Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

አቡጊዳ – ትብብር መኢአድ እና አንድነት ካልተዋሃዱ እኛ ከአንዱ ጋር እንቀጥላለን አለ

$
0
0

የሰባት ፓርቲዎች ስብስበ የሆነው ትብብር በአንድነት እና በመኢአድ መካከል ፖለቲካ ፕሮግራሞቻቸው ተመሳሳይ እንደመሆናቸው መዋሃድ እንዳለባቸው ማሳሰባቸው አገር ቤት የሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ ገለጸ። ስብሰቡ ሁለቱ ፓርቲዎች ከተዋሃዱ በኋላ እነርሱም ያንን ዉህደት እንደሚቀላቀሉ፣ የትብብሩ ሊቀመንበር መናገራቸውን ሰንደ አክሎ ዘግቧል።

መኢአድ እና አንድነት የማይዋሃዱ ከሆነ ግን ትብብሩ፣ ከአንዳቸው ጋር እንደሚዋሃድ ሰንደቅ የትብብሩን ሊቀመንበር ጠቅሶ አትቷል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው አንድ ከፍተኛ የአንድነት አመራር አባል፣ «አንድነት ከመኢአድ ጋር ለመዋሃድ በሩ ምንጊዜም ክፍት ነው። ስምምነት ደርሰን ፣ የቅድመ ዉህደት ፊርማ ሊፈረም 2 ቀናት ሲቀሩት፣ መኢአዶች መቆየት እንፈልጋለን አሉ። ወደ ዉህደት እንዳይመጡ ያሳሰባቸው ጉዳዮች ካሉ በማናቸዉም ጎዜ ለመወያየት ዝግጂ ነን» ሲሉ በአንድነት ዘንድ ፍላጎት እንዳለ ገልጸዉልናል።

«በአንድ እጅ አይጨበጨብም ። በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ስላለው ዉህደት፣ ከመነጋገር ዉጭ ምን አይነት ነገር የለም። ዉህደቱ የሚፈጸም ከሆነ፣ በጊዜዉ ያኔ እኛው ራሳችን እናሳዉቃለን» ሲሉ ሕዝቡ ብዙም ትኩረቱን ከዉህደት ወሬ አንስቶ ወደ ሚሊዮኖች ንቅናቄ እንዲያዞር ጥሪ አቅርበዋል። የአመራር አባሉ፣ ከመኢአድ ጋር የሚደረገው ዉይይት፣ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር እንዳይወያዩ አለማገዱን ገልጸው፣ ከመኢአድ ጋር ዉህደት ባይደረግም፣ ከሌሎች ጋር ሊደረግ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችልም አሳስበዋል።

የሰንደቅ ጋዜጣን ዘገባ እንደሚከተለው አስፈረናል

ሕዝቡ የሚሊዮኖች አንዱ ሆምኖ በትግሎነገር የ ፡እንደሆነና ስምምነት ተደርሶ የቅድመ ሁኔታ ፊርማ ሊፈረም ትቂት ቀናት ሲቀሩት መኢአዶች ምቆየር የገለጹልን ሲሆን፣ ከመኢአድ የራሱ በሆኑ ምክንያቶች ዉህደቱን ለመፈጸም ለጊዜው ዝግጁ ካልሆነ ፣ አንድነት ከሌሎ
ትዴኢ አንድነትና መኢአድን ለመዋሐድ እየጣረ ነውትዴኢ አንድነትና መኢአድን ለመዋሐድ እየጣረ ነው

የሰባት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው “ትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ” ወይም “ትብብር” የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እንዲዋሐዱ የመጨረሻ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

የትብብሩ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ ትናንት ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት “ትብብሩ” ሁለቱ ፓርቲዎች እንዲዋሐዱ ጥረት እያደረገ ያለው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በጉጉት ሲጠብቀው የቆየው ውህደት ያለበቂ ምክንያት የመስተጓጎል አዝማሚያ በማሳየቱ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ትብብሩ እንደባለድርሻ አካል ደግሞ በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል ያለው ልዩነት በሰላም ተጠናቆ ውህደቱ እውን ሆኖ የኢትዮጵያ ሕዝብ የውህደት ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ የራሱን አዎንታዊ አስተዋፅኦ ለማድረግ ነው ብለዋል።

ትብብሩ ይሄንኑ ዓላማ ለማሳካት ከሁለቱም ፓርቲዎች ጋር ለመዋሐድ የውህደት ጥያቄ በደብዳቤ ማቅረቡን የገለፁት አቶ ግርማ የትብብሩ የመጀመሪያ ፍላጎት ሁለቱ ፓርቲዎች ውህደት ከተጠናቀቀ በኋላ ትብብሩ አዲስ ከሚፈጥረው ውህደት ጋር መልሶ መዋሐድ እንደሚፈልግ አስታውቀዋል።

ይሁን እንጂ በመኢአድና በአንድነት መካከል የሚደረገው ውህደት የማይሳካ ከሆነ ከሁለት አንዳቸው ጋር ለመዋሐድ መዘጋጀታቸውን የጠቀሱት አቶ ግርማ ወደዚህ ውሳኔ ከመምጣታቸው በፊት ግን የሶስትዮሽ ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

ፓርቲዎቹ ከመዋሐዳቸው በፊት የፓርቲዎች ርዕዮተ ዓለምና የአደረጃጀት ጥያቄዎች በምን መልኩ ማስታረቅ እንዲሚቻል የተጠየቁት አቶ ግርማ፤ ችግሩ የርዕዮተዓለምና የአደረጃጀት አለመሆኑን ገልፀዋል። እሳቸው የሚመሩት “ትብብር” በአራት የክልልና በሶስት ህብረብሔራዊ ፓርቲዎች የተዋቀረ መሆኑን በማስታወስ ከመኢአድም ሆነ ከአንድነት ጋር ሊያዋህዳቸው የሚችለውን መሠረታዊ መነሻ አጥንተው ማጠናቀቃቸውን አስረድተዋል። ያስቸገራቸው ግን የተዋሐደ ፕሮግራም ያላቸው መኢአድና አንድነት ለመዋሐድ አለመወሰናቸው ነው ሲሉም ገልጸዋል።

“የአንድነትና የመኢአድ ፕሮግራም ስታየው ሁለቱ ያልተዋሐዱ ማን ሊዋሐድ ይችላል የሚል ጥያቄ ያጭርብሃል” የሚሉት አቶ ግርማ ትብብሩ እንደተፈለገው የሚሳካ ከሆነ በቅርቡ የሶስትዮሽ መግለጫ እንደሚሰጡ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ባለፈው ሰኞ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት በዚሁ ጉዳይ ለመወያየት ኮረም ባለመሟላቱ ለመጪው ቅዳሜ ቀጠሮ መያዙ ለማወቅ ተችሏል። በመኢአድ በኩል እስካሁን የውህደት በሩ አለመዘጋቱን ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው ወገኖች እየገለፁ ነው። ሆኖም “ትዴኢ” ወደ አንድነት እንዲገባ በትብብሩ ላይ ግፊት እያደረገ ነው በሚል ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የመኢአድ አመራሮች ስጋታቸውን ገልፀዋል።

“ትብብር ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ” ወይም “ትብብር” ሰባት በብሔርና በህብረብሔር የተደራጁ በአመዛኙ በደቡብ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የተሰበሰቡትና በቅርቡም በይፋ መተባበራቸውን ያስታወቁ የፓርቲዎች ስብስብ መሆኑ አይዘነጋም።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>