Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

“ፀሐይለኢትዮጵያወጥቶላታል።ከአሁንበኋላአይጨልምም::”ወ/ትብርቱካንሚደቅሳትግሉንይቀላቀሉኪሚሊዮኖችአንዱይሁኑ ! እንዴትካሉየሚከተለዉንያንብቡ

$
0
0
ትግሉን ይቀላቀሉ ኪሚሊዮኖች አንዱ ይሁኑ ! እንዴት ካሉ የሚከተለዉን ያንብቡ
======================================

የባህር ዳር ሰልፍ በአስደናቂ ሁኔታ በሰላም ተጠናቋል። ሕዝቡ ከፍተኛ አፈናን ተቋቁሞ፣ ፍርሃትን አዉልቆ የነጻነትን ደዉል አውጇል። ሕዝብ በባህር ዳር ተናግሯል። በዚህ በባህር ዳር ሰልፍ፣ መኢአድ እና አንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ስለጠሩ ብቻ አይደለም ሕዝብ የተሰባሰበው። ዉስጥ ዉስጡን ከፍተኛ ድርጅታዊ ሥራ ስለተሰራ፣ ሕዝቡን በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ማንቀሳቀስ ስለተቻለ ነው። ድርጅቶች (መኢአድ፣ አድንነት እና ትብብር) በተናጥል ሳይሆን በትብብርና አብሮ በመስራት ስለመሩት ነዉ።

ይህ የባህር ዳር ሰልፍ በየቤታችን ትልቅ ደስታን እንደፈጠረ ይገባናል። ዜጎች በድፍረትና በነጻነት ድምጻቸዉን ሲያሰሙ የመሰለ ደስታ የለም። ሁላችንም ተደስተናል፣ በባህር ዳር ሕዝብም ኮርተናል።

የባህር ዳሩ ሰልፍ ግን ጅማሬ እንጂ ፍጻሜ መሆን የለበትም። ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እየተደጋገሙ፣ በጥራትና በብቃት፣ በመቀሌ፣ በአዋሳ፣ በድሬደዋ፣ በጂማ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ በመሳሰሉ ሌሎች ከተሞች መደረግ አለባቸው። የነጻነት፣ የሰላም፣ የኢትዮጵያዊነት እሳት መቀጣጠል አለበት።

አንድነት/መኢአድ በፊታቸው ከፍተኛ ሥራ አለባቸው። ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። በባህር ዳር የታየዉን አይነት ሥራ ለመስራት ትልቅ ወጭ አለው። ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቀበቶዉን እንዲታጠቅ፣ ትግሉን እንዲቀላቀል፣ የድርሻዉን እንዲወጣ ያስፈልጋል። ከአሁን በኋላ ወደ ኃላ መመለስ የለም። ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ በባህር ዳር እንደተደረገዉ፣ በአገራችን ግዛቶች ሁሉ ሕዝቡን ማደራጀትና ማንቀሳቀስ ያስፈልጋል፤ የግድ ነው። ይቻላልምም።

በባህር ዳር ሁኔታዎች ስለተመቻቹ አልነበረም። የፖለቲካ ምህዳሩ ስለተከፈተ አልነበረም። የመኢአድ እና አንድነት አባላት፣ ደጋፊዎች፣ ታስረዋል፣ ተዋክበዋል ከሥራ ተባረዋል፣ የግድያ ዛቻ ደርሶባቸዋል። ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል፤ እየከፈሉም ነዉ። ነገር ግን የተዘጋዉን በር በትግላቸው አስከፍተው ነዉ በባህር ዳር እንዳየነው ሕዝቡን ያንቀሳቀሱት።

በአገር ቤት ያለን ምሁራን፣ ተማሪዎች፣ ሴቶች ፣ ወንዶች ፣ ወጣቶች አረጋዉያን፣ ክርስቲያኑ ፣ ሙስሊሙ፣ ትግሬው፣ አማራዉ፣ ኦሮሞዉ፣ ቅልቅሉ … ሁሉን ኢትዮጵያዊ ከአንድነት ጎን እንዲሰለፍ እንጠይቃለን። አንድነት ጠመንጃ እንደ ሌሎች ጠመንጃ የለውም። አንድነት የፈረንጆችን ጥቅም እንደሚያስጠብቁት እንደ ሌሎች የዉጭ መንግስታት ድጋፍ የለዉም። የአንድነት ኃይልና መተማመኛ ሕዝብ ብቻ ነው።

እንግዲህ

1. አገር ቤት ያለን በአካባቢያችን ወዳሉ የአንድነት ጽ/ቤቶች፣ በዉጭ ደግሞ ያለን የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶች በመሄድ እንዴት መርዳትና መተባበር እንዳለብን እንጠይቅ።

2. http://www.andinet.org/ በመሄድ በክሬዲት ካርድ ወይንም ፔይ ፓል የገንዘብ ድጋፍ እናድርግ።

3. የሚሊየነም ድምጽ ለነጻነት ፌስ ቡክ እና የፍኖተ ነጻነት ገጽ ላይክ በማድረግ እየተሰሩ ያሉትን እንከታተል። መልእክቶችን በማስተላለፍ የቅስቀሳቅዎች አካል እንሁን::

https://www.facebook.com/FinoteNestanet https://www.facebook.com/MillionsOfVoicesForFreedomUdj

4. አገር ዉስጥ ላለን በአካባቢያችን የአንድነት መዋቅር ከሌለ፣ በዉጭ ደግሞ የድጋፍ ድርጅት ከሌሉ፣ ሁለት ሶስት ፣ ሆነን እራሳችንን አደራጅተን፣ ፓርቲዉን ፓርቲዉን በማሳወቅ ትግሉን እንቀላቀል። የድጋፍ ድርጅቶች ከሌሉ፣ የአገር ቤቱን ትግሉ የሚደገፉ ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ በነርሱ በኩል ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።

5. በግለሰብ ደረጃም በጽሁፍ፣ በሃሳብ መርዳት ከፈለግን organizingethiopia@gmail.com በሚለው ኢሜል አድራሻ ያሳውቁን።

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ አንድ ወቅት እንዳለችዉ፣ ፀሐይ ለኢትዮጵያ ወጥቶላታል። ከአሁን በኋላ አይጨልምም::

Image

Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

Trending Articles