ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም
ወያኔ/ኢሕአዴግ ጥሩምባ ነፍቶ የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦች ነጻነት ብሎ ከአወጀና ሁሉንም ለሃያ ሁለት ዓመታት በተስፋ ከአስፈነደቀ በኋላ ችግር ተፈጠረበት፤ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ የቆጡንአወርድብላየብብቷንጣለች የሚባለው ነው፤ ችግሩ አፍ ከሚችለው በላይ ለመጉረስ ከራስ ጋር መተናነቅ ሆነ፤ ችግሩ የማሰብ ድርቀት ነው፤ ችግሩ ከአሜሪካና ከአውሮፓ መንግሥታት ጀምሮ እስከቀበሌ መዋቅር ያሉትን ሁሉ በአንድ ዘዴ እያባበሉና እያታለሉ ማደናበር ነው፤ ችግሩ በሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ ዘዴው ሻግቶ ዓላማው ደብዛው መጥፋቱ ነው፤ ቸግሩ የዘዴው መሻገትና የዓላማው መክሸፍ መጋለጡ ነው፤ ችግሩ ወያኔ የተቀመጠበት የሥልጣን ወንበር መቆርቆር መጀመሩ ነው።