(By “Abel Sog Sos”)
እስኪ እውነቱን እንነጋገር!
አሁን ባለንበት ዘመን ሃገርን ስለመውደድ የምንማረው/የተማርነው ከየት ነው? ከቤተ እምነቶች ወይስ ከስነ ዜጋና ስነ ምግባር ወይም "ሲቪክስ" ኮርስ? የጸረ ሙስና ኮሚሽን ሳይቋቋም ማን ነበር የራስ ያልሆነን ስላለመውሰድ ያስተማረው? አሁንስ ቢሆን? የሃይማኖት ተቋማት አይደሉምን?
እድሜ ለማኅበረ ቅዱሳንና ወጣቱ በየግቢጉባዔያቱ ተኮትኩቶ ባይወጣ ምን ይውጠን ነበር? አገሩ ሁሉ ሙሰኛ በሙሰኛ ይሆን አልነበር! (መንግስት እንዲያውም ቢያውቅበት ሊደግፈው ይገባ ነበር፤ የ'ርሱን ስራ ማኅበረ ቅዱሳን እየሰራለት ስለሆነ!)
በመልካም ገጽታ ግንባታ (የተዋስኳት ከኢቲቪ ነው።) ከመንግስት ባልተናነሰ የሃገር ሃብት የሆኑ ቅዱሳት መካናትን ጠብቆ በማቆዬት የአንበሳውን ድርሻ ማኅበረ ቅዱሳን አይወስድም?
የእናት ጡት ነካሽ ፖለቲከኛ ሁላ ዛሬ ማኅበሩን አፍርሰው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የተኩላ መፈንጫ ለማድረግ ከላይ ታች ማለቱን ተያይዘውታል፤ ቤተክህነቱ ውስጥ በተሰገሰጉ "አማኝ መሳይ" ካድሬዎች በኩል።
በጣም የሚገርመኝ ነገር ቢኖር በቁም ሳሉ ሊያፈርሷት የታተሩ ሁሉ በኋላ ግብአተ መሬታቸው እንደ ሥላሴ ባሉ ታላላቅ ካቴድራልና አድባራት ሲፈጸም "እገሌ ታላቅ ሰው ነበሩ። እትት እትት" ተብሎላቸው ይቀበራሉ። የሚቀብሯትን የምትቀብር ቤተክርስቲያን!
ማኅበረ ቅዱሳንን መቅበር ማሰብ ከብርቱውና ኃያሉ አምላክ ጋር መታገል ነው፤ እግዚአብሔር ወድዶና ፈቅዶ የመሰረተው ማኅበር ነውና።