Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all 13695 articles
Browse latest View live

ኢትዮጵያዊነት – ”የለህም ይሉኛል፤ እውነት የለሁም ወይ?”

$
0
0

ከመስፍን ነጋሽ (ጋዜጠኛ)
(የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ)

(ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ)

(ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ)

ከማንነት ጋራ የተያያዙ ጥያቄዎች፣ ሙግቶች፣ በተቃራኒውም አስቀያሚ ሐሳብ አልባ ስድድቦች ሰሞኑን በርከትከት ብለዋል። ጥያቄዎቹና ሙግቶቹ መኖራቸውን አጥብቄ እደግፈዋለሁ። በእኔ እይታ አብዛኞቹ ምልልሶች ወይም ሙግቶች በመሠረቱ አዲስ ጭብጥም ሆነ መከራከሪያ አላቀረቡም። ቢሆንም የነበረውንም ቢሆን በአግባቡ በተደጋጋሚ እያነሱ ሐሳብ መለዋወጡ ጠቃሚ ነው፤ ሙከራው ቢያንስ እርስ በርስ መተዋወቅን ይጨምራል፤ አልፎም አዲስ ሐሳቦችን ለማፍለቅ እድል ይሰጣል።

የማነ ናግሽ ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት የለም፤ ያለው በብሔረሰብ ላይ የተመሰረተ ማንነት ብቻ ነው የሚለውን ሐሳብ በትግሪኛ ጽፎት ተመልክቼ ነበር። ኃላም ራሱ ወደ አማርኛ እንደመለሰው ይህን ጽሑፍ ወደማጠናቀቁ ስቃረብ ተመልክቻለሁ። በመሠረቱ ሐሳቡ አዲስ አይደለም። በየማነ አስተያየት መነሻነት ሌሎችም አመለካከታቸውን አካፍለዋል፤ ጥቂቶቹን በሚገባ አንብቤያለሁ። በሒደቱ የታየው ጉዳዩን ከመመርመር ይልቅ ተናጋሪውን የማጥቃት ስልት ጠቃሚ ስላልሆነ ወደዚያ አንመለሰም። በሐሳቡ ላይ ግን አስተያየቴን ላካፍል።

1. ስለማንነት እንደመነሻ

ሁልጊዜም ከጥንቱና ከስሩ መጀመር ጠቃሚ ቢሆንም ጽሑፌን ወደ መጽሐፍ ምእራፍነት እንዳይቀይረው በመስጋት፣ ከዚያ በላይ ደግሞ አንባቢዎቼ ስለማንነት እና ስለፖለቲካው መሠረታዊ ጉዳዮች ያውቃሉ ከሚል እምነት ስለማንነት ወደመዘርዘር አልገባም። በምትኩ ለክርክሬ የሚሆኑኝን መነሻዎች ብቻ እጠቅሳለሁ። አምስት ጭብጦች ላስይዝ፤
Map ethiopia
1.1. አንድ ሰው ብዙ አይነት ማንነቶች ሊኖሩት ይችላሉ፤ ይኖሩታልም። አንድ ማንነት በጉልህ የሚታየው ከሌላው ጋራ ሲነጻጸር እንደመሆኑ መጠን፣ አንድ ሰው ማንነቱን የሚገልጽበት መንገድ እንደሁኔታው ይለያያል። ጥያቄው ሃይማኖትን ሲከተል፣ ሃይማኖታዊ ማንነቱን ያስቀድማል እንደማለት። እዚህ የምናነሰው ግን ቋንቋን ጨምሮ ከተመሳሳይ ባህል፣ ታሪክ እና ስነልቦና ጋራ ስለተቆራኘው ማንነት ነው። የማንነት ፖለቲካ በአገራችን በዋናነት የሚወከለውም በዚሁ ነው። ለውይይታችን እንዲረዳ በብሔረሰባዊ እና በአገራዊ ማንነት ላይ ብቻ እናተኩር።

1.2.ማንነት (ብሔረሰባዊም ይሁን አገራዊ) ማኅበረሰብ ሠራሽ ነው፤ ተፈጥሯዊ አይደለም። ማንነት ከቤተሰብ፣ ከማኅበረሰብና ከትምህርት ቤት የምንማረው ነው። ስለዚህም ባለበት አይረጋም፤ መጠነኑና ፍጥነቱ ቢለያየም ይለወጣል።

1.3.ማንነት በአጋጣሚ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ በመወለድ እና/ወይም በማደግ፣ አለዚያም በተጽእኖ ሊገኝ ወይም ሊለወጥ ይችላል። ይህ ብቻ ግን አይደለም። ማንነት በምርጫም ሊገኝ ይችላል፤ አንድ ሰው በፍላጎቱ የአንድ ማንነት አካል ሊሆን ይችላል፤ ምን ያህል ይሳካለታል የሚለውን የሚወስኑ ብዙ ከእርሱ ውጭ የሆኑ ሁኔታዎች ቢኖሩም። አንዳንድ ማኅበረሰቦችና ማንነቶች ከሌላው የበለጠ አዲስ መጤን የመቀበልና የማዋሐድ ጠባይ አላቸውና።

1.4. አንድ ማንነት ከቀላል ጀምሮ ወደ ውስብስብና ብዙ እንደሚያድግ ሁሉ፣ ማንነቶች ሊወራረሱ፣ አልፎም ማንነቶች ተደባልቀው/ተዋሕደው ”አዲስ/የተለየ” ማንነት ሊፈጥሩም ይችላሉ።
1.5. በማንኛውም መንገድ መስተጋብር የመፍጠር እድል ያገኙ ማንነቶች የተለያዩ እሴቶቻቸውን ይለዋወጣሉ፣ ይዋዋሳሉ፣ ያዳቅላሉ። እንዳለ የሚያስጠብቁት የማንነታቸው አካል መኖሩ እንደማይቀርም እሙን ነው። ስለዚህም ንጹህ የሚባል ማንነት አይኖርም። ንጹሕ የሚባል ማንነት ካለ ያ ማንነት በላቦራቶር የተፈጠረና እስካሁንም ወደምንኖርባት የሰው ዓለም ያልመጣ ማንነት ነው።

ከዚህ የሚከተለው ክርክሬ ቢያንስ በእነዚህ አምስት መንደርደሪያዎች ላይ የተመሠረተ ይሆናል። እነዚህን መነሻዎች ይዘን ወደ ጥያቄው እንመለስ። እውነት ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም?

በአገራችን የብሔረሰብ ማንነት አለ፤ ራሱን የዚህ ወይም የዚያኛው ብሔረሰብ አባል አድርጎ የሚመለከት ሰውም አለ። ይሄ ለክርክር የሚቀርብ፣ ያልተረጋገጠ ጉዳይ አይደለም። ይህኛው ቡድን ”ብሔርሰብ ነው ወይስ ዘውጌ ወይስ ጎሳ?” የሚለው ጥያቄ ላነሳነው ክርክር አስፈላጊ አይደለም። ለአሁኑ፣ ቁም ነገሩ፣ የራሳችን ባህላዊና ታሪካዊ ማንነት አለን የሚሉና ያላቸው ብድኖች መኖራቸው ነው። ስለዚህ ”እኔ የእገሌ ብሔረሰብ አባል ነኝ፤ የዚያኛው አይደለሁም፤ ማንነቴም አገው፣ ትግራዋይ፣ ጉሙዝ፣ ኦሮሞ፣ አማራ…ነው” የሚሉ ሰዎች አሉ። መኖራቸው እውነት ነው፤ በአግባቡ ከተያዘም ጸጋ ነው። አሁን የቀረበው ጥያቄ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት እነዚህ ብሔረሰባዊ ማንነቶች ብቻ ናቸውን የሚል ነው። ወይም፣ ኢትዮጵያዊ ማንነት የለምን? እርግጥ የአንድ ማንነት ታጋሪዎች ነን የሚሉ ሰዎች እስካሉ ድረስ ስለማንነቱ ለማረጋገጥ ሌላ ምርመራ ማድረግ የግድ አይደለም ብሎ የሚከራከር ይኖር ይሆናል። በዚህ ስሌት፣ ”ኢትዮጵያዊ ማንነት አለን” የሚሉ ሰዎች መኖራቸው ብቻውን በቂ ማስረጃ በሆነ ነበር። ቢሆንም ተጨማሪ ሐሳቦችን መለዋወጡ አይጎዳም።

2. ኢትዮጵያዊ/አገራዊ ማንነት የለም የሚሉ ሰዎች ቢያንስ አራት ስሕቶችን ይፈጽማሉ።

2.1. ከፍ ሲል የጠቀስኩትን የማንነቶችን መወራረስ፣ አልፎም የአዲስ ማንነቶች መፈጠር አይቀበሉም። ይህ ማለት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ብሔረሰቦች (የፖለቲካ ማኅበረሰቡ አባል የሆኑት ወደውም ይሁን ተገደው) በታሪክ ባካሔዱት መስተጋብር የሁሉም ”ቅልቅል” የሆነ (ምናልባትም የሆኑ) አዲስ ማንነቶች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ አይቀበሉም ማለት ነው። አዳዲስ ማንነቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ ብለው ካመኑ ክርክራችን በአገራችን አዲስ ማንነቶች ስለመፈጠራቸው እና ስለተፈጠረው/ስለተፈጠሩት አዲስ ማንነቶች ስያሜ ይሆናል ማለት ነው። በእኔ እምነት፣ በረጅሙና በውስብስቡ የአገረ ኢትዮጵያ መስተጋብር አዳዲስ ማንነቶች ተፈጥረዋል። (ይህ ማለት የብሔረሰብ ማንነቶች ጠፍተዋል ማለት አይደለም፤ እርግጥ ባሉበት አንዳችም ሳይለወጡ ቀጥለዋል – ንጽሕ የሚለው ቁልምጫ ትርጉሙ እርሱ ይመስላል- ማለትም ቢያንስ ፖለቲካዊ የዋህነት ይሆናል።) ከተፈጠሩት ”አዲስ/የተለዩ” ማንነቶች አንዱና ዋናው ብዙዎቻችን ”ኢትዮጵዊነት” የምንለው ማንነት ነው። ስለዚህ ማንነት አይነቶች ወይም አረዳዶች ወደ ኋላ አነሳለሁ፤ የችግሩ መነሻ ”ኢትዮጵያዊነት” የሚለው ስያሜ ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም መስጠቱ ሊሆን ይችላልና።

2.2. ተከታዩ ስህተት አንድ ሰው ከአንድ በላይ ማንነት ሊኖረው አይችልም፣ አንዱን ማንነት ሲቀበል ሌላውን መተው አለበት፣ ወይም የቀደመ ማንነቱን ከአዲስ ማንነት ጋራ ማዳበል ወይም ማዋሐድ አይችልም ከሚል የተሳሳተ አመለካከት የሚመነጭ ነው። ይህ በንድፈ ሐሳብም ሆነ በተግባር የተሳሳተ ነው። አሁን ያለችውን ኢትዮጵያ ተጨባጭ እውነታም መረዳት ይጎድለዋል። ዛሬ፣ ራሳቸውን በብሔረሰባዊም በአገራዊ ማንነታቸውም የሚገልጹ በሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሰዎች አሉ። ልብ በሉ፣ ለእነዚህ ሰዎች ኢትጵያዊነት ዜግነት ብቻ አይደለም፣ ማንነትም ጭምር ነው። ራስን በብሔረሰብ ማንነት ብቻ ሳይሆን በሃይማኖት ማንነትም ደርቦ መግልጽ እንደሚቻለው፣ ኢትዮጵያዊነትን ተጨማሪ ማንነት ማድረግ እውነት የማይሆንበት ምክንያት አይታየኝም። ብሔረሰባዊም አገራዊም ማንነት ያለቸው ሰዎች ስለመኖራቸው ማረጋገጥ ከባድ አልመሰለኝም። አገራዊ ማንነት የለንም የሚሉ ሰዎችን የግድ ይኑራችሁ ብዬ አልከራከርም። ዝርዝሩ ሌላ ውይይት ይፈልጋልና ልተወው።

2.3. ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም የሚሉት ሰዎች የሚሰሩት ሌላው ስሕተት ከፍትሕ ጋራ የተያያዘ ነው። እነርሱ ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ ”ማንነታችንን ሳታከብር ኖራለች፣ እውቅና ተነፍገን ኖረናል፣ ይህም ሊለወጥ ይገባል” ብለው ይከራከራሉ። ተገቢና እውነት ያለው የፍትሕ ጥያቄ ነውና ከልቤ እደግፈዋለሁ። ይህን እነርሱ የሚጠይቁትን ፍትሕ ግን ለሌሎች፣ ዛሬ ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት አለን ለሚሉትን ወገኖቻቸው እየከለከሉ ነው። አሁንም ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ማንነት ወደ ኋላ አነሳለሁ።

2.4. እነዚህ ሰዎች ከሚሰጡት ማብራሪያ የምንረዳው ሌላው ጭብጥ እውነተኛው/ደንበኛው ማንነት በብሔረሰብ ላይ የተመሰረተው ነው የሚል ነው። እነርሱ ባወጡት የማንነቶች ደረጃ መሠረት፣ ከብሔረሰባዊ ማንነት ውጭ ያሉት ማንነቶች አንድም ውሸት ናቸው አለዚያም ጠንካራ አይደሉም። ብሔረሳባዊ ማንነት ከሌሎቹ ማንነቶች ቀዳሚነት እንዳለው ይሰብካሉ። ይህንን ለፖለቲካ መቀስቀሻነት የሚጠቀሙት ሰዎች ዓላማ የተሰወረ አይደለም። ሐሳቡ ግን በግማሽ እውነት ላይ የተመሰረተ ስንኩል መከራከሪያ ነው። ግለሰቦችና ቡድኖች የሚያስቀድሙት የማንነት መለያ የሚወሰነው በኖሩበትና ባሉበት ታሪካዊ ሁኔታ እንጂ አስቀድሞ በወጣ የማንነቶች ደረጃ አይደለም። ከሌላው ማንነቱ በፊት በሃይማኖታዊ ማንነቱ ራሱን የሚገልጽ ሰው/ቡድን ይኖራል፤ ለሌላው ደግሞ ብሔረሰባዊ አለዚያም አገራዊ ማንነቱን ቀድሞ ይሰማው ይሆናል። ሁሉም የማኀበረሰባቸው ታሪክ ውጤቶች ናቸው። አንዱ ከሌላው የበለጠ ትክክል አይደለም፤ እንደ ግለሰቡ እና ቡድኑ ሊለያይና ሊለዋወጥ የሚችልም ነው። ይህ አመለካከት አንዳንድ ጊዜ ብሔረሰባዊ ማንነታቸውን የማያስቀድሙ ሰዎችን ”የማንነት ችግር” እንዳለባቸው ወይም እየዋሹ እንደሆነ የመክሰስ ድፍረት ተላብሶ የሚታይበት ጊዜም አለ።

3. ኢትዮጵያዊነቶች?

እንደማንኛውም ማንነት ኢትዮጵያዊነትም ብዙ ገጽታዎች አሉት። በታራካዊ ሂደቶችም ብዙ ተለውጧል፤ ገና ይለወጣልም። ኢትዮጵያዊ ማንነት ብዙ ገጽታዎች አሉት ወይም ብዙ አይነት ኢትዮጵያዊ ማንነቶች አሉ ብሎ መነሳት ይቻላል። ለዚህ ጽሑፍ አግባብነት አላቸው ያልኳቸውን ሦስት የኢትዮጵያዊ ማንነት አረዳዶች ብቻ ላስቀምጥ።፡ይህን የማደርገው፣ ኢትዮጵያዊ የምንለው ማንነት ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም እየሰጠ አለመግባባት ፈርሮ እንደሆነ በሚል መነሻ ነው። ለመግባባት ሲባል ለማንነቶቹ ሌላ ስያሜም መስጠት እንችል ነበር፣ ለጊዜው ይቆየን።

3.1. አንደኛው ኢትዮጵያዊ ማንነት ራሱን የሁሉም የአገራችን ብሔረሰቦች አካል አድርጎ ይመለከታል፤ ለአንዱ የተለየ ቅርበት አይሰማውም። እነዚህ ሰዎች ምክንያቱ ምንም ይሁን፣ ራሳቸውን የዚህ ወይም የዚያኛው አንድ ብሔረሰብ አባል አድርገው አይቆጥሩም። የዚህ ማንነት ባለቤት የሆነው ኢትዮጵያዊ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ነገር እኩል ተጋሪ ባለቤት እንደሆነ ያምናል። ብሔረሰባዊ ማንነትን ያከብራል። ብሔረሰባዊ ማንነትን ተገዳዳሪው አድርጎ አይፈራውም። ይህ ማንነት ድንገት ከሰማይ ወርዶ የሁሉም አካል ነኝ የሚል፣ ባለቤት አልባ ማንነት አይደለም። በአብዛኛው በተለይ በከተሞች አካባቢ ያደጉ (ለረጅም ጊዜ የኖሩ) ሰዎች የዚህ ማንነት ተጋሪዎች ናቸው። ባህላዊና ስነልቦናዊ ማንነታቸውን የቀረጸው ያለፉበት ታሪክ ነው፤ ፖለቲካው፣ ጦርነቱ፣ የሕዝብ እንቅስቃሴውና መስተጋብሩ፣ ትምህርቱ፣ የከተሜ ኑሮ…። ለእነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያዊነት ዜግነት ብቻ ሳይሆን ማንነትም ጭምር ነው። ቁጥር የበለጠ ትርጉም የሚሰጣቸው ሰዎች ካሉ፣ የዚህ ማንነት ባለቤቶች ቢያንስ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ስለመሆናቸው አልጠራጠርም። (እኔም ራሴን ያገኘሁት እና መሆንም የመረጥኩት እዚህ ውስጥ ነው።)

