ስመኝ ከፒያሣ
የኢትዮጵያ ፕሬስ የሚታወሰው ወይም የሚነሳበት ዘመን ቢኖር ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ ኢህአዴግ መላ ሀገሪቱን ከተቆጣጠረበት ከግንቦት 20/1983 ዓ.ም እስከ 1985 ዓ.ም ድረስ ምንም ያደረገው ነገር አልነበረም፡፡ ፀጥታ የነገሰበት ጊዜ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ማለትም 1985 ዓ.ም ላይ የኤርትራ ሪፈረንደም የተፈቀደበት ጊዜ ነበር፡፡ ከዛ በኋላ ደግሞ በሙሉ ነፃነት ነገሮችን መግለፅ ተጀመረ፡፡ታዲያ በነዚህ ጊዜያት ከወጡትና ስለኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት አለን ብለው መፃፍ ከጀመሩት መካከል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አንዱ ነው፡፡ እስክንድር ነጋ በምድረ አሜሪካ ይኖር የነበረ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ከደርግ ውድቀት በኋላ ነው፡፡ በቤተሰቦቹ ላይም ሆነ በእሱ ላይ ከፍተኛ እንግልት፣ ስቃይና በርካታ የንብረት ውድመት በደርግ መንግስት ደርሶባቸዋል፡፡ እሱና እናቱ በቀይ ሽብር ወቅት ከፍተኛ ጭፍጨፋ ፈፅመዋል ከሚባሉት አንዱ በሆነው ” ግርማ ከበደ” ከፍተኛ እንግልትና የንብረት ውድመት ሲያደርስባቸው ወደ አሜሪካ ተሰደዱ፡፡
እስክንድር በአሜሪካ በነበረበት ወቅት ደርግ ይፈፅማቸው ለነበሩ ያልተገቡ ተግባራት በሙሉ በአሜሪካ ይገኙ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን በደርግ መንግስት ላይ ጫና ይደረግ የሚል መርህ ባነገቡ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ ቀርተው አያውቁም፡፡ ሁሌም ስለሀገሩ ያስብም ነበር፡፡ የእስክንድር ፍላጐት ሀብት ንብረትና ገንዘብ ሣይሆን የኢትዮጵያ እድገትና ለውጥ ማየት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከሌላው ሀገር በተሻለ ለውጥ ማምጣት የምትችል ሀገር በመሆኗ ይህ ለምን መሆን አልቻለም ብሎ የሚናገር ጋዜጠኛም ነበር፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣም በኋላ “ኢትዮጲስ” የተባለ ጋዜጣን ከሟች ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ ጋር በመሆን አቋቋመ፡፡ በወቅቱ በኢትዮጵያ ኢህአዴግ ዴሞክራሲን አስፍኛለሁ ያለበት ጊዜ ነበር፡፡ ዴሞክራሲ ያለገደብም ተብሎ ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት በርካታ ዜናዎች ማቅረብ ጀመሩ፡፡ በወቅቱ እነሱ የጀመሩት ጋዜጣ ዋጋ 75 ሳንቲም ቢሆንም ይዘውት የሚወጡት ዘገባ ከባድነት “ኢትዮጲስ” ጋዜጣ ሰባት ብር ድረስ ትሸጥ ነበር፡፡ የዛሬ 20 አመት ሰባት ብር የነበረውን ጥቅም ማንም ቢሆን የሚዘነጋው አይደለም፡፡
ታዲያ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ኢትዮጲስ ተቋረጠች፡፡ እነ እስክንድርም ታስረው ወጡ፡፡ ከዛ “ሀበሻ” የተባለ ጋዜጣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ ማሣተም ጀመረ፡፡ ይሁንና ግን ብዙም ሣይራመድ “ጐበዝ አምስት አመት ሞላ” የሚለው ዘገባ ችግር ፈጠረ፡፡ እስክንድር መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያነበው ዘንድ ሀበሻን ይጠብቋት ብሎ የጋዜጣውን ማስታወቂያ በካርቶን ይዘው የሚዞሮ ወጣቶችን መድቦ ነበር፡፡ ይሁንና እስከ እነሱ ጭምር በድጋሚ ታሰረ፡፡ ወጣቶቹ ሲፈቱ እስክንድር ግን በማረሚያ ቤት ቀረ፡፡ የእስክንድር ቀኝ እጅ የተሰበረውም በዛ ጊዜ ነበር፡፡ እስክንድር ከተፈታ በኋላም ዳግም ታስሯል፡፡ እንደውም በ1987 አብሯቸው ከታሰራቸው መካከል የግብፁን ፕሬዝዳንት ሁሴኒ ሙባረክን ለመግደል ሙከራ ያደረጉና በቁጥጥር ስር ከዋሉ አሸባሪዎች ጋር ነበር፡፡ እዚህ ላይ የምገልፀው ነገር ቢኖሩ እስክንድር ነጋን እኔ እንደማውቀው ነው፡፡ ከዛ በኋላ ወይም ከረጅም ጊዜ እስር በኋላ ግን ተፈቶ እስክንድር ነጋ ወደ ጋዜጣ ሕትመት ሲመለስ “ምኒልክ” የተባለውን ጋዜጣ ይዞ ብቅ አለ፡፡ ምኒልክ ጋዜጣ መቼም በሀገሪቱ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ በህትመት ግንባር ቀደም የነበረ ጋዜጣ ነበር፡፡
እስክንድር ነጋ የተለየ ነገር ወይም ባህሪ አለው፡፡ ይህ ባህሪው ደግሞ ስለገንዘብና ጥቅም የሚያስብ ሰው አልነበረም፡፡ በወቅቱ ጋዜጦች በኪሳራ ከጨዋታ ሊወጡ ሲሉ የሚደጉም የለኝም ብሎ ለመጣ ሁሉ የሚሰጥ ሰው ነበር፡፡ እኔ እስክንድርን ከተዋወኩበት ጊዜ ጀምሮ ሁሌም እሱን ማወቅ ያጓጓኛል፡፡ ምክንያቱም ከእሱ የሚወጡት ሀሣቦችና ቃላት የተለዩና በውስጣቸው እውነትነት ያላቸው ነበሩና፡፡ እስክንድር ስለገንዘብ ጥቅም ወይም ተንደላቆ ስለመኖር የሚያስብ ሰው ፈፅሞ አይደለም፡፡ የየትኛውንም ሰው ሀሣብ ይቀበላል በፅሞናም ያዳምጣል፡፡
የትልቅነት መለኪያው ደግሞ ምንም ሣይሆን ሰዎችን ማዳመጥና መስማት መቻል ነው፡፡ እስክንድር በጋዜጦቹ ላይ በርካታ ነገር ይፅፋል፡፡ አንድም ጊዜ ቢሆን ግን ምስሉን ለጥፎ እኔ እስክንድር ነጋ ነኝ ብሎ አያውቅም፡፡ ከዛ ባለፈ ደግሞ “ሀበሻ” ጋዜጣ ከታገደበት በኋላ በስሙ ያወጣው ጋዜጣ የለም፡፡ ፎቶውን ሣይሆን ስሙን አውጥቶ የፃፋቸው ፅሁፎች ቢኖር የማስታውሰው የደርግ ባለስልጣናትን በሚመለከት በሚወጡ ፅሁፎች ላይ ነበር፡፡ ከዛ ውጭ ግን በሰራው ስራ በሕዝብ እንዲወደዱ እወቁኝ እወቁኝ እያለ በአደባባይ የወጣ ወይም ደረቱን ነፍቶ ይህ ይሁን ያለ ሰው አይደለም፡፡
እስክንድር የተለየ ቦታ ያለው ሰው ነው፡፡ አንድ ታሪክ ልንገራችሁ ይህን ታሪክ ግን ስም ሣልጠቅስ ባወራው እመርጣለሁ፡፡እስክንድር አሁንም በስራ ላይ ላለ ጋዜጣ ባለቤት እባክህ እከሌ የተባለን ባለሰልጣን ለማነጋገር ፈልጌ ሪፖርተሬን መላክ ፈለኩ እናም አስጨርስልኝ አለው፡፡ ይህ ሰውም ባለስልጣኑን ሲያናግር ባለስልጣኑ ሪፖርተሩ ሣይሆን ራሱ እስክንድር ነጋከመጣ ቃለመጠይቁን እሰጠዋለሁ አሉ፡፡ በዚህ ምክንያት እስከንድር ሣይሄድ ቀረ፡፡ እኚህ ባለስልጣን ታዲያ አሉ ወይም ተናገሩ በተባለው ቃል “እስክንድር የገንዘብ ችግር እንደሌለበት አውቃለሁ የሚሰራው ለጥቅም ወይም ለፖለቲካ ፓርቲ አይደለም፡፡ አላማው ምን እንደሆነ እሱን አግኝቼ ማናገር እፈልጋለሁ” ሲሉ ገለፁ፡፡
የእስክንድርን መንፈስ ስናስበው ታዲያ በዚህች ሀገር ላይ እውነተኛው ዴሞክራሲ መስፈን አለበት ከሚል አንፃር በመነጨ የሚሰራ እንጂ አትራፊ ጋዜጠኛ ወይም የሕዝቡ የልብ ትርታ ይሄ ነው ብሎ ምስሉን ለጥፎ የሚነግድ አይደለም፡፡ ርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ በሀገሪቱ ከታተሙ ነፃ ጋዜጦች እስክንድር ነጋ የሚሰራባቸውን ጋዜጦችን በቁጥርና በጥራት የሚደርስ አልነበረም፡፡ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ እስከንድር ሻይ እንጠጣ ብሎ ኪሱ ሲገባ ገንዘብ ሣይዝ ረስቶ የሚወጣ ሰው ነው፡፡ ስለገንዘብና ስለዝና አይኖርም፡፡ በእሱ ስር የሚሰሩ ሰራተኞች ግን የበለጠ እንዲጠቀሙ ያደርጋል፡፡ እስክንድር ተቸገርኩ ላለው ሰው ሆዱ የማይጨክንና የሚራራ ደግ የሚባል ጋዜጠኛም ጭምር ነው፡፡
የእስክንድር ጋዜጣ ነው ከተባለ ጋዜጣ አዙሪዎች ለማውጣት አይፈሩም፡፡ ምክንያቱም እስክንድር ጋዜጣ አደረብኝ የሚል አዙዋሪ በሙሉ ይመለስለታል፡፡ ጋዜጣ አዙዋሪ የሌላውን ለማውጣት መጠን ያበጃል በእስክንድር ጋዜጣ ላይ ግን ቢመለስብኝስ ብሎ አይፈራም፡፡ 12 ሰአት ካለፈ በኋላ እድሜ ለእስክንድር ብሎ ቤቱ ይገባል፡፡ ጠዋት አምጥቶ ይመልሳል፡፡ አዟሪ በሙሉ ሌላ አሣታሚ አልመልስ ካለው እስክንድር እንኳን እየመለሰ ሲል ሁሉም ለእሱ ክብር ሲል መመለስ ጀመረ፡፡
እስክንድር የየትኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ አባል አይደለም፡፡ አልነበረምም፡፡ ሁሌም ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ይወቅሳል፡፡ ይናገራል፡፡ ምኒልክ ጋዜጣ በነበረበት ጊዜ በመጀመሪያ የተጋጨው ከኢ/ር ኃይሉ ሻወል ጋር ነበር፡፡ የግጭቱ መንስኤ ደግሞ የፓርቲያችሁ አቋም ይሄ ነው ለምን ሆነ በሚል ነው፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ ለኢህአዴግ ስጋት ፈጥሮ የነበረው ፓርቲ “ቅንጅት” በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እስክንድር አንድም ቀን ተገኝቶ አያውቅም፡፡ በእነሱ አሰራር ወይም አካሄድ ላይ ቅሬታ ካለው ግን ይናገራል፡፡ ኢ/ር ኃይሉ ሻወል በልጃቸው አማካይነት ተቃውሞውት ወደ ክስ አመራለሁ ብለው ያውቃሉ፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በውስጣቸው ያለውን ችግር ይገልፃል፡፡ ሌላው ይቅርና አቶ ልደቱ አያሌውን ማንዴላ በተባሉበት ወቅት ሣይቀር የእሣቸው አካሄድ ላይ በድፍረት ቅሬታውን የገለፀ ሰው ቢኖር እስክንድር ነጋ ነው፡፡
ዘመን ሲቀየር ሕዝብ ሊቀየር ወዳጅም ሊከዳና ሊርቅ ይችላል፡፡ እስክንድር ነጋ ግን ዛሬ አብጠው ሲሰሩ ከማያቸው አንዳንድ ጋዜጠኞች የእሱ ምክርና ድጐማ የሌለባቸው አሉ ብሎ ለመናገር ይከብዳል፡፡ ይህቺ ሀገር ጋዜጠኛ አፈራች እስክንድር ነጋን ብል የማፍርበት ሰው አይደለም፡፡ ሁሌም የምኮራበት ሰው ነው፡፡ ከላይ እንደገለፅኩት እስክንድር የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አይደለም፡፡ ሁሌም “ምርጫ 97″ የሚለውን መፅሐፍ ሣስበው አለም የእሱን የእውቀት ደረጃ እንዲለካ እፈልጋለሁ፡፡ ከእሱ በኋላ እሱን አጣጥመው የማያውቁት ተነስተው ታሪክ ለመስራት ቢሞክሩ እነሱን በወንፊት አጥልሎ ማንነታቸውን ለማወቅ ይከብዳልና፡፡ የማያውቁት አገር አይናፍቅም እንደሚለው ዘፈን እስክንድር ነጋን ያየ ዛሬ በሌሎች ያልተጣራና ያልተረጋገጠ ተግባር ሊደመም አይችልም፡፡ የፅሁፌ ሳጠቃልል እስክንድር ነጋ በኢትዮጵያ የነፃ ፕሬስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለውና ስለእውነት ብቻ የሚናገር ምርጥ ጋዜጠኛ መሆኑን ምስክርነቴን በመስጠት ነው፡፡
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና እኔ እንደማውቀው
ሁለት የአረና ለትግራይ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ከፓርቲው ለቀቁ
“ለዓረና/መድረክ አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ ስላሳለፍነው ጥሩ የአብሮነት ጊዜ ማመስገን እንፈልጋለን። ብዙ የትግል ልምድ ካለው አመራር ጋር አብሮ መስራት በራሱ እንደ አንድ ትልቅ እድል ነው ምናየው። ለዓላማ የመኖር ፅናት፣ ትዕግስትና ፖለቲካዊ ተሞክሮ አግኝተንበታል። ከዚህ በተጨማሪም ስለአገራችን ፖለቲካ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለመረዳት እድል ፈጥሮልናል። በእዚያ ባሳለፍነው አስቸጋሪ የፖለቲካ ጉዞ ውስጥ ስብዕናህን የሚፈታተኑ፣ ትግል የምታደርግበትን ምክንያት እስኪጠፋህ ድረስ የሚያደርሱና ፀጉር የሚያቆሙ ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የነበሩበት ቢሆንም፤ የዚያው ያህል ደግሞ ብዙ የተማርንበት፣ አቅምና ክህሎት ያገኘንበት፣ ከአገር ውስጥም ከውጭም ብዙ ለአገርና ለወገን ተቆርቋሪ የሆኑ ዜጎች ለመተዋወቅ ዕድል የፈጠረልን በመሆኑ ሁላችሁም እናመሰግናለን።” ያሉት አቶ አስራት አብርሃም እና ጉ ዕሽ ገብረጻዲቅ “ከሁሉም በላይ ደግሞ ዓረና የፖለቲካ ጥርሳችን የነቀልንበት፣ ስለሀገር፣ ስለሰው ልጅ፣ ስለስልጣን ምንነት፣ ስለሁሉም ነገር በጥልቀት እንድናውቅ ዕድል የሰጠን ፓርቲ በመሆኑ በህይወታችን ሁሉ ስናስታውሰው የሚኖር ነው። ባለፉት ስድስት ዓመታት የተማርነው ነገር ብዙ ነው፤ አገራችን የብዙ ችግሮች ባለቤት መሆኗም ተገንዝበናል። ይህ ሁሉ ችግር ለማቃለልም አሁንም ቢሆን እልህ አስጨራሽ ትግል ማድረግ ግድ የሚል መሆኑን እንረዳለን፤ ከዚሁ ትግል ደግሞ እኛ ወደኋላ እንል ዘንድ ስብዕናችንና ተፈጥሯዊ ባህርያችን የሚፈቅድልን አይደለም።” ብለዋል።
“ዛሬ ከፓርቲው በዚህ ሁኔታ ብንለይም ፓርቲው እስከ አሁን ይዞት የመጣውን ለመርህ የመገዛት፣ በጋራ አመራር የማመንና ተግባብቶ የመስራት ባህሉ መቀጠልና መጠናከር አለበት እንላለን። ውስንነት ቢኖረውም ውስጣዊ ልዩነቶችን አቻችሎ የሚጓዝበት፣ ችግሮች ሲከሰቱ ደግሞ በሰከነ ሁኔታ የሚፈታበት መንገድ ለሌሎችም ትምህርት ሊሆን የሚችል ነው። ይህ ልምድም መጠበቅ አለበት። በአንፃሩ ደግሞ ጎጂ የሆኑ ዝንባሌዎች ማለትም ወግ አጥባቂነትን፣ ቡድናዊነትን፣ ግላዊ ጥቅመኝነትንና ስልጣን ወዳድነትን ሥር እንዳይሰዱ ነቅቶ መጠበቅና መታገል የሚገባ ነገር ነው።” ሲሉ በደብዳቤያቸው ላይ ያተቱት የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚዎች “በተለይ ደግሞ መድረክ አሁን ካለበት የተሻለ አደረጃጀትና አሰራር እንዲኖረው፣ በአባል ፓርቲዎች መሀከል ያሉትን ጥቃቅን ልዩነቶች በማቀራረብና በማመቻመች የተሻለ መተማመንና አብሮ መስራት የሚቻልበት ብሎም ወደ ውህደት የሚመጣበትን መንገድ እንዲፈጠር ጠንክሮ መስራቱ ለሁሉም የሚበጅ ነው የሚሆነው። ዓረና በዚህም በእኩል ከሸምጋይነት ሚናው ወጥቶ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ የሚጠበቅበት ነው። ጠብ እና አለመተማመን በመርህ፣ ብሎም ተቀራርቦ በመስራት ይፈታሉ እንጂ የመርህ ችግር በሽምግልና የሚፈታ አይደለም።” ሲሉ አስረድተዋል።
“መድረክ የአመራር ዳይናሚዝም ለመፍጠር የሚያስችል አሰራር መከተል፣ ብቃት ያላቸው አዳዲስ አመራሮች ማብቃና ወደፊት ማምጣት ይጠበቅበታል። ነባርና ልምድ ያለው አመራር መኖር ለአንድ ፓርቲ እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም የተለየ እንቅስቃሴ ማድረግ ግድ ለሚለው የሀገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚመጥን ፖለቲካዊ አመራር መስጠት ባልተቻለበት ሰዓት ግን “የማርያም መንገድ አለኝ” ለሚል አዲስ አመራር ዕድል መስጠት ተገቢ ይሆናል። ደግሞም አመራርነት በብቃትና በአባላቱ ዘንድ በሚኖረው ቅቡልነት ላይ የተመሰረተ መሆን ይገባዋል እንላለን።” በሚል የተነተኑት እነዚህ ሁለት አመራር አባላት “ውድ የዓረና/መድረክ አባላትና ደጋፊዎች፣ እኛ ዜጋ በዜግነቱ የሚከበርባት፣ ፍትሃዊትና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እስክትፈጠር ድረስ ፖለቲካዊ ትግሉን የምናቆም አይደለንም። ከዚህ በኋላም ቢሆን በሀሳብና በተግባር በአጠቃላዩ የሀገራችን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ መኖራችን የሚቀጥል ነው የሚሆነው። እኛ የትግራይ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ተስማምቶና ተግባብቶ ለመኖር ያለውን መልካም ፍላጎት ከማንፀባረቅና ከማሳየት ውጪ ሌላ ዓላማ የለንም። ከአሁን በኋላም ቢሆን ይህን ጉዳይ ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ከመግለፅና ከማሳየት ወደኋላ የምንል አይደለንም። ከሁሉም በላይ ደግሞ በአገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትህ፣ ፖለቲካዊ እኩልነትና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማንነቱ፣ መብቱና ክብሩ እኩል ተጠብቆለት፣ በአገሪቱ ውስጥ እንደ ዜጋ በሙሉ ነፃነት የመንቀሳቀስ እና ሰርቶ የመኖር መብቱ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ እንዲከበር በምንችለው አቅም ሁሉ ከመታገል ወደኋላ አንልም።” ሲሉ የወደፊቱን የትግል አቅጣጫቸውን አስምረውበታል።
“በአንድ መንገድ ይሁን በሌላ፣ ለሁላችንም የምትስማማ፣ የተሻለች አገር ለመፍጠር መታገላችን እስከቀጠልን ድረስ ተለያየን አንልም። የእኛ እና የሌሎች በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደረጉ ትግሎች ተደማምሮ ነው ውጤት ሊመጣ የሚችለው።” የሚሉት አቶ አስራት እና አቶ ጉዕሽ “እንግዲህ በዚሁ ስንሰናበት ሀዘናችን በጣም ጥልቅ ነው። ስትለያይ ሀዘን መኖሩ፣ ቅር ማለቱ ያለና የማይቀር ነገር ቢሆንም ሀዘናችን እጅግ በጣም ጥልቅ እንዲሆን የሚያደርገው በዚህ ሁኔታ መለያየታችን ነው። ብፆት ሰላም ኹኑ! ድል ለዴሞክራሲያውያን ታጋዮች! ድል አዲሱ ኢትዮጵያዊ ትውልድ!” በማለት ለድርጅታቸው የጻፉትን ግልጽ ደብዳቤ ቋጭተዋል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ አቶ አስራት አብርሃም እና ጉዕሽ ገብረፃዲቅ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ይቀላቀላሉ ተብሎ በሰፊው እየተወራ ነው።
Sport: ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ የፊታችን እሁድ በአ.አ. ወሳኝ ጨዋታ ይጠብቃታል
ከአሰግድ ተስፋዬ
ለ2014 የአለም ዋንጫ ተሳትፎ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ይጫወታል። ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ይህን የእሁዱን ጨዋታ አሸንፎ ምድቡን በበላይነት ካጠናቀቀም አህጉሪቱን በብራዚሉ የአለም ዋንጫ የሚወክሉ 5 ቡድኖችን ለመለየት በ10 ብሄራዊ ቡድኖች መካከል በሚደረገው የደርሶ መልስ ጨዋታ ከሚደርሰው ቡድን ጋር እንደሚጫወት ተገልጿል።
የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ አቶ ሰውነት አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከክለብ ጨዋታዎች ያለ እረፍት ወደ ቡድኑ በመቀላቀላቸው ከቦትስዋና አቻቸው ጋር በነበራቸው ጨዋታ ላይ በተለይም በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ የተፈጠረባቸው የድካም ስሜት ውጤቱ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ እንዳይጠናቀቅ የራሱ ድርሻ እንደነበረውም አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያ ደቡብ አፍሪካን በእሁዱ ጨዋታ ካላሸነፈች ወደ ቀጣዩ ውድድር ስለማትገባ ቡድኑ አጥቅቶ መጫወት እንደሚገባው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው እሁድ አዲስ አበባ ላይ ብሄራዊ ቡድኑች ሲጫወት ሕዝቡም በድጋፉ እንዲበረታ ጥያቄ አቅርበዋል።
ምድብ አንድን ኢትዮጵያ በ10 ነጥብ እየመራች መገኘቷ እና ደቡብ አፍሪካም በ8 ነጥብ በቅርብ ርቀት መከተሏ የእሁዱን ጨዋታ ተጠባቂ አድርጎታል።
በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አገሪቱ ከመሠረተችው የአፍሪካ ዋንጫ ተፎካካሪነት ከራቀችና የሩቅ ተመልካች ከሆነች ከ31 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ መሳተፉን እንዲሁም የአገሪቱ አንጋፋ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ ያሳየውን ተፎካካሪነትን ተከትሎ በርካታ የስፖርቱ ጸሐፍት «ኢትዮጵያ የእግር ኳስ የበላይነቷን እያስመለሰች ነው» ማለት ጀምረዋል ።
ጸሐፍቱ እንዲህ ማለት ከጀመሩ የሰነባበቱ ቢሆንም፣ ዋሊያዎቹ ባለፈው ቅዳሜ ቦትስዋናን በሜዳዋ ላይ ሁለት ለአንድ ከረቱና በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው የምድብ መሪነታቸውን ያስጠበቀ ውጤት ካስመዘገቡ በኋላ አጠናክረው ቀጥለዋል።
ይህንን ሐሳብ ከሚጋሩት መካከል ኢኬና አጉ የተሰኘው ጸሐፊ ይገኝበታል። ጸሐፊው ዋሊያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው ምድባቸውን መምራት መቻላቸው የአገሪቱ እግር ኳስ መነቃቃት እያሳየ እንደሚገኝና ኢትዮጵያም ወደፊት በስፖርቱ ብርቱ ተፎካካሪ አገር እንደምትሆን አመላካች መሆኑን ጽፏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሶማሊያውን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሳይጨምር አራት ጨዋታዎች አድርጎ አንድም አለመሸነፉ ቡድኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዋሃደና ጥንካሬ እያገኘ በመሄድ ላይ እንደሚገኝም ጸሐፊው ጠቁሟል።
ዋሊያዎቹ ምድብ አንድን በአስር ነጥብ ከደቡብ አፍሪካ በሁለት ነጥቦች በልጠው ከአናት መቀመጥ መቻላቸውና ደቡብ አፍሪካን በአዲስ አበባ የሚያስተናግዱ መሆናቸው ከምድቡ የማለፍ ከፍተኛ እድል በመያዝ ቀዳሚ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል ሲልም በጽሑፉ አስነብቧል።
«ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኗ ለዓለም ዋንጫ አልፎ ባያውቅም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2014 ላይ በብራዚል የሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ይህን የቆየ ታሪክ የሚቀየርበት እንዲሆን ለማድረግ ቆርጠው የተነሱ ይመስላልም » ብሏል ኢኬና አጉ።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መስራቿና የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳታፊ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ እንዲሁም ዋንጫውን ያዘጋጀችና ያሸነፈችዋ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ በስፖርቱ ከነበራት ስፍራ ቀስ በቀስ እየተንሸራተተች ሄዳ ደካማ ከሚባሉ አገሮች ተርታ መመደቧን ጸሐፊው አስታውሶ፣ «የ2013ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የአገሪቱ እግር ኳስ እያንሰራራ ለመምጣቱ ግልጽ ማሳያና አገሪቱ በአህጉሪቱ የነበራትን ስፍራ ለመመለስ በሂደት ላይ መሆኗን አመላካች ሆኗል» ብሏል።
ብሔራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ ከምድብ ማጣሪያው ማለፍ ባይችልም እንኳን ነገሮች በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ እንደሚገኙ አመላካች እንደነበሩ ያመለከተው ጸሐፊው፣ ከዚያ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምድብ ድልድል ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መግባቱና ዋሊያዎቹ በአራት ጨዋታዎች ባገኟቸው አስር ነጥቦች ምድብ አንድን መምራት መቻላቸውን በማሳያነት በጽሑፉ ጠቅሷል።
የኢኤስፒኤን ጸሐፊው ፍርዶስ ሙንዳም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ስፖርት በማንሰራራት ላይ እንደሚገኝ ከጻፉት መካከል አንዱ ነው። ጸሐፊው ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ 1962 የአፍሪካ ዋንጫ ብታነሳም እስካሁን በአህጉራዊ ውድድሮች ምድብ ድልድል ውስጥ የገባ አንድም ክለብ እንዳልነበራት ያስታውስና ኤሲ ሌኦፓርድ የተባለው ክለብ የኮንጎን እግር ኳስ እንዳነቃቃ ሁሉ ቅዱስ ጊዮርጊስ በቅርቡ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመዘገበው ውጤት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ግምቱን አስፍሯል።
ከዚሁ ጋር አያይዞ ብሔራዊ ቡድኗ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በማሳየት ላይ የሚገኘው አስደናቂ ብቃትና ውጤታማነት የአገሪቷን የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪ እጅጉን ማርካቱን ጠቁሟል።
ዋሊያዎቹ በሚቀጥለው እሁድ ከባፋናባፋናዎች ጋር አዲስ አበባ ላይ የሚያደርጉትን ጨዋታ በበላይነት የሚያጠናቅቁ ከሆነ ሕዝቡ የሚኖረው ደስታ ባለፈው ጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም ሱዳንን በማሸነፍ ከ31 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ያረጋገጠበት እለት ካሳየው በእጅጉ የተለየ ሊሆን እንደሚችል ገምቷል።
