#udj@addisabeba
የአዲስ አበባ የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባዎች ማሳወቂያ ክፍል ኦፊሰር የሆኑት አቶ ማርቆስ ብዙነህ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ላቀረበላቸው የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ደብዳቤ ህገ ወጥ ምላሽ በመስጠታቸው ፓርቲው ደብዳቤውን የተቃወመበትን የህግ አግባብ በመጥቀስ ደብዳቤ ልኮላቸው ነበር፡፡
አቶ ማርቆስ በጽ/ቤታቸው በአካል የተላከላቸውን ደብዳቤ ምስክሮች ባሉበት ‹‹አልቀበልም ብትፈልጉ ክሰሱኝ››በማለት በህጋዊ መንገድ የቀረበላቸውን ደብዳቤ አልቀበልም በማለት መልሰዋል፡፡አንድነት ፓርቲ ሰዎች ሁሉ በህግ ፊት እኩል መሆናቸውንና በመንግስት የሃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጡ ሰዎችም ህዝቡን ማገልገል ቅሬታውንም ማድመጥ ግዴታቸው ጭምር መሆኑን በማመን ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የቅሬታ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡
መስተዳድሩ በቅርብ ቀናት ውስጥ በግለሰቡ ላይ ህጋዊ እርምጃ የማይወስድ ከሆነም ፓርቲው በመደበኛ ፍርድ ቤት ፍትህን እንደሚጠይቅ አስታውቋል፡፡