ነገ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቅድቀሳእ በደመቀ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሆነ ተገልጸ። አቶ ሃብታሙ አያሌዉ ከስፋራዉ ይሄን አስተላልፈዋል ፡
=====================
“እረ ደሴ ደሴ ገራዶ ረጋዶ……..
አለቀልሽ ልቤ አንድነትን ወዶ”
ይህንን የማጀቢያ ዘፈን እያሰማ ህዝቡ ከጎናችን ተሰለፈ …… ደሴ በአንድነት አባላትና ደጋፊዎች እንደደመቀች፤ ትንቅንቁም እንደቀጠለ …..ለዚህ ሰዓት ደርሰናል…ነጻነት ከፍርሃት አይገኝም!!! ድል የህዝብ ነው!! ትግሉ ይቀጥላል ጊዜ ሳገኝ በዝርዝሩ እመለሳለሁ………ማየት ማመን ነው ….!!!! እመነኝ ድል የህዝብ ነው
==================================
ፖሊሲ በሰልፉ ጣልቃ እየገባ ችገር ለመፍጠር እንደሞከረ የዘገበው የፍኖት ፍኖት ጋዜጣ ሁኔታውን እንደሚከተለው ዘግቧል ፡
=============
«የአንድነት ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተውን የቅስቀሳ ቡድን ተግባር ለማደናቀፍ ፖሊሶችና ደህንነት ነን የሚሉ ግለሰቦች በስውር ቪዲዮ በመቅረፅ እና ስለሙስሊሙ የመብት ጥያቄ የሚስተጋቡ መፈክሮችን ለማስቆም ሙከራ አድርገዋል፡፡ በተለይም የከተማዋ የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ ቅስቀሳው በተደረገባቸው ስፍራዎች በመገኘት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ለማስፈራራትና ከቅስቀሳ ቡድኑ አባል ላይ የቅስቀሳ ቁሳቁስ ለመንጠቅ ሲሞከር በዝምታ ተመልክተዋል፡፡ ይህ ሁሉ የማደናቀፍ ሙከራ ቢደረግም ቅስቀሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ የደሴ ህዝብ ከአንድነት ፓርቲ ጎን በመሆን ቅስቀሳውን አጧጡፎታል፡፡»
====================