«ዴይታይምስዶትኮምዶትኤንጂ » የተሰኘው ድረ ገጽም በተመሳሳይ « የአፍሪካ የእግር ኳስ ኃያልነት ቀስ በቀስ ወደ ኢትዮጵያ እየተመለሰ ነው » ሲል ጽፏል።
ድረ ገጹ ለማሳያነትም የቅዱስ ጊዮርጊስንና ዋሊያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው በማስመዝገብ ላይ የሚገኙትን ውጤት ጠቅሶ፤ የአገሪቱ ውጤት በአጭር ጊዜ ከአህጉሪቱ ኃያል ከሚባሉት ተርታ ሊሰለፍ እንደሚችል ገልጿል።
ዋሊያዎቹ በማስመዝገብ ላይ የሚገኙት ውጤት የአገሪቱ እግር ኳስ ስፖርት መነቃቃትና በአፍሪካም ደረጃ ወደፊት ከፍተኛ ተወዳዳሪ እንደሚሆን ማሳያ ሆኖ በብዙዎች ዘንድ ተወስዷል።
ይህንን ተከትሎም በቀጣይነት ከዋሊያዎቹ ጋር በአዲስ አበባ ላይ ጨዋታ የሚያደርጉትን የደቡብ አፍሪካን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ጎርደን ኢግሰንድንና የቀድሞ የቡድኑን አባላት አስግቷል።
ባፋናባፋናዎች በዓለም ዋንጫው ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከዋሊያዎቹ ጋር አድርገው ሳላዲን ሰኢድ ባስቆጠራት ግብ ሲመሩ ከቆዩ በኋላ አቻ ለ አቻ መለያየታቸው ይታወሳል። የባፋናባፋናዎች አሠልጣኝ ጎርደን ኢግሰንድ ባለፈው ቅዳሜ ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ጋር ካሜሩን ላይ ከመጫወታቸው በፊት ብዙ የሚያሳስባቸው አዲስ አበባ ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ መሆኑን ገልጸዋል።
ከእርሳቸው በተጨማሪ የቀድሞው የቡድኑ አምበል ሉካስ ራዴቤ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫው ለመሳተፍ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ ተፎካካሪ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንደሆነ አስተያየቱን ሰጥቷል። ባፋናባፋናዎች አዲስ አበባ ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ እጅግ ፈታኝ እንደሚሆንባቸውም ግምቱን ከሰጠ በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማድረግ ላይ የሚገኘው መሻሻል እንዳስደነቀው ተናግሯል።
በበርካታ የእግር ኳስ ስፖርት ተንታኞችና ጸሐፍት ዘንድ አድናቆትንና ሙገሳን በማግኘት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው መመራት ከጀመረ በኋላ በሥነልቡና፣ በቴክኒክና በታክቲክ ረገድ ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱ እውነት ነው።
ይህንንም አገሪቱን በስፖርቱ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደመነሻ መውሰድና መሥራት ይጠበቃል።
“ወንድሞቻችንን እና ልጆቻችንን የገደሉትን መንግስት ቢወድቅ እንኳ አንረሳም” ኦባንግ ሜቶ
የሰማያዊ ፓርቲ ተስፋ
ታክሎ ተሾመ
ወያኔ / ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረበት ቀን ጀምሮ በአገርና በሕዝብ ላይ የሚደርሰው እልቂት ከፍተኛ ስለመሆኑ ነጋሪ የሚያስፈልግ አይመስለኝም። የከፋፍለህ ግዛውን ይትባህል ለማስወገድም ሆነ እድሜውን ለማስቀጠል በደጋፊና በተቃዋሚ መካከል ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ትግል ተካሂዷል። በዘር ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ዛሬም ሆነ ነገ እልቂትን ይጋብዛል፤ እየታየ ያለውም እልቂት ነው።
ውጭም ሆነ አገር ውስጥ ድርጅት መሰረትን ያሉት የትግል ስልታቸውም ሆነ ጥንካሬያቸው አንድነትን የተላበሰ ባለመሆኑ ከራሳቸው ፍጆታ ውጭ ለሕዝብ የሚጠቅም ሥራ እየሰሩ አለመሆናቸው በየጊዜው እየታየ ነው። በየጊዜው ሥማቸውንና መልካቸውን እየቀየሩ የሚወለዱ ድርጅቶችና ስቪክ ማኅበር ስብስቦች የሕዝቡ ትግል እንዲወሳሰብና አንድ ወጥ እንዳይሆን አድርጐታል።
በቅርቡ ወጣቱን ማዕከል ያደረገ ሰማያዊ ፓርቲ የተባለው ወጣቱን በማደራጀት ሥር-ነቀል ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ቀደም እንደ አሸን ከፈሉ ድርጅቶች በተሻለ ሁኔታ የትግል ስልት የተከተለ ይመስላል።
ለዚህ ማስረጃ ግንቦት 2 ቀን 2013 አዲስ አበባ ውስጥ የጠራው ሰላማዊ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ወደፊት ተስፋ ሰጭ ብቻ ሳይሆን የአንድነት ተምሳሌነቱን አሳይቷል ማለት ይቻላል። አገር ቤት እንዳገኘሁት መረጃ ከሆነ የሰልፉ መንፈስ ብሄር፤ እስላም፤ ክርስቲያን ሳይይል የብዙዎችን የትግል ወኔ የቀሰቀሰና ወደፊት ትግሉ ቀጣይ እንደሚሆን ያመላከተና የለውጡን አይቀሬነት ተስፋ ሰጭ እንደሆነ ነው።
በወጣቱ የሚጀመር ትግል ለውጤት እንደሚበቃ የካቲትን 1966 አብዮት ተመልሶ መቃኘት የሚቻል ይመስለኛል። ከታሪክ አመጣጥ መረዳት እንደሚቻለው ወጣቱ አዲስ ሃሳብ አፍላቂ ብቻ ሳይሆን ከዘመኑ ፖለቲካ ጋር የመጓዝ እድሉ የተመቻቸ ነው። ሕዝብ ከቀዩው እየተፈናቀለ፤ አገር እየተደፈረች መሆኑ እውነት ነው። ዛሬ ወጣቱ የቆየች አገሩን የመንከባከብ ኃላፊነት እንዳለበት ከተገነዘበበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብሎ መናገር ይቻላል። እስከ ዛሬ የወያኔ እድሜ የተራዘመው የወጣቱ አለመደራጀትና በጋራ አለመቆም፤ እድሜ ጠገብ ፖለቲከኞች እኔ አውቃለሁ ባይነት፤ ጧት ተፈጥረው እንደጤዛ የሚበኑ፤ ስቪል ማኅበራት ነን የሚሉ ስብስቦች ወጣቱን ለማደራጀት ያላቸው ቁርጠኝነት አለመኖር ነው።
ይሁን እንጅ ዛሬ ወጣቱ አገሩን የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት በመረዳት የአያቶቹን ገድል ለመሥራት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን ግንቦት 2 2013 ያደረገውን የተቃውሞ ሕዝባዊ ሰልፍ ልብ ይሏል። በመሆንም ወጣቱ ለዴሞክራሲ፤ ለመልካም አስተዳደር ለዘላቂ ነፃነት ቆርጦ የተነሳ ስለመሆኑ ማንነቱንና አይበገሬነቱን ለወያኔ ለመንግሥት አሳይቷል።
አገራችን ቀደምትና የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌ ብትሆንም ዴሞክራሲያዊ የሆነ አስተዳደር ባለመኖሩ የሕዝቦች ሰባዊ መብት የተገደበ ነው። ከመሳፍንቱ፤ ከቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ እስከ ደርግ የግዛት ዘመን ድረስ ለዴሞክራሲና ለመልካም አስተዳደር ሲባል አገር ውስጥ የተለያዩ የተቃውሞ ትግሎች ተካሂደዋል። ነገር ግን ደርግ ወድቆ ወያኔ ኢሕአዴግ አዲስ አበባ እንደገባ አገር ውስጥ ይደረጉ የነበሩ የተቃውሞ ትግሎች ጠቅልለው ውጭ ወጥተዋል።
በውጭ የሚደረጉ የተቃውሞ ትግሎች ያለውጤት 22 ዓመታትን እያስቆጠሩ ይገኛሉ። በእርስ በርስ መናቆር ምክንያት ያለው መንግሥት ያለተቃዋሚ እንዳሻው አገሪቱን የመዘወር እድል እንዳገኘ አይካድም። በ1966 የተካሄደው ሕዝባዊ አብዮት እንደ ዛሬው ውጭ ሆነው በታገሉ ድርጅቶች አማካኝነት ሳይሆን የተገኘው ድል አገር ውስጥ በተደረገው ሕዝባዊ ተቃውሞ ነው።
የነፃነት ትግሉ ውጭ ሳይሆን አገር ቤት መሆን እንዳለበት በተለያዩ መጣጥፎቼ ገልጨ ነበር። ዛሬም አበክሬ የማምንበት አገር ቤት የሚደረገውን ትግል ነው። እንዳልኩትም በቅርቡ በሰማዊ ፓርቲ አማካኝነት የተደራጀው ወጣት 22 ዓመት የተራዘመውን ትግል ከሕዝቡ ጋር ለማቀናጀት እየሞከረ ያለው አገር ቤት በመሆኑ ነው።
የውጩ ትግል ከዲፕሎማሲና ከገንዘብ እርዳታ ያለፈ ዘልቆ እንደማይሄድ ከአገሪቱም ሆነ ከዓለም ተጨባጭ ሁኔታ መረዳት ይቻላል። ስለዚህ በውጭ እንደ አሸን የፈሉ ድርጅቶች ዲሲና አውሮፓ ሆነው በአገር ቤት መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጡ እንዳልቻሉ ልብ ሊሉት ይገባል። እውነታው ይህ ሆኖ እያለ አንዳንዶች በውጩ ትግል መኩራራትን ስለሚፈልጉ እውንቱን አምኖ ከመቀበል ይልቅ ለምን ተደፈርን በሚል አካኪ ዘራፍ የሚሉ መኖራቸው ሃቅ ነው። ቢሆንም ከዚህ አጉል ዝና የሚወጡበትን አእምሮ እግዚአብሄር ይስጣቸው ከማለት ያለፈ ሌላ የምለው አይኖርም።
የአገር ቤት ጠላት ሊንበረከክና ሥልጣን ለሕዝብ እንዲያስረክብ ከተፈለገ አገር ውስጥ ሆኖ እየታገሉ መስዋዕት መክፈል የሚያስፈልግ መሆኑ እርግጥ ነው። ወደፊት ትግሉ ቀጣይነት እንዲኖረውና ውጤት ለማምጣት ከተፈለገ የተለያዩ ፖለቲካ ድርጅቶች ከወጣቱ ጐን በመሰለፍ፤ በማደራጀት፤ የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ መስጠ ይጠበቅባቸዋል። በውጩ የሚኖረው ትውልደ ኢትዮጵያዊ/ ማኅበረሰብ የአገር ቤቱ ትግል እንዲጐለብትና ለውጤት እንዲበቃ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ሁሉ ዛሬም ይበልጥ ተጠናክሮ ለአገር ቤቱ ትግል የገንዘብና የሞራል ድጋፍ ማድረግ የሚጠበቅበት ይመስለኛል።
በመጨረሻም ሰሞኑን አባይን አስመልቶ የግብጽ መንግስት የሚያስተላልፋቸው ቱልቱላዎች እየተሰሙ ቢሆንም ለኢትዮጵያ አዲሲ ነገር አይደለም። ስለዚህ ድርጅቶችም ሆኑ አገር ወዳድ ወገኖች የመቻኮል ባሕሪ ሳያሳዩ ጉዳዩን በጥሞና ቢከታተሉት የሚሻል ይመስለኛል። ነገር ግን የምሁራን ጥናት በደንብ ሳይታከልበት በመጣደፍ በየድህረ-ገጾችም ሆነ በሬዲዮ ሊወጡ የሚችሉ መጣጥፎች ለትግሉም ሆነ ለአገራችን አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል እገምታለሁ። ይህን በተመለከተ ወደፊት የምለው ይኖረኛል።
ሁሉም ፊቱን ወደ ሀገሩ !!!!!!!!!!
የዶ/ር መሠረት ቸኮል አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
(ዘ-ሐበሻ) በቅርቡ ያረፉት ዶ/ር መሠረት ቸኮል ላለፉት 8 ዓመታት ሲለፉባት የነበረውና የኢትዮጵያን የ100 የፕሬስ ታሪክ የሚያሳይ መጽሐፍ ለገበያ መቅረቡን ቤተሰቦቹ ገለጹ። ጥልቀት ባላቸው ትንታኔዎቹና ቀላል አቀራረቡ የሚታቀው ጋዜጠኛና መምህር ዶ/ር መሠረት ቸኮል የጻፈው ታሪካዊው መጽሐፍ “The Quest for Press Freedom: One Hundred Years of History of the Media in Ethiopia” የሚሰኝ ሲሆን በamazon.com እንዲሁም በባርነስ ኤንድ ኖብል የመጽሐፍት መሸጫ መደብሮች እንደሚገኙ ቤተሰቦቹ ገልጸዋል።
ይህ መጽሐፍ ለማስተማሪያነት ሁሉ ታስቦ እንደተጻፈ የገለጹት የዶ/ር መሠረት ባለቤት ወ/ሮ በልዩ ወደፊት መጽሐፉን በአማርኛ ለማሳተም እንደተዘጋጁም ገልጸዋል። “ዶ/ር መሠረት ይህን መጽሐፍ በአማርኛም ጀምሮት ነበር። ሆኖም ግን በድንገት ሳጨርሰው በማረፉ ወደፊት አስተርጉመን ለማቅረብ እንሞክራለን” ያሉት ወ/ሮ በልዩ ይህን መጽሐፍ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲያነቡት ጋብዘዋል።
የዶ/ር መሠረት ቸኮልን መጽሐፍ ከኢንተርኔት ላይ ለመግዛት እዚህ ይጫኑ
በመጽሐፉ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለምትፈልጉ ወ/ሮ በልዩን በስልክ ቁጥር 651-983-2052 በመደወል ማነጋገር ትችላላችሁ።
ዶ/ር መሠረት ቸኮል ማን ነበር?
ከአባቱ ከአቶ ቸኮል ረታ እና ከ እናቱ ወ/ሮ የእናት ፋንታ አስረስ በ1950 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ ተወለደ። በአምስተኛው ዓመቱ በፈንጣጣ በሽታ ተጠቂ በመሆኑ በተደረገለት ህክምና ሕይወቱን ለማትረፍ ቢቻልም የዓይን ብርሃኑን የማጣት አደጋ በስምንት ዓመት ዕድሜው ደረሰበት። በሰበታ የዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ተከታትሏል። በተማሪነት ዘመኑ ለመዝሙርና ለሙዚቃ እንዲሁም ለመጽሐፍ የነበረው ፍቅር ከፍተኛ ነበር። በዕድገት በህብረት ዘመቻ በባህር ዳር ከተማ በመምህርነት ተመድቦ ግዴታውን ለመውጣት ችሏል። በ1971 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ጥናት ኢንስቲቱት በ እንግሊሽ ዲፓርትመንት ገብቶ በ1974 ዓ.ም ከጠቅላላው ተማሪ በላቀ ውጤት የዓመቱ ኮከብ ተማሪ ሆኖ ከወቅቱ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት እጅ የወርቅ ተሸላሚ በሆን የመጀመሪያውን ዲግሪ አገኘ።
ከዚያም Ethiopian Extrnal Service ተብሎ በሚታወቀው መስሪያ ቤት በጋዜጠኝነት ተቀጥሮ በሪድዮ ጣቢያው በየሳምንቱ የሚደረገውን የባህልና የሙዚቃ እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች የሚጋበዙበት የውይይት ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ በመሆን ያገለገለ ሲሆን ማዘር ትሬዛን በፕሮግራሙ ላይ ለማቅረብ የቻለ፤ በአነባበቡ፣ በፕሮግራሙ ጥልቀት፣ ታማናዊ በሆነ አቀራቡ የብዙ አድማጮችን ቀልብ የሳበ ነበር። በተለያዩ ሃጉሮች የተለያዩ ስልጠናዎችን ያገኘ ሲሆን ከቀይ ጨረቃ አፍሪካ አቀፍ የሬድዮ ፕሮግራም አምስት ጊዜ እውቅና አግኝቷል።
በ1982 ዓ.ም ከባለቤቱ ወ/ሮ በልዩ በላይ ጋር ህጋዊ ጋብቻ በመፈጸም በ1983 ዓ.ም የትምህርት ዕድል በማግኘቱ ወደ ሜኔሶታ በማቅናት የማስትሬት ዲግሪውን ጀምሮ በ1986ና በ1989 ዓ.ም የኮምዩኒከሽንና በፖለቲካል ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪውን፣ በ1991 እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪውን (PHD) በመገናኛ ብዙሃን ትምህርት ከዩኒቨሪሲቲ ሚኒሶታ አግኝቷል።
ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ በከፍተኛ ተምህርት ተቋሞች በማስተማር ሥራ ተሰማርቶ በዩኒቨርሲቲ ሚኒሶታ፣ በዊስካንሰን ሪቨል ፎል ዩኒቨርሲቲ፣ በኦሃዮ በሚገኘው አሽላንድ ዩኒቨርስቲቲ፣ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚቺጋን ከመምህርነት እስከ ተባባሪ ፕሮፌሰርነት አገልግሏል።
ከማስተማሩና ከምርምሩ ተጨማሪ የተለያየ ኮሚቴዎች አባልና ስብሳቢ በመሆን ሙያዊ ግልጋሎት ሰጥቷል። በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፊችን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች አቅርቧል። እንዲሁም ከአካዳሚ ጋር ያልተያያዙ ሁለት መፅፎችን ለአንባብያን አበርክቷል።
The quest for press freedom በኢትዮጵያ የ100 ዓመታት ሜዲያ ታሪክ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ሰጥቷል። ይህ መጽሐፉ በቅርብ ጊዜ በገበያ ላይ እንደሚውል ሕይወቱ ከማለፉ በፉት ለጓደኞቹና ለዘመድ አዝማድ አብስሯል። እንዲሁም ሁለት ለመጨረስ ያልታደላቸው ያሬድ ገብረሚካኤልና የዛሪኤይቱ ኢትዮጵያ ጽሁፎችን ለ Encyclopedia Aethiopica Vol.5 አዘጋጅቶ እንደነበር ይታወቃል።
ዶክተር መሠረት ከመምህርነትና ከምርምር ሥራዎቹ ባልተናነሰ መልኩ የሚታወቀው በሰባዊ መብት ተሟጋችነቱ፤ ለሃገሩ ባለው ቅናቂ አስተሳሰብና በተለይም ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በሚሰጠው ትንታኔ ነበር። በዚህ በሚኒሶታ የሚገኘው የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ የ እንግሊዘኛ ዜና በማዘጋጀት፤ በአሜሪካ ሬድዮ ጣቢአ የዘወትር ተባባሪ በመሆን፤ በ1995 ምርጫ ዘመን ድምጽ ላጡ ድምጽ በመሆን ጊዜውን፣ ገንዘቡን፣ ዕውቀቱን በመለገስ፣በተለይዩ ከተሞች በተናጋሪነት በመጋበዝ አስተዋጽሆ አድርጓል።
በ2007 በሜሪላንድ ተቀማጭ የሆነ የታዋቂ ግልሰቦችን ታሪክ የሚያጠናቅር ድርጅት በማቁቋምና የድርጅቱም ሊቀመንበር በመሆን አገልግሏል። በሕይወት ዘመኑ ብዙ ልጆችን የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ አድርጓል።
መሠረት በሥራው ላይ የማይኩራራ፣ ይህን አደረኩ ብሎ የማይናገር፣ እራሱን ዝቅ አድርጎ ከማንኛውም ሰው ጋር ተግባብቶ የሚኖር፣ ለ እውነት ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ እንደነበር በቅርብ የሚያውቁት ጓደኞቹ ይናገራሉ።
ባለፉት ሁለት ወራት የጉበት ካንሰር በሽተኛ መሆኑን ካወቀ በኋላ ከእራሱ ይቅል ለወገኖቹ በማሰብ ሌሎች ተገቢውን ምርመራ እንዲያከናውኑ ያሳስብ ነበር። ዶ/ር መሠረት ቸኮል በተወለደ 55 ዓመቱ ቅዳሜ ሕዳር ስምንት ቀን 2005 ከጠዋቱ 5am ላይ ህክምና ሲደረግለት በነበረው በፓርክ ኒክለት ሜተዲስት ሆስፒታል ባለቤቱን ወ/ሮ በልዩ በላይን፣ ልጁን ኤደን መሠረትን፣ ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን በመለየት ከዚህ ዓለም አልፏል።
ዛሬም እዚያው ነሽ ወይ (ሸንቁጤ፤ ከአዲስ አበባ)
በአቤ ቶኮቻው
ወዳጃችን ሸንቁጤ ከአዲስ አበባ ይቺን ጨዋታ ከላከልን ሶስት ቀን አለፈው በራሴ ጣጣ አዘገየሁት መዘግየት አልነበረባትም በሉ አሁንም በርዶ ሳይበርድ ፉት አድርጉልኝማ…!
ዛሬም እዚያው ነሽ ወይ
የዱሮ ግጥሞች መሰረታቸው የማይነቃነቅ፤ ትርጉማቸው ረቂቅ በመሆናቸው እወዳቸዋለሁ፡፡ለምሣሌ
እዚያው ነሽ ወይ ዛሬም እዚያው ነሽ ወይ
አስሮ የሚቀጣ ዘመድም የለሽ ወይ
ዛሬም እዚያው ነሽ ወይ?
ይህ የተባለላት መግባባት ተስኗቸው ከተለያዩ በኋላ እንቅፋት በመታ፤ አስደንጋጭ ነገር በተሰማ ቁጥር፤ ያንን የተፈታውን ባል ስም በመጥራት ለምትፎክር የተገጠመ ነው ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡እንዲያው በግርድፉ እንተርጉመውም ቢባል የቀረን ነገር ለሚያስታውሱና ባለፈው ላይ ለሚንጠላጠሉ፤ አለያም ተበልቶ ያለቀን እቁብ የሚመኙትን በተመለከተ የተገጠመ ነው ማለት ይቻላል፡፡
እኔ ደሞ ከግንቦት 25 በፊትና ከዚያም ተሻግሮ ገዢው ፓርቲና ባለስልጣናቱ ሲያዜሙት የነበረውን ያረጀ ያፈጀ፤ ለዛው የተሟጠጠውን፤ አድማጭ ጆሮ የነሳውን፤ የገረጣ ዘዴ አሁንም እንደገና እንካችሁ ማለታቸው ስላስገረመኝ ለነሱ የተገጠመ ነው አልኩ፡
ባለፈው 1997 ላይ የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ገዢው ፓርቲ ላይ ጭንቀት፤ ምጥ፤ መደነባበር በመፍጠሩ ሳቢያ በሰላማዊ መንገድ የምርጫ ካርዳችን ተሰረቀ በማለት የወጡትን ንጹሃን ዜጎች መሳሪያቸውን ወድረው ለመግደል ብቻ በወጡ ሰብአዊነታቸውን በጥቅምና በጊዜያዊ ድጎማ በለወጡ የጥፋት አርበኞች ተጨፈጨፉ፡፡
ከዚያ በማስከተል ደግሞ ግፍ በቃን፤ ባርነት ሰለቸን፤ መገፋት አስከፋን፤ ስደት መረረን፤ አንተም ገዢ ፓርቲ ሆይ! የሰለጠነ ፖለቲካ ማወቂያ ሕሊናህ ስለሻገተ፤ የማሰቢያ ሃይልህ በጥቅማ ጥቅም ስለተሸነገለና ስለተሰናከለብህ፤ የምትበድለው ሕዝብ ምሬት ያንገሸገሸው መሆኑን ባለማወቅህ በከንቱ ውዳሴ እየተሞኘህ ያለህ ነውና በቃሕ! በቃህ! ስትባል ማዳመጥ የሚሉት ባህል ስለሌለህ በቃህን እንደጋግመዋለን ያሉትን በሙሉ በእውር ድንብርብር ያወጣኸውን የሽብር አዋጅህን ጠቅሰህ ንጹሃን ለሃገርና ለወገን ተቆርቋሪዎችን አስረህ፤ ያም አልበቃ ብሎህ ያላዋቂ ሳሚ እንዲሉ በተደበቀ ካሜራና ቴፕ ቀርጸህ እንድናይ ያቀረብከው ‹‹አኬልዳማ››ህ ክስረትህን እንጂ ሌላ ያሳየው አንዳችም ጉዳይ የለም፡፡
ያም አልበቃህ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንንና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያንን ማምለኪያ ቦታቸውን ‹‹ለልማት›› በሚል ልታፈርስ በመነሳትህና፤ሙስሊም ኢትዮጵያውያንም በሃይማኖታቸው ጣልቃ ገብተህ የማይፈቅዱትንና ያልመረጡትን አስተምህሮ ከድንበር ማዶ አምጥተህ የነበረውን አፍርሳችሁ በዚህ መንገድ ሂዱ በማለትህ ‹‹ምን ጥልቅ አርጎህ›› በማለታቸው ተቃውሟቸውን እንደድፍረት በማየት ትንኮሳህን አባብሰህ የማይጠፋ እሳት ለኩሰህ አስካሁንም ድረስ በመደከር ላይ ነህ፡፡
ያንንም ሁኔታ በተመለከተ በፈረደበት የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ሌላ ካለፈው ተመሳሳይ ዳማ ጨዋታህን አኬል ብለህ ስታቀርብ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ለዚህ ነው ‹‹ዛሬም እዚያው ነህ ወይ››ን ያነሳሀት፡፡
ገና ግጥሙን አስታውሼ ሳልጨርስ ግንቦት 25 ደረሰና ‹‹ማንም አይወጣላቸውምና ፍቀድ!›› በሚል ትዕዛዝ ተፈቀደው ሰልፍ ተካሄደ፡፡ መንግስታዊ ግብር በላ ጋዜጠኞች ከቢሯቸው ሳይነቃነቁ ነው ‹‹በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊ ባለመገኘቱ ጠሪዎቹ ይህን ዘገባ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ከመነሻ ጣቢያቸው……….›› ብለው አረፍተ ነገሩን ሳይጨርሱ በአሰርት ሺህ የሚቆጠረው ሰልፈኛ ‹‹ኢትዮጵያ ሃገሬ!›› በማለት ድምጹን ከፍ አድርጎ በመዘመር ሲተም በጋዜጠኛው ቢሮ ብቻ ሳይሆን በኮሙኒኬሽን ቢሮ መስኮቶች ደርምሶ በመግባት የገዢውን ሎሌዎች ጋኔል እንደሰፈረበት ሕመምተኛ ከየወንበራቸው እየፈነቀለ ያስበረገጋቸው፡፡
በዚህን ጊዜ ነው ሽመልስ ከማል ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠትና ባላየው ግን በሃይለኛ ‹‹ኢትዮጵያ ሀገሬ›› ዜማ ባስደነበረው ድምጽ በመናደድ ሰበብ አስባብ መደርደር የጀመረው፡፡ ሰልፉ ሳይጠናቀቅ ገና በሂደት ላይ ሳለ ነው የሽመልስ ከማልና የሬድዋን መግለጫ ለቴሌቪዢናቸውም ለሬዲዮናቸውም የተሰጠው፡፡
እዚህ ላይ የላይኛውን ግጥም ደጋግሜ አልኩት ሳቅ እያፈነኝ፤ ትዝብት እያደረብኝና ምኖቹ ናቸው የሚመሩን እያልኩ በማዘን፡፡
የሚገርመው ጉዳይ ሽመልስ ከማል በሰልፉ ላይ ሙስሊሞች ተሳትፈዋል፤ ብሎ ሲጸልዩ ማሳየት ምን ለማለት ነው? ክርስቲያኖች በጠሩት ሰልፍ ላይ ሙስሊሞች ተሳተፉ ለማለት ነው ወይስ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች በአንድ ላይ ለአንድ ሃገር ክብር ለአንድ ሕዝብ እኩልነት ለዴሞክራሲ፤ ለፍትሕ፤ ለነጻነት አብረው መቆም አይችሉም ተብሎ የታወጀ አለ እንዴ? ሙስሊሙና ክርስቲያኑ እኮ ለዘመናት አብረው የኖሩ፤ በችግራቸው ሲረዳዱ፤ በደስታቸው ሲጠራሩ፤ የኖሩ ናቸው፡፡ አንዱ የሌላውን ሃይማኖት አክብሮ በመተሳሰብና በመከባበር ዘመናት አሳልፈዋል፡፡ ይሄንን ደግሞ ሽመለስ ከራሱ ስም አወጣጥ ጀምሮ ሊገነዘበው የሚገባ ጉዳይ ነበር አልሆንልህ አለው እንጂ፡፡ እርግማን ይሰራል ከተባለም የአቶ ከማል እርግማን ሰርቶላቸዋል፡፡ የሰው ፍቅር ይንሳህ ብለውት ነበርና ይሄው እሳቸው ባይኖሩም እኛ እያየንላቸው ነው፡፡
ግራም ነፈሰ ቀኝ ወጣቱ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪው ተሰምቶለት፤ ፕሮግራሙ ሰምሮለት፤ ምኞቱ ተሳክቶለት፤ ሰልፉ ደምቆለት፤ ሠላማዊ መሆኑ ተረጋግጦለት ጠጠር ኮሽ ሳይል፤ ዝናብም ጠብ ሳይል ፖሊስም ስርአት ሳይጥስና ‹‹የገዢውን ስም በክፉ›› ያነሳ ብሎ ሳይደነፋ በሰላማዊ መንድ ተጠናቆ ሁሉም እየዘመረ ተሰባስቦ እየዘመረ ተሰነባበተ፡፡
ታዲያ ከምኑ ላይ ነው የነሽመልስና ረድ ዋን አካኪ ዘራፍ የተፎከረበት፡፡ ምን ተደረገ ነው የሚሉን? ባንዲራውን እናውጣ አታወጡም ክርክርና ትግል የጀመሩትም ተልከው የመጡ ሽብር ፈጣሪዎች ስለነበሩ የቴሌቪዠዥን ካሜራም ጀምሩ ስላላቸው የፈጠሩት ለመሆኑ ማስረጃ የማያስፈልገው የተለመደ አካሄድ ስለሆነ ማንም አልተቀበለውም፡፡
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ቢሆን በሽታ ስላለበት ተቃዋሚዎች ፕሮግራም ላይ የሚገኘው ‹‹ካንዲድ ካሜራ›› ፕሮግራም ለማንሳት ስለሆነ ያንኑ አድረጓልና አለቆች ሽላማት ቢጤ ቢጥሉለት መልካም ነው፡፡ለመሆኑ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጥሩና እውነት ሆነን ነገር እንዳያነሳ ተብሎ በቻይና የተገጣጠመ ይሂን እንዴ፡፡ ልብ ብላችሁ እንደሆነ ስንት ጸአዳ ልብስ የለበሰ ሰው ባለበት እንደምንም ብሎ ያለቀና የተቀዳደደ ልብስ ማንሳትን ይመርጣል፡፡ስንት እውነት በሚነገርበት ቦታ ተጠምዶ እንደምንም ቅጥፈት ፈልጎ ይቀርጻል፡፡ አያሰዝንም?
