Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all 13695 articles
Browse latest View live

ምንድነው ጉዱ?

$
0
0

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ምንድነው ይሄ በየሄድኩበት የማየው ሀገራዊ ጉድ? የዚህ ሁሉ አፍዝ አደንግዝ መንስኤ ምን ይሆን? በእውነት ኢትዮጵያ የማን ወይም የነማን ናት? እንታይ ኢዩ ጉዱ! እንታይ ኢዩ’ሞ ብላዕሊ ሕዝቢ ኢትዮጵያ ዝወረደ? መአዝ ኢዩ እዙይ ኩሉ ህማምን ፃዕርን ዝክላዕ ወይን ድማ ዝውገድ? ብሃፋሽኡ ኩሉ አብዚ ዘመን እዚ ዝርዐይ ዘሎ ኩነት የጭ’ንቅን የስምብድን!ጎይታና ኢየሱስ ክርስቶስ እንተዘይመፀን እንተዘይተራድኣን ብዙኃት ነገራትና ናብ አዲ ሦርያ እንዳወፈሩ ኢዮም …
እውነትም የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው፡፡ ዶክተር ኃይሉ አርአያን ያፈራች ትግራይ፣ ገ/መድኅን አርአያን የፈጠረች ትግራይ፣ አስገደ ገ/ሥላሤን የወለደች ትግራይ፣ ወጣት አብርሃ ደስታን ያፈራች ትግራይ፣ በኢትዮጵያ ሲመጡበትና የመጡበት ሲመስለው አራስ ነብር የሚሆነውንና የደመ ቁጡነቱ የብዕር ወላፈን ከጠላት አልፎ ለየዋሃን ወዳጆቹ የሚተርፈውን የኢትዮሰማይ ብሎግ አዘጋጅ ጌታቸው ረዳን ያፈራች ትግራይ(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ጌታቸው ረዳም ስላለ ነው)፣ አብርሃ በላይን የወለደች ትግራይ፣ … ስንቶቹን ዘርዝሬ እጨርሳለሁ … እነዚህን ውድና ብርቅዬ ልጆች ያፈራች ኢትዮጵያዊት ትግራይ ከዚህ በታች የምዘረዝረውን አጸያፊ ተግባር የሚፈጽሙ ምግባረ ብልሹ ልጆችን ትወልዳለች ብሎ መገመት ይከብዳል፡፡ ነገር ግን በአንድ ሀገር ጉድ ሲወለድ የጉዱን መጠን መተንበይ አይቻልምና የማንም ምድራዊ ፍጡር አእምሮ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ግፍና በደል የሚሠሩ የትግራይ ልጆች መላዋን ኢትዮጵያን ወርረው በመቆጣጠር አሁን የምነግራችሁንና እናንተም ከዚህ ቀደም የምታውቁትን ግፍ እየሠሩ ናቸው፡፡
[አንድ ጓደኛየ ሁለት ዶሮዎች አሉት - አንዲት ሴት አንድ ወንድ፡፡ ጥሬ ሲበትንላቸው ሴቲቱ ወንዱን አታስበላውም፡፡ እርሷ ብቻ ስትበላ እርሱ አጠገቧ ሣር ቢጤ ይነጫል፡፡ እውነቴን ነው የምላችሁ፡፡ አዘናግቶ ሊለቅም ሲጀምር አርቃ ታባርረዋለች - በመንቆሯ እየነከሰች፡፡ ሌሎች ወፎችና እርግቦች አብረዋት ሲለቅሙ ግን እነሱን ምንም አታደርጋቸውም፡፡ ከራስዋ ጋር በአንድ ቆጥ የሚያድረውን ወገኗን ግን ታሳድደዋለች፡፡ ይህ ነገር ብዙ ካሳሰበኝ በኋላ የዚህን ምግብ ላይ ያለመስማማት ጉዳይ ምክንያቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ጓደኛየን ጠየቅሁት፤ ከኔው ጋር ተመሳሳይ እሳቤ እንዳለው ተረዳሁ፡፡ የዚህች ዶሮ ችግር የምግብ መኖር አለመኖር አይደለም፤ ችግሯ ማሸነፏን ለማሳወቅ የምታደርገው ጥረት ነው፤ በባዶ ሜዳና ባላስፈላጊ ሁኔታ እንዲህ የምትደክመው ሥነ ልቦናዊ የበላይነቷን ለሚመለከተው ሁሉ በተለይም በ‹ሰብኮንሸሷ› ውስጠኛ ክፍል ተሰንቅሮ ፍዳዋን ለሚያስቆጥራት ‹ኢድ/ኢጎ› ለማሳየት ነው፡፡ እርሷ ጠግባ ብዙ ጥሬ ሜዳው ላይ ፈስሶ እያለ እርሷ እዚያ አካባቢ እያለች ያ ምሥኪን ዶሮ ወደዚያች ምግብ ትውር አይልም - ሌሎች አእዋፋት ግን እንደልባቸው ይለቅማሉ - የሚገርም እውነተኛ የነገር ምስስሎሽ (አናሎጂ)! ፡፡ እሱም አቅሙን አውቆ ይኖራል፤ አሳዳጅና ተሳዳጅ አንዳቸው ባንዳቸው በጎ ፈቃድ ‹አብረው› ይኖራሉ - መኖር ተብሎ፡፡ ]
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዕዝ – ቀደም ሲል በግንቦት ሰባት እንደተገለጠውና እኛ በሀገር ቤት ያለነው ወገኖችም በቅርበት እንደምናውቀው – ለይስሙላና ለታይታ አልፎ አልፎ ከሚስተዋል የታችኛው የዕዝ መስመር ላይ የሚታይ የሌላ ብሔር ተወላጅ ምደባ በስተቀር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሥልጣኑና የውጊያ አመራሩ የተያዘው በትግሬዎች ነው፡፡ መቶ ወታደር ካየህ – ጨዋነት በተሞላበት ግምት – መላ አመራሩን ጨምሮ ሰማንያዎቹ ትግሬዎች ቢሆኑ አይግረምህ፡፡‹ታዲያ ምን ይጠበስ?› አትበለኝ፡፡ ምንም አይጠበስም፤ እኛው እንደለመድነው በአጋዚም በለው በትርሃስና በሐጎስ እንጠበሳታለን፡፡
አደራ! ወያኔ ወይም ትግሬ ስል መልካሞቹን ሳይሆን በአሁኑ ሰዓት በወያኔ አመራር ሥር ተኮልኩለው ሲያበቁ የኢትዮጵያውያንን ደም እንደመዥገር የሚመጡትን፣ እንደአልቅትና ትኋን የሚመገምጉትን ብቻ ነው፡፡ እርግጥ ነው ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ መንግሥት ኖሮን ችሎታንና ብቃትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ በእኩል የዜግነት መብታቸው የሚቀጠሩ ትግሬዎችን ለመለየት ባለመቻሉ ሁሉም የትግሬ ሠራተኛ እንደወያኔ መቆጠሩ ጊዜው ያመጣብን ፈውስ የለሽ ደዌ ነውና ይህን እውነታ ለመገንዘብ ጊዜና ትግስት እስኪኖረን ድረስ ይቅርታ መጠየቅ የሚገባን ጥቂት ትግራውያን ዜጎች መኖራቸውን ላስታውስ እፈልጋለሁ፡፡ ‹ከኑግ ጋር የተገኘሽ መጭ(ሰሊጥ?) አብረሽ ተወቀጭ› እንዲሉ እነዚህ በችሎታና ብቃታቸው ሊያውም ከሌሎች ጋር ተወዳድረው (በሜሪታቸው) ቦታውን ሊያገኙ ይችሉ የነበሩ ትግሬዎች በትግሬነታቸው ብቻ ሲታሙ ሳይ በግሌ ይሰማኛል – የሚገኙበት ሥነ ልቦናዊ ምስቅልቅሎሽ ይገባኛል፤ ህመማቸው ህመሜ መሆኑን ሳልገልጽ አድበስብሼ ማለፍም አልፈልግም፡፡ ችግራቸውን ልንረዳላቸው ይገባል እንጂ እኚህን መሰል ወንድምና እህቶቻችንን ከደናቁርትና ከእጅ እስካፋቸው ብቻ ማሰብ ከሚችሉ አንበጣ ወያኔዎች ጋር አዳብለን በነገርም ይሁን በርግማን መጎሸም እንደማይገባን እንወቅ፡፡ ይህ ችግር ደግሞ መጥፎና ማንም በቀላሉ ሊረዳው የማይችል ስስ ነገር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ከፍርደ ገምድልነት እንድንቆጠብ ማሳሰብ እፈልጋለሁ፡፡ የምናያቸው ብዙ መጥፎ ነገሮች ዕድገታቸውን ጠብቀው ያልፋሉ፤ እንኳን ይህ ዘመን የአህመድ ግራኝና የዮዲት ጉዲትምም የመንጌ ቀይ ሽብርም የዘመነ መሣፍንት ትርምስም … ሁሉም በሰዓቱ አልፏል፡፡ ይህም ያልፋል – ሰንኮፉ ወድቋል፡፡ የቀረው ካልቀረው በእጅጉ ያነሰ ነውና እንዲያው አጃኢብ ከማለትና ከጸሎት ጀምሮ የበኩላችንን ለማድረግ ከመትጋት በስተቀር በስተቀር ብዙም አይሰማን፡፡ ከሁሉም ከሁሉም ቂም በቀል የሚቋጥር ሰው በተመሳሳይ አረንቋ ለመዳከር ያለመ ነውና ከዚህ አዙሪት ባፋጣኝ እንውጣ፡፡ በነሱም አላማረ፡፡ ስቃያችን እንዳይረዝም ከብቀላና ከሸፍጥ ነጻ ሆነን ፈጣሪ ሀራ እንዲያወጣን ከልብ እንለምነው – ይቻለዋል፡፡ እየሆነ ያለውን የፈቀደው ሆን ብሎ እኛን ለመፈተን መሆኑን እንረዳ፡፡ አለበለዚያማ እነኚህ ጉዶች ይህን ሁሉ ሚሊዮን ሕዝብ እንደከብት ሊነዱት እንዴት ይቻላቸዋል? …
በተረፈ ግን ሀገራችሁ እንዲህ ሆናላችኋለች፡፡ አዲስ ነገር እየነገርኳችሁ እንዳልሆነ እኔም አውቃለሁ፡፡
የምነግራችሁ በጥቅስና በምንጭ የተዥጎረጎረ ጥናታዊ ዘገባ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሆን ብዬና በሥራዬ አጋጣሚ በመዘዋወር ያገኘሁት መረጃ ነው፡፡ መረጃየ እጅግ አስደንጋጭ በመሆኑ በቀላሉ የሚያኮርፍ ትግሬ ይህን ትንግርተኛ ጉድ የያዘ መጣጥፍ ባያነብ ይሻለዋል፡፡ በኋላ እኔ ላይ የሚለጥፈውን ታርጋ በመፈለግ እንዳይንገላታ ቀድሞውን አያንብ ዌም ድረ ገጽም ከሆነ አይለጥፈው፡፡ እዚያው በጠቡሉ እኔም እዚችው በጠበሌ፡፡ ያልተበረዘ ያልተከለሰ እውነቱ ግን ይሄውና፡፡

