አገዛዝን ለመቌቌም ከመጠቀም ይልቅ ከጎናቸው ካለው የሌላ ሃይማኖት ድርጅት ጋር ላለው ሽኩቻ ላይ በማድረግ ያላቸውን ጉልበትና ግዜ በዚሁ ተግባር ላይ ያባክናሉ ይሄንን ሁኔታ አገዛዙ በፈገግታ አየተመለከተ ሲረግብ አየወጠረ ሲቀዘቅዝ እያሞቀ ትኩረታቸውን ሙሉ ለሙሉ ወደሱ እንዳይዞር የማድረግ ሚናውን ያለማቋረጥ ይጫወታል፤ይሄንን የመንግስት ተግባር አውቀው በእውቀት ሳያውቁ በድፍረት የሚተባበሩ የሐይማኖት ተከታዮች የመንግስት ባለ ውለታዎች ናቸው።
ሌሎቹ ደሞ መንግስትን በመሞዳሞድ አገዛዙ ወደነሱ በገንዘብም ፤በድጋፍም፤ በመደገፍም ለመሳብ የሚያደርጉት ጥረት የሚሳካው የሐይማኖት ነጻነታቸውን ለመንግስት አስረክበው የተባሉትን እያደረጉ የሚቀጥሉ ሎሌዎች እስከሆኑበት ግዜ ድረስ ብቻ ነው።
የሃይማኖትና የእምነት ነጻነትን በተመለከተ ዊኪፒዲያ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፦
“Freedom of religion or Freedom of belief is a principle that supports the freedom of an individual or community, in public or private, to manifest religion or belief inteaching, practice, worship, and observance; the concept is generally recognized also to include the freedom to change religion or not to follow any religion.[1] The freedom to leave or discontinue membership in a religion or religious group —in religious terms called “apostasy” — is also a fundamental part of religious freedom, covered by Article 18 of the Universal Declaration of Human Rights. Freedom of religion is considered by many people and nations to be a fundamental human right. In a country with a state religion, freedom of religion is generally considered to mean that the government permits religious practices of other sects besides the state religion, and does not persecute believers in other faiths.”

በስራ ላይ ያለውም የሃገሪቱ ህገመንግስት ደግሞ በአንቀጽ 27 ስለ ሃይማኖት ነጻነት የሚከተለውን ይላል Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia Article 27
“Freedom of Religion, Belief and Opinion
1. Everyone has the right to freedom of thought, conscience and religion. This right shall include the freedom to hold or to adopt a religion or belief of his choice, and the freedom, either individually or in community with others, and in public or private, to manifest his religion or belief in worship, observance, practice and teaching.
2. Without prejudice to the provisions of sub-Article 2 of Article 90, believers may establish institutions of religious education and administration in order to propagate and organize their religion.
3. No one shall be subject to coercion or other means which would restrict or prevent his freedom to hold a belief of his choice.
4. Parents and legal guardians have the right to bring up their children ensuring their religious and moral education in conformity with their own convictions.
5. Freedom to express or manifest one’s religion or belief may be subject only to such limitations as are prescribed by law and are necessary to protect public safety, peace, health, education, public morality or the fundamental rights and freedoms of others, and to ensure the independence of the state from religion.”
በራሱ በስልጣን ላይ ባለው መንግስት የተጻፈው ህገመንግስቱ ስለ ሃይማኖት ነጻነት ከላይ እንደተቀመጠው ከገለጸ ታዲያ መንግስት ስለምን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ይገባል ለሚለው ጥያቄ አብዛኛውን ሰው የሚያስማማው መልስ አገዛዙ የሃይማኖት ተቌማት ላይ ያለው ፍላጎት ወይም ጥቅም ሌሎች ነጻ ተቌማትን ለመቆጣጠር እንዳለው አይነት ተመሳሳይ ፍላጎት ነው የሚል ነው አንባገነን ስርአቶች ነጻ ተቋማት እንዳይኖሩ ይፈልጋሉ የሃይማኖት ነጻነት፤ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት፤የግለሰብ ነጻነት ወ.ዘ.ተ… እና እነዚህን እሴቶች ያቀፍ ነጻ የሃይማኖት የፖለቲካ የሲቪክ ወይም ሌላ ማናቸውም አይነት ነጻ እና ገለልተኛ ተቋማት ለይስሙላ ካልሆነ የምር እንዲኖሩ አይፈልጉም ወይም አይፈቅዱም እንዳይኖሩም አጥብቀው ይሰራሉ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት የተለያዩ እሴቶች ደግሞ አንድ የሚያደርጋቸው ነጻነትና ነጻነትን የመፈለግ ስሜትና ሁኔታ ነው ምንም እንኳን አንዱ ከአንዱ በተወሰነ ደረጃ መጠላለፋቸው ባይቀርም አንድ የሚያደርጋቸውና የሚያስተሳስራቸው መሰረት ይሄው ነጻነት ነው።
የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ሂደቶች ደግሞ የምር የሚካሄዱ ከሆነ ነጻነትን ይፈልጋሉ፤አብዛኖቹ የሃይማኖት ትእዛዛት የማድረግ ወይም ያለማድረግ ውሳኔና ነጻነት የግለሰቡ እንደሆነ ነው የሚገልጹት ፖለቲካም እንደዛው ነው አንድን የፖለቲካ አስተሳሰብ ለመደገፍ ወይ ለመቃወም የግለሰቡ -የአስተሳሰብ ደረጃው ነው የሚወስነው ተጽህኖ ካልተጨመረበት በስተቀር፤ ይሁንና በተጽህኖ ግን የግለሰቡን ፍላጎት ወደ አልፈለገበት አቅጣጫ ማዞር ይቻላል ያ ግን እንደ ግለሰቡ አቌም መውሰድ አይቻልም ምክንያቱም ተጽህኖው ሲነሳ አብሮ ስለማይኖር።
ነጻ ግለሰቦች፤ ነጻ ተቌማት ለአንባገነን ስርአት አይመቹም በነጻነት ማሰብ ፤በነጻነት መደገፍና መቃወም እንዲሁም የፈለጉትን ሃይማኖት ያለማንም ጣልቃ ገብነት በነጻነት ማምለክ የሚሉ ጉዳዮች መንግስትን የሚደሉትና በፍቅር የሚያያቸው ነገሮች አይደሉም። የሐይማኖት ይሁን የፖለቲካ ፤የመናገር ይሁን የመጻፍ የመምረጥ፤ ይሁን የመመረጥ ነጻነቶች በነጻነት መካሄድ የሚችሉት ደግሞ ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ሲኖር ብቻ ነው አንዱ ተከብሮ አንዱ ሊተው ወይ ሊዘነጋ አይችልም ነጻነት ሙሉ ነው ጎዶሎ ነጻነት የለም የሃይማኖት ነጻነት ተከብሮ የፖለቲካው ሊተው ወይም የፖለቲካ ነጻነት ተከብሮ የሃይማኖት ነጻነት ሊተው አይችልም የአንዱ ነጻነት ከሌላኛው ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተቆራኝ ስለሆነ፤ ስለዚህም የተበጣጠሰና የተከፋፈለ ነጻነት ከመፈለግ ይልቅ ለተሟላ ሁሉንም ለሚያካትት ነጻነት መታገል ግዜን፤ ጉልበትንና፤ ገንዘብን ቆጣቢ አማራጭ ይመስላል።
ቴዎድሮስ ጌታቸው ፀሐፊውን ለማግኘት thhe2011@gmail.com


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>