በዕለቱ የተፈራው የተደፈረበት፤ የተዘጋው የተከፈተበት፤ የታሰበው የተፈጸመበት፤ ሠላም ተብሎ ሠላም የነገሰበት፤ እኩይ ድርጊት ፈላጊዎች ያሰቡት የከሸፈበት፤ ያልጠበቁት የወጣት አርበኛ የተመመበት፤ ዕለት ነበር፡፡ ወጣቱ አሁንም ለውጥ ፈላጊነቱንና ለለውጥ መነሳሳቱን በተግባር አሳይቷል፡፡ ከእንግዲህ በሚታቀደው ሠላማዊ እንቅስቃሴ ሚያዝያ 30/1997ን መድገም ሳይሆን ያ ዕለት የያዘውን ክብረወሰን መስበር ነው መሆን የሚጠበቅብንና ወጣቱ ጎን በመቆም የወጣቱን ሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ ለመተግበር ዝግጁ እንሁን፡፡ በየጓዳችን ቁጭ ብለን ማውራት ጠቀሜታ ስለሌለው ሁላችንም ለነጻነት፤ ለዴሞክራሲ፤ ለሰብአዊ መብት መከበር፤ ለፍትሕ የበላይነት፤ አብረን እንቁም፡፡
አንዳንድ አልኩ ባዮች እራሳቸው ከፍርሃት ለመላቀቅና የተካሄደው የሰማያዊ ፓርቲ ሠላማዊ ሰልፍ ሕዝባዊ አጀንዳ መሆኑንና ዘር ሃይሞኖት ፆታ ሳይለይ ኢትዮጵያዊ የሆነና መገዛት ያንገፈገፈው፤ ኑሮን መግፋት የተሳነው፤ መብቱ የተደፈረበት፤ ፍትህ የተነፈገ፤ የዴሞክራሲ መብት የተነፈገ ወንድ ሴት ትልቅ ትንሽ ሳይል ሁሉም እንዲወጣ ማለታቸውን ቸል በማለት በብዛት የወጡት ሴቶች ናቸው፤ የሙስሊሙ ቁጥር በዛ፤ የሰማያዊ ፓርቲ አባሎች ምነው አነሱ በማለት ከቤቱ ቁጭ ብሎ ቡናውን ሲያንቃርር የዋለ ሁሉ ለትችት ቀደም ቀደም ይላል፡፡ለመሆኑ ይህን መሰሉ ሕዝባዊ ጥሪ ማንንም ከማንም አይለይም ሲባል ለምን ተብሎ ነው በሃይማኖት በፆታ እየመዘኑ በዛ አነሰ ማለት ያስፈለገው፡፡ ይቺ ተልእኮ ያላት አካሄድ ስለሆነች አድማጫ አታገኝም እዚያው መንደር ተቦክታ ሳትጋገር ኮምጥጣ ትደፋለች፡፡
ግንቦት 25 የማይረሳ ሆኖ ባለፈ ማግስት ደግሞ የገዢው ፓርቲ ቅርሻቶች እነ ሰራዊት ፍቅሬ ሌላ ሴራ አውጠንጥነው ቀርበዋል፡፡ አርቲስቶችና ጋዜጠኞች ወደጂጂጋ ወርደው የሶማሌን ክልል ጎበኙ ለልማት ቃል ገቡ፤ ምኑ ቅጡ፡፡ በሰሞኑ ሙስና ለእስር ከተዳረጉት መሃል በጥላቻ የተወነጀሉ እንደመኖራቸው ያህል በምርም የተጠረጠሩበትን ፈጽመው የተከሰሱ መኖራቸው ግልጽ ነው ባይባልና ሊደመደም ባይቻልም በሂደት የምናየው ሆኖ ሠራዊት ፍቅሬ መዘለሉ ግን ብዙውን ያስገረመ ጉዳይ ነው፡፡
ሠራዊት ምልጃና ጉዳይ ማስፈጸምን እንደቋሚ ስራው፤ ግን በከለላ የሚያካሂደው የሙስና ሽምቅ አቀባባይ ድልድይ ለመሆኑ አቃቤ ሕግ ቢሮ ያሉ በርካታዎቹ የሚያውቁት ነው፡፡ ሠራዊት እኮ ግንባር ቀደም የአርቲስቶች ተጠሪ እንዲሆን በሹመት መልክ የተሰጠው ቦታ እንጂ ባለሙያዎቹማ ምን አውቀው፡፡ ብቻ ዝም ብለው በፍርሃት ሲጠራቸው እየተንጋጉ ይሄዳሉ፤ ምነው ሲሏቸው ከጀርባው ያሉት ሴት ሃይላቸው ከፍተኛ በመሆኑ ይላሉ፤ ማን ባለቤቱ ሲባሉም እንዲያውም ዋናዋ የነበሩት ሴት እንጂ፤ ይላሉ፡፡ ስም አይጠሩም በደፈናው ነው የሚናገሩትም የሚፈሩትም፡፡ ለነገሩ ይህን ማከናወን ከነበረበትም መከናወን ያለበት በየሙያ ማሕበሩ ሲሆን ሠራዊት ጥልቆ በመን ደንብና ሕግ ዘው እንዳለ ሲታሰብ ከገዢው ፓርቲና ከባለስልጣናቱ ለወንጀል ማካካሻ እንዲሆን የተሰማራበት ቦታ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ሰይፉ ፋንታሁን፤ ሙሉዓለም ታደሰ፤ተስፋዬ አበበ፤ አበበ ባልቻ፤ጌትነት እንየው፤……….ሌሎችም አንድ ሕበረት ፈጥረው በመታደም ገዢውን ፓርቲ ለማገልገል ተማምለው የቆሙ ስለሆኑ በተጠሩ ቁጥር እጥፍ ዘርጋ በማለት ሕዝብን ክደው፤ ሃገርን ዘንግተው፤ ራሳቸውን በማስቀደም ለሆዳቸው አድረዋል፡፡ ሲነጋስ ምን ይሉን ይሆን?
ጊዜ ምስክር ሆኖ ለማየት ያብቃን፡፡
ሌላው እንዳይታወቅበት አድብቶ ዋነኛ አቀንቃኝ በመሆን ከአዜብ መስፍን ጉያ በመወሸቅ ማንኛው ነጋዴ ምን አደረገ፤ ምን አተረፈ፤ ምን አዘዘ ከውጭ ምን አስመጣ፤ እነማን ምን እያደቡ ነው የሚለውን በሽምቅ እያሰባሰበ ዕለት ተዕለት ሪፖርት በማቅረብ ቀደም ብሎ ተቀራርቦ ጥቅሙን በማስጠበቅና ባለሙያውን ሁሉ በተለይም በቪዲዮ ፕሮዳክሽን በኩል ሲኒማ ቤቶችን ማዘዝና ፕሮግራም በማሰረዝ የራሱ ብቻ እንዲታይ፤ የራሱን ፊልሞች ሲያዘጋጅም አስፈላጊውን ሁሉ ያለ ችግር እንዲመቻችለት ቀጭን የትዕዛዝ ሰነድ በጉያው ያነገበው፤ በኤግዚቢሽን አዳራሽ ያለውን የሴቫስቶፖልን የፊልም ማሳያ እንደንብረቱ እንዲያዝበትና በጣም አነስተኛ ክፍያ ብቻ ከፍሎ እንዲረከበው የተመቻቸለት ቴዎድሮስ ተሸመ የተባለው ፍቅር ሲፈርድ፤ ቬጋስ ወይስ አባይ፤ እና ሌሎችንም የቪዲዮ ፊልሞች በአዘጋጅነትና በፕሮዲዩሰርነት ያቀረበው ነው፡፡
ቴዎድሮስ ከወ/ሮ አዜብ ጋር ባለው የጠበቀ ቁርኝት ወ/ሮ አዜብ የኤይድስ መቆጣጠርያ ቢሮ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በሚሰየሙበትና በርከት ያለ የውጭ ምንዛሪ እርዳታ ለተጠቂዎች እንዲውልና ለመከላከል ተብሎ ለሚነደፍ ፕሮግራም ማካሄጃ እንዲሆን የታቀደውን ገንዘብ ቴዎድሮስ እንደልቡ እንዲገለገልበት መንገዱ የተመቻቸለት ለሆዱ ያደረና በስውርም ራዊት ፍቅሬ ጋር ግንባር ፈጥሮ ለወያኔ አገልግለ፤ት አበርካችና ሰብቀኛ ነው፡፡
ብዙ በጥበብ ስም ጥበበኛውን በሽርፍራፊ ክፍያ እየገዙ የራሳቸውን ገቢ የሚያዳብሩ ስለ ጥበብም ሆነ ስለ ጥበበኛው አንዳችም ደንታ የሌላቸው ከሚጨበጠው በርካታ ቁጥር ገንዘብ ተርፎ የሚንጠባጠበውን በመላስ እራሳቸውን ለባርነት ያስገዙ ሞልተዋል ወደፊት ማን ምን እንዴት በሚል ዘርዘር ተደርጎ እስኪቀርብ ለመነሻ ያህል ይህን ካልኩ ዘንዳ፤
ከስንብቴ በፊት ግን አንድ መሰረት ያለው ጥያቄ ላንሳና መልስ የሚሰጥ ካለ ልጠብቅ፡፡
ለመሆኑ ሠማያዊ ፓርቲ ጥሪ ያደረገላቸውና በዚህ ሕዝባዊና ሃገራዊ በሆነው ሠላማዊ የትግል ሰልፍ ላይ አብረን እንቁም ያላቸው የየተቃዋሚ ድርጅቶች አባላትና አመራሮች በዕለቱ የት ገቡ?
ተቃዋሚ ድርጅቶቹ አባላት ሌላው ቢቀር በአደባባዩ ተገኝተው የድጋፍ ንግግር ለማድረግ አለመብቃታቸው ምናልባት ገዢው ፓርቲ ፈቅዶ አደጋ የጣለ እንደሁ ብለው ይሆን በየቤታቸው የመሸጉት?
ከሰልፍ በኋላ አንዳንዶቹ መግለጫ ሰጥተዋል ሲባል ሰማሁ ዕለቱ ካለፈና ክንዋኔው ተስፋ ያሳየ፤ ጥንካሬን ያረጋገጠ፤ ሲሆን የዚያ አካል ለመሆን ነው መግለጫው?
እስቲ ይህ የገባው ካለ ቢያስረዳኝ!
“ቤቲ አዋረደችን!” ከያሬድ አይቼህ
ኢትዮጵያዊቷ ቤቲና ፥ ቢግ ብራዘር አፍሪካ 2013 (Big Brother Africa 2013) በሚባለው የቴሌቪዥን ትርዒት ላይ ፥ ሴራሊዮናዊው ቦልት ያደረጉትን ‘ወሲብ’ ያዩ ሰዎች “ቤቲ አዋረደችን” ሲሉ ሰማሁ። ለመሆኑ ምናችን ነው የተዋረደው? ከየት ወዴት ነው የወረድነው? ክብር እና ውርደት አንጻራዊ ቢሆኑም ፡ መጠን ግን አላቸው። ቤቲ ኢትዮጵያውያንን ከዬት ወዴት እንዳዋረደችን አልገባኝም። ለመሆኑ ኢትዮጵያውያን ክብር አለንን?
ክብር
በምግብ ራሳችንን ያልቻልን ህብረተሰብ ከመሆናችን የተነሳ በእርዳታ ድጎማ የምንኖር ህዝብ መሆናችንን አንርሳ። ከዛ አልፎ መንግስታቸን በአመት 2 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ያገኛል። ያለዚያ ድጎማ የኢትዮጵያ መንግስት በአጭር ጊዜ ተንኮታኩቶ ሚወድቅ ነው።
ከስደተኛም ስደተኞች ፡ ከድሃም ድሆነች ፡ ከኋላቀርም ኋላቀሮች መሆናችንን ረስተን ‘ቤቲ አዋረደችን’ ማለቱ የአስተሳሰብን አለመደባር የሚያመላክት ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ኢትዮጵያውያን ኋላቀርነታችን በአስተሳሰባችን ከሚንጸባረቅባቸው መንገዶች አንዱ ስለራሳችን ባለን የተሳሳተ ፡ በሃሰት ላይ በተመረኮዘ ራስን ማግዘፍ ነው። ይህ ራስን ማግዘፍ ለህብረተሰባችን መሰረታዊ ችግር ነው ብዬ አምናለሁ።
ክህደት
አንድ ህብረተሰብ ክቡር ሳይሆን ክቡር ነኝ ብሎ ካመነ ለብዙ ችግሮቹ መፍትሄ የማግኘት አቅሙ የጠበበ ይሆናል። ለምሳሌ፦ አንድ በጠና የታመመ ሰው ፡ ሃኪም ጋር ሄዶ ሃኪሙ “በጠና ታመሃል ፡ ይሄን መድሃኒት ውሰድ” ብሎ የመከረውን ምክር “እኔ ጤነኛ ነኝ” በማለት ችላ ቢል ፡ በሽተኛ መደየሙ አይቀሬ ነው።
ኢትዮጵያውያን ያልሆነውን ነን ከምንልባችው ምክንያቶች አንዱ ካለንበት የተዋረደ አገራዊ ፡ ማህበራዊ ፡ ኢኮኖሚያዊ እና አጠቃላይ መንፈሳዊ አዘቅጥ የተነሳ ከሚሰማን ጥልቅ ስለልቦናዊ ውርደት የተነሳ ይመለስለኛል። ሰዎች በክህደት አስተሳሰብ የሚዘፈቁት ያሉበትን ሁኔታ መቀበሉ እጅግ በጣም ቅስማቸውን ስለሚሰብር ነው።
የግለሰብ ነጻነት
የቤቲና ቦልትና ጉዳይ የህብረተሰባችንን የመንጋ አስተሳሰብም በግልጽ ያሳያል። ኢትዮጵያውያን ለግለሰብ ነጻነት የምንሰጠው ቦታ በጣም ትንሽ ነው። ሰዎች ግላዊ እንዲሆኑ ሳይሆን መንጋዊ እንዲሆኑ ከፍተኛ ጫና ይደረግባቸዋል። በአገራችን “ብቻውን የበላ ፡ ብቻውን ይሞታል” የሚሉት የድህነት ፍልስፍናዎች አሁንም በሰፊ አሉ።
ቤቲ የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት አይደለችም። ቤቲ አንድ ግለሰብ ናት። የፈለገችውን የማድረግ አቅምና መብት ያላት ጎልማሳ ሰው ናት። ቤቲ ኢትዮጵያዊ ናት ማለት የኢትዮጵያ ንብረት ናት ማለት አይደለም። ግን ይሄ ጉዳይ የፆተኝነትም ጉዳይ ጭምር ይመስለኛል። ቤቲ ሴት በመሆኗ ነው ይሄ ሁሉ ትቺት የደረሰባት። በአገራችን ሴቶችን እንደ ንብረት የማየቱ ዝንባሌ አሁንም የተንሰራፋ እምነት ነውና።
ጉዳዩ ግን በአንድ ኢትዮጵያዊ ወንድና በአንዲት አፍሪካዊት ሴት መካከል ቢሆን ኖሮ ፡ የ“ቤቲ አዋረደችን” አይነት ትችት በብዛት አንሰማም።
ታዲያ ቤቲ ምን አደረገችን? እሷ ያደረገችው ቦልትን እንጂ።
- – - – - – - – -
አስተያየት ፡ ትችት ምናምን በዚህ ይላኩልኝ፦ yared_to_the_point@yahoo.com
EHSNA 3rd Annual Festival 2013
ኢትዮጵያ በግብፅ ላይ ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃ ለመውሰድ 1ሺ 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል መታጠቅ ብቻ ይበቃታል
በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምርጫ እንዲሳተፉ ሊደረግ ነው
በዘሪሁን ሙሉጌታ
በተለያዩ የውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ዜጎች በሀገሪቱ በሚካሄዱ የምርጫ ስርዓት በመሳተፍ ድምፅ እንዲሰጡ ሊደረግ ነው።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ህግና ደንብ መሰረት በአረብ አገራት ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በሌሎች አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምርጫ መምረጥ የሚችሉበት ዕድል እየተመቻቸ ነው።
በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ተሊል ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ምርጫው የሚከናወነው የሀገሪቱን አቅም ባገናዘበ ሁኔታ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚገኙባቸው ማዕከላት ውስጥ የምርጫ ጣቢያዎችን በማደራጀት ዜጎቹ ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን እንዲወጡ ይደረጋል ብለዋል።
አዲስ የተዘጋጀው የዲያስፖራ ፖሊሲ ካካተታቸው ዋና ዋና ጉዳዮች አንዱ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምርጫ እንዲሳተፉ ማድረግ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ቅዳሜ ሰኔ 8 ቀን 2005 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የዲያስፖራ ፖሊሲ ላይ በውጪ ሀገር ከሚኖሩ፣ ቁጥራቸው ከአንድ ሺ እስከ ሁለት ሺ ከሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር በፖሊሲው ላይ ምክክር እንደሚካሄድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም።n
ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ጁን 12 ቀን 2013 ዕትም
ኮንዶሚኒየም ፎቅ ላይ የወጣውን ጅብ ለማስወጣት በተከፈተ ተኩስ አንድ ወጣት ቆሰለ
በሐያት ኮንዶሚኒየም ሶስተኛ ፎቅ ላይ ወጥቶ አልወርድም ያለውን ጅብ ለማስወጣት በተተኮሰ ጥይት አንድ ወጣት ቆስሎ ሆስፒታል ገባ።
በህንጻው ላይ የሚኖሩ የአይን እማኞች እንደገለፁት፤ ከትናንት በስቲያ ከምሽቱ አራት ሰዓት ገደማ ወደ ህንጻው በማምራት ሶስተኛ ፎቅ አንድ መኖሪያ ቤት በር ላይ የተኛውን ጅብ ትላንት ለማስወጣት አምስት ጥይቶች ተተኩሰው ጅቡ የተገደለ ሲሆን፤ በአካባቢው የነበረ አንድ ወጣት በነጠረ ጥይት ሆዱ ላይ ተመትቶ ሆስፒታል ገብቷል። ፎቁ ላይ የወጣው ጅብ እስከ ትናንት ከረፋዱ አራት ሰዓት ገደማ ድረስ እዚያው ፎቁ ላይ መቆየቱን የተናገሩት ነዋሪዎቹ ጅቡን እንዳዩት በማስፈራራት ለማስወጣት ቢሞክሩም አልቻሉም። ነዋሪዎቹ ለፖሊስ ስልክ ደውለው ያሳወቁ ሲሆን፤ ፖሊስም “ለአካባቢ ጥበቃ በስልክ ጉዳዩን አሳውቀናል” በማለቱ ጅቡ እዚያው ሊያድር ችሏል።
ጅቡ በህንጻው ላይ እስካለበት ጊዜ ድረስ ፎቁ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች ከቤታቸው ሳይወጡ መቆየታቸውን የገለፁ ሲሆን፤ ትናንት ጠዋት ላይም አንዳንድ ወላጆች በዱላ እና በአንዳንድ ነገሮች ጅቡን እየተከላከሉ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላካቸውን ገልፀዋል። ጅቡ በህንፃው ላይ ሌሊቱን ሙሉ በማሳለፉ ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ሆነው ማደራቸውን የገለፁት የህንጻው ነዋሪዎች፤ ጅቡ ከቦታው እስከተነሳበት ሰዓት ድረስም እንደልባቸው በህንጻው ላይ ለመንቀሳቀስ መቸገራቸውን ገልጸዋል። በህንጻው ላይ እንዲህ አይነቱ ነገር ሲፈጠር ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የገለፁት ነዋሪዎቹ፣ በሁኔታው በጣም መደናገጣቸውን ገልጸዋል።
ጅቡ በህንጻው ላይ ሌሊቱን ሙሉ ካሳለፈ በኋላ እስከ ትናንት ረፋድ አራት ሰዓት ድረስ እዚያው የቆየ ሲሆን፤ አራት ሰዓት ተኩል አካባቢ በፖሊስ አማካይነት በአምስት ጥይቶች ተገድሎ ከህንጻው ላይ ሊወርድ ችሏል።n
(ምንጭ፡-ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 405 ሰኔ 5/2005)
Sport: የመሠረት ደፋርና ገንዘቤ ዲባባ የኦስሎ ፉክክር ዛሬ በጉጉት ይጠበቃል
ከቦጋለ አበበ
ከረጅም ርቀት ንግሥቶች መካከል አንዷ የሆነችው መሠረት ደፋር ከወጣቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ጋር በዛሬው የኦስሎ ዳይመንድ ሊግ ጠንካራ ፉክክር ታደርጋለች ተብሎ ተገምቷል፡፡ ሁለቱ አትሌቶች በአምስት ሺ ሜትር የሚያደርጉት ፉክክር ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው ሆኗል፡፡
መሠረት በአምስት ሺ ሜትር ርቀት የዓለም ቁጥር አንድ አትሌት መሆኗ አያጠያይቅም፡፡ ይሁን እንጂ በተለያዩ ርቀቶች ድንቅ አቋም ይዛ ብቅ ያለችው ወጣቷ አትሌት ገንዘቤ ዘንድሮ መሠረትን ሁለት ጊዜ አሸንፋታለች፡፡ አትሌት መሠረት ደግሞ ክብሯን ለማስጠበቅ ብርቱ ጥረት የምታደርግ በመሆኗ የዛሬውን የዳይመንድ ሊግ ፉክክራቸውን ጠንካራ ያደርገዋል ተብሎ ተገምቷል፡፡
መሠረት ባለፈው ለንደን ኦሊምፒክ አስደናቂ ብቃት በማሳየት ከስምንት ዓመት በኋላ የአምስት ሺ ሜትር የቀድሞ ክብሯን ማስመለስ ችላለች፡፡ ይህም መሠረትን የርቀቱ ንግሥት መሆኗን ያስመሰከረላት ሆኗል፡፡ መሠረት በዛሬው ውድድርም ለንደን ኦሊምፒክ ላይ ያስመለሰችውን ክብሯን ትደግማለች የሚል ግምት እንዲሰጣት አድርጓል፡፡
በኦስሎ ዳይመንድ ሊግ ላይ የወጡ የተለያዩ ዘገባዎች የውድድሩ አሸናፊ ማን ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ አልሰጡም፡፡ ይሁን እንጂ መሠረት በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ በገንዘቤ ከተቀደመች በኋላ ሰፊ የልምምድ ጊዜ ስላገኘት አቋሟን አስተካክላ ወደ ውድድር እንደምትገባ ተገምቷል፡፡
ምሽት ላይ ቢስሌት ስታድየም ውስጥ በሚካሄደው በዚህ ውድድር በርቀቱ ሁለት የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ የቻለችው መሠረት የተለየ ብቃት ይዛ ብቅ እንደምትል የስፖርቱ ተንታኞች እምነት አላቸው፡፡
ገንዘቤ በውድድሩ ብቃቷ ቀንሶ ትቀርባለች የሚል እምነት ባይኖርም ሰሞኑን በተለያዩ ርቀቶች እንደመሳተፏ መጠን ድካም ስለሚኖርባት መሠረትን እስከ መጨረሻ መታገል ላይሆንላት ይችላል ተብሎ ይታመናል፡፡ በዚህም የተነሳ መሠረት የገንዘቤን ድካም ተጠቅማ የማሸነፍ እድል አላት፡፡
አትሌት መሠረት በአምስት ሺ ሜትር ከገንዘቤ የተሻለ ትልቅ ስም አላት፡፡ ከሁለት የኦሊምፒክ ድሎቿ በተጨማሪ አራት የዓለም ሻምፒዮና ሜዳሊያዎች(አንዱ የወርቅ ነው)፣ ስድስት የዓለም የቤት ውስጥ ሜዳሊያዎች (አራቱ የወርቅ ነው) እንዲሁም አራት የአፍሪካ ሻምፒዮና ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ ችላለች፡፡
እ.ኤ.አ 2007 ላይ መሠረት የርቀቱን የዓለም ክብረወሰን ኦስሎ ላይ ወደ 14፡16፡63 ማሻሻሏ ይታወሳል፡፡ በወቅቱም የመሠረት የአጨራረስ ብቃት በርካታ ደጋፊዎች እንድ ታፈራ አስችሏት ነበር፡፡ በዛሬው ውድድርም መሠረት ቢስሌት ስታድየም ውስጥ በርካታ ደጋፊዎች እንደሚኖሯት ይጠበቃል፡፡
መሠረት በወጣቶች ሻምፒዮና የርቀቱን ክብረወሰን ከአንድም ሁለት ጊዜ ያሻሻለች አትሌት ነች፡፡ በአሁኑ ወቅትም የሦስትና አምስት ሺ ሜትር የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ባለክብረወሰን ነች፡፡ ይህን የመሳሰሉት እውነታዎች ከመሠረት የርቀቱ ልምድ ጋር ተዳምረው የአሸናፊነት ሚዛኑ ወደ እርሷ እንዲያደላ ያደርጋሉ፡፡
በአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር የቀድሞ ጓደኛዋ አበባ አረጋዊን እየተፎካከረች የምትገኘው ገንዘቤ፣ በዘንድሮ ዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በሁለት ዓይነት ርቀቶች በመሳተፍ የእህቷ ጥሩነሽ ዲባባ ተተኪ እንደምትሆን አሳይታለች፡፡
ገንዘቤ የውድድሮች መደራረብና ድካም ከሌለባት የሻንጋዩን ድሏን በመድገም መሠረት ላይ የበላይ እንደምትሆን ይጠበቃል፡፡ ገንዘቤ ይህን ውድድር ካሸነፈች በዳይመንድ ሊግ በአምስት ሺ ሜትር የሚኖራት የነጥብ የበላይነት ከፍ ይላል፡፡
በዓለም ወጣቶች የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር ቀዳሚ ሆና በማጠናቀቅ የአገራችንን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ማድረግ የቻለችው ገንዘቤ በመካከለኛና ረጅም ርቀቶች አመርቂ ውጤት እያስመዘገበች መሆኗ የተለየች አትሌት ያደርጋታል፡፡
የዛሬው ውድድር የመሠረትና ገንዘቤ ፍጥጫ ብቻ ሳይሆን የኬንያውያን አትሌቶች ጭምርም እንደሆነ የተለያዩ ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡ ኬንያውያን አትሌቶች በተለይም በለንደን ኦሊምፒክ በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተወሰደባቸውን የበላይነት ለማስመለስ ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
በለንደን ኦሊምፒክ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩ የኬንያ አትሌቶች በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል መነሳታቸውን ተከትሎ ትልቅ ቁጭት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ይህን ቁጭታቸውን የሚወጡበት ውድድርም በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ የዛሬው ውድድር የቁጭታቸው መወጫ ከሚሆኑ ውድድሮች መካከል ሊካተት ይችላል፡፡
በዛሬው ውድድር የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮኗ ሜርሲ ቺሮኖ በውድድሩ ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብለው ከሚገመቱ ኬንያውያን አትሌቶች መካከል አንደኛዋ ነች፡፡ በሌላ በኩል የአገሯ ልጅ ቪዮላ ኪቢዎት የውድድሩ ተካፋይ መሆኗ ፉክክሩን ጠንካራ ያደርገዋል፡፡
Health: በእንቅልፍ ልቤ ከብልቴ የሚወጣውን ፈሳሽ እንዴት መቆጣጠር እችላለሁ?
