Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

የአብነት መምህራኑ የምክክር ጉባኤ እገዳ የስልታዊ ጫና ማሳያ ነው

$
0
0

(ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፬ የካቲት ፳፻፮ ዓ.ም.)

FACT Magazine cover,Yekatitማኅበረ ቅዱሳን ለሦስተኛ ጊዜ ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ ላይ በፓትርያርኩ ደብዳቤ የተጣለው እገዳ በማኅበሩ ላይ ይደረጋል ለሚባለው ስልታዊ ጫና ማሳያ እንደኾነ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ለፋክት መጽሔት ገለጹ፡፡

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሚጠራቸው አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን የተመለከቱ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር መድረኮች ላይ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካላት ይኹንታ የተቋቋሙ የወጣት ማኅበራት አደረጃጀቶች የአክራሪዎች ምሽግ እንደኾኑ በግልጽ የሚቀርቡ ክሦች መኖራቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የአመራር አካሏ በኾነው በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ መተዳደርያ ደንብ አጽድቃ የአገልግሎት ይኹንታ የሰጠችው ማኅበር ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ተጠሪ የኾነው ማኅበረ ቅዱሳን መኾኑን ምንጮቹ አረጋግጠው፣ ሚኒስቴሩ በዚኽ ማኅበር ውስጥ መሽገዋል የሚላቸውንና ለይቶ የማይጠቅሳቸውን አካላት እየተጠቀመና ማኅበሩ ለፀረ ዴሞክራሲ ፍላጎቶች ከለላ እንደኾነ በመክሠሥ፣ ይኹንታ ከሰጡት የሃይማኖት አባቶች ጋራ ‹‹ውጦአችኋል፤ መቆጣጠር አልቻላችኹም፤ ከአቅማችኹ በላይ ኾኗል፤ መሥመር አላስገባችኋቸውም›› በሚል ፍጥጫ ውስጥ እንዲገባ ስልታዊ ጫና እተየፈጠረበት ነው ብለዋል፡፡

An Accomplished Scholars of the Ethiopain Orthodox Tewahido Church Traditional Schools

ማኅበሩ ከየካቲት 7 – 9 ቀን 2006 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል፣ በብሔራዊ ሙዝየም አዳራሽ እና በኢትዮጵያ ባህል የስብሰባ ማእከል ያዘጋጀው ሦስተኛው ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ ከቀትር በኋላ ፓትርያርኩ ለዋና ሥራ አስኪያጁ በጻፉት ደብዳቤ መታገዱ ተዘግቧል፡፡

በዐሥራ አንደኛው ሰዓት የተጻፈው ደብዳቤ ለእግዱ የሰጠው ዋናው ምክንያት፣ ማኅበሩ የጉባኤውን መካሔድ ለሚመለከተው አካል ካለማሳወቅ ጋራ የተያያዘ ቢኾንም የማኅበሩ አመራሮች ጉባኤው በማኅበሩ ዓመታዊ ዕቅድ የተካተተና መምህራኑ የተጋበዙባቸው አህጉረ ስብከት ከአንድ ወር በፊት እንዲያውቁት ተደርጎ መምህራኑ በየአህጉረ ስብከቱ ዕውቅና ለጉባኤው የተጋበዙ መኾናቸውን ምንጮቹ አስረድተዋል፡፡

በመሀል ለተፈጠረው የተግባቦት ክፍተት የማኅበሩ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጁን በደብዳቤ ይቅርታ መጠየቁ ተገልጧል፡፡ ይኹንና ለጉባኤው ተዘጋጅተው የነበሩት የአብነት ት/ቤቶችን ተቋማዊ ኹኔታ የተመለከቱ አጀንዳዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስኑ በመኾናቸው የማይደራደርባቸውና ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት ጋራ በመነጋገር መከናወናቸው አይቀሬ መኾኑን የማኅበሩ አመራሮች ማስታወቃቸውን ምንጮቹ ለፋክት መጽሔት ገልጸዋል፡፡

slide presentation by Dr. Shiferaw000

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም ‹‹አክራሪነትና ጽንፈኝነት ማብራሪያዎቻቸውና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ በሐዋሳ – ሌዊ ሪዞርት ጥር ፴ እና የካቲት ፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ለተካሔደው የሃይማኖት ተቋማት ምክክር ጉባኤ ካቀረቡት ስላይድ

 



Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>