ደጉ ተፈራ
በሚኒሶታ መዳኒዓለም ቤተርስቲያን የደረሰዉን ዉጣዉረድ ከሩቅ ሆኜ ሳስተዉል ስታዘብ ቆየዉና ዉሸት ሲበዛ ባጭሩ ምስክርነቴን ልሰጥ ተነስቻለሁ።
እባካችሁ የእግዚዓብሄርን ስም በከንቱ አትጥሩ፤ ቃሉ ያዛልና!
ክርስቶስ የከበረ ደሙን አፍስሶ ቅዱስ ሥጋዉን ቆርሶ ያዳነን በከንቱ ስሙን እንድንጠቀምበት አይደለም።
በመጀመጀመሪያ መልእክቴ፣ መላዉ ህዝበ ክርስቲአን ሆይ በማስተዋል ባላችሁበት ጽኑ ማንም ስለኣግዚዓብሄር ቤት የተጣላ የለም።
ስለገንዘብና ስለስልጣን ነዉ እንጂ፤ ለዚህም መረጃ ልፃፍ ብል ወረቀት አይበቃኝም። መዳኒታችን እዉነት ቢሆን እውነት በሉ ሐሰትም ቢሆን አይደለም በሉ ብሎ አስተምሮናልና፤ እባካችሁ በአፈጮሌዎች እንዳትደናበሩ። ወጣት አዛዉንቱ በጥይት ሲደደበደብ፣ ሕዝብ በዘር ሲከፋፈል ሲጋደል፣ ገዳም ሲመዘበር ሲቃጠል እግዚኦታና ምህላ የነፈገ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያን ነዉ ብላችሁ እንዳትገቡ።
የሚቀጥለው መልእክቴ ለአቶ አብርሃም ሰለሞን
ጤይናይስጥልኝ አቶ አብርሃም ስሜንም ባልነግርሆት በሃሳብ በደንብ እንተዋወቃለን። በሬዲዮ እንደሰማሁት ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ቤት እንጂ የደርግም አይደለችም የወያኔም አይደለችም የቅንጀትም አትሆንም ብለው አሳምረው ተናግረዋል አቤት አማርኛው አናጋገሩ ሲያምር ምናለ ግን እውነት ቢሆን? ትዝ ይልዎታል የዛሬ 12 ዓመት የመሐበረ ቅዉሳን አባላት በመዳኒዓለም ቤ/ክ ሲሰባሰቡ ምን ነበረ ያሉት ያስታውሳሉ? ላስታውሶዎት፤ እነዚህ ልጆች ከተሰባሰቡ ቤተክርስቲያናችንን በወያኔ በሚመራው ሲኖዶስ ያሶስዱብናል በማለት በድብቅ ያሳደሙባቸው እና ወደማሪያም ቤ/ክ እንዲሰደዱ ያደረጉት የዉስጥ ዘመቻ ማሳደም እንዴት ረሱት ወይስ ታዛቢ የለም ብለው ነው? ወይስ ለወያኔው ሲኖዶስ ንስሐ ገብተው ነው? ኽረ ያስታዉሱ አዲስ አገልጋይ ሲመጣ እንኳ ዘሩን ያጣሩ ነበር ቤተክርስቲያንዎት እንዳይወሰድብዎት! ከዚበዋላ በእግዚዓብሄ ስም አትነግዱ ይበቃል።
ደግሞም ስለሲኖዶስ ለማውራት ሲቃጣዎት ስምቼ ገርሞኛል እባካቹ ምመኑን ግራ አታጋቡት ስልሲኖዶስ ትርጉም እንማማር ካላችሁ በትክክል በፍትሃነገስቱ ላይ ያለዉን፣ የሐዋሪያት ጉባአኤ እንደሆነ መወያየት እንችላለን ደግሞም ግብጽም፣ ግሪክም፣ ራሺያም ሌሎቹም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲአናት እንደዚሁ ሽፍታ ሲያስቸግራቸዉ ለህዝባችው ደንነት ሲሉ ሁለተኛም ሲኖዶስ ነበራቸው ገለልተኛም ሆነዋል። ሌላው መዘንጋት የሌለበት ገለልተኝንትን የጀመሩት አቡነ ጳውሎስ እንደነብሩና ወያኔ ስልጣን ሲይዝ እሳቸውም ስልጣን እንደተስጣቸውና የወያኔው ሲኖዶስ ፓትሪያርክ እንደነበሩ እናስታውሳልን። ስለዚህ ስለሲኖዶስ ትርጉም መቀባጠራችሁን አቁሙ።
አቶ አበርሃም እኔ እንደርስዎ ያዳነኝን የመዳኒቴን ስም ያለአግባብ ለግል ጥቅሜ ለማጭበርበር አልጠራም እባክዎን የግል ሐሳብሆን ያለመጽሓፍውዱስ ጥቅስ ለመጥቅስ ሞክሩ ካለብለዛ ግን የርስዎ ብእር ለውሸት ከበረታችና ቃል ካጣመመች የኔ ብእር ደግሞ ለህዝቡ እያቃናች ታቀርባልች።
በእግዚዓብሄር የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሆይ ሰላም ከሁላችን ጋራ ይሁን።