(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 51 ላይ ታትሞ የወጣ)
ጂቲ እባላለሁ፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ፡፡ ዋነኛ ችግሬ ምን መሰላችሁ? በእንቅልፍ ልቤ በተደጋጋሚ የዘር ፍሬዬ እየፈሰሰ ተቸግሬያለሁ፡፡ ይህ ችግር በተደጋጋሚ መከሰት ከጀመረ አንድ ዓመት ይሆነኛል፡፡ በሳምንት ቢያንስ ሶስት ቀን ይህ ችግር ይከሰትብኛል፡፡ ሁሌም ከእንቅልፌ ስነቃ በተደጋጋሚ የሌሊት ልብሴ፣ የውስጥ ሱሪዬ እና አንሶላዬ ረጥቦ እና አልጋዬ ባልተለመደ ጠረን ታውዶ አገኘዋለሁ፡፡ ይህ ነገር ደግሞ ለሀፍረት ስሜት ያጋልጠኛል፡፡ ለራስ ምታት ህመምም ይዳርገኛል፡፡ ገና ተማሪ ስሆንኩ እስካሁን የሴት ጓደኛ የለኝም፡፡ ወሲብም ፈፅሜ አላውቅም፡፡ አልፎ አልፎ ግን ማስተርቤት አደርጋለሁ፡፡ ስለዚህ ውድ የዘ-ሃበሻ አዘጋጅ ይሄ ነገር የሚከሰትብኝ ለምንድን ነው? ወሲብ ብጀምርስ ይህ ነገር ይጠፋል? ከዚህ ነገር መላቀቅ የምችለው እንዴት ነው? እባክህ ለችግሬ መልስ ፈልግልኝ፡፡ ጂቲ ነኝ
የዶ/ር ዓብይ ዓይናለም ምላሽ፡- በተፈጠረብህ ነገር ብዙ አትደናገጥ፡፡ ምክንያቱም ይህ ችግር ያንተ ብቻ ሳይሆን የብዙ ወንድ እና ሴት ወጣቶች እንዲሁም ጎልማሶች ችግር ነው፡፡ እንደ የተለየ ጤና ችግር በመቁጠርም አትረበሽ፡፡
በእንግሊዝኛ ኖክቱርናል ኢሚሽን (Nocturnal Emission) በመባል የሚታወቀው በሌሊት የሚከሰት የዘር ፍሬ በዘፈቀደ መፍሰስ በአብዛኛው በወጣትነት ዕድሜ ላይ በሰውነት ውስጥ የሚከሰት ባይኮሎጂካል እና የሆርሞን ለውጦችን ተከትሎ በስፋት የሚከሰት ጤናማ የጉርምስና ምልክት ነው፡፡ በተደጋጋሚ የሚከሰት ከሆነ ግን ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ እንገደዳለን፡፡ ነገር ግን ይህ ችግር በአነስተኛ መጠንም ቢሆን በጎልማሶች እና በአረጋዊያን ላይም ሊከሰት ይችላል፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በእንቅልፍ ልብ የዘር ፍሬ የሚፈሰው በሁለት መልኩ ነው፡፡ የመጀመሪያው እና በአብዛኛው የሚከሰተው በእንቅልፍ ልብ የብልት መወጠርን (መቆምን) ተከትሎ ነው፡፡ ይህ ነገር በአብዛኛው ወሲባዊ ህልሞችን በመመልከት እና በወሲባዊ ሀሳብ መወጠርን ተከትሎ የሚከሰት ነው፡፡ በአንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ ብልት ሳይወጠርም የዘር ፍሬ ሊፈስ ይችላል፡፡ ይህ ነገር ደግሞ ከወሲባዊ ሀሳቦች ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡ ስለዚህ የአንተ ችግር ከሁለቱ በየትኛው ውስጥ እንደሚወድቅ ለራስህ መልስ ስጥ፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ወንዶች 84 በመቶ የሚሆኑት ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይህ ችግር ይከሰትባቸዋል፡፡ በተደጋጋሚ የማስተርቤሽን ተግባር የሚፈፅሙ ወጣቶች በእንቅልፍ ልብ የዘር ፈሳሽ ለመፍሰስ ችግር የተጋለጡ ናቸው፡፡ በመንስኤው ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚገልፁት በእንቅልፍ ልብ የሚከሰተው የዘር ፍሬ መፍሰስ ወሲብ ካለመፈፀም ጋር እንደማይገናኝ ይጠቁማሉ፡፡ በእንቅልፍ ልብ ዘር ፍሬ የመፍሰስ አጋጣሚ የሚፈጠረው በተለያዩ ምክንያቶች ነው፡፡ በሰውነታችን ውስጥ በሚከሰት የሆርሞኖች ለውጥ የመጀመሪያው ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የዘር ፍሬ ክምችት በሰውነታችን ውስጥ መኖር ደግሞ በሁለተኛነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች በተጨማሪ ወሲብ እና ተያያዥ ጉዳዮችን ሲፈፅሙ ህልም ማየት እና ስለወሲብ ደጋግሞ ማሰብ እንዲሁም ከመኝታ በፊት ወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞችን መመልከት እንዲሁም መጽሐፍትን ማንበብ በእንቅልፍ ወቅት ዘር ፍሬ የመፍሰስ ችግርን እንደሚያስከትል ይጠቁማሉ፡፡
ወድ ጠያቂያችን ጂቲ በወር አንድ ጊዜ እና ሁለት ጊዜ በእንቅልፍ ልብ የዘር ፍሬ የመፍሰስ ችግር ጤናማ እንዲሁም ተፈጥሯዊ እና ምንም አይነት ችግር የሌለው ነው፡፡ ነገር ግን በየቀኑ እና እንደ አንተ በሳምንት ሁለት ሶስቴ የሚከሰት ከሆነ እና እሱን ተከትሎ መደበርን፣ ራስ ምታትን፣ አቅም እንዲሁም እንቅልፍ ማጣትን የሚያስከትል ከሆነ ግን ጤናማ ስላልሆነ በፍጥነት ባለሞያን ማማከር ያስፈልግሃል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በሰውነታችን ወስጥ የሚኖረውን የቴስቴስትሮን መጠን በማሳነስ ለተለያዩ ሆርሞን ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የዘር ፍሬ በብዛት መፍሰስ በሰውነታችን ውስጥ ጤናማ ያልሆነ የዘር ፍሬ ፈሳሸ ምርት ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ጤናማ ያልሆነ የዘር ፍሬ ምርት ደግሞ በተለይ ወንዶችን ለመሀንነት ችግር ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ የዘር ፍሬ ብዛት በመመረቱ የተነሳ የዘር ፍሬ በብዛት የሚፈስ ከሆነ የሚፈሰው የዘር ፍሬ በአብዛኛው ትክክለኛ ቅርጽ እና መጠን ያለው ስለማይሆን ከሴት እንቁላል ጋር ተገናኝቶ ጽንስ የመፍጠር አቅሙ እጅግ አነስተኛ ይሆናል፡፡
በተመሳሳይ ይህ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ያለው የዘር ፍሬ ክምችት አነሰተኛ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ በአንድ ጊዜ በሚፈስ የዘር ፍሬ ውስጥ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሴሎች ይገኛሉ፡፡ በአንድ ሚሊ ሊትር የዘር ፈሳሽ ውስጥ የሴሎች ብዛት ከ20 ሚሊዮን በታች ከሆነ ጽንሰ የመፍጠር አቅም አይኖረውም፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በእንቅልፍ ልብ የዘር ፍሬን መፍሰሰ በወሲብ ወቅት ከሴቷ በፊት ቀድሞ የመርካት ችግርን እና ሌሎች ስንፈተ ወሲብ ችግሮችን ያስከትላል፡፡ የሰውነት ክብደት መቀነስን እና በራስ የመተማመን መንፈስንም ያሳጣል፡፡ ለራሳችን የምንሰጠውን ግምት በመሸርሸርም የፀፀት እና የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡
ወደ መፍትሄው ስንመጣ የመጀመሪያው በጀርባ አለመተኛት ነው፡፡ ወደ መኝታ ከመሄድ በፊት ወተት አለመጠጣት እና ብዙ ምግብ አለመመገብም ይመከራል፡፡ በተለይ ደግሞ እራት ወደ መኝታ ከመሄዳችን ቢያንስ ከ3 ሰዓት በፊት መመገብ እና እራት ላይ ብዙ ቅመም የበዛበት ምግብን፣ ከመጠን በላይ ወይን ከመጠጣት፣ እንቁላል፣ ስጋ እና ሌሎች አነቃቂ ነገሮች የበዛባቸው ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ ቢቻል እራት ላይ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን ማዘውተር ጠቃሚ ነው፡፡ ሌላው መፍትሄ ደግሞ ምግብን በደምብ አድቅቆ መመገብ እንዲሁም የፈሳሽ አወሳሰዳችንን ማስተካከል ነው፡፡ በተለይ ከእራት በኋላ ብዙ ፈሳሽ አለመውሰድ፣ ቀን ላይ ብዙ ውሃ መጠጣት፣ ከመኝታ በፊት ሽንትን መሽናት ጠቃሚ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የዘር ፍሬ የሚፈሰው ሊነጋጋ ሲል ስለሆነ በጠዋት የመነሳት ልማድን ማዳበርም ይመከራል፡፡
ውድ ጂቲ ፈረስ መጋለብን እና ሳይክል መንዳትን የመሳሰሉ ችግሮችንም ለዚህ ችግር ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ መሰል ተግባራትን መቀነስም ጠቃሚ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የእግር ጉዞ ማድረግ፣ ከመኝታ በፊት ወሲብ ቀስቃሸ ፊልሞችንም ሆነ ጽሁፎችን ከመመልከት እና ከማንበብ መቆጠብ፣ እለታዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማዘውተር እንዲሁም ብልት እና አካባቢውን በየቀኑ በአግባቡ ማጽዳት እና የተመጣጠነ የአመጋገብ ስርዓትን ማዳበር ጠቃሚ ነው፡፡
በእንቅልፍ ልብ ካለፍቃድ እና ካለፍላጎት የዘር ፍሬ የመፍሰስ ችግርን ከላይ በመፍትሄነት የተዘረዘሩትን ነገሮች በአግባቡ እና ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ በማድረግ ካለብህ ችግር መላቀቅ ትችላለህ፡፡ በእነዚህ መንገዶች የምትፈልገውን ለውጥ ማምጣት ካልቻልክ ግን በአፋጣኝ ባለሞያዎችን ማማከር ይገባሃል፡፡ S
(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 51 ላይ ታትሞ የወጣ)
በጀርመን የሚገኙ የፖለቲካና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት ኢቲቪ ላቀረበው ቪዲዮ ምላሽ ሰጡ (Video)
ከአረብ ሃገራት ሰማይ እስከ ሚሊንየም አዳራሽ!
ከነቢዩ ሲራክ
እኔን ያሰፈራኝ ጎርበጥባጣው መንገድ . . . ኢትዮጵያውያን በግብጽ . . .
ሰሞነኛ የማለዳ ወጌን ወደ እናንተ ላደርስ አንዱን አንስቼ አንዱን ስጥል አንድ ወዳጀ ስልክ ደውሎ በግብጵ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአባይን ግድብ ውዝግብ ተከትሎ አደጋ ላይ መሆናቸውን መረጃ ቢጤ አቀበለኝ ። በማስከተልም ከጥቆማ መረጃው ጋር በቀጣዩ ቀን ነዋሪዎች በነቂስ ሰላማዊ ስልፍ ለማደረግ እንዳቀዱ በመግለጽ እንዳነጋግራቸው መከረኝ ። መረጃ ለመሰብሰብ የሚረዱኝን ወንድሞች አድራሻ የሰጠኝን ወንድም አመስግኜ ወደ ሃገረ ግብጽ ካይሮ ደጋግሜ ደወልኩ። ከብዙ ጥረት በኋላ ግን የፈለግኩትን መረጃ ሙሉ በሙሉ ባላገኝም ያገኘሁትን ሰባስቤ ለተጨማሪ መረጃ የሚረዱኝን ተጨማሪ ስልክ ቁጥሮች ሰባሰብኩ። ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ግን ለኢትዮጵያ መጻኤ ህይወት እንድሰጋ እንድፈራ አድርገውኛልና ፈራሁ! ልቤ እንቢ እያለኝ ጥረቴን ገፋሁበት . . . ” በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ ” እንዲሉ ድሮም በመገለል ቋፍ ላይ የነበሩት ግብጵ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የአባይን ግድብ የመንግስታቱ ፍጥጫ ኑሯቸውን እንዳላስመቸው ሰምቻለሁ፣ ደረሰባቸው የተባለው መገለልና ያላባራውን ተደጋጋሚ ጥቃት ለሚመለከታቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃላፊዎች “አቤት!” ለማለት የኦነግን እና የግብጽን ባንዴራ ይዘው የተቃውሞ ሰልፍ የማድረጋቸው ዜና ተከታትሎ ደረሰኝ ፣ ይህን መስማቱ በራሱ ያማል . . . እናም ፈራሁ !
ሰላማዊው የሙስሊም ወገኖች ተቃውሞ . . .
ሙስሊም ወገኖቻችን አመት ከመንፈቅ የደፈነ ያልተፈታ ጥያቄ አላቸው ፣ መሪዎቻቸው ዘብጥያ ከወረዱ አመት ከመንፈቅ ሊደፍን ነው ፣ ከዚያም ወዲህ በርካታ ደጋፊዎቻቸው ነጋ ጠባ ዘብጠያ እንደሚወረወሩ እየሰማን ነው ፣ ከሁሉም አስገራሚ በሆነ መንገድ ከአመጽ ርቀው የማህተመ ጋንዲን ሰላማዊ ተቃውሞ ያስናቀ ስላማዊ ተቃውሞ ያሳዩን ሙስሊሞች ለአመት ከመንፈቅ በዋሉት አብዛኛው የአርብ የህብረት ጸሎት በተክታታይ ጊዜያት ” ህገ መንግስት ይከበር ፣ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ!” በማለት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ቢያሰሙም ሰሚ አላገኙም። የታሰሩት የፍርድ ሂደት በገደምዳሜ ሲንከባለል ፣ ሰው ትዕግስቱን እንዳያጣ ያስፈራል። ይህ ሂደትም ውሎ ሲያድ ነገሩ እንዳያከረው ፣ ሰላማዊውን ተቃውሞ በሃይል ሊገታ ከታሰበ ሊፈጠር የሚችለው ሁከት ፣ ሁሉም ሲከር እንዳይበጠስ ፣ ግሎ እንዳይቀልጥ ያሰጋኝ ያስፈራኝ ይዟል ! እናም የመሪ ፣የአስተዳዳሪ፣ የባለ መላ ዳኛ ያለህ አልኩ ቢጨንቀኝ ! ግና ፈራሁ !
ተቆርቋሪ ፣ሳቢ ያጣን ዜጎች በደል …
ይህ ሁሉ ሃሳብ ሲንጠኝ ብዕሬን ወርውሬ ጥዬ ልወጣ ብከጅልም ሌላ ጉድ አዳፍቶ አስቀመጠኝ ። የሰው ክብሩ ቢቀርብን ወደ ውጭ እንደሚላክ እቃ የሻጭ ገዥ ውል መፈጸሚያ ስምምነት ውል በህግ ማዕቀፍ ተላኩ ለሚባሉት ዜጎች አልተበጀልንም። ይህ አያስቆጭ አያንገበግብ ይሆን? ታዲያ ወላጆች ልጆቻቸውን ለገንዘብ ሲሉ ይልካሉ የምንለውስ በየትኛው ሞራል ይሆን? ደላላ ኤጀንሰጀ መውቀሱ ፋይዳው ምኑ ላይ ነው? ከረር ያለው ጥያቄ ማጠየቄ ያለ ነገር አይደለም ። የሰማሁት ቢያመኝ ነው! ዜጋ ከሃገር ለስራ ኮንትራት ሲወጣ ሁለት ሃገራት መካከል ሁለትዮሽ የጋራ ስምምነትና የስራ ውል መሰረታዊ ጥያቄ ነው ። ይህ ግን በእኛ አልሆነም! ለዘመናዊ ባርነት የሚላኩ ዜጎች በደል ከባለቤቶቹ ሌት ተቀን እሰማለሁ ። እናም ጩኸት ምሬቱ ቢታዎሰኝ የሸበበኝ የፍርሃት ልጓም በጥሼ የልብ ልብ የሰጠኝ የነፍስ ውስጥ ሙግት እነሳለሁት ፣ የስደት ቁስሉን የሚያሽረው እውነተኛ መፍትሄ ብቻ ነው በሚል የጀመርኩት የዚያን ሰሞን ጅምር የማለዳ ወግ መልኩን ቀይሬ እንዲህ መሞነጫጨሬን ጀመርኩት ! ያልተደፈሩ ፣ የተደበቁ እውነቶች ቅስማችን እሰከ ሰበረው ስደትና ፍርሃት እዳስሰው ዘንድ አናኳር አንኳር ምክንያቶቸን ደራደርኩ ! ጥቂቶች አስቀድመን የምናውቀውን ፣ ሃላፊዎችን ዳጋግመን ስንጠይቅ “ስምምነት አለ!” ሲሉ ሲወሸክቱን የባጁትን፤የከረሙትን ጭብጥ የሌለው እውነት የጅዳው ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ ከበደ ገላልጠው የነገሩን ባሳለፍነው ሳምንት ነበር ። በአብዛኛው በእድሜ ያልበሰሉ ፣ ለዘመነው የአረቦች ቤት አይደለም ፣ ባደጉ በተማሩበት መንደር ዙሪያ ባሉ ወረዳ እና ቀበሌ የዘመኑ ጎጆዎች እንግዳ ለሚሆንባችው ድሃ አደግ ታዳጊ ጉብሎች የሚገኙባቸው ቁጠራቸው ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በኮንትራት ስራ ስም ከዘመናዊ ባርነት ለማይተናነሰው የሳውዲ ባለ ጸጎች የቤት ስራተኝነት ተልከዋል። ይህ የሆነው ግን ያለ ሁለትዮሽ የስራ ኮንትራት ስምምነት መሆኑን የጅዳው ቆንስል አቶ ዘነበ ከበደ ባሳለፍነው እሁድ ከጀርመን ራዲዮ ጋር ባደረጉት ውይይት አርድተውናል ።
በህግና ስርአት ሃገር አስተዳድራለሁ፣ ድህነትን ለማጥፋት የማልፈነቅለው ድንጋይ የለም ከሚል መንግስት ሁለት ሶስት ገጽ የማትሞላ የሰራተኛ ህግን ማርቀቅ እንዴት ገደደው? እንደ ቀሩት ሩቅ ምስራቅ ሃገራት ጠንከር ያለ መብት ማሰከበሪያ አንቀጾችን እንኳ ማስቀመጥ ቢገድ እን ጎረቤት ኬንያ ደመወዝ ፣ የስራ ሰአት፣ ህክምናና መብት ረገጣና የሚከላከሉ ስስ አንቀጾችን አካቶ ፣ ውል ስምምነት ፈጽሞ ዜጎችን በኮንትራት ስራ መላክ ከገደደው መንግስትነቱ ምኑ ላይ ነው? ብየ አጠየቅኩ ፣ ግን መልስ አጣሁ ! ይህም እንዝህላልነት አይሉት ሃገር ማለት ሰው መሆኑን ያለማገናዘብ እዳ? የምናገረው፤ የምለውን ቢያሳጣኝ ፣አንገብግቦ አስቆጨኝ ! የረጅሙ አውራ መንገድ መነሻ መንገድ ማጣት ግራ ያጋባል። ለሃገር ለወገን የሚል መጥፋቱን ማስተዋሌ አራደኝ ! ፈራሁ !
የሰቆቃ እንባ በሚሊንየሙ አዳራሽ . . .
ባለፍነው ሳምንት “በስደት ይብቃ! ” መሪ ቃል ሃገር አቀፍ ስብሰባ በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዶ ትረሱታላችሁ አልልም ። ዝግጅቱ እንደ ጅማሬው ባይዘልቅም ቀልብን ሳቢ ነበር ለማለት እደፍራለሁ ። የተሰበሰቡት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንባና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት አስደምሞኛል። ከማውቀው ከሰማሁት ሳይሆን ካየሁት ተነስቼ “ህግን ተከተሉ ይሉናል ! ” እነሱ ግን ህግን አይከተሉም ስል በመረጃ እያስረገጥኩ አጫውታችኋለሁ ብልም ወኔው ከዳኝ. . . እኛ ኢትዮጵያውያን ለሃገራችን ቀናኢ ነን ፣ አሁን አሁን ግን ለሃገሬው ሰው መብት ነጻነት መከበር ብዙም ግድ አለን ብዬ አፊን ሞልቸ ለመናገር ሞራል የለኝም ! ለሰው ልጅ ደህንነት፣ ሰላምና ብልጽግና ቀርቶ ለሰብአዊ መብቱ መከበር ስንተጋ አለመስተዋሉ እየተለመደ ሄዷል ! ግን እኮ ሐገር፤ ምድር ማለት ሰው እኮ ነው ! ሃገሬውን ሰው በዘር በሃይማኖት ሳንለይ ሰብዕናውን ካላከበርነው ካልጠበቅነው ሃገር ያለሰው ምድረ በዳ ነው፣ ሃገር ያለ ሰው ፣ ሰው ያለ ሃገር ምን ትርጉም አለው? ! ብየ ስጠይቅ ችግሩን አወሳስበው እዚህ ያደረሱት ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎቻችን ለትክክለኛ መፍትሔ የመትጋት ተሞክሮ አሰጋኝና ይህም አስፈራኝ ! አዎ ፈራሁ !
የወገን የሰቆቃ ጥሪ . . .
የአረብ ሃገሩን ስደት እንደ ጋዜጠኛ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ለሚያውቅ እንደኔ ላለ ብኩን ብዙ ለማለት የሚያስችሉ ጥቂት የተጨበጡ ማስረጃዎችን ብቻ ማቅረብ ረዥሙን ውጣ ውረድ በአጭር መቃኘት አይገደውም። ሆኖም ግን መረጃ ማስረጃዎችን በቅርብ ጎላጉሎ ለማሳየት አቅሙ እያለኝ አቅሙ ከዳኝ! እውነቱን ልቦናየ ሲያውቀው” ነገር አብርድ !”የምትለው የአንድ ወዳጀ ይትበሃል በውስጤ ተሰንቅራ አወከችኝ! ይህም ነፍሴ ብዙ ከማለት ገታችኝ ፣ የሁለት ብላቴናዎች አባት ናፍቆት ሲፈትነኝ ፣የፈጣሪ ቸርነት ሰመረ የምለው ህይወቴ ውጤት በእናቷ ሆድ ያለችው” ማህሌት”ለማየት ያለኝ ጉጉት ብዕሬን አነጠፈው! የምወዳት እናቴን ሃገር ቤት ተመልሶ ” የማየት ምኞት መጨናጎል ሲያቆስለኝ “ሃገሬን፤ አፈሬን ዳግም እንዳልረግጥ እሆናለሁ !”የሚለው እኩይ ስጋት ነፍሴን አርቆ አንገላታኝ ! የፍርሃቴ የስጋቴ ደረቅ እውነቱ ይህ ሆነና ሳልፈራው የኖርኩት አስፈሪው ፍርሃት ሳላስበው ጠለፈኝ ! እናም ዝም አልኩ. . .እውነቱን ውሸት ባልልም ላፍታም ቢሆን አፊን በፍርሃት ለጎምኩ ! የወገኔን መከራ፤ ስቃይ ሃገር በግላጭ ፣ መንግስት በድፍረት የተመለከቱትና የአለቀሱት፤ ያነቡት በቁጭት ሲደብኑ አየሁ ! የአስከፊውን ስደት የጉብል እህቶች ስቅየት በውስጤ ያደረውን የተጫነኝን የፍርሃት መንፈስ አሽቀንጥሮ ጣለልኝ ፣ አባረረልኝም ! ተመስገን አምላኬ! የሆድ የሆዴን እነግራችኋለሁ ! እስከዚያው ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ሠርቶ ወይንስ ሰርቆ?