የመከላከያ ሠራዊት ሕንጻ

የመከላከያ ሠራዊት ሕንጻ

መከላከያ ሚኒስቴር ሄድኩ፡፡ ከበር ጀምሬ ስታዘብ ከሞላ ጎደል ሁሉም ትግሬ ነው፡፡ ወደ ውስጥ ለመግባት ምክንያቴን ገልጬ ተረኛው ዘብ ለውስጠኛው ሰው የይለፍ ፈቃድ ሊጠይቅልኝ በስልክ ሲያናግር የተጠቀመው ቋንቋ ትግርኛ ነው – አውቃለሁ፡- ከተጓዳኝ ፍካሬያዊ መልእክቱ ባለፈ ይህ ክስተት በራሱ ክፋት የለውም – የራስን ቋንቋ መጠቀምም የሚበረታታ እንጂ የሚያስነቅፍ አይደለም – መቼና የት ለምን የሚሉትን ጥያቄዎች ማጤን ግን የብዙ ልጆች እናት የሆነችን አንዲት ‹ፌዴራላዊት› ሀገር በ‹እኩልነትና በፍትህ› የሚያስተዳድሩ ወገኖች ሊያስቡበት ይገባቸው የነበረ ጉዳይ መሆኑን ማስታወስ እወዳለሁ – በዚያ ላይ የሚታሙበትን ብዙ ነገር መገንዘብና ለተጨማሪ ሃሜት በር መክፈትም ተገቢ አይደለም ፡፡ ብቻ እኔም በትግርኛ አናግሬው – በዚያም ምክንያት በጣም ተደስቶ – ገባሁ፡፡ በአገዛዙ ውስጥ በወያኔነት የተገጠገጡ ትግሬዎች – አዝናለሁ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልክ – የዋሆች ናቸው- በቋንቋ የሚያመልኩ፣ ለጎሣዊ አንድነት በቀላሉ የሚንበረከኩና ለወያኔያዊ ማንነት የሚሰግዱ ጅሎች ናቸው፡፡ ትግርኛ ጥርት አድርገህ ከተናገርክ ብዙ ሥራ ልትሠራ ትችላለህ – ከደረሱብህ ግን አንተን አለመሆን ነው(ትግርኛ በመናገሩ ምክንያት አምባሳደር ሊያደርጉት የመለመሉት ሰው ኋላ ላይ ትግሬ አለመሆኑን ሲያውቁ መሸወዳቸው ገባቸውና ሥልጠናውን ጨርሶ ሊመደብ ሲል እንዳባረሩት ቀደም ሲል ሰምቻለሁ – ከዓለም በዘረኝነታቸው የሚስተካከላቸው የነበረና የሚኖር አይመስለኝም – ከአፓርታይድም ይብሳሉ፡፡ በሀገር የጋራ ሀብት እንደልባቸው የሚፏልሉ የአሁን ጅሎች የነገ የታሪክ ዝቃጮች መሆናቸውን በድፍረት የምመሰክረው የነገ ዕጣ ፋንታቸውን ከወዲሁ ቁልጭ አድርጌ እያየሁ ለነሱና ለጠፋው ትውልዳቸው ከልቤ በማዘን ነው)፡፡ ምን አለፋህ – ወያኔዎች ቂሎች ናቸው – ብልጥነት ሲበዛ ሰውን የሚያጃጅል ይመስለኛል፡፡ ለዚህ ይመስለኛል ይሉኝታና ሀፍረት የሚባል ጨርሶውን የሌላቸው፡፡ እነዚህ ወያኔ ትግሬዎች 0.000…1 በመቶ ይሉኝታ የላቸውም፡፡ የጅልነታቸው መሠረትም ይሄው ‹ሰው ምን ይለኝ ይሆን? ታዛቢ ምን ይለኛል? › ማለት አለመቻላቸው ነው፡፡ ሀገሪቱን እኮ የአንድ ቤተሰብ ንብረት ያህል ነው የቆጠሯት! አይገርምም? ‹የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም›ና እንደልቤ መናገሬን ከጥፋት ላለመቁጠር ሞክር፡፡
[አማራ እንደወይራና ደሬ ፍልጥ ሥጋውና አጥንቱ ወያኔዎች በሚለኩሱትና በሚያስለኩሱት እሳት እየነደደ ሳለ በደስታ እየቦረቃችሁ ይህን እሳት የምትሞቁ ትግሬዎችም ሆናችሁ ሌሎች ዜጎች ወዮላችሁ! እሳት በባሕርይው ተዛማች ነው፡፡ በሰው ስቃይ የምትደሰት ሁላ ነገ ወር ተራህ ሲደርስ አንተም አይቀርልህም፡፡ ይህን ፍርድ ሰው አይደለም የሚጥልብህ፡፡ ተፈጥሮ ራሷ ናት - እግዚአብሔርም ልትል ትችላለህ፡፡ … አንድ ጉብታ ቦታ ላይ ቤቶች በእሳት መቀጣጠል ይጀምራሉ፡፡ ሰዎች በኅብረት ሆነው ውሃ ያለው በውሃ፣ ሌሎች በአፈርም በቅጠልም ያን እሳት ብዙ ውድመት ሳያስከትል ለማጥፋት ይሞክራሉ፡፡ ከጉብታው ወረድ ብሎ በሚገኝ ረግረጋማ ኩሬ ውስጥ ዕንቁራሪቶች አሉ፡፡ አንዲት ቀበጥና የሰው ችግር የማይገባት ኮረዳ ዕንቁራሪት የእሳቱ ነበልባልና ጪስ በሚሰጣት የደስታ ስሜት ተውጣ የእልልታ በሚመስል ዕንቁርቁርታ ጩኸቷን ታስነካው ያዘች፡፡ እናቷ ግን ‹ተይ ዕረፊ፤ አያድርስ ነው› ብላ ብትመክራትም ‹እንዴ እማዬ! እዚህ ውሃ ውስጥ ሆኜ ምን እሆን ብለሽ ነው› በማለት የደስታ ቡረቃዋን ትቀጥላለች፡፡ … መንደርተኛው ባለው ‹ሪሶርስ› እሳቱን ለማጥፋት ያደረገው ጥረትና ሙከራ ሁሉ አልሳካ ይለውና እንሥራ ያለው በእንሥራው ቅል ያለው በቅሉ ውሃ እየቀዳ ያን ጠንቀኛ እሳት ለማጥፋት ወደኩሬው ይወርዳል፡፡ ሁኔታው ያላማራት እናት ወደታች ወርዳ ትመሽጋለች፤ ልጅ በሰው ስቃይ እየተደሰተች በኩሬው የላይኛው ክፍል ቡረቃዋን ትቀጥላለች፡፡ እንደተባለው አያድርስ ነው ያኔ በአንዱ ቅል ውስጥ ትጠለፍና እሳት ማጥፊያ ሆና አርራ ትሞታለች፤ እናትም ብዙ አላዘነችም - ቀድማ አስጠንቅቃለችና፡፡ ሁልጊዜ ፋሲካ የለም ወንድሜ፡፡ ዘመነ መርዓ እንዳለ ሁሉ ዘመነ ፃማ ወብካይ እንዳለም ማወቅ ተገቢ ነው ያገሬ ልጅ፤ ሁልጊዜ ጅልነት ከጥቅሙ ጉዳጡ ያመዝናል እህቴ፡፡ ጥጋብንና ቂላቂልነትን ገታ አድርጎ ወደኅሊና መመለስ ለሟች ብቻ ሳይሆን ለገዳይም የሚተርፍ እርባና አለውና ጎበዝ ነቃ እንበል፡፡]
መከላከያ ሠራዊት የሀገር ሀብት ነው፡፡ አሁን ግን የወያኔ ትግሬዎች ብቻ ነው፡፡ ማንም ሌላ ኢትዮጵያዊ ‹የኔ መከላከያ ሠራዊት› ብሎ የሚቀበል አይመስለኝም – ፖሊሱንም፣ ቤተ መንግሥቱንም፣ ባንዲራውንም፣ ብሔራዊ መዝሙሩንም እንዲሁ ‹የኔ ነው› ብሎ የሚቀበል የለም፤ ባይገርማችሁ ኢትዮጵያንም የኔ ናት ብ የሚቀበላት እየጠፋ ነው፡፡ ‹እነሱው እንደፍጥርጥራቸው ያድርጓት› ብሎ አብዛኛው ሰው ትቷታል – መጥፎ የነገሮች ሂደታዊ ዕድገት! (ባንዲራ ሲሰቀልና ሲወርድ ሰዓቱ ካለመጠበቁም በላይ አክብሮ የሚቆምነና ሰላምታ የሚሰጥ ወታደር አላይም፤ ጎበዝ እንደሕዝብም እንደሀገርም አልሞትንም ብለን እንዳንወሽ!) በአመራር ሳይሆን በሌሎች ድጋፍ ሰጪ የሥራ ክፍሎች የሚገኙ ሌሎች ወገኖች እንዴት በመሰለ ፍርሀትና መሽቆጥቆጥ እንደሚኖሩ አትጠይቁኝ፡፡ በደርግና በአፄው ዘመነ መንግሥቶች ሥልጣን ላይ የነበሩ ትግሬዎች ወንበራቸው የፈቀደውን የሥራ ኃላፊነት ያለመሸማቀቅ ሲያከናውኑ የዛሬው የይስሙላ ኮሎኔል ተብዬ ‹አዛዥ› ከተላላኪ የትግሬ ወያኔ ፈቃድ ሳያገኝ አንዳችም ነገር አይሠራም፤ አስገራሚና ከአእምሮ የመቀበል አቅም በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ዘመን! ኧረ በኢትዮጵያ ጉድ ፈልቶላችኋል! የት ነበርክና ዛሬ እንዳዲስ እንዲህ ያንዘረዝርህ ያዘ እንዳትሉኝ ብቻ፡፡ አጠቃላይ ነገረ ሥራቸውና እያደር ጥሬነታቸው ደም ፍላቴን ቀስቅሶብኝ ነው አሁን በብዕር የማወጋችሁ፡፡
ሜክሲኮ ወደሚገኘው ፌዴራል ፖሊስ ሄድኩ፡፡ ዘብ አካባቢ ጥቂት ኢትግሬዎችን አየሁ፤ ወደውስጥም ገባሁ – ግን ያው እንደመከላከያው የተሞላው በአብዚ አብዚ ነው፡፡ በጥልቀት ለተመለከተው ወያኔ ትግሬዎች ያሳዝናሉ፡፡ ይህን ሁሉ ሀገራዊ ሥልጣን ለብቻቸው የያዙት እኮ ለኢትዮጵያ ዕድገትና ብልጽግና የሚጨነቅ ከሌላው ብሔር ሰው ስላልተገኘ ነው! ሸክማቸው ከበደ፤ አጋዥም አልፈለጉ፤ ብቻቸውን ይዳክራሉ፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ ብቻቸውን ሲባዝኑ ስታዩዋቸው አንጀታችሁን ይበሏችኋል፡፡ እናግዛችሁ ብትሏቸው ‹በገዛ ሀገራችን አንተን ምን አገባህ?› ከሚል ይመስላል አይፈቅዱልህም፡፡ አንድ ጊዜ በአንድ መሥሪያ ቤት አንድ ባለዲግሪ ሰው አወዳድራችሁ ላኩልን የሚል ትዕዛዝ ይወርዳል፡፡ ትግሬው አለቃ ትግሬ ባለዲግሪ ቢያፈላልግ ያጣል፡፡ ነገሩን የሚያውቅ አማራ ባለዲግሪ ቢጠይቀው በለበጣ ስቆ ‹ያንተን ዲግሪ እንጨት ስበርበት፤ ውሃ ቅዳበት› በሚል ምፀታዊ የምልክት ቋንቋ ጥያቄውን ውድቅ እንዳደረገበትና ባለዲፕሎማ ትግሬ እንደላከ አጫውቶኛል – ልጆቼን ይንሳኝ የምነግራችሁ እውነቴን ነው፡፡ ቢሆንም ይህም ያልፋልና በግብዞች ተናድዳችሁ ግብዝ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ፡፡ ሆድ ብዙ ይችል የለም? ባይሆን በዚሁ ይብቃችሁ እንዲለንና እንዲምረን ጌታን መማፀን ነው፡፡ በመሠረቱ የመንግሥት ሥልጣንና ደመወዝ የሚቀኑበትና የሚጎመዡለት ሆኖ አይደለም፡፡ ሊስትሮ ሆኖ መኖር ይሻላል፡፡ የሚያናድደን ግን ካለችሎታቸውና ካለዕውቀታቸው ሱቅ ውስጥ እንደገባ ሕጻን በዐይነ ዐዋጅ ሁሉንም ነገር እየያዙ ሥራ ስለሚያበላሹ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ በበኩሌ ሀገራዊ ሥራ እስከተቃና ድረስ፣ አስተዳደራዊ ግፍና በደል እስከተወገደ ድረስ እንኳንስ አንድ ብሔር አንድ ቤተሰብም ሀገሪቱን ቢገዛ ጉዳየ አይደለም፡፡የነዚህ ግን ለዬቅል ነው፡፡ ከዘበኝነት በቀጥታ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ሲመደብ ብታይ፣ ከጽዳት በቀጥታ የመኪና አሽከርካሪ አሰልጣኝነት በአንዲት ቀላጤ ተመድቦ ብታይ ከመገረም ባለፈ የምትለው ነገር የለህም – ኢትዮጵያ የነሱ እንጂ የአንተ ሀገር አይደለችማ! ለካንስ ዜጎች በነቂስ ከሀገር ለመውጣት የሚጥሩት ለዚህ ኖሯል?
የመኮንኖች ማሰልጠኛ ኮሌጅ ሄድኩ፡፡ የግቢው ኦፊሴል ቋንቋ ከበር ጀምሮ ትግርኛ ነው፡፡ ቤተ መጻሕፍትም ግባ መስተንግዶም ግባ የትም ግባ የትም የምታገኘው ትግሬ ነው፡፡ አደራችሁን ጥሩዎች ትግሬዎች በጉዱ ካሣ ‹ዕብደትና ምቀኝነት› የተሞላበት ንግግር እንዳትከፉብኝ፤ የመንታ እናት ተንጋላ ታጠባ ዓይነት ሆነብኝ፡፡ ራሴው ፈርቼ ሰውን አደራ ማለት ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው እባካችሁን? ግን ለምን ፈራሁ? አሃ – በይሉኝታ ባህል ነዋ ያደግሁት፡፡ እነሱ ቢተውት እኔም ልተው?
ምግባረ ሠናይ ወደተባለው ሆስፒታልም አመራሁ፡፡ ከዘበኛ እስከ ላይኛው ሜዲካል ዳይሬክተር ትግሬ ነው – በነገራችን ላይ የአሁኑን አታስዋሹኝ ማን እንደሆነ አላውቅም – እኔ በሄድኩ ሰሞን ግን ሁሉም ትግሬዎች ነበሩ፡፡ በጣም አልፎ አልፎ ጽዳቶችና ዕቃ አቀባባዮች ከሌሎች ጎሣዎች አይቻለሁ – የሄድኩበት ጊዜ ራቅ ስለሚል ነው የአሁኑን አለማወቄን የተናዘዝኩት፤ ለነገሩ ገዢዎቻችን ይሉኝታቸውን ቀቅለው የበሉ ወይም ባወጣ የሸጡ በመሆናቸው ለውጥ ይኖራል ብዬ አልጠብቅም፡፡ ሰው በጊዜ ሂደት ይማራል እነሱ ግን እየባሰባቸው ነው የሚሄድ፤ ሰዎች አልመስልህ እያሉኝ ነው ወገኖቼ፡፡
እዚያው ሆስፒታል አካባቢ የሚገኘውን የመኮንኖች መኖሪያ ካምፕ ውጪ ሆኜ ወጪ ገቢውን ታዘብኩ፡፡ እንደወያኔ የምርጫ ውጤት 99.98 የሚሆነው ወጪ ገቢ ያው ትግሬ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በአንድ የወታደር ሚኒባስ ወይም የራሽያ ዋዝ ሊፍት አግኝተህ ብትሳፈር ከአሥሩ ወታደራዊ መኮንኖች የሌላ ጎሣ የምታገኘው – ለዚያውም ዕድለኛ ከሆንክ – አንድ ቢሆን ነው፤ አንድ ጊዜ ይህን ዕድል አግኝቼ ሾፌሩ ብቻ ኢትግሬ ሆኖ ታዝቤያለሁ፡፡ እኛ በትግርኛችን ወሬያችንን እስከጣራ ስናቀልጠው ሾፌሩ ከሃሳቡ ጋር ነበር የቤቱን ጣጣ ያወጣ ያወርድ የነበረው – ያልታደለ፡፡ ምን ቅብጥ አድርጎት አማራ ሆነ?
ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ሄድኩ – ይገርማችኋል አሁን አሁን እርሱ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ብዙ ተቀጣሪ ኢትግሬዎች አየሁ፡፡ የኃላፊነት ቦታዎችን ግን አትጠይቁኝ፤ ግቢው የተጥለቀለቀው የሚመስላችሁ በ‹ጌትነታችን ይታወቅልን› ሥነ ልቦናዊ ደንባራ ስሜት እየተነዱ ጮክ ብለው በሚያወሩ ወያኔ ትግሬዎች ነው፡፡ ይሄ ‹ምቀኝነቴ› ዛሬ የት እንደሚያደርሰኝ አይቼው፡፡ በነገራችን ላይ ቦታው ለመንግሥት ሥልጣን አሰጋም አላሰጋም በተለይ የሚበላበትና የሚጠጣበት የሥልጣን ቦታ ላይ ወያኔ ትግሬ ይጠፋል ማለት ዘበት ነው – ዋና ቦታ ለይምሰል ኢትግሬ የያዘው ቢመስል ጉዳዩ ሌላ ነው፡፡ ሀገሪቱ በአንድ ብሔር ሥር በጥገትነት ስለተያዘች ትግሬ በሥልጣን የሌለበትን መሥሪያ ቤት ለማግኘት እንደዲዮጋን ጠራራ ፀሐይ ላይ ፋኖስ ጨምረህ ብትዞር አታገኝም – እንዴት ብሎ? ሀገርን የፊጥኝ አሥሮ የመምራት ታሪካዊ ኃላፊነት በትግሬዎች ጫንቃ ላይ ወድቆ ትግሬን ከማንኛውም የሥልጣን ቦታ ማጣት በፍጡም አይታሰብም፡፡ ማንንስ ያምናሉ? ማንንም! ‹ሌባ እናት ልጇን አታምንም› ይባላል፡፡
የዚህ ሁሉ ከንቱ ተግባራቸው መንስኤ ሌሎችን ያለማመን ችግር ነው፡፡ ማይም ወያኔ ትግሬ የቢሮ ኃላፊ ሆኖ ሲሾም የተማረ ኢትግሬ አስፋልት ለአስፋልት ጫማውን ሲጨረስ እሚውለው ሀገሩ የርሱም ስላልሆነች ሳይሆን ወያኔዎች ‹ጥቅማችንን ይጋራብናል፤ ንግሥናችን ይጨናገፍብናል› ብለው ስለሚያምኑ ማንንም ወደመንግሥት የኃላፊነት ቦታ ማስጠጋ ስለማይፈልጉ ነው፡፡ የቬንዞላው ኒኮላስ ማዱሮ ከአውቶቡስ ዘዋሪነት በቀጥታ ወደ ምክትል ፕሬዚደንትነትና ከዛም ሳይታሰብ ወደ ዋና ፕሬዚደንትነት የተሸጋገረው በችሎታው ሳይሆን በአምባገነኖች በጎ ፈቃድ መሆኑን ለሚገነዘብ ሰው የወያኔ ደናቁርት፣ ማይምና ነቀዝ ባለሥልጣናትን የሹመት ሂደት መረዳት አያቅተውም – ወዮ ለሀገራቱ ሕዝቦች፡፡ የመማር ያለመማር ጉዳይ አይደለም፤ በመታመንና ባለመታመን መሀል ያለው ክፍተት በታሳቢነት እንደተጠበቀ ሆኖ በበላዮች ለማመን የመፈለግና ያለመፈለግ ጉዳይ ነው ዋናው ወሳኝ ነገር፡፡ ለአፍሪካዊ የፖለቲካ ሥልጣን መማር እንዲያውም አስፈላጊ አይደለም፡፡ ከተማርክ ለምን ትላለህ፤ ካልተማርክ ግን ለምሳሌ ግደል ብትባል ስንት እንጂ ለምን ብለህ አትጠይቅም፡፡ ሆድ እንጂ ራስ እንዲኖርህ አይፈለግም፡፡ የዘር ራ እንጂ የዕውቀት ምጥቀት የትም አያደርስህም፤ ደምህ እንጂ ችሎታህ አያዋጣህም፤ አጭበርባሪነትና መስሎ አዳሪነት እንጂ ለኅሊናና ለሀገር ታማኝነት ዘብጥያ ሊያወርድህ ይችላል፡፡
[ኢትዮጵያ የጉድ ሀገር ናት፡፡ ሕገ መንግሥት ተብዬውን ጨምሮ እያንዳንዱ ሕግ ሁለት ‹ቨርዥን›/መልክ አለው፡፡ አንዱ የተጻፈውና ይበልጡን ለኢትግሬዎች የሚሠራው ነው፤ ሌላው ያልተጻፈውና ለወያኔ ትግሬዎች ብቻ የሚሠራው ነው፡፡ የሰማይና የምድር ያህል የሚራራቁ አንደኛው የእንጀራ ልጆችን የሚያሰቃይ ሌላኛው የአብራክ ልጆችን የሚያስተዳደር ሁለት መንግሥታት በአንድ መንግሥት ሥር ይሉሃል እንዲህ ነው፡፡ ትግሬም ሁን ትግሬም አትሁን ወያኔ ትግሬን በሕግ አስተዳድራለሁ ብለህ ከተነሣህ መዳረሻህ ቃሊቲ ነው - እነሱ ሕግና ሥርዓት ጠላታቸው ነው ወንድሜ፡፡ ዘብጥያ የምትወርድበት ሰበብም አሸባሪነት፣ ሙሰኝነት፣ ነፍጠኝነት… ብዙ የክስ ቻርጅ ሞልቶልሃል፡፡ በአንጻራዊ ሁኔታ ደህና ልትኖር የምትችለው ያገኘኸውን እንደከብት እያመነዠክህ እንደነሱው እንደከብቶቹ ለመኖር ከወሰንክ ነው፡፡ ያ ደግሞ ለብዙዎች ስለማይስማማ ብዙው ሕዝብ ከቀን ቀን ወደዕብድነት እየቀየረ ነው፡፡]
ወደ ጥቁር አንበሣ ሆስፒል ተጓዝኩ፤ እዚያ ይልቅ የተሻለ ነገር አየሁ፤ በግቢው በአማርኛ የሚነጋገሩ ሠራተኖችን ተመለከትኩ – ያኔም የኢትዮጵያዊነት ስሜቴ በውስጤ ሲያንሠራራ ተሰማኝ፡፡ ትግርኛችን ከሰማንያ በላይ ከሚገመቱ የኢትዮጵያ ቋንቋዎቻችን አንዱ እንጂ ሁሎችንም በጋራ ቋንቋነት ሊያግባባ የሚችልን የጋራ መግባቢያ በ‹ፌዴራል› ደረጃ እንዲተካ ሕገ መንግሥቱም አያዝምና በትምክህተኝነት የሚከሰኝ ሰው ቢኖር እኔ የለሁበትም – ራሱ ይኮነንበታል፡፡ በኃላፊነት ደረጃ አሁንም አትጠይቁኝ፡፡ ከትግሬ እጅ የሚወጣ የሀገሪቱ ሥልጣን የለም – የነብርን ጅራት አይዙም ፤ ከያዙም አይለቁም ወዳጄ፡፡ ከንቱነታቸው ግን አሁንምና መቼም ያሳዝናል፡፡ ልበ ውልቆች! ጥንጥዬ ይሉኝታ እንዴት አጡ? በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ከሚተራመስ ከዚያ ሁሉ የወያኔ ትግሬ ሠራተኛ ውስጥ ‹ኧረ ጎበዝ ይሄ አካሄዳችን የኋላ ኋላ መዘዝ ያመጣብናል! ይሄ ጥጋባችን ወደርሀብ እንዳይነዳን ብዙ ሳይመሽ ቆም ብለን እናስብ!› ብሎ በዝግ ስብሰባቸው ላይ የሚያስታውስ አንድ ቆራጥ ወያኔ እንዴት ይጥፋ? እንዴት ነው ሁሉም እንደተራበ ጅብ የሚሰለቅጠውን እየሰለቀጠ፣ የሚግጠውን እየጋጠ ተያይዞ ለማለቅ የወሰነው? ምን ዓይነት አጥፍቶ የመጠፋት ቃል ኪዳን ነው? የሰውስ ይቅር የፈጣሪ ፍርድ እንዴት ተዘነጋ? ይህ ሁሉ ጉድ አልፎ አይቼው መቼስ!
ለናሙናነት እንዲሆኑኝ ወደጥቂት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ሄድኩ፡፡ ድፍን ያልተማረ ትግሬና አጨብጫቤ ኢትግሬ በብቃት ሳይሆን በታማኝ አገልጋይነት ከሚሰገሰጉባቸው የመንግሥት ተቋማት መካከል እነዚህ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ እንደጣሊያን ሶላቶ እዚህም እዚያም እንደልቡ ሲጮህና ሲያናፋ የምታዩት የወያኔ ትግሬው ባለሥልጣን ነው – ቀላልነታቸው ሲታይህ ውስጥህ በሰዎች ማንነትና ሰዎች ስንባል አንድ ያልተጠበቀ ነገር ስናገኝ ከሚታይብን ብርቅ ድንቃዊ ጠባይ አኳያ የማንነታችን ትርጓሜ ከእንደገና ይደነፈይ(to be redefined) ዘንድ ትመኛለህ፡፡ በነዚህ አካባቢዎች ጥቂት የማይባሉ ኢትግሬዎች ቢኖሩም በሥልጣናቸው የሚያደርጉት ነገር ከስንት አንድ ነው፤ ሁሉም ለትግሬዎች እጁን ሰጥቷል፡፡ የቀበሌ ምርጫ እንኳን ሲኖር ኢትግሬዎች ራሳቸው የሚጠቁሙት ታሪክ ‹ኢትዮጵያን አደራ› ያላቸውን የወያኔ ትግሬዎችን ነው – እነሱው እንዳቦኩት እነሱው ይጋግሩት› ለማለት ይመስላል፤ ሌላው በሀገሩ ውስጥ የሚኖር መስሎ ከሀገሩ ወጥቷል – ይህን ደግሞ ትግሬዎቹ አይረዱም ወይም መረዳት አይፈልጉም፤ የሌሎቸ ዜጎችን የ‹ሬዚግኔሽን› ወይም ‹ዊዝድራዋል› ስሜት ወያኔዎች የሚወስዱት እንደሽንፈትና እንደመንበርከክ እንደበጎ አጋጣሚም ነው፡፡ ብቻ የትም ቀበሌ ሂዱ ፈላጭ ቆራጩ ባብዛኛው ያው ታሪክ የፈረደበት ሀፍረተቢሱ ወያኔ ትግሬ ነው፡፡
ወደጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንዲሄድ የምናብ ሳይሆን እውነተኛ ፈረሴን ኮለኮልኩ፡፡ ይዘገንናችኋል፡፡ ለነገሩ ከሀገሪቱ ስድስት በመቶ ከሚሆን ሕዝብ በብቃታቸውና በደም ጥራታቸው ተመርጠው የአንዲትን የ87 ሚሊዮን ሕዝብ ሀገር የጦር ኃይሎች ሆስፒታል ለብቻቸው ቢቆጣጠሩ እነሱን ካላደከማቸው ምን ችግር አለው? በዚህ ጉዞየ ለነሱ ተሳቀቅሁላቸው፤ ክፉኛ አፈርኩላቸው፡፡ በተወሰነ ዲግሪም ቢሆን በደሜ ውስጥ ያለችውን ትግሬነት አውጥተህ ጣላት የሚለኝ እርኩስ መንፈስ አንሾካሾከብኝ፡፡ ወንድሞቼ – ማርም ሲበዛ ይመራል፡፡ ሰው ባይቆጣ፣ ተቆጥቶም ባይናገር፣ ተናግሮም ባይደመጥ… ፈጣሪ ምን ይለኛል ተብሎ ሀፍረተቢስነትን በትንሽ ይሉኝታ ሸፈን ማድረግ ማንን ገደለ? በዚህ ሆስፒታል የትም ግባ የትም ካለትግሬ ሌላ የሆስፒታል ሠራተኛ ለማግኘት ያለህ የመቶኛ ስሌት ዕድል በዜሮና በአንድ መካከል ነው ቢባል ከእውነቱ አንጻር ሲታይ ግነቱ እጅግ ጥቂት ነው፡፡ በተለይ አንተ ጤናማ ትግሬ ሆነህ ወደዚያ ቦታ ለጉብኝትም ሆነ ለሥራ ወይም ለህክምና ጎራ ብትል በሀፍረት ተሸማቀህ የጎሣ አባሎቼ ናቸው በምትላቸው ሰዎች በሚሠራው ያልተገባ ሥራ በመናደድ ራስህን ልትሰቅል ትደርሳለህ፡፡ የነፍጠኛ ሥርዓት ናፋቂ እንዳትባልና መቀበሪያም እንዳታጣ በመሥጋት ግን ትተሃቸው ትወጣና ወደሚመስሉህ ወገኖችህ ትቀላቀላለህ፡፡ በዚህ ሆስፒታል በዝቅተኛ ሥራ ላይ የሚገኙ ጥቂት ኢትግሬዎችን አይቻለሁ፡፡ በተረፈ ንግግራቸው ብቻ ሳይሆን ሳቃቸው ሁሉ ትግርኛ የሆነ የ‹ፌዴራል ሪፈራል የመከላከያ› ሆስፒታል ነርሶችን፣ የጤና መኮንኖችንና የህክምና ዶክተሮችን ለማየት ወደዚህ ቦታ አምራ – የሆነ ቀጭን ሰበብ ፈልግና፡፡ ግን አትናደድ – ሁሉም ሊሆን የግድ ነውና በሞኝነታቸው ለነሱው ከማዘን በስተቀር ቂምና በቀልም አትያዝባቸው፡፡ አትፍረድባቸው – እየፈሩ ነው እንዲህ ያለ የነሱን ኅሊና ሳይቀር ሊረብሽ የሚገባው መጥፎ ሥራ ውስጥ (ወጥመድም ብለው እችላለሁ) የገቡት፡፡ እልሁንና ለሥልት የሚጠቀሙበትን የዘር ጥላቻ ለጊዜው ወደጎን ትተን ለመሆኑ አንድ ወያኔ ትግሬ ከኔ የበለጠ ሆድ አለው? ለዚህች ከአንድ እንጀራ ለማታልፍ ለቆታስ ይህን ያህል ርቀት ተጉዘው ለታሪክና ለሕዝብ ትዝብት መዳረግ ነበረባቸው? አልፎ አይተነው!
ቦሌ ካርጎ ማራገፊያም ሄድኩ፡፡ ያው ነው፡፡ ትግሬ ብቻ! ወይ ዕዳቸው፡፡ በየትም ሊገጥምህ የሚችል ነገር ደግሞ ላስታውስህ፡፡ በጦርነትም ይሁን በግል ጠብ፣ በጥይትም ሁን በጎራዴ እጁ የተቆረጠ ወይም ሌላ አካሉ የጎደለ የትግሬ ሠራተኛ በብዙ ቦታ ማግኘት የተለመደ ነው – አሃ! እሱ እኮ ‹የነሱው› ነው – ደሙን ለሕወሓት ያፈሰሰ ጅግና ተጋዳላይ፡፡ ይህ ዓይነቱ ዕድል ለኢትግሬ እንደሚሰጠውና እንደማይሰጠው ለማወቅ ‹ያደረግሁት ጥረት ለጊዜው አልተሳካም›፡፡ በዚህም ቦታ አዛዥ ናዛዡ ትግሬ ነው፡፡ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂድ፣ ቤተ መንግሥት ግባ፣ ፓርላማ ሂድ፣ በማንኛወም የሚኒስቴርና የኮሚሽን መሥሪያ ቤቶች ግባ፣ ኢቲቪና ዋልታ ሂድ፣ ኢዜአም ሂድ፣ ጅምሩክ ሂድ፣ ባቡር ጣቢያ ግባ፣ አየር መንገድ ግባ፣ ሲቪል አቪየሽን ሂድ፣ ቴሌ ግባ፣ ኤልፓ ሂድ፣ ቤተ ክርስቲያን ግባ ፣ መስጊድ ሂድ፣ የትም ግባ አብዛኛውን የሀገሪቱን ሥልጣንና የጥቅም ቦታ የያዙት እነሰውና እነሱ ብቻ ናቸው፡፡ አዲ አበባ ላይ በንግዱም በፖለቲካውም ትግሬዎች ከመብዛታቸው የተነሣ መቀሌ ላይ እንዳለህ ቢሰማህ ወቅቱ የፈቀደው ፖለቲካዊ ፋሽን ውና ብዙ አትደነቅበት፡፡ መዝናኛማ በአብዛኛው የነሱ ርስተ ጉልት ነው፡፡ ሌላው ገንዘቡን ከየትአባቱ አምጥቶ ይዘባነናል? አይ ያለው ማማሩ! (የሌለው ደግሞ መደበሩ)፡፡ ወዩ አንቺን በጎጥና በሸጥ እየከፋፈለ በነገርና በቡጢ ሲያደባድብሽ፣ ለስደትና ለእንክርት ሲዳርግሽ፣ የጋራ ሀገርሽን ሲመዘምዝልሽ… እያንዳንድሽ በ‹ከነገሩ ጦም እደሩ› የማምለጫ መንገድ ራስሽን ለማዳን አላስካና ሶሎሞን ደሤቶች ድረስ እግር አውጪኝ ትያለሽ፡፡ እዚህ ያለው ደግሞ ሰማይ ምድሩ ተደፍቶበት እንደክርስቶስ ኤሎሄ ይላል፡፡ ምን ይበጃል? መጠበቅ ነው፡፡
አንድ ቀበሌ ለንግድ ከገነባቸው አሥራ ሦስት ክፍሎች ውስጥ ለላንቲካ አንዱ ብቻ ለኢትግሬ ሲከራይ አሥራ ሁለቱ ለትግሬ መከራየታቸውን የማረዳህ ይህ ሸፋፋ አካሄድ ነገ ሊያመጣ የሚችለውን ሀገራዊ ዳፋ በዓይነ ቁራኛ አጮልቄ እየተመለከትኩ በሚሰማኝ ከፍተኛ ሀዘን ተውጬ ነው – ያን ሰውዬ ከሠልፉ ለማስወጣትም ጥረት እየተደረገ እንደነበር ራሱ አጫውቶኛል፡፡ ወያኔ ትግሬ ሁሉ በጁ ሁሉ በደጁ ነው፤ ያልተሞዳሞደ ኢትግሬ ዜጋ ግን በግብር ቁልል፣ በኪራይ ቁልል፣ በ‹እንዳያማህ ጥራው፣ እንዳይበላ ግፋው› ዘዴ ከንብረትም ከሀብትም ከቤትም ከትዳርም እንዳይሆን እየተደረገ ሜዳ እንዲወድቅ ሁኔታዎች ሁሉ ይመቻቻሉ፡፡ አንድ ወያኔ ትግሬ ያለውን መብት አንድ መቶኛ ያህል እንኳን አንተ የለህም፡፡ ኢ. ቅጣው ሰባተኛ ዜጋ እንደሆንን የገለጸውን አሁን በሕይወት ኖሮ የመከለስ ዕድል ቢገጥመው ወደ ዐርባና ሃምሳ የዜግነት ደረጃ ያወርደው ነበር፡፡ እየተሠራ ያለው ግፍ ሰማይና ምድር አይችሉትም፡፡ ክፍያውን ግን ማን ሊችለው ይሆን?
አንድ ነገር ትዝ አለኝ፤ የዛሬ 23 ዓመታት ገደማ በፊት ከሬዲዮ የሰማሁት ነው፡፡ በዚያ የሬዲዮ መጣጥፍ ላይ የተገለጸው ትንቢታዊ ቃል አሁን ድረስ ከጆሮየ አልጠፋም፡፡ እንዲህ ነበር ሲባል የሰማሁት – እጠቅሳለሁ -‹ወያኔ የሚቃዥባትን የአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ከተቆጣጠረ አማራን እንኳንስ ለኃላፊነት ቦታ ለዘበኝነትም አያበቃውም› የጥቅሱ መጨረሻ፡፡ ትንቢት ይቀድሞ ለነገር ይላሉ ካህናት፡፡ ትክክለኛ ግን መጥፎ ትንቢት፡፡
ለኢትግሬዎች ታዲያ ምን ቀራቸው ብሎ መጠየቅ ከብልህ አንባቢ ይጠበቃል፡፡ ለቀሪው ሕዝብ የተረፈው በስደት ዓለምን መዞርና ዕድል ካልቀናም በመንከራተት ሕይወትን በጨለማ አዘቅት ውስጥ ሆኖ መግፋት፤ በሀገር ውስጥ ለእሥርና እንግልት መዳረግ፤ በአማራነት ሰበብ ከምድረ ገጽ መጥፋት፣ ወያኔ ትግሬ በሀገርና ከሀገር ውጪ እየተንደላቀቀና እየተንፈላሰሰ ሲኖር በበይ ተመልካችነት መታዘብ፣ ከሲዖል ለመውጣት በሚደረግ ጥረት በየበረሃው የአውሬና የሰውነት ክፍልን በቁም እየበለቱ ለሚሸጡ ጨካኞች ሲሳይ ሆኖ መቅረት፣ (ፀረ-አማራ ፍሊት ከየት እንደሚገዙ አላውቅም ያን ወዳማራው ክልል በብዛት ሲልኩ ወደትግራይ ደግሞ ኢንኪውቤተር የሚልኩ ይመስለኛል – ሊያውም ማርገዝ፣ መውለድ፣ ማሳደግና ማስተማር ሳያስፈልግ ሰውን ያህል ፍጡር ትልቅ አድርጎ ለአቅመ አገዛዝ አድርሶ የሚፈለፍል ኢንኪውቤተር፤ አለበለዚያ ይህን ሁሉ የኢትዮጵያ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የሚሞላ ትግሬ ወያኔ በነዚህ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከየት አፈለቁት ሊባል ነው? አማራን መፍጀት – በምትኩ ትግሬን ማብዛት! ትልቅ የሚሌኒየሙ የወያኔ ዕቅድ፡፡ ወዮ ለመጨረሻው የ‹ቂያማ ቀን›!)
ምን ቀረኝ? ሁሉንም ቢያወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል፡፡ ስለዚህ ተመራርቀን እንለያይ፡፡ ወያኔዎች ሆይ መልካም የደስታና የሥልጣን ዘመን ይሁንላችሁ፡፡ ለሌላውም ልብ ይስጠው፡፡ ፈጣሪ ለሁሉም ጊዜና ዕድልን አመቻችቶ ይሰጣል፡፡ አንዱ ከአንዱ እየተማረ ይህችን አጭር ግን አሰልቺ የምድር ሕይወት ማጣፈጥ ሲቻል እያመረሩ መጓዝ ለምንም ለማንም አይጠቅምምና ሁላችንም እያሳለፍነው ካለነው የመከራና የስቃይ አዙሪት ተምረን መልካም ሰዎች እንድሆን ፈጣሪ ይርዳን፡፡

እግዚአብሄር ሆይ ና፤ የቅድስቲቱን ምድርም ባርክ፤ ሕዝብህንም ከብዔልዘቡሎች የእሳት ጅራፍ አድን፡፡ አሜን፡፡

(ሰበር ዜና፡- ይህን ወረቀት ጽፌ ከጨረስኩ በኋላ የሰማሁት ነገር ነው፡፡ የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ ነጩ ብር 2200 ሲገባ ጥቁሩ 2000ን ዘለቀ አሉኝ – ከገዛ ሰው ነው የሰማሁት፡፡ ወያኔ ዕድገታችንን ማለቴ ሞታችንን በየአቅጣጫው እያፋጠነልን ነው፡፡)


ሰላማዊ ሰልፉን ከበካዮች እንጠብቀው!

