ከሆሳዕና እስከ ማዕዶት
በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል ተከብሮ የሚውለው፣ በዕለተ እሑድ ነው። ጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው በዕለተ እሑድ-መጋቢት 29 ቀን ነው። የግዕዝ ቋንቋ ሊቃውንት እንደሚተረጉሙት ከሆነ፣ “ትንሣኤ ማለት-መነሳት ማለት ነው።” ሞትን ድል አድርጎ፣ ከሙታን ተለይቶ መነሳት ማለት ነው። “ሕይወት ማግኘት፣ ነፍስ መዝራት፣ ሕልው መሆን” ማለት ነው።