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ሰሞኑን አዲስ አበባን የሚዘዋወር ሰው በብዙ አካባቢዎች ከሚያያቸው ወያኔያዊ መፈክሮች አንዱና ጎልቶ የሚታየው “በሀገር ውስጥ ሠርቶ መለወጥ ይቻላል!” የሚለው ነው፡፡በትላልቅ የጨርቅ ጀንዲዎች ላይ ከባባድ ተምኔቶችን በመፈክርነት ጽፎ በየአደባባዩ መስቀል የወያኔ ትልቁ መገለጫ ነው – የደርግም፡፡ ግን አብዛኞቹ መፈክሮች ከምኞትና ሰውን ከማቁልጭለጭ አልፈው አያውቁም – የሁለቱም፡፡ ያን ስንት ድሃ ሊያለብስ በሚችል አቡጄዲ የተሰቀለ መፈክር ሳነብ ወዲያው ያልኩት ‹በሀገር ውስጥ ሠርቀህ መለወጥ ይቻላል›፡፡ (ሠርተው በድካማቸው ፍሬ የሚያልፍላቸው የሉም ማለት በመሠረቱ ስህተት ነው፤ ሠርተህ ሲያልፍልህ ግን በሥራህና በቁሣዊ ዕድገትህ መካከል የሚጠበቅ የጊዜ፣ የመነሻ ወረት፣ የጥረት፣ የትርፍ ‹ማሪጂን›፣ የዕውቀት፣ ለመክሰር የመዘጋጀት፣ ከሠራተኞች ጋር የሚኖር የጥቅማ ጥቅምና የመሳሰለው ግንኙነት ሊታዩ ይገባል፡፡ አለበለዚያ እንደወያኔ ሀብታም ትናንት ሥራ ጀምረህ በማግሥቱ ቀጭን ጌታ ከሆንክ ከሥራህ ቀድሞ ብልግናህ ማለቴ ብልጽግናህ ታዬ እንደማለት ነውና ይህ ንግድ ሳይን ማጅራት መምታት ነው – እኛ ባልተወለደ አንጀት እየተመታን እንዳለነው፡፡)
በላይኛው አንቀጽ የጠቀስኩትን መፈክር ሳነብ እስቃለሁ፤ ፍርፍር ብዬ ነው የምስቀው፡፡ ምክንያት አለኝ፡፡ ትልቅ ምክንያት፡፡ ለዝርዝሩ በ‹አዲስ መስመር እንገናኝ› – (ኩረጃ በኔ አልተጀመረም)፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአሁኑ ዘመን ሠርተህ ሊያልፍልህ አይችልም፡፡ በየትኛው ሒሣብ? ኧረ እንዴት ተደርጎ? ምን ሠርተህና ማንስ አሠርቶህ? ሕግን ጠብቀህ ከሠራህ የመጀመሪያው ከሣሪ አንተ ነህ፡፡ ቀረጡ፣ ግብሩ፣ ኪራዩ ባንተ በሕጋዊው ነጋዴ ላይ ይቆለላል፡፡ ባይገርምህ ከዘር አኳያ ማውራት ስልችት አለኝ እንጂ ወያኔዎች አንድን ትግሬ ያልሆነ ምሥኪን ነጋዴ በነባሩ የመንግሥት የኪራይ ቤት ላይ – ለምሳሌ የ200 ብሩን ኪራይ በአንድ ጊዜ 10000 በማድረግ እሱ አጨብጭቦ – አብዶም ሊሆን ይችላል – ሲወጣላቸው ከ200 ባነሰ ኪራይ ‹የኛ ነው› ለሚሉት ሰው የሚያከራዩ ዓለም ከምታመርታቸው ግፈኛ ዜጎቿ መካከል ተወዳዳሪ የሌላቸው አረመኔዎች ናቸው ብዬ ብናገር ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ሂድ አይሉህም – እንድትሄድ ግን ያደርጉሃል፡፡ በትግርኛ ‹ውፃዕ አይተበሎ፤ ከምፅወፅዕ ግበሮ› ይባላል፡፡ የተንኮልና የወንጀል ማምረቻ ዘመናዊ ፋብሪካዎች ናቸው፡፡ ግፋቸውና የሸራቸው ድርና ማግ ተጎልጉሎ አያልቅም፡፡
ስለ “ባገር‹ህ› ሠርተህ ያልፍልሃል” የማሞኛ ፈሊጥ የኔን ልናገር፡፡ ሰለቸኝ፤ ደከመኝ፣ አጣሁ – ገረጣሁ ሳልል በንጹሕ ኅሊና ራሴንና ቤተሰቤን ለማኖርና ሀገሬን በሙያየ ለማገልገል ከሙያዎች በአንዱ ተሠማርቼ መሥራት ከጀመርኩ ጥቂት አሠርት ዓመታት አለፉ፡፡ የጀመርኩበት ደሞዝ የኢት. ብር 500 ነበር – ለእናት ሀገር ጥሪና (በአሁኑ የወያኔ ዘመን የአባይ ግድብ ዓይነት መሆኑ ነው) ለጡረታ ተቆራርጦ ብር 385 ይደርሰኝ ነበር፡፡ ለተለያዩ የሠራተኞች ድንገተኛ የንብረት መጥፋትና ሞትን ጨምሮ የጤና መጓደል ችግሮች ከተከሰቱም እንደብሔራዊ ሎቶሪ የዕጣ ቀን ደመወዝ መክፈያ ቢሮ ተኮልኩለው የሚጠብቁ የደመወዝ ቀበኞች ካሉም የሚደርሰኝ ገንዘብ ከዚያም ሊያንስ ይችላል፡፡ ለማንኛውም ያንን ገንዘብ ወስጄ ወር እስከ ወር የመድረስ ግዴታ ነበረብኝ፡፡ ቀስ እያለ ቤተሰብ ስጨምር ደመወዙም እያሽኮተኮተ አንድ ሺን መጠጋቱና ማለፉም አልቀረም፡፡ ያኔ ታዲያ አልዘባነን እንጂ በቤቴ ውስጥ በተለይ በምግብና በመጠጥ በልብስም ያን ያህል እንዳሁኑ የጎላ ችግር አልነበረብኝም፡፡ በአንጻራዊ ሁኔታ ሁሉም ነገር እርካሽ ስለነበር በጣም መቀናጣት ይቅር እንጂ መሠረታዊ ፍላጎቶቼን ማሟላት የሚሳነኝ አልነበርኩም፡፡
አሁን ግን አጠቃላይ የወር ገቢዬ ወደ አምስት ሺህ ብር ገደማ ደርሶ መማል ሳያስፈልገኝ እውነቱን ለመናገር ከወር እወር እምደርሰው ብዙ ፍላጎቶቼን ለምሳሌ የእንስሳት ተዋፅዖዎችን፣ አትክልትና ፍራፍሬ ወዘተ. ለማሟላት መከጀል ብቻም ሳይሆን ለማሰብም ዕድል ሳላገኝ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የምትኖሩ ዜጎች የአራት ሺህ ብር የተጣራ ደመወዝን ገንዘባዊ ዋጋ ታውቃላችሁና ይህን ለማስረዳት ብዙ መድከም አይገባኝም፡፡
እኔ – ልብ አድርጉ – ይህን መጠን የማገኘው ሁለት ቦታ ሠርቼ ነው፡፡ እንዲህ የምላችሁ “ተጨማሪ ሥራ ሥራ” ብላችሁ ለምትመክሩኝ ነው፡፡ ምን አለፋችሁ – ኢትዮጵያ ውስጥ ካላጭበረበርክና ካልሰረቅህ በቀን 48 ሰዓት ብትሠራ ከጓያ ሽሮ አታልፍም፡፡ ሰዎች እንዴት ይኖራሉ ታዲያ? ብለህ ስትጠይቅ ብዙ ነገር ዕንቆቅልሽ ሊሆንብህ ይችላል፡፡ ጠጋ ብለህ ከመረመርክ ግን ግልጽ ነው፡፡
ብዙ ሰዎች በተለይም ወጣች የተዘባነነ ሕይወት ሲመሩ ታያለህ – የአህያ ጆሮውን ከየኪሣቸው እየመዘረጡ፣ በቆንጆ መኪናዎቻቸው እየተንፈላሰሱ፣ በየቀኑ የሚቀያየሩ ቆነጃጅትን እጎናቸው ሻጥ እያደረጉ፣ ሙዚቃቸውን ልክ እንደኬንያ ማታቱ እስከጣራ ለቅቀው ከትከሻቸው ጀምሮ በስሜት እየተወዛወዙ በከተማዋ ሲንሸራሸሩ … ማታና ውድቅት ላይም በየጭፈራና ዳንኪራ ቤቱ እየተውረገረጉ ታያቸዋለህ፤ እነዚህ ወጣቶች የሚያቀርቡልህን ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን በሌለህ ኢኮኖሚ ከአቅምህ በላይ እየተበጣጠስክ – እየተበደርክ እየተለቀትክ – ያልኖርክበትን ጊዜ ደመወዝም በሞዴል ስድስትና ከብድርና ቁጠባ እየተበደርክ የምትገዛው የነሱ ድሎት እንዳይጓደል መሆኑን ታዲያ ዕወቅ፡፡ በዚያውም ላይ አንተ ለሀገርህ ብዙ ለፍተህና ደክመህ ስታበቃ የነተበ ሸሚዝ፣ የተንሻፈፈና አቧራ የሚቅም ጫማ፣ መልኩን ከአንዴም አልፎ ሁለት ሦስቴ የቀየረ ኮት ወይም ጃኬት፣ አንገቱ በዐይጥ የተበላ የሚመስል የተቦተረፈ ካናቴራ… ለብሰህ ተቆሳቁለህ ትታያለህ – መጥፎ የማይባል ደመወዝ እያገኘህ፡፡ ሀገራችን በቅጡ ልትመረመር ይገባታል፡፡ የኑሮ ልዩነት የትም ሀገር ያለ ቢሆንም የኛ ግን ከየትኛውም ጋር አይወዳደርም፡፡
ብዙ ነገሮች ብልጭልጭ ናቸው – የምታየው እውነት ከምትሰማው እውነት ይለይብሃል፡፡ የምትኖረው ሕይወት እንደምትኖር ከሚነገርልህ ሕይወት የተለዬ ነው፡፡ የተያዘው የአፍ ጂዶ ነው፡፡
የዕለትም ይሁን የወር ገቢውን በራሱ የሚወስን ሰው ጥሩ ሊኖር ይችላል፡፡ ምክንያቱም ገበያውን ተከትሎ – ወጪና ገቢውን አጢኖ የሚሸጠውን ዕቃ ዋጋ ወይም የአገልግሎት ክፍያ በዚያው መጠን ያስተካክላልና፡፡ እንደኔ ዓይነቱ መንግሥት ወይም አሠሪየ የደነገገልኝን ወርሃዊ ምንዳ የሚያገኝ ሰው ግን ሕይወቱ በመኖርና ባለመኖር አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ወደሌላኛው ዓለም እስኪጠራ ድረስ በነፍስ በሥጋም ይዋትታል፡፡ በዚህ ሁኔታ “ሀገርህ ውስጥ ሠርተህ መለወጥ ትችላለህ” ሲሉህ ብትሰማ አቅመቢስነትህን ተረድተው በደካማ ጎንህ እየቀለዱ ሊያስቁብህ እንደሆነ ይገባሃል፡፡ ለሠላሣ ዓመታት በተመሥጋኝነት የሠራሁ ሰውዬ በስተርጅናየ ደመወዜ አልበቃኝ ብሎ ለልመና ልዳረግ ምንም ባልቀረኝ ሁኔታ ይህ የወያኔ አባባል ምን ስም ሊሰጠው እንደሚችል አይገባኝም፤ “በሀገር ውስጥ ሠርቶ መለወጥ ይቻላል፡፡”
ወጣት የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎችንና ልዩ ልዩ የግለሰብም ይሁን የመንግሥት ተቀጣሪዎችን ኑሮ ብታዩ ይዘገንናችኋል፡፡ ያልሞትን የመሰልነው እራፊ ጨርቅ ትከሻችን ላይ ጣል አድርገን በየመንገዱ ወንከር ወንከር ስንል ስለምንታይ እንጂ ከሞትን ቆይተናል፡፡ እስኪ የእግር ኳስ ጨዋ ልናይ ስቴዲየም ስንገባ እዩን – ከዚያ በነአርሰናልና ማንችስተር ጨዋታ ጊዜ ስቴዲየም የሚገባውን የአውሮፓን ጨዋታ ተመልካች ደግሞ እዩ – አወዳድሩንና የጉስቁልናችንን ደረጃ ታዘቡ – እኛን ያፈራ መንግሥት ነው እንግዲህ በምሥኪን ጎስቋሎች ላይ በደረሰው የፈጠራ ተውኔት እየተኮፈሰ ‹አድጋችኋል› እያለ በሬሣችን ላይ እያላገጠ የሚገኘው፡፡ ጭንቅላት የሌላቸው ደግሞ መንግሥት ተብዬው ብቻ ሳይሆን ባለሀብቶችም ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች – ጨካኝ አትበሉኝና – መቅሰፍት ቢወርድባቸው ደስተኛ ሀዘንተኛ ነኝ፡፡ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡ ማሰብ አይችሉም፤ እነሱ ያላቸው የመኖር መብት ሠራተኞቻቸው ያላቸው አይመስላቸውም፡፡ እነሱ እየተንደላቀቁ ሲኖሩ ሠራተኞቻቸው በስቃይና በመከራ ይኖራሉ፡፡ እነሱ በበርሜል እየዛቁ አዝመራውን ወደቤታቸው ሲከቱ ለሠራተኞቻቸው የሚከፍሉት ደሞዝ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ እናም የእውነት አምላክ እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጣቸው፡፡…
ስለዚህ ተቀጣሪ ሠራተኛ በመንግሥትም ሆነ በግል ተቀጥሮ መሥራትን ባይፈልግ አይፈረድበትም፡፡ የኗሪ አኗኗሪ ሆኖ በሀገሩና በቀየው በርሀብ አለንጋ እየተገረፈ ከሚሞት በማያውቀው ሀገር ተሰድዶ ከሁለቱ ዕድሎች በአንደኛው እንደፍጥርጥሩ መሆንን ይመኛል – መሞት ወይም መዳን፡፡ በሀገሩ የበይ ተመልካች ሆኖ ነቀዞችና ግሪሣዎች የገዛ ሀብት ንብረቱን ሲመዘብሩና እርሱን ለከፋ ድህነት ሲዳርጉ ከሚያይ ዐረብ ሀገርና አፍሪካ ሀገራት አይደለም የቀይ ባሕር ዓሣና በበረሃ እያደፈጡ የሰውነት አካልን ለመለዋወጫነት የሚዘርፉ ሽፍታዎች ሲሳይ መሆንን ይመርጣል – ተጠየቁ ቀላል ነው – እዚህም ሞት ነው – እዚያም ያው ሞት ነው፤ የሞት ደግሞ ነጭና ጥቁር የለውም፡፡ በበኩሌ ይህን የወጣቶቹን መጥፎ ምርጫ መደገፌ አይደለም፡፡ ነገር ግን እኛን በነሱ ቦታ ተክተን ስናስበው የምርጫዎች መጥበብ የማያስደርጉት ነገር እንደሌለ መረዳት አይከብደንም የሚል ግምት አለኝ፡፡ ሰው ሲጨክንብህ፤ ‹የኔ ዜጋ ነው፤ አለኝታውና ዋስ ከለላው ልሁንለት› የሚልህ ተቆርቋሪ መንግሥት በሀገርህ ስታጣ፣ የኔ መንግሥት የምትለው አንተን እንደባይተዋር ቆጥሮ የእንጀራ ልጁ ሲያደርግህና እርጎውንና ዐይቡን የኔ ለሚላቸው ወገኖች እየሰጠ ለአንተ ሞትንና እሥራትን የሚያከፋፍልህ ከሆነ ምርጫህ እግርህ ባወጣ ያቺን የሲዖል ምድር ኢትዮጵያ ለቅቀህ መሄድ ነው፡፡ ዜጎች እያደረጉ ያሉትም ይህንኑ ነው፡፡ ለአፍ አቀበት የለውምና መንግሥትና አሽቃባጭ የጥቅም ተጋሪዎቹ በያዙት ሚዲያ ቢያሽቃብጡ ሰርቆ እንጂ ሠርቶ ሊያልፍለት የሚችለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እጅግ አነስተኛ በመሆኑ አምላከ ኢትዮጵያ ፊቱን እስኪመልስልን ድረስ ያለን ብቸኛ አማራጭ ስደትና ፍልሰት ነው – እንደኔ ይህ ባይሆን ምርጫየ ነው፡፡ እናም ይህን “ከሠራህ በሀገርህ ያልፍልሃል” የሚሉትን ፈሊጥ ራሳቸው ለራሳቸው ይዘምሩት፤ እኔ ትልቁ አብነት ነኝ፤ ሠራሁ ፣ለፋሁ፣ ግን ምን ተጠቀምሁ? ባይገርማችሁ ለስደት የተነሳሳው ደህና ሥራ ያለው ሁሉ ነው፤ ሁሉም ሕዝብ ነው ለስደት የጓጓው ማለት ይቻላል፡፡ ግን ዕድሉ ጠባብ ነው፡፡ የኔ ዓይነቱ ጎምቱ ሰው ደግሞ ከእንግዲህ በኋላ ተነስቶ ነጋዴ ልሁን ቢል አንደኛ የወያኔ አሽቃባጭ መሆን ሊኖርበት ነው፤ ሁለተኛ የንግድን ሀሁ ስለማያውቅ ‹ሀ› ብሎ መማር አለበት፤ ሦስተኛ ሁሉም ሰው ነጋዴና ሁሉም ሰው ሸቃጭ ሊሆን አይጠበቅበትም፤ በሚሠራው ሥራ ሕይወቱን በአግባቡ ሊመራ የሚያስችለው ክፍያ እንደወቅቱ የገንዘብ የመግዛት አቅም እየተሰላ ሊከፈለው ሲገባ ‹ሁልህም ነጋዴ ሁን፤ ሁልህም እጅ መንሻ ወደሚያስገኝ ሥራ ተዛወር› ብሎ ፍርደ ገምድል ብያኔ መስጠቱ አግባብ አይመስለኝም፡፡
ተንቀባርረው ስለሚኖሩ ዜጎች ትንሽ ልጨምር፡፡ እነዚህ እጅጉን “የሚያስቀና” ቁሣዊ ሕይወት የሚመሩ ዜጎች ባጭሩ እነዚህ ናቸው፡- ኅሊናቸውን ለገንዘብና ለሥልጣን የሸጡ ወያኔዎች፣ የወያኔ ጋሻ ጃግሬዎች፣ ብር እንደፈለጉ እንደሚያሣትሙ የሚወራላቸው የሥርዓቱ ምሰሦዎችና ወጋግራዎች፣ በማንኛውም ዓይነት መንግሥታዊም ይሁን ኅሊናዊ ወይም ሃይማኖታዊ ሕግ የማይገዙ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ጥገኛ ነጋዴዎች፣ ካለቀረጥና ካለግብር ዕቃ ከውጭ እያስገቡ እንደፈለጉ በሀገሪቱ ላይ የሚፈነጩ ዘበናይ አልቅቶችና መዥገሮች፣ ከቻይናና መሰል ነፍሰ በላ ሀገሮች ‹ፌክ› ዕቃዎችን እያስመረቱ በጠፍ ጨረቃ በማስገባት በሕዝብ ሀብትና ገንዘብ የሚቀልዱ፣ ትላልቅ ደመወዝ የሚያገኙ የመያድና የዓለም አቀፍ ተቋማት ሠራተኞች፣ በሥራቸው አጋጣሚ ጉቦና ሙስና ውስጥ የሚዘፈቁና ደመወዛቸውን እስከመርሳት የሚደርሱ “የሕዝብ አገልጋዮች”፣ ቤትና ዕቃ የሚያከራዩ ሰዎች፣ ከሞላ ጎደል በሁሉም የሽያጭና የገንዘብ ዝውውር ከተፍ የሚሉ በጠበቀ መረብ የተደራጁ ደላሎች፣ የባንክና ኢንሹራንስ እንዲሁም የሌሎች ሴክተሮች የአክሲዮን ማኅበራትና ካምፓኒዎች ባለቤቶች፣ ለዲያብሎስ መንግሥት ያደሩ መታቾችና አስመታቾች፣ በሃይማኖትና በዕርዳታ ሽፋን ኅብረተሰቡ ውስጥ ለተለያየ ዓላማ የተሰገሰጉ ሃሳዊ መሢሆች፣ ከፍ ባለ የሽርሙጥና ‹ሙያ› ላይ የተሠማሩ ሴተኛ አዳሪዎች(በአንድ አዳር መኪና ወይ ቤት የሚያስገዙ እሳት የላሱ ሴቶች አሉ!)፣ ገንዘብ መራሽ አየር በአየር ነጋዴዎች፣ የመንግሥትን መሬት ከባለሥልጣናቱ ጋር እየተሻረኩ በብዛትና በነጻ በመውሰድ የሚቸበችቡ ዜጎች፣ የዕቃ ግዢ ሠራተኞች፣ ዕቃና ንብረትን በጨረታ ለመሸጥ ወይም ለመግዛት የሚቋቋሙ ኮሚቴዎች አባላት፣ በሀሰት የማወራረጃ ሠነድ የመንግሥትንም ይሁን የግል ድርጅትን ገንዘብ የሚሞልጩ ዜጎች፣… እነዚህና እነዚህን መሰል ወገኖች እኛ ብንራብና ብንጮህ፣ ብንሰደድና በአውሬ ተበልተን ብንሞት ያቺ ምሥኪን ታሪካዊት የፈረንሣይ ልዕልት ዳቦ ዳቦ እያሉ ለጮኹ ገበሬዎችና ሠራተኞች ‹ቤታቸው ሄደው ለምን ኬክ አይበሉም› እንዳለችው የኞች ደደቦችም ‹በሀገር ውስጥ ሠርቶ መለወጥ ይቻላል› ቢሉ የደደብነታቸው ብዛት ብዙም እንዳናዝንባቸው ያደርገናል፡፡
አንዲት ሀገር ውስጥ ችግር መኖሩን እንዴት እናውቃለን? ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሆነንን የትም ሳንዋትት ከቅርባችን ከሚገኘው የትዝብታችን ማኅደር ውስጥ እየመዘዝን ብዙ ነጥቦችን መናገር እንችላለን፡፡ ከዚህ በታች የምጠቅስላችሁ ሀገራዊ የጤናማነት መጓደል አመላካች ነጥቦች ራሴው የታዘብኳቸው ናቸው፡፡
ሀ. ዋጋው ቀነስ ወደሚለው ወደየትኛውም ሆስፒታልና የመንግሥት ጤና ጣቢያ ሂዱ፡፡ ለምሳሌ ጥቁር አንበሣ ሬፈራል ሆስፒታልን ላስቃኛችሁ፡፡ ይህ ሆስፒታል ከአዲስ አበባና ከክፍለ ሀገር በሚመጡ ህሙማንና አስታማሚዎች ሁልጊዜ (24/7) እንደተጨናነቀ ነው፡፡ ግቢው ውስጥ በአንድ ጊዜ ሲተረማመስ የምታዩት ሕዝብ ያለማጋነን የአንዲት ትንሽዬ ሀገር ጠቅላላ የሕዝብ ቁጥር ሊሆን ይችላል፡፡ የበሽተኛ መብዛት እንግዲህ የአንዲትን ሀገር የጤና ደረጃ ዝቅተኛነት ስለሚጠቁም (ድንገተኛ ወረርሽኝ – ኤፒደሚክ እስካልተከሰተ ድረስ ማለት ነው) የሚወራው የሀገራችን ዕድገት አፋዊ እንጂ እውናዊ ሊሆን አይችልም፡፡
በዚያ ላይ በየሆስፒታሉ የምናያቸው ዜጎቻችን የሚታይባቸው ጉስቁልና ልብን ይሰብራል፡፡ አለባበሳቸው፣ የሰውነት ይዞታቸው(ክሳት፣ግርጣት፣የአካል መጠን…)፣ ጠረናቸው፣ ወዘተ. ከአንዲት በያመቱ 11 በመቶ እንደምታድግ ከሚነገርላት የ“መካከለኛ ገቢ ከሚያገኙ” ሀገሮች ተርታ ልትሠለፍ በወራት የሚቆጠር ጊዜ ከቀራት “ፌዴራላዊት” ሀገር የተገኙ ዜጎች አያስመስላቸውም፡፡ ጥቁር አንበሣን ያዬ ሀገር የለኝም ይላል፤ ሀኪሞቹ ብዙዎቹ ሰልችተዋል፤ ሰውን እንደውሻ ይቆጥራሉ፤ በሽተኛው ከሞተ በኋላ እንዲመጣ የሚቀጥሩት – ቀጠሮ አሳጣሪ ዘመድ ከሌለ – ብዙውን ጊዜ ከስድስት ወር በላይ ነው፡፡ አልጋ የለም – ማደንዘዣ የለም – መቀስ የለም – ወስፌ የለም… እያሉ ማጉላላት የብዙዎች ሐኪሞች የደስታና የሃሤት ምንጭ ይመስላል፡፡ ሞት ጥንቡን ስለጣለ ማንም ለማንም የሚያዝን አንጀት የለውም ፡፡ ለነገሩ “ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም” እንዲሉ መንግሥት ከመጤፍ የማይቆጥረውን ሕዝብ የበታች ሠራተኛ ቢያዋርደውና በአግባቡ ባያስተናግደው አይፈረድበትም፡፡ (ወደግል እንዳይኬድ ክፍያው ሕክምናውን ሳይጨምር ለአንድ አዳር ብቻ የሚያስከፍሉት ከባለ አሥራ አምስት ኮከብ የሱትሩም ክፍያ ቢበልጥ እንጂ አይተናነስም – ዘመኑ የዝረፍ እንዝረፍ በመሆኑ የሚቆጣጠራቸው አካልም የለም – ከፈለጉ በእግርህ ገብተህ ሬሣህን ዘመዶችህ በብዙ ሺህ ብር እንዲገዙ ሊጠየቁ ይችላሉ – በቀላል የሕክምና ስህተት፡፡ ገንዘብ ማግበስበስ እንጂ ሙያዊ ሥነ ምግባር ብሎ ነገር በሁሉም ዘርፍ አርቀን ቀብረናል)፡፡ …
ለ. ፖሊስ ጣቢያም ሂድ፡፡ ሕዝቡ አዳርና ውሎው እዚሁ ነው ወይ ትላለህ፡፡ በደረቅ ወንጀልም ይሁን በፍትሐ ብሔር እየተከሰሰና እየተካሰሰ ፖሊስ ጣቢያዎችን የሙጥኝ ብሎ የምታየውን ሕዝብ ማን ሠርቶ እንደሚቀልበው ስታስብ አንዳችም መልስ አታገኝም፡፡ ወንጀልና ወንጀለኝነት የባሕርይ ስጦታዎቻችን የሆኑ ይመስል በተለይ በአሁኑ ወቅት ተካሳሹና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚውለው ወገን በጣም እየተበራከተ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ደግሞ የሀገርን ዕድገት ሳይሆን በችግር ውስጥ ያለን መሆናችንን ነው፡፡
ሐ. ፍርድ ቤቶችን እንጎብኝ፡፡ ልክ እንደሆስፒታሉ ሁሉ እነሱም በሰው ግጥም እንዳሉ ይውላሉ፡፡ ፍትህን የምታገኘው – በአብዛኛው – በገንዘብ መሆኑ እንኳንስ ፍትህና ርትዕ ታጥበው ገደል በገቡበት በዘንድሮው ዘመንና ጥንትም የነበረ መሆኑ አይካድም – እንዳሁኑ ግን ዐይን ያወጣ የፍትህ መዛባት ታይቶ የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ በግ የሰጠው ባለጉዳይ በሬ በሰጠው ባለጉዳይ እስኪረገጥና የፍርድ ሚዛኑ በሕጉ መሠረት ሳይሆን ዳኛውና ዐቃቤ ሕጉ በተቋደሱት ንዋይ እስኪወሰን ድረስ እዚያም ቤት ብዙ መጉላላት አለ፡፡ ይህ በተለይና ይበልጡኑ በባልና ሚስት ፍቺ ጉዳይና በንብረት ክርክር ዙሪያ የሚስተዋለው የፍርድ ቤት ጭንቅንቅ የሀገርን ጤናማነት የሚያሳይ አይደለም፡፡ በነዚህም ሥፍራዎች ሰዎች ሥራ ፈትተው ከአምራችነትና ከሠራተኝነት ይልቅ አፈኛነትንና የነገር ብልት አወጣጥን እየተማሩ ስለሚውሉ ሀገር ችግር ላይ ለመውደቋ አንዱ ምልክት ነው፡፡
መ. ከተማ አውቶቡስንና ሌሎች የትራንስፖርት መኪኖችን እንቃኝ፡፡ እነዚህ ተሸከርካሪዎች ከጧት እስከማታ ሰው አርግዘው እንደወረገብ ነፍሰጡር ተንገፍጥጠው ነው የሚታዩ፡፡ በመሠረቱ ሰው አይዘዋወር አይባልም፡፡ ነገር ግን በሥራ ሰዓት ይህ ሁሉ ሕዝብ በመኪኖች እየታጨቀ ሲዘዋወር እኔን መሰል ሥራ ፈቶች ምክንያቱን ማጠያየቃችን አይቀርም – ወትዋቹ ኅሊናችን እየጠየቀ ያስቸግረናልና፡፡ በአውቶቡስ ውስጥ መቼም ሥራ እንደማይሠራ ይታወቃል፡፡ የሰዎቹን ሁኔታ ስናይ ደግሞ ብዙዎቹ የቢሮ ሠራተኞች አይመስሉም፡፡ ምናልባት የክፍለ ሀገር ተጓጓዦችን ለሥራና ለቤተሰብ ጥየቃ ልንል እንችል ይሆናል፤ በከተሞች ያለው ዝውውር ግን ብዙም ግልጽ አይደለም – በመኪናም ይሁን በእግር ሰውን ስታዩት በገፍ ተጓዥ ሆኗል፡፡ በዚያ ላይ በየአደባባዩና በየቦታው በሥራ ሰዓት የሚታየው የሕዝብ ትርምስ በእውኑ ይህ ሁሉ ሕዝብ እህል ቀምሶ ያድር ይሆን ወይ ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡ አሳሳቢ ነው፡፡ በሌሎች ሀገሮች ስናይ – በፊልምም ቢሆን – ሕዝቡ በሥራ ሰዓት ከተማ ውስጥ አይታይም፡፡ በየሥራው ይከታል፡፡ የኛ ግን ሰኞ የለ፣ እሁድ የለ፣ ጧት የለ፣ ቀትር የለ – ሲርመሰመስ ነው የሚውል፡፡ ይህ የሚያሳየው የሥራ አጡና ምናልባትም የሥራ ፈቱ ቁጥር ሥራ ከሚሠራው ይልቅ የገነነ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ጥቂቶች ሠርተው ብዙዎችነን የማስተዳደር ሁኔታ ደግሞ ክንድን የሚያዝልና ድህነትን የሚያስፋፋ ተስፋንም የሚያሳጣ እንግዳ ክስተት ነው፡፡ ‹አደጋ አለው!› – ትላለች የዘሩ ሚስት – እውነቷን ነው፡፡ በላተኛ በዝቶ ሠራተኛ ከጠፋ አደገኛ ችግር አለ – በሂደት እርስ በርስ መበላላትም ሊመጣ ይችላል፡፡ ይህን የሕዝብ ኃይል በአድልዖ ሳይሆን በአግባቡ አስተምሮና አሰልጥኖ ለሥራና ለአገልግሎት የሚያበቃ የመንግሥት ተቋም በአፋጣኝ ያስፈልገናል፡፡ የአሁኑን መንግሥት መንግሥት ካልነው ተሳስተናል፡፡ ይህ ሸውራራ የወያኔ መንግሥት በሰማሁት መረጃ መሠረት ከ50 ቢሊዮን ዶላር ከሚበልጥ ዕርዳታና ብድር ውስጥ ከ12 ቢሊዮን የሚልቀውን መዝብሮና አስመዝብሮ ወደውጭ የላከ፣ ከቀሪው 38 ቢሊዮን ዶላር ውስጥም በሙስናና ንቅዘት የአንበሣ ድርሻውን አውድሞ በተረፈችዋ መናኛ ፍራንክ ጥቂት የአስፋልት መንገዶችንና የልማት አውታሮችን ለታይታ ያህል ዘረጋ እንጂ እምነት የሚጣልበት አይደለም፡፡ አደጋ አለው ወገኖቼ! መንግሥት ቢኖረን ወገናችን እንደጨው ዘር በመላዋ ዓለም ይበተን ነበርን?
ሠ. ሥራ አለው ከሚባለው ዜጋ የማይናቅ ቁጥር ያለው ወገን ለሥራ ያለው ተነሳሽነትና የሙያ ፍቅር አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን የሚናገሩ አሉ፡፡ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ለይስሙላና ለሰዓት ፊርማ ቢሮ ይገባሉ እንጂ አጥጋቢ ሥራ እንደማይሠሩ፣ የሥራ ፍቅርና ወኔ እንደሌላቸው፣ ሥራ ገበታቸው ላይ ተገኝተዋል እንዲባሉ ብቻ ግን እንዲሁ ወለም ዘለም እያሉ ውለው እንደሚሄዱ ከጥርጣሬ በላይ ገሃድ እየሆነ መምጣቱ ይወራል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሥራን በአግባቡ ያለመሥራት ወይም ሊያሠራ የሚችል አካል መጥፋት ሀገሪቱን ባለቤት አልባ እንደሆነች ያስጠረጥራል፡፡ ብዙዎች እንደሚሉት በየመሥሪያ ቤቱ ከቅርጽ ባለፈ አጥጋቢ የሥራ ሂደት እንደማይከናወን ይታመናል፡፡ የደንበኞች አገልግሎት በሚሰጥባቸው ብዙ የመንግሥት መ/ቤቶች ደግሞ ባለጉዳዮች በደቂቃዎች ለሚያልቅ አነስተኛ ነገር ብዙ ሣምንታትንና ወራትን እንደሚጉላሉ የታወቀ ነው፡፡ በብዙ ቦታዎች በእጅ ተሂዶ ምንም ጉዳይ አይፈጸምም፤ በጅ ተሄዶም ቢሆን ‹የሉም፤ ስብሰባ ላይ ናቸው…› እየተባለ መመላለስ የተለመደ ነው፡፡ አደጋ አለው!
ረ. በየቦታው ትዳር እየፈረሰ፣ ልጆች ወደ ጎዳና እየተበተኑ፣ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸው አእሩግ ወደበረንዳና ወደደጀሰላሞች እያቀኑ በውጤቱም ማኅበራዊ ሕይወት ክፉኛ እየተናጋ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአንዲት ሀገር ውስጥ የትልቅ ችግር መስፋፋትን ያመለክታል፡፡ ቤተሰብ የማኅበረሰብ መሠረት ነው፤ ብዙ ቤተሰብ በሞራልና በሃይማኖት እየዘቀጠ ሲመጣ በሂደት ችገሩ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ጫና ያመጣና መሪዎቹም የዚሁ የሞራልና የሃይማኖት መላሸቅ ውጤቶች ሆነው አሁን እኛና ኢትዮጵያ እየተሰቃየንበት ያለው ነገር ፋሽን እንደሆነ ይቀራል፡፡ በዚህ ረገድም አደጋ አለብን፡፡ ዘር መተካት አቅቶናል፡፡ ከአሁኑ ዘመን ይልቅ የወደፊቱ በእጅጉ አሳሳቢ ነው፡፡ ሀገሪቱን ማን ይረከባት? በጎጠኝት ምች የተመታ ወያያዊ ከፋፋይ ትውልድ ወይንስ ሰፊ ራዕይ ያለው ሁሉንም በእኩልነት የሚመለከት የዘመናዊ አስተሳሰብ ባለቤት የሆነ ትውልድ? ሁለተኞቹና ‹ቆንጆዎቹ› የት አሉ? ተወልደዋል ወይንስ ገና ምጥ ላይ ነን?