$
0
0

ግርማ ሞገስ Girma Mogesግርማ ሞገስ

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ይደረጋል የሚል ዜና ዘሃበሻ ድረ ገጽ ላይ ሐሙስ ምሽት ተመለከትኩት። አንድነት ፓርቲ እና መኢአድም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በአንድነት መቆማቸውን እና መንግስት ሰላማዊ ሰልፉን መፍቀዱን ጨምሮ ይገልጻል ጽሑፉ። ወዲያውኑ ሰላማዊ ሰልፉ እንከን የለሽ እንዲሆን እጅጉን ተመኘሁኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ዐማራው በአገር አትኖርም ተብሎ እየተባረረ ኤርትራውያን ባለመብቶች ሆነው በአገሪቱ ንብረት ይዝናናሉ” ሞረሽ

$
0
0

moresh(ዘ-ሐበሻ) ሞረሽ ወገኔ የሚባለው የአማራ ድርጅት “የኢትዮጵያ አንድነት መልካም ውርስና ቅርሶቹን ተጠብቆና በእነርሱም መሠረትነት ዳብሮ መቀጠል አለበት ብላችሁ ለምታምኑ ኢትዮጵያዊትና ኢትዮጵያውያን!” በሚል ርዕስ በበተነው መልዕክት ” በምርጫው ሳይሆን ፣በተፈጥሮ ሕግ ምክንያት የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አማርኛ ከሆነ ወላጆች የተወለዱ የነገደ ዐማራ ማኅበረሰብ አባላት ባለፉት የትግሬ ወያኔ ዘረኛና ናዚያዊ አገዛዝ፡-
 በኢትዮጵያዊነት ብሔርተኝነት አራማጅነት፣
 በኢትዮጵያ አንድነት ጠበቃነት፣
 በነፍጠኝነት፣
 በትምክህተኝነት፣
 በአድኃሪነት፣
 በጨቋኝ ብሔርተኝነት፣
 በገዥ መደብነት ፣ ወዘተርፈ
ፈርጆ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል የተፈጸመበትና እየተፈጸመበት ያለ መሆኑ በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በሶማሊያ፣ በቤንሻጉል ጉምዝ ይኖሩ የነበሩ ዐማሮች በዘራቸው ምክንያት በወረንጦ እየተለቀሙና በቀን መብራት እየተፈለጉ በወታደራዊ ኃይል በታገዘ አፈና እየታፈሱ መባረራቸውንና በርካታዎቹም መገደላቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ድርጊት በየትኛውም ዘረኛ፣ ፋሽስትና አምባገነን አገዛዞች ያልተደረገ፣ በኢትዮጵያ በዘረኛው የወያኔ ትግሬ አገዛዝ ለመጀመሪያ ጊዜ አካባቢዎችን ከአንድ ዘር የጸዳ የማድረግና ይህንኑ ዘር አድኖ የማጥፋት ተግባር በማን አለብኝነት ሲከናወን እያየን ነው፡፡” አለ።
“ኤርትራውያን ኢትዮጵያዊ አይደለንም፣ በኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት የተያዝን ነን ብለው ለ30 ዓመታት ታግለው፣ በወያኔ የመገንጠል መብት አገኝተው፣ ከተገነጠሉ በኋላ በአገሪቱ ሁለንተናዊ ሀብት ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ እየተደረገ ነው፡፡ ዐማራው በአገር አትኖርም ተብሎ እየተባረረ ኤርትራውያን ባለመብቶች ሆነው በአገሪቱ ንብረት ይዝናናሉ፡፡” ያለውን የሞረሽ መል ዕክት ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የኢሕአፓ ወጣት ክንፍ ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን እንቁም አለ

$
0
0

eprpyl (1)(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያዊ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ወጣት ክንፍ ድርጅት (ኢሕአፓ ወክንድ) “በሀገር ቤት በመጭው አሁድ በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ወጣት ክንፍ ድርጅት (ኢሕአፓ ወክንድ) በሙሉ ልብ ይደግፋል። በዚህም ጸረ ወያኔ ህዝባዊ ተቃውሞ በሀገር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን ሁሉ አንዲሳተፉ ጥሪያችንን አናሥተላልፋለን።” ሲል በበተነው መግለጫ አስታወቀ።
“ኢሕአፓ ወከንድ ለአምባገነንነት መወገድና ለሕዝብ መብት መከበር በአመቺው መንገድ ሁሉ ከመደራጀት ባሻገር በድርጅት አጥር ታስሮ ከመቀመጥ ይልቅ ትከሻ ለትከሽ ተደጋግፎ የህዝብን የነቃ ተሳትፎ ለማረጋገጥ መስራት እንደሚያሻ ለአፍታም አይጠራጠርም።” ያለው ወክንድ “የኢትዮጵያ የመከራ ዘመን ሊያጥር የሚችለው በጥቂት ቡድኖች ወይም ግለሰቦች ሳይሆን አምርረው ፀረ ወያኔውን ትግል በጋራ በመታገል መሆኑን ኢሕአፓ ወክንድ አጥብቆ ያምናል።” ብሏል።
ወክንድ በጋዜጣዊ መግለጫው ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፈው ጥሪ “ስለሆነም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለጋራ ሀገራችን በጋራ እንቁም በሕዝብ የነቃ ተሳታፊነት አምባገነንነት ተወግዶ ሕዝብ ወሳኝ የሚሆንበት ሥርዓት እውን ይሆን ዘንድ በእሁዱ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን እንቁም::” ብሏል።

በዓባይ ግድብ ላይ የተደረገ ክርክር

$
0
0

Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 23 ቀን 2005 ዓ.ም. May 31, 2013)፦ አልጀዚራ በ"ኢንሳይድ ሰቶሪ" ዝግጅቱ የዓባይን ግድብ እንዲሁም ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ.ም. የወንዙን ተፈጥሯዊ ፍሰት አቅጣጫ እንዲቀይር መደረጉን አስመልክቶ፤ ትናንት ጋዜጠኛ ዴቪድ ፎስተር አቶ በረከት ስምዖንን ከአዲስ አበባ፣ ላማ ኤል-ካታውን ከካይሮ እና ክሊዮ ፓስካልን ከሎንዶን አሟግቷቸዋል። (ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

የግብጹ ኮፕቲክ ቤ/ክ ፓትሪያርክ በአባይ ጉዳይ እንድናደራደርና ግፊት እንድናደርግ አልተጠየቅንም አሉ

$
0
0

pope-Tawadros
የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር የነበራትን የብዙ ዘመናት የበላይነትና የጠነከረ ቅርርብ መሠረት አድርገው በፖፕ ታዋድሮስ 2ኛ በኩል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ ግፊት ለማድረግና የግጭት መነሻ እንዳይሆን ጫና እንዲያሳድሩ በመሐመድ ሙርሲ በኩል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል የሚል ሰፊ ዘገባ ይዘው የወጡትን የግብጽ ጋዜጦች መነሻ በማድረግ የፓትርያርኩ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥቷል። አናዶሉ የተባለው የዜና ወኪልም በቀጥታ ፖፕ ታዋድሮስ ጉዳዩን ያውቁት እንደሆነ በስልክ አነጋግሮአቸው በሰጡት ምላሽ እንደገለጹት «የግብጽ ጋዜጦች ይህንን ዜና ከየት እንዳገኙት አላውቅም፤ ለእኔ በግሌ ከፕሬዚዳንት ሞርሲ በኩል የኢትዮጵያን ግድብ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ጋር የሽምግልና ድርድር እንዳደርግ የጠየቁኝ ምንም ዓይነት ነገር የለም» በማለት ምላሻቸውን ሰጥተዋል ሲል ደጀ ብርሃን ብሎግ ዘገበ።

የደጀብርሃንን ዘገባ እንደወረደ ያንብቡት።
የፓትርያርኩ ጽ/ቤት ለዜና ወኪሉ በተጨማሪ እንደገለጸው ጥያቄው ቢቀርብላቸው የኮፕት ቤተ ክርስቲያን በጉዳዩ ላይ ለመሥራት ምንም ቅሬታ የሌላት ቢሆንም መታወቅ ያለበት ነገር ግን፤ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ መንግሥት የውሳኔ ሰጪነት ሥልጣን ውስጥ ምንም ድርሻ የሌላት መሆኑን መረዳት እንደሚያስፈልግ በመግለጫው ተመልክቷል። ለግብጽና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ጥቅምና ሰላም በሚበጅ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ዝግጁ ነን፤ ይህንን በተመለከተም የኢትዮጵያው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ሐምሌ 19/2013 ግብጽ በሚመጡበት ወቅት ስለግድቡ ጉዳይ እናነሳላቸዋለን በማለት ጽ/ቤቱ ያለውን ሃሳብ በተጨማሪ አስረድቷል። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቀድሞ በነበራት ተደማጭነት በመንግሥት ላይ የምታሳድረው ተጽእኖ ባለመኖሩ በግድቡ ጉዳይ ላይ የጎላ ሚና ይኖራታል ተብሎ አይጠበቅም ሲል በዜና ዘገባው ላይ «አናዶሉ» የዜና ወኪል ያገኘውን ማብራሪያ መነሻ አድርጎ የራሱን ትንታኔ በመስጠት ስለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የወቅቱ አቅም እስከየት ድረስ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጧል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የደርግን የውድቀት ቀን ተጠግቶ ግንቦት 20 የመፍሰሻ አቅጣጫው መለወጡ ስለተነገረው ታላቁ ኅዳሴ ግድብ የግብጽ ሚዲያዎች የጩኸትና የጦርነት ዜማ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። የጃማአ አል ኢስላሚያ ሙፍቲ የሆኑት ሼክ አብደል አክሄር ሐማድ ለተከታዮቻቸው ባሰሙት ንግግር እንደተጠቆሙት «ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ አቅጣጫ መቀየሯ በግብጽ ሕዝብ ላይ ጦርነት እንዳወጀች ያህል ይቆጠራል» በማለት ጠጣር መልዕክት አስተላልፈዋል። «አል አረቢያ» ለተሰኘው ቴሌቪዥን ጣቢያም በቀጥታ ስርጭት ባደረጉት ንግግር «የኢትዮጵያን ድርጊት የግብጽ መንግሥት በትዕግስትና በዝምታ ሊመለከተው አይገባም፤ የኢትዮጵያ ድርጊት በግብጽ ላይ የተፈጸመ የጦርነት አዋጅ ነው፤ ይህንን ድርጊት በፍጹም አንታገስም፤ በሽምግልና ብቻ የሚፈታ ጉዳይ ስላልሆነ መብታችንን በኃይል እስከማስከበር መሄዳችን የግድ ወደሚል ሁኔታ ውስጥ እየገባን ነው» በማለት አቋማቸውን ለአድማጭ፤ ተመልካቹ በግልጽ ተናግረዋል። ግብጾች የሚጠብቀንን ግዴታ ሳንዘነጋ የዲፕሎማሲውን ጉዳይ ጎን ለጎን በማካሄድ ትኩረት መስጠት ይገባናል ማለታቸውም ተወስቷል።
በሌላ በኩልም በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ወቅት የግብጽ ጦር አዛዥ የነበሩት ጀነራል ሞሐመድ አሊ ቢላል እንዳስገነዘቡት ግብጽ በዓባይ ግድብ ላይ የጥቃት እርምጃ ብትወሰድ ቀጣናውን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚቀይረው ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ሰፊ የጋራ ጥቅም ያላት ቻይናና የግብጽ ባላንጣ የሆነችው እስራኤልን ወደጉዳዩ እንዲገቡ ሊያደርጋቸው ስለሚችል ግብጽ በምትወስደው የጥቃት እርምጃ ምንም ትርፍ አታገኝም ሲሉ ለአል አረቢያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ የረቡዕ 30/ 5/2013 ዕለት ስርጭት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የሰሞኑ የግብጽ ሚዲያዎች እያራገቡ የሚገኙበትን ዘገባ ስንቃኝ ጦር፤ ጦር የሚሸት መንፈስን ባዘለ መልኩ መሆኑ ምናልባትም አንዳንዶቹ ለኢትዮጵያ ባላቸው ዝቅተኛ ግምትና ለራሳቸው ጥቅም አብልጦ የማሰብ ራስ ወዳድነት ሲሆን አንዳንዶቹም በከፍተኛ ፖለቲከኞች በኩል ሆን ተብሎ በማስፈራሪያ ሰበብ የሚሰራጭና የግብጽ እርምጃ የት ድረስ ሊሄድ እንደሚችል ለኢትዮጵያ መንግሥት መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
በዚህም ተባለ በዚያ «አስቀድሞ ነበር መጥኖ መደቆስ፤ አሁን ምን ያደርጋል ድስትን ጥዶ ማልቀስ» እንዳይሆን አንዴ የገቡበትን ሥራ ቀድሞ ባልጀመርነው ኖሮ ከማለት የኢትዮጵያ መንግሥት ከዲፕሎማሲው ጎን ለጎን ራሱን ማዘጋጀት ይገባዋል እንላለን። መንግሥት ልቡን ሰፊና እጁን ረጅም አድርጎ በፖለቲካ ያኮረፉትን በመጥራት በሀገር የጋራ ጉዳይ ላይ ማግባባት ወደሚችል የግል ሁኔታ ለመግባት የመድብለ ፓርቲውን ሥርዓት በር ከፈት ማድረግ አለበት። እንደኢትዮጵያ ባለና ውጥንቅጡ በወጣ አመለካከት ውስጥ ልማት ብቻውን ሀገር አይገነባም። አሸባሪ የተባለ ማንም ተነስቶ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው ቢል አያስገርምም። ባራቅነውና በረገምነው ቁጥር መራቁ ባህሪያዊ ነውና። አሁን በኢትዮጵያ የሚታየው ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን በልማት ዜማ የማዳፈን ጉዳይ አኩራፊ ማበራከቱና ለጠላት በር መክፈቱ አይቀሬ ይሆናል። ግብጾች ራሳቸው መሥራት ያልቻሉትን የውጪ ሥራ በሌሎች እጅ ከማሰራት ይመለሳሉ ማለት የዋህነት ነው።
ዓለማችን በአየር ለውጥ የተነሳ ሙቀቷ እየጨመረና በረሃማነትም እየተስፋፋ እንደመሄዱ መጠን አንድ ዓባይን ብቻ በተስፋ የምትጠብቅ ግብጽ በሆነ አጋጣሚ አንድ ክረምት ዝናብ በበቂ ባይጥልና ወንዙ ጎድሎ በትነት መጠኑን ከቀድሞው ቢቀንስባት ወደአጥፍቶ መጥፋት አትገባም ማለት አይቻልም። ረጅም እሳቤ ያለው እቅድ ለዓባይ የዛሬው ግድብ አስፈላጊው ነው እንላለን።
እንዲያውም ስለዓባይ የተነገረው የግብጽ ሸክም የሚራገፍበት ዘመን ደርሶም ይሆን? የሚል የትንቢት ጥያቄም እናነሳለን።
«ግብጻውያንንም በጨካኝ ጌታ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል። ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብጽም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም ደንገልና ቄጤማ ይጠወልጋሉ። በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፥ ይበተንማል፥ አይገኝምም። ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ»
ኢሳ 19፤ 4-8

Health: የመራራው ሎሚ ጣፋጭ ጠቀሜታዎች

$
0
0

ከቅድስት አባተ

lemone10ምንጭ፡ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 51

የሎሚ ስረ መሰረት ባይታወቅም፣ የመጀመሪያዎቹ ዛፎች በደቡባዊ ህንድ፣ ሰሜናዊ ምያንማር (በረማ) እና ቻይና እንደበቀሉ ይገመታል፡፡ በሎሚ ስረ መሰረት ዙሪያ የተደረገ ጥናት ፍሬው የመራራ ብርቱካንና የባህረ ሎሚ ድቃይ እንደሆነ አመላክቷል፡፡

ሎሚ ወደ አውሮጳ የገባው በጥንታዊት ሮም ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ በአንደኛው ምዕተ ዓመት በደቡባዊ ጣልያን ነው፡፡ ይሁን እንጂ፣ በወቅቱ በሰፋት አልተተከለም፡፡ በቀጣይነት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ፋርስ ከገባ በኋላ ወደ ኢራቅና ግብፅ ተሰራጭቷል፡፡ ሎሚ ለመጀመሪያ ጊዜ በስነ ጽሑፍ ላይ ሰፍሮ የምናገኘው በ10ኛው ምዕተ ዓመት በአረብኛ ቋንቋ በእርሻ ዙሪያ በተፃፈ አንድ ጽሑፍ ላይ ነው፡፡ ሎሚ በቀደምት የሙስሊም አፀድ ውስጥ በጌጥ ተክልነት ጥቅም ላይ ይውል ነበር፡፡ በ1000 እና 1150 ዓ.ም መካከል ባሉት ዓመታት ደግሞ በዐረቡ ዓለምና በሜዲትራኒያን ክልል በስፋት ተሰራጭቷል፡፡

የመጀመሪያው የሎሚ መጠነ ሰፊ እርሻ በአውሮጳ የተጀመረው በ15ኛው ምዕተ ዓመት አጋማሽ በጀኖዋ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ ክሪስቶፈር ኮለምበስ በባህር ጉዞዎቹ የሎሚ ዘርን ወደ ሂስፓኒዮላ በወሰደበት 1493 ዓ.ም ከምዕራቡ ንፍቀ ክበብ ገብቷል፡፡ ስፔናውያን አዲሱን ዓለም በወረራ ማስገበራቸው የሎሚ ዘሮችን ስርጭት አግዟል፡፡ ሎሚ በምዕራቡ ንፍቀ ክበብ በአብዛኛው ጥቅም ላይ ይውል የነበረው እንደ ጌጥ ተክልና ለመድሃኒት ነበር፡፡ ሎሚ በ18ኛውና 19ኛው ምዕተ ዓመት በስፋት በፍሎሪዳና ካሊፎርኒያ ግዛት ይተከል ነበር፡፡

ጀምስ ሊንድ የተባለው እንግሊዛዊ ሐኪም በ1747 ዓ.ም በእስከርቪ በሽታ በሚሰቃዩ መርከበኞች ላይ ባደረገው ጥናት የሎሚ ጭማቂ በመጠቀም በአመጋገብ ስርዓታቸው ላይ ቪታሚን ሲ ጨምሮ ውጤታማ መሆን ችሏል፡፡

ጥቅሞች

የሎሚ ዘይት ለአሮማቴራፒ ያገለግላል፡፡ የኦሃዩ ግዛት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የሎሚ ዘይት ሽታ በሰው ልጅ የቅስሙ ተፈጥሮ መከላከያ ስርዓት ላይ ተፅዕኖ ባያሳድርም፣ ስሜታዊ ሁኔታን ሊያሻሽል እንደሚችል ደርሰውበታል፡፡

በፍሌት (Fermentation) ላይ የተመሰረቱ ሂደቶች ከመዳበራቸው ቀደም ብሎ ሎሚ ዋነኛው የሲትሪክ አሲድ ምንጭ ነበር፡፡ ብዙ የገንዘብ ኖት የሚቆጠሩ የባንክ ገንዘብ ከፋዮችንና ገንዘብ ተቀባዮችን የመሰሉ ሰራተኞች ጣታቸውን ለማርጠብ ለሁለት የተከፈለ ሎሚ ይጠቀማሉ፡፡

የሎሚ ጭማቂ ለማጽጃነት ሊያገለግል ይችላል፡፡ ለሁለት የተከፈለ ሎሚ በጨው ወይም ሶዲየም ባይካርቤኔት (baking powder) ውስጥ ነከር አድርጎ ከመዳብ የተሰራ ድስትና መጥበሻ መሰል የወጥ ቤት ቁሳቁሶችን እስኪያንፀባርቁ ድረስ ለመወልወል ይውላል፡፡ የሎሚው አሲድ ቆሻሻውን ሲያስወግድ፣ ጨው ወይም ሶዲየም ባይካርቦኔቱ በማጽዳቱ ሂደት ያግዛሉ፡፡ የሎሚ ጭማቂው መልካም ጠረን ሊሰጥ፣ ቅባትን ሊያስወግድ፣ ቆሻሻን ሊያነጣና ጀርሞችን ሊያስወግድ ይችላል፡፡

ከሶዲየም ባይካርቦኔት ጋር ሲደባለቅ ደግሞ ከፕላስቲክ ሰራሽ ምግብ መያዣ እቃዎች ላይ ቆሻሻን ያስወግዳል፡፡

የሎሚ ልጣጭ ዘይትም እንዲሁ የተለያዩ ጥቅሞች አሉት፡፡ የመሟሟት ባህርዩ የቆየ ሰም፣ የጣት አሻራ፣ ላብና አቧሯ ለማሟሟት ጥቅም ላይ በሚውልበት ለዕንጨት ማጽጃነትና መወልወያነት ያገለግላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ የሎሚ ልጣጭ ዘይት መርዛማ ላልሆነ ፀረ ተባይ መድሃኒት ማምረቻነት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

ተመራማሪዎች ኤሌክትሮዶችን ከሎሚ ጋር በማያያዝና ኤሌክትሪክ ለማመንጨት እንደ ባትሪ የተጠቀሙበት አንድ ሙከራ ተካሂዷል፡፡ ምንም እንኳን አነስተኛ ኃይል ቢያመነጩም፣ በርካታ ሎሚ ሰራሽ ባትሪዎች አንድ አነሰተኛ ዲጂታል ሰዓት ለማንቀሳቀሰ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፡፡ ይህ አይነቱ ሙከራ በሌሎች ፍራፍሬዎችና አትክልቶች ጭምር ሰርቷል፡፡ የሎሚ ጭማቂ አንዳንድ ጊዜ በትምህርታዊ የሳይንስ ሙከራዎች በአሲድነት ጥቅም ላይ ይወላል፡፡

ሎሚ በህንድ ለባህላዊ ህክምና ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ የህንድ ባህላዊ ሐኪሞች ሎሚን እንደ ጠቃሚ ፍራፍሬ በመመለከት ባህርያቱን ያደንቃሉ፡፡ የሚኮመጥጠው፣ የሚሰነፍጠውና የአካልን ህብረ ህዋሳት የሚያኮማትረው ሎሚ የሐሞትን ከመጠን ያለፈ ፍሰትን ይቆጣጠራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ አፍን ያፀዳል፡፡ አክታን ከማስወገድ ባለፈ ያስገሳናል፡፡ በምግብ መንሸራሸር ሂደት እገዛ የሚያደርገውና የሆድ ድርቀትን የሚያስወግደው ሎሚ፣ ትውከትን፣ የጉሮሮ ችግርን፣ አሲዳማነትንና ቁርጥማትን ይከላከላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ የአንጀት ትላትሎችን ያሰወግዳል፡፡

የሎሚ ጭማቂ ጠንካራ ፀረ ባክቴሪያ ነው፡፡ የወባ፣ የኮሌራ፣ የታይፎይድና የሌሎች ገዳይ በሽታዎች ባክቴሪያ በሎሚ ጭማቂ እንደሚጠፋ በሙከራ ተረጋግጧል፡፡ ሎሚ የተወሰነ ቪታሚን ኤ እና ከሰው ሰራሹ የበለጠ ውጤታማ የሆነ ቪታሚን ሲ በውስጡ ይዟል፡፡ በሎሚ ጭማቂ ውስጥ ያለው ቪታሚን ሲ ከቪታሚን ቢ ጋር ስለሚጣመር ይበልጥ ፍቱን ነው፡፡ ሎሚ ከቪታሚን ሲ በተጨማሪ ቢ ኮምፕሌክስ ቪታሚኖችን በአነስተኛ መጠን ይዟል፡፡

