አዲስ አበባ በቅስቀሳ ደምቃ ዋለች ፣ ብዙዎች ታሰሩ::
የአንድነት ፓርቲ የእሪታ ቀን በሚል እሑድ ሚያዚያ 29 ቀን ለጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ የሚደረገዉ ቅስቀሳ በደመቀ ሁኔታ ቀጥሏል። ብዙዎች ቢታሰሩም ቅስቀሳው እንዳልቆመ ለማወቅ ችለናል።
በመኪና ቅስቀሳዎች ሲደረጉ ሕዝቡ በብዛት መኪናዎችን እየተከተለ ቅስቀሳውን ራሱ ሰልፍ ያሰመሰለበት ሁኔታ እንደነበረም ዘገባዎች ይገልጻሉ።
ፖሊስ በ በእግራቹህ እየሄዳችሁ ወረቀት ማደል እንጂ በመኪና እንድትቀሰቅሱ ፋቃድ አልተሰጣችሁም በሚል ብዙ መኪኖችን ቢያግቱም፣ ሌሎች መኪኖች እየተተኩ ቅስቀሳው ቀጥሏል።
የታሰሩ እስረኖችን እና የቅስቀሳዉን ሂደት የሚመለከተ ፎቶዎችን ይመለከቱ