3.2. ሁለተኛው ኢትዮጵዊነት የአንድ ብሔረሰብ ማንነት ያለው፣ ነገር ግን በተጨማሪም ኢትዮጵያዊ ማንነት ያለው ነው። በብሔረሰብ ማንነቱ የብሔረሰቡ የሆነውን ሁሉ ይጋራል፤ እዚያ ግን አያቆምም፤ በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ከሎሎች ኢትዮጵያዊ ማንነት ካላቸው ጋራ የሚጋራው ሌላም ብዙ ነገር አለ። ይህ ሰው የሚረዳው ኢትዮጵያዊ ማንነቱ፣ ብሔረሰባዊ ማንነቱን እንዲተው የሚጠይቅ አይደለም። ይህ ማንነት፣ ከከተሞች መስፋፋት፣ ከትምህርትና ከመንግሥት ቢሮክራሲ ዝርጋታ ጋራ እያደገ እንደመጣ እገምታለሁ። አሁንም የዚህ ቡድን አባላት ቁጥር ከአገሪቱ ሕዝብ ከግማሽ በላይ እንደሚሆን አልጠረጥርም። ይህ ባይሆን አገሪቱ ህልውናዋ ባከተመ ነበር ከሚል መነሻ።

3.3. ሦስተኛው ኢትዮጵያዊነት፣ ብሔረሰባዊ ማንነትን የሚክድ ወይም ለማጥፋት የሚፈልግ ተጻራሪ ማንነት አድርጎ የሚመለከት አረዳድ ነው። ከታሪክ አንጻር በከፊል እውነት ነው። ለዚህ አረዳድ፣ ኢትዮጵያዊነት ማለት የክርስቲያን ሰሜን ኢትዮጵያ ባህልና ማንነት ነው። እንደ ጉዳዩ አቅራቢ ይህ ኢትዮጵያዊነት የአማራ ባህልና ማንነት ብቻ ተደርጎ የሚቀርብበት አጋጣሚም አይጠፋም። ለዚህ አመለካከት አስፈላጊው ጭብጥ ግን፣ ”ኢትዮጵያዊ” ማንነት ቀድሞም ይሁን አሁን ሌሎች ባህላዊ ማንነቶችን ለመደፍጠጥ ያሰፈሰፈ ማንነት ተደርጎ መታየቱ ነው። ይህ መሠረተ ቢስ ስጋት ነው ብዬ እንዳልደመድም እነርሱ ”ኢትዮጵያዊነት” ከሚሉት ውጭ ያለ አገራዊም ሆነ ብሔረሰባዊ ማንነት እንዲጠፋ አዋጅ ማወጅ የሚቃጣቸው ሰዎች አሉ። ማለት የምችለው፣ የእኔ ኢትዮጵያዊነት ከዚህ ይለያል። ይህ የኢትዮጵያዊ ማንነት አረዳድ የብሔረሰብ ማንነቶችን የማያከብር፣ ስለመኖራቸውም ሙሉ እውቅና የማይሰጥ ነው። ይህ ኢትዮጵያዊነት ብሔረሳባዊ ማንነቶችን በጥርጣሬ ይመለከታል፣ የአገራዊ መተሳሰር ጠላቶች አድርጎ ይፈርጃል፣ ማንነቶቹን ማዳከምም ይፈልጋል። የዚህ ማንነት አቀንቃኞች በአብዛኛው በአማራ ልሒቃን መካከል የሚገኙ ጥቂቶች ናቸው። እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያዊ ማንነት በዚህ ገጽታው ብቻ ሲወከል ይስተዋላል።

ህወሓት/ኢሕአዴግ በስልጣን ዘመኑ የመጀመሪያ አስር ዓመታት ሆን ብሎ ሁሉንም ኢትዮጵያዊነቶች በጅምላ እንዲጠሉ ብዙ ሰርቷል። ሌሎቹ ብሔረሰብ ተኮር ፓርቲዎችም ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ስትራቴጂ ተከትለዋል። ስጋታቸው ግልጽ ነው፤ የብሔረሰባቸው አባላት ኢትዮጵያዊ ማንነትን ከደረቡ የደጋፊ መጠናቸው ሊቀንስ ይችላል። በውጤቱም፣ ዛሬ፣ ”ኢትዮጵያዊ ማንነት” ሲባል በብዙ የአደባባይ ሰዎች ዘንድ አስቀድሞ የሚጠቀሰው ይህ ሦስተኛው አመለካከት ብቻ ሆኗል። የፖለቲካ ልሒቃኑ ኢትዮጵያዊነትን በቀዳሚዎቹ ሁለት መልኮቹ የሌለ በማስመሰልም፣ ሦስተኛውን ግን በማጉላት፣ የማንነቱን ባለቤቶች በጅምላ ጥፋተኞችና ተጠርጣሪዎች አስመስለው ያቀርቧቸዋል። ይህ ስህተት ብቻ ሳይሆን ሸፍጥም ነው። የሸፍጥነቱ ስላቅ ወደዜኒቱ የደረሰው፣ እነመለስ ደርሶ የሁለተኛው ዓይነት/አረዳድ ኢትዮጵያዊነት (3.2) አራማጆች ሆነው፣ ባንዲራ መስቀልና ስለሺህ ዓመት የኢትዮጵያ ታሪክ መስበክ ሲጀምሩ ነበር። ሌላው በጣም የሚገርመኝ ነገር፣ የመጀመሪያው ዓይነት ኢትዮጵያዊ ማንነት ያላቸው ዜጎች መኖራቸውን ገዢው ፓርቲ ጭምር ዛሬም ድረስ እውቅና ለመስጠት መፍራታቸው ነው።

ብሔረሰባዊ ማንነትን የፖለቲካቸው ማቀጣጠያ አድርገው መጠቀም የሚፈልጉ ልሒቃን፣ እንዲሁም ከማንነት ፖለቲካና የውድድር ስሜት የሚመጣው ስሜተ-ስሱነት የሚያስከትለውን ሚዛን የመሳት አደጋ ቀድመው ያልጠረጠሩ ሰዎች፣ በአገራችን ውስጥ ያሉት ብሔረሰባዊ ማንነቶች ብቻ ናቸው ይላሉ። ይግረማችሁ በማለትም፣ ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም ይላሉ።

ማንኛውም ማንነት እና ከእርሱ ጋራ ተያይዘው የሚመጡ ስሜቶች (የኩራት-ሃፍረት፣ የበላይ-የበታችነት፣ የአሸናፊ-ተሸናፊነት፣ የጊዜው የእኛ ነው-አይደለም፣ የተስፋ-ስጋት ወዘተ) መኖራቸውን ማስቀረት ባይቻልም መጠናቸውን ሲያልፉ ከፍተኛ አደጋን ይጋብዛሉ። አደጋው ሐልዮታዊ ብቻ ሳይሆን ማኅበረሰባዊም ነው። በሐልዮት ደረጃ፣ አሁን እንደምናየው፣ ”ያለሁት እኔ ነኝ እንጂ አንተ አይደለም” እስካማስባል ያደርሳል። አገራችንም ሆነች ዓለማችን በዚህ መሰሉ ሚዛኑን የሳተ የማንነት ስሜት ብዙ ዋጋ ስለመክፈላቸው ታሪክ ብዙ ያስነብበናል። አገራዊ ማንነት ሲጦዝ ሌላውን አገር በእብሪት ወደ መውረር ስካር ያመራል፤ በቆዳ ቀለም መኩራት (የሚያኮራ ከሆነ) ከዚያ አልፎ የበላይነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሆኖ ሲወሰድ ወደ አፓርታይድ ያደርሳል፤ በብሔረሰባዊ ማንነት ኮርቶ ራስን ማስተዳደርና ባህልን ማዳበር ከዚያ አልፎ የሌላውን (በተለይ ተፎካካሪ ተደርጎ የሚቆጠረውን) ማንነት መኖርና አለመኖር (በሐልዮትም ይሁን በአካል) ለመወሰን ወደሚያስችል ስልጣንነት ሲቀየር የመጠፋፋት በር ማንኳኳቱን ልብ እላለሁ፤ እሰጋለሁም።

ማንኛውም ብሔረተኝነት በጋራ ታሪክና መጻኢ እጣ ሚዛን መገደብ አለበት። ይህ ካልሆነ፣ ገደብ አልባ በራስ የመተማመን እና የእርግጠኝነት ስሜት ይፈጥራል። ትህትናንና መተሳሰብን ከግለሰብ ልብ፣ ከቡድን የጋራ ስነልቦና ያጠፋል። ይህ ስሜት በግለሰብም በቡድንም ደረጃ ሊንጸባረቅ ይችላል።

ኢትዮጵያዊ ማንነት አለ። ኢትዮጵያዊ ማንነት የሚለው አገላለጽ የሚወክለው መጥፎ የታሪክ አሻራም አለ። የመጥፎው አሻራ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያዊነት አረዳድ በሒደት እየተዳከመ መሔዱ ግልጽ ነው። ምኞቴም ነው። ሌሎቹ ሁለቱ አይነት ኢትዮጵያዊ ማንነቶች ግን የታሪካችን ተጨባጭና በጎ ውጤቶች አድርጌ አያቸዋለሁ። ምንልባትም መጻኢው የኢትዮጵያ መልካም እጣም ያለእነርሱ እውን የሚሆን አይመስለኝም። ራሴንና መሰሎቼን እንዴት ከነገው መልካም ቀን አውጤቼ ልመለከት እችላለሁ? እንዴትስ፣ ”እንኳን የነገው አካል ልትሆን፣ ዛሬም የለህም” ስባልስ ዝም እላለሁ?! ኢትዮጵያዊነት አለ። የለም ስለተባለም አይጠፋም። እኔ አለሁ።

* መስፍን ይህ ጽሁፍ በፌስቡክ ሰሌዳው ላይ ያቀረበው ነው። ጽሁፉን በፌስቡ ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአንድነት መሪዎች መታሰርን አይፈሩም – ግርማ ካሳ

$
0
0

አዲሱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉ፣ ለገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የሰላምና የእርቅ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። «ኢሕአዴግ እኛን እንደ ጠላት እና ሽብርተኛ ማየቱን ማቆም አለበት። እኛም ደግሞ ኢሕአዴግን እንደ አዉሬ ማየት ማቆም አለብን። ከጥላቻ ፖለቲካ በመዉጣት ችግሮቻችንን በሰላም መፍታት መማር አለብን» ሲሉ ነበር፣ ለአገር በሚጠቅሙ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢሕአዴግ ጋር ለመስራት፣ ያሉትን ልዩነቶችን በዉይይት ለመፍታት አንድነት ፍላጎት እንዳለው የገለጹት።

ይህ የአንድነት ዘመናዊ፣ የሰለጠነ፣ የፍቅርና የመግባባት ፖለቲካ፣ በኢህአዴግ ዉስጥ ያሉ ሞደሬቶችን ሳይቀር፣ አብዛኛዉን ኢትዮጵያዊ ያስደሰተ ቢሆንም፣ ስልጣኑን በያዙ በኢሕአዴግ አክራሪዎች ዘንድ ግን የተገኘዉ የአጸፋ ምላሽ የሚያስደስት አይደለም። ገዥዊ ፓርቲ ኢሕአዴግ ፣ አሁንም የአንድነት ፓርቲን እንደ ጠላት በማየት ፣ አንድነትን ለማዳከም አሳዛኝና አሳፋሪ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነዉ። ወደ መሃል መጥተዉ፣ ለዉይይት ይዘጋጃሉ ብለን ስንጠብቅ፣ ጭራሹኑ እያከረሩ ነዉ። የታሰሩ የሕሊና እስረኞቹን ይፈታሉ ብለን ስንጠብቅ፣ ጭራሽ የጊዜ ገደባቸው የጨረሱ እንደ አቶ በቀለ ገርባ ያሉ እስረኞችን አንፈታም እያሉ ነዉ። ጭራሽ ሌሎች ሰላማዊ የፖለቲካ ታጋዮችን በተለይም ከአንድነት ፓርቲ እያሰሩና ለማሰርም እየተዘጋጁ ነዉ።

ለረዥም ጊዜ የአንድነት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ሆነው ያገለገሉትና፣ አሁን ደግሞ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት፣ አቶ አስራት ጣሴ በአሁኑ ጊዜ ታስረዋል። የታሰሩት በአንድ ጋዜጣ ላይ፣ «በፍርድ ቤቶች ፍርድ ማግኘት አይቻልም» በማለታቸው ነዉ። እዉነትን በመናገራቸው።

የአንድነት ልሳን ፍኖት ጋዜጣም፣ በፍትህ ሚኒስቴር ዉስጥ ያሉትን ምንጮች በመጥቀስ፣ በኢሕአዴግ ጽ/ቤት ትእዛዝ፣ አቶ ዳንኤል ተፈራ እንዲሁም ሌሎች የአንድነት አመራር አባላትን ለማሰር የክስ ሰነድ እንደተዘጋጀም ዘግቧል።

ይህ የአንድነት አመራር አባላትን ለማሰርና ለማዋከብ የሚደረገዉ ጥረት፣ ምክንያቱ አንድና አንድ ነዉ። ኢሕአዴግ፣ የአንድነት ፓርቲ አሰላለፍ በጣም ስላሰጋዉ፣ መሪዎችን በማሰርና የፓርቲዉን አባላትና ደጋፊዎች በማስፈራራት፣ ፓርቲዉን ከወዲሁ ለማዳከም ነዉ።

የአንድነት ፓርቲ በአሁኑ ወቅት፡

1) ከሰማያዊና ከኤዴፓ በስተቀር፣ ከበርካታ ደርጅቶች ጋር ለመዋሃድ ትልቅ ሥራ እየሰራ ነዉ። በተለይም ከመኢአድ እና ከአራና ጋር ዉይይቱ ሥር የሰደደ ይመስላል።

2) በአድዋ ከተማና በአዲስ አበባ፣ የአድዋን ድል በአል ለማክበር፣ እንዲሁም፣ በአማራዉ ክልል የሚኖረዉን ሕዝብ የተሳደቡ የብአዴን አመራር አባል ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚጠይቅ፣ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በባህር ዳር ለማድረግ አቅዷል።

3) የሚሊየነም ድምጽ ለነጻነት ክፍል ሁለት ዘመቻ በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ይፋ ለማድረግ በዝግጅት እንዳለ ይነገራል።

እነዚህና የመሳሰሉት የአንድነት እንቅስቃሴዎች፣ የፖለቲካዉን አስተላለፍ በእጅጉ የሚቀየሩ እንደመሆናቸው፣ በገዢው ፓርቲ ዉስጥ ያሉ ፖሊሲ አዉጭዎችን ማሳሰቡ አያስገርምም። አንድነት፣ የኢሕአዴግ ስርዓት ለመቀየር ና ለዉጥ ለማምጣት ሰላማዊና ሕግን በተከተለ መንገድ ስራዉን ሲሰራ፣ ኢሕአዴጎችም በስልጣናቸው ለመቆየት የራሳቸዉን ሥራ መስራት የሚጠበቅ ነዉ። የሚያወቁትና የለመደባቸው ደግሞ ዜጎችን ማሰርና ማዋረድ ስለሆነ ይኸዉ እያሰሩ ነዉ።

ይህ በኢሕአዴግ፣ አመራር አባላቱን በማሰር አንድነቶች ለማስፈራራት የሚደረገዉ እንቅስቃሴ የሚሰራ ግን አይመስለኝም። የአንድነት ፓርቲ መሪዎች፣ ትግሉን ሲቀላቀሉ፣ እንደሚታሰሩ፣ ሊገደሉ እንደሚችሉ በማወቅ ነዉ። በብርቱካን ሚደቅሳ፣ በአንዱዋለም፣ በእስክንደር ነጋ …የሆነዉን ያውቃሉ። ነገር ግን ከምቾታቸዉና ከጥቅማቸው ይልቅ አገራቸውን ያስቀደሙ በመሆናቸው ፣ ለእስራቱም ሆነ ሊመጣ ለሚችለው መከራ የተዘጋጁ ይመስላል።

እንግዲህ መልእክቴ ይሄ ነው። ኢሕአዴግ በአንድነት ፓርቲ ላይ በአንድ በኩል የያዘዉን ጠመንጃ ተጠቅሞ ጫና ሲያሳደር፣ አገር ቤት ያሉ ታጋዮች ሕይወታቸውን መስመር ላይ አድርገዉ ዋጋ ለመክፈል ሲዘጋጁ፣ እኛ ደግሞ የአንድነት ፓርቲን ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ በመርዳትና በመደገፍ ማጠናከር አለብን። የአራት ኪሎ ባለስልጣናት በያዙት ዱላ ይተማመናሉ። አንድነት፣ በኔ እና በ እናንት፣ በኛ ፣ አገር ቤት ባለነውም ሆነ በዉጭ በምንኖር ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ጉልበት ይተመመናል።

እንግዲህ ጨዋታዉ ተጀምሯል። ፊሽካዉ ተነፍቷል። ተስፋ ቆርጠን፣ «አይቻልም» ብለን ሜዳዉን ለቀን ከወጣን በፎርፌ ዜሮ ገባን ማለት ነዉ። ነገር ግን ዝምታ፣ ተስፋ መቁረጥ አይሁን። ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ።

ለኢሕአዴጎች ይህንን እላለሁ። «ጸሃይ ሳትጠልቅ ቀናዉን ነገር ማድረግ ተማሩ። ትንሽ እንኳ የሰላም ነገር ልባችሁ ይግባ። ይህ በሌሎች ላይ የመዘዛችሁት ሰይፍ መልሶ እናንተኑ ነዉ ስለሚበላችሁ ሰይፋችሁን ወደ ሰገባው መለሱና ለሰላም እጆቻችሁን ዘርጉ»