የሎሚ ጭማቂ ከመጠጣቱ በፊት በውሃ መቅጠን አለበት፡፡ ንፁህ የሎሚ ጭማቂ የጥርስን ጥሩር (መስተዋት መሰል ክፍል) የሚጎዳ አሲድ አለው፡፡

ጠዋት በባዶ ሆድ ከቀዝቃዛ ውሃና ማር ጋር የተደባለቀ የሎሚ ጭማቂ መጠጣት የውስጥ አካላችንን ያፀዳልናል፡፡ የሆድ ድርቀትን ለማስወገድ ከፈለግን አልፎ አልፎ ቀዝቃዛውን ለብ ባለ ውሃ መተካት እንችላለን፡፡

የሎሚ ጭማቂ እንፍሎዌንዛን፣ ወባንና ጉንፋንን ይከላከላል ወይም እንዳይጠናከር ያግዛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ ትኩሳትን ያቃልላል፡፡ ከውሃ ጋር የተደባለቀ የሎሚ ጭማቂ የስኳር ህመምተኛን የውሃ ጥም ለመቁረጥ ይጠቅማል፡፡ ለሆድ ዕቃ ችግሮች ፈጣን ማስታገሻ ነው፡፡ ሎሚ ለነርቮችና ለልብ የማረጋጋትን ሚና ይጫወታል፡፡

ሎሚ በተለይ ለቪታሚን ሲ ጥቅም እጅጉን ይፈለጋል፡፡ ቫስኮ ዳ ጋማ በደቡብ አፍሪካ፣ የመልካም ተስፋ ርዕሰ ምድር በኩል አድርጎ ከፖርቹጋል ወደ ህንድ በተጓዘበት ወቅት ከመርከበኞቹ መካከል ሁለት ሶስተኛው ያህሉ በእስከርቪ በሽታ ሳቢያ ሞተውበታል፡፡ በአሁኑ ዘመን ግን ሎሚ በስፋት ጥቅም ላይ በመዋሉ እንዲህ አይነቱ ጥፋት አይከሰትም፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው መርከበኞች ሎሚን በመጠቀም ሕይወታቸውን መታደግ ችለዋል፡፡

በሎሚ ዙሪያ የተደረጉ ምርምሮች እንዳሳዩት፣ የሎሚ ዘይት የማረጋጋት ባህርይ ስላለው ድካምን፣ ዝለትን፣ መጫጫንን፣ ጭንቀትን፣ ስጋትንና ውጥረት በመቀነሱ በኩል እገዛ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ የሎሚ ዘይትን በአፍንጫ መማግ ማስተዋልንና ንቁነትን ሊያሳድግ ይችላል፡፡ ስለዚህም፣ የሠራተኞችን ቅልጥፍና ለማሳደግ በቢሮ ውስጥ እንደ ፍሬሽነር ሊያገለግል ይችላል፡፡ የመንፈስ ጭንቀት ከተሰማን ጥቂት የሎሚ ዘይት መሐረባችን ላይ በማድረግ በአፍንጫችን መማጉ ጥሩ ነው፡፡

ሎሚ የተወሰኑ ቅመማ ቅመሞችን፣ አልኮል መጠጥ ወይም ሲጋራ ከወሰድን በኋላ፣ አሊያም በቂ ምራቅ በማጣት ሳቢያ የሚፈጠረውን መጥፎ የአፍ ጠረን ያሰወግድልናል፡፡ ጥሩ የአፍ ጠረን እንዲኖረን ከፈለግን የአንድ ሎሚ ጭማቂ ከአንድ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሃ ጋር በመደባለቅ አፋችንን በተደጋጋሚ መጉመጥመጥ እንችላለን፡፡ ምግብ ከበላን በኋላ ሎሚ መምጠጡም እንዲሁ እገዛ ያደርጋል፡፡

ቃር፣ የኩላሊት ወይም የፊኛ ችግር ወይም የሲትረስ አለርጂ ካለብን ሎሚ ከመብላታችን ወይም ከመጠጣታችን በፊት የጤና ባለሙያ ማማከር ይኖርብናል፡፡ የጥርሳችንን ጥሩር ለመከላከል ሎሚ ከተጠቀምን በኋላ ጥርሳችንን ቢያንስ ለግማሽ ሰዓት መቦረሽ የለብንም፡፡ በሎሚ ጭማቂ ማሸት ወይም የሎሚ ጭማቂ መጠጣት ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት አይመከርም፡፡ S

tenaadam.comን ይጎብኙ

ግልጽ መልእክት ለአገራችን የታሪክ ፀሃፊዎችና ፖለቲከኞች! – (ክፍል 2)

$
0
0
ግልጽ መልእክት ለአገራችን የታሪክ ፀሃፊዎችና ፖለቲከኞች !
                                                               የታሪክ ተወቃሽነቱን በራሳችን እንጀምር !
                                                                                       (ክፍል 2)
                                                                                                                                                በመንገሻ ሊበን
 
   በዚህ ፅሁፍ የመጀመርያ ክፍል ላይ ፣ ባለፍ ገደም ከተፃፉ ተራ ዘለፋዎች ባሻገር ፣ የብዙ አንባቢዎችን ገንቢ ነቀፌታና አስተያየት ተቀብያለሁ ። በዚህ አጋጣሚ ለሁሉም አስተያየት ሰጭዎችና ነቀፌታ አቅራቢዎች ያለኝን ልባዊ አክብሮት እየገለፅኩ በቀጥታ ወደ ጀመርኩት ርእሰ ጉዳይ አመራለሁ ።
   “ የታሪክ ተወቃሽነቱን በራሳችን እንጀምር ” በሚል ርእስ ስር በተከታታይ ክፍሎች የማቀርበው ይህ ጽሁፍ፣ በማንኛውም ወገን ላይ የተነጣጠረ ጥቃት አለመሆኑን ሁሉም አንባቢዎች እንዲገነዘቡልኝ እወዳለሁ ። የፅሁፉ ዋነኛ አላማ “በሃገር ደህንነት ስም” ወይም በሌላ ሽፋን ፣ ከህዝባችን የተደበቁና በታሪክ ፀሃፊዎቻችንና ፖለቲከኞቻችን ብእሮች እምብዛም ያልተዳሰሱ ታሪኮች ይፋ ወጥተው ትውልድ ይማርባቸው ዘንድ እንዲተጉ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን አካላት ማሳስብና ማስገንዘብ ነው።
 
   እርግጥ ነው በቀዳሚው ፅሁፌ መግቢያ ላይ እንዳልኩት ካሁን በፊት ከተፃፉልንና ካነበብናቸው “ወገንተኛ” አልያም “የተዛነፉ” ታሪክ ቀመስ መጣጥፎች አኳያ…በዚህ ርዕስ ስር በንዑስ አቅም የሚቀርቡ ጭብጦች ፣ እንደ እሬት የሚመረን በርካታ ሰዎች መኖራችን የሚጠበቅ ነገር ነው። ይሁን እንጅ የራሳችን ታሪክ የራሳችን ነውና ወደድንም ጠላንም ልንቀበለው የግድ ይለናል !!
 
      ከተወሰኑ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የአመራር አባላት ጋር በተለያየ አጋጣሚ አብሬ የሰራሁ ሰው እንደመሆኔ መጠን ፣ አብዛኛዎቹ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የአመራር አባላት ፣ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ታሪክ ላይ ፣ በተለይም ደግሞ በኤርትራ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋም በቅርበት የማወቅ እድሉን አግኝቻለሁ ፣፣ በእርግጥ አንዳንድ መሪዎቻችን ለአገራችን ካላቸው ጥልቅ ፍቅር አኳያ፣ የኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠል በእጅጉ እንደሚያንገበግባቸው ጠንቅቄ ባውቅም …አብዛኛዎቹ መሪዎቻችን ግን በተቃራኒው ፣ የኤርትራን ጉዳይ በተለይም ደግሞ የአሰብን ጉዳይ ከአምባገነኑ የወያኔ መንግስት ጋር ለሚያደርጉት ትንቅንቅ ፣ የህዝባችንን ቀልብ ለመሳብ ሲሉ ብቻ “እንደመጫዎቻ ካርታነት” እንደሚጠቀሙበት አሳምሬ አውቃለሁ። (“አሰብ የማን ነች” በሚል ርእስ ስር ከዓመታት በፊት ታትሞ ለንባብ በበቃው የዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም መፅሃፍ ላይ የቀረቡትን የተዛነፉና የተንጋደዱ ታሪኮችን ልብ ይሏል ። በዚሁ መፃህፍ ላይ የአሰብን ኢትዮጵያዊነት ለማሳመን እንደማስረጃነት የቀረበው የደርግ የራስ-ገዝ ሽንሸና የዶክተሩን “ብስለት-አልባ ፖለቲከኝነት” ወይም “አውቆ አጥፊነት” ያሳበቀ ይመስለኛል።ለማንኛውም በዚህ ጉዳይ ላይ ለወደፊቱ ሰፋ ያሉና በማስረጃ ላይ የተደገፉ ፅሁፎችን ለማቅረብ እሞክራለሁ ።
 
     በመሰረቱ እኔ ለኤርትራና ህዝቧ ጥብቅና የመቆም ሃሳብም ምኞትም የለኝም ። ይልቁንም እንደ አንድ አገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ መጠን የኤርትራዊያን ከኢትዮጵያ መገንጠል በእጅጉ ያንገበግበኛል ። የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች የመጨረሻ እድል በእንዲህ አይነቱ አሳዛኝ ድምዳሜ መቋጨቱም እጅጉን ያሳዝነኛል ።
 
      ነገር ግን ፣ የኤርትራን ህዝብ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ያበቃው ዋነኛ ምክንያት ምንድን ነው በእውን ይህ ህዝብ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የወሰነው ፣ አብዛኛዎቻችን እንደምንለው “ ሻእቢያና ወያኔ ባቀነባበሩት ሴራ ብቻ ነው ” ወይስ ከኛ የተሰወረ አልያም የተዛነፈ ሌላ ታሪክ አለ…የሚለው አንኳር ነጥብ ፣ ከትላንቱ የሃቀኛ ታሪካችን ፍፃሜ አኳያ መቃኘት አለበት የሚል የፀና እምነት አለኝ ። ምክንያቱም የዚህ ታሪክ ይፋ መውጣት ፣ ለኢትዮጵያችን የወደፊት ደህንነትና አህዳዊነት የማይናቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋልና !! 
 
      ትላንትና ከትላንት ወዲያ ፣ ኤርትራን ጨምሮ በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የተከተልነው አቋም ከእውነተኛ ፍፃሜው በታቃረነ መልኩ እንደተሸፋፈነ አልያም እንደተዛነፈ ይቀጥል ካልን ግን፣ ነገና ከነገ ወድያ የኢትዮጵያን አንድነተት ለሚፈታተኑ ከፍተኛ አደጋዎች ራስን ማጋለጥ ከመሆኑም ባሻገር የወደፊቱ ትውልድ ታሪክም እንዳሳለፍናቸው አሰቃቂ ታሪኮች ሁሉ የጦርነትና የእልቂት እንዲሆን መፍረድ ማለት ነው ። ስለዚህ “ያለፈው ይበቃል እውነተኛው ታሪካችን ሳይዛነፍና ወደ የትኛውም ወገን ሳያጋድል ይነገረን ፤ ይፃፍልን ” የምንልበት ወቅት አሁን መሆን አለበት ።
 
      አሁንም ሆነ ወደፊት ደጋግሜ ለመግለፅ የምፈልገው ነገር ቢኖር፣ የታሪክ ድርሳን ማለት አኩሪ ፍፃሜዎች ብቻ እየተመረጡ የታጨቀቡት ተራ መዝገብ አለመሆኑን ነው። ታሪክ ማለት ጣፋጭና መራራው ፤ድክመትና ጥንካሬው በአንድ ላይ ተቀይጦ የሰፈረበት የትላንት እውነተኛ ፍፃሜዎች ሰነድ ነው ። ትላንትና ከትላንት ወዲያ በአያቶቻችንና ቅድመ አያቶቻችን የተፈፀሙ ታሪኮች በሙሉ የተሳሳቱ ናቸው አልያም ደግሞ ከነበሩበት ጊዜና ዘመን አንፃር ፍፃሜዎቻቸው በሙሉ የተወገዙ ናቸው የሚል አቋም የለኝም ። ምክንያቱም አንድ አስተያየት ሰጭ እንዳሉት.. “ የአያቶቻችን ስራ የሚመዘነው በአሁኑ ዘመን ሳይሆን…. እነርሱ በነበሩበት ዘመን ነውና ” ። ይሁን እንጅ በእነርሱ የተፈፀመው የትላንቱ ታሪክ ለኛና ለልጅ ልጆቻችን ትምህርት ይሆነን ዘንድ ሳይዛነፍና ሳይንጋደድ መቅረብ አለበት የሚለው አቋሜ መቼም ቢሆን የሚቀየር አይሆንም ።
 
       በየትኛውም ዘመን የነበሩ መሪዎቻችን፣ ለአገራችን ኢትዮጵያ ያበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦና ስራ መቼም ቢሆን የሚረሳ አይደለም። ከሰሯቸው ታሪኮች መካከል ደግሞ አዎንታዊ ስራዎቻቸው ይበልጥ የጎሉ መሆናቸውን ማንም ሊክደውም አይችልም። ግን ደግሞ ታሪካቸው በሙሉ አዎንታዊ ብቻ ነበር ማለት አይደለም፤ አሉታዊ ስራዎቻቸውም የታሪካቸው አካል ነውና። የአፄ ዮሃንስን አንገት ቀንጣሽነት አልያም ደግሞ የአፄ ቴድሮስን እግርና እጅ ቆራጭነት የማያምን ኢትዮጵያዊ ካለ፣ ወደ ወሎ ፤ ወደ ጎጃም አልያም ወደ ሸዋ ጎራ ይበልና ፣ ሆን ተብለው እንዲድበሰበሱ የተደረጉ ታሪኮችን ያፈላልግ ። የአፄ ምኒልክን ጡት ዘልዛይነት ለማጣራት የሚሻ ኢትዮጵያዊ ካለም …. ወደ ኦሮምያ ክልል(አርሲጎራ ይበልና በየስፍራው የሚገኙ እድሜ ጠገብ አዛውንቶችን ይጠይቅ ። ነፍጠኛ የሚለው “የተዛነፈ” ስማችንም መነሻው ምን እንደሆነ ይመርምር ። ይህ ሁሉ ታሪክ የኛ የራሳችን ነው ። ከዚህ ያለፈ ታሪክ ነው መማር ያለብን ። ከዚህ እውነተኛ ታሪክ ስንማር ነው… በወያኔና መሰሎቹ የሚነዛውን የዘረኝነት ፕሮፓጋንዳ ያላንዳች ልዩነት በጋራ ልናመክነው የምንችለው ። ከዚህ ውጭ ግን ሁሉም በየፊናውና በየዘመኑ እየተነሳ፣ ለራሱ እንዲመቸው አድርጎ የሚነግረን የተንጋደደና የተዛነፈ ታሪክ እንዲቀጥል የምንፈቅድ ከሆነ፣ ትውልድን ያሳስታል ብቻ ሳይሆን አገራችንንም ሊያሳጣን ይችላል !!
 
ertria        በእኔ እምነት ዛሬ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ላለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ መሰረቱ የትላንቱ የተዛባ ታሪክ ነው ። እንደ በርካታ የትግራይ እድሜ ጠገብ አዛውንቶች አባባልና፣ እንደህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ መሪዎች እምነት፣ ለአጼ ዮሃንስ በድርቡሾች መገደልና ለትግራይ ስርወመንግስት ማክተም ዋነኞቹ ተጠያዎች የአማራ መሳፍንቶች ናቸው። እንደነዚህ ወገኖች እምነት ፣ የአማራ መሳፍንቶች የተለያዩ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለድርቡሾች አሳልፈው ባይሰጡ ኖሮ…አጼ ዮሃንስ ባልተገደሉ፣ ትግራይን ማእከል ያደረገው ስርወ መንግስትም ከትግራይ ወደ ሸዋ ባልጋዘ ነበር ። ይህ እምነታቸው ነው እንግዲህ ከ100 አመታት በኋላ በአማራ ህዝብ ላይ የበቀል ሰይፍ እንዲመዙ ያበቃቸው ።እነ አቶ ስብሃት ነጋ ሳይቀር “ እንደ አያቶቻችሁ አርቀን እንቀብራችኋለን ” እያሉ የሚፎክሩብን፣ ከልጅነታቸው ጀምረው እየተጋቱት ባደጉት በዚህ የተዛባና የተንጋደደ ታሪክ ምክንያት ነው ። የኤርትራም ጉዳይ ከዚህ ተነጥሎ የሚታይ አይደለም ። በኦሮሚያና በሶማሌ አልያም በሌሎች ክልሎች አልፎ አልፎ የሚንጸባረቀው ስሜትም የዚህ መሰሉ ታሪክ አንድ ነፀብራቅ ነው ።ይህን መሰሉን ታሪክ ነው እንግዲህ “ ታሪክ እንደፀሃፊው ነው በሚል ወገንተኛ ስሜት ሳይሆን ፣ በሃቀኛና ሚዛናዊ መልኩ ግልፅ ይሁንና ፣ ሁላችንም እንማማርበት እያልኩ ያለሁት።
 
    ያም ሆነ ይህ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ጊዜ ከማባከንና … ለመፃፍ ከተነሳሁበት ርእሰ ጉዳይ ላለማፈንገጥ ስል፣ በእንጥልጥል ወዳቆምኩት ርእሰ ጉዳይ ልመለስ ። እንቀጥል………
 
      በኢትዮጵያና በፋሽስት ጣልያን መካከል ከተደረሱት ሶስት ስምምነቶች (190019021908) በፊትም ሆነ በኋላ ባሉት ረጅም ዓመታት ፣ ኤርትራን አሁን ባላት ቅርፅና ይዞታ ግዛቴ ናት የሚል ጥያቄ በኢትዮጵያ በኩል ስለመቅረቡ ምንም የተገኘ ማስረጃ የለም ። የፋሽስት ሰራዊት በአገራችን ላይ ያካሄደውን ሁለተኛውን ወረራ ተከትሎ በመንግስታቱ ማህበር ስብሰባ ላይ የተቃውሞ ንግግር ያስደመጡት ቀዳማዊ ሃይለስላሴም ቢሆኑ ፣ ታሪካዊ በተባለለት የዚያን ጊዜው ንግግራቸው ላይ አስረግጠው የተቃወሙት የኢትዮጵያን በግፍ መወረር ነው እንጅ ፣ የኤርትራን ለ 60 ዓመታት በጣልያን መገዛት አይደለም ። የኤርትራን መገዛት ለመቃወም ቢፈልጉ ኖሮ፣ መላዋ ኢትዮጵያ እስከምትወረር ድረስ መጠበቅ ባላስፈለጋቸው ነበር ። እንደማንኛውም ተጠቂ አካል በማንኛውም ጊዜ “ ሉዓላዊነቴ ተደፈረ ፤የሰሜኑ ግዛቴ በውጭ ሃይል ተወረረ ፤ የባህር በሬን ተነጠቅሁ” ብሎ ማወጅም በቻሉ ነበር ። ግን አላደረጉትም በመንግስታቱ ማህበር ታሪካዊ ዲስኩራቸው ላይም ስለ ኤርትራና ህዝቧ አንድም ቃል አልተነፈሱም ። ለምን……?
 
     ይህንን የተዳፈነ ታሪክ ነው ተመፃዳቂ ፖለቲከኞቻችን ፍርጥርጥ አድርገው እንዲነግሩን የምንጠይቃቸው ። ይህን የተንጋደደ ታሪክ ነው ፀሃፊዎቻችን በሰላ ብእራቸው ግልጥልጥ አድርገው እንዲከትቡልን የምንሻው ። ምክንያቱም በዚህ የተንጋደደ ታሪክ ምክንያት በሽዎች አልያም በመቶ ሽዎች ሳይሆን… በሚልዮን የሚቆጠሩ ልጆቻችንን ከሁለቱም ወገን አጥተናልና..!! እዚህ ላይ ቆም ልበልና…..መቼም ቢሆን ስለማይረዳኝ አንድ አንኳር ነጥብ ላንሳ..!
 
      እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ መጠን ፣ አገሬ ኢትዮጵያ በምንም አይነት የባእድ ሃይል ቅኝ እንዳልተገዛችና ፣ አውሮፓዊያን ወራሪዎችን ድባቅ መትታ በማባረር በአፍሪካ ብቸኛዋ የነፃነት ቀንዴል ለመሆን እንደበቃች እየተነገረኝ ያደግኩ ሰው ነኝ ። በእርግጥ ይህን ታሪክ እውነተኛ ታሪክ ነው ብዬ ልቀበለው ። ይሁን እንጅ ምንግዜም ቢሆን ሊገባኝ የማይችል ሌላ ታሪክ አለ ። ይሄውም የኤርትራ “ ክፍለ ሃገር ” ለ 400 አመታት ያህል በቅኝ ግዛት መላሸቅ ነው ። እንግዲህ ዋናውና እርስ በእርሱ የሚጣረሰው ነጥብ ያለው እዚህ ላይ ነው ።
 
      እውን ኤርትራ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ አካልነቷ የኢትዮጵያ ከሆነ… ለምን ይሆን ኢትዮጵያ አገራችን በምንም አይነት የባእድ ሃይል አልተገዛችም ብለን ለመመፃደቅ የምንሞክረው ???! የኤርትራ በባእድ ሃይል መገዛት እኛን አይመለከተንምን…የአንድ አካልህ መጎዳት ወይም መቁሰል… ሌላውን የሰውነት ክፍልህን አይመለከተውምን….? የቀይ ባህርንና የሁለቱንም ወደቦች የማያወላውል ኢትዮጵያዊነት ቋቅ እስኪለን ድረስ የሚነግሩን ፖለቲከኞቻችንና የታሪክ ፀሃፊዎቻችን ፣ ይህን እርስ በእርሱ የሚጣረስ ታሪክ ለምን ይሆን በግልፅ መንፈስ ሊያስረዱን የማይፈልጉት ..? የኢትዮጵያችንን በቅኝ ግዛት አለመያዝ በየሄድንበት በኩራት ስናውጅ… የኛ አካል የምንላት ኤርትራን የምንረሳት ለምን ይሆን…..? ስለዚህ በእኔ እምነት ከሁለቱ አንዱን እንምረጥ !! በኤርትራ የኢትዮጵያ አካልነት አምነን … “ ኢትዮጵያ በውጭ ሃይሎች ቅኝ ተገዝታለች’’ ብሎ አዲስ ታሪክ መፍጠር አንዱ ሲሆን….ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ የኢትዮጵያን በማንም የውጭ ሃይል አልተገዛችም ታሪክ ለማስቀጠል፣ ኤርትራን ለቀቅ ማድረግ ነው…!! እንደ እሬት ቢመረንም ምርጫው ይህና ይህ ብቻ ነው !! ከዚህ ውጭ ግን እርስ በእርሱ በተጣረሰ ታሪክ እየተጥመዘመዙ ለዘለቄታው መቀጠል ከቶውንም አይቻለንም !!
 
