![]() |
ጽዮን ግርማ
tsiongir@gmail.com |
![]() |
ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ |
በአነጋገሩ ቀጥተኛና በጠባዕዩ ገራገር ነው። ‹ጥርስ ያሳብራሉ› በሚባሉ ስብሰባዎች፣ በኃይለ ቃል በተሞሉ የኤዲቶሪያል ውይይቶችና ግምገማዎች ሳይቀር ስሜቱን ውጦ በተረጋጋ መንፈስና በለዘብታ ቃል መመላለስ ጸጋው ነው። በኤዲቶሪያል ጠረጴዛዎችና ዴስኮች ዙሪያ በሐሳብ ለመግባባት ከሚደረጉ ግብግቦች ውጭና ባሻገር ቂምና በቀል አያውቅም። በደሙ ውስጥ ከሚዘዋወረውና ራሱን ከሰጠለት የጋዜጠኝነት ሞያውና የጋዜጠኝነት መርሕ የተነሳ ሌላ ዓለም፣ ሌላ ጥቅም፣ ሌላ ኑሮ ያለም አይመስለው። ለእርሱ ኑሮው፣ ለእርሱ ዓለሙ ተጨባጭ መረጃን ከወገናዊነት በጸዳ መልኩ ለሕዝብ ማድረስ ነው - ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ።