Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

ሕወሓትለኦሕደድሊቀመንበርእናምክትልሊቀመንበርመደበ።

$
0
0
Image

በሕወሓት የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ተመደበ።

በዚሁ መሰረት ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሙክታር ከድር የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆነው ተመድበዋል። የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት ወይዘሮ አስቴር ማሞ ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመድበዋል።
የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር በሕወሓት የተመደቡት ሕወሓት በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ነው።ተመዳቢዎቹ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት የሚወጡ መሆናቸው ታምኖባቸዋል።

በሕወሓት በወረደው ትእዛዝ የኦሕደድ ማዕከላዊ ኮሚቴው የተባለው ምድብ በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበሩት የሕክምና ውጪያቸው ከክልሉ በጀት እኩል ስለሆነ ባለመፈለጋቸው አቶ አለማየሁ አቶምሳ በህመም ምክንያት ተብሎ ከስልጣናቸው የተሰናበቱ ሲሆን በቦታው ላይ ከተመደቡ ጀምሮ ምንም አይነት ስራ አልሰሩም ሲል ሕወሓት አማሯል።

Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>