በደቡብ ክልል፣ በጋሙ ጎፋ ዞን የምትገኝ ወረዳ ናት። ወደ 150 ሺህ የሚጠጋ ነዋሪ አላት። በዚያ ያሉ ገበሬዎች ከሚያርሱበት ቦታ በግድ እንዲፈናቀሉ ከመደረጉ በተጨማሪ፣ ብዙዎች ያታሰሩባት ወረዳ ናት። የቁጭ ወረዳ ትባላለች።
በአንድነት ፓርቲ አነሳሽነት ለሕዝብ የፋ የሆነው የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ትኩረት ከሰጠባቸው ወደ አሥራ የሚሆኑ አካባቢዎች አንዷ ቁጫ ናት። በቁጫ ሊደረግ የታሰበዉን ትእይነተ ሕዝብ በመደገፍ፣ በዚያም ለሚኖረው የተገፋዉ ሕዝብ ሶሊዳሪቲ በማሳየት የቃሌ ፓልቶክ ክፍል ፣ የቁጫን እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ እንደሚሸፍን እና ስፖንሰር እንደሚያደርግ ይፋ አደርጓል።
ሌላዋ የሚሊይን ድምጽ ዘመቻ የሚደረግባት ከተማ፣ የኢትዮዮጵያ ሁለተኛ ከተማ የሆነችዋ አንጋፋዉ ድሬዳዋ ናት። የደብተራዉ ፓል ቶክ ክፍል ፣ ድረደዋን ስፖንሰር እንደሚያደርግም ለማወቅ ተችሏል።
የቃሌ እና የደብተራዉ ፓል ቶክ ክፍሎች ከአለም ዙሪያ ሁሉ የተሰባሰቡ ፣ በኢንተርኔት ፓልቶክ አፕሊኬሽን ፣ በአገራቸው ጉዳይ ላይ ዘወተር የሚመካከሩ፣ የአገራቸው ጉዳይ የሚያስጨንቃቸው ኢትዮጵያዊያን የተሰባሰቡበት ክፍሎች ነው።
በኢትዮጵያ የሚደረገዉ ሰላማዊ ትግል፣ ስለተመኘንና ስላወራን ብቻ ዉጤት የሚያመጣ አይደለም። አገዛዙ ዘወትር ስለሚፈጽማቸው ግፎች ማዉራት አንድ ነገር ነው። እነዚህ ግፎች እንዲያቆሙና የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ ማድረግ ሌላ ነገር ነው።
የቃሌና የደብተራው ታዳሚዎች ፣ ከዉይይት አልፈው፣ አገር ወዳድነታቸውን በተግባር በማሳየት፣ በሜዳ ፊት ለፊት አምባገነንነትን እየተጋፈጡ ያሉ ጀግኖችን በቁጫና በድሬደዋ በመደገፍ የሚሊዮኖች አንዱ ነን እያሉ ነው።
የቃሌና የደብተራዉ ፓልቶክ ክፍሎች ለወሰዱት አኩሪና አገር ወዳድ አቋም ያለንን አድናቆት እየገለጽን፣ የተቀረነዉ በየአካባቢያችን እየተሰባሰብን ትግሉን እንድንቀላቀል፣ከሚሊዮኖች አንዱ እንሆን ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።
ትግሉን ለመርዳት፣ ለመደገፍ፣ ከሚሊዮኖች አንዱ ለመሆን የምንፈልግ ካለን በሚከተለው አድራሻ ሊያገኙን ይችላሉ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
millionsforethiopia@gmail.com