Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሃይልን ተቀላቀለ

$
0
0

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ያለ ህብረቱ እውቅና ከሁለት ዓመታት በፊት ዘምቶ የቆየው 4 ሺ የሚጠጋው የኢትዮጵያ ጦር በመጨረሻም በህብረቱ ስር እንዲሆን ተፈቅዶለታል። የኢትዮጵያ ጦር ሲደመር በሶማሊያ አልሸባብን ለመዋጋት የዘመተው የህብረቱ ጦር 22 ሺ ይደርሳል። የኢትዮጵያ ጦር በደቡብ ምእራብ የሶማሊያ ግዛት ፣ በጌዶ፣ ቤይ እና ባኮል ግዛቶች ይቆያል።

የአፍሪካ ህብረት ጦር አልሸባብን ከሞቃዲሾ ቢያስወጣውም፣ ጦሩ ግን አሁንም ወደ ሞቃዲሾ ሰርጎ በመግባት ጥቃት እየፈጸመ ነው። የቢቢሲው ማርክ ዶየል እንደሚለው በአፍሪካ ውስጥ በውጊያ የደነደነው የኢትዮጵአ ሰራዊት ከሞቃዲሾ 300 ኪሜ ርቆ በሚገኘው ባይዶዋ  ይሰፍራል ። የኢትዮጵያ ጦር የኡጋንዳና የብሩንዲ ጦር ወደ ዝቅተኛውና መካከለኛው አዋሽ እንዲወርድ ድጋፍ ሊሰጠው ይችላል ተብሎአል።

አንዳንድ ተንታኞች የኢትዮጵያ ጦር በቋሚነት በሶማሊያ መስፈሩ እየተዳከመ ያለውን አልሸባብ ሊያጠናክረው ይችላል ይላሉ። የኢትዮጵያ ሰራዊት ካለፉት 8 ዓመታት ጀምሮ በሶማሊያ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ጦሩ ሶማሊያን መቼ ለቆ እንደሚወጣ የሚታወቅ ነገር የለም።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>