ESAT Radio Feb 08

$
0
0
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ESAT Fund Raising event Melbourne Australia Feb 15.2014

ኢትዮጵያዊነት – ”የለህም ይሉኛል፤ እውነት የለሁም ወይ?” – መስፍን ነጋሽ

$
0
0

ከማንነት ጋራ የተያያዙ ጥያቄዎች፣ ሙግቶች፣ በተቃራኒውም አስቀያሚ ሐሳብ አልባ ስድድቦች ሰሞኑን በርከትከት ብለዋል። ጥያቄዎቹና ሙግቶቹ መኖራቸውን አጥብቄ እደግፈዋለሁ። በእኔ እይታ አብዛኞቹ ምልልሶች ወይም ሙግቶች በመሠረቱ አዲስ ጭብጥም ሆነ መከራከሪያ አላቀረቡም። ቢሆንም የነበረውንም ቢሆን በአግባቡ በተደጋጋሚ እያነሱ ሐሳብ መለዋወጡ ጠቃሚ ነው፤ ሙከራው ቢያንስ እርስ በርስ መተዋወቅን ይጨምራል፤ አልፎም አዲስ ሐሳቦችን ለማፍለቅ እድል ይሰጣል።

የማነ ናግሽ ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት የለም፤ ያለው በብሔረሰብ ላይ የተመሰረተ ማንነት ብቻ ነው የሚለውን ሐሳብ በትግሪኛ ጽፎት ተመልክቼ ነበር። ኃላም ራሱ ወደ አማርኛ እንደመለሰው ይህን ጽሑፍ ወደማጠናቀቁ ስቃረብ ተመልክቻለሁ። በመሠረቱ ሐሳቡ አዲስ አይደለም። በየማነ አስተያየት መነሻነት ሌሎችም አመለካከታቸውን አካፍለዋል፤ ጥቂቶቹን በሚገባ አንብቤያለሁ። በሒደቱ የታየው ጉዳዩን ከመመርመር ይልቅ ተናጋሪውን የማጥቃት ስልት ጠቃሚ ስላልሆነ ወደዚያ አንመለሰም። በሐሳቡ ላይ ግን አስተያየቴን ላካፍል።

1. ስለማንነት እንደመነሻ
ሁልጊዜም ከጥንቱና ከስሩ መጀመር ጠቃሚ ቢሆንም ጽሑፌን ወደ መጽሐፍ ምእራፍነት እንዳይቀይረው በመስጋት፣ ከዚያ በላይ ደግሞ አንባቢዎቼ ስለማንነት እና ስለፖለቲካው መሠረታዊ ጉዳዮች ያውቃሉ ከሚል እምነት ስለማንነት ወደመዘርዘር አልገባም። በምትኩ ለክርክሬ የሚሆኑኝን መነሻዎች ብቻ እጠቅሳለሁ። አምስት ጭብጦች ላስይዝ፤
1.1. አንድ ሰው ብዙ አይነት ማንነቶች ሊኖሩት ይችላሉ፤ ይኖሩታልም። አንድ ማንነት በጉልህ የሚታየው ከሌላው ጋራ ሲነጻጸር እንደመሆኑ መጠን፣ አንድ ሰው ማንነቱን የሚገልጽበት መንገድ እንደሁኔታው ይለያያል። ጥያቄው ሃይማኖትን ሲከተል፣ ሃይማኖታዊ ማንነቱን ያስቀድማል እንደማለት። እዚህ የምናነሰው ግን ቋንቋን ጨምሮ ከተመሳሳይ ባህል፣ ታሪክ እና ስነልቦና ጋራ ስለተቆራኘው ማንነት ነው። የማንነት ፖለቲካ በአገራችን በዋናነት የሚወከለውም በዚሁ ነው። ለውይይታችን እንዲረዳ በብሔረሰባዊ እና በአገራዊ ማንነት ላይ ብቻ እናተኩር።
1.2.ማንነት (ብሔረሰባዊም ይሁን አገራዊ) ማኅበረሰብ ሠራሽ ነው፤ ተፈጥሯዊ አይደለም። ማንነት ከቤተሰብ፣ ከማኅበረሰብና ከትምህርት ቤት የምንማረው ነው። ስለዚህም ባለበት አይረጋም፤ መጠነኑና ፍጥነቱ ቢለያየም ይለወጣል።
1.3.ማንነት በአጋጣሚ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ በመወለድ እና/ወይም በማደግ፣ አለዚያም በተጽእኖ ሊገኝ ወይም ሊለወጥ ይችላል። ይህ ብቻ ግን አይደለም። ማንነት በምርጫም ሊገኝ ይችላል፤ አንድ ሰው በፍላጎቱ የአንድ ማንነት አካል ሊሆን ይችላል፤ ምን ያህል ይሳካለታል የሚለውን የሚወስኑ ብዙ ከእርሱ ውጭ የሆኑ ሁኔታዎች ቢኖሩም። አንዳንድ ማኅበረሰቦችና ማንነቶች ከሌላው የበለጠ አዲስ መጤን የመቀበልና የማዋሐድ ጠባይ አላቸውና።
1.4. አንድ ማንነት ከቀላል ጀምሮ ወደ ውስብስብና ብዙ እንደሚያድግ ሁሉ፣ ማንነቶች ሊወራረሱ፣ አልፎም ማንነቶች ተደባልቀው/ተዋሕደው ”አዲስ/የተለየ” ማንነት ሊፈጥሩም ይችላሉ።
1.5. በማንኛውም መንገድ መስተጋብር የመፍጠር እድል ያገኙ ማንነቶች የተለያዩ እሴቶቻቸውን ይለዋወጣሉ፣ ይዋዋሳሉ፣ ያዳቅላሉ። እንዳለ የሚያስጠብቁት የማንነታቸው አካል መኖሩ እንደማይቀርም እሙን ነው። ስለዚህም ንጹህ የሚባል ማንነት አይኖርም። ንጹሕ የሚባል ማንነት ካለ ያ ማንነት በላቦራቶር የተፈጠረና እስካሁንም ወደምንኖርባት የሰው ዓለም ያልመጣ ማንነት ነው።

ከዚህ የሚከተለው ክርክሬ ቢያንስ በእነዚህ አምስት መንደርደሪያዎች ላይ የተመሠረተ ይሆናል። እነዚህን መነሻዎች ይዘን ወደ ጥያቄው እንመለስ። እውነት ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም?

በአገራችን የብሔረሰብ ማንነት አለ፤ ራሱን የዚህ ወይም የዚያኛው ብሔረሰብ አባል አድርጎ የሚመለከት ሰውም አለ። ይሄ ለክርክር የሚቀርብ፣ ያልተረጋገጠ ጉዳይ አይደለም። ይህኛው ቡድን ”ብሔርሰብ ነው ወይስ ዘውጌ ወይስ ጎሳ?” የሚለው ጥያቄ ላነሳነው ክርክር አስፈላጊ አይደለም። ለአሁኑ፣ ቁም ነገሩ፣ የራሳችን ባህላዊና ታሪካዊ ማንነት አለን የሚሉና ያላቸው ብድኖች መኖራቸው ነው። ስለዚህ ”እኔ የእገሌ ብሔረሰብ አባል ነኝ፤ የዚያኛው አይደለሁም፤ ማንነቴም አገው፣ ትግራዋይ፣ ጉሙዝ፣ ኦሮሞ፣ አማራ…ነው” የሚሉ ሰዎች አሉ። መኖራቸው እውነት ነው፤ በአግባቡ ከተያዘም ጸጋ ነው። አሁን የቀረበው ጥያቄ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት እነዚህ ብሔረሰባዊ ማንነቶች ብቻ ናቸውን የሚል ነው። ወይም፣ ኢትዮጵያዊ ማንነት የለምን? እርግጥ የአንድ ማንነት ታጋሪዎች ነን የሚሉ ሰዎች እስካሉ ድረስ ስለማንነቱ ለማረጋገጥ ሌላ ምርመራ ማድረግ የግድ አይደለም ብሎ የሚከራከር ይኖር ይሆናል። በዚህ ስሌት፣ ”ኢትዮጵያዊ ማንነት አለን” የሚሉ ሰዎች መኖራቸው ብቻውን በቂ ማስረጃ በሆነ ነበር። ቢሆንም ተጨማሪ ሐሳቦችን መለዋወጡ አይጎዳም።

2. ኢትዮጵያዊ/አገራዊ ማንነት የለም የሚሉ ሰዎች ቢያንስ አራት ስሕቶችን ይፈጽማሉ።
2.1. ከፍ ሲል የጠቀስኩትን የማንነቶችን መወራረስ፣ አልፎም የአዲስ ማንነቶች መፈጠር አይቀበሉም። ይህ ማለት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ብሔረሰቦች (የፖለቲካ ማኅበረሰቡ አባል የሆኑት ወደውም ይሁን ተገደው) በታሪክ ባካሔዱት መስተጋብር የሁሉም ”ቅልቅል” የሆነ (ምናልባትም የሆኑ) አዲስ ማንነቶች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ አይቀበሉም ማለት ነው። አዳዲስ ማንነቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ ብለው ካመኑ ክርክራችን በአገራችን አዲስ ማንነቶች ስለመፈጠራቸው እና ስለተፈጠረው/ስለተፈጠሩት አዲስ ማንነቶች ስያሜ ይሆናል ማለት ነው። በእኔ እምነት፣ በረጅሙና በውስብስቡ የአገረ ኢትዮጵያ መስተጋብር አዳዲስ ማንነቶች ተፈጥረዋል። (ይህ ማለት የብሔረሰብ ማንነቶች ጠፍተዋል ማለት አይደለም፤ እርግጥ ባሉበት አንዳችም ሳይለወጡ ቀጥለዋል – ንጽሕ የሚለው ቁልምጫ ትርጉሙ እርሱ ይመስላል- ማለትም ቢያንስ ፖለቲካዊ የዋህነት ይሆናል።) ከተፈጠሩት ”አዲስ/የተለዩ” ማንነቶች አንዱና ዋናው ብዙዎቻችን ”ኢትዮጵዊነት” የምንለው ማንነት ነው። ስለዚህ ማንነት አይነቶች ወይም አረዳዶች ወደ ኋላ አነሳለሁ፤ የችግሩ መነሻ ”ኢትዮጵያዊነት” የሚለው ስያሜ ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም መስጠቱ ሊሆን ይችላልና።

2.2. ተከታዩ ስህተት አንድ ሰው ከአንድ በላይ ማንነት ሊኖረው አይችልም፣ አንዱን ማንነት ሲቀበል ሌላውን መተው አለበት፣ ወይም የቀደመ ማንነቱን ከአዲስ ማንነት ጋራ ማዳበል ወይም ማዋሐድ አይችልም ከሚል የተሳሳተ አመለካከት የሚመነጭ ነው። ይህ በንድፈ ሐሳብም ሆነ በተግባር የተሳሳተ ነው። አሁን ያለችውን ኢትዮጵያ ተጨባጭ እውነታም መረዳት ይጎድለዋል። ዛሬ፣ ራሳቸውን በብሔረሰባዊም በአገራዊ ማንነታቸውም የሚገልጹ በሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሰዎች አሉ። ልብ በሉ፣ ለእነዚህ ሰዎች ኢትጵያዊነት ዜግነት ብቻ አይደለም፣ ማንነትም ጭምር ነው። ራስን በብሔረሰብ ማንነት ብቻ ሳይሆን በሃይማኖት ማንነትም ደርቦ መግልጽ እንደሚቻለው፣ ኢትዮጵያዊነትን ተጨማሪ ማንነት ማድረግ እውነት የማይሆንበት ምክንያት አይታየኝም። ብሔረሰባዊም አገራዊም ማንነት ያለቸው ሰዎች ስለመኖራቸው ማረጋገጥ ከባድ አልመሰለኝም። አገራዊ ማንነት የለንም የሚሉ ሰዎችን የግድ ይኑራችሁ ብዬ አልከራከርም። ዝርዝሩ ሌላ ውይይት ይፈልጋልና ልተወው።

2.3. ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም የሚሉት ሰዎች የሚሰሩት ሌላው ስሕተት ከፍትሕ ጋራ የተያያዘ ነው። እነርሱ ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ ”ማንነታችንን ሳታከብር ኖራለች፣ እውቅና ተነፍገን ኖረናል፣ ይህም ሊለወጥ ይገባል” ብለው ይከራከራሉ። ተገቢና እውነት ያለው የፍትሕ ጥያቄ ነውና ከልቤ እደግፈዋለሁ። ይህን እነርሱ የሚጠይቁትን ፍትሕ ግን ለሌሎች፣ ዛሬ ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት አለን ለሚሉትን ወገኖቻቸው እየከለከሉ ነው። አሁንም ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ማንነት ወደ ኋላ አነሳለሁ።

2.4. እነዚህ ሰዎች ከሚሰጡት ማብራሪያ የምንረዳው ሌላው ጭብጥ እውነተኛው/ደንበኛው ማንነት በብሔረሰብ ላይ የተመሰረተው ነው የሚል ነው። እነርሱ ባወጡት የማንነቶች ደረጃ መሠረት፣ ከብሔረሰባዊ ማንነት ውጭ ያሉት ማንነቶች አንድም ውሸት ናቸው አለዚያም ጠንካራ አይደሉም። ብሔረሳባዊ ማንነት ከሌሎቹ ማንነቶች ቀዳሚነት እንዳለው ይሰብካሉ። ይህንን ለፖለቲካ መቀስቀሻነት የሚጠቀሙት ሰዎች ዓላማ የተሰወረ አይደለም። ሐሳቡ ግን በግማሽ እውነት ላይ የተመሰረተ ስንኩል መከራከሪያ ነው። ግለሰቦችና ቡድኖች የሚያስቀድሙት የማንነት መለያ የሚወሰነው በኖሩበትና ባሉበት ታሪካዊ ሁኔታ እንጂ አስቀድሞ በወጣ የማንነቶች ደረጃ አይደለም። ከሌላው ማንነቱ በፊት በሃይማኖታዊ ማንነቱ ራሱን የሚገልጽ ሰው/ቡድን ይኖራል፤ ለሌላው ደግሞ ብሔረሰባዊ አለዚያም አገራዊ ማንነቱን ቀድሞ ይሰማው ይሆናል። ሁሉም የማኀበረሰባቸው ታሪክ ውጤቶች ናቸው። አንዱ ከሌላው የበለጠ ትክክል አይደለም፤ እንደ ግለሰቡ እና ቡድኑ ሊለያይና ሊለዋወጥ የሚችልም ነው። ይህ አመለካከት አንዳንድ ጊዜ ብሔረሰባዊ ማንነታቸውን የማያስቀድሙ ሰዎችን ”የማንነት ችግር” እንዳለባቸው ወይም እየዋሹ እንደሆነ የመክሰስ ድፍረት ተላብሶ የሚታይበት ጊዜም አለ።

3. ኢትዮጵያዊነቶች?
እንደማንኛውም ማንነት ኢትዮጵያዊነትም ብዙ ገጽታዎች አሉት። በታራካዊ ሂደቶችም ብዙ ተለውጧል፤ ገና ይለወጣልም። ኢትዮጵያዊ ማንነት ብዙ ገጽታዎች አሉት ወይም ብዙ አይነት ኢትዮጵያዊ ማንነቶች አሉ ብሎ መነሳት ይቻላል። ለዚህ ጽሑፍ አግባብነት አላቸው ያልኳቸውን ሦስት የኢትዮጵያዊ ማንነት አረዳዶች ብቻ ላስቀምጥ።፡ይህን የማደርገው፣ ኢትዮጵያዊ የምንለው ማንነት ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም እየሰጠ አለመግባባት ፈርሮ እንደሆነ በሚል መነሻ ነው። ለመግባባት ሲባል ለማንነቶቹ ሌላ ስያሜም መስጠት እንችል ነበር፣ ለጊዜው ይቆየን።

3.1. አንደኛው ኢትዮጵያዊ ማንነት ራሱን የሁሉም የአገራችን ብሔረሰቦች አካል አድርጎ ይመለከታል፤ ለአንዱ የተለየ ቅርበት አይሰማውም። እነዚህ ሰዎች ምክንያቱ ምንም ይሁን፣ ራሳቸውን የዚህ ወይም የዚያኛው አንድ ብሔረሰብ አባል አድርገው አይቆጥሩም። የዚህ ማንነት ባለቤት የሆነው ኢትዮጵያዊ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ነገር እኩል ተጋሪ ባለቤት እንደሆነ ያምናል። ብሔረሰባዊ ማንነትን ያከብራል። ብሔረሰባዊ ማንነትን ተገዳዳሪው አድርጎ አይፈራውም። ይህ ማንነት ድንገት ከሰማይ ወርዶ የሁሉም አካል ነኝ የሚል፣ ባለቤት አልባ ማንነት አይደለም። በአብዛኛው በተለይ በከተሞች አካባቢ ያደጉ (ለረጅም ጊዜ የኖሩ) ሰዎች የዚህ ማንነት ተጋሪዎች ናቸው። ባህላዊና ስነልቦናዊ ማንነታቸውን የቀረጸው ያለፉበት ታሪክ ነው፤ ፖለቲካው፣ ጦርነቱ፣ የሕዝብ እንቅስቃሴውና መስተጋብሩ፣ ትምህርቱ፣ የከተሜ ኑሮ…። ለእነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያዊነት ዜግነት ብቻ ሳይሆን ማንነትም ጭምር ነው። ቁጥር የበለጠ ትርጉም የሚሰጣቸው ሰዎች ካሉ፣ የዚህ ማንነት ባለቤቶች ቢያንስ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ስለመሆናቸው አልጠራጠርም። (እኔም ራሴን ያገኘሁት እና መሆንም የመረጥኩት እዚህ ውስጥ ነው።)