      ከጊዜ መጥበብ አንፃር እንጅ ሌላም ብዙ…እጅግ ብዙ ጥያቄዎችን መዘርዘር በተቻለ ። ይህን እርስ በርሱ የተጣረሰ ታሪክ ነው ለመጭው ትውልድ ትምህርት ይሆን ዘንድ በግልፅ እንናገረው እያልኩ ያለሁት ። ይህ ታሪክ ወደድንም ጠላንም የኛ የራሳችን ታሪክ ነው ። አዎ አሁንም ደግሜ ደጋግሜ የምናገረው ነገር ቢኖር ፣ ይህ ታሪክ የኛ የራሳችን እስከሆነ ድረስ፣ ለመጭው ትውልድና ለልጅ ልጆቻችን ሰላምና እፎይታ ስንል እንደ እሬት ቢመረንም የግድ ልንውጠው ይገባናል ። እኛ ተደናግረን…ልጆቻችንም እንዲደናገሩና ተጨባጭነት በሌለው የታሪክ አዙሪት ውስጥ ገብተው እንዲዋልሉ መፍቀድ የለብንም ።
                                                                                                                                                              &n bsp;                                                   ይቀጥላል…..
                                                                                                                                                              &n bsp;                                                መንገሻ ሊበን
ማንኛውንም አስተያየትና ነቀፌታ መላክ ለሚፈልግ ግለሰብም ሆነ ድርጅት የጸሓፊው ኢ-መይል እንሆ ፣mengesha.libenn@yahoo.com


Sport: ሞዬስ እና ሩኒ ይስማሙ ይሆን? – የማንችስተር ዩናይትድ ውስጣዊ ጉዳይ

$
0
0

David Moyes Wayne rooneyለሊቨርፑሉ አንጋፋ ተከላካይ ጄሚ ካራገር ክብር ከዛሬ ሶስት አመት በፊት የኤቨርተን ምርጥ 11 እና ሊቨርፑል ተጫውተው ነበር፡፡ ለዚያ ጨዋታ የኤቨርተንን ማሊያ የለበሱት ምርጦች ስብስብ ቡድን የሚሰለጥነው በዴቪድ ሞዬስ ነው፡፡ አሰልጣኙ ከዌይን ሩኒ ጥያቄ ቀረበላቸው፡፡ የማንቸስተር ዩናይትዱ አጥቂ በኤቨርተን ደጋፊነት ያደገ የሊቨርፑል ከተማ ተወላጅ መሆኑ ምስጢር አይደለም፡፡ ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ የኤቨርተንን ማልያ በድጋሚ ይለብስ ዘንድ እድሉን እንዲሰጡት ሞዬስን ይወተውታቸው ያዘ፡፡ ያሰበው ግን አልተሳካም፡፡ በተጨዋቹና በፕሪሚየር ሊጉ ላይ እንዲጫወት የመጀመሪያውን በር በከፈቱለት አሰልጣኝ መካከል የነበረው መልካም ግንኙነት ይበልጥ ንፋስ የገባው ግን በአዲሱ የፈረንጀች ሚሊኒየም አጋማሽ ላይ በታተመው የሩኒ ግለ ታሪክ (Autobiography) መጽሐፍ ነው፡፡ ‹‹My story so far›› የተሰኘው መፅሐፍ የስነ ፅሑፍ ልምድ ባለው ፀሐፊ እርዳታ የተፃፈ የሩኒ ግለ ታሪክ ነው፡፡ ዌይን የመጽሐፉ በርካታ ገፆች ላይ ስለሞዬስ ተርኳል፡፡ በአሰልጣኙ ላይ ያለውን አሉታዊ አመለካከት የገለፀበት መንገድ ግን ሁለቱን ሰዎች እስከ ችሎት ፊት አድርሷቸዋል፡፡

‹‹ሞዬስን ለመሸሽ ስል (ኤቨርተንን ለቅቄ) ወደየትም ክለብ ለመዛወር ፍቃደኛ ነበርኩ›› ይላል ሩኒ በመጽሐፉ፡፡ ‹‹ኒውካስል ጥያቄ አቅርቦልኝ ቢሆን ኖሮ ወደዚያው ማምራቴ አይቀርም ነበር፡፡ ለእኔ (ሞዬስ) ሌሎችን ሰዎች በመጥፎ አቀራረብ በራሱ ቁጥጥር ስር ለማስገባት የሚሻ ሰው ነው፡፡ እርሱን ለማስቆጣት ወይም ለተናገረው ነገር ምላሽ  ለመስጠት አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ እኔ በማደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ደስተኛ ያልሆነና የሚበሳጭብኝ ሰው ቢኖር ሞዬስ ብቻ ነው›› ሲል ይቀጥላል፡፡

ሩኒ ይህንን በማድረጉ ብዙዎች ትችት እንጂ ሙገሳን አላጎናፀፉትም፡፡ ይልቅስ መፅሐፉ ከቁም ነገር ይልቅ አንድ ያልበሰለ ታዳጊ በሚሰነዝረው አርቲቡርቲ የተሞላ ነው በሚል ተወርፏል፡፡ መፅሐፉ ለንባብ ሲበቃ ሩኒ ገና የ20 ዓመት ወጣት ነበር፡፡ ‹‹ለሁሉም ነገር የሚደርስበት ሆኖ ሳለ ቸኩሏል›› በሚል ነገሩ የልጅ ነገር… መሆኑን ተቺዎቹ ጠቁመዋል፡፡

ሞዬስ ግን በዚህ አልተከፉም፡፡ ስኮትላንዳዊው በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያሰለጠኑትን ተጫዋች በመክሰስ የመጀመሪያ ያደረጋቸውን እርምጃ የወሰዱት በመፅሐፉ ሌላ ገፅ ላይ የሰፈረው ጉዳይ ነው፡፡ አሰልጣኙ የግል ህይወቴን ምስጢሮች የሚገልፁ መረጃዎችን ‹ሊቨርፑል ኤኮ› ለተባለው የከተማዋ ጋዜጣ ሰጥተዋል ሲል ሩኒ ወቅሷቸዋል፡፡ ሞዬስም ንቀው ሊተውት አልቻሉም፡፡ ይህ ግልፅ ስም የማጥፋት ወንጀል በመሆኑ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዘውት ሄዱ፡፡ የሞዬስን ክስ የተመለከተው ፍርድ ቤት አሰልጣኙ በተጨዋቹ ያለአግባብ መወንጀላቸውን ተመልክቶ ፈርዶላቸዋል፡፡ እንደአንዳንድ ዘገባዎች ሞዬስ በስም ማጥፋት ካሳ 500 ሺ ፓውንድ ካሳ ተከፍሏቸዋል፡፡ ገንዘቡንም ለኤቨርተን የቀድሞ ተጨዋቾች ፋውንዴሽን አበርክተውታል፡፡

ዕድሜው እየጨመረ ሲሄድ ጥፋቱ የተሰማው ሩኒ በ2010 ለሞዬስ ደውሎ ይቅርታ ጠይቋቸዋል፡፡ በመጽሐፉ ላይ እርሳቸውን በተመለከተ ያሰፈረው ተገቢ አለመሆኑንና መሳሳቱን አምኖ ይቅር እንዲሉት ተማፅኗቸዋል፡፡ ሞዬስም ይቅርታውን ተቀብለው ከኤቨርተን ጋር መስራትን ቀጠሉ፡፡

ሞዬስ ቆይቶም ቢሆን ሩኒ ይቅርታውን መጠየቁ ተጫዋቹ ዕድሜ ሲጨምር እየበሰለ ለመምጣቱ ማስረጃ መሆኑን ገልፀው እርሳቸውም ይቅር እንዳሉት በሰከነ አንደበት ለሚዲያው ነግረዋል፡፡ ሩኒ በችሎታ እያደገ ሲሄድ መመልከት በጣም እንደሚያስደስታቸው ሞዬስ በወቅቱ ተናግረዋል፡፡

በመገናኛ ብዙሃን ፊት የሚታየውን መከባበር ወደጎን ብንተወው በእውነተኛው የእግርኳስ ህይወታቸው ሞዬስ በኤቨርተን የ16 ዓመቱን ‹‹ጎረምሳ›› መቆጣጠር አስቸግሯቸው ነበር፡፡ ሩኒ ነውጠኛ ሆኖባቸው ሳለ ማንቸስተር ዩናይትድ የከፍተኛ ገንዘብ የዝውውር ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡ አጥቂውም ወደ ኦልድትራፎርድ አመራ፡፡ በአዲሱ ክለቡ ውስጥ ግን ቆፍጣና የዲሲፕሊን ሰው

ከሆኑት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር ተገናኘ፡፡ የተጨዋቹን እምቅ ብቃት የተረዱት ፈርጊ ሩኒን ፀጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛና ለውጤታማነቱ ብቻ እንዲተጋ አደረጉት፡፡

ሰር አሌክስም ቢሆኑ በሩኒ ባህሪይ አልተቸገሩም ብሎ መናገር አይቻልም፡፡ በየወቅቱ አዛውንቱን የሚያስከፋ ባህሪያት እንደነበሩት አይካድም፡፡ ሞዬስም ይህንን ያምናሉ፡፡ በ2010 ላይ የታየው ግን የፈርጉሰንን ትዕግስት እጅጉን የተፈታተነ ነበር፡፡ ወቅቱ ሩኒ ማንቸስተር ዩናይትድን እንደሚለቅ ያስታወቀበት ወቅት ነበር፡፡ ዩናይትድን ቡድኑን በታላላቅ ተጨዋቾች ለማጠናከርና ዋንጫዎችን ለማሸነፍ ያለው ተነሳሽነት ደካማ መሆኑን የገለፀው ሩኒ ይህንን ፍላጎቱን ለማሟላት ሲል ወደ ሌሎች ክለቦች ለመሻገር ማሰቡን ገለፀ፡፡ ድርጊቱ ዲሲፕሊን የአሰልጣኝነታቸው አብይ መሰረት የሆነውን የሰር አሌክስን ቆሽት አሳረረ፡፡ ደጋፊውንም አስቆጣ፡፡ ብዙ ሳይቆይ የኮንትራት ማራዘሚያና ከፍተኛ የደመወዝ ጭማሪ በማግኘቱ ሩኒ ‹‹የእግር ኳስ ህይወቴን በዩናይትድ ማጠናቀቅ እፈልጋለሁ›› የሚል መግለጫ ሰጠ፡፡ ሩኒ በደሉን ቢረሳም፣ ሰር አሌክስ እና ደጋፊዎች ቂም ቋጥረው ቀሩ፡፡

እነዚህ እውነታዎች ባሉበት የ71 ዓመቱ አሰልጣኝ የጡረታ ጊዜያቸው መድረሱን በድንገት ተናገሩ፡፡ ከዚያም ሩኒ የቀድሞ አሰልጣኙና ከሳሹ ሞዬስ ቀጣዩ የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ እንደሚሆኑ ተገለፀ፡፡

የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ በአንድ ወቅት ሩኒን እስከመክሰስ ቢደርሱም ቅሉ በመኖሪያ ቤታቸው በሚገኘው የግል ቢሯቸው ግድግዳ ላይ እስካሁንም ድረስ በኤቨርተን ማሊያ በሊድስ እና በአርሰናል ላይ የማሸነፊያ ጎሎችን ካስቆጠረ በኋላ በደስታ የሚዘለውን ሩኒ ፎቶግራፍ እንደሰቀሉ ይገኛሉ፡፡ ሞዬስ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ቁልፍ እስከመሆን የደረሰውን ተጨዋች በማፍራታቸው ኩራት ይሰማቸዋል፡፡

ሞዬስ በሩኒ መቆየት እንደሚጠቀሙ አይጠረጠርም፡፡ አሁን ጥያቄው በሁለቱ መካከል ከነበረውና እልባት ካገኘው ልዩነት ይልቅ ተጨዋቹ በኦልድ ትራፎርድ ለመቀጠል ደስተኛ አለመሆኑ ይበልጥ ወደ መውጫው በር የሚገፋው ይመስላል፡፡ የሞዬስ ሹመት ወሬ መደመጥ ሳይጀምር ሩኒ ወደሰር አሌክስ ቢሮ ሄዶ በዩናይትድ ደስተኛ ያልሆነባቸው ምክንያቶች መኖራቸውንና የተጨዋችነት ህይወቱን በሌላ ክለብ መቀጠሉ የተሻለ መሆኑን እንደሚያምንበት ነግሯቸዋል፡፡ አሰልጣኙም ወደ ሌላ ክለብ የመዛወሩ ነገር የሚወሰነው በክለቡ ፍላጎት እንጂ በእርሱ ውሳኔ እንዳልሆነ አስረድተውታል፡፡ ሩኒ በመጭውም የውድድር ዘመን የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሆኖ እንዲቀጥል ለመገናኛ ብዙሃን ከተናገሩ ሰነባብተዋል፡፡

የእንግሊዙ ሻምፒዮን ሩኒን እንደማይረባ ዕቃ የሚጥል ሞኝ አይደለም፡፡ 197 ጎሎችን ያስቆጠረውና በምንጊዜም የክለቡ ታሪካዊ ጎል አስቆጣሪዎች ተርታ አራተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው፣ ዘንድሮም 31 ጊዜያት በቋሚነት እንዲሁም ሰባት ጊዜ በተጠባባቂነት ተሰልፎ 16 ጎሎችን ያስቆጠረው አጥቂ ጠቃሚ መሆኑን ያውቃል፡፡ ፈርጉሰን ያመፀባቸውን ተጨዋች የማሰናበት ታሪክ ቢኖራቸውም በሩኒ ላይ ጨክነው አላደረጉትም፡፡ ዘንድሮ የሩኒ ጠቃሚነት በአንፃራዊነት ቀደም ካሉት ዓመታት መቀነሱ አይካድም፡፡ ዘንድሮ ሩኒ በሁሉም ውድድሮች 36 ጨዋታዎች ላይ ብቻ ተሳትፏል፡፡ በዘጠኝ ዓመቱ የኦልድትራፎርድ ቆይታው ዝቅተኛ ጨዋታ የተጫወተበት የውድድር ዘመን መሆኑን ነው፡፡ ከፕሪሚየር ሊጉ ስድስት ሃያላን ጋር በተደረጉት ጨዋታዎች ማስቆጠር የቻለው ሁለት ጎሎችን ብቻ ነው፡፡ አምስት ጊዜ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡ ዩናይትድ ባደረጋቸው ስድስት የቻምፒየንስ ሊግ ግጥሚያዎች አንድ ጎል ብቻ (በብራጋ ላይ) ቀንቶታል፡፡ አምና በ44 ጨዋታዎች 34 ጎሎችን ላገባ ተጨዋች ይህ የሚያመረቃ ነው ሊባል አይችልም፡፡ ከጎን ርቆ የተጫወተባቸው ጨዋታዎች በርካታ መሆናቸው በምክንያትነት ቢቀርብ እንኳን የሩኒ የአማካይነት ተፅዕኖ እጅግ የፈዘዘ ነበር፡፡

የልቀቁኝ ጥያቄውን ካቀረበበት ከኦክቶበር 2010 በኋላ በአሰልጣኙ እና በተጨዋቹ መካከል ያለው ግንኙነት ከመጋረጃ ጀርባ ሻክሯል፡፡ ፈርጉሰንም የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋች ሆኖ እንዲቀጥል ፍላጎት ያላቸው አይመስሉም ነበር፡፡ ዘንድሮም የሩኒ ቦታ በሺንጂካጋዋ ብቃት አደጋ እንደተደነቀረበት ለመገናኛ ብዙሃን ሲናገሩ ይደመጡ ነበር፡፡ በመጪው የውድድር ዘመንም የጃፓኑ ኢንተርናሽናል ከዚህም በላይ ብቃቱን እንደሚያጎለብት ሰር አሌክስ ተንብየውለታል፡፡ በሌላ አነጋገር ሩኒ በ2013/14 ሊጫወትበት በሚመርጠው ቦታ ላይ የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ነው፡፡

ሰር አሌክስን ቅር የሚያሰኛቸው ሌላው አብይ ርዕስ የዘንድሮው የተጫዋቹ አካላዊ ብቃት ደረጃ ነው፡፡ ሩኒ ራሱ ከቅድመ ውድድር ዘመን እረፍት በኋላ ወደ ቡድኑ ሲመለስ ክብደት መጨመሩን አምኗል፡፡ ፈርጊ የሰውነቱን ክብደት እንዲቆጣጠር አጥብቀው አዘውት ነበር፡፡ እርሳቸው ወደሚፈልጉት ደረጃ ዝቅ ሊያደርገው ግን አልቻለም፡፡ ዴቪድ ሞዬስም ይህንን የሩኒ ችግር የተገነዘቡ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ናቸው፡፡ ልጁ በኤቨርተን ሳለ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በኋላ ሳይቀር የመብላት መጥፎ ልምድ እንደነበረበትና ለቋሊማ (sausage) ያለው ፍቅር የሰውነት ክብደቱን ለመቆጣጠር የማያስችል መሆኑን ያውቁት ነበር፡፡ ሞዬስ የሩኒ የጉዲሰን ፓርክ ችግር ወደ ኦልድ ትራፎርድ ተከትሏቸው ሳይመጣ አልቀረም፡፡ ሞዬስ በአዲሱ ስራቸው ከተጨዋቹም ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ለሩኒ ችግር እልባት የማግኘት የቤት ስራ ይጠብቃቸዋል የተባለው ለዚህ ነው፡፡

የአካላዊ ብቃቱን ጉዳይ ደጋግመው በምክንያትነት ሲያነሱ የተደመጡት ፈርጉሰን ሮቢን ቫን ፔርሲን የመሰለ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በያዘው የዘንድሮ ቡድናቸው ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች እያሰለፉት ታይተዋል፡፡ በጥልቀት ወደኋላ በተሳበ የመሀል አማካይነት ቦታ ሳይቀር እንዲጫወት መደረጉ ሩኒን አስከፍቶታል፡፡ በኦልድ ትራፎርድ የቻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ከሪያል ማድሪድ ጋር ሲጫወቱ ተጠባባቂ በማድረግ በሩኒ ሁኔታ ደስተኛ አለመሆናቸውን ለዓለም አሳይተዋል፡፡

ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት ‹‹ልቀቁኝ ወደ ፈለግኩበት ልዛወር›› በሚለው ጥያቄ እንደ ፈርጉሰን ሁሉ የተከፉት የዩናይትድ ደጋፊዎች ቡድናቸው ሩኒን ይዞ እንዲቀጥል አይፈልጉም መባሉ የተጨዋቹን መውጫ የሚያፋጥነው ይመስላል፡፡ ዴይሊ ኤክስፕረስ የተባለው ጋዜጣ ባሳለፍነው ሳምንት እንደዘገበው Red cafe.net በተሰኘው የዩናይትድ ደጋፊዎች የኢንተርኔት መድረክ ላይ ይኸው ፍላጎታቸው በግልፅ ተስተውሏል፡፡ በመድረኩ ላይ የሩኒ ጉዳይ 1.1 ሚሊዮን አንባቢ ያገኘ ሲሆን 10 ሺ ገደማ አስተያየቶች ሰፍረውበታል፡፡ ከተጠቀሱት አስተያየቶች መካከል ሚዛን የሚደፉት ደጋፊዎች በተጨዋቹ ሁኔታ ደስተኛ አለመሆናቸውንና አዲሱ አሰልጣኝም እንዲሸጡት እንደሚፈልጉ የሚገልፁት ናቸው፡፡ ‹‹ዩናይትድ ሩኒን ሊያሰናብት ይገባዋል፡፡ ሩኒን የመሰለ እንደ ልቤ ካልሆንኩ የሚል ተጨዋች አያስፈልገንም፡፡ ከዚህ በኋላም እጅግ ተፈላጊው ተጨዋቻችን አይደለም›› ሲል አንደኛው ደጋፊ ፅፏል፡፡ ሌላኛውም ‹‹ሩኒ እንዲለቅ እመኛለሁ፡፡ በቃ ትክክለኛው ውሳኔ ይኸው ይመስለኛል›› ብሏል፡፡ ‹‹ቫን ፔርሲና ካጋዋን የመሳሰሉ ምርጥ ተጨዋቾች አሉን፡፡ ቢለቅ እርሱ እንጂ፣ እኛ አንፀፀትም፡፡ ከዚህ በኋላ የተለየ ተጨዋች አይደለም›› የሚለው ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ነው፡፡ ሩኒ ዘንድሮ ከተጫወተባቸው ጨዋታዎች በግማሽ ያህሉ ለደጋፊዎች ሳያጨበጭብ መውጣቱም እንደ ቂም ተይዞበታል፡፡

‹‹የተለየ ተጨዋች›› ለማምጣት የክለቡ ጥረት መቀጠሉ ደግሞ የሩኒን ተፈላጊነት ይበልጥ ሊቀንሰው ይችላል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት ቺፍ ኤግዜኪዩቲቭ ዴቪድ ዢል ‹‹ሱፐር ኤጀንት›› በሚል ቅጽል የሚታወቁትን ሆርጌ ሜንዴዝን ለማነጋገር ወደ ማድሪድ ተጉዘው ነበር፡፡ የጉዟቸው ዓላማ በ2009 በዓለም የተጫዋቾች ዝውውር ሪከርድ ዋጋ (80 ሚሊዮን ፓውንድ)  የሸጡትን ክሪስቲያኖ ሮናልዶን መልሶ ማስፈረም ነው፡፡ የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ የመመለስ ፍላጎት እንዳለው በስፋት ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ ፈርጉሰንም የሂሳቡ ጉዳይ ውድነት ካላገዳቸው በስተቀር ፖርቹጋላዊውን ተመልሶ ለቀድሞ ክለቡ እንዲጫወት የማድረግ ፍላጎት ለመኖሩ ጥቆማ ሰጥተዋል፡፡ የአሰልጣኙን የጡረታ ስንብት ዜና ተከትሎ በትዊተር ገፁ ላይ ‹‹ስለ ሁሉ ነገር አመሰግናለሁ አለቃዬ›› የሚል አስተያየቱን ያሰፈረው ሮናልዶ ከተሰናባቹ አሰልጣኝ ጋር ያለው ግንኙነት አባታዊና እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ፈርጉሰን ቢለቁም ሮናልዶ በዩናይትድ ማልያ በድጋሚ ለመጫወት ያለው ፍላጎት ይቀዘቅዛል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ፈርጉሰን በዕለት ተዕለት ስራ በማይጠምዳቸው የክብር ባለስልጣንነት ቦታ ስለሚያገኙ ለተጨዋቹ መመለስም የጎላ አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ፡፡

የሮናልዶ ‹‹መመለስ›› ሩኒ በክለቡ እንዲቆይ ሊያማልለው ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡ ለሪያል ማድሪድ 200ኛ ጎሉን ያስቆጠረው ክሪስቲያኖ ከሩኒ ጋር የፈጠሩት የሜዳ ላይ ቅንጅት ዩናይትድን ለበርካታ ክብሮች እንዳበቃው አይዘነጋም፡፡ የሮናልዶ መምጣት ግን ዘንድሮ በአንድ ቦታ ባልረጋ ሚና በአጥቂ፣ በአማካይ፣ በአጥቂ አማካይና በክንፍ ተጨዋችነት የተጫወተውን ሩኒ ከቡድኑ ቁልፍ ባለተፅዕኖነት ምን ያህል ዝቅ እንደሚያደርገው ገምቱ፡፡

ዩናይትድ ሩኒን እንደማይሸጥ ያለውን አቋም አልቀየረም፡፡ ከሰሞኑ እንኳ የክለቡ ቃል አቀባይ ‹‹ሩኒ አይሸጥም›› የሚል አስተያየት በመስጠት አቋማቸውን አጠናክረዋል፡፡ የተጨዋቹን የመልቀቅ ፍላጎት ተከትለው ለግዢ በኦልድ ትራፎርድ አናት ላይ የሚሽከረከሩ ‹‹ጭልፊቶች›› በርካቶች ናቸው፡፡ ቼልሲ፣ ባየር ሙኒክና ፓሪ-ሰን-ዠርመ ከፈላጊዎቹ ተርታ ተቀምጠዋል፡፡ ሩኒ ከተሸጠ ዩናይትድ ቢያንስ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ያገኛል ተብሎ ተገምቷል፡፡ ገንዘቡንም እንደ ሮበርት ሊቫንዶቭስኪ ወይም ራዳሜል ፋልካኦን የመሰሉ አጥቂዎችን ለማስፈረም የግዢ አቅሙን ያሳድግለታል፡፡ መጪዎቹ ወራትም ለሩኒ ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ ይሰጡናል፡፡ መልሱ ‹‹እሺ›› ከሆነ ዩናይትድ ለፕሪሚየር ሊጉ ተፎካካሪዎች ይሸጠዋል ብሎ ማሰብ ስለማይቻል የሩኒ መጨረሻ ከፕሪሚየር ሊጉ ውጪ ሊሆን ይችላል፡፡ የጥያቄው ምላሽ ‹‹እምቢ›› ከሆነ ደግሞ ዌይን ሩኒ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነቱ የመጀመሪያ አሰልጠኙ ከሆኑት ሞዬስ ጋር ተስማምቶ ከሚደቅንባቸው ፈተና ይልቅ ሊጠናቀቅ ሁለት ዓመት ብቻ የቀረውን ኮንትራት በማራዘሙ ላይ የሚጋረጡትን ጥያቄዎች መመለሱ ከባድ ሊሆንባቸው ይችላል፡፡ ሩኒ በ2010 ያራዘመው ውል በሳምንት እስከ 250 ሺ ፓውንድ ደመወዝ የሚያስገኝለት መሆኑ በስፋት ይነገራል፡፡ (ክለቡ ትክክለኛውን የደመወዝ መጠን በይፋ ባይገልፅም) 30 ዓመት ሊሞላው ገና ሶስት ዓመት የሚቀረውን ኢንተርናሽናል ተጨዋች ኮንትራት ማራዘም ደግሞ የደመወዝ ጭማሪን ያስከትላል፡፡ የሞዬስ ማንቸስተር ዩናይትድ ብቃቱ ላሽቆለቆለው ተጨዋች ከዚህ በላይ ለመክፈል ይስማማ ይሆን? ሞዬስ ምላሹን ለመስጠት በጥሞና ማሰብ ይኖርባቸዋል፡፡S

የነመላኩ ፈንታን የሙስና ጉዳይ ከማጣራት ቢላደንን ማግኘት ይቀል ነበር ማለት ነው?

