ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
‹‹…የውሳኔ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቀቀ፡፡ የባሕር መዝገቡም ተዘጋ፡፡ …ቀፋፊ ምሽት ነበር፡፡ በእያንዳንዳችንም ፊት ፈገግታ አይታይም፡፡ ከአዳራሹ ሳንርቅ ከራሳችን ጋር ብቻ እየተነጋገርን በሃሳብም ርቀን እየሄድን አመሸን፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ አዳራሹ እንድንገባ ተነገረን፡፡ በፍጥነት ገብተን ቦታችንን ያዝን፡፡ ሊቀ-መናብርቱም ቦታቸውን ያዙ፡፡ ‹ዛሬ ስለወሰድነው እርምጃ ለጦር አዛዦች ማሳወቁ ይበጃል በማለት ጠርተናቸው እዚሁ ይገኛሉ› ብለው ወደ አጃቢዎቻቸው ፊታቸውን ዘወር አድርገው ‹አስገቧቸው!› የሚል ትዕዛዝ ሻለቃ መንግስቱ ሰጡ፡፡ ጄነራል ጃጋማ ኬሎ፣ ጄነራል ግዛው በላይነህ፣ ጄነራል ታደሰ ገብሬ፣ ጄነራል ወርቁ መኮንን ተከታትለው ገቡ…››
↧
እኛና “እነርሱ”!
↧