3.2. ሁለተኛው ኢትዮጵዊነት የአንድ ብሔረሰብ ማንነት ያለው፣ ነገር ግን በተጨማሪም ኢትዮጵያዊ ማንነት ያለው ነው። በብሔረሰብ ማንነቱ የብሔረሰቡ የሆነውን ሁሉ ይጋራል፤ እዚያ ግን አያቆምም፤ በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ከሎሎች ኢትዮጵያዊ ማንነት ካላቸው ጋራ የሚጋራው ሌላም ብዙ ነገር አለ። ይህ ሰው የሚረዳው ኢትዮጵያዊ ማንነቱ፣ ብሔረሰባዊ ማንነቱን እንዲተው የሚጠይቅ አይደለም። ይህ ማንነት፣ ከከተሞች መስፋፋት፣ ከትምህርትና ከመንግሥት ቢሮክራሲ ዝርጋታ ጋራ እያደገ እንደመጣ እገምታለሁ። አሁንም የዚህ ቡድን አባላት ቁጥር ከአገሪቱ ሕዝብ ከግማሽ በላይ እንደሚሆን አልጠረጥርም። ይህ ባይሆን አገሪቱ ህልውናዋ ባከተመ ነበር ከሚል መነሻ።

3.3. ሦስተኛው ኢትዮጵያዊነት፣ ብሔረሰባዊ ማንነትን የሚክድ ወይም ለማጥፋት የሚፈልግ ተጻራሪ ማንነት አድርጎ የሚመለከት አረዳድ ነው። ከታሪክ አንጻር በከፊል እውነት ነው። ለዚህ አረዳድ፣ ኢትዮጵያዊነት ማለት የክርስቲያን ሰሜን ኢትዮጵያ ባህልና ማንነት ነው። እንደ ጉዳዩ አቅራቢ ይህ ኢትዮጵያዊነት የአማራ ባህልና ማንነት ብቻ ተደርጎ የሚቀርብበት አጋጣሚም አይጠፋም። ለዚህ አመለካከት አስፈላጊው ጭብጥ ግን፣ ”ኢትዮጵያዊ” ማንነት ቀድሞም ይሁን አሁን ሌሎች ባህላዊ ማንነቶችን ለመደፍጠጥ ያሰፈሰፈ ማንነት ተደርጎ መታየቱ ነው። ይህ መሠረተ ቢስ ስጋት ነው ብዬ እንዳልደመድም እነርሱ ”ኢትዮጵያዊነት” ከሚሉት ውጭ ያለ አገራዊም ሆነ ብሔረሰባዊ ማንነት እንዲጠፋ አዋጅ ማወጅ የሚቃጣቸው ሰዎች አሉ። ማለት የምችለው፣ የእኔ ኢትዮጵያዊነት ከዚህ ይለያል። ይህ የኢትዮጵያዊ ማንነት አረዳድ የብሔረሰብ ማንነቶችን የማያከብር፣ ስለመኖራቸውም ሙሉ እውቅና የማይሰጥ ነው። ይህ ኢትዮጵያዊነት ብሔረሳባዊ ማንነቶችን በጥርጣሬ ይመለከታል፣ የአገራዊ መተሳሰር ጠላቶች አድርጎ ይፈርጃል፣ ማንነቶቹን ማዳከምም ይፈልጋል። የዚህ ማንነት አቀንቃኞች በአብዛኛው በአማራ ልሒቃን መካከል የሚገኙ ጥቂቶች ናቸው። እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያዊ ማንነት በዚህ ገጽታው ብቻ ሲወከል ይስተዋላል።

ህወሓት/ኢሕአዴግ በስልጣን ዘመኑ የመጀመሪያ አስር ዓመታት ሆን ብሎ ሁሉንም ኢትዮጵያዊነቶች በጅምላ እንዲጠሉ ብዙ ሰርቷል። ሌሎቹ ብሔረሰብ ተኮር ፓርቲዎችም ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ስትራቴጂ ተከትለዋል። ስጋታቸው ግልጽ ነው፤ የብሔረሰባቸው አባላት ኢትዮጵያዊ ማንነትን ከደረቡ የደጋፊ መጠናቸው ሊቀንስ ይችላል። በውጤቱም፣ ዛሬ፣ ”ኢትዮጵያዊ ማንነት” ሲባል በብዙ የአደባባይ ሰዎች ዘንድ አስቀድሞ የሚጠቀሰው ይህ ሦስተኛው አመለካከት ብቻ ሆኗል። የፖለቲካ ልሒቃኑ ኢትዮጵያዊነትን በቀዳሚዎቹ ሁለት መልኮቹ የሌለ በማስመሰልም፣ ሦስተኛውን ግን በማጉላት፣ የማንነቱን ባለቤቶች በጅምላ ጥፋተኞችና ተጠርጣሪዎች አስመስለው ያቀርቧቸዋል። ይህ ስህተት ብቻ ሳይሆን ሸፍጥም ነው። የሸፍጥነቱ ስላቅ ወደዜኒቱ የደረሰው፣ እነመለስ ደርሶ የሁለተኛው ዓይነት/አረዳድ ኢትዮጵያዊነት (3.2) አራማጆች ሆነው፣ ባንዲራ መስቀልና ስለሺህ ዓመት የኢትዮጵያ ታሪክ መስበክ ሲጀምሩ ነበር። ሌላው በጣም የሚገርመኝ ነገር፣ የመጀመሪያው ዓይነት ኢትዮጵያዊ ማንነት ያላቸው ዜጎች መኖራቸውን ገዢው ፓርቲ ጭምር ዛሬም ድረስ እውቅና ለመስጠት መፍራታቸው ነው።

ብሔረሰባዊ ማንነትን የፖለቲካቸው ማቀጣጠያ አድርገው መጠቀም የሚፈልጉ ልሒቃን፣ እንዲሁም ከማንነት ፖለቲካና የውድድር ስሜት የሚመጣው ስሜተ-ስሱነት የሚያስከትለውን ሚዛን የመሳት አደጋ ቀድመው ያልጠረጠሩ ሰዎች፣ በአገራችን ውስጥ ያሉት ብሔረሰባዊ ማንነቶች ብቻ ናቸው ይላሉ። ይግረማችሁ በማለትም፣ ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም ይላሉ።

ማንኛውም ማንነት እና ከእርሱ ጋራ ተያይዘው የሚመጡ ስሜቶች (የኩራት-ሃፍረት፣ የበላይ-የበታችነት፣ የአሸናፊ-ተሸናፊነት፣ የጊዜው የእኛ ነው-አይደለም፣ የተስፋ-ስጋት ወዘተ) መኖራቸውን ማስቀረት ባይቻልም መጠናቸውን ሲያልፉ ከፍተኛ አደጋን ይጋብዛሉ። አደጋው ሐልዮታዊ ብቻ ሳይሆን ማኅበረሰባዊም ነው። በሐልዮት ደረጃ፣ አሁን እንደምናየው፣ ”ያለሁት እኔ ነኝ እንጂ አንተ አይደለም” እስካማስባል ያደርሳል። አገራችንም ሆነች ዓለማችን በዚህ መሰሉ ሚዛኑን የሳተ የማንነት ስሜት ብዙ ዋጋ ስለመክፈላቸው ታሪክ ብዙ ያስነብበናል። አገራዊ ማንነት ሲጦዝ ሌላውን አገር በእብሪት ወደ መውረር ስካር ያመራል፤ በቆዳ ቀለም መኩራት (የሚያኮራ ከሆነ) ከዚያ አልፎ የበላይነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሆኖ ሲወሰድ ወደ አፓርታይድ ያደርሳል፤ በብሔረሰባዊ ማንነት ኮርቶ ራስን ማስተዳደርና ባህልን ማዳበር ከዚያ አልፎ የሌላውን (በተለይ ተፎካካሪ ተደርጎ የሚቆጠረውን) ማንነት መኖርና አለመኖር (በሐልዮትም ይሁን በአካል) ለመወሰን ወደሚያስችል ስልጣንነት ሲቀየር የመጠፋፋት በር ማንኳኳቱን ልብ እላለሁ፤ እሰጋለሁም።

ማንኛውም ብሔረተኝነት በጋራ ታሪክና መጻኢ እጣ ሚዛን መገደብ አለበት። ይህ ካልሆነ፣ ገደብ አልባ በራስ የመተማመን እና የእርግጠኝነት ስሜት ይፈጥራል። ትህትናንና መተሳሰብን ከግለሰብ ልብ፣ ከቡድን የጋራ ስነልቦና ያጠፋል። ይህ ስሜት በግለሰብም በቡድንም ደረጃ ሊንጸባረቅ ይችላል።

ኢትዮጵያዊ ማንነት አለ። ኢትዮጵያዊ ማንነት የሚለው አገላለጽ የሚወክለው መጥፎ የታሪክ አሻራም አለ። የመጥፎው አሻራ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያዊነት አረዳድ በሒደት እየተዳከመ መሔዱ ግልጽ ነው። ምኞቴም ነው። ሌሎቹ ሁለቱ አይነት ኢትዮጵያዊ ማንነቶች ግን የታሪካችን ተጨባጭና በጎ ውጤቶች አድርጌ አያቸዋለሁ። ምንልባትም መጻኢው የኢትዮጵያ መልካም እጣም ያለእነርሱ እውን የሚሆን አይመስለኝም። ራሴንና መሰሎቼን እንዴት ከነገው መልካም ቀን አውጤቼ ልመለከት እችላለሁ? እንዴትስ፣ ”እንኳን የነገው አካል ልትሆን፣ ዛሬም የለህም” ስባልስ ዝም እላለሁ?! ኢትዮጵያዊነት አለ። የለም ስለተባለም አይጠፋም። እኔ አለሁ።

ማንነት ውበት ነው። የማንነት ፖለቲካ ግን አስቀያሚ ገጽታው ይበዛል። እንዳለመታደል ሆኖ እርሱን መዝለል፣ መካድ፣ ንቆ መተው አይቻልም፤ አይገባምም። ስለዚህ በመከባበርና በመረዳዳት መንፈስ መነጋገሩ ይጠቅመናል።

አቡጊዳ – ኦፌኮ የወጣቶች ሊግ አቋቋመ

$
0
0

በዶር መራራ ጉዱና የሚመራዉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፣ የወጣቶችን ሊግ ማቋቋሙ የዶር መራራ እና አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ፌስቡክ ዘገበ። ሊጉ የኦሮሞዎች መብት በኢትዮጵያ እንዲከበር ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ በኦሮሚያ ዞኖች ይንቀሳቀሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ofc1

አዲስ አበባን ጨምሮ ሃያ አንድ የኦሮሞያ ዞኖች ሲኖሩ፣ አዲስ ለተቋቋመዉ የወጣቶች ሊግ፣ ተወካዮች ከአሥራ ሁለት ዞኖች እንደመጡም ለማወቅ ተችሏል። ወጣት ተወካዮች የመጡት፣ ከሰሜን ሸዋ ዞን፣ ከምእራብ ሸዋ ዞን፣ ከኢሊባቡር ዞን፣ ከቀለም ወለጋ ዞን፣ ከምስራቅ ሃረርጌ ዞን፣ ከጉጂ ዞን፣ ከምእራብ ወለጋ ዞን፣ ከምስራቅ አርሲ ዞን እና ከፊንፊኔ/አዲስ አበባ ሲሆን፣ ከደቡብ ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ከምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ከአርሲ ዞን፣ ከባሌ ዞን፣ ከምእራብ ሃረርጌ ዞን፣ ከቦረና ዞን፣ ከጂማ ዙሪያ ዞን፣ ከጅማ ከተማ ልዩ ዞን ፣ ከቡራዩ ልዩ ዞን እና ከአዳማ/ናዝሬት ልዩ ዞን ተወካዮች አልተገኙም።

የወጣቱ ሊግ 50 ወጣቶች ያሉበት አመራር ያሉት ሲሆን፣ 11 አባላት ያሉበትም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንዲኖረው ተደርጓል።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ የመድረክ አባል ድርጅት ሲሆን ከአምስት አመታት በላይ ከአረና ትግራይ፣ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከመሳሰሉ ጋር ጠንካራ የሥራ ግንኙነት የፈጠረ፣ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ጠንካራ አቋም ያለው ድርጅት ነዉ። ሊቀመንበሩ ዶር መራራ ጉዳና፣ ኦሮሞዉ የኢትዮጵያ ግንድ እንደሆነ በመገልጽ፣ «እንዴት ግንድ ከቅርንጫፍ ይገነጠላል ?» በማለት የአንዳንድ ጽንፈኛ የኦነግ ዘረኛ የመገነጠል ፖለቲካን በይፋ ማጣጣላቸው ይታወቃል።

አንዳንድ የመድረኩ አባል ድርጅቶች፣ በመድረኩ ያሉ የፖለቲካ ልዩነቶችን ሰጥቶ በመቀበል መርህ አጣቦ ፣ ወደ ዉህደት የመምጣት ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም፣ በኦፌኮ ዘንድ ብዙ ተቀባይነት እንዳላገኝ ዉስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። ከአገር አቀፍ ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት እንጂ የሚፈልጉት፣ የ«ኦሮሞ» ድርጅትነታቸውን እና ኦሮሞ ለሚሉት ብቻ የመቆም አላማቸውን ማከሰሙ እንደማይመቻቸው፣ ያከሉት የዉስጥ አዋቂዎች፣ «የኦሮሞ ስማችንን ከቀየርን ፣ ከአክራሪ የኦሮሞ ብሄረተኞች ጥቃት ይደርስብናል» የሚል ስጋት እንዳላቸው ይናገራሉ።

ኦፌኮ በመድረክ ዉስጥ ዉህደትን ከመፍጠር ፣ በቅርቡ «ወደ አገር ቤት ገብቼ እታገላለሁ» የሚል አቋም የያዘው፣ በቀድሞ ነባር የኦነግ አመራር አባላት በነበሩ፣ በነአቶ ሌንጮ ለታ፣ አቶ ዲማ ነግዎ በመሳሰሉ በተቋቋመው ፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ጋር ዉህደት መመስረቱን እንደሚመርጥ የሚናገሩት ዉስጥ አዋቂዎች፣ «ሁለቱም አሁን ያለውን በቋንቋ ላይ ያለው ፌደራል አወቃቀር እንዲቀጥል ይፈልጋሉ። ሁለቱም የሚታገሉት ለኦሮሞዉ ነዉ። ሁለቱም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ነው ለመታገል የሚፈልጉት። ሁለቱም በምርጫ ለመወዳደር ፍላጎት አላቸዉ» ሲሉ፣ በኦፌኮ እና በኦዴግ መካከል በፖለቲካ ፕሮግራሞቻቸው ሆነ በትግል ስትራቴጂዎች አኳያ ምንም ልዩነት እንደሌላቸው ያስረዳሉ።

ሕወሓት ከመለስ ጋር አብሮ ተቀብሯል – ክፍል 2

$
0
0

Bereket Simon weeping with his wife over Meles Zenawi's death
ከነፃነት አድማሱ
dalul@gmail.com

የሰው ልጅን ነፃነት የማይገባው ነፃ አውጪ!!

በትግራይ የህወሓት እኩይ ተግባር በቅርብ የተከታተሉት አንድ የሽሬ እንዳስላሴ አዛውንት እንዲህ በማለት በምሬት ይገልፁታል። “ደርግ ሰው ገድሎ በአደባባይ ይፎክር ነበር። ዛሬ ህወሓት ግን ሰው ገድሎ ልቅሶ ይደርሳል” ሲሉ የድርጅቱን እርኩስነት፣ አስከፊነትና የሰብኣዊ ፍጡር ባላንጣነት ካለፈው የደርግ አገዛዝ ጋር በማነፃፀር ቁጭታቸውን በትካዜ ሲናገሩ አጋጥሞኛል። የዛሬው ፅሑፌም ካለፈው ክፍል አንድ የቀጠለ ነው። በክፍል አንድ የተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎችም በኋላ በዝርዝር ለማስቀመጥ እሞክራለሁ። ለዛሬ ግን ቀደም ብዬ በክፍል አንድ የጀመርኩትን “አደናግረህ፣ አስፈራርተህ፣ አሸብረህ፣ ወገን ከወገኑ ጋር አናቁረህና ለያይተህ ግዛ” የሚለውን የህወሓት የደደቢት የደንቆሮ ፍልስፍናና መፈክር በሚመለከት አጭር ማጠቃሊያ በማከል ፅሑፌን እቋጫለሁ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

አቡጊዳ – ህወሓት ፀረ ዴሞክራሲ (ፀረ የወላጆቻችን ትግል) መሆኑ በተግባር አስመስክሯል አሉ አቶ አብርሃ ደስታ

$
0
0

አረና በሁመራ ለማድረግ ያቀደው ህዝባዊ ስብስበ በአዲግራት እንደተደረገው ሁሉ በሕወሃት አምባገነንነት ሳይሳካ ቀርቷል። የአረና አመራር አባል አቶ አብርሃ ደስታ በፌስቡክ ብሎጋቸው :