ሰ. በኑሮው ጥመትና በኢኮኖሚው ድቀት ምክንያት ዜጎች አእምሯቸውን መቆጣጠር እየተሳናቸው በተለይ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የሚታየው የዕብዶችና የወፈፌዎች ብዛት ከግምት በላይ ሆኗል፡፡ ሆስፒታሎችና አውራ ጎዳናዎች የተጨናነቁት በየሴኮንዱ በሚወፍፉ ዜጎች ነው፤ ልብ ያለው ሰው የተገኘ ግን አይመስለኝም፡፡ በመሆኑም ዕብደትን የሚያባብስ እንጂ የሚቀንስ ነገር ሲከናወን አላይም፡፡ ሀገራዊ ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ዘንድሮ ካበደው ይልቅ በመጪው ዓመት ለማበድ እየተሰናዳ ያለው በእጅጉ ይብሳል፡፡ በየመንገዱ ብቻውን እያወራ የሚሄደው ወገናችን ብዙ ነው በማለት ብቻ አንገልጸውም – ሱፉን ግጥም አድርጎ ለብሶ እጁን ከወዲያ ወዲህ እያወናጨፈና ብቻውን እያወራ አስፋልቱን ሲያቋርጥ ስታየው በዚያ ጎበዝ ኢትዮጵያዊ ዕድል አንጀትህ ይላወሳል – ነገ አንተም እንደሱ እንደማትሆን ደግሞ እርግጠኛ መሆን አትችልም – እስካሁን ካልሆንክ፡፡ አደጋ አለው!
ሸ. በሰውነት ውስጥ ነጭ የደም ሕዋስ ሲበዛ አንዳች በሽታ እንዳለ ይገመታል – በአንዲት ሀገር ውስጥ የወታደሮች ባልተለመደ ሁኔታ መርመስመስና መራወጥ አንዳች የፀጥታ ችግር መከሰቱን እንደሚጠቁም ሁሉ ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አንዲት ሀገር ውስጥ የጫት ቃሚዎች፣ የጠጪዎችና የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ሄዶ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከደረሰ ያች ሀገር ወዮላት! እንደሚመስለኝ በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ውስጥ የተደሰተውም ይጠጣል – ያዘነውም ይጠጣል፡፡ የከፋውም ይቅማል – የተደሰተውም ይቅማል… ‹የዘገነም አዘነ፣ ያልዘገነም አዘነ›፡፡ እርግጥ ነው – መጽሐፉ ‹ድሃ ጭንቀቱን ይረሳ ዘንድ የወይን ጠጅ ይጠጣ› ይላል፡፡ ከዚህ አንጻር የድሆች ተረከዛቸውን ወትፈው ያገኙትን መጠጣታቸው በተወሰነ መልኩ ይገባኛል – እኔም አለሁበትና፡፡ የሀብታሞች መጠንበዝ ግን ግራ ነው እሚያጋባኝ – የሚያስጨንቁንን ለመርሳት ይሆን? ዋናው ግን በአንዲት ሀገር የጠጭዎችና የጫት ቃሚዎች እንዲሁም የሀሺሽ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየገነነ ከመጣ በዚያች ሀገር አንዳች የተስፋ መቁረጥ መንፈስ እየተበራከተ ነውና አሁንም አደጋ አለው፡፡ እርግጥ ነው – አምባገነን ገዢዎች ይህንን መሰሉን ሕዝባዊ ተስፋ መቁረጥና አልባሌ ተግባር ውስጥ ገብቶ መደበቅ ይወዱታል – እንደወያኔ ዓይነቶቹ ስግብግቦች ሳይሆኑ እንደኮሚኒስት ራሽያ ዓይነቶቹ ይህንን የጥንበዛ ፕሮግራም በገንዘብ ይደጉማሉ፤ በተዛዋሪም ያረታታሉ – ሰው በሥካር ውስጥ ተዘፍቆ ፖለቲካቸውን እንዳያስብ፡፡ ‹ያውጡብሽ እምቢ፣ ያግቡብሽ እምቢ› ዓይነቱ ወያኔ ግን በገንዘብ ፍቅር በማበዱ ምክንያት ሁሉንም አክርሮ ሰውን መደበቂያ እንኳ በማሳጣት በገላጣ ሥፍራ ላይ በየአቅጣጫው ሕዝበ አዳምን በጅራፍ እየሸነቆጠው ነው፡፡ ይሄ ቫት እሚሉት ነገር በሁሉም ዘርፍ ገብቶ የመጠጡም የምግቡም ዋጋ በመሰቀሉ አብዛኛው ሕዝብ ታዛቢ እንጂ ተሣታፊ ሊሆን አልቻለም፡፡
ቀ. በአንድ ሀገር ውስጥ ጧት ቤተ ክርስቲያን ወይም መስጂድ ያገኘኸው ሰው ማታ ጠንቋይ ቤት ካየኸው በዚያ ሀገር ውስጥ መስተካከል የሚገባው የተበላሸ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ እንደማይዋጣ ሁሉ ለሁለት ጌቶች ለመገዛት መሞከር ችግርን በራስ ላይ መጋበዝ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ችግር በሀገራችን በስፋት ስለሚስተዋል የዕድገታችን ምልክት ሳይሆን የመንፈሳዊ ድቀታችን ዓይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ ታላላቅ የኪነ ጥበብ፣ የንግድ፣ የፖለቲካና የአትሌቲክስ ዘርፎችን በዋናነት ጨምሮ ብዙ ሰው በዚህ ብልሹ ሕይወት ውስጥ መመላለሱን መረዳት አይከብድም – በጥንቆላ ባገኘው ገንዘብ ቤተ ክርስቲያን የሠራ ሰው አውቃለሁ – አንድ ብቻም አይደለም – በዚህ መልክ ፈጣሪን ጡጦ እንዳልጣለ ሕጻን እየቆጠሩ ሊያታልሉት የሚሞክሩ እጅግ ብዙ ሰዎች አሉ ፤ ካህናትንና ቃለ እግዚአብሔርን ዐዋቂዎችን ጨምሮ – እሱው በምሕረቱ ያስባቸው፡፡ ‹የሐሙሱ ፈረስ› በጣም ከፍተኛ የሆነ አፍራሽ ሚና እየተጫወተብን አለ – አንድ ታምራት የሚሉት ዓይነት አራተኛ ክፍልን በቅጡ ያልጨረሰ የሚባል አጭበርባሪ ጠንቋይና አንዲት ‹ማርያም ነኝ› የምትል ማይም ሴት እንዲሁም ባህታዊ ነኝ ባይ አፈ ቅቤ ‹ሊቀ ትጉሃን› በቀላሉ የሚያታልለን/ የሚያነሆልለንና ወደተፈለገው አዘቅት የሚያሰምጠን ሕዝብ ከሆንን ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱም ጭምር አደጋ አለው! በዬጉራንጉሩ እየሄድን ብናይ ብዙዎቻችን ከዕውቀት ማዕድ የመራቃችን ጣጣ ያመጣብን ጠንቅ ሥር ሰድዶ እግር ከወርች የጠፈነገን መሆናችነን እንገነዘባለን፡፡ እግዚአብሔር በቶሎ ካልደረሰልን በቁማችን ጠፍተናል ወገኖቼ፡፡
ተ. በአንዲት ሀገር ውስጥ ጉቦ ወይም ሙስና እግር አውጥቶ የሚሄድ ከሆነ ወዮ ለዚያች ሀገር ሕዝብ! ሕግም ሥርዓትም ፍትህም… በግለሰቦች ፈቃድ የሚወሰኑ እንጂ አድልኦ የሌለበት ሕግን መሠረት አድርገው በአስተዋይነትና በጥበብ የሚከናወኑ አይሆኑም፡፡ በአንዲት ሀገር ውስጥ ወሳኙ የበላይ አለቃ ገንዘብ ከሆነ የሕዝቡና የመንግሥቱ ግንኙነት ልክ እንደተራ የአከራይ ተከራይ ግንኙነት ነው ማለት ነው፡፡ አንድ አከራይ ያከራየውን ሰው ሲፈልግ ‹ምነው ወንድም – ቀስ ብለህ አስነጠስ እንጂ! ለጣራና ኮርኒሱም አስብለት› ወይም ‹የኔ እህት በቀን አንድ ባልዲ ተዋዋልን እንጂ በጆግ ማን ጨምሪ አለሽ?› እንደሚባሉ ሁሉ መንግሥትና ግለሰብ ከተቀላቀሉ ልክ በመለስና በመንግሥቱ ኃ/ ማርያም እንዳየነው የሚሊዮኖች ዕጣ ፋንታ በአንድ ጫታም ወይም በአንድ ሠካራም ወይም በአንድ ሀበሾኣምና ሀሺሻም እየተወሰነ ሕዝብ ዐይኑ እያየ እንጦርጦስ ይወርዳል ማለት ነው፡፡ የ80 እና 90 ሚሊዮን ሕዝብ የመኖርና ያለመኖር ዕጣ በአንድ ግለሰብ ወይም እልፍ ሲልም በአንድ የወሮበሎች ጭፍራ የሚወሰን ከሆነ ወዮ ለዚያ ሀገር ሕዝብ! ከዚህ አንጻር በሀገራችን ትልቅ አደጋ አለ፡፡ ይህ አደጋ በቅርብ ካልተገፈፈ የኛንስ ተውት ከሞላ ጎደል ጨርሰነዋል – ተተኪ ግን አይኖረንም፡፡
ቸ. በአንድ ሀገር ውስጥ የኢምግሬሽን ቢሮ በጣም ሥራ የሚበዛበት ከሆነና የተሰዳጁ ሕዝብ ቁጥር ከበዛ በዚያ ሀገር ውስጥ ከፍተኛ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ የኛን ሀገር ሁኔታ ከዚህ ነጥብ አኳያ ብመለከተው ልዩ ታሪክ እንታዘባለን፡፡ ጥቁር አንበሣ አካባቢ የሚገኘውን የኢሚግሬሽን ቢሮ ተመልከቱ፤ እንደዝናር ጥይት በዕጥፍ ድርብ ዙሪያውን እየተጠማዘዘ የሚሰለፈው ሕዝብ ለሽርሸር ወይም ለቱሪስትነት ሳይሆን በምትቀና ሚስት ከፎቅ ለመወርወር ወድዳና ፈቅዳ የተዘጋጀች ወጣት ሴትና በዘበኝነትም ይሁን በአትክልተኝነት ሠርቼ ትንሽ ፍራንክ ልቋጥርና ቤተሰቤን ልደግፍ ብሎ የቆረጠ ጉብል ናቸው፡፡ ዜጎች አለኝታ ሲያጡ የሚሰማቸው መሪር ስሜት ለእንደዚህ ያለ የባርነት ሕይወት ዐይናቸውን እንዳያሹ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህ ሂደት ሀገሬ ብሎ ለባንዴራው የሚዋደቅ ወጣት አይኖርም – ለጊዜው ሀገርም ሁላችንን የሚያስማማ ባንዴራም ባይኖረንም፡፡ በዚያ መንገድ ሳልፍ በእጅጉ አፍራለሁ – የኢቲቪ የሀገር ዕድገት ዲስኩር ትዝ እያለኝም በውስጤ ፈገግ ማለቴ አይቀርም፡፡ ከዋሹ አይቀር ታዲያ እንዲህ ነው፡፡ መላው ዜጋ ከሀገር ለመውጣት ሌት ከቀን ተሰልፎ በሚታይበት ሁኔታ ሀገር አድጋለች እያሉ ማንቋረሩ ማንን ለማታለል እንደሆነ ፈጽሞ አይገባኝም፡፡ የሚያደርጉትን አያውቁምና ፈጣሪ ይቅር ይበላቸው፡፡
ኀ. ከፍ ሲል በጨረፍታ ለመግለፅ እንደተሞከረው የሴተኛ አዳሪነት አለቅጥ መስፋፋት፣ የዘመድ አሠራር(ሥራ ለመቀጠር፣ ለዕድገትና ለሹመት…)፣ የሀገሪቱ ዋና ዋና የሥልጣንና የጥቅም ቦታዎች በአንድ ብሔር ሥር ተጠቃሎ መግባትና ሌሎችን ባይተዋር ማድረግ፣ ኢትዮጵያዊነት የአባት ገዳይ ይመስል ጥምድ አድርጎ መያዝና ለዚህች ታሪካዊት ሀገር ትንሣኤ የሚተጉ ዜጎችን በገቡበት እየገቡ ማሳደድ… የዕድገት ምልክቶች ሳይሆኑ የክስረት መገለጫዎች ናቸውና በእንፉቅቅ እየመጣ ያለው የዕልቂት ዘመን ድንገት ሳይደርስብን – በተለዋጭ ቃላት ልድገመው – ቢዘገይም እንኳን መምጣቱ በጭራሽ የማይቀረው የመቅሰፍት ዘመን ሳይመጣብን እገሌ ከእገሌ ሳንል ሁላችን ወደየኅሊናችን እንመለስና እያንዣበበብን ያለውን ከፍተኛ አደጋ እንግፈፍ፤ ኋላ ጊዜ ላይኖረን ይችላልና፡፡
ነ. ከዚህ በላይ በድርበቡ የተጠቀሱ ነገሮች በሙሉ ኢትዮጵያና ልጆቿ በቋንቋ ሊገለጽ የማይችል የችግር አረንቋ ውስጥ እንደገቡ የሚያመለክቱ ናቸው፤ ስለሆነም መፍትሔ ያሻቸዋል፡፡ መፍትሔው ደግሞ አንድም ከሰው አንድም ከእግዜር ነው፡፡ የሰው እስካሁን አልተሳካም – በተለያዩ ሰውኛ ምክንያች የተነሣ፡፡ የእግዜሩ ግን ቀደም ሲል ጀምሯል – አሁንም ሳይቋረጥ በራሱ ጊዜና በራሱ ፍጥነት ቀጥሏል፤ ማንም ደግሞ አያደናቅፈውም፡፡ ለመነሻነት እነኚህን ሂደቶች ልብ በሉ፡፡ ከዚያም ቀጥሎ ምን ይሆን ይሆን? ብላችሁ ስለወደፊቱ አስቡ፡፡
ኘ. በ83ዓ.ም ሕወሓት ኢትዮጵያን የማጥፋት ትልሙን በአሜሪካን በጎ ፈቃድና ቡራኬ በሄርማን ኮኸን የፖለቲካዊ ፕትርክና ቡራኬ መንግሥት ሆኖ በይፋ ጀመረ፡፡ ከትክክለኛው የጊዜ አቆጣጠር አንጻር ከአራት ዓመታት ገደማ በኋላ በ88 ትልቅ የመሰነጣጠቅ ጥፊ ደረሰበት – የጊዜው ጠ/ሚኒስትር ታምራት ላይኔ በ”ስኳር ቅሌት” ወህኒ ወረደ፡፡ አንድ በሉ፡፡ ሦስት ዓመታትን ቆይቶ በ90ዓ.ም ያልታሰበ ዱብ ዕዳ ወርዶ ከፍተኛ ዕልቂት ያስከተለ የሻዕቢያና ወያኔ የማይጠገን ስብራት ደረሰ፡፡ ሁለት በሉ፡፡ ፈጣሪ ሌሎች ሦስት ዓመታትን ታግሦ ወያኔ ራሱ በውስጥ ደዌ እንዲመታ አደረገና የሕወሓት መንደር ምንቅርቅሩ ወጣ – በሻዕቢያም በኩል እንደዚሁ፡፡ ሦስት በሉ፡፡ አራት ዓመታትን ቆይቶ በ97ዓ.ም ወያኔን እርቃኑን ያወጣ ሀገራዊ ክስተት ተፈጠረ፡፡ አራት በሉ፡፡ ሌሎች አራት ዓመታትን ቆይቶ በ2001 እና ከዚያም በኋላ እሳቱ እማይጠፋ ትሉ እማያንቀላፋ የኑሮ ውድነት ባልታወቀ ኃይል ታወጀና በየቀኑ ሽቅብ በሚወረወር የዋጋ ንረት ሕዝብ ማልቀስና ዕንባውን ወደላይ ወደአርያም መፈንጠቅ ተያያዘ፡፡ ይህም ብሶት ከተጨማሪ ወያኔዊ የዕብሪትና የትምክህት ሥራዎች ጋር ተባብሮና ተደማምሮ ሌሎች የወያኔን ሥርዓት ማብቂያ አመላካች ምልክቶችን በግልጽም በሥውርም ያሳይ ያዘ፡፡ አምስት በሉ፡፡ ከሦስት ዓመታት በኋላ በ2004 መገባደጃ ላይ በዋልድባ ገዳምና በሕዝብ ዕንባ መዘዝ ታላላቁ የብኤል ዘቡል ወኪሎች አቶ መለስ ዜናዊና ሃይማኖትን በዓሣማ ጋጣ ላይ አጋድመው የረመረሙት “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ” ጳውሎስ የአጋንንት መንጋቸውን ደጅ ላይ ለብርድና ለንፋስ እንዳጋለጡ በፈጣሪ ልዩ ‹ሰርጂካል ኦፐሬሽን› ተመትተው እስወዲያኛው አሸለቡ – ሰማይ ምድርን ‹ዕፁብ ድንቅ› ያሰኘ ሰማያዊ በረከት፡፡ ስድስት በሉ፡፡ ፈጣሪ እንደዱሮው ሦስትና አራት ዓመታትን መጠበቅ ሳያስፈልገው በዓመቱና አሁን ደግሞ ምን እየሠራ እንደሆነ በዐይናችን በብረቱ እያየን ነው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን እኛ ሀገር ቤት ያለነው ምሥኪን ዜጎችም ሆንን የተቃውሞው ጎራ በየአምበሉና በየጎራው እየተቧደነ የነገር ጦር ከመስበቅ፣ በደብዳቤና በድርጅታዊ መግለጫ ‹የጦፈ ጦርነት› ከማካሄድ በዘለለ አንዳች አስተዋፅዖ አድርገን ከሆነ ገና ወደፊት የሚጣራ ይሆናል፤ የታሪክ አጣሪ ኮሚሽን ብዙ ሥራ ሊሠራ ከፊት ለፊታችን ቆሞኣለ፡፡
አ.. የተኛም ይተኛ፤ ያንቀላፋም ያንቀላፋ፤ የደከመም ይድከም፤ የተሸነፈም ይሸነፍ፤ አብሮና ተባብሮ የሚዘርፍና የሚያዘርፍ – የሚገድልና የሚያስገድልም – ይዝረፍም ይግደልም፡፡ እኛ ደግሞ እንጮሃለን፤ የሚያነብብ ያንብ፤ የሚሰማ ይስማ፤ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ እንደጨለመ አይቀርም፤ ያኔ የጨለማው ውስጥ ብካያችን በገሃድ ይገለጥና በምን ዓይነት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ምን ዓይነት የመከራ ሕይወት እያሳለፍን እንደነበር ቀጣዩ ትውልዳችን ይማራል፤ እንዲሆን የታዘዘን ከመሆን የሚያሰናክል የለም፤ ሁሉም በጊዜው ይሆናል፡፡ ጠቢቡ ቀድሞ ተናግሮታል – ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም፡፡ የብርሃንና የጨለማ መፈራረቅም የነበረ እንጂ ዛሬ የተጀመረ አይደለም፡፡ አገኘሁ ብለህ አትኩራ፤ አጣሁ ብለህም ከመጠን ባለፈ አትፍራ፡፡ ይልቁንስ ሰው ለመሆን ጣር – ሰው ሆኖ መገኘት ትልቅ የወቅቱ ፈተና ነውና፤… ከገዳይ ይልቅ ሟች የበለጠ የፅድቅ ቦታ አለው፤ ጊዜው ቀርቧል፡፡ ለዚያ ጊዜ ወዮ እንበል!!
ከ. እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አብዝቶ ይባርክ፤ ለሦርያና ለኢራቅ ከተመዘዘ ሠይፍና ጦርም ይሠውረን፡፡ የጥጋበኞችን ጥጋብ ወደስክነት፣ የትዕቢተኞችን ዕብሪት ወደብስለት፣ የጠይዎችን ጥላቻ ወደፍቅር፣ የሆዳሞችን ስግብግብነት ወደእርካታ ለውጦ ያለብዙ ወጪ በሚገነባ አዲስ ስብዕና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ባለቤቶች ያድርገን – ይቻለዋልና፡፡ (የፊደል ተራ ቅደም ተከተሉን ልክ እሆን ብላችሁ ነው?)
ኸ. በቀናነት ለሚያስተምረኝና ጉድለቴን ለሚሞላልኝ ብቻ አድራሻየ ከምሥጋና ጋር ይሄውና፡- ma74085@gmail.com
ሠርቶ ወይንስ ሰርቆ? ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ሰሞኑን አዲስ አበባን የሚዘዋወር ሰው በብዙ አካባቢዎች ከሚያያቸው ወያኔያዊ መፈክሮች አንዱና ጎልቶ የሚታየው “በሀገር ውስጥ ሠርቶ መለወጥ ይቻላል!” የሚለው ነው፡፡በትላልቅ የጨርቅ ጀንዲዎች ላይ ከባባድ ተምኔቶችን በመፈክርነት ጽፎ በየአደባባዩ መስቀል የወያኔ ትልቁ መገለጫ ነው – የደርግም፡፡ ግን አብዛኞቹ መፈክሮች ከምኞትና ሰውን ከማቁልጭለጭ አልፈው አያውቁም – የሁለቱም፡፡ ያን ስንት ድሃ ሊያለብስ በሚችል አቡጄዲ የተሰቀለ መፈክር ሳነብ ወዲያው ያልኩት ‹በሀገር ውስጥ ሠርቀህ መለወጥ ይቻላል›፡፡ (ሠርተው በድካማቸው ፍሬ የሚያልፍላቸው የሉም ማለት በመሠረቱ ስህተት ነው፤ ሠርተህ ሲያልፍልህ ግን በሥራህና በቁሣዊ ዕድገትህ መካከል የሚጠበቅ የጊዜ፣ የመነሻ ወረት፣ የጥረት፣ የትርፍ ‹ማሪጂን›፣ የዕውቀት፣ ለመክሰር የመዘጋጀት፣ ከሠራተኞች ጋር የሚኖር የጥቅማ ጥቅምና የመሳሰለው ግንኙነት ሊታዩ ይገባል፡፡ አለበለዚያ እንደወያኔ ሀብታም ትናንት ሥራ ጀምረህ በማግሥቱ ቀጭን ጌታ ከሆንክ ከሥራህ ቀድሞ ብልግናህ ማለቴ ብልጽግናህ ታዬ እንደማለት ነውና ይህ ንግድ ሳይን ማጅራት መምታት ነው – እኛ ባልተወለደ አንጀት እየተመታን እንዳለነው፡፡)
በላይኛው አንቀጽ የጠቀስኩትን መፈክር ሳነብ እስቃለሁ፤ ፍርፍር ብዬ ነው የምስቀው፡፡ ምክንያት አለኝ፡፡ ትልቅ ምክንያት፡፡ ለዝርዝሩ በ‹አዲስ መስመር እንገናኝ› – (ኩረጃ በኔ አልተጀመረም)፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአሁኑ ዘመን ሠርተህ ሊያልፍልህ አይችልም፡፡ በየትኛው ሒሣብ? ኧረ እንዴት ተደርጎ? ምን ሠርተህና ማንስ አሠርቶህ? ሕግን ጠብቀህ ከሠራህ የመጀመሪያው ከሣሪ አንተ ነህ፡፡ ቀረጡ፣ ግብሩ፣ ኪራዩ ባንተ በሕጋዊው ነጋዴ ላይ ይቆለላል፡፡ ባይገርምህ ከዘር አኳያ ማውራት ስልችት አለኝ እንጂ ወያኔዎች አንድን ትግሬ ያልሆነ ምሥኪን ነጋዴ በነባሩ የመንግሥት የኪራይ ቤት ላይ – ለምሳሌ የ200 ብሩን ኪራይ በአንድ ጊዜ 10000 በማድረግ እሱ አጨብጭቦ – አብዶም ሊሆን ይችላል – ሲወጣላቸው ከ200 ባነሰ ኪራይ ‹የኛ ነው› ለሚሉት ሰው የሚያከራዩ ዓለም ከምታመርታቸው ግፈኛ ዜጎቿ መካከል ተወዳዳሪ የሌላቸው አረመኔዎች ናቸው ብዬ ብናገር ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ሂድ አይሉህም – እንድትሄድ ግን ያደርጉሃል፡፡ በትግርኛ ‹ውፃዕ አይተበሎ፤ ከምፅወፅዕ ግበሮ› ይባላል፡፡ የተንኮልና የወንጀል ማምረቻ ዘመናዊ ፋብሪካዎች ናቸው፡፡ ግፋቸውና የሸራቸው ድርና ማግ ተጎልጉሎ አያልቅም፡፡
ስለ “ባገር‹ህ› ሠርተህ ያልፍልሃል” የማሞኛ ፈሊጥ የኔን ልናገር፡፡ ሰለቸኝ፤ ደከመኝ፣ አጣሁ – ገረጣሁ ሳልል በንጹሕ ኅሊና ራሴንና ቤተሰቤን ለማኖርና ሀገሬን በሙያየ ለማገልገል ከሙያዎች በአንዱ ተሠማርቼ መሥራት ከጀመርኩ ጥቂት አሠርት ዓመታት አለፉ፡፡ የጀመርኩበት ደሞዝ የኢት. ብር 500 ነበር – ለእናት ሀገር ጥሪና (በአሁኑ የወያኔ ዘመን የአባይ ግድብ ዓይነት መሆኑ ነው) ለጡረታ ተቆራርጦ ብር 385 ይደርሰኝ ነበር፡፡ ለተለያዩ የሠራተኞች ድንገተኛ የንብረት መጥፋትና ሞትን ጨምሮ የጤና መጓደል ችግሮች ከተከሰቱም እንደብሔራዊ ሎቶሪ የዕጣ ቀን ደመወዝ መክፈያ ቢሮ ተኮልኩለው የሚጠብቁ የደመወዝ ቀበኞች ካሉም የሚደርሰኝ ገንዘብ ከዚያም ሊያንስ ይችላል፡፡ ለማንኛውም ያንን ገንዘብ ወስጄ ወር እስከ ወር የመድረስ ግዴታ ነበረብኝ፡፡ ቀስ እያለ ቤተሰብ ስጨምር ደመወዙም እያሽኮተኮተ አንድ ሺን መጠጋቱና ማለፉም አልቀረም፡፡ ያኔ ታዲያ አልዘባነን እንጂ በቤቴ ውስጥ በተለይ በምግብና በመጠጥ በልብስም ያን ያህል እንዳሁኑ የጎላ ችግር አልነበረብኝም፡፡ በአንጻራዊ ሁኔታ ሁሉም ነገር እርካሽ ስለነበር በጣም መቀናጣት ይቅር እንጂ መሠረታዊ ፍላጎቶቼን ማሟላት የሚሳነኝ አልነበርኩም፡፡
አሁን ግን አጠቃላይ የወር ገቢዬ ወደ አምስት ሺህ ብር ገደማ ደርሶ መማል ሳያስፈልገኝ እውነቱን ለመናገር ከወር እወር እምደርሰው ብዙ ፍላጎቶቼን ለምሳሌ የእንስሳት ተዋፅዖዎችን፣ አትክልትና ፍራፍሬ ወዘተ. ለማሟላት መከጀል ብቻም ሳይሆን ለማሰብም ዕድል ሳላገኝ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የምትኖሩ ዜጎች የአራት ሺህ ብር የተጣራ ደመወዝን ገንዘባዊ ዋጋ ታውቃላችሁና ይህን ለማስረዳት ብዙ መድከም አይገባኝም፡፡
እኔ – ልብ አድርጉ – ይህን መጠን የማገኘው ሁለት ቦታ ሠርቼ ነው፡፡ እንዲህ የምላችሁ “ተጨማሪ ሥራ ሥራ” ብላችሁ ለምትመክሩኝ ነው፡፡ ምን አለፋችሁ – ኢትዮጵያ ውስጥ ካላጭበረበርክና ካልሰረቅህ በቀን 48 ሰዓት ብትሠራ ከጓያ ሽሮ አታልፍም፡፡ ሰዎች እንዴት ይኖራሉ ታዲያ? ብለህ ስትጠይቅ ብዙ ነገር ዕንቆቅልሽ ሊሆንብህ ይችላል፡፡ ጠጋ ብለህ ከመረመርክ ግን ግልጽ ነው፡፡
