Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

ሰበር ዜና ፤ መቀሌ – የፀጥታ ኃይል እጥረት አለብን ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አትችሉም!!

$
0
0

ሰበር ዜና፤ አቶ ጌታቸው ገ/ስላሴ የከንቲባ ጽ/ቤት ሀላፊ ፣አቶ ወልዳይ የተባሉና የመቀሌ ዞን የፀጥታ ኃላፊ እንዲሁም ከመቀሌ ወጣቶች ማህበር ተወከልኩ ያለ ግለሰብ የአንድነት አመራሮቸን በመጥራት “መንግስት አጠቃላይ ግምገማ ላይ ስለሆነ የፀጥታ ኃይል እጥረት አለብን” በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አትችሉም ብለዋቸዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችም መልሳቸሁ ህግ የተከተለ አይደለም፤ እኛ ህገመንግስታዊ መብታችንን ጠይቀናል በየትኛውም ሁኔታ ሰልፉን አንሰርዝም፡፡” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በመቀሌ የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ አባላት በደህንነት ኃይሎች ዛቻ እየደረሰባቸው መሆኑ የደርሰን ዜና ያመለክታል።
የሰላማዊ ሰልፍ “የአሸባሪዎች ተላላኪ ናችሁ የመቀሌ ህዝብ እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ አይፈልግም” በማለት አንድነት ፓርቲን የሚመለከት በራሪ ወረቀት የመበተንም ሆነ የቅስቀሳ ስራ የሚያከናውን ሰው ላይ ጥብቅ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉም ዝተውባቸዋል፡፡ ሆኖም በመቀሌ የሚገኙት የአንድነት አመራሮች ለሰላማዊ ሰልፉ ቅስቀሳ ለመጀመር ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ለአከባቢው ባለስልጣናት አሳውቀዋል፡፡ ‪#‎milionsofvoicesforfreedom‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬


Viewing all articles
Browse latest Browse all 13695

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>