«ዓረና መድረክ በሑመራ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ለዓርብ ጥር ሰለሳ ቀጠሮ ይዞ፣ አስተዳዳሪዎችን አሳውቆ፣ የማዘጋጃቤት አዳራሽ ተፈቅዶለት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር የተሳካ ቅስቀሳ ቢያደርግም የሑመራ (እንዲሁም የወልቃይት) ህዝብ ጥሩ አቀባበል ያስደነገጣቸው የከተማው አስተዳዳሪዎች ቃላቸው በማጠፍ የጠራነው ስብሰባ ሕገ ወጥ መሆኑና ማካሄድ እንደማንችል ዛሬ ሐሙስ ጥር ሃያ ዘጠኝ ትእዛዝ ሰጥተውናል። ለስብሰባው የሁለት ቀናት ሙሉ ቅስቀሳ ተደርጓል። ከ አስር ሺ በላይ በራሪ የጥሪ ወረቀት በሑመራና ሌሎች ስምንት የአከባቢው ከተሞች ታድሏል። ስልሳ አራት የፓርቲው አባላት በቅስቀሳው ተሳትፈዋል። ሁለት የድምፅ ማጉልያ በመጠቀም አውጀናል። ህዝቡ በስብሰባው ለመሳተፍ ያሳየው ተነሳሽነት በመገንዘብ ካድሬዎቹ ስብሰባው አግደውታል። ማስፈራርያም ተሰጥቷል» ሲሉ የነበርየወልቃይት ሑመራ ህዝብ ላደረገልን መልካም አቀባበል እናመሰግናለን»

ሲሉ፣ የነበረዉን ሁኔታ ያብራሩ አብራርተዋል። የወልቃይጥ ጠገዴ ሕዝብም ላደረገላቸው ትብብርና ድጋፍ ምስጋናቸዉንም አቅርበዋል።

የትግራይ ህዝብ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ የከፈለው ትልቅ ዋጋ ሃይጃክ እንደተደረገ ያስረዱት አቶ አብርሃ፣ የሕወሃት፣ ሕዝብን የማፈን ተግባራትን፣ የጭካኔ ተገባራት ብልዉታል።

«ህወሓት በትክክል ጨካኝ ነው። “ጨካኝ” የሚል ቃልም አይገልፀውም። ትናንት ማታ ካድሬዎች በሑመራ ከተማ አልጋ እንዳናገኝ ባለ ሆቴሎችን ያስፈራሩ ነበር (አልጋ እንዳያካራዩን)። እራት ለመብላት ስንንቀሳቀስ እየተከታተሉ የምግብቤት ባለቤቶችን እራት እንዳያቀርቡልን ያስጠነቅቁ ነበር። እራት ካቀረቡልን ግን (ነገ ጠዋት) የንግድ ፍቃዳቸው እንደሚሰረዝ ይነግሯቸው ነበር። ይህ የተደረገው ሐሙስ ማታ ነበር። ከሐሙስ በፊት ግን አስተዳዳሪዎቹን ሳይቀሩ ጥሩ አቀባበል አድርገውልን ነበር። ህወሓቶች ግን ለቂም በቀል ባትጋብዙን ምን አለበት? ለምን ህዝብ ፊት በሐሳብ ተከራክረን አሸናፊው በህዝብ ድምፅ አይለይም? ለነፃነትና ዴሞክራሲ ብለው ህይወታቸው የሰዉ ወላጆቻችንን አሳዘኑኝ። የወላጆቻችን ትግል ዉጤቱ እንዲህ ዓፈና ከሆኑ አባቶቻችን ባደረጉት ትግል ከስረዋል ማለት ነው። ምክንያቱም እነሱ የህይወት መስዋእት ቢከፍሉም የታለመው የልጆቻቸው ነፃነትና ዴሞክራሲ ግን ከሽፏል። እኛ ልጆቻቸው እንደገና መስዋእት ልንከፍል ነው። ወላጆቻችን ጭቆናን መታገል እንጂ መቀበል አላስተማሩንም። ስለዚህ ወላጆቻችን የጀመሩት የነፃነት ትግል እንጨርሰዋለን። ዴሞክራሲ በተግባር እስኪረጋገጥ ድረስ እንታገላለን። ህወሓት ፀረ ዴሞክራሲ (ፀረ የወላጆቻችን ትግል) መሆኑ በተግባር አስመስክሯል። በጨቋኞች አንምበረከክም። ከባርነት ነፃነት ይሻላል። ወላጆቻችን ለስልጣን አልታገሉም። ህወሓት ግን የወላጆቻችን ትግል የስልጣን ኮረቻ ለመጨበጥ ተጠቀመበት። የነፃነት መንገድ ትግል ነው» ሲሉም ትግላቸዉን በምንም ሁኔታ እንደማያቋርጡም አረጋግጠዋል።

በሁመራ ስለነበረዉ ሁኔታ ሲዘረዝሩ «የዓረና ፓርቲ የድርጅቶች ጉዳዮች ሐላፊ አቶ ስልጣኑ ሕሸና የፓርቲው አመራር አባል የሆነው አቶ ሃይለኪሮስ ታፈረ ትናንት ምሽት በሑመራ ከተማ በፖሊስ ታስረዋል። ዛሬ ዓርብ ተለቀዋል። በስብሰባው ለመሳተፍ የመጣ ህዝብ በአስተዳዳሪዎች ተበትኗል። ዛሬ በሑመራ ከተማ ከ አምስት ሰው በላይ ተሰባስቦ መንቀሳቀስ ወይ መቀጠም ወይ ሻይ መጠጣት አይፈቀድም ነበር። የፀጥታ ሃይሎች እየተዘዋወሩ ይበትኑም ያስሩም ነበር። ባጠቃላይ ዛሬ በሑመራ ከተማ ‘State of Emergency’ ታውጆ ነበር። ከአባሎቻችን ጋርም መሰብሰብ አልቻልንም። ህወሓት የሰለማዊ ትግል በር እያጨለመው ይገኛል። የወልቃይት ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ስርዓቱ ለመቀየር ከሚታገል ማንኛውም ሃይል ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆኑ አረጋግጦልናል» ነበር ያሉት።

ብዙ ውህደትና ተጨማሪ ትብብር ለኢትዮጵያ ፓርቲዎች (አንድነት እያደረገ ስላለው የዉህደት ጥረት) – ዳዊት ሰለሞን

$
0
0

የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎቻቸው እንዲወዳደሩ ወይም ስልጣን እንዲይዙ ለማድረግ የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ናቸው፡፡የውክልና ዴሞክራሲ እንዲጠነክርና እንዲጎለብት ፓርቲዎች የሚጫወቱት ሚናም ቁልፍ ነው፡፡

በሰለጠነው አለም የፖለቲካው ልቀት የሚለካው በፓርቲዎች ብዛት ነው፡፡የፖለቲካ ስልጣንን ለማግኘት የሚፎካከሩ ፓርቲዎች ቁጥር ሁለት ቢበዛ ሶስት ነው፡፡ለምሳሌ በአሜሪካ ኋይት ሃውስ ለመግባት የሚፎካከሩት ፓርቲዎች ሁለት ናቸው፡፡ዴሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች፡፡ በእንግሊዝ ዋነኞቹ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሶስት ናቸው፡፡ወግ አጥባቂዎቹ (ኮንሰርቫቲቭ)የሰራተኛው(ሌበር ፓርቲ)እና ሊበራሎች፡፡

የአሜሪካና የእንግሊዝ ፓርቲዎች ጥርት ባለ የፖለቲካ አይዶሎጂ (Clear Ideologies) ላይ የተመሰረቱና ህዝቡን በፖለቲካ፣በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዩች በማንቃት ምርጫው እንዲያደርጋቸው የሚታገሉ ናቸው፡፡ ፓርቲዎቹ ጥርት ያለ አደረጃጀት ያላቸው በመሆናቸው በመሪዎቻቸው መለዋወጥ የሚለዋወጡ አይደሉም፡፡

ወደ አገራችን ስንመለስ መሬት ላይ የምናገኛቸው ፓርቲዎች ቁጥር ከ73 ይልቃል፡፡ፓርቲዎቹ በአብዛኛው በመሪዎቻቸው የፖለቲካ ቁመና የሚመዘኑ ስፖንሰሮቻቸው በማዕበል እንደተመታች መርከብ ከወዲያ ወዲህ የሚያላጓቸው ናቸው፡፡የፓርቲዎቹ ጥንካሬ የመሪዎቻቸው የፖለቲካ ቁመና ብቻ ነው፡፡

የአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር የፓርቲዎችን ፕሮግራም አንብቦና አማርጦ ተከታያቸው ለመሆን የሚያስችል ባለመሆኑም የየፓርቲዎቹ አመራሮች ጭምር ፓርቲያቸው ስለሚከተለው የፖለቲካ ፕሮግራም እውቀት ያላቸው ስለመሆኑ አፍን ሞልቶ ለመናገር ያስቸግራል፡፡

የሊበራል የፖለቲካ ፍልስፍናን በሚያራምድ ፓርቲ ውስጥ በሶሻሊስት አይዶሎጂ የተጠመቀ መሪ ቢያገኙ መደነቅ አይኖርብዎትም፡፡ምክንያቱም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተሳትፎ ማድረግ የፕሮግራም ጉዳይ ሳይሆን የህልውና በመሆኑ ነው፡፡
የምርጫ ቦርድን መዝገብ ያጣበቡት የሚበዙት ፓርቲዎች በአይዶሎጂ የተፈበረኩ ሳይሆኑ ዘውግ ተኮር በመሆናቸውም አንደኛቸው ከሌላኛቸው የሚለዩት ‹‹የእኛ›› ‹‹የእነርሱ›› በሚለው የዘውግ አጥር ነው፡፡በእነዚህ ፓርቲዎች ሐሳብ፣ፕሮግራምና የፖለቲካ ፍልስፍና ቦታ የላቸውም፡፡ምርጫ ሲቀርቡ የዘውጌያቸው ተወላጅ የሆነ እንዲመርጣቸው ከመጠየቅ ባለፈ ከዘውጌያቸው ውጪ ያለ ሊመርጣቸው የሚችልበት መንገድ አይኖርም፡፡ስለዚህ እነዚህ ፓርቲዎች የፖለቲካ ስልጣን መዘውሩን የመጨበጥ እድላቸው በዜሮ የሚባዛ ይሆናል፡፡

ዘውግ ተኮር ፓርቲዎች የስርዓቱ ስጋት ተደርገው የሚታዩ ባለመሆናቸውም የምርጫው አድባር ኦዲት ተደረጉም አልተደረጉ አልያም ጠቅላላ ጉባኤ ባያደርጉም ይፈልጋቸዋል፡፡

ተቃዋሚዎች በቁጥር በዝተው በምርጫ ገበያው ራሳቸውን ማቅረባቸው ሁልግዜም የሚጠቅመው ስልጣን ላይ የሚገኘውን አካል ብቻ ነው፡፡የገዢውን ፓርቲ የፖለቲካ ሃይል ለመቀናቀን ፓርቲዎች ቁጥራቸውን ለመቀነስ የሚያስችላቸውን ብስለት የተሞላበት ውሳኔ ማሳለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ያለፈው የህብረት፣የውህደት፣የትብብርና የግንባር ልምድ ጥሩ ባለመሆኑ ብቻ ውህደት ፣ቅንጅት፣ህብረትና ትብብር አያስፈለግም ማለት የገዢውን ፓርቲ እድሜ ለማራዘም ከመወሰን ተለይቶ መታየት አይኖርበትም፡፡

የከዚህ በፊቶቹ ውህደቶች፣ቅንጅቶች፣ህብረቶች ያልሰሩበትን ምክንያት በማየት የተሻለ ሆኖ ለመውጣት መስራት ይገባል እንጂ የከሸፉ ታሪኮችን በማስታወስ ማላዘን የትም አያደርስም ደግሞስ ‹‹Those who do not learn from past mistakes are doomed to repeat it››ይባል የለምን፡፡ትምህርት ቀስሞ የሚሰራ ውህደት፣ትብብር ወይም ቅንጅት ለመፍጠር መስራት ከሁሉም ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ይጠበቃል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከመኢአድ ጋር የጀመረውን የውህደት ድርድር ከዳር በማድረሱ ሁለቱ ፓርቲዎች በቅርቡ አንድ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡አረና ከአንድነት ለመዋሐድ እያደረገ የሚገኘው ድርድርም በአስተማማኝ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ መረጃ አለኝ፡፡አንድነት ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር የጀመረው ትብብር ከፍተኛ ስኬት በማስመዝገቡ ፓርቲዎቹ በውህደት ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ለመፈራረም መብቃታቸው አይዘነጋም፡፡እናም ብዙ ውህደትና ተጨማሪ ትብብር ለኢትዮጵያ ፓርቲዎች !!

አቡጊዳ – አረናዎችን ለመገድል ህወሃት እያሴረ ነዉ ተባለ

$
0
0

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመዋሃድ ንግግር እያደረገ ያለው የአረና ፓርቲ፣ ከሕወሃት ጋር ከፍተኛ የሰላማዊ ትግል ትንቅንቅ ላይ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነዉ። በቅርቡ በአዲግራት ሊደረግ ታስቦ በነበረዉ ሕዝባዊ ስብስባ ከሌላ አኡራጃዎች የመጡ የሕወሃት ካድሬዎችና ዱርዬዉን ድንጋይ እየወረወሪ ሲበጠብጡ፣ የአመራር አባላትን ሲደበድቡ እንደነበረ የሚታወስ ነዉ። ህወሃት እነዚህ ዱርዮዎችን አሰማርቶ የሽብር ተግባራትን በመፈጸሙ ምክንያት፣ ስብሰባዉን ማድረግ ካለመቻሉ የተነሳ፣ የአዲግራት ሕዝብ አማራጮችን እንዳይሰማ ተደርጓል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በሁመራ ሕወሃት በሕግ ተፈቅዶ የተጠራን የአረና ስብሰባ በኋይል ለማጨናገድ ችሏል። አረናዎች ሳይታክቱ በየከተሞቹ የሚያደርጉት ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ፣ በሌላ ብኩል ደግሞ ህወሃት እያሳያቸው ያለው ፍጹም ጸረ-ሰለማ እና ጸረ-ዲሞርካሲ ተግብራት አብዛኛዉን የህወሃት ደጋፊ የነበሩትን ሁሉ እያስገረመና እያስቆጣ ሲሆን፣ በርካታ ሕወሃቶች ወደ አረና እየተጎረፉ እንደሆነ ምንጮች ይጠቁማሉ።

ከዚህም የተነሳ ሕወሃት የአረናን ግለት መግታት ስላልቻሉ የአመራር አባላቱን የመግደል ሴራ አያሴሩ መሆናቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች እየተነበቡ ናቸው።

የአረና ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት አቶ አብርሃ ደሳታ በዚህ ጉዳይ ላይ በፌስቡክ የጻፉትን እንደሚከተለዉ አቅርበናል፡

=========================
ሑመራ (ዳንሻ) በነበርኩበት ግዜ ከተወሰኑ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ጋር ተገናኝቼ ነበር። ሁለት ታጋዮችን የነገሩኝ ላካፍላቹ። “ለምንድነው የትግራይን ህዝብ ፈሪ የሆነው?” አንድ ጓደኛዬ የጠየቀው ነበር። ታጋይ አንድ (ወንድ ነው) ሲመልስ “የትግራይን ህዝብ ፈሪ የሆነው ከድሮ ጀምሮ የህወሓትን ጭካኔ ስለሚያውቅ ነው። ህወሓት ሰው በሊታ መሆኗ የትግራይ ህዝብ በደንብ ያውቃል” አለ። “እሺ የትግራይ ህዝብስ ይፍራ እናንተ ታጋዮችስ ለምን ትፈራላቹ?” ብዬ ጠየቅኩ። ታጋይ ሁለት (ሴት ናት) “እኛ ታጋዮችምኮ የህወሓትን ጭካኔ በደንብ እንረዳለን። ከህዝብ በላይ ህወሓትን የምናውቃት እኛ ነን። አብዛኞቹ የህወሓት ታጋዮችኮ በህወሓት የተረሸኑ ናቸው። በደርግ ከተገደሉብን ብፆት (ጓዶች) በራሷ በህወሓት የተገደሉ ይበዛሉ። በህወሓት እንደተረሸኑ እያወቅንም ‘በጦርነት ተሰውተዋል’ ብለን ነው የምንናገረው። አብዛኞቻችን እናውቀዋለን። ግን እንፈራለን። አሁን ግን ማንን እንደምንፈራ አላውቅም” አለች። “ፍርሓት ፍርሓት … መጨረሻ ድፍረት ይሆናል” ብዬ ተሰናበትኳቸው።

የህወሓት መሪዎች ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሳ የዓረናን መሪዎች እስከመግደል ሊደርሱ እንደሚችሉ አንድ የህወሓት የደህንነት ሐላፊ ዛሬ አጫውቶኛል። ተስፋ የቆረጡበት ምክንያት … የራሳቸው (የህወሓት) አባላትም ዓረናዎች የሚያነሷቸው ሐሳቦች እያነሱ ስለሚጠይቁና በብዛት ከህወሓት አባልነት እየለቀቁ በመሆናቸው ነው። ባሁኑ ግዜ በትግራይ ክልል የሚገኙ የህወሓት አመራር አባላት በየዞኗቸው ተሰብሰበው የሚገኙ ሲሆን ከሚያነሷቸው ሐሳቦች በመነሳት የህወሓት መሪዎች በአባሎቻቸውም እምነት የላቸውም። እስካሁን ድረስ በሰሩት ወንጀል ምክንያት ተጨናንቀዋል። (ሁሉም አመራር አባላት በየዞን ከተሞች የተሰበሰቡ ሲሆን የተምቤኖች ግን ለየት ይላል። ተምቤኖች ጠንከር ያለ ተቃውሞ ያነሳሉ በሚል ስጋት ለብቻቸው በዓድዋ ከተማ እንዲሰበሰቡ ተደርጓል። ሌሎች የማእከላዊ ዞን አባላት ግን በአክሱም ይገኛሉ)። የህወሓት የ አባላት ለስብሰባ ሲገቡ ሞባይላቸው እንዲዘጉ በጥብቅ ይታዘዛሉ። የመሪዎች ንግ ግር መቅረፅ በጥብቅ የተከለከለ ነው። ህወሓት እንኳንስ ህዝብ የራሱ አባላትም አይመርጡትም። የሰሩት ወንጀል ራስ ምታት ሁኖባቸዋል። ስልጣን መልቀቅ የሞትን ያህል አስፈርቷቸዋል። በዚሁ አካሄዳቸው ደግሞ በስልጣን ሊቆዩ እንደማይችሉ በሚገባ ተረድተዋል።