ብዙ ሰዎች በተለይም ወጣች የተዘባነነ ሕይወት ሲመሩ ታያለህ – የአህያ ጆሮውን ከየኪሣቸው እየመዘረጡ፣ በቆንጆ መኪናዎቻቸው እየተንፈላሰሱ፣ በየቀኑ የሚቀያየሩ ቆነጃጅትን እጎናቸው ሻጥ እያደረጉ፣ ሙዚቃቸውን ልክ እንደኬንያ ማታቱ እስከጣራ ለቅቀው ከትከሻቸው ጀምሮ በስሜት እየተወዛወዙ በከተማዋ ሲንሸራሸሩ … ማታና ውድቅት ላይም በየጭፈራና ዳንኪራ ቤቱ እየተውረገረጉ ታያቸዋለህ፤ እነዚህ ወጣቶች የሚያቀርቡልህን ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን በሌለህ ኢኮኖሚ ከአቅምህ በላይ እየተበጣጠስክ – እየተበደርክ እየተለቀትክ – ያልኖርክበትን ጊዜ ደመወዝም በሞዴል ስድስትና ከብድርና ቁጠባ እየተበደርክ የምትገዛው የነሱ ድሎት እንዳይጓደል መሆኑን ታዲያ ዕወቅ፡፡ በዚያውም ላይ አንተ ለሀገርህ ብዙ ለፍተህና ደክመህ ስታበቃ የነተበ ሸሚዝ፣ የተንሻፈፈና አቧራ የሚቅም ጫማ፣ መልኩን ከአንዴም አልፎ ሁለት ሦስቴ የቀየረ ኮት ወይም ጃኬት፣ አንገቱ በዐይጥ የተበላ የሚመስል የተቦተረፈ ካናቴራ… ለብሰህ ተቆሳቁለህ ትታያለህ – መጥፎ የማይባል ደመወዝ እያገኘህ፡፡ ሀገራችን በቅጡ ልትመረመር ይገባታል፡፡ የኑሮ ልዩነት የትም ሀገር ያለ ቢሆንም የኛ ግን ከየትኛውም ጋር አይወዳደርም፡፡
ብዙ ነገሮች ብልጭልጭ ናቸው – የምታየው እውነት ከምትሰማው እውነት ይለይብሃል፡፡ የምትኖረው ሕይወት እንደምትኖር ከሚነገርልህ ሕይወት የተለዬ ነው፡፡ የተያዘው የአፍ ጂዶ ነው፡፡
የዕለትም ይሁን የወር ገቢውን በራሱ የሚወስን ሰው ጥሩ ሊኖር ይችላል፡፡ ምክንያቱም ገበያውን ተከትሎ – ወጪና ገቢውን አጢኖ የሚሸጠውን ዕቃ ዋጋ ወይም የአገልግሎት ክፍያ በዚያው መጠን ያስተካክላልና፡፡ እንደኔ ዓይነቱ መንግሥት ወይም አሠሪየ የደነገገልኝን ወርሃዊ ምንዳ የሚያገኝ ሰው ግን ሕይወቱ በመኖርና ባለመኖር አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ወደሌላኛው ዓለም እስኪጠራ ድረስ በነፍስ በሥጋም ይዋትታል፡፡ በዚህ ሁኔታ “ሀገርህ ውስጥ ሠርተህ መለወጥ ትችላለህ” ሲሉህ ብትሰማ አቅመቢስነትህን ተረድተው በደካማ ጎንህ እየቀለዱ ሊያስቁብህ እንደሆነ ይገባሃል፡፡ ለሠላሣ ዓመታት በተመሥጋኝነት የሠራሁ ሰውዬ በስተርጅናየ ደመወዜ አልበቃኝ ብሎ ለልመና ልዳረግ ምንም ባልቀረኝ ሁኔታ ይህ የወያኔ አባባል ምን ስም ሊሰጠው እንደሚችል አይገባኝም፤ “በሀገር ውስጥ ሠርቶ መለወጥ ይቻላል፡፡”
ወጣት የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎችንና ልዩ ልዩ የግለሰብም ይሁን የመንግሥት ተቀጣሪዎችን ኑሮ ብታዩ ይዘገንናችኋል፡፡ ያልሞትን የመሰልነው እራፊ ጨርቅ ትከሻችን ላይ ጣል አድርገን በየመንገዱ ወንከር ወንከር ስንል ስለምንታይ እንጂ ከሞትን ቆይተናል፡፡ እስኪ የእግር ኳስ ጨዋ ልናይ ስቴዲየም ስንገባ እዩን – ከዚያ በነአርሰናልና ማንችስተር ጨዋታ ጊዜ ስቴዲየም የሚገባውን የአውሮፓን ጨዋታ ተመልካች ደግሞ እዩ – አወዳድሩንና የጉስቁልናችንን ደረጃ ታዘቡ – እኛን ያፈራ መንግሥት ነው እንግዲህ በምሥኪን ጎስቋሎች ላይ በደረሰው የፈጠራ ተውኔት እየተኮፈሰ ‹አድጋችኋል› እያለ በሬሣችን ላይ እያላገጠ የሚገኘው፡፡ ጭንቅላት የሌላቸው ደግሞ መንግሥት ተብዬው ብቻ ሳይሆን ባለሀብቶችም ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች – ጨካኝ አትበሉኝና – መቅሰፍት ቢወርድባቸው ደስተኛ ሀዘንተኛ ነኝ፡፡ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡ ማሰብ አይችሉም፤ እነሱ ያላቸው የመኖር መብት ሠራተኞቻቸው ያላቸው አይመስላቸውም፡፡ እነሱ እየተንደላቀቁ ሲኖሩ ሠራተኞቻቸው በስቃይና በመከራ ይኖራሉ፡፡ እነሱ በበርሜል እየዛቁ አዝመራውን ወደቤታቸው ሲከቱ ለሠራተኞቻቸው የሚከፍሉት ደሞዝ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ እናም የእውነት አምላክ እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጣቸው፡፡…
ስለዚህ ተቀጣሪ ሠራተኛ በመንግሥትም ሆነ በግል ተቀጥሮ መሥራትን ባይፈልግ አይፈረድበትም፡፡ የኗሪ አኗኗሪ ሆኖ በሀገሩና በቀየው በርሀብ አለንጋ እየተገረፈ ከሚሞት በማያውቀው ሀገር ተሰድዶ ከሁለቱ ዕድሎች በአንደኛው እንደፍጥርጥሩ መሆንን ይመኛል - መሞት ወይም መዳን፡፡ በሀገሩ የበይ ተመልካች ሆኖ ነቀዞችና ግሪሣዎች የገዛ ሀብት ንብረቱን ሲመዘብሩና እርሱን ለከፋ ድህነት ሲዳርጉ ከሚያይ ዐረብ ሀገርና አፍሪካ ሀገራት አይደለም የቀይ ባሕር ዓሣና በበረሃ እያደፈጡ የሰውነት አካልን ለመለዋወጫነት የሚዘርፉ ሽፍታዎች ሲሳይ መሆንን ይመርጣል – ተጠየቁ ቀላል ነው – እዚህም ሞት ነው – እዚያም ያው ሞት ነው፤ የሞት ደግሞ ነጭና ጥቁር የለውም፡፡ በበኩሌ ይህን የወጣቶቹን መጥፎ ምርጫ መደገፌ አይደለም፡፡ ነገር ግን እኛን በነሱ ቦታ ተክተን ስናስበው የምርጫዎች መጥበብ የማያስደርጉት ነገር እንደሌለ መረዳት አይከብደንም የሚል ግምት አለኝ፡፡ ሰው ሲጨክንብህ፤ ‹የኔ ዜጋ ነው፤ አለኝታውና ዋስ ከለላው ልሁንለት› የሚልህ ተቆርቋሪ መንግሥት በሀገርህ ስታጣ፣ የኔ መንግሥት የምትለው አንተን እንደባይተዋር ቆጥሮ የእንጀራ ልጁ ሲያደርግህና እርጎውንና ዐይቡን የኔ ለሚላቸው ወገኖች እየሰጠ ለአንተ ሞትንና እሥራትን የሚያከፋፍልህ ከሆነ ምርጫህ እግርህ ባወጣ ያቺን የሲዖል ምድር ኢትዮጵያ ለቅቀህ መሄድ ነው፡፡ ዜጎች እያደረጉ ያሉትም ይህንኑ ነው፡፡ ለአፍ አቀበት የለውምና መንግሥትና አሽቃባጭ የጥቅም ተጋሪዎቹ በያዙት ሚዲያ ቢያሽቃብጡ ሰርቆ እንጂ ሠርቶ ሊያልፍለት የሚችለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እጅግ አነስተኛ በመሆኑ አምላከ ኢትዮጵያ ፊቱን እስኪመልስልን ድረስ ያለን ብቸኛ አማራጭ ስደትና ፍልሰት ነው – እንደኔ ይህ ባይሆን ምርጫየ ነው፡፡ እናም ይህን “ከሠራህ በሀገርህ ያልፍልሃል” የሚሉትን ፈሊጥ ራሳቸው ለራሳቸው ይዘምሩት፤ እኔ ትልቁ አብነት ነኝ፤ ሠራሁ ፣ለፋሁ፣ ግን ምን ተጠቀምሁ? ባይገርማችሁ ለስደት የተነሳሳው ደህና ሥራ ያለው ሁሉ ነው፤ ሁሉም ሕዝብ ነው ለስደት የጓጓው ማለት ይቻላል፡፡ ግን ዕድሉ ጠባብ ነው፡፡ የኔ ዓይነቱ ጎምቱ ሰው ደግሞ ከእንግዲህ በኋላ ተነስቶ ነጋዴ ልሁን ቢል አንደኛ የወያኔ አሽቃባጭ መሆን ሊኖርበት ነው፤ ሁለተኛ የንግድን ሀሁ ስለማያውቅ ‹ሀ› ብሎ መማር አለበት፤ ሦስተኛ ሁሉም ሰው ነጋዴና ሁሉም ሰው ሸቃጭ ሊሆን አይጠበቅበትም፤ በሚሠራው ሥራ ሕይወቱን በአግባቡ ሊመራ የሚያስችለው ክፍያ እንደወቅቱ የገንዘብ የመግዛት አቅም እየተሰላ ሊከፈለው ሲገባ ‹ሁልህም ነጋዴ ሁን፤ ሁልህም እጅ መንሻ ወደሚያስገኝ ሥራ ተዛወር› ብሎ ፍርደ ገምድል ብያኔ መስጠቱ አግባብ አይመስለኝም፡፡
ተንቀባርረው ስለሚኖሩ ዜጎች ትንሽ ልጨምር፡፡ እነዚህ እጅጉን “የሚያስቀና” ቁሣዊ ሕይወት የሚመሩ ዜጎች ባጭሩ እነዚህ ናቸው፡- ኅሊናቸውን ለገንዘብና ለሥልጣን የሸጡ ወያኔዎች፣ የወያኔ ጋሻ ጃግሬዎች፣ ብር እንደፈለጉ እንደሚያሣትሙ የሚወራላቸው የሥርዓቱ ምሰሦዎችና ወጋግራዎች፣ በማንኛውም ዓይነት መንግሥታዊም ይሁን ኅሊናዊ ወይም ሃይማኖታዊ ሕግ የማይገዙ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ጥገኛ ነጋዴዎች፣ ካለቀረጥና ካለግብር ዕቃ ከውጭ እያስገቡ እንደፈለጉ በሀገሪቱ ላይ የሚፈነጩ ዘበናይ አልቅቶችና መዥገሮች፣ ከቻይናና መሰል ነፍሰ በላ ሀገሮች ‹ፌክ› ዕቃዎችን እያስመረቱ በጠፍ ጨረቃ በማስገባት በሕዝብ ሀብትና ገንዘብ የሚቀልዱ፣ ትላልቅ ደመወዝ የሚያገኙ የመያድና የዓለም አቀፍ ተቋማት ሠራተኞች፣ በሥራቸው አጋጣሚ ጉቦና ሙስና ውስጥ የሚዘፈቁና ደመወዛቸውን እስከመርሳት የሚደርሱ “የሕዝብ አገልጋዮች”፣ ቤትና ዕቃ የሚያከራዩ ሰዎች፣ ከሞላ ጎደል በሁሉም የሽያጭና የገንዘብ ዝውውር ከተፍ የሚሉ በጠበቀ መረብ የተደራጁ ደላሎች፣ የባንክና ኢንሹራንስ እንዲሁም የሌሎች ሴክተሮች የአክሲዮን ማኅበራትና ካምፓኒዎች ባለቤቶች፣ ለዲያብሎስ መንግሥት ያደሩ መታቾችና አስመታቾች፣ በሃይማኖትና በዕርዳታ ሽፋን ኅብረተሰቡ ውስጥ ለተለያየ ዓላማ የተሰገሰጉ ሃሳዊ መሢሆች፣ ከፍ ባለ የሽርሙጥና ‹ሙያ› ላይ የተሠማሩ ሴተኛ አዳሪዎች(በአንድ አዳር መኪና ወይ ቤት የሚያስገዙ እሳት የላሱ ሴቶች አሉ!)፣ ገንዘብ መራሽ አየር በአየር ነጋዴዎች፣ የመንግሥትን መሬት ከባለሥልጣናቱ ጋር እየተሻረኩ በብዛትና በነጻ በመውሰድ የሚቸበችቡ ዜጎች፣ የዕቃ ግዢ ሠራተኞች፣ ዕቃና ንብረትን በጨረታ ለመሸጥ ወይም ለመግዛት የሚቋቋሙ ኮሚቴዎች አባላት፣ በሀሰት የማወራረጃ ሠነድ የመንግሥትንም ይሁን የግል ድርጅትን ገንዘብ የሚሞልጩ ዜጎች፣… እነዚህና እነዚህን መሰል ወገኖች እኛ ብንራብና ብንጮህ፣ ብንሰደድና በአውሬ ተበልተን ብንሞት ያቺ ምሥኪን ታሪካዊት የፈረንሣይ ልዕልት ዳቦ ዳቦ እያሉ ለጮኹ ገበሬዎችና ሠራተኞች ‹ቤታቸው ሄደው ለምን ኬክ አይበሉም› እንዳለችው የኞች ደደቦችም ‹በሀገር ውስጥ ሠርቶ መለወጥ ይቻላል› ቢሉ የደደብነታቸው ብዛት ብዙም እንዳናዝንባቸው ያደርገናል፡፡
አንዲት ሀገር ውስጥ ችግር መኖሩን እንዴት እናውቃለን? ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሆነንን የትም ሳንዋትት ከቅርባችን ከሚገኘው የትዝብታችን ማኅደር ውስጥ እየመዘዝን ብዙ ነጥቦችን መናገር እንችላለን፡፡ ከዚህ በታች የምጠቅስላችሁ ሀገራዊ የጤናማነት መጓደል አመላካች ነጥቦች ራሴው የታዘብኳቸው ናቸው፡፡
ሀ. ዋጋው ቀነስ ወደሚለው ወደየትኛውም ሆስፒታልና የመንግሥት ጤና ጣቢያ ሂዱ፡፡ ለምሳሌ ጥቁር አንበሣ ሬፈራል ሆስፒታልን ላስቃኛችሁ፡፡ ይህ ሆስፒታል ከአዲስ አበባና ከክፍለ ሀገር በሚመጡ ህሙማንና አስታማሚዎች ሁልጊዜ (24/7) እንደተጨናነቀ ነው፡፡ ግቢው ውስጥ በአንድ ጊዜ ሲተረማመስ የምታዩት ሕዝብ ያለማጋነን የአንዲት ትንሽዬ ሀገር ጠቅላላ የሕዝብ ቁጥር ሊሆን ይችላል፡፡ የበሽተኛ መብዛት እንግዲህ የአንዲትን ሀገር የጤና ደረጃ ዝቅተኛነት ስለሚጠቁም (ድንገተኛ ወረርሽኝ – ኤፒደሚክ እስካልተከሰተ ድረስ ማለት ነው) የሚወራው የሀገራችን ዕድገት አፋዊ እንጂ እውናዊ ሊሆን አይችልም፡፡
በዚያ ላይ በየሆስፒታሉ የምናያቸው ዜጎቻችን የሚታይባቸው ጉስቁልና ልብን ይሰብራል፡፡ አለባበሳቸው፣ የሰውነት ይዞታቸው(ክሳት፣ግርጣት፣የአካል መጠን…)፣ ጠረናቸው፣ ወዘተ. ከአንዲት በያመቱ 11 በመቶ እንደምታድግ ከሚነገርላት የ“መካከለኛ ገቢ ከሚያገኙ” ሀገሮች ተርታ ልትሠለፍ በወራት የሚቆጠር ጊዜ ከቀራት “ፌዴራላዊት” ሀገር የተገኙ ዜጎች አያስመስላቸውም፡፡ ጥቁር አንበሣን ያዬ ሀገር የለኝም ይላል፤ ሀኪሞቹ ብዙዎቹ ሰልችተዋል፤ ሰውን እንደውሻ ይቆጥራሉ፤ በሽተኛው ከሞተ በኋላ እንዲመጣ የሚቀጥሩት – ቀጠሮ አሳጣሪ ዘመድ ከሌለ – ብዙውን ጊዜ ከስድስት ወር በላይ ነው፡፡ አልጋ የለም – ማደንዘዣ የለም – መቀስ የለም – ወስፌ የለም… እያሉ ማጉላላት የብዙዎች ሐኪሞች የደስታና የሃሤት ምንጭ ይመስላል፡፡ ሞት ጥንቡን ስለጣለ ማንም ለማንም የሚያዝን አንጀት የለውም ፡፡ ለነገሩ “ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም” እንዲሉ መንግሥት ከመጤፍ የማይቆጥረውን ሕዝብ የበታች ሠራተኛ ቢያዋርደውና በአግባቡ ባያስተናግደው አይፈረድበትም፡፡ (ወደግል እንዳይኬድ ክፍያው ሕክምናውን ሳይጨምር ለአንድ አዳር ብቻ የሚያስከፍሉት ከባለ አሥራ አምስት ኮከብ የሱትሩም ክፍያ ቢበልጥ እንጂ አይተናነስም – ዘመኑ የዝረፍ እንዝረፍ በመሆኑ የሚቆጣጠራቸው አካልም የለም – ከፈለጉ በእግርህ ገብተህ ሬሣህን ዘመዶችህ በብዙ ሺህ ብር እንዲገዙ ሊጠየቁ ይችላሉ – በቀላል የሕክምና ስህተት፡፡ ገንዘብ ማግበስበስ እንጂ ሙያዊ ሥነ ምግባር ብሎ ነገር በሁሉም ዘርፍ አርቀን ቀብረናል)፡፡ …
ለ. ፖሊስ ጣቢያም ሂድ፡፡ ሕዝቡ አዳርና ውሎው እዚሁ ነው ወይ ትላለህ፡፡ በደረቅ ወንጀልም ይሁን በፍትሐ ብሔር እየተከሰሰና እየተካሰሰ ፖሊስ ጣቢያዎችን የሙጥኝ ብሎ የምታየውን ሕዝብ ማን ሠርቶ እንደሚቀልበው ስታስብ አንዳችም መልስ አታገኝም፡፡ ወንጀልና ወንጀለኝነት የባሕርይ ስጦታዎቻችን የሆኑ ይመስል በተለይ በአሁኑ ወቅት ተካሳሹና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚውለው ወገን በጣም እየተበራከተ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ደግሞ የሀገርን ዕድገት ሳይሆን በችግር ውስጥ ያለን መሆናችንን ነው፡፡
ሐ. ፍርድ ቤቶችን እንጎብኝ፡፡ ልክ እንደሆስፒታሉ ሁሉ እነሱም በሰው ግጥም እንዳሉ ይውላሉ፡፡ ፍትህን የምታገኘው – በአብዛኛው - በገንዘብ መሆኑ እንኳንስ ፍትህና ርትዕ ታጥበው ገደል በገቡበት በዘንድሮው ዘመንና ጥንትም የነበረ መሆኑ አይካድም – እንዳሁኑ ግን ዐይን ያወጣ የፍትህ መዛባት ታይቶ የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ በግ የሰጠው ባለጉዳይ በሬ በሰጠው ባለጉዳይ እስኪረገጥና የፍርድ ሚዛኑ በሕጉ መሠረት ሳይሆን ዳኛውና ዐቃቤ ሕጉ በተቋደሱት ንዋይ እስኪወሰን ድረስ እዚያም ቤት ብዙ መጉላላት አለ፡፡ ይህ በተለይና ይበልጡኑ በባልና ሚስት ፍቺ ጉዳይና በንብረት ክርክር ዙሪያ የሚስተዋለው የፍርድ ቤት ጭንቅንቅ የሀገርን ጤናማነት የሚያሳይ አይደለም፡፡ በነዚህም ሥፍራዎች ሰዎች ሥራ ፈትተው ከአምራችነትና ከሠራተኝነት ይልቅ አፈኛነትንና የነገር ብልት አወጣጥን እየተማሩ ስለሚውሉ ሀገር ችግር ላይ ለመውደቋ አንዱ ምልክት ነው፡፡
መ. ከተማ አውቶቡስንና ሌሎች የትራንስፖርት መኪኖችን እንቃኝ፡፡ እነዚህ ተሸከርካሪዎች ከጧት እስከማታ ሰው አርግዘው እንደወረገብ ነፍሰጡር ተንገፍጥጠው ነው የሚታዩ፡፡ በመሠረቱ ሰው አይዘዋወር አይባልም፡፡ ነገር ግን በሥራ ሰዓት ይህ ሁሉ ሕዝብ በመኪኖች እየታጨቀ ሲዘዋወር እኔን መሰል ሥራ ፈቶች ምክንያቱን ማጠያየቃችን አይቀርም – ወትዋቹ ኅሊናችን እየጠየቀ ያስቸግረናልና፡፡ በአውቶቡስ ውስጥ መቼም ሥራ እንደማይሠራ ይታወቃል፡፡ የሰዎቹን ሁኔታ ስናይ ደግሞ ብዙዎቹ የቢሮ ሠራተኞች አይመስሉም፡፡ ምናልባት የክፍለ ሀገር ተጓጓዦችን ለሥራና ለቤተሰብ ጥየቃ ልንል እንችል ይሆናል፤ በከተሞች ያለው ዝውውር ግን ብዙም ግልጽ አይደለም – በመኪናም ይሁን በእግር ሰውን ስታዩት በገፍ ተጓዥ ሆኗል፡፡ በዚያ ላይ በየአደባባዩና በየቦታው በሥራ ሰዓት የሚታየው የሕዝብ ትርምስ በእውኑ ይህ ሁሉ ሕዝብ እህል ቀምሶ ያድር ይሆን ወይ ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡ አሳሳቢ ነው፡፡ በሌሎች ሀገሮች ስናይ – በፊልምም ቢሆን – ሕዝቡ በሥራ ሰዓት ከተማ ውስጥ አይታይም፡፡ በየሥራው ይከታል፡፡ የኛ ግን ሰኞ የለ፣ እሁድ የለ፣ ጧት የለ፣ ቀትር የለ – ሲርመሰመስ ነው የሚውል፡፡ ይህ የሚያሳየው የሥራ አጡና ምናልባትም የሥራ ፈቱ ቁጥር ሥራ ከሚሠራው ይልቅ የገነነ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ጥቂቶች ሠርተው ብዙዎችነን የማስተዳደር ሁኔታ ደግሞ ክንድን የሚያዝልና ድህነትን የሚያስፋፋ ተስፋንም የሚያሳጣ እንግዳ ክስተት ነው፡፡ ‹አደጋ አለው!› – ትላለች የዘሩ ሚስት – እውነቷን ነው፡፡ በላተኛ በዝቶ ሠራተኛ ከጠፋ አደገኛ ችግር አለ – በሂደት እርስ በርስ መበላላትም ሊመጣ ይችላል፡፡ ይህን የሕዝብ ኃይል በአድልዖ ሳይሆን በአግባቡ አስተምሮና አሰልጥኖ ለሥራና ለአገልግሎት የሚያበቃ የመንግሥት ተቋም በአፋጣኝ ያስፈልገናል፡፡ የአሁኑን መንግሥት መንግሥት ካልነው ተሳስተናል፡፡ ይህ ሸውራራ የወያኔ መንግሥት በሰማሁት መረጃ መሠረት ከ50 ቢሊዮን ዶላር ከሚበልጥ ዕርዳታና ብድር ውስጥ ከ12 ቢሊዮን የሚልቀውን መዝብሮና አስመዝብሮ ወደውጭ የላከ፣ ከቀሪው 38 ቢሊዮን ዶላር ውስጥም በሙስናና ንቅዘት የአንበሣ ድርሻውን አውድሞ በተረፈችዋ መናኛ ፍራንክ ጥቂት የአስፋልት መንገዶችንና የልማት አውታሮችን ለታይታ ያህል ዘረጋ እንጂ እምነት የሚጣልበት አይደለም፡፡ አደጋ አለው ወገኖቼ! መንግሥት ቢኖረን ወገናችን እንደጨው ዘር በመላዋ ዓለም ይበተን ነበርን?
ሠ. ሥራ አለው ከሚባለው ዜጋ የማይናቅ ቁጥር ያለው ወገን ለሥራ ያለው ተነሳሽነትና የሙያ ፍቅር አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን የሚናገሩ አሉ፡፡ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ለይስሙላና ለሰዓት ፊርማ ቢሮ ይገባሉ እንጂ አጥጋቢ ሥራ እንደማይሠሩ፣ የሥራ ፍቅርና ወኔ እንደሌላቸው፣ ሥራ ገበታቸው ላይ ተገኝተዋል እንዲባሉ ብቻ ግን እንዲሁ ወለም ዘለም እያሉ ውለው እንደሚሄዱ ከጥርጣሬ በላይ ገሃድ እየሆነ መምጣቱ ይወራል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሥራን በአግባቡ ያለመሥራት ወይም ሊያሠራ የሚችል አካል መጥፋት ሀገሪቱን ባለቤት አልባ እንደሆነች ያስጠረጥራል፡፡ ብዙዎች እንደሚሉት በየመሥሪያ ቤቱ ከቅርጽ ባለፈ አጥጋቢ የሥራ ሂደት እንደማይከናወን ይታመናል፡፡ የደንበኞች አገልግሎት በሚሰጥባቸው ብዙ የመንግሥት መ/ቤቶች ደግሞ ባለጉዳዮች በደቂቃዎች ለሚያልቅ አነስተኛ ነገር ብዙ ሣምንታትንና ወራትን እንደሚጉላሉ የታወቀ ነው፡፡ በብዙ ቦታዎች በእጅ ተሂዶ ምንም ጉዳይ አይፈጸምም፤ በጅ ተሄዶም ቢሆን ‹የሉም፤ ስብሰባ ላይ ናቸው…› እየተባለ መመላለስ የተለመደ ነው፡፡ አደጋ አለው!
ረ. በየቦታው ትዳር እየፈረሰ፣ ልጆች ወደ ጎዳና እየተበተኑ፣ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸው አእሩግ ወደበረንዳና ወደደጀሰላሞች እያቀኑ በውጤቱም ማኅበራዊ ሕይወት ክፉኛ እየተናጋ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአንዲት ሀገር ውስጥ የትልቅ ችግር መስፋፋትን ያመለክታል፡፡ ቤተሰብ የማኅበረሰብ መሠረት ነው፤ ብዙ ቤተሰብ በሞራልና በሃይማኖት እየዘቀጠ ሲመጣ በሂደት ችገሩ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ጫና ያመጣና መሪዎቹም የዚሁ የሞራልና የሃይማኖት መላሸቅ ውጤቶች ሆነው አሁን እኛና ኢትዮጵያ እየተሰቃየንበት ያለው ነገር ፋሽን እንደሆነ ይቀራል፡፡ በዚህ ረገድም አደጋ አለብን፡፡ ዘር መተካት አቅቶናል፡፡ ከአሁኑ ዘመን ይልቅ የወደፊቱ በእጅጉ አሳሳቢ ነው፡፡ ሀገሪቱን ማን ይረከባት? በጎጠኝት ምች የተመታ ወያያዊ ከፋፋይ ትውልድ ወይንስ ሰፊ ራዕይ ያለው ሁሉንም በእኩልነት የሚመለከት የዘመናዊ አስተሳሰብ ባለቤት የሆነ ትውልድ? ሁለተኞቹና ‹ቆንጆዎቹ› የት አሉ? ተወልደዋል ወይንስ ገና ምጥ ላይ ነን?
ሰ. በኑሮው ጥመትና በኢኮኖሚው ድቀት ምክንያት ዜጎች አእምሯቸውን መቆጣጠር እየተሳናቸው በተለይ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የሚታየው የዕብዶችና የወፈፌዎች ብዛት ከግምት በላይ ሆኗል፡፡ ሆስፒታሎችና አውራ ጎዳናዎች የተጨናነቁት በየሴኮንዱ በሚወፍፉ ዜጎች ነው፤ ልብ ያለው ሰው የተገኘ ግን አይመስለኝም፡፡ በመሆኑም ዕብደትን የሚያባብስ እንጂ የሚቀንስ ነገር ሲከናወን አላይም፡፡ ሀገራዊ ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ዘንድሮ ካበደው ይልቅ በመጪው ዓመት ለማበድ እየተሰናዳ ያለው በእጅጉ ይብሳል፡፡ በየመንገዱ ብቻውን እያወራ የሚሄደው ወገናችን ብዙ ነው በማለት ብቻ አንገልጸውም – ሱፉን ግጥም አድርጎ ለብሶ እጁን ከወዲያ ወዲህ እያወናጨፈና ብቻውን እያወራ አስፋልቱን ሲያቋርጥ ስታየው በዚያ ጎበዝ ኢትዮጵያዊ ዕድል አንጀትህ ይላወሳል – ነገ አንተም እንደሱ እንደማትሆን ደግሞ እርግጠኛ መሆን አትችልም – እስካሁን ካልሆንክ፡፡ አደጋ አለው!
