ናይል ቤዚን ኢኒሽየቲቭ እየባለ የሚጠራው የናይል ተፋሰስ ጅማሮ ባለፈው ሣምንት አዲስ አበባ ላይ ባካሄደው የምሥራቅ ናይል ሃገሮች ስብሰባ ላይ ግብፅ እንደማትሣተፍ በፅሁፍ አሣውቃ መቅረቷ ተገልጿል፡፡
የምሥራቅ ናይል ንዑስ ተፋሰስ መርኃግብር ሚኒስትሮች ምክር ቤት ደቡብ ሱዳንን አባል አድርጎ ተቀብሏታል፡፡
የግብፅ የመስኖ ሚኒስቴር ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ መሠረት ግብፅ ባለፈው ሣምንት ከጥር 21 እስከ ጥር 23 / 2006 ዓ.ም ቢሾፍቱ ላይ በተካሄደው የምሥራቅ ናይል ንዑስ ተፋሰስ የድርጊት መርኃግብር አባል ሃገሮች ስብሰባ ላይ እንደማትገፀ አስታውቃ ቀርታለች፡፡
የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ሞሐመድ አብዱል ሙታሊብ ዩም-7 ለሚባል የሃገራቸው ጋዜጣ በሰጡት ቃል ግብፅ የናይል ተፋሰስ የትብብር ጅማሮ ወይም የናይል ቤዚን ኢኒሽየቲቭን የስብሰባ ጥሪ...
↧