ለህጋዊ ሰልፍ ሲቀሰቅሱ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙት የአንድነት አባላት በዋስ ተለቀቁ ባሳለፍነው ሐሙስ ካዛንቺስ አካባቢ በፖሊስ ተይዘው ስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ የታሰሩት ጋዜጠኛ ነብዩ ሐይሉ፣አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን፣ዘላለም ደበበና ሹፌራቸው አርብ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው የአስራ አንድ ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ እንዲመለሱ መደረጋቸው አይዘነጋም፡፡
የእጅ አሻራ እንዲሰጡ ከተደረጉ በኋላ አራቱም ሰዎች የመታወቂያ ዋስ በመጥራት ፖሊስ ጣብያውን ከግማሽ ሰዓት በፊት እንዲለቁ ተደርገዋል፡፡
እነ ጋዜጠኛ ነብዩ ሐይሉ ነገ ፍርድ ቤት የሚቀርቡት ጋዜጠኞችና የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን መልካም ዜና እንዲሰሙ ተመኝተዋል፡፡አንድነት ፓርቲ ባሳለፍነው እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ የተሳካ ሰላማዊ ሰልፍ ማከናወኑ ይታወቃል፡፡