ህወሓት ፍፁም አምባገነንነቱን እያጠናከረ ነው። ትናንት ዓርብ በሑመራ ከተማ ሰዓት እላፊ ማወጁ ይታወሳል። በዓረና እንቅስቃሴ በጣም የሰጋ ህወሓት ዛሬ የዓረና አባላትን ሲያስፈራራ ዉሏል። አቶ መሰለ ገብረሚካኤል የተባሉ የዓረና ስራ አስፈፃሚ አባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና አባላት አስተባባሪ ዛሬ ታስረው እየተገረፉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። የዓረና ፓርቲ ቢሮ (በሑመራ) በህወሓት ካድሬዎች ዛሬ ተዘርፏል፤ ኮምፒተሮች ተወስደዋል (የአቶ መሰለ የግል ላፕቶፕም ጭምር በባለስልጣናቱ ተዘርፋለች)። የመንግስት ስልጣን የያዘ አካል እንዲህ የተራ ሽፍታ ስራ ሲሰራ ይደንቃል። ለአምባገነናዊ ስርዓት አንምበረከክም። ማሸነፋችን አይቀርም።

የሌለውን ልማት መካድ

$
0
0

ሰሞኑን በአዲስ ዘመን እና ኢዜአ ‹‹ጥናት›› ስም ገበያ ላይ ከወጡ አዲስ አባባሎች ውስጥ ‹‹ልማቱን መካድ›› የሚል ይገኝበታል፡፡ አባባሉ እንዲህ እንደዛሬው ጥናታዊ ዕውቅና አላገኘም ነበር እንጂ እንዲሁ በገደምዳሜው ግን ስሙ ይታወቅ ነበር፡፡ ኢሕአዴግ እና ቲፎዞዎቹ ‹‹ተቃዋሚዎች ልማቱን ይክዳሉ›› ይላሉ፤ ልማቱ የኢሕአዴግ ትልቁ መንጠልጠያ ነው፡፡

ራሱን ‹‹ልማታዊ መንግሥት›› ብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያ መንግሥት ‹ሥልጣኑን ጠቅልዬ መያዝ የሚኖርብኝ እና ዴሞክራሲ ለመንፈግ የተገደድኩት ልማቱን ለማፋጠን ብዬ ነው› ይላል፡፡ አባባሉ ‹እኔ ሥልጣኑ ላይ ካልቆየሁ ልማት አይኖርም› የሚል ይመስላል፤ ሌሎች ልማት ማምጣት ስለማይችሉ ይሁን እነሱ ሥልጣን ላይ ከሌሉ አገሪቷ ላይ ሌላ ኃይል እንዳይመጣ ጦርነት ስለሚከፍቱ እኔንጃ - ልማቱ የሚጨናገፈው በምን እንደሆነ ተናግረው ግን አያውቁም፡፡ መቼም ልማት ማለት ግንባታ ሆኗል እና የግንባታ መሣሪያዎቹን እና መሥሪያ ቦታዎቹን ይዘው ከሥልጣን አይወርዱም ብለን እናስባለን፡፡
የበኩር ስህተት

የኢሕአዴግ እና የቲፎዞዎቹ የበኩር ስህተት ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን እና ልማትን እንደ አንድ ዓይነት ነገሮች መመልከታቸው ነው፡፡ ኢሕአዴግ ለዐሥር ዓመታት ያክል በተከታታይ አስመዝግቢያቸዋለሁ ለሚለውና ከሞላ ጎደል የዓለም ባንክ እና የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሚያረጋግጡለት የኢኮኖሚ ዕድገቱን ነው፡፡ የኢኮኖሚ ዕድገቱ በኢትዮጵያ መንግሥት አነባበብ ሁለት አሐዝ ይደርሳል፡፡ እርግጥ ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢያቸው (GDP) አነስተኛ የሆኑ አገራት ሁለት አሐዝ የሚደርስ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያስመዘግቡበት ዕድል ሰፊ ነው፤ በተረጋጋ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ሒደት ውስጥ እስከሆኑ ድረስ፡፡ ችግሩ ይህንን የኢኮኖሚ ዕድገት ልማት ብለው የተረጎሙት ዕለት ነው የተጀመረው፡፡

ኢኮኖሚስቶች ኢኮኖሚያዊ ልማት ከኢኮኖሚያዊ ዕድገት በሰፊው እንደሚለይ፤ ዕድገት የልማት አንድ የአካል ክፋይ እንጂ አቻ ስያሜ እንዳልሆነ ይከራከራሉ፡፡ ባለሙያዎቹ ልማትን በጥቅሉ ሲተረጉሙት ‹የሕዝቦች የኑሮ ደረጃ መሻሽል፣ ለራሳቸው ያላቸው ግምት/አመለካከት መጨመር፣ ከጭቆና እና ጥገኝነት ነጻ መውጣት እንዲሁም ለኑሮ የሚበጁ የተለያዩ አማራጮች› ማግኘትን› ይመለከታል ይላሉ፤ ልማት በዜጎች ላይ በሚታዩ ለውጦች ላይ ያተኩራል፡፡ በዕድገት ምዘና ግን ድምር የአገሪቱ ገቢ ከዓመት፣ ዓመት መጨመሩ ላይ ብቻ የሚያተኩር በመሆኑ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ባይኖርም፣ የዜጎች የኑሮ ሁኔታ ባይሻሻልም፣ ዜጎች ኢኮኖሚያዊም ይሁን ፖለቲካዊ ነጻነት ባይኖራቸውም በጥቂት የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እና በጥቂት የሀብታሞች የበለጠ መበልፀግ ላይ ብቻ የተመሠረተ የቁጥር መሻሻል ከታየ ዕድገት ሊባል ይችላል፡፡ (ንፅፅሩን የአንድን ሰው ተራ የዕድሜ እና የክብደት መጨመርን፤ ከሌሎች የሥነ-አዕምሮ፣ ምግባር፣ ኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ደረጃ ዕድገት ጋር እንደማነፃፀር  ነው - የመጀመሪያው ኢኮኖሚ፤ ሁለተኛው ልማት መሆኑ ነው፡፡)

ይህ የትርጉም ልዩነት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት እንጂ ልማት አለመሆኑን ይናገራል፤ ስለዚህ ልማቱ ከመካዱ በፊት በቦታው መኖር ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ (ከዚህ ርዕስ ጋር የተገናኘ ሙግት እዚህ ዞን ዘጠኝ ላይ የተጻፈ ጽሑፍ ላይም ማግኘት ይችላሉ፡፡)

የኢትዮጵያ ተርታ

ኢትዮጵያ የምዕራባውያን ዋነኛ ዕርዳታ ተቀባይ አገር ውስጥ ናት፡፡ እንግሊዝ እርዳታ ከምትለግሳቸው አገራት ከፍተኛ መጠን ያለውን የምትቀበለው ኢትዮጵያ ናት፡፡ ካናዳ ከሐይቲ እና አፍጋኒስታን ቀጥሎ በሦስተኝነት ደረጃ እጇን የምትዘረጋው ለኢትዮጵያ ነው፡፡ እርዳታ አያኮራም፤ ሆኖም እንደኛ አገር ላለው ቁስለኛ ኢኮኖሚ አንድ የአገር መሪ እርዳታ ማስገኘት መቻሉን እንደ ድል መቁጠር የተለመደ ነው፡፡ የእኛም መንግሥት በዚህ ኩራት ይሰማዋል፡፡

አሳፋሪው ነገር ግን የሚመጣው ብዙዎቹ ለጋሽ ሃገራት የሚለግሱን ከነማን ተርታ አሰልፈው እንደሆነ የተመለከትን ዕለት ነው፡፡ ልገሳዎቹ ባብዛኛው በጦርነት ከተጎዱ አገራት ተርታ ነው፡፡ እኛ የእርስ በርስ ጦርነታችንን ካቆምን ሀያ ዓመታት ቢያልፉንም ዛሬም በጦርነት ከተጎዱና በተፈጥሩ አደጋ ከተናጡ አገሮች ተርታ እርዳታ የሚመደብልን አገር ነን፡፡ ይህ በልማት ምን ያህል ወደኋላ እንደቀረን አመላካች መራር እውነት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ አገራችን ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉ አገሮች ተርታ ተሰለፈች ተብሎ ዝርዝሩ ሲታይ በኢኮኖሚያቸው ድቅቅ ካሉ አገራት ተርታ መሰለፏን ማየት የሚያስደስት ነገር አይደለም፤ የሚደሰኮርበትም አይሆንም፡፡ አንድ መቶ ብርን በሁለት እጥፍ ማሳደግ፣ አንድ መቶ ቢሊዮን ብርን በእጥፍ ከማሳደግ ይቀላል፡፡ የዕድገታችን ፐርሰንታይል ከፍ ብሎ መታየትም በዚህ ይገለፃል እንጂ የመንግሥታችንን በልማት መመንደግ የሚያረጋግጥ እውነታ አይደለም፡፡

ጠቅላላ ገቢያችን ከሕዝብ ብዛታችን አንፃር

ኢትዮጵያ በጠቅላላ የገቢ ዕድገቷ በዓለም 14ኛ ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ፍጥነት እያደገ ያለው ጠቅላላ ገቢ ለሕዝብ ቁጥራችን ሲካፈል ዛሬም ውራ እንደሆንን ይነግረናል፡፡ በጠቅላላ ገቢ ለሕዝብ ቁጥር ምጣኔ ኢትዮጵያ በአይ.ኤም.ኤፍ. ደረጃ ላይ169ኛ ከ187 አገራት እና የዓለም ባንክም 169ኛ ከ180 አገራት አንፃር ተቀምጣለች፡፡ ያውም ይህ  ምጣኔ በሀብታሞች እና በድሆች መካከል ያለውን የገቢ ክፍተት ከግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም፡፡ ጠቅላላ የዜጎች የኑሮ ሁኔታ ተሻሽሎ እንደሆነ እና እንዳልሆነ የሚገመግመው የተባበሩት መንግሥታት ሰብኣዊ ልማት ኢንዴክስ ላይ ኢትዮጵያ ከዚህም በላይ ዝቅ ብላ 173ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ ስለዚህ ከልማት ራቅ ብለን እንደምንገኝ ብዙ እማኝ መጥራት አይጠበቅብንም፡፡

በዚያ ላይ ደግሞ በቅርቡ የኢኮኖሚስቱ ኢንተሊጀንስ ዩኒት እ.ኤ.አ. በ2014 ፈጣን ዕድገት ያስመዘግባሉ ብሎ ከገመታቸው ዐሥር አገራት ውስጥ ኤርትራ ሳትቀር 8 በመቶ እንደምታድግ (በ9ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ) ኢትዮጵያ ግን ዝርዝሩ ውስጥ መግባት አልቻለችም፡፡ ይህ ማለት የተጀመረው ዕድገትም፣ ልማት ደጃፍ ላይ ሳይደርስ ሊሸረሸር እንደሚችል እና መንግሥት የባለሙያዎቹን ምክር በመስማትና ሕዝባዊ ተሳታፊነትን በማሳደግ ለዘላቂ ልማት የሚያደርስ የኢኮኖሚ ግንባታ መስመር ማስመር እንዳለበት አመላካች ነው፡፡ ከዚያ ውጪ በኢኮኖሚ ስርዓቱ ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችን እየቆጠሩ ‹‹ልማት መካድ›› የሚል ባጅ መለጠፍ ‹‹ልማታዊ›› አይደለም፡፡

ሕወሓት ከመለስ ጋር ተቀብሮአል ክፍል ሁለት ከነፃነት አድማሱ

አሜሪካውያን ባለስልጣኖችን ያጃጃለ አለማቀፍ አራዳ፤ በብርሃኑ አስረስ መጽሐፍ መነሻነት

$
0
0

ከክፍሉ ሁሴን

penራሱን ካልናቀ እና ጣል ጣል ካላደረገ በቀር ማንኛውም ጎልማሳ የተካበተ፣ሊወሳ እና በታሪክ ሊዘከር የሚችል የሕይወት ልምድ አለው።አንዳንዶች እንዲያውም የራሳቸውን ግለ ሕይወት ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ የአንድን ማህበረሰብ ታሪክ በእጅጉ ሊመለከት ከሚችል ሁነት ጋር ባጋጣሚ ይገናኙና የታሪክ ሁነቱ አካል ወይም ማዕከል እስከመሆን ይደርሳሉ።የሚያሳዝነው በኛይቱ አገር ይህንን አውቀን ማስታወሻ በመያዝ ለሚቀጥለው ትውልድ ትምህርት እንዲሆን ትውስታችንን በጽሁፍ የምናበረክት እጅግ ጥቂቶች ነን።ለዚህም ነው በቅርቡ ያነበብኩትን የ “ማን ይናገር የነበረ–የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ”ን መጽሐፍ ደራሲ አቶ ብርሃኑ አስረስን ለማድነቅ፤ከማድነቅም አልፎ በመጽሐፋቸው የተነሱት አንዳንድ የታሪክ ሁነቶች እኔንም በትውስታ ብልጭታ (flashback )ወደኋላ ስለወሰዱኝ ይህንኑ በማነሳሳት ሌሎች ልክ እንደ አቶ ብርሃኑ አስረስ የተካበተ ልምድ ያላቸው እንዲሁም አገራችንን በሚመለከት የታሪክ ሁነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተሳተፉ እንዲጽፉ ለመጎንተልም ጭምር ነው።እርግጥ ባሁኑ ወቅት የግለ ሕይወት ታሪክ (Autobiography )መጽሐፍ ትንሳኤ የሆነ እስኪመስል ድረስ ታዋቂም፤ እጅግም ታዋቂ ያልሆኑ ግን ባንድ የታሪክ ክስተት የተሳተፉ ሰዎች የጻፏቸው መጽሐፍት በብዛት እየታተሙልን በማንበብ ላይ እንገኛለን።በዚህ አይነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (አአዩ) ፕሬስ ከታተሙት መጽሓፍት ይህን እንድጭር የጎነተለኝ የአቶ ብርሃኑ መጽሐፍ አንዱ ነውና ዩኒቨርሲቲውንም በዚህ አጋጣሚ ይበል ይበል ማለት ተገቢ ይመስለኛል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ/PDF

Health: የጨጓራ ህመሜ ወደ ካንሰርነት ተቀይሮ ይሆን? መፍትሄውን ጠቁሙኝ እባካችሁ

$
0
0

ዕድሜዬ 43፣ ፆታዬ ወንድ፣ ስራዬ ደግሞ በግል ስራ የምትዳደር፣ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነኝ፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ የተጠናወተኝ ጨጓራ እስካሁን ያሰቃየኛል፡፡ አንቲ አሲድ ሽሮፕና የጨጓራ ክኒኖች ቀለቦቼ ናቸው፡፡ በሳምንት ውስጥ ውስጤ ሳይቃጠል በሰላም የማሳልፋቸው ቀናት ሁለት አይሞሉም፡፡ የጭንቀቴ መንስኤ ግን ይህ የጨጓራ ህመም ብቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ እንደ እኔው በኃይለኛ ጨጓራ ሲቸገር የነበረው አባቴም በመጨረሻ ችግሩ የጨጓራ ካንሰር ሆኖ ተገኘ፡፡ ሐኪሞቹም በኦፕሬሽን ሊሞከር ከሚቻለው በላይ ተስፋፍቷልና ጨረር ይሞከርለት ተብሎ ነበር፡፡ እሱም ብዙም ሳይረዳው ካረፈ ዓመት ሞላው፡፡ እናም እኔም ጨጓራዬ በለበለበኝ፣ ቃር በበዛብን ቁጥር ውስጤን ከሚሰማኝ የማቃጠል ፀባይ ይበልጥ የሚረብሸኝ ወደ ካንሰርነት ተቀይሮ ይሆን? ወይ የሚለው ስጋቴ ነው፡፡ ይሄን ስጋቴን በምን ላጥፋው? ወደ ካንሰርነት ተቀይሮ ከሆነስ የኦፕሬሽ ጥቅም እምን ድረስ ነው?
ተድላ ነኝ

ask your doctorየዶ/ር ዓብይ ምላሽ፦ ውድ ተድላ ጥያቄህን ከአክብሮት ጋር በሚከተለው መንገድ አስተናግደነዋል፡፡ በተለምዶ ጨጓራ እያልን የምንጠራው ህመም ለጨጓራ ብቻ የተወሰነ ህመም ሳይሆን ትንሹን አንጀት ጨምሮ በተናጠል ወይንም በጋራ የውስጥ ግድግዳቸው ተልጦ ሲቆስል የሚኖር የማቃጠል የህመም ስሜት ነው፡፡ ቃር፣ ደረት እና ከእምብርት በላይ ማቃጠል፣ ጀርባ እና ውስጥ እጅ መንደድ፣ ማግሳት፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ ሁሉ ከጨጓራ ህመም ምልክቶች ሊመደቡ ይችላሉ፡፡ የጨጓራ ካንሰርም ተመሳሳይ ምልክቶች ሊኖሩት ሲችሉ ጨጓራ ካንሰር ቁስሉ የሚገኘው ግን እዛው ጨጓራ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ የካንሰርነት ባህሪይ ያላቸው ሴሎች ግን ከጨጓራም አልፈው አካባቢውን ሊያዳርሱት ወይንም በደም እና ሊምፍ አማካኝነት ወደ ሩቅ ቦታ ሊዛመቱ ይችላሉ፡፡