ሸ. በሰውነት ውስጥ ነጭ የደም ሕዋስ ሲበዛ አንዳች በሽታ እንዳለ ይገመታል – በአንዲት ሀገር ውስጥ የወታደሮች ባልተለመደ ሁኔታ መርመስመስና መራወጥ አንዳች የፀጥታ ችግር መከሰቱን እንደሚጠቁም ሁሉ ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አንዲት ሀገር ውስጥ የጫት ቃሚዎች፣ የጠጪዎችና የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ሄዶ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከደረሰ ያች ሀገር ወዮላት! እንደሚመስለኝ በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ውስጥ የተደሰተውም ይጠጣል – ያዘነውም ይጠጣል፡፡ የከፋውም ይቅማል – የተደሰተውም ይቅማል… ‹የዘገነም አዘነ፣ ያልዘገነም አዘነ›፡፡ እርግጥ ነው – መጽሐፉ ‹ድሃ ጭንቀቱን ይረሳ ዘንድ የወይን ጠጅ ይጠጣ› ይላል፡፡ ከዚህ አንጻር የድሆች ተረከዛቸውን ወትፈው ያገኙትን መጠጣታቸው በተወሰነ መልኩ ይገባኛል – እኔም አለሁበትና፡፡ የሀብታሞች መጠንበዝ ግን ግራ ነው እሚያጋባኝ – የሚያስጨንቁንን ለመርሳት ይሆን? ዋናው ግን በአንዲት ሀገር የጠጭዎችና የጫት ቃሚዎች እንዲሁም የሀሺሽ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየገነነ ከመጣ በዚያች ሀገር አንዳች የተስፋ መቁረጥ መንፈስ እየተበራከተ ነውና አሁንም አደጋ አለው፡፡ እርግጥ ነው – አምባገነን ገዢዎች ይህንን መሰሉን ሕዝባዊ ተስፋ መቁረጥና አልባሌ ተግባር ውስጥ ገብቶ መደበቅ ይወዱታል – እንደወያኔ ዓይነቶቹ ስግብግቦች ሳይሆኑ እንደኮሚኒስት ራሽያ ዓይነቶቹ ይህንን የጥንበዛ ፕሮግራም በገንዘብ ይደጉማሉ፤ በተዛዋሪም ያረታታሉ – ሰው በሥካር ውስጥ ተዘፍቆ ፖለቲካቸውን እንዳያስብ፡፡ ‹ያውጡብሽ እምቢ፣ ያግቡብሽ እምቢ› ዓይነቱ ወያኔ ግን በገንዘብ ፍቅር በማበዱ ምክንያት ሁሉንም አክርሮ ሰውን መደበቂያ እንኳ በማሳጣት በገላጣ ሥፍራ ላይ በየአቅጣጫው ሕዝበ አዳምን በጅራፍ እየሸነቆጠው ነው፡፡ ይሄ ቫት እሚሉት ነገር በሁሉም ዘርፍ ገብቶ የመጠጡም የምግቡም ዋጋ በመሰቀሉ አብዛኛው ሕዝብ ታዛቢ እንጂ ተሣታፊ ሊሆን አልቻለም፡፡
ቀ. በአንድ ሀገር ውስጥ ጧት ቤተ ክርስቲያን ወይም መስጂድ ያገኘኸው ሰው ማታ ጠንቋይ ቤት ካየኸው በዚያ ሀገር ውስጥ መስተካከል የሚገባው የተበላሸ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ እንደማይዋጣ ሁሉ ለሁለት ጌቶች ለመገዛት መሞከር ችግርን በራስ ላይ መጋበዝ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ችግር በሀገራችን በስፋት ስለሚስተዋል የዕድገታችን ምልክት ሳይሆን የመንፈሳዊ ድቀታችን ዓይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ ታላላቅ የኪነ ጥበብ፣ የንግድ፣ የፖለቲካና የአትሌቲክስ ዘርፎችን በዋናነት ጨምሮ ብዙ ሰው በዚህ ብልሹ ሕይወት ውስጥ መመላለሱን መረዳት አይከብድም – በጥንቆላ ባገኘው ገንዘብ ቤተ ክርስቲያን የሠራ ሰው አውቃለሁ – አንድ ብቻም አይደለም – በዚህ መልክ ፈጣሪን ጡጦ እንዳልጣለ ሕጻን እየቆጠሩ ሊያታልሉት የሚሞክሩ እጅግ ብዙ ሰዎች አሉ ፤ ካህናትንና ቃለ እግዚአብሔርን ዐዋቂዎችን ጨምሮ – እሱው በምሕረቱ ያስባቸው፡፡ ‹የሐሙሱ ፈረስ› በጣም ከፍተኛ የሆነ አፍራሽ ሚና እየተጫወተብን አለ – አንድ ታምራት የሚሉት ዓይነት አራተኛ ክፍልን በቅጡ ያልጨረሰ የሚባል አጭበርባሪ ጠንቋይና አንዲት ‹ማርያም ነኝ› የምትል ማይም ሴት እንዲሁም ባህታዊ ነኝ ባይ አፈ ቅቤ ‹ሊቀ ትጉሃን› በቀላሉ የሚያታልለን/ የሚያነሆልለንና ወደተፈለገው አዘቅት የሚያሰምጠን ሕዝብ ከሆንን ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱም ጭምር አደጋ አለው! በዬጉራንጉሩ እየሄድን ብናይ ብዙዎቻችን ከዕውቀት ማዕድ የመራቃችን ጣጣ ያመጣብን ጠንቅ ሥር ሰድዶ እግር ከወርች የጠፈነገን መሆናችነን እንገነዘባለን፡፡ እግዚአብሔር በቶሎ ካልደረሰልን በቁማችን ጠፍተናል ወገኖቼ፡፡
ተ. በአንዲት ሀገር ውስጥ ጉቦ ወይም ሙስና እግር አውጥቶ የሚሄድ ከሆነ ወዮ ለዚያች ሀገር ሕዝብ! ሕግም ሥርዓትም ፍትህም… በግለሰቦች ፈቃድ የሚወሰኑ እንጂ አድልኦ የሌለበት ሕግን መሠረት አድርገው በአስተዋይነትና በጥበብ የሚከናወኑ አይሆኑም፡፡ በአንዲት ሀገር ውስጥ ወሳኙ የበላይ አለቃ ገንዘብ ከሆነ የሕዝቡና የመንግሥቱ ግንኙነት ልክ እንደተራ የአከራይ ተከራይ ግንኙነት ነው ማለት ነው፡፡ አንድ አከራይ ያከራየውን ሰው ሲፈልግ ‹ምነው ወንድም – ቀስ ብለህ አስነጠስ እንጂ! ለጣራና ኮርኒሱም አስብለት› ወይም ‹የኔ እህት በቀን አንድ ባልዲ ተዋዋልን እንጂ በጆግ ማን ጨምሪ አለሽ?› እንደሚባሉ ሁሉ መንግሥትና ግለሰብ ከተቀላቀሉ ልክ በመለስና በመንግሥቱ ኃ/ ማርያም እንዳየነው የሚሊዮኖች ዕጣ ፋንታ በአንድ ጫታም ወይም በአንድ ሠካራም ወይም በአንድ ሀበሾኣምና ሀሺሻም እየተወሰነ ሕዝብ ዐይኑ እያየ እንጦርጦስ ይወርዳል ማለት ነው፡፡ የ80 እና 90 ሚሊዮን ሕዝብ የመኖርና ያለመኖር ዕጣ በአንድ ግለሰብ ወይም እልፍ ሲልም በአንድ የወሮበሎች ጭፍራ የሚወሰን ከሆነ ወዮ ለዚያ ሀገር ሕዝብ! ከዚህ አንጻር በሀገራችን ትልቅ አደጋ አለ፡፡ ይህ አደጋ በቅርብ ካልተገፈፈ የኛንስ ተውት ከሞላ ጎደል ጨርሰነዋል – ተተኪ ግን አይኖረንም፡፡
ቸ. በአንድ ሀገር ውስጥ የኢምግሬሽን ቢሮ በጣም ሥራ የሚበዛበት ከሆነና የተሰዳጁ ሕዝብ ቁጥር ከበዛ በዚያ ሀገር ውስጥ ከፍተኛ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ የኛን ሀገር ሁኔታ ከዚህ ነጥብ አኳያ ብመለከተው ልዩ ታሪክ እንታዘባለን፡፡ ጥቁር አንበሣ አካባቢ የሚገኘውን የኢሚግሬሽን ቢሮ ተመልከቱ፤ እንደዝናር ጥይት በዕጥፍ ድርብ ዙሪያውን እየተጠማዘዘ የሚሰለፈው ሕዝብ ለሽርሸር ወይም ለቱሪስትነት ሳይሆን በምትቀና ሚስት ከፎቅ ለመወርወር ወድዳና ፈቅዳ የተዘጋጀች ወጣት ሴትና በዘበኝነትም ይሁን በአትክልተኝነት ሠርቼ ትንሽ ፍራንክ ልቋጥርና ቤተሰቤን ልደግፍ ብሎ የቆረጠ ጉብል ናቸው፡፡ ዜጎች አለኝታ ሲያጡ የሚሰማቸው መሪር ስሜት ለእንደዚህ ያለ የባርነት ሕይወት ዐይናቸውን እንዳያሹ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህ ሂደት ሀገሬ ብሎ ለባንዴራው የሚዋደቅ ወጣት አይኖርም – ለጊዜው ሀገርም ሁላችንን የሚያስማማ ባንዴራም ባይኖረንም፡፡ በዚያ መንገድ ሳልፍ በእጅጉ አፍራለሁ – የኢቲቪ የሀገር ዕድገት ዲስኩር ትዝ እያለኝም በውስጤ ፈገግ ማለቴ አይቀርም፡፡ ከዋሹ አይቀር ታዲያ እንዲህ ነው፡፡ መላው ዜጋ ከሀገር ለመውጣት ሌት ከቀን ተሰልፎ በሚታይበት ሁኔታ ሀገር አድጋለች እያሉ ማንቋረሩ ማንን ለማታለል እንደሆነ ፈጽሞ አይገባኝም፡፡ የሚያደርጉትን አያውቁምና ፈጣሪ ይቅር ይበላቸው፡፡
ኀ. ከፍ ሲል በጨረፍታ ለመግለፅ እንደተሞከረው የሴተኛ አዳሪነት አለቅጥ መስፋፋት፣ የዘመድ አሠራር(ሥራ ለመቀጠር፣ ለዕድገትና ለሹመት…)፣ የሀገሪቱ ዋና ዋና የሥልጣንና የጥቅም ቦታዎች በአንድ ብሔር ሥር ተጠቃሎ መግባትና ሌሎችን ባይተዋር ማድረግ፣ ኢትዮጵያዊነት የአባት ገዳይ ይመስል ጥምድ አድርጎ መያዝና ለዚህች ታሪካዊት ሀገር ትንሣኤ የሚተጉ ዜጎችን በገቡበት እየገቡ ማሳደድ… የዕድገት ምልክቶች ሳይሆኑ የክስረት መገለጫዎች ናቸውና በእንፉቅቅ እየመጣ ያለው የዕልቂት ዘመን ድንገት ሳይደርስብን – በተለዋጭ ቃላት ልድገመው – ቢዘገይም እንኳን መምጣቱ በጭራሽ የማይቀረው የመቅሰፍት ዘመን ሳይመጣብን እገሌ ከእገሌ ሳንል ሁላችን ወደየኅሊናችን እንመለስና እያንዣበበብን ያለውን ከፍተኛ አደጋ እንግፈፍ፤ ኋላ ጊዜ ላይኖረን ይችላልና፡፡
ነ. ከዚህ በላይ በድርበቡ የተጠቀሱ ነገሮች በሙሉ ኢትዮጵያና ልጆቿ በቋንቋ ሊገለጽ የማይችል የችግር አረንቋ ውስጥ እንደገቡ የሚያመለክቱ ናቸው፤ ስለሆነም መፍትሔ ያሻቸዋል፡፡ መፍትሔው ደግሞ አንድም ከሰው አንድም ከእግዜር ነው፡፡ የሰው እስካሁን አልተሳካም – በተለያዩ ሰውኛ ምክንያች የተነሣ፡፡ የእግዜሩ ግን ቀደም ሲል ጀምሯል – አሁንም ሳይቋረጥ በራሱ ጊዜና በራሱ ፍጥነት ቀጥሏል፤ ማንም ደግሞ አያደናቅፈውም፡፡ ለመነሻነት እነኚህን ሂደቶች ልብ በሉ፡፡ ከዚያም ቀጥሎ ምን ይሆን ይሆን? ብላችሁ ስለወደፊቱ አስቡ፡፡
ኘ. በ83ዓ.ም ሕወሓት ኢትዮጵያን የማጥፋት ትልሙን በአሜሪካን በጎ ፈቃድና ቡራኬ በሄርማን ኮኸን የፖለቲካዊ ፕትርክና ቡራኬ መንግሥት ሆኖ በይፋ ጀመረ፡፡ ከትክክለኛው የጊዜ አቆጣጠር አንጻር ከአራት ዓመታት ገደማ በኋላ በ88 ትልቅ የመሰነጣጠቅ ጥፊ ደረሰበት – የጊዜው ጠ/ሚኒስትር ታምራት ላይኔ በ”ስኳር ቅሌት” ወህኒ ወረደ፡፡ አንድ በሉ፡፡ ሦስት ዓመታትን ቆይቶ በ90ዓ.ም ያልታሰበ ዱብ ዕዳ ወርዶ ከፍተኛ ዕልቂት ያስከተለ የሻዕቢያና ወያኔ የማይጠገን ስብራት ደረሰ፡፡ ሁለት በሉ፡፡ ፈጣሪ ሌሎች ሦስት ዓመታትን ታግሦ ወያኔ ራሱ በውስጥ ደዌ እንዲመታ አደረገና የሕወሓት መንደር ምንቅርቅሩ ወጣ – በሻዕቢያም በኩል እንደዚሁ፡፡ ሦስት በሉ፡፡ አራት ዓመታትን ቆይቶ በ97ዓ.ም ወያኔን እርቃኑን ያወጣ ሀገራዊ ክስተት ተፈጠረ፡፡ አራት በሉ፡፡ ሌሎች አራት ዓመታትን ቆይቶ በ2001 እና ከዚያም በኋላ እሳቱ እማይጠፋ ትሉ እማያንቀላፋ የኑሮ ውድነት ባልታወቀ ኃይል ታወጀና በየቀኑ ሽቅብ በሚወረወር የዋጋ ንረት ሕዝብ ማልቀስና ዕንባውን ወደላይ ወደአርያም መፈንጠቅ ተያያዘ፡፡ ይህም ብሶት ከተጨማሪ ወያኔዊ የዕብሪትና የትምክህት ሥራዎች ጋር ተባብሮና ተደማምሮ ሌሎች የወያኔን ሥርዓት ማብቂያ አመላካች ምልክቶችን በግልጽም በሥውርም ያሳይ ያዘ፡፡ አምስት በሉ፡፡ ከሦስት ዓመታት በኋላ በ2004 መገባደጃ ላይ በዋልድባ ገዳምና በሕዝብ ዕንባ መዘዝ ታላላቁ የብኤል ዘቡል ወኪሎች አቶ መለስ ዜናዊና ሃይማኖትን በዓሣማ ጋጣ ላይ አጋድመው የረመረሙት “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ” ጳውሎስ የአጋንንት መንጋቸውን ደጅ ላይ ለብርድና ለንፋስ እንዳጋለጡ በፈጣሪ ልዩ ‹ሰርጂካል ኦፐሬሽን› ተመትተው እስወዲያኛው አሸለቡ – ሰማይ ምድርን ‹ዕፁብ ድንቅ› ያሰኘ ሰማያዊ በረከት፡፡ ስድስት በሉ፡፡ ፈጣሪ እንደዱሮው ሦስትና አራት ዓመታትን መጠበቅ ሳያስፈልገው በዓመቱና አሁን ደግሞ ምን እየሠራ እንደሆነ በዐይናችን በብረቱ እያየን ነው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን እኛ ሀገር ቤት ያለነው ምሥኪን ዜጎችም ሆንን የተቃውሞው ጎራ በየአምበሉና በየጎራው እየተቧደነ የነገር ጦር ከመስበቅ፣ በደብዳቤና በድርጅታዊ መግለጫ ‹የጦፈ ጦርነት› ከማካሄድ በዘለለ አንዳች አስተዋፅዖ አድርገን ከሆነ ገና ወደፊት የሚጣራ ይሆናል፤ የታሪክ አጣሪ ኮሚሽን ብዙ ሥራ ሊሠራ ከፊት ለፊታችን ቆሞኣለ፡፡
አ.. የተኛም ይተኛ፤ ያንቀላፋም ያንቀላፋ፤ የደከመም ይድከም፤ የተሸነፈም ይሸነፍ፤ አብሮና ተባብሮ የሚዘርፍና የሚያዘርፍ – የሚገድልና የሚያስገድልም – ይዝረፍም ይግደልም፡፡ እኛ ደግሞ እንጮሃለን፤ የሚያነብብ ያንብ፤ የሚሰማ ይስማ፤ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ እንደጨለመ አይቀርም፤ ያኔ የጨለማው ውስጥ ብካያችን በገሃድ ይገለጥና በምን ዓይነት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ምን ዓይነት የመከራ ሕይወት እያሳለፍን እንደነበር ቀጣዩ ትውልዳችን ይማራል፤ እንዲሆን የታዘዘን ከመሆን የሚያሰናክል የለም፤ ሁሉም በጊዜው ይሆናል፡፡ ጠቢቡ ቀድሞ ተናግሮታል – ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም፡፡ የብርሃንና የጨለማ መፈራረቅም የነበረ እንጂ ዛሬ የተጀመረ አይደለም፡፡ አገኘሁ ብለህ አትኩራ፤ አጣሁ ብለህም ከመጠን ባለፈ አትፍራ፡፡ ይልቁንስ ሰው ለመሆን ጣር – ሰው ሆኖ መገኘት ትልቅ የወቅቱ ፈተና ነውና፤… ከገዳይ ይልቅ ሟች የበለጠ የፅድቅ ቦታ አለው፤ ጊዜው ቀርቧል፡፡ ለዚያ ጊዜ ወዮ እንበል!!
ከ. እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አብዝቶ ይባርክ፤ ለሦርያና ለኢራቅ ከተመዘዘ ሠይፍና ጦርም ይሠውረን፡፡ የጥጋበኞችን ጥጋብ ወደስክነት፣ የትዕቢተኞችን ዕብሪት ወደብስለት፣ የጠይዎችን ጥላቻ ወደፍቅር፣ የሆዳሞችን ስግብግብነት ወደእርካታ ለውጦ ያለብዙ ወጪ በሚገነባ አዲስ ስብዕና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ባለቤቶች ያድርገን – ይቻለዋልና፡፡ (የፊደል ተራ ቅደም ተከተሉን ልክ እሆን ብላችሁ ነው?)
ኸ. በቀናነት ለሚያስተምረኝና ጉድለቴን ለሚሞላልኝ ብቻ አድራሻየ ከምሥጋና ጋር ይሄውና፡- ma74085@gmail.com
ዕውን እንደሚባለው የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ አልሆነም?
በዓይን የታየንና በጆሮ የተሰማን እውነታ በመጨበጥ፤ በእውነት ፈራጅ ልብና መስካሪ አንደበት ይኖራል፤
የተለያዩ ሰዎች፣ ከሁሉም በላይ “ሕዝብ የማወቅ መብት አለው” ብለው ዕውነተኛ መረጃን ለሕዝብ ዓይንና ጆሮ የማድረስ ኃላፊነት አለብን ብለው የተሰለፉ ጋዜጠኞች፣ “ወያኔ አጥፊ ቡድን ነው! መወገድ አለበት” ብለው ሲጮኹ የሚሰሙ ሰዎች፣ “ወያኔንና የትግራይን ሕዝብ አንለይ? የትግራይ ሕዝብ በአገዛዙ ተጠቃሚ አይደለም!” እያሉ ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ ይሰማል፡፡ ሌሎች ወገኖች ደግሞ `የለም በወያኔ አገዘዝ የትግራይ ሕዝብ በነቂስ ተጠቃሚ ነው` ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ እነዚህ የክርክር ጭብጦች ናቸው፡፡ ሰሚ ወገን የትኛው አባባል ዕውነት እንደሆነ የራሱን የኅሊና ውሣኔ ሊወስን የሚችለው በዓይን ታይተው በእጅ የሚዳሰሱ መረጃዎች ሲቀርቡለት ነው፡፡ በዚህ ረገድ ግራና ቀኝ የቆሙት ሀሳቦች፣ ሦስተኛ ወገን ሊረዳውና የራሱን ውሣኔ ሊሰጥ እንዲችል፣ በሁለቱ ጭብጦች በኩል የሚቀርቡ የመከራከሪያ ሀሳቦች ደጋፊ መረጃዎችን መመዘን ለሚደረስበት መደምደሚያ ጽኑ መሠረት እንደሚሆን ይታመናል፡፡ ስለሆነም መከራከሪያ ሀሳቦቹን ደረጃ በደረጃ እንፈትሽ፡፡
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ የቁንጅና ፈቃድ ቢሮ ሃላፊ ፋሲል አ.
ፋሲል አ.
ሰሞኑን ቤቴልሄም አበራ(ቤቲ) የተባለች ወጣት ኢትዮጵያዊት በቢግ ብራዘር አፍሪካ ትእይንት (show) ላይ ከሴራሊዮኑ ቦልት ጋር ፈጸመችው ስለተባለው ወሲብ በተለየዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾች እና መገናኛ ብዙሃን የሚሰጠው አስተያየት እንደቀጠለ ነው::በዚህ የቢግ ብራዘር ትእይንት ላይ ከዚህ በፊት በተደረጉ ውድድሮች ላይ የተለያዩ ጥንዶች እንደዚህ አይነት የወሲብ ድርጊት መፈጸማቸው የተዘገበ ሲሆን ይህ የቢግ ብራዘር ትእይንት በባህሪው ለእንደዚህ አይነት ድርጊቶች የተጋለጠ ለመሆኑ ከዚህ ቀደምም ሆነ አሁን የተደረጉት ድርጊቶች በቂ ማሳያ ናቸው :: ይህ እንዳለን ሆኖ ቤቲ ፈጸመችው ለተባለው ድርጊት ብዙ ኢትዮጵያኖች በተለያዩ ድረ ገጾች ”አዋረደችን” አሰደበችን” ምነው ባትሄድ ቢቀርባት ኖሮ “እና የመሳሰሉትን የተቃውሞ አስተያየቶች እየሰጡ ሲሆን ከነዚህም አስተያየቶች አንዱ ታዋቂው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በሬድዮ የሰጠውን አስተያየትም ተከታትዬው ነበር::
ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ እንደጋዜጠኛ ሳይሆን እንደ ተጋባዥ እንግዳ ከሌላ ጋዜጠኛ የሚቀርብለትን ጥያቄዎች እየመለሰ በቀረበው በዚህ ፕሮግራም ላይ አለምነህ አስተያየቱን ሲጀምር በዚህ ቢግ ብራዘር አፍሪካ ትእይንት ላይ ከሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች የሚመጡት ተወዳዳሪዎች በሃገራቸው ታዋቂነት ያላቸው የቲቪ ሾው አዘጋጆች፣ አርቲስቶች ወይንም በሞያቸው ዝናን ያተረፉ ታዋቂ ሰዎች (celebrities) ሲሆኑ ከእኛ ግን የሚወስዱት እኔ የማላውቃቸው ሰዎች ናቸው ( ለማለት የፈለገው በሞያቸው በህዝብ ዘንድ ታዋቂ ያልሆኑትን ለማለት ነው) ሲል የቢግ ብራዘርን አዘጋጆችን ይወቅሳል::
እንግዲህ እኔን እንደገባኝ ከቤቲ ይልቅ የሃገራችን ታዋቂ አርቲስቶች (celebrities ) ቢሄዱ ኖሮ ይሻል ነበር ምናልባትም አንዋረድም ነበር ብንዋረድም ውርደቱ የጋራ ይሆን ነበር ሲል ይገልጻል::ይገርማል በመጀመሪያ ደረጃ የቢግ ብራዘር አዘጋጆች ከአንድ ሃገር ታዋቂ አርቲስትም ይምረጡ መደበኛ ኖርማል ሰው ያ የተመረጠው ግለሰብ ወደ ውድድሩ ከመግባቱ በፊት የውድድሩን ህግጋቶች ከማጥናቱም በተጨማሪ በግሉ ደግሞ እንዴት ማሸነፍ እንዳለበት የአቅሙን ዝግጅት አድርጎ የሚገባ ሲሆን በተጨማሪም ወደ ውድድሩ ከገባም በኋላ በውድድሩ ውስጥ በሚፈጠሩ የተለያዩ አጋጣሚዎች እራሱን እያስተካከለና እያዋሃደ የሚሄድበት ሲሆን የሸመደደውን ወይም ያጠናውን የሚያንበለብልበት መድረክ ሳይሆን ከሁኔታዎች ጋር የራሱን የግል ስብእና፣ ስሜትና አስተሳሰብ የሚያንጸባርቅበት ትእይንት በመሆኑ ተወዳዳሪው አርቲስት ይሁን ወታደር፣ ፖለቲከኛ ይሁን መምህር፣ ድንገት በሚፈጠሩ አጋጣሚዎች የሚመልሰው ( የሚወስነው) ግብረ መልስ (reaction ) እንደየሰው የውስጥ ስብእና፣ ልምድ፣ አስተሳሰብና ውስጣዊ ጥንካሬ የሚለያይ እንጂ አርቲስት ስለሆነ ትክክለኛ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ሌላው ሰው ግን ሊከብደው ይችላል ብሎ ሙሉ በሙሉ መደምደም ይከብዳል::
ሌላው አለምነህ ከዚሁ ጋር አያይዞ የገለጸው ነገር የምናከብራቸው አርቲስቶች ወደ ውድድሩ ቢሄዱ ያስደስቱናል! ያኮሩናል! የሚፈጽሙትም ነውር ነገር ካለ አብረን ችግሩን እንቀበላለን ሲል ይገልጻል:: ወይ አለምነህ ታዲያ ቤቲስ ይህንን ድርጊት ባትፈጽምና ብታሸንፍ ኖሮ ታስደስተን! ታኮራን! የለም እንዴ? እንዲሁም ያው ልክ አንተ እንዳልከው ነውር ነገር ካለም ያው ችግሩ የጋራ ይሆናል ማለት ነው ስለዚህ አብረን መቀበል የለብንም እንዴ ? ነው ወይስ ቢያኮሩንም ቢያሳፍሩንም አርቲስቶች ብቻ ናቸው መሄድ ያለባቸው እያልከን ነው?
ቀደም ሲል አርቲስት ወደ ውድድሩ ተልኮ ቢሆን ኖሮና ነውርም ካለ አብረን እንቀበለዋለን ሲል የነበረው አለምነህ ቤቲ መምህርት ናት በመሆኑም ትልቁ የሚሰቀጥጠው ነገር ልጆቻችንን ወዴት ነው የምንልከው? ሲል የተምታታ ስጋቱን ይገልጻል:: እንዴ ደግሞ ነውር የአርቲስትና የመምህር የሚባል ልዩነት አለው እንዴ ጋዜጠኛ አለምነህ? ልጆቻችን ትምህርት እና ስነ ምግባር የሚማሩት ት/ቤት ብቻ ነው እንዴ? በዲቪዲው በሲዲው የአርቲስቶቻችን ስራ በየቤታችን እየገባ አይደለም እንዴ? አርቲስትስ አንድን ጤናማ ማህበረሰብ ለመቅረጽ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አልሰማህ ይሆን?
የጋዜጠኛውና የአለምነህ ውይይት ሲቀጥል ጠያቂው ጋዜጠኛው ጥያቄ መሰል አስተያየቱን በማስከተል ቤቲ ይህን ውድድር ካሸነፈች ወደ ሆሊውድ መሄድና የራሷን የጉዞና አስጎብኝ ድርጅት መክፈት እንደምትፈልግ ገልጻለች በማለት ካብራራ በኋላ ቤቲ ወደ ሆሊውድ ከሄደችማ ሌላ ነገር ነው ማለት ነው ሲል ቤቲ ወደ ሆሊውድ ሄዳ ሌላ ተመሳሳይ የሆነ ነገር መፈጸሟ አይቀርም የሚል ቃና ያለው አስተያየት ሲሰጥ ሁሉ ይደመጣል:: በእውነት በጣም የሚያሳዝን አስተያየት ነው:: በአንድ ውድድር ላይ በመዘናጋት መጠኑን የዘለለ ድርጊት የፈጸመች መምህርት እህታችን ( ለኔ ወሲብ መፈጸሟ ሙሉ በሙሉ እንደ ወንጀኛ የሚያስቆጥራት ሳይሆን በመዘናጋት ትንሽ መጠኑን ያለፈና ባታደርገው ሁላችንም የምንመርጠው ድርጊት ነው) ምንም ማረጋጫ ሳይኖር ወደፊት በማንኛውም ጊዜና የትም ቦታ ይህንኑ የምታደርግ ተደርጎ በሚድያ ከአንድ ጋዜጠኛ አስተያየት መስማት እጅግ ያማል::
አለምነህ አስተያየቱን በመቀጠል ቤቲ ይህንን ድርጊት የፈጸመችበት የተለያዩ በጣም ብዙ አሳሳችና አዘናጊ ምክንያቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ ብዙም ሊፈረድባት እንደማይገባ ይገልጽና መልሶ ደግሞ ቤቲ ለፍቅር ብላ ቢሆን እንደዚህ ያደረገችው እኔ አንገቴን ለቢላ እሰጥላት ነበር ግን አይደለም ለገንዘብ ብላ ነው ይህን ሁሉ ያደረገችው ብሎ በአንድ ጊዜ ሁለት የሚጋጩና ባልተረጋገጠ መላምት ላይ የተመሰረቱ አስተያየቶችን ያስደምጠናል::
አለምነህ በማጠቃለያው ቤቲ ውድድሩን አቋርጣ እንድትመለስም ይመክራል:: ይገርማል የውድድሩን ህግና ስርአት ያላፋለሰች እና ምናልባትም ጠንክራ በውድድሩ ውስጥ ከቆየች የማሸነፍ ተስፋ ሊኖራት የሚችልን ተወዳዳሪ እኔ ማየት የማልