Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

ሁለተኛውዙርየሰሞኑየጠለፋጉድይትንታኔ 2 ሃይለመድህንአበራከጀግንነትእስከአእምሮሕመምተኝነት

$
0
0
ምንሊክ ሳልሳዊ :- የረዳት አብራሪው ወንድም "ወንድሜ የአእምሮ ህመምተኛ ነው::" ብሎ ለመመስከር ወደ ስዊዘርላንድ በወያኔ ወጪ እንደሚሄድ የመረጃ ማረጋገጫዎች የተገኙት በዚሁ ሰሞን ሲሆን ከመሄዱ በፊት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑን ከቤተሰቡ የተገኙ መረጃዎች ያሳይሉ::

ቤተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ እንደሆነ እና የሃይለመድህን አበራ መኖሪያ ቤት ተገልብጦ መፈተሹን ከሱ ጋር ቀረቤታ አላት የተብለችው እህቱ በቁም መታሰሯን የስዊዝ ፖሊስ ለሃይለመድህን የፍርድ ሂደት .. እና የብኣዴን የዲያስፖራ አስተባባሪ እንዲሆን በእጩነት ተመልምሎ በስር ብዛት ምክንያት የተዘነጋው ወንድሙ ዶ/ር እንዳለማው የአሜሪካ ራዲዮ ቃለምልልስ እና በቤተሰብ ውስጥ የተነስው አለመግባባት እንዲሁም ሌሎችን በዚህ ባለፉ ቀናቶች የሰማናቸው የረዳት አብራሪ ሃይለመድህን ጉዳዮች ናቸው::ምንሊክ ሳልሳዊ

ለመንደርደሪያ ያህል ባለፈው ካየነው የውል ጫፉን ለመያዝ ያህል ሃይለመድህን የመንፈስ ጭንቀት ስለተጠናወተው የሚለውን የመንግስት እጅ አለበት የተባለበት እና ቤተሰቡ በችኮላ የአብራሪውን መልካም ስም ያጎደፈበት የተባለለት ጹሁፍ ተከትሎ እህቱ የጻፍኩት ሱሁፍ ተጠልፏል እኔ እንዲህ አላልኩም ያልኩት ሌላ ነው ባለችበት ይህንንም በሌሎች የቤተሰቡ አባላት በተረጋገጠበት ሁኔታ እንዳለ ሆኖ የቤተሰቡ አባላት በራሳቸው ጥንቃቄ ጉድለት ለመንግስት የፖለቲካ ፍጆት ከመዋላቸውም በላይ ተምረው በራስ አለመተማመን እና ጥንካሬያቸውን እንዲያጡ የተደረገበት አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን ይጠቁማል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ተበራክተዋል::

ረዳት ካፒቴኑ ቤተሰቡ ላይ የሚደርሰው ጫና በግልጽ የሚታወቅ ሲሆን ይህንንም መስካሪ የማያሻው ጉዳይ ነው:: አዝውንት የሆኑት እናት እና አባቱ ላይ ከሚደርስ ውንጀላ እና እየደወሉ ከማስፈራራት ጀምሮ በሃገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቹን ምንም አይነት መግለጫ እንዳይሰጡ እስከመከልከል እስከመዛት እስከማስፈራራት ተመሳሳይ ወያኔያዊ ሽብሮች ካለማቋረጥ እንደቀጠሉ ነው::