ውድ ዓለሙ አባትህን በጨጓራ ካንሰር ማጣትህ ጭንቀትህን ቢያንረው አያስገርምም፡፡ አስፈላጊውን ምርመራዎች በማድረግ ግን ይህን ጭንቀትህን ማስወገድ ትችል እንደነበር ስንነግርህ አሁንም አልረፈደምና ምርመራዎችን ልታደርጋቸው እንደምትችል ልናሳስብህ እንወዳለን፡፡

በመጀመሪያ የጨጓራ ካንሰር ጠቋሚ ምልክቶችን ለማብራራት ያህል የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ በል፡፡ የጨጓራ ካንሰር ዕድሜ ሲገፋ ይበልጥ የሚስተዋል ህመም እንደመሆኑ
ከአርባ ዓመት ዕድሜ በኋላ ድንገት የሚጀምር የጨጓራ ህመምን በቸልታ ማለፍ አያስፈልግም፡፡ አዲስ የተነሳ የጨጓራ ህመም ብቻም ሳይሆን ድንገት ከአርባዎቹ ዕድሜ በኋላ ተባብሶ እረፍት የሚነሳ የጨጓራ ህመምንም ሐኪም ጋር ቀርቦ የጨጓራ ካንሰር አለመሆኑን ማየት ያስፈልጋል፡፡

ክብደት መቀነስ፣ ሆድ ላይ የሚስተዋል እብጠት ወይንም ምግብ መዋጥ አለመቻልም እንዲሁ ከጨጓራ ህመም ምልክቶች ጋር በህብረት ከታዩ የጨጓራ ካንሰር ተከስቶ ሊሆን ይችላልና መዘግየት አያስፈልግም፡፡

ask your doctorከሁሉ ይበልጥ ግን የጨጓራ ክኒኖችን እየዋጥክ የማቃጠል ስሜቱን ለማሸነፍ ከመጣር ይልቅ በደንብ ልትመረመር እና ልትታከም ይገባል፡፡ በቀላሉ አልታገስ ያለ የጨጓራ ህመም ሔሊኮባክተር ፓይሎሪ በሚባለው ባክቴሪያ አማካኝነት የተነሳ የጨጓራ ህመም ሊሆን ይችላልና በቀላል የደም ምርመራ ማወቅ ይቻላል፡፡ ህክምናውም እጅግ ቀላል ሲሆን ሶስት አይነት መድሃኒቶችን (ሁለት አይነት አንቲ ባዮቲክስ እና አንድ የአሲድ ምርት የሚቀንስ ታብሌት) ለሁለት ሳምንት ብቻ በመውሰድ ለዓመታት የጨጓራ ህመም እንዳይመለስ ያደርጋል፡፡

ባክቴሪያው በደም ምርመራ እንደሌለ ከተረጋገጠና ሐኪምህ የጨጓራህን ቁስል ባህሪይ ለማወቅ ከፈለገ (የካንሰርነት ባህሪይ ይኑረው፣ አይኑረው) የራጅ ምርመራ ያደርግልሃል፡፡

ይሄኛው የራጅ ምርመራ ግን ከተለመደው የተለየ ነው የሚሆነው፡፡ ምክንያቱም የጨጓራህን ውስጣዊ ግድግዳ ያለበትን ሁኔታ በራጁ እንዲታይ አስቀድመህ የምትጠጣው ኬሚካል ይኖራል፡፡ ወይንም ደግሞ ሐኪምህ በኢንዶስኮፒ የጨጓራህን ውስጣዊ ግድግዳ ሊመለከትና ከተጠራጠረም ከቁስሉ አካባ ናሙናዎችን ወስዶ በፓቶሎጂ ምርመራ የካንሰርነት ባህሪይ እንዳለውና እንደሌለው ማረጋገጥ ይችላል፡፡

ገና በ43 ዓመት ዕድሜህ ህመምህ የጨጓራ ካንሰር የመሆን ዕድሉ እጅግ አናሳ ቢሆንም ጥያቄህን ለመመለስ ያህል ለጨጓራ ካንሰር የሚደረገው ህክምና በዋነኝነት በኦፕሬሽን ቆርጦ ማውጣት መሆኑን ልንጠቁምህ እንወዳለን፡፡ በሽታው ሳይሰራጭ ከተደረሰበት ከካንሰሩ ሙሉ ለሙሉ የመፈወስ እድል ሲኖር ብዙው ጊዜ ግን ይህ አያጋጥምህም፡፡ በተጨማሪም ከቦታው አልፎ ለተስፋፋ የጨጓራ ካንሰር ከኦፕሬሽ ጎን ለጎን የጨረር ህክምና መስጠትም ይቻላል እያልን ወድ ተድላ ሳትዘገይ ሐኪም ዘንድ ቀርበህ ትታይ ዘንድ በድጋሚ እንመክርሃለን፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ መጻዔ-ዕድል

$
0
0
የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት፤ ከምድቡ ማጣሪያ ውድድሮችን አሸንፎ በአፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ፤ ከ 31 ዓመታት ጥረት በኋላ ለመሳተፍ መብቃቱ ፤…

ምኒልክን ብትወቅሱ ማንነታችሁን ትረሱ – ከኃይሌ ላሬቦ (ባለ 51 ገጽ ሰፊ ትንታኔ)

$
0
0

minilik
የኔልሶን ማንደላን ለቅሶና ቀብር ሳይ በጣም ተገረምሁ ብቻ ሳይሆን እፍሪቃዊ መሆኑ ራሱ አኰራኝ። ከዚህም ተነሥቼ፣ታሪክን ወደኋላ መለስ ብዬ በኅሊናዬ መስተዋት ቃኝቼ ሳበቃ፣ ጊዜው እንደዛሬ ሁኖ ቢያመችለት ኖሮ፣ እንደሳቸው ሊለቀስ የሚገባ ሰው በአፍሪቃ ምድር ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅምን ብዬ ራሴን በራሴ ደጋግሜ ጠየቅሁ። ማንዴላ የሚደነቁት፣ በቀለሙ በመጀነንና፥ በዘመናዊ መሣርያው በመተማመን፣ በበላይነት ረግጬው ልግዛው ብሎ፣ ለብዙ ዘመናት በሥልጣን ላይ ሁኖ ያሠቃይ የነበረውን ጨቋኙን የነጮች ግዛት ከነሥርዐቱ አሸንፈው፣ ለሀገራቸው ጥቊር ሕዝብ የድል ዋንጫ አጐናፅፈው፣ ነፃነቱንና ክብሩን ስለመለሱለት ነው። ግፈኞቹን የድሮ ጠላቶቻቸውንም እንደመበቀል ፈንታ በፍቅር ያዟቸው። ሁሉም የደቡብ አፍሪቃ ዜጋ በጐሣና በዘር፤ በሃይማኖትና በቀለም ሳይለያይና ሳይከፋፈል፣ ታዲያ በመቻቻል፣ ባንድነትና በፍቅር ተቀራርቦ እንዳንድ ሀገር ሕዝብ እንዲኖር አደረጉ። ለኻያ ሰባት ዓመታት በእስራት ራሳቸውን በመሠዋት፣ ጠላታቸውን በማሸነፍ፣ ራሳቸውንና ሀገራቸውን ያኰሩ ደግና ብልህ መሪ፣ ሰውን በማንነቱና በእምነቱ ሳይሆን በሙያውና በችሎታው የሚፈርጁ፤ ጠላትን እንኳ የሚራሩና የሚወዱ ሰው ነበሩ። ይኸንን በዐይነ ኅሊናዬ መላልሼ ካሰላሰልሁ በኋላ፣ የዓለምን ታሪክ ደግሞ ቃኝቼ ሳበቃ አንድ እጅግ በጣም ታላቅ ሰው አገኘሁ። አፄ ምኒልክ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ/PDF

ሕንድ ወደ ሃገሯ የሚገቡ ኢትዮጵያውያንን እና ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎቿን የፖሊዮ ክትባት እንዲወስዱ አዘዘች

$
0
0

polio
(ዘ-ሐበሻ) ሕንድ ወደ ሃገሯ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን የፖሊዮ ክትባት እንዲወስዱ የሚያስገድድ ሕግ ማውጣቷ ተሰማ። ፖሊዮ ወይም የልጅነት ልምሻ በቫይረስ ምክንያት የሚነሳ በሽታ ሲሆን፣ አካልን ከማጉደል ባሻገር ህይወት እስከ ማሳጣት ያደርሳል። በሽታውም ቀጥታ የሚያድን መድኃኒትም የለውም።

ዘሒንዱ የተባለው የህንድ ጋዜጣ ዛሬ እንዳስነበበው ከመጪው ማርች 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ ማንኛውም የፖሊዮ ተጠቂ የሆኑ ሃገራት ዜጎች ህንድ ከመግባታቸው በፊት የፖሊዮ ክትባት እንዲወስዱ አዲስ የወጣው ህግ ያስገድዳል።

የሕንድ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከህንድ ወደ ፖሊዮ ተጠቂ የሆኑ ሃገራት ለሚጓዙ ዜጎቹም ለአንድ ዓመት የሚቆይ OPV የተባለ ክትባት (oral polio vaccine) ያዘጋጀ ሲሆን የአፍጋኒስታንን፣ የናይጄሪያን፣ የፓኪስታንን፣ የኢትዮጵያን፣ የኬንያን፣ የሶማሊያን እና የሶሪያን ሃገራት ከፖሊዮ ተጠቂ ሃገራት በመመደብ ወደነዚህ ሃገራት የሚጓዙ ዜጎችም ሆነ ወደ ህንድ የሚገቡ የነዚህ ሃገራት ዜጎች የፖሊዮ ክትባት እንዲወስዱ ከማርች 1 ቀን ጀምሮ ያስገድዳል።

እንደ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ገለጻ የOPV ክትባት የወሰዱ ዜጎች ሰርተፊኬት የሚሰጣቸው ሲሆን ሰርተፍኬቱ ለአንድ ዓመት ያገለግላል። የOPV ክትባትን በየትኛውም ዕድሜ ክልል ያለ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከላይ ከተጠቀሱት 7 ሃገራት የሚመጡ ዜጎችም ሆኑ ወደዚያ ሃገር የሚጓዙ የህንድ ዜጎች መውሰድ አለባቸው ሲል የሂንዱ ዘገባ ጨምሮ ገልጿል።

ኢትዮጵያ በ2008 ዓ.ም ፖሊዮን ከኢትዮጵያ አጥፍቻለሁ ስትል ብታውጅም ባለፈው ኦገስት ላይ ግን በምስራቁ የሃገሪቱ ክፍል የፖሊዮ ተጠቂ መገኘቱ አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል። ባለሙያዎች እንደሚሉት በሶማሊያና በኬንያ እስካሁን ድረስ የፖሊዮ ቫይረስ ያልጠፋ በመሆኑ ወደ ምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል መግባቱ ብዙም ላያስገርም ይችላል ይላሉ።

ESAT Radio Sun, Feb 9 2014

$
0
0
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

“እግዚአብሔርና ፋሺሽቶቹ” ቫቲካን ከሙሶሊኒ ጋር ስለ ነበራት ሕብረት ስለ ዴሽነር መጽሐፍ፤ በኪዳኔ ዓለማየሁ

$
0
0

ይህ ጽሑፍ የሚያተኩረው ዋናው ምንጩ በሆነው፤ እ.አ.አ በ2013 (2006 ዓ/ም) ታትሞ ለንባብ በደረሰው፤ ካርልሔንዝ ዴሽነር (Karlheinz Deschner) “እግዚአብሔርና ፋሺሽቶቹ – የቫቲካን ሕብረት ከሙሶሊኒ፤ ፍራንኮ፤ ሒትለርና ከፓቬሊች ጋር” “God and The Fascists – The Vatican Alliance with Mussolini, Franco, Hitler, and Pavelic” በተሰኘው መጽሐፍ በተካተተው ማስረጃ ላይ ነው። የጽሑፌ ዓላማም በፋሺሽቶች ኢትዮጵያ ላይ ስለ ተፈጸመው እጅግ መራር የጦር ወንጀል፤ የቫቲካንና የሙሶሊኒ ግንኙነት ምን ይመስል እንደ ነበር ደራሲው ተመራምሮ ያቀረበው ማስረጃ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰፊ ግንዛቤ እንዲያገኝ ለማድረግ ነው። ስለዚህ፤ ደራሲው ቫቲካን ከሒትለር፤ ከፍራንኮና ከፓቬሊች ጋር ስለ ነበራት ግንኙነት ያቀረበውን ማስረጃ በዚህ ጽሑፌ አላካተትኩትም።
እንደሚታወቀው፤ በሙሶሊኒ ትመራ የነበረችው ፋሺሽት ኢጣልያ፤ በቫቲካን ያልተቆጠበ ድጋፍ፤ ኢትዮጵያ ላይ በፈጸመችው የጦር ወንጀል አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከመጨፍጨፋቸው በላይ 2 000 ቤተ ክርስቲያኖችና 525 000 ቤቶች ወድመዋል። ሌላም እጅግ አስከፊ ግፍ ተፈጽሟል።

በዓለም-አቀፍ ሕግ በተከለከለ የመርዝ ጋዝ ጭምር በመጠቀም ፋሺሽቶች በፈጸሙት የጦር ወንጀል፤ ቫቲካን ስለ ነበራት ሚና በተለይም መሪዋ ስለ ነበሩት ፖፕ ፓየስ 11ኛና ፋሺሽቱ ሙሶሊኒ ሕብረት በብዙ ማስረጃ ተረጋግጧል። በበኩሌ ከዚህ ቀደም ባቀረብኳቸው መጣጥፎች፤ እነአልቤርቶ ስባኪ (Alberto Sbacchi, “Ethiopia Under Mussolini”) አቭሮ ማንሐታን (Avro Manhattan: “The Vatican in World Politics”), ሥዩም ገብረእግዚአብሔር (“The Symphony of My Life”) ወዘተ. መጽሐፎች እንዲሁም ታዋቂ በሆኑ ጋዜጦች (New York Times) እና (Manchester Guardian) የቀረቡትን አስተማማኝ ማስረጃዎች አካፍያለሁ። በተገኙት ማስረጃዎች ሁሉ ፖፕ ፓየስ 11ኛ ከሙሶሊኒ ጋር በነበራቸው ፖለቲካዊ ቅርበትና የመጠቃቀም ሥልት፤ “ላተራን” (Lateran) የተሰኘ ውል ተፈራርመው ሲደጋገፉ እንደ ነበር፤ ፖፑ ራሳቸው የኢጣልያን ንጉሥ፤ ኡምቤርቶን “የኢጣልያ ንጉሥና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት” ብለው የባረኳቸው መሆኑን፤ የቫቲካን መሪዎችና ካሕናት የፋሺሽቱን ጦር መባረካቸውን በተጨባጭ ማስረጃ ፍንትው ብሎ ቀርቧል።

ፖፕ ፓየስ 11ኛና ሙሶሊኒ እጅና ጓንት ሆነው እንዲተባበሩ ያመቻቸላቸው ዋናው መሠረታዊ ምክንያት ሁለቱም መሪዎች ለዲሞክራሲ፤ ለሕብረተ-ሰብዓዊነትና ለኮሙኒዝም ይጋሩት የነበረው ጥላቻ ነበር። በአበው አነጋገር፤ “የጠላቴ ጠላት፤ ወዳጄ ነው” በሚለው ሰንካላ መርሆ ይመሩ ነበር ማለት ነው።

የ”እግዚአብሔርና የፋሺሽቶቹ” ደራሲ፤ ካርልሄንዝ ዴሽነርስ ምን ብሏል?