$
0
0

(ከአዘጋጁ፡ ይህ ጽሁፍ በኢሜይል የደረሰን ነው፤ ጽሁፉ ጸሐፊውን አይገልጽም። ለሀገር ቤት ኢሜይል ያደረገልልንን ሰው የጸሀፊውን ስም እንዲነግረን ብንመይልለትም ከዛ በኋላ ምላሽ አልሰጠንም። ለማንኛውም ያንብቡት።)

Woyyane
የኢትዮጵያ ታሪክ መቼም አያልቅም፡፡ ታዲያ በዚህ በማያልቀው ታሪክ ውስጥ በጣም ብዙ የሰማሁች ታሪክ ቢኖር በኢህአዴግ ዘመን ነው ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ ኢህአዴግ ስልጣን ከጨበጠ 22 አመት ሞልቶታል፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት ላይ “ትልቅ ሙስና” ብሎ ታላላቅ ባለስልጣናትን ወደ ማረሚያ ቤት አወረደ፡፡ መቼም ይህንን በማድረጉ ኢህአዴግ “ዴሞክራት ነው” የዚህ አይነት እርምጃ የሚወስድ መንግስት የለም ሊባል ይቻላል፡፡ ግን የኢህአዴግ የሙስና ጉዳይ ልክ እንደ ቼዝ እየዘገየ የሚደረግ ነገር ነው፡፡ በአለማችን ረጅም ጊዜያት የሚቆይ ጨዋታ ቢኖር ቼዝ ነው፡፡ የአለማችን የቼዝ ሻምፒዮን ሩሲያዊው ሰው ለሰባት አመት በቆየ የቼዝ ጨዋታ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ታዲያ ከዚህ ቀደም በ1987 ዓ.ም. የቀድሞ ታምራት ላይኔ ከሙስና ጋር በተያያዘ ወደ ዘብጥያ ወረዱ፡፡ ከሰባት አመት በኋላ ደግሞ በ1994 ዓ.ም. ላይ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትሮችና ስዬ አብርሃ ከቤተሰባቸው ጋርና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ወህኒ ወረዱ፡፡ ይህ ሲሆን መቼም ያልተገረመና ያልተደነቀ ሰው የለም፡፡ ይሁንና ታዲያ ከአስር አመት በኋላ ግን ዳግም የሙስናን ጉዳይ ሰማን ወይም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከሙስና ጋር መታሰራቸው ነበር፡፡
በርካቶች የኢህአዴግ ጠንካራ እርምጃ በሙስና ላይ ወሰደ ሊሉ ይችላሉ፡፡ከሙስና ጋር በተያያዘ ግን የታሰረው ወገን ስንናገር “ይሄ ቼዝ አውራዎቹንና ዋናዎቹን” ብለን እንድናስብ ያደርገናል፡፡ ከሁሉ ከሁሉ ግን የገረመኝና ያስደነቀኝ ነገር ቢኖር እነዚህ ሰዎች ከሙስና ጋር በተያያዘ ወደ ወህኒ ከወረዱ በኋላ የፀረ ሙስና ኮሚሽነሩ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርበው ያሉት ነገር ነው፡፡ “ይህ ጉዳይ ጠ/ሚ መለስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ከአንድ አመት ከስምንት ወር በፊት የተጀመረ ነገር መሆኑን” ገለፁ፡፡ በዚህን ያህል ጊዜ ውስጥ ደግሞ እርምጃዎች ያልተወሰዱት ጠ/ሚ መለስ ተረጋግታችሁ በስህተት ሰውን እንዳታገላቱ ብለው በማለታቸው እንደሆነ ተናገሩ፡፡
ይህ የእሣቸው አነጋገር ግን አንድ ነገር በአእምሮዬ ውስጥ እንዳስብ አደርገኝ፡፡ ሙስኛን ወይስ አሸባሪን መያዝ ይከብዳል የሚል፡፡ መቼም ሙስናን የሚፈፅምን ሰው በርግጠኝነት በሕብረተሰቡ ዘንድ መረጃ ከተገኘበት ቀላል ነገር ነው፡፡ የሽብር ተግባር የሚፈፅምን ሰው መያዝ ግን በአሁን ሰአት እንኳን ለኛ ለአሜሪካ የከበደና አሜሪካንን ሆድ ያስባሰው ቢላደን እንኳን ከስንት አመት በኋላ እንደተገኘና እንደሞተ የምናውቀው ነገር ነው፡፡ ታዲያ አሁን ምን ታዘብን ብትሉ ከሽብርተኛ ሙስና በለጠ የሚለውን ነገር ነው፡፡ ይህንን ነገር ደግሞ በምንም ሣይሆን ከባለፈው የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሊቀመንበር የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መግለጫ ማወቅ የምንችለው ነገር ሆኗል፡፡ ታዲያ ምናልባትም እሣቸው አንድ የገለፁት ነገር አለ፡፡ ይህ ነገር ወይም ክትትሉ የተጀመረው ጠ/ሚ መለስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት መሆኑንና በፍጥነት ሄዳችሁ ሰው ማጉላላት የላባችሁም ማለታቸውን ገለፀ፡፡ ስለጠ/ሚ መለስ ራእይ ምናልባትም ተራው ለመናገር የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ከሽብርተኛና ከሙስኛ የትኛውን ወገን መያዝ ወይም በፍጥነት ማወቅ ይቻላል የሚለውን እናስብ ይህንን ነገር ስናስብ ደግሞ ጉዳዩን የምንመለከተው ከሰብአዊ ወይም ከምርመራና ከውሣኔ አንፃር ሊሆን ይችላል፡፡ መቼም ኢትዮጵያ እንግዳ ተቀባይ ሀገር ናትና ከአሜሪካ ጀምረን ወደኛ እንመለስ፡፡
ባራክ ኦባማና ኦሳማ ቢላደን
በ2000 ወይም በፈረንጆቹ ሚሊኒየም በአሜሪካ የደረሰው ነገር መቼም ለመላው አለም ይዞት የመጣው ነገር ጥሩ አይደለም፡፡ በአሜሪካን የሽብር ጥቃት ደረሰ በርካታ ሰዎችም ሕይወታቸው አለፈ፡፡ አሜሪካ የምትታወቅበት የኒውዮርክ መንታ ህንፃዎች ሣይቀር የዚህ ጥቃት ሰለባ ሆኑ፡፡ አለም ሽብርተኝነት የሚለውን ትርጉም ወይም “አሸባሪ” የሚለውን ነገር ያወቀው በዚህ ጊዜ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ይሁንና ግን ታዲያ ይህንን የሽብር ተግባር ማን ፈፀመው የሚለው ነገር ሲነሣ “ኦሣማ ቢላደን” መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ ከሽብርተኝነትም በላይ የድፍረትም ያህል የቆጠረችው አሜሪካ ከሁልጊዜ ሸሪኳ እንግሊዝ ጋር በመሆን አልቃይዳ ይገኘበታል ያላቸውን አፍጋኒስታን ላይ ጥቃት ለማሰንዘር “በተባበሩት መንግስታት ድርጅት” ተ.መ.ድ አማካይነት ዘመቻ ጀመረች፡፡ ይህ ሁኔታ ሁሉም ዜጋ የሞተበትና የተፈፀመው የሽብር ጥቃት ከዚህ ቀደም የማይታወቅ በመሆኑ ድምፀ ተአቅቦ ማድረግ ሽብርተኝነትን ማበረታታት በመምሰሉ ውሣኔው ፀደቀ፡፡ ይሁንና የአሜሪካና እንግሊዝ ጦር ወደ አፍጋኒስታን ዘልቆ ገባ፡፡
የታሊባን ኃይሎች ወይም ለአልቃይዳ ቦታ ሰጡ የተባሉት ኃይሎች እየተሸነፉ ጭምር የተባበሩት ኃይሎች ድል እያገኙ መጡ፡፡ ግን ይህ ድል ለአሜሪካ አንጀት የሚያርስ አይደለም፡፡ ለአሜሪካዊያንም ሆነ ለሌሎች ወገኖች ደስታው ይህን የሽብር ጥቃት በመንደፍ የአሜሪካ መለያ የነበሩትን መንታ ፎቆች ሣይቀር ያወደመውን አሸባሪው ኦሳማ ቢላደንን መያዝ ነበር፡፡ ይህ ግን አልሆነም፡፡ በአፍጋኒስታን ታሊባን ወርዶ የሽግግር መንግስት ቢቋቋምም ቢላደን አለመገኘቱ የኪሳራ ያህል ነበር፡፡ የሪፖብሊካኑ የጆርጅ ቡሽ አስተዳደር በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ጥሮ ምንም ሣይሣካ ወረደ፡፡ ከዛ በመቀጠል የኦባማ አስተዳደር ተተካ፡፡ ይሁንና ኦባማ ሙሉ ትኩረታቸውን በዚህ ጉዳይ ሣያደርጉ ስራ ጀመሩ፡፡ ይሁንና ግን በ2010-11 ላይ አንድ ያልተጠበቀ ዜና ተሰማ፡፡ ይህ ዜና ደግሞ አሜሪካ ትፈልገው የነበረው አሸባሪው ኦሳማ ቢላደን መገደሉንና ይህንን ያደረገው የአሜሪካ ጦር መሆኑን ተናገሩ፡፡ የኦባማ ቃል ለአለም አስገራሚ ነበር፡፡ ምክንያቱም ኦባማ ሲገልፁ ኦሣማ ቢላደን ያለበትን ቦታ አውቆ በእሱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ የአንድ አመት ጊዜ መውሰዱን ጭምር ገልፀው ነበር፡፡ ኦሣማ የሚኖርበት ቦታ ላይ ማስረጃ /መረጃ/ ካገኘን በኋላ የዚህን ያህል አንድ አመት የቆየው እሱና ቤተሰቡ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማግኘት ስለነበረብን ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አንድ አመት መቆየቱን ግን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ሊያውም አቅም ያለው አሸባሪን በሚመለከት፡፡ ታዲያ በኛ ሀገር ባለፈው ሰሞን የፀረ ሙስና ኮሚሽነር የሆኑት አሊ ሱሌይማን ሲገልፁ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሆኑት አቶ መላኩ ፈንታና ምክትላቸው የሆኑት ሰዎችን ለመያዝ አንድ አመት ከስምንት ወር መፍጀቱን ገልፀዋል፡፡ ይህ ስራ የተጀመረው ጠ/ሚመለስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት መሆኑንና መለስም ዝም ብላችሁ የራሣችሁን ነገር አታድርጉ በጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ ማለታቸውን ገልፀዋል፡፡
ምናልባትም የእሣቸው ጉዳይን ከመለስ ጋር ማያያዝ ምናልባት ከውለታ ጋር እናገናኝ፡፡እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሙስና ተግባራት ይከናወናል ተብሎ ከሚጠበቅባቸው ተቋማት መካከል የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ነው፡፡ በየአመቱ የየሀገራችን የሙስና ጉዳይ የሚመረምረው ተቋም የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ባለፉት አስር አመታት ውስጥ ሙስና የተፈፀመበትና ከባድ ምዝበራ የሚከናወነው የገቢዎችና ጉምሩክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ይህ ነገር ደግሞ መቼም በስልጣን ላይ ለሚገኘው መንግስት የማንቂያ ደውል ሊሆን ይችላል፡፡ በዛው መጠን መለስ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መ/ቤት ላይ ትኩረት አደረጉ፡፡ ታዲያ የአለም ባንክ ሪፖርት ግን አስር አመት ነው፡፡ አሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት መላኩ ፈንታና “ግብረ አበሮቻቸው” ሣይሆን የስራ ባለደረቦቻቸው ከተሾሙ ደግሞ ገና ሦስት አመታቸው ነው፡፡
ይህ ጉዳይ በፍርድ ላይ የተያዘ ነው፡፡ ምናልባት የፍርድ ሂደቱን ተከትሎ ብዙ ነገር ማለት ቢቻልም ስናየውና ስንገነዘበው ገና ውሣኔያቸው አልታወቀም፡፡ በኢትዮጵያ ወይም በኢህአዴግ አሠራር ከሆነ ግን አሜሪካ ወይም ኦባማ መኖሪያውን አረጋግጠው ከያዙት ቢላደን ይልቅ ጠ/ሚ መለስ ጀምረው የእሣቸው ሕይወት ካለፈ ወይም በሕይወት ጀምረውት አንድ አመት ከስምንት ወር የፈጁት መላኩ ፈንታ በለጡ ማለት ነው፡፡ ይህ ነገር መቼም በጣም የሚገምር ይሆናል፡፡ ምክንያቱም አሜሪካ በየአመቱ ከምታወጣውና ለሌሎች ሀገሮች የምትረዳው የሽብር ጉዳይን ለመከላከል ይህ ሆኖ እንኳን በቅርቡ በቦስተን ማራቶን የሽብር ጥቃት ደርሷል፡፡ሙስና ደግሞ ቀላል ነገር ነው፡፡ ሙሰኛው ሰው ላይ ለቀናት የሚደረግ ትኩረት ግለሰቡን ያጋልጣል፡፡ ሌለው ቢቀር አካውንቱን በማስመርመር ብዙ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡ ታዲያ አሁን የገቢዎችና ጉምሩክ ሰዎች መታሰርን ከዛም ይህን እርምጃ ለመውሰድ የፈጀውን አንድ አመት ከስምንት ወር ስናስብና አንድ አመት የፈጀውን የቢላደን መኖሪያን ስንጨምርበት የትኛው በለጠ ብለን እንድስብ ያደርገናል፡፡ ገና ያደረጉት ነገር ያልተረጋገጠው ክስ የተመሠረተባቸው እነ መላኩ ፈንታን ጉዳይ ለማወቅና ለማግኘት ኦባማ ካደረጉት የቢላደን ዘመቻ በለጠ ማለት ነው፡፡

Sport: ቀነኒሳ በቀለ ያሸነፈበትን ሙሉውን የሩጫ ቪድዮ ይመልከቱ

እኛ ያልነው ለፉገራ… ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

$
0
0
The Nile River has become a point of contention between Egypt and Ethiopia.

The Nile River

በሰሞኑ ቀልድ ልጀምር። የአፍሪካ ህብረት ድርጅት 50ኛ አመቱን በያዝነው ሳምንት በአዲስ አበባ ሲያከብር በነበረው የሻምፓኝ ስነ-ስርዓት ላይ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ብቻ ከመሪዎቹ ተነጥለው ያለ ብርጭቆ ቆመዋል። ለፕሮቶኮል እንዲመሳሰሉ ቢጠየቁ አሻፈረኝ አሉ። የህብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበር ስለነበሩ ለይሰሙላ እንኳን ብርጭቆዋን ጨብጡ ቢባሉ አይሆንም፣ ሃይማኖቴ አይፈቅድም አሉ። በመጨረሻ ግን በረከት ስምዖን በጆሯቸው አንዳች ነገር ነገራቸውና የያዘውን ብርጭቆ ሲሰጣቸው ተቀብለው በደስታ ጨለጡት።

በረከት ለጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ በጆሯቸው እንዲህ ነበር ያላቸው። “ብርጭቆ ውስጥ ያለው መለስ የጀመረው ወይን ነው።”

አሁን አሁን መቀለጃ እየሆኑ የመጡት ሃይለማርያም ደሳለኝ፤ መለስ የጀመረውን ሁሉ፤ ፉገራም ቢሆን – ያንን ለመጨረስ ነው የተቀመጥኩት ይሉናል። እየደጋገሙ!

***

ብርኖ በምትባል የቼክ ሪፐብሊክ ትንሽ ከተማ ከነበርኩበት ሆቴል ውሰጥ የተሰቀለ ቲቪ ካለወትሮው የ’ሕዳሴውን’ ግድብ የሚያሳይ ምስል ይዞ ብቅ አለ። የምሽት ዜና ትንተና መሆኑ ነው። በቼክ ቋንቋ ይተላለፍ የነበረው የዜና ትንተና ባይገባኝም ከምስሉ የመልእክቱን ይዘት ለመረዳት አላስቸገርኝም።

ግን ምን አዲስ ነገር ተገኘ?

የቲቪውን ጣቢያ መቀያየር ጀመርኩ። ሲ.ኤን.ኤን፣ ቢ.ቢ.ሲ.፣ አል ጃዚራ…ቪ.ኦ.ኤ.። የኳታሩ አል ጃዚራ ጉዳዩን በስፋት ይዞታል። Death on the Nile (በአባይ ላይ ግድያ) በሚለው አምዱ ምሁራንን እና ባለስልጣናትን እያቀረበ ስለ ‘ሕዳሴው’ ግድብ ያወያያል። በአሜሪካን መንግስት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የግብጹ ሱኒ ‘አል ጋማ አል ኢስላሚያ’ ድርጅት ደግሞ ኢትዮጵያን በጦር ለመውጋት ዝግጁ መሆኑን ባለፈው ረቡዕ አውጇል።

ሂደቱ እንደገና ሌላ ጥያቄ አጫረብኝ። የግድቡ ወሬም ሆነ ስራ ከተጀመረ ሁለት አመት ሊሞላው ነው። ዓለም አቀፉ ሜዲያና ዘራፍ ማለት የጀመሩት ቡድኖች ዛሬ ያባነናቸው ምስጢር ምንድነው? አመቱን ሙሉ የት ነበሩ? መልሱን የምናውቀው እኛ ባለቤቶቹ ብቻ ነን። በእርግጥ አቶ መለስ የአባይ ካርድን ይዘው ይጫወቱት የነበረውን ጨዋታ ግብጾች ጠንቅቀው ያውቁት ኖሮ የ’ሕዳሴው’ን ሽርጉድ ከቁብ አልቆጠሩትም ነበር።

ከሁሉም ነገር እንግዳ የሚሆነው፣ በየመገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ አስተየት የሚሰጡ የፈረንጅ ‘ምሁራን’ ጉዳይ ብቻ ነው። እነዚህ ተመራማሪዎች ስለ አባይ፣ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ…ወዘተ ሊቅ ሆነው የተሳሳተ ግምታቸውን እያቀረቡ ሌላውንም ግራ ያጋቡታል። ስለ ግድቡ በአልጃዚራ አስተያየት ትሰጥ የነበረችዋ ኤክስፐርትም ሂደቱን ‘ብቀላ’ እንደሆነ ገልጻዋለች። ሌላውም እንዲሁ ‘የሕዳሴው ግድብ’ ጦርነት እንደሆነ ገልጿል። የአካባቢ ጥበቃ፣ ኤኮሎጂ… ወዘተ ችግር ያስከትላል የሚሉም አሉ። ሁሉም አስተያየቶች ግን ከኛ ከሃገሬው አመለካከት የራቁና ከመላምት ያለፉ አይደሉም። እውነታው ሌላ ነው። ፉገራ እና ፉከራ!

በደርግ ጊዜ ነው። መንገድ ላይ ቆሞ አላፊ አግዳሚውን ‘የሚቀፍል’ አንድ ወጣት ነበር። በዚህ ሰው የፖለቲካ ‘ፉገራ’ ፈገግ የሚሉም ሳንቲም ጣል ያደርጉለታል። አነድ ቀን ‘ኢሰፓኮ፣ ባዶ ባኮ! ‘ እያለ ሲቀልድ ካድሬዎች አይን ውስጥ እንደገባ ነቃና ማምለጫ ዘዴ ፈጠረ። መንጌን ማወደስ። ‘የሰው ጥራቱ፣ እንደ መንግስቱ!…’ እያለ ከተማውን አቀለጠው። ይህ ዘዴው ከተደገሰለት ሞት ቢያስተርፈውም፣ ከእስር ግን አላስመለጠውም። የማታ ማታ በሚሊሽያዎች ተይዞ ታሰረ። እዚያው ሆኖ እነዲህ አለ። ‘እኛ ያልነው ለፉገራ እነሱ ግን ለመግደል ሙከራ።’

የነጻ ትግል ስፖርት የሚሰሩ አትሌቶች ተመልካቾቻቸውን አልፎ አልፎ ‘Be smart. Don’t try this at home’ ሲሉ ይመክራሉ። ‘አስተውሉ! ይህንን ነገር እቤታችሁ አትሞክሩ።’ እንደማለት ነው። በቦክስ ሪንግ ውስጥ የሚያደረገው መዝለል፣ መውደቅ እና መነሳት ሁሉ ቀድመው ተለማምደው የሰሩት አክሽን መሆኑን ነው የሚናገሩት። እነዚህ አትሌቶች ለመኖር ሲሉ የሚሰሩት ድራማ እንጂ፣ የሚታየው ድብድብ ሁሉ የ’ፉገራ’ መሆኑን ነው በማስታወቂያቸው የሚናገሩት። በግልጽ ባይሉትም። እንዲህ አይነቱ ጨዋታ ጥበብን ስለሚጠይቅ ማየት እንጂ መሞከሩ አደጋ ያመጣል።

አቶ መለስ ‘Be smart. Don’t try this at home.’ ሳይሉ ማለፋቸው ይመስላል እነ ሃይለማርያም ዛሬ ማኖ እየነኩ ያሉት። ‘መለስ የጀመረውን ለመጨረስ ቃል ገብቻለሁ።’ አይደል እያሉን ያሉት?

ባለፈው ማክሰኞ የአባይ ወንዝ አቅጣጫ መቀልበስ ስራ በኢቲቪ የቀጥታ ስርጭት መታየት ሲጀምር ነው ጫጫታው በዓለም አቀፍ ሜዲያ የተከተለው። እስከዚህች ቀን ድረስ ግን ኢቲቪ ይቀርበው የነበረው ፕሮፓጋንዳ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማሰልቸት ያለፈ የሜዲያ ትኩረት አልሳበም ነበር። ዜጎችን በፕሮፓጋንዳ በማሰልቸት ኢቲቪ በእውነቱ የሂትለሩን ጆሴፍ ጎብልስ ሚና በደንብ ነው የተጫወተው። ጆሴፍ ጎብልስ እንዲህ ብሎ ነበር። “ውሸትን እየደጋገምክ ተናገር። በመጨረሻ ሕዝቡ እውነት ነው ብሎ ይቀበለዋል።”

የቅልበሳው ትእይንት ማክሰኞ እስከታየበት ቀን ድረስ የ’ሕዳሴው’ ግድብ ተረት-ተረት እንደሆነ ነበር እነ ግብጽ የሚያውቁት ለማለት የሚያሰቸል ክስተት ነው ያየነው። የግበጽና ሱዳን ጩኸት፣ የሌሎች ቡድኖች ማስፈራሪያ ዛቻና የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ማግኘት የጀመረውም ከዚያ በሗላ ነው። “እኛ የመሰለን ፉገራ …።” እንደማለት ነው።

ነብሳቸውን ይማረውና አቶ መለስም በህይወት ቢኖሩ ኖሮ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ጠርተው፡ “እኛ ያልነው ለፉገራ፤ እናንተ ለመገደብ ሙከራ!” ይሏቸው ነበር።

ኢትዮጵያ ከአባይ ወንዝ ከ80 እጅ በላይ ድርሻ አላት። ይህንን ያህል ለአባይ እየገበርን እሰካሁን በአባይ ወንዝ ተጠቃሚ ያለመሆናችን የሚያንገበግብ ጉዳይ ነው። አባይ ተገድቦ ለኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ቢውል የማይደሰት ሰው ቢኖር የኢትዮጵያ ጠላት በቻ ነው።

አሁን በተያዘው መልኩ አባይ ተገድቦ ስራ ላይ ይውላል ብሎ የሚያስብ ካለ ግን ልጅ ውይንም ጅል መሆን አለበት። ‘አባይ ይገደባል’ ብለው የሚከራከሩኝ ወዳጆቼ ለሃገራችን እድገት ካላቸው በጎ ምኞት ያለፈ ሌላ እውነታ እንደሌለው ነው ማስረዳቸው።

የ’ሕዳሴው’ ግድብ፤ የቱኒዥያውን ቤን አሊ፣ የግብጹን ሆስኒ ሙባረክ፣ እንዲሁም የሊቢያውን ጋዳፊ የጠራረገው የሰሜን አፍሪካው ህዝባዊ ማእበል የወለደው ሃሳብ ነው። ለችግር ጊዜ ተቀምጦ የነበረ ጆከር ነው የሳቡት። ይህ ደግሞ የወጣቱን አንደበት ከያዘው የኮብል ስቶን ፕሮጀከት ጋር በመታገዝ እነ መለስን ከማዕበሉ ጠብቋቸዋል።

የ ‘ሕዳሴው ግድብ’ ፕሮጀክት በአምስት አመቱ የ’እድገትና ትራንስፎርሜሽን’ እቅድ ውስጥም አልነበረም። እንደ እንጉዳይ ተክል ከመቅጽበት ብቅ ያለ ነገርም አይደለም። ለዘላቂ ሳይሆን ይልቁንም ላጭር ጊዜ እንደሚወሰድ የእድሜ ማራዘሚያ መድሃኒት አይነት ነው። አቶ መለስ ዜናዊ የግድቡን መሰረት ሲጥሉ 6ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨቱ ጉዳይ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችልም ጠንቅቀው ያውቁታል።

ለዚህም አንደኛው ምክንያት በ1993 (እ.ኤ.አ.) አቶ መለስ ዜናዊ ከግብጹ ሆስኒ ሙባረክ ጋር ያደረጉት ስምምነት ነው። (የሁለቱን መሪዎች ፊርማ የያዘውን ይህንን ሚስጥራዊ ስምምነት በወቅቱ ለህትመት በማብቃቴ ለማእከላዊ እስር ተዳርጌ ነበር።) በዚህ ሁለትዮሽ ውል በአንቀጽ አምስት ላይ ‘አንዱ ሃገር ሌላውን ሃገር በሚጎዳ መልኩ ውሃውን መጠቀም አይችልም።’ በማለት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን የተፈጥሮ መብት የሚገፍ ሃረግ ተቀምጧል። ይህ ዲፕሎማሲዊ አንቀጽ በህግ ቋንቋ ሲገለጽ ‘ኢትዮጵያ አነዲት ማንኪያ ውሃ ከአባይ ላይ ብትቀዳ፡ የግብጽን ተፋሰስ ሰለሚቀንስ ከዚህ ድርጊት መቆጠብ አለባት።’ እንደማለት ነው። ከኛ አልፎ ግብፅ ምድር ላይ የሚንፏለለውን ውሃ ካይሮ ተጠቀመች አልተጠቀመች እኛ ምን አገባን?