የመንግስት አካላት አለማቀፍ ውርደት እና የፖለቲካ ሽንፈት ያላበሰው የሃይለመድህን ጄኔቭ ላይ መክተም ለሚሰጡት መልስ የጨነቃቸው ወያኔዎች ቤተሰቡ ለፍጆታቸው ለመጠቀም እንደተገደዱ እያየን ነው:: ህይለመድህን የኢኮኖሚ ችግር የሌለበት እና በፈለገው ጉዳይ ከሃገር ወጥቶ መቅረት እንደሚችል የወያኔ አደርባዮች በአንደበታቸው መስክረዋል::የሃይለመድህን በሰላማዊ የእገታ ድርጊቱ የጠየቀው የፖለቲካ ጥገኝነት እንጂ ሌላ አይደለም ለምን ይህንን ሊጠይቅ ቻለ እንዴት ሊያስበው ቻለ ማለት የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ቢሆንም በሁለት የነጻነት እና የአፈና ክልል የሚኖሩ ቤተሰቦቹ ልእሱ ቅርብ ነን ያሉ የተጋጩ ምላሾችን አስቀምጠዋል:: የአጎቱ ልጅ ነኝ ያለንው እና በነጻነት ለመናገር እድሉ ያላት በአሜሪካ የምትኖረው የአጎቱ ልጅ ... ሃይለመድህን የሃገሩ ጉዳይ የሚያንገበግበው ጀግና ወንድማችን ነው ስትል .... ለአሜሪካ ራዲኦ የወያኔ ቃላቀባይ ተብሎ በሚታማው ጋዜጠኛ የተጠየቀው የብኣዴን እጩ ምልምል የሆነው የአብራሪው ታላቅ ወንድም ድ/ር እንዳለማው ደሞ ወንዴሜ የፖለቲካ እውቀት ያሌለው የኣእምሮ ጭንቀት የተጠናወተው ሲል ቤተሰባዊ ሞራል ባልጠበቀ መልኩ ሲናገር ወንድሙ የስዊዝን መንግስት የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁት ይዘንጋው አሊያም የወያኔን የፖለቲካ ፍጆት ያጡዘው ሊያብራራ አልቻለም ::ምንሊክ ሳልሳዊ

የሃይለመድህን አበራ ኢምፔሪያል ሆቴል አከባቢ የሚገኘው መኖሪያው ግኡዝ ቤት እንኳን እስኪደነግጥ የተባለለት የደህንነት ፍተሻ ተደርጎ ንብረቱ በመንግስት ተዘርፎ መወረሱን እያየን ባለንበት ወቅት ቤተሰቡ ምን ያህል አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ እያየን መንግስት በራሱ ሽብር ስራ ምን ያህል እንደተጋለጠ እና እንደተሸበረ እያወቅን ባለንበት ሰአት በአለም ላይ የሚኖሩ ዲያስፖራዎች ድምጻቸውን በአደባባይ ለማሰማት ከያሉበት እየተጠርሩ መሆናቸው ሌልው ወያኔ ላይ የደረሰ ሽንፈት ነው:: አለማቀፍ የዲያስፖራው ቡድኖች በኢትዮጵያ ያለውን የመብት መጣስ በተመለከተ አትኩሮት እንዲያገኝ የተደረገ ድርጊት ነው ብለው አምነውበት ሃይለመድህን አበራን በነጻ ለማስለቀቅ የራሳቸውን ዘመቻ በመጀመር ጀግና የሚል ስያሜ ሰተውት ስራቸውን በግብረሃይል በተግባር እየሰሩ ነው::

የስዊዝ ፖሊስ የሃይለመድህንን ጤንነት መስክሮ ጠበቃ እንደሚያቆምለት እና የፍርድ ሂደቱም በቅርቡ እንደሚጀምር በገለጸበት በዚህን ወቅት ኢትዮጵያውያን ሃይለመድህን ይለቀቅ !!! ብለው ድምጻቸውን እያሰሙ ባሉበት ሰኣት የወያኔው መንግስት ጨንቆት የሚለው ባጣበት እና በፈጠራ ወንጀል ድራማ ለመስራት በሚኳትንበት በዚህ ጊዜ እውነታውን ለአለማቀፉ ማህበረሰብ ለመስረዳት የእያንዳንዳችን ጥረት ወሳኝነት እንዳለው እና ለሕዝቦች የመብት ትግል የሚከፈሉ መስዋትነቶች እንዳይዳፈኑ አጥብቀን መታገል ያለብን መሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ::ምንሊክ ሳልሳዊ #MinilikSalsawi

Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>