1ኛ/ እ.አ.አ ከ1922 በፊት፤ ቫቲካንና የኢጣልያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተጻራሪዎች ነበሩ። ቫቲካን ባንድ በኩል ስትሆን በሌላ በኩል፤ የሶሺያሊስትና የኮሚዩኒስት ፓርቲዎች ሐገሪቱን ለመቆጣጠር ይፎካከሩ ነበር። በተለይ ሙሶሊኒን በተመለከተ፤ በጊዜው እሱ በእግዚአብሔር የማያምን፤ እንዲያውም ስለ ክርስቶስ ተገቢ ያልሆኑ ቃላት በጽሑፍ ያቀርብ እንደ ነበረና ይህንን ሁኔታ የተገነዘቡ ሌሎች ጸሐፊዎች በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንና በፋሺሽቶቹ መሀል ምሕረት የሌለው ግጭት ሊከሰት እንደሚችል ይተነብዩ ነበር። (ገጽ 28-29)
“Mussolini was certainly an atheist. His first essay, published in 1904 and titled “There is No
God.” was about the nonexistence of God…..” (p 28) (ትርጉም፤ ሙሶሊኒ በእርግጥ በእግዚአብሔር የማያምን ሰው ነበር። (እ.አ.አ.) በ1904 ያሳተመው “እግዚአብሔር የለም” የተሰኘው የመጀመሪያ ጽሑፉ ስለ አምላክ አለመኖር ነበር።)(ገጽ 28)
2ኛ/ እ.አ.አ በ1921 ግን ሊከሰት የሚችለው ግጭት ቀርቶ ፋሺሽቶቹ ባወጡት መግለጫ፤
“…the Fascist leader announced “that the only universal idea that exists in Rome today is
the one that emanates from the Vatican.” (p. 29) (ትርጉም፤ የፋሺሽቱ መሪ (ሙሶሊኒ)፤
“ባሁኑ ጊዜ በሮም የሚገኘው ዓለም-አቀፋዊ አስተሳሰብ ከቫቲካን የሚመነጨው ነው።” በማለት
አስታውቋል። (ገጽ 29)

ስለዚህ፤ አኪሌ ራቲ (Achille Ratti) በመባል ይታወቁ የነበሩት የካቶሊክ ካርዲናል እ.አ.አ የካቲት 5 ቀን 1922 (February 5, 1922) ፖፕ ፓየስ 11ኛ (Pope Pius XI) ተሰኝተው እንደ ተመረጡ ሙሶሊኒ ከሁለት ጓደኞቹ ጋር በእለቱ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ የቫቲካን አደባባይ በመሔድ የተሰማውን ጥልቅ ስሜት አንጸባርቆ ነበር። ከጥቂት ጊዜ በኋላም ሙሶሊኒ በጻፈው ደብዳቤ ለፖፕ ፓየስ የነበረውን አድናቆት እንዲሁም በፖፑና በኢጣልያ መሀል የነበረው ግንኙነት እንደሚሻሻል አስተያየቱን ገልጾ ነበር። (ገጽ 29፤ ምንጭ (Neisser Zeitung, March 12, 1929)

የሙሶሊኒ ድርጊት ግን ሃይማኖተኛ ወይም ካቶሊካዊ በመሆኑ አልነበረም። እንዲያውም፤ ሃይማኖት ንጉሦችና ጨቋኞች ለሥልጣናቸው የሚጠቀሙበት መሣሪያ መሆኑን ያምን ነበር።
“But on the other hand, Mussolini knew that religion, as he had himself stated in his
first atheist piece of writing, is “a trick of kings and oppressors to keep their subjects
and slaves under control” (p. 30) (ትርጉም፤ በሌላ በኩል፤ በሙሶሊኒ እውቀት፤
በመጀመሪያው የኢአማኝ ጽሑፉ፤ “ሃይማኖት ንጉሦችና ጨቋኞች ሕዝቦቻቸውንና
ባሪያዎቻቸውን በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ የሚጠቀሙበት ማታለያ” መሆኑን አትቶ ነበር።)(ገጽ 30)

3ኛ/ ካርዲናል አኪሌ ራቲ፤ ለፖፕነት ከመመረጣቸው በፊት እ.አ.አ. በ1921 ስለ ሙሶሊኒ የነበራቸውን ከፍ ያለ አድናቆት እንደሚከተለው ገልጸው ነበር፤
“ Mussolini is making quick progress and will crush everything that gets in his way with
elemental force. Mussolini is a wonderful man. Did you hear? A wonderful man!…..
The future belongs to him.” (p 30)
(ትርጉም፤ ሙሶሊኒ በፍጥነት እየገሰገሰ ነው፤ የሚጋረጥበትንም ማንኛውንም ነገር በኃይል ያወድመዋል።
ሙሶሊኒ ግሩም ሰው ነው። ሰማችሁኝ? ግሩም ሰው!…..መጪው ዘመን የሱ ነው።” (ገጽ 30) (ምንጭ፤ Paris,
The Vatican, 69)

4ኛ/ አኪሌ ራቲ፤ ፖፕ ፓየስ 11ኛ በመባል ከተመረጡ በኋላ ከፈጸሟቸው ለሙሶሊኒ እጅግ ጠቃሚ ተግባሮች አንደኛው እ.አ.አ. ጥር 20 ቀን 1923 (January 20, 1923) የቫቲካን ዋና ደጋፊ የነበረውን “ፓርቲቶ ፖፑላሬ” (Partito Populare) የተሰኘውን የካቶሊክ ፓርቲ ማውደም ነበር። የዚህም ዋናው ምክንያት ለቫቲካን የፋሺሽቱ ፓርቲ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ መሆኑን በማመን ነበር።

5ኛ/ ሙሶሊኒ ለቫቲካን ያበረከተው የመጀመሪያው አገልግሎት 1.5 ቢሊዮን ሊሬ በማበርከት ነበር፤
“The first service the ex-socialist rendered to the Holy See was a financial one. He saved the
“Banco di Roma” to which the curia and many of its prelates had entrusted large amounts of
money, from bankruptcy by stepping in with approximately 1.5 billion lire at the expense of the
Italian state.” (p31-32) (ትርጉም፤ የቀድሞው ሶሺያሊስት (ሙሶሊኒ) ለቫቲካን ያበረከተው የመጀመሪያው
አገልግሎት የገንዘብ እርዳታ ነበር። በኢጣልያ መንግሥት ወጪ፤ 1.5 ቢሊዮን ሊሬ በማበርከት ቫቲካንና
መንፈሳዊ መሪዎቿ ብዙ ገንዘብ ያስቀምጡ የነበረበትን “ባንኮ ዲ ሮማ”ን ከክስረት አዳነው። (ገጽ 31-32፤ ምንጭ፤
Manhattan, 112)

በሙሶሊኒና በፖፕ ፓየስ 11ኛ መሀል የነበረው ግንኙነትና ሕብረት እጅግ የተጠናከረ ስለ ነበረ፤ ፋሺሽቶች ተቃዋሚ ካቶሊኮችን ሲያሰቃዩና ሲገድሉ ፖፑ ምንም ተቃውሞ አላሰሙም ነበር። እንዲያውም፤ የካቶሊክ ካሕናት በሙሉ ከካቶሊክ ፓርቲ ራሳቸውን እንዲያገልሉ በማዘዝ ለፋሺሽት ፓርቲ ከፍተኛ እንቅፋት የነበረውን ሁኔታ አስወገዱለት። ከዚህ በተጨማሪ፤ ከዚህ በታች ያለውን መግለጫ ለዓለም አስታወቁ፤
“Mussolini has been sent to us by Providence.” (p. 33) (ትርጉም፤ ሙሶሊኒ በፀጋ (በአምላክ) የተላከልን
ነው።) (ገጽ 33፤ ምንጭ፤ Manhattan, 115)

6ኛ/ ሌላው ሙሶሊኒና ፖፕ ፓየስ 11ኛ የተጠቃቀሙበት እጅግ ከፍተኛ ጉዳይ፤ “ላተራን” (Lateran) የተሰኘውን ውል በመዋዋል ነበር። በዚህ ውል መሠረት፤ ቫቲካን መንግሥታዊ ልዑላዊነት እንዲኖራት ከመደረጉ በላይ የኢጣልያዊ ብሔራዊ ሃይማኖት ካቶሊካዊነት እንዲሆን ተደረገ። ቫቲካንም የፋሺሽቶቹ ዋና ደጋፊ፤ አጋር ሆነች፤
“The church rejoiced. On February 13, 1929, the pope once again praised Mussolini as the man
“who was sent to us by Providence” and shortly after ordered the clergy to say prayer “for the
King and the Duce” (“Pro Rege et Duce”) at the end of daily mass.” (p. 36) (ትርጉም፤ ቤተ
ክርስቲያኗ (ቫቲካን) ፈነደቀች። እ.አ.አ. የካቲት 13 ቀን 1929 ፖፑ (ፖፕ ፓየስ 11ኛ) ሙሶሊኒን አመሥግነው
“በፀጋ የተላከ ሰው” መሆኑን እንደ ገና ገልጸው፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ካሕናቱ ለንጉሡና ለዱቼ (ለሙሶሊኒ) በየእለቱ
ሥርዓት እንዲጸልዩ አዘዙ።) (ገጽ 36፤ ምንጭ፤ Tondi, Die geheime Machr [The Secret Power], 34,
and Die Jesuiten [The Jesuits], 73, Manhattan, 118)

7ኛ/ የሙሶሊኒና የፖፕ ፓየስ 11ኛ ጠንካራ ሕብረት የተንጸባረቀበት ከባድ ክስተት በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመው የጦር ወንጀል ነበር። በቫቲካን በኩል፤ እነካርዲናል ኢልዲፎንሶ ሹስተር (ሚላን) (Cardinal Ildefonso Schuster of Milan) ኢትዮጵያን የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታይ ለማድረግና የኢጣልያን ግዛት ለማስፋፋት ወረራውን በይፋ ሲደግፉ በፋሺሽቶቹ በኩል ደግሞ ቁጥሩ እየጨመረ ለሔደው ለኢጣልያ ሕዝብ የቅኝ ግዛት ማስፈለጉን እንደ በቂ ምክንያት በማቅረብ ጦርነቱ እንዲከናወን ገፉበት። ፖፕ ፓየስ 11ኛ የፋሺሽቱን ወረራ በሚቀጥለው ቋንቋ ደገፉት፤

“On August 27 (1935), when the Italian war preparations were running at full speed, the
Pope announced-interwoven in many calls for reason and peace-that a defensive war (!) for
the purposes of the expansion (!) of a growing population could be just and right.”
(ትርጉም፤ እ.አ.አ. ነሐሴ 27 (1935) የኢጣልያ የጦርነት ዝግጅት እየተጧጧፈ ሳለ፤ ፖፑ (ፖፕ ፓየስ 11ኛ)-
ከተገቢነትና ከሰላም ጥያቄዎች ጋር እያወሳሰቡ፤ ታዳጊ ለሆነው የሕዝብ ብዛት ግዛትን ለማስፋፋት (!) የመከላከያ
ጦርነት (!) ማከናወን ተገቢና ትክክል መሆኑን ገለጹ።” (ገጽ 43፤ ምንጭ፤ Manhattan, 121 ff. The speech is
Printed in Reichspost, Vienna, August 30, 1935)
ፖፕ ፓየስ 11ኛ የፋሺሽቱን የኢትዮጵያ ወረራ የደገፉት ከላይ በተጠቀሰው መግለጫ ብቻ አልነበረም። ብዙ ሌሎች ተጨባጭ እርምጃዎች ወስደው ነበር። ከነዚህ ውስጥ፤ (ገጽ 41-49)

(ሀ) ጳጳሶቹ የወርቅ መስቀሎቻቸውንና የአንገት ሰንሰሎቻቸውን እንዲያስረክቡ አዘዙ። በተጨማሪም፤ ጳጳሶቹና
ካሕኖቹም የካቶሊክ ምእመናን ወርቆቻቸውንና ጌጦቻቸውን ለፋሺሽቱ መንግሥት ጦርነት እንዲያበረክቱ
አደረጉ።
“According to Professor Salvemini from Harvard University, at least seven Italian
cardinals, twenty-nine archbishops, and sixty-one bishops supported the Fascist
raid (on Ethiopia) immediately,….) (p. 46) (ትርጉም፤ የሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር
ሳልቬሚኒ (እንዳቀረቡት) ቢያንስ 7 (የካቶሊክ) ካርዲናሎች፣ 29 ሊቀ-ጳጳሶች እና 61 ጳጳሶች ወረራውን
(በኢትዮጵያ ላይ) ወዲያውኑ ደገፉ።” (ገጽ 46፤ ምንጭ Manhattan, 123)
(ለ) ጀርመን ሐገር የነበረው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ንብረት ለሙሶሊኒ እንዲዛወርና ለጦርነቱ የሚያስፈልገው
እንዲገዛበት አደረጉ፤
(ሐ) ሌሎች ሐገሮች የሚገኙ ካቶሊኮች የኢጣልያን ወረራ እንዲደግፉ አደረጉ፤
(መ) የካቶሊክ ካሕናትና ሰባኪዎች ለኢጣልያ ጦር ድል እንዲጸልዩ ተደረገ፤
(ሠ) የፋሺሽት ወታደሮች፤ መድፍና የመርዝ ጋዝ በተጋዘበት መርከብ የቅድስት ማርያም ምስሎችም አብረው
እንዲጓዙ ተደረገ፤

“…..Abyssinians, who had neither gas masks nor shelters, unsuspectingly fell victim to the
dangers of Catholic culture. After the so-called Battle of Amba Aradam, an Italian
captain counted more than sixteen thousand butchered “enemies” (Ethiopians). They lay
there, dead or half-dead, where the skin-burning, lung-tearing gas that was sprayed
from the air had reached them, and they were all eliminated in the most hygienic
possible way – that is, by flamethrowers. (p. 49) (ትርጉም፤ ጭንብልና መጠለያ
የሌላቸው ያልጠረጠሩ ሐበሾች (ኢትዮጵያውያን) የካቶሊክ ባህል ሰለባ ሆኑ። አምባ አራዶም
ከተሰኘው ጦርነት በኋላ አንድ የኢጣልያ ካፕቴን በቆጠረው መሠረት ከ16 000 “ጠላቶች”
(ኢትዮጵያውያን) በላይ ከአየር በተነሰነሰባቸው የመርዝ ጋዝ ቆዳቸው ተቃጥሎ፤ ሳምባቸው ተበጣጥሶ
የሞቱ ወይም በመሞት ላይ የሚገኙ ነበሩ። ሁሉም በተወረወረባቸው የእሳት ቃጠሎ በቅልጥፍና
ተወገዱ። (ገጽ 49፤ ምንጭ፤ Borgese, 400)

(ረ) የፋሺሽቱ ጦር ኢትዮጵያን 90% ሲቆጣጠር፤ ፖፕ ፓየስ 11ኛ የደስታ መግለጫ አሰምተው ነበር፤
“And the Pope also shared in the “triumphant joy of the truly great and good people
about the peace, which,” he said on May 12, 1936, “as one may hope and agree, will be
an effective contribution, a prelude to true peace in Europe and the whole world”. (p 49)
(ትርጉም፤ እ.አ.አ. ግንቦት 12 ቀን 1936 ፖፑ (ፖፕ ፓየስ 11ኛ) የደስታ ተካፋይነታቸውን ሲገልጹ፤
“ለአውሮፓና ለመላው ዓለም እውነተኛ ሰላም አስተዋጽኦ የሚኖረው ለታላቅና ግሩም ሕዝብ (የኢጣልያ)
ታላቅ ድል መሆኑ እንደሚታወቅ ተስፋ ይደረጋል።” (ገጽ 49፤ ምንጭ፤ Manhattan, German edition,
116)
8ኛ/ ፖፕ ፓየስ 11ኛን የበታቾቻቸው ከሆኑት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ተግባሮች ነጻ ለማድረግ የሚደረገው ሙከራ ሁሉ መሠረተ ቢስ ነው።
“….But all attempts to exculpate the pope are in vain because his own words are a testament
to the contrary. Quite apart from the fact that the bishops can do only what he wants. Or
should they collect gold, bless weapons, and give martial speeches to Italy, of all places, if
the pope has banned it? If he really desires peace? (p. 44) (ትርጉም፤ የራሳቸው ቃላት
ተቃራኒውን ስለሚያረጋግጡ፤ ፖፑን ከኃላፊነት ለማዳን የሚደረገው ሙከራ ዋጋ ቢስ ነው። ተጨባጩ ጉዳይ
ጳጳሶቹ ሊያከናውኑ የሚችሉት ፖፑ የፈቀዱትን ብቻ ነው። ፖፑ ከልክለው ቢሆን ኖሮ (ጳጳሶቹ) ወርቅ
መሰብሰቡን፤ የጦር መሣሪያ መባረኩንና ቀስቃሽ የሚሊታሪ ንግግሮችን፤ ሌላ ሐገር ሳይሆን በኢጣልያ ማከናወን

ይችሉ ነበር?(ፖፑ) ሰላም ቢፈልጉ ኖሮ? (ገጽ፤ 44)

መደምደሚያ፤

በኢትዮጵያ ላይ ለተፈጸመው አሰቃቂ ግፍና የጦር ወንጀል፤ በሙሶሊኒና በፖፕ ፓየስ 11ኛ መሀል ስለ ነበረው የጠበቀ ግንኙነትና ሕብረት፤ ብዙ አስተማማኝ ማስረጃ በማቅረብ ግንዛቤያችንን ስላጠናከረልን፤ ደራሲውን ዴሽነርን አመሠግናለሁ። ስለዚህ ጉዳይ፤ ተቃራኒውን በመጻፍ የማያስፈልግ ውዥንብር የፈጠሩ ጸሐፊዎችም፤ በተለይ ኢትዮጵያውያን፤ ተገቢውን እርምት በማከናወን ለውድ ሐገራችን ለኢትዮጵያ የሚገባትን ፍትሕና ክብር ለማስገኘት እንዲተባበሩ በዚህ አጋጣሚ አደራ እላለሁ።
በተጨማሪም፤ ዓለም-አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ (Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause) የተሰኘው ድርጅት በኢትዮጵያ ለደረሰው የፋሺሽት ግፍ ተገቢው ፍትሕ እንዲገኝ ለሚከተሉት ዓላማዎች እየጣረ ነው፤

(ሀ) ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤
(ለ) የኢጣልያ መንግሥት ተገቢውን ካሣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲከፍል፤
(ሐ) ቫቲካንና የኢጣልያ መንግሥት ከኢትዮጵያ የተዘረፉትን ንብረቶች እንዲመልሱ፤
(መ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤የፋሺሽቱን ጦር ወንጀል በመዝገቡ እንዲያውል፤ እና
(ሠ) በቅርቡ፤ የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት፤ አፊሌ (ኢጣልያ) ለፋሺሽቱ ወንጀለኛ የተመረቀው ኃውልት
እንዲወገድ።

ባሁኑ ጊዜ፤ ከላይ የተጠቀሰው ድርጅትና ደጋፊዎቹ በመተባበር፤ የዚህ ዓመት የካቲት 12 የሰማእታት ቀን በዓለም ዙሪያ በ30 ከተሞች እንዲከበር ጥረት እየተደረገ ነው።
ለበለጠ ዝርዝር የድርጅቱን ድረገጽ፤ www.globalallianceforethiopia.org መመልከት ይቻላል። በዚያውም፤ ኢጣልያኖች ጭምር የፈረሙት አንድ ዓለም-አቀፍ አቤቱታ ስለሚገኝ አንባቢዎች በፊርማችሁ ድጋፋችሁን እንድትገልጹ በትሕትና ተጋብዛችኋል።

ለኢትዮጵያ ክብርና ፍትሕ እንታገል!

ባረጀ ባፈጀ የጭቆና መሳሪያ የግፍ ስረአትን ጠጋግኖ ለማቆየት አይቻልም ሸንጎ

Viewing all 13695 articles
Browse latest View live

<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>