በአለም አቀፍ ህግ፣ ሁለት ሃገሮች ተስማመተው የሚያጸድቁት ሰነድ ደግሞ ሁለቱ ተስማምተው እስካላፈረሱት ድረስ ሀጋዊ ሰነድ ሆኖ ይቆያል።

አቶ በረከት ስምዖን አልጃዚራ ላይ ባለፈው አርብ ቀርበው፤ በቅኝ ግዛት ወቅት የነበረውን ሰነድ ሲያነሱ፤ የራሳቸው ስርዓት በ1993 ያፀደቀውን ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ያላትን የተፈጥሮ እና ሀጋዊ መብት አሳልፎ የሰጠውን ውል እንደዋዛ አልፈውታል። ይህ ሰነድ በቅኝ ግዛት ዘመን ከነበሩ ስምምነቶች ሁሉ የከፋና ለክርክር እንኳን የማያመች ነው።

በአባይ ወንዝ 84 በመቶ ድርሻ ያላት ኢትዮጵያን ያላሳተፉ እነዚያን የቅኝ ግዛት ውሎች ሁሉ ውድቅ ለማድረግ የህግም ሆነ የሞራል የበላይነት አለን ብዬ አምናለሁ። ግና የ1993ቱ ምስጢራዊ ሰነድ እንዴት ነው ሊፈርስ የሚችለው? ይህ ውል ሳይፈርስ እንዴትስ ነው አባይ ሊገደብ የሚችለው? ለዚህ ጥያቄ እነበረከት በእርግጠኝነት መልስ ሊስጡን አይችሉም።

በሁለተኛ ደረጃ ማየት ያለብን አባይ ዓለም አቀፍ ወንዝ መሆኑን ነው። ዓለም አቀፍ ወንዝ ደግሞ በአንድ ሃገር አዋጅ ሳይሆን፤ በዓለም አቀፍ ህግ ነው የሚመራው። የአባይ ወንዝ ለመጠቀም የላይኛውና የታችኛው ተፋሰስ ሀገሮች ሁሉ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳለባቸው ህጉ ያስገድዳል።

በሶስተኛ ደረጃ አባይን ከምር መገደብ ካስፈለገ፤ አባይን መገደቢያ ገንዘብ አይጠፋም። የህወሃቱ ኢፈረት ብቻውን አንድ አይደለም፤ አራት አባይን መገደብ የሚያስችል ገንዘብ አለው። ገዢው ፓርቲ እርግጥ ለኢትዮጵያ እድገት እና ትራንስፎርሜሽን ስኬት ካሰበ በፓርቲው ስም ያከማቸውን ገንዘብ አውጥቶ ለግድቡ ተግባር ማዋል ይችላል። የኢፈርት ህለቀመሳፍርት ገንዘብ ቢያጓጓው እንኳ በአክሲዎን ሽያጭ ገንዝብ መሰብሰብ ይችል ነበር። ለግድቡ ያስፈልጋል የሚሉን 80 ቢሊየን ብር ነው። እስካሁን ከህዝብ በውዴታም ሆነ በግዴታ ተገኘ የተባለው ደግሞ 7 ቢሊየን ብር። 73 ቢሊየኑን ታዲያ ማን ሊሞላው ይሆን? ወይንስ እንዳሁኑ አይነት ያልተጠበቁ ችግሮች ሲገጥሙ ስራውን ለማቆም እንደምክንያት ሊቀርብ?

ከውስጥ ሰዎች እንደምንሰማው ከሆነ ደግሞ እነ መሶበ ሲሚንቶ እንዲሁም የህወሃት ኮንስትራክሽን ድርጅቶች የግድቡን መሰረት በመጣል ስም ከህዝብ የተሰበሰበውን 7 ቢሊየን እየተቋደሷት ይገኛሉ። በአንድ ወንጭፍ ሁለት ወፍ .. እንዲሉ። 7 ቢሊየን ቀላል ገንዘብ አይደለም። በቅጡ ቢያዝ ኢትዮጵያን ጸብ ውስጥ የማይጨምራት እጅግ ብዙ የሚተገበር የልማት ስራ ላይ ሊውል ይችል ነበር። ኢትዮጵያ ሃይል ሊያመነጩ የሚችሉ በርካታ ትናንሽ ወንዞችም አሏት።

የ’ሕዳሴው ግድብ’ በዚህ ሂደት ተግባራዊ ይሆናል ወይ? የሚለውን ጥያቄ ምላሽ በቅርብ የምናየው ይሆናል። ለገዢው ፓርቲ ግዜ መግዣነት ስለማገልገሉ ግን ቅጥ ያጣው የፕሮፓጋንዳ ስራ ብቻ ምስክር ነው። ጫወታው ሳይገባቸው በሃገር ፍቅር ስሜት ብቻ የተሸውዱ እንዳሉ ሁሉ ሕዝቡን ባልተጨበጠ ነገር የሚያሞኙት ልማታዊ ጋዜጠኞች እና ልማታዊ አርቲስቶች ነገ ትዝብት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

በአንድ ጽሁፌ ለመዳሰስ እንደሞከርኩት በኡጋንዳ – ጂንጃ የነጭ አባይ ምንጭ የሆነው የቡጃጋሊ ግድብ ስራ ተጠናቋል። ኡጋንዳ የነጭ አባይ ምንጭ ነች። ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ የሃገሪቱን የሃይል አቅርቦት ችግር ለማቃለል የሚያስችል የነጭ አባይ ፕሮጀክት ዘርግተው ተግባራዊም አድርገዋል። ለዚያውም በአለም ባንክ እና በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ እርዳታ! ነጭ አባይ የሃገሪቱን የሃይል ምንጭ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይገመታል።

ይህ ግድብ ሲታቀድም ሆነ ሲሰራ ታዲያ በጩኸት እና በመፈክር አልነበረም። የሃገሪቱ አርቲስቶች አልዘፈኑለትም። ሕዝቡ ስለፕሮጀክቱ እንዲጮህለትም ሆነ እንዲጮህበት አልተደረገም። እነደ”ህዳሴ”ው መዋጮ ሁሉ የዜጎች ኪስ አልተበረበረም፤ ከወር ደመወዙ የተቆረጠ ነገር የለም። ቡጋጃሊ ሲገደብ ቦንድ አልተሸጠም፤ ወታደራዊ ማርሽም አልተሰማም። ሙሴቬኒ አንባገነን ቢሆኑም ለሃገራቸው እድገት ብልሃት በተሞላበት መንገድ ሄደዋል። ‘Think global, act local’ ነው ጫወታቸው። ‘ሞያ በልብ ነው’ ብለን ልንተረጉመው እንችላለን።
አባይን በፕሮፓጋንዳና በጩኸት ለመገደብ የተነሱት የኢትዮጵያ ገዢዎች ታዲያ ይህንን እያዩ እንኳን አልተማሩም። አባይ ሲቀለበስ በላይቭ ቲቪ ማሳየት ከፕሮፓጋንዳነቱ ባሻገር ምንድነው ጥቅሙ? ድርጊቱ ህልውናው በአባይ ወንዝ ላይ የሆነ ሕዝብን ለጦርነት መጋበዝ ይመስላል። ውግዘቱና ጫናው ሲበዛ ጉዳዩን ለማቆም ምክንያት ለመፍጠርም ያመቻል።
አለም አቀፉ ህብረተሰብ በ’ሕዳሴው ግድብ’ ጉዳይ ላይ ዝምታን ነው የመረጠው። ለዚህም ምክንያት አለው። ኢትዮጵያ ጨለማ ውስጥ ሆና ሌሎች ሃብትዋን ያላግባብ ሲጠቀሙ፤ ድልድሉ ትክክል እነዳልሆነ አለም ሳይረዳው ቀርቶ አይደለም። የመለስና ሙባረክ ፊርማ ሳይቀደድ የተጀመረው የአንድዮሽ ውሳኔም የት ተጀምሮ የት ላይ እንደሚያልቅ ያውቁታል። ለዚህም ይመስላል ለግድቡ የገንዘብም ሆነ የሞራል ድጋፋቸውን ሊነፍጉ የቻሉት። የግድቡ ጅማሮ አንደኛ አመት ሲከበር የመንግስት ባለስልጣናት እና የውጭ ዲፕሎማቶች የእግር ኳስ ግጥሚያ እንደሚያደርጉ ፕሮግራም ወጥቶ ነበር። ዲፕሎማቶቹ ግን በስፍራው ሳይገኙ ቀሩ። ለ’ሕዳሴው’ ግድብ እውቅና በመስጠት የፖለቲካ ስህተት ላለመስራት የመከሩ ይመስላል።

ፕራግ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፡ ግንቦት 24፣ 2005 ዓ.ም.

ቀጣዩ ታሳሪ ወይም ፈርጣጭ የፍትህ ሚ/ሩ ብርሃን ኃይሉ?

$
0
0

አቶ ብርሃን ለቃሊቲ በሮች ተቃርበዋል

Berhan Hailu በአዲስ አበባ ዛሬ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው በቅርቡ ከስልጣን የተነሱት የፍትህ ሚኒስትር አቶ ብርሃነ ኃይሉና ከአስር በላይ አቃቤ ህጐች በሙስና፣ በሽብርተኝነትና በግድያ ወንጀል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የተመሰረተን ክስ ያለአግባብ አቋርጠዋል በሚል በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ምንጮቹን ጠቅሶ ዘገበ፡ ፖሊስ በሚኒስትሩና በአቃቤ ህጐቹ ቢሮ ባካሄደው ከፍተኛ ብርበራ በርካታ መዝገቦችን ማግኘቱንና ለምርመራ መውሰዱን ምንጮች ተናግረዋል ያለው ጋዜጣው በፖሊስ ብርበራ የተገኙት መዝገቦች ያለአግባብ ተቋርጠው እንዲዘጉ የተደረጉ ክሶች ናቸው ተብሏል፡፡

ተከሳሾች ላይ በቂ ማስረጃ ማቅረብ ካልተቻለ ክሶቹን አቋርጦ መዝገቡን መዝጋት የፍትህ ሚኒስትርና የአቃቤ ህጐች ስልጣን መሆኑ ቢታወቅም ከሙስና፣ ከሽብርተኝነትና ከግድያ ጋር የተያያዙት እነዚህ በፖሊስ ብርበራ የተገኙ ከደርዘን በላይ የሆኑ መዝገቦች ግን፣ በቂ ማስረጃ እያለ፣ ያለ አግባብ የተቋረጡ ናቸው ተብሏል ያለው የጋዜጣው ዘገባ ምርመራው ተጠናቆ እንዳበቃ በሚኒስትሩና በአቃቤ ህጐቹ ላይ ክስ እንደሚመሰረትም ምንጮች ጠቁመዋል ብሏል። ለሰራተኞች አቤቱታ ምላሽ ባለመስጠትና በሥራ ድልድል በደል ፈጽመዋል በሚል ቅሬታ ይቀርብባቸው የነበሩት የፍትህ ሚኒስትሩ፤ በተለይ የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ይታያሉ የተባሉ ችግሮችን እንዲፈቱ አራት የማሳሰቢያ ደብዳቤዎች ተጽፎላቸው እንደነበር ምንጮቹን ጠቅሶ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገቧል።

በቅርቡ በተካሄደው የኢህአዴግ ዘጠነኛ ጉባኤ ላይ ከፓርቲው መሪዎችና አባላት ለሚኒስትሩ የቃል ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸው እንደነበር ጋዜጣው ጠቅሶ ፓርላማም የመ/ቤቱ በርካታ ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው ማሳሰቡን ጠቅሷል።
በዚህ ዓመት ብቻ ሶስት ሚኒስትሮች በወንጀል ተጠርጥረው ከስልጣን የወረዱ ሲሆን፣ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ከአገር መኮብለላቸው ይታወሳል፡፡ ቀጣዩ ባለሳምንት እንደጁነዲን ፈርጣጭ ወይም እንደ መላኩ ዘውዴ ቃሊቲ የፍትህ ሚ/ሩ ብርሃን ኃይሉ?

የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አስተያየት ይጠበቃል።

Breaking News: በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ አዳዲስ ጳጳሳትን ሊሾም ነው

$
0
0
አቡነ መርቆሪዮስ እና የሲኖዶሱ አባቶች  (በዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ) ፎቶ የዘ-ሐበሻ ምንጮች

አቡነ መርቆሪዮስ እና የሲኒዶሱ አባቶች
(በዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ)
ፎቶ የዘ-ሐበሻ ምንጮች

(ዘ-ሐበሻ) ለረዥም ዓመታት በገለልተኝነት ቆይቶ አሁን ወደ ስደተኛው ሲኖዶስ በተቀላቀለው የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ሲደረግ የሰነበተው የሕጋዊው ሲኖዶስ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቀቀ። ላለፉት 6 ቀናት በዳላስ ከተማ ሲደረግ በቆየው የሲኖዶሱ ጉባኤ ላይ በርከት ያሉ ጉዳዮች የተነሱና ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመት እንደሚገኝ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገቡ።

የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች የጉባኤውን ፎቶ ግራፍ ጭምር በማያያዝ እንደዘገቡት ከሆነ ለጊዜው የቁጥራቸው ብዛት የማይገለጽ ጳጳሳት ሹመት እስከ መጪው ሐምሌ ወር ድረስ ይደረጋል። ቅዱስ ሲኖዶሱ በጉባኤው ላይ በተለይ ባለፉት 6 ወራት የተሰሩ ሥራዎችን መገምገሙን ያስታወቁት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በጉባኤው ላይ ባለፉት ስድስት ወራት ቅዱስ ሲኖዶሱ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ከበፊቱ የተሻሉ ሥራዎችን መፈጸሙን፤ በገቢ ደረጃም ከፍተኛውን ገቢ እንዳስገኘ ተገልጿል ብለዋል።

በዚህ ጉባኤ ላይ በተለይ ለብጹዕ አቡነ ዮሐንስ ሹመት ተሰጥቷል ያሉት የዘ-ሐበሻ ምንጮች አቡነ ዮሐንስ የቴክሳስ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሆኑ መደረጉንም አስታውቀዋል።

አቡነ ዮሐንስ የቴክሳስ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ

አቡነ ዮሐንስ የቴክሳስ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ

በጉባኤው ላይ በቅርቡ በአማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን የማፈናቀል ተግባር አባቶቹ ማውገዛቸውን ያስታወቁት ምንጮቻችን በባህርዳር የተፈጸመውን ግድያም አባቶች አውግዘው ጸሎት እንዳደረጉላቸው ዘግበዋል።

በተለይም ባልተሳካው የሁለቱ ሲኖሶች እርቅ፤ ለእርቁ አለመሳካት ተጠያቂውን የወያኔ/ኢሕአዴግን መንግስት ተጠያቂ ያደረገው ይኸው ጉባኤ በሁለቱ ሲኖዶስ መካከል ወደ መግባባት ተደርሶ በመጨረሻው ላይ በመንግስት የተሰናከለው እርቅ ከአሁን በኋላ ሊሳካ የሚችለው ስርዓቱ ሲወድቅ ብቻ ስለሆነ ሕዝቡ ተደራጅቶ በአንድነት እንዲታገል፤ እንዲጸልይም ጥሪ አቅርበዋል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ ዛሬ ወይም ነገ ጠዋት ለሚዲያዎች እንደሚላክ ታውቋል። ዘ-ሐበሻም መግለጫው እንደደረሳት ለአንባቢዎቿ እንደምታካፍል ከወዲሁ ትገልጻለች።

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስም በተመሳሳይ ጉባኤ ተቀምጦ ነው የሰነበተው። ስብሰባው በምን መልክ ይጠናቀቅ ይህን ዜና እስከሚጠናቀቅ ባንደርስበትም ትናንት ሐራ ተዋሕዶ የተሰኘው ብሎግ ሲኖዶሱ የሚወያይባቸውን እና የማይወያይባቸውን ር ዕሶች ዘርዝሮ ነበር። ለግንዛቤዎ እንደወረደ ይኸው፦

  • ምልአተ ጉባኤው 18 የመነጋገሪያ አጀንዳዎችን ለይቶ ውይይቱን ቀጥሏል

ምልአተ ጉባኤው በዋናነት ከሚነጋገርባቸው ጉዳዮች ውስጥ፡-

  • ቤተ ክርስቲያኒቱ በመሪ ዕቅድ መመራት እንዳለባት የታመነበት በመኾኑ መሪ ዕቅዱ ‹‹ተዘጋጅቶ ሲቀርብ›› ተመርምሮ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡
  • የሕገ ቤተ ክርስቲያን እና ቃለ ዐዋዲ ማሻሻያ ረቂቆች በኮሚቴው ቀርበውና ተደምጠው ተጨማሪ ሐሳብ ይሰጥባቸዋል፤
  • በቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደርና ሙስና ችግሮች ላይ ‹‹መጠነ ሰፊ›› ውይይት ተደርጎ ውሳኔ  ይተላለፋ በጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያዎችና ድርጅቶች፣ በሁሉም አህጉረ ስብከት መዋቅሮች ሙስናን የመከላከያውና መቆጣጠርያው አግባብ ከሚያሰፍነው ጥብቅ ሥርዐት አንጻር አጀንዳው አነጋጋሪና አከራካሪ እንደሚኾን ይገመታል፡
  • የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የጠ/ቤ/ክህነት ዋና ሥ/አስኪያጅ ምርጫ ይካሄዳል በቂ የሰው ኀይልና በበጀት ተደግፎ በሦስት ዴስኮች እንዲደራጅና የራሱ ወርኃዊ መጽሔት እንዲኖረው የተወሰነለት የውጭ ግንኙነት መምሪያ አዲስ ሓላፊና ሊቀ ጳጳስ ይሾምለታል፤ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የቅድሚያ ግምት የተሰጣቸው ቢኾንም ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ይጠበቃሉ፤
  • ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌምን ጨምሮ አባቶች እንዲመደቡባቸው የሚያስፈልጉና ችግር ያለባቸው አህጉረ ስብከት ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፤ በአጀንዳው የተጠቀሱት አህጉረ ስብከት÷ የአዲስ አበባ፣ የትግራይ ማእከላዊ ዞን አክሱም፣ የሐዋሳ ቡርጂና ቦረና ብቻ ናቸው፡፡ በሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ የቅዱስ ላሊበላ ደብርና ሌሎች ወረዳዎች አስተዳደር ከሙስናና ጎጠኝነት፣ በድሬዳዋና ምዕ. ሐረርጌ፣ በምሥራቅ ጎጃም፣ በዋሽንግተን ዲሲና ካሊፎርኒያ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካከኑፋቄና ጎጠኝነት ጋራ የተያያዙ የካህናትና ምእመናን አንገብጋቢ ጥያቄዎችስ?
  • የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት አዲስ አሠራርን ተመርምሮና ተጣርቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡

ከሌሎች የምልአተ ጉባኤው አጀንዳዎች፡-

  • የቀድሞው ፓትርያሪክ ንብረትን በተመለከተ ውሳኔ መስጠት፤
  • ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ቀድሞ በሰሜን አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ) አስመልክቶ የቀረበውን ጽሑፍ በንባብ ሰምቶ መወሰን፤
  • የቀጣይ የቋሚ ሲኖዶስ አባላትን መመደብና በጽሑፍ የሚቀርቡ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የዝውውር ጥያቄዎችን መወሰን የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በምልአተ ጉባኤው አጀንዳ ያልተካተቱና ሊታዩ የሚገባቸው ወቅታዊ ጉዳዮች፡-

  • የአንድ ዓመት ጊዜ ገደብ የተሰጠው የፌዴራል ጉዳዮ ሚ/ር የሃይማኖትና እምነት ተቋማት ምዝገባ መመሪያ ረቂቅበተመለከተ ከቤተ ክርስቲያናችን አሐዳዊነት፣ ነባራዊነትና ሉዓላዊነት አኳያ የሚኖረን አቀባበል፤
  • የቅዱሳት መካናት /ገዳማትና አድባራት/ ይዞታና ክብር መጠበቅ ከመንግሥት ሰፋፊ የልማት ፕሮጀክቶች /በጣና በለስ የተቀናጀ ስኳር ልማት ፕሮጀክት፣ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት. . .አንጻር እንዲሁም የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ግልጽ ጥፋት /መዝባዕ ገዳም/
  • በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ  የትምህርት አስተዳደሩ ብቃትና አግባብነት ባላቸው ሓላፊዎችና ዲኖች እንዲመራ፣ አስተዳደሩ ከሙስናና ብልሹ አሠራር የጸዳ እንዲኾን ደቀ መዛሙር ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ ኮሚቴው /ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ሦስት፣ ከመንግሥት ሁለት አባላት የተውጣጡበት/ ያቀረበውና በዋናነት ሦስት ነጥቦችን የያዘው የመፍትሔ ሐሳብ፤ ከዚሁ ጋራ በተያያዘ የጠ/ቤተ ክህነቱ ትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ለመንፈሳዊ ኮሌጆቻችን፣ የካህናት ማሠልጠኛዎቻችንና የአብነት ት/ቤቶቻችን አመራርና ድጋፍ ለመስጠት ያለው ብቃት፤  

የኢትዮጵያውያን ሰሜን አሜሪካ ፌዴሬሽን አመራሮች በቬጋስ ተጫዋቾች ሊከሰሱ ነው

$
0
0

ፌዴሬሽኑ ተጫዋቾች አይወክለንም ባሉት ግለሰብ ስር ተመዝግበው እንዲመጡ ውሳኔ ወስኗል

<<ይሔ ችግር የፌዴሬሽናችንን ህልውና ሳያጠፋ ቦርዱ ውሳኔ እንዲሰጥ እጠይቃለሁ>> አቶ ተካበ ዘውዴ

የፌዴሬሽኑ የውድድር አስተባባሪና የቀድሞ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ

የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን አንዳንድ አመራሮች ከፌዴሬሽኑ ሕግና ደንብ ውጭ ቦርዱን ስብሰባ ሳይጠሩ ለነሱ ስልጣን ማራዘሚያ ድምጽ ለሰጡዋቸውና ከየከተማው ውክልና የሌላቸውን ግለሰቦች የቡድን መሪዎች እነሱ ካልሆኑ ተጫዋቹ ራሱ የመረጠው ተወካይ አንቀበልም በማለት ኢትዮጵያውያንን ሊያቀራርብ የተቋቋመውን ፌዴሬሽን የግል መጠቀሚያ አድርገው መብታችንን ገፈዋል ያሉ የቬጋስ የኢትዮ ስታር ፋሲለደስ አባላት ትላንት በከተማው ከፌዴሬሽኑ ተወካይ ጋር ተወያይተው መፍትሔ ባለማግኘታቸው መብታቸውን ለማስከበር ወደ ሕግ እንደሚሔዱ ከተጫዋቾቹ ተወካይ አንዱ ሲራክ ለህብር ሬዲዮ ገልጿል።

የቡድኑ አባላት ላለፉት ሁለት ዓመታት በደብዳቤ፣በስልክ ለፌዴሬሽኑ የስራ አስፈጻሚና ለቦርድ አባላት ችግሩን እንዲያውቁ ማድረጋቸውን ነገር ግን ፌዴሬሽኑ አሁንም ሊሰማቸው እንዳልፈቀደ ይህም የሆነው በስራ አስፈጻሚ ውስጥ በግል በተደራጀና የራሱን ደጋፊ ባሰባሰበ ቡድን ኢትዮጵያውያንን እየከፋፈሉ መሆናቸውን የገለጸው ወጣት ሲራክ ስብሰባው ያለ ስምምነት እንደተበተነ ለህብር በሰጠው ሰፋ ያለ ማብራሪያ አመልክቷል።

ትላንት ረቡዕ ሜይ 29 በቬጋስ ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ የፌዴሬሽኑ ተወካይ አቶ ተካበ ዘውዴ ፌዴሬሽኑ በተወካይነት የሚያውቀው አመራር ላይ ያሉትን ተወካዮች መሆኑን ተጫዋቾቹ ባሉበት ባካሄዱት ስብሰባ ጠቅሰዋል። ተጫዋቾቹ መጫወት ከፈለጉ በተወካዩ በኩል የተዘጋጀውን ፎርም ሞልተው በሱ ቡድን መሪነት ለውድድሩ ሊመጡ እንደሚገባ በስብሰባው ላይ ገልጸዋል።ችግር ካለ ወደፊት ንገሩን ብለዋል። በከተማው የሚገኝን የቀድሞ የቡድኑን መስራች አቶ ዘውዱም ስላለ እኔም አለሁ የሚገጥማችሁ ችግር የለም ብለዋል።

የቬጋስ ኢትዮ ስታር ቡድን አባላት የፌዴሬሽኑ ተወካይ በተገኘበት በቀድሞው አመራሮችና በቡድኑ አባላት መካከል ያለውን ችግር እንወያይ ሲሉ የጠየቁ ሲሆን ተወካዩ<< እኔ ይህን ለማድረግ ስልጣን አልተሰጠኝም >>ሲሉ ደጋግመው የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ወሰነ ያሉትን ውሳኔ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያውያን ሰሜን አሜሪካ ፌዴሬሽን አመራሮች በቬጋስ ተጫዋቾች ሊከሰሱ ነው<<እሱ ስልጣን ስትይዙ እጅ ስላወጣላችሁ ነገም እጅ ያወጣልናል በማለት ነው የእኛን ጥያቄ የማትመልሱት? ብቃት የለውም አይወክለንም!>> ያለ አንድ የቡድኑ አባል በፌዴሬሽኑ አመራር ተሰጠ የተባለውን ውሳኔ እንደማይቀበሉት ገልጿል። ተጨዋቾቹ አንቀበልም አይወክለንም ያሉትን ተወካይ ፌዴሬሽኑ በግድ ተቀበሉ ማለቱ አግባብ አይደለም ብሏል።ምፍትሔ የማትሰጡን ከሆነ ለምን መጣችሁ? ሲሉ በምሬት ጠይቀዋል።

ከቬጋስ ኢትዮ ስታር አባላት መካከል አንዱ ወጣት ብዙነህ አሁን ያለውን ችግር ለመፍታት አስታራቂ ያለውን ሀሳብ አቅርቧል። በዚህም አንድ ከቀድሞ ስራ አመራር አንድ ከተጫዋች ተወክሎ ቡድኑን ለዘንድሮ ወደ ዲሲ ይዘው ይሒዱ ብሏል።በዚህ ተጫዋቾቹ ስምምነት ያሳዩ ቢሆንም የፌዴሬሽኑ ውሳ ድጋፍ ያለው የቡድኑ ተወካይ በፌዴሬሽኑ ውሳኔ መሰረት መጫወት የሚፈልግ እሱ ያዘጋጀውን ፎርም እንዲሞላ ጠይቋል።አቶ ተካበም የመጡበት ውሳኔ ይሆው መሆኑን አስረድተው ከተጫዋቾቹ መፍትሄ ተብሎ የመጣውን የመወሰን ስልጣን እንደሌላቸው ገልጸዋል።

በፌዴሬሽኑ የተወሰኑ አመራሮች በተያዘ አቋም እየተበደሉ መሆኑን የሚገልጹት የቡድኑ አባላት መካከል አንዱ ለአቶ ተካበ የቡድኑ ተወካይ የሰጣችሁ ድምጽ እኮ የእኛ ድምጽ ነው? በማለት የተጫዎቹን መብት ረግጠው የሚወስኑትን ውሳኔ እንደማይቀበሉት ተናግረዋል።

<<ፌዴሬሽኑ ጊዜው ሳይሄድና አየር ትኬት ሳይወደድ ከዓመት በላይ ለቀረበለት አቤቱታ እንዴት ምላሽ አይሰጥም? >> ተብለው የተጠየቁት አቶ ተካበ ለዚህ እሳቸው መልስ እንደሌላቸው ተጫዋቾች ሲበደሉ እንደማይወዱ ነገር ግን የተጠየቀውን ምላሽ ለመስጠት ስልጣን አልተሰጠኝም ሲሉ ገልጸዋል።

በተጫዋቾቹ ገለጻ ፌዴሬሽኑ ለሁለት በተከፈለበት ወቅት የቬጋሱ ኢትዮ ስታር ቡድን ተወካይ እና የቡድኑ አባላት ከነባሩ አመራር አባላት ጋር የቆዩ ሲሆን ከዓመት በፊት የቡድኑ ተወካይ ለረጅም ጊዜ በስልጣን መቆየትን ተከትሎ ተጫዋቾች ወኪላችንን በዲሞክራሲያዊ መንገድ መርጠናል ያሉ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ከማውቀው ተወካይ ውጭ ያለውን አመራር አልቀበልም በማለቱ ተጫዋቾች በማይወክለን ሰው ወደ ዳላስ አንሔድም በማለት የቀሩ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ከውድድሩ በሁዋላ ችግራችሁን እፈታለሁ ቢልም ዛሬም ለችግሩ መፍትሄ ለምን እንዳልሰጠ በስብሰባው ላይ የተጠየቁት አቶ ተካበ ይህን እኔ አላውቅም ሲሉ ተናግረዋል።

ጉዳዩ በይቅር ባይነት እንዲፈታ በቡድኑ መካከል የተፈጠረውን ችግር ማንሳት እንደማይፈልጉ የገለጹት አቶ ተካበ ዘውዴ የሳቸው ስልጣን ያዩትንና የሰሙትን ለፌዴሬሽኑ ማቅረብ መሆኑን ገልጸዋል።

<<ይሔ ችግር ፌዴሬሽኑን ለማጥፋት የደረሰበት ደረጃ ላይ ነው።ቦርዱ መፍትሔ እንዲሰጥበት እጠይቃለሁ >> ሲሉ ለህብር ሬዲዮ ከስብሰባው በሁዋላ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ለቦርዱ ጥሪ ያቀረቡት አቶ ተካበ ዘውዴ በስብሰባው ወቅት ተጫዋቾች የራሳቸውን ተወካይ የመምረጥ መብት እንዳላቸው እንደሚያምኑ ሲገልጹ ይሄ ለቬጋስ ኢትዮ ስታር ፋሲለደስ ክለብ ለምን አልሰራም ተብለው ሲጠየቁ ይሄን ለመመለስ ስልጣን የለኝም ብለዋል።

የፌዴሬሽኑ ተወካይ በቬጋስ ኢትዮጵያ ኮምኒቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተጠራው የረቡዕ ስብሰባ ያለ ውጤት የተበተነ ሲሆን ተወካዩ አቶ ተካበ ከስብሰባው በፊት አስቀድመው የቡድኑን አባላት ልምምድ በሚያደርጉበት ሜዳ ላይ ያስተዋሉ ሲሆን በስብሰባው ወቅት ተጫዋቾቹ ተወካዮቹ ተጫዋች አለን ካሉ የታሉ እስቲ ያሳዩዋችሁ ሲሉ ሞግተዋል። አቶ ተካበን ለፌዴሬሽኑ በአግባቡ ያዩትን በትክክል እንዲናገሩ አሳስበዋል።

ከቡድኑ ነባር አባላት አንዱ ሲራክ የፌዴሬሽኑ ጥቂት አመራሮች ኢትዮጵያውያንን በሚያቀራርበው ፌዴሬሽን ስልጣን ላይ ተቀምጠው ለግለሰቦች ወግነው ፍትህ የሚያጣምሙበትን አሰራር እውነተኛ የሆኑ የቦርዱ አመራሮችና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መፍትሄ ይሰጡበታል ብለው ለሁለት ዓመት ከፌዴሬሽኑ ጋር በመጻጻፍ መቆየታቸውን ገልጾ አሁን ግን እንደትላንቱ ጊዜያችንን አናቃጥልም የሕግ አማካሪ ይዘን የፈጸሙብንን በደል እንጠይቃለን ሲል ይህንኑ ውሳኔ ከፌዴሬሽኑ ተወክለው ለመጡት አቶ ተካበ ጭምር እንደሚነግር ለህብር ሬዲዮ ደግሞ አረጋግጧል።

የፌዴሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዮሀንስ ብርሃኑ ባለፈው ዓመት ለህብር ሬዲዮ በሰጡት ቃል የቬጋሱን የኢትዮ ስታር ፋሲለደስ ቡድንና ተመሳሳይ ችግር ያለባቸውን ሌሎች ክለቦች ችግር ፌዴሬሽኑ ከዳላሱ ውድድር በሁዋላ በሚያደርገው የቦርድ ስብሰባ ይፈታዋል ሲሉ ማረጋገጫ ሰጥተው ነበር።

ህብር ሬዲዮ የፌዴሬሽኑ ተወካይ በቬጋስ ተገኝተው ያደረጉትን ስብሰባ ሙሉ ገጽታ የሚያሳይ ድምጽና የቪዲዮ ቅጂ የሚከተለው ነው፦


ፍፁም ሰላማዊ! (ይቺን ነው መኮረጅ!) – ከአቤ ቶኪቻው

$
0
0

ከአቤ ቶኪቻው

980132_456214187800412_886270627_oቀጥሎ ስለ ሰላማዊ ሰልፉ ጥቂት ልናወጋ ነው፡፡ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ እና በጥቅሉ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ስለ ሰላማዊ ትግል ስናወራ ስለ ሙስሊም ኢትዮጵያውን በማውራት ብንጀምር የወጋችንን ደረጃ ከፍ ደርገዋል ሞገስም ይሰጠዋል እና እንቀጥል…

መንግስታችን በዛን ሰሞን በገዛ ቴሌቪዥኑ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ተቃውሞ በሌላው ህብረተሰብ ላይ የተቃጣ ትንኮሳ አስመስሎ ኮሳሳ የሆነ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሲሰራ አይተን ታዝበን ታዝበን ታዝበን አልወጣልንም፡፡

በተደጋጋሚ እንዳየነው ሙስሊም ኢትዮጵያውን ከአመት በላይ በመስጂዳቸው ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ያሳዩን ጨዋነት ገዢዎቻችንን ያሳፈረ ነበር የሚለው ቃል አይገልፀውምና “አፈር ያስበላቸው ነበር” ማለት ይሻላል፡፡ (አረ እንደውም አፈር ደቼ እንበል እንጂ… ሃሃ… “ደቼ” የምትለውን ቃል ትርጓሜ ከሳቴ ብርሃን መዝገበ ቃላትን ላይ ባገላብጥም፤ ደቸር፣ ደቻሪ ደቻራ፣ ደችሮ ብሎ ይዘላታል እንጂ ትርጉሟን አላስኮርጅ አለኝ…) የምር ግን የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጨዋነት የተላበሰ ተቃውሞ ገዢውን እና አሳሪውን መንግስታችንን አፈር ደቼ ያበላ ነበር ከሚለው ውጪ ገላጭ ቃል ከየት ይገኝለታል?

የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጥያቄ የሌላው ኢትዮጵያዊም ጥያቄም ነው፡፡ ኢትዮጵያውን ሙስሊሞች፤ “መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ አይግባ” ይላሉ፡፡ ሌላውም ኢትዮጵያዊ፤ “አዎን እንኳንስ በሀይማኖት እና በታክሲ ወረፋም ጣልቃ መግባት ነውር ነው” ይላል፡፡ ኢትዮጵያውን ሙስሊሞች፤ “መንግስት የምንጠይቀውን ጥያቄ በእስር እና በጠብ መንጃ አይመልስልን” ይላሉ፡፡ ሌላውም ኢትዮጵያዊ “አዎ ሰው ማሰርን በሬ እንደማሰር አታቅልሉት ሰው ለመጥመድም በሬ እንደመጥመድ አትቸኩሉ” ይላል፡፡ በጥቅሉ ኢትዮጵያውን ሙስሊሞች “ድምፃችን ይሰማ” ይላሉ፡፡ ሌላው ኢትዮጵያዊም፤ “ጮክ ብሎ ዜና እናሰማለን ማለት ብቻ ዋጋ የለውም የእኛንም ድምፅ መስማት ልመዱ” ሲል በየአጋጣሚው ሁሉ ይጮሃል፡፡

እስከ አሁን ኢትዮጵውን ሙስሊሞች በአንድ ላይ ሆነው በየሳምንቱ በየ መስጂዳቸው ድምፃችን ይሰማ ሲሉ የቆዩ ሲሆን፤ የተቀረው ኢትዮጵያዊ ደግሞ በጋራ ሆኖ ኡኡ የሚልብት አማካይ ቦታ ተቸግሮ “የት ሄጄ ልፈንዳ” እያለ ይገኛል፡፡

አሁን እድሜ ለሰማያዊ ፓርቲ፤ ሁሉን በጋራ የሚያሰባስብ አንድ መድረክ ተፈጥሯል፡፡ እሁድ ግንቦት 25 ዋቄፈታውም፣ ኦርቶዶክሱም፣ ሙስሊሙም፣ ፕሮቴስታንቱም፣ ካቶሊኩም በአንድ የሚሰባሰቡበት መድረክ ተፈጥሯል፡፡ በጥቅሉ ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምፅ ተባብረው “ድምፃችን ይሰማ” ይላሉ፡፡ መንግስት ሊሰማም ላይሰማም ይችላል፡፡ የጋራ የሆነው የሰማዩ አምላክ ግን እንደሚሰማ ግን በጣም ርግጠኛ ነን!

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤

እስከ አሁን በደረሰኝ ወሬ ከቢሸፍቱ (ደዘዎች) እና ከአዳማ (ናዝሬት) በርካቶች በሰልፉ ለመታደም ተነሳሽነት አሳይተዋል፡፡ እንደ ቅንጅት ጊዜው በክልላችሁ ተሰለፉ ካልተባሉ በስተቀር፤

በመጨረሻም

ፖሊስ እና ወታደሩ የተሰላፊው ወገን መሆኑን መርሳት ራስን ከመርሳት ጋር እኩል ነው፡፡ ተሰላፊዎች ሃምሳም ሁኑ ሃምሳ ሺህ አንድ ፀባይ ግን ያስፈልጋል እርሱም ፍፁም ሰላማዊ መሆን! ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሚሊዮን ሆነው አቤት ሲሉ የአቤቱታው ፀባይ አንድ ነበር ፍፁም ሰላማዊ! (ይቺን ነው መኮረጅ!)

በመጨረሻው መጨረሻ

ለሰላማዊ ተቃዋሚዎች፤ ሰላሙን ያብዛ! ብለን እንመርቃለን!

አሜን!

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ የፎቶ ዘገባ

$
0
0

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ተገኙ። የፎቶ ዘገባውን ይመልከቱ። (ፎቶዎቹ የጋዜጠና በፍቃዱ ኃይሉ ናቸው)
463787_10200726544579943_1927157516_o

463813_10200726548540042_1752304564_o

737064_10200726533179658_1146948848_o

964050_10200726454377688_1498466_o

964160_10200726506378988_351801364_o

964382_10200726554220184_1320094080_o

964529_10200726535019704_2096094436_o

964989_10200726449297561_2096771415_o

965358_10200726557420264_1775746088_o

965628_10200726516779248_1690226839_o

965836_10200726448057530_536932729_o

965873_10200726551140107_1183655609_o

967118_10200726502298886_1077028948_o

976879_10200726555860225_1504955293_o

977861_10200726226811999_641498735_o

979885_10200726530979603_470373367_o

980342_10200726537499766_444268736_o

981835_10200726504818949_491585949_o

semayawi

በአዲስ አበባ የተደረገውንና የዛሬውን ሰልፍ የሚያሳዩ ቪድዮዎች

$
0
0

ጭቆና ይጥፋ ወኔ የሌለው የሀገር ሸክም ነው

አንድነት ለሃገራችን

ሃገራችን እንደዳዳቦ አንቆራርስም

መማር ያስከብራል ሀገርን ያኮራል

ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በሰላም ተጠናቀቀ

$
0
0

980132_456214187800412_886270627_o(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ዛሬ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም የተደረገውን የሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞ የኃይለማርያም ደሳለኝ መንግስት ፍቃድ መስጠቱ የሚያስመሰግነው ቢሆንም የሕወሓት/ኢሕአዴግ ወታደሮች በሌላ በኩል ሰልፉ እንዳይካሄድ ሲያውኩ ነበር የከረሙት። ትናንት በአዲስ አበባ 6 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሾላ የካ ሚካኤል አካባቢ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው የነበረ ሲሆን ነገር ግን ፍርሃት የሚባለውን ነገር እያስወገደ የመጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአካባቢው የሚገኙ ህብረተሰቦች በግምት ወደ 200 የሚጠጉ ልጆቹን ለማስፈታት ባደረጉት ጥረት ከአንድ ሰአት ግርግር በኋላ የታሰሩትን ልጆች ማስፈታት እንደቻሉና፤ ባካባቢው የነበረውም ህብረተሰብ ጭብጨባና ዘፈን በማሰማት ከአካባቢው መበተኑን ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቆ ነበር።
981090_456217131133451_659197631_oመንግስት ይህን የተቃውሞ ሰልፍ በአንድ በኩል ፈቃድ ሰጪ በሌላ በኩል አሰናካይ በመሆን ቢቀርብም ለሰላማዊ ሰልፍ የወጣው በበብዙ ሺዎች የሚቆጠረው ህዝብ ግን ጥያቄው አሁንም ሰላማዊ መሆኑን አሳይቶ ድምጹን በሚገባ በማሰማት በሰላም ወደ መጣበት ተመልሷል።
ከምርጫ 97 በኋላ ሟቹ ጠ/ሚ/ር ከቤት ውጭ የሚደረጉ ማናቸውንም የተቃውሞ ሰልፎች ከከለከሉ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በተደረገው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገኘው ህዝብ በተለይ የታሰሩ የፖለቲካ፣ የሃይማኖትና ጋዜጠኛ ህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፤ በአባይ ስም የሚደረገው ማጭበርበር እንዲቆም፣ የተማረ ቤቱ ቃሊቲ እንዳይሆን፣ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ የመናገርና የመጻፍ መብት እንዲከበርና ሌሎችንም ጥያቄዎችን ማንሳታቸውን የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።
“በሃገራችን ሰላም አጣን”
“የኑሮ ውድነት ያጎበጠው ትከሻችን እረፍት ይሻል”
“የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ይፈቱ”
“መማር ያስከብራል ሃገርን ያኮራል”
“ነፃነት የሌላት ሃገር ጨለማ ናት”
“መማር ያሳስራል፤ ቃሊቲ ያስገባል”
“የመንግስትን በኃይማኖት ጣልቃ ገብነት እናወግዛለን”
“ኮሚቲዎቻችንን ይፈቱ”
“ልማት እያሉ ሙስና ሰሩ”
“ፍትህ! ፍትህ! ፍትህ!”
“መብትን መጠየቅ ወንጀል አይደለም፤ መብትን መጠየቅ ስልጣን አይደለም”
“ዜጎችን ማፈናቀል የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው”
“መብትን መጠየቅ አሸባሪነት አይደለም”
“ኢቲቪ ሌባ፤ ውሸት ሰለቸኝ”
“የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች ይመለሱ”
“ህገመንግስቱን የሚጻረሩ ህጎችን እንቃወማለን”
የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮችን ያሰሙት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ መንግስት በአስቸኳይ ድምጻቸውን እንዲሰማም ጠይቀዋል።
(ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እስከምንመለስ ከአዲስ አበባ ከተደረገው ሰልፍ በኋላ እዚያው አዲስ አበባ የነበረው ገጣሚ ፋሲል ተካልኝ ስለስልፉ በግጥም የተሰማውን ጽፏል። እናካፍላችሁ)

_ጥቂቶች ስንት ነን?!?___
“ጥቂቶች” አትበሉን..እናንት ብዙኃኑ!
የጊዜ ጉዳይ ነው..እልፍ አዕላፍ መሆኑ::
እናንት ብዙኃኑ!..
ተዉ አታሳንሱን..ተዉ አታንኩዋስሱን..
እናንተም ጥቂቶች..
እንደነበራችሁ.. እኛን አታስታውሱን::
ወር ተራው ደርሷችሁ..
አውነታው ጠፍቷችሁ..
…ዛሬ ስታገሉን
ጥቂት እንኩዋ’ አታፍሩም?!?
…”ጥቂቶች” ስትሉን
እናንተ ብዙኃን..”ጥቂቶች” አትበሉን
ሐቁን ስነግራችሁ..ሐቁን ተቀበሉን::
“…ተባዝቶ..ተባዝቶ..
ዛሬ ምድርን ሞልቶ..
ሰባት ቢሊዮናት..ቁጥሩ የደረሰው
ከጥቂትም..ጥቂት..ከጥቂት እሚያንሰው
የኦሪቱም አዳም..ነበረ’ኮ አንድ ሰው::…”
እናንት ብዙኃኑ!..
ኧረ ለመሆኑ…
እማንታያችሁ..በቁጥራችን ገነን
“ጥቂቶች” ስትሉን..”ጥቂቶች ስንት ነን?!?”
* * *
___ፋሲል ተካልኝ አደሬ___
___________________________________________________
በሌላ በኩል የቀድሞ የኢትኦጵ እና የአዲስ ዜና ዋና አዘጋጅ ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን በፌስቡክ ገጹ ስለዛሬው ሰልፍ የሚከተለውን ጽፏል።
“አሂምሳ!”
ዝምታው ተሰበረ!!!
ሠማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሰልፈኞች አደባባይ ወጥተው ስለ ፍትህ ዘመሩ፡፡ እጅግ አስደናቂ፣ እጅግ አስገራሚ፣ ፍፁም ሠላማዊ የሆነ ሰልፍ…!!
በግሌ በሠላማዊ ትግል ላይ ያለኝ ጠንካራ ዕምነት የሚያመረቃ ፍሬ ያፈራበት፣ እጅግ በጣም የተደሰትኩበት፣ በተለይ በወጣተ ትውልድ መነቃቃት የኮራሁበት ቀን ነው፡- ዛሬ፡፡
እንደዛሬ “የፎቶ ካሜራ በኖረኝ” ብዬ የተመኘሁበት ቀን የለም፡፡ እንዲያም ሆኖ በሞባይል ካሜራ አስደናቂውን ሰላማዊ ሰልፍ በምስል ላሳያችሁ ሞክሬአለሁ፡፡ እውነት እውነት እጅግ በጣም የሚያኮራ ቀን ነበር ዛሬ፡፡ የሠላማዊ ትግል ትንሳኤ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
ጋንዲ ለሚታወቁበት “የጨው አብዮት” ለሠልፍ የወጡት በ20 ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ነበሩ፡፡ ዋናው ግብ ቦታ የደረሱት ግን በቁጥር 193 ሰዎች ነበሩ፡- ታሪክ እንደዲነግረን፡፡

“አሂምሳ” እንዲሉ ማህተመ ጋንዲ ጠንካራ ወኔ መንፈስ የተላበሱ ሠልፈኞች በቸርችል ጎዳና ላይ በእምነት ፈሰሱ፡፡…ያኮራሉ! ኮርቻለሁ!

የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ከድጡ ወደ ማጡ

$
0
0

London churchዘመነ ካሳ (ከጀርመን)
በዚህ በትልቁ የአውሮፓ ክፍል የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ለረጅም ዘመናት አገልግሎት የሰጠች እንደመሆንዋ መጠን በሙያ የበሰሉ አገልግሎታቸው የተመሰገኑ አባቶች አገልግሎት የሰጡበት መሆኑ ታሪክ የሚያስታውሳቸው ነው:: ከነዚህም አባቶች መካከል በቀድሞው ስማቸው አባ አረጋዊ በኋላ ብጹእ አቡነ ዮሐንስ እንዲሁም ሊቀ ካህናት ሰሎሞን ገብረ ስላሴና ሌሎችም ይገኙበታል:: ይህቺ ቤተ ክርስቲያን ለተዋህዶ እምነት ተከታዮች ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክተች ቤተ ክርስቲያን ስትሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከኣውሮፓ ቀደምት ተብለው ከሚጠሩት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በቁጥር አንድ የምትቀመጥ ከመሆንዋም በላይ ከሀገራችው ተሰደው ከወገን ከዘመድ ተለይተው ለሚገኙ ምእመናን ከፍተኛ መጽናናት ትንሿ እናት ሀገር ኢትዮጵያ መሆንዋ የማይካድ ነው::
ስለሆነም በካህናቱ መልካም አገልግሎት በምእመናኑ ያልተቆጠበ ጥረት ህንጻ ቤተ ክርስቲያን በመግዛት አርያነቱ ለሌሎች የሚተርፍ ቅርስና ታሪኩ ለትውልድ የሚተላለፍ አስደናቂ ተግባር ፈጽመው በባእድ ሀገር የህንጻ ቤተ ክርስቲያን ባለቤት ለመሆን በቅተዋል::

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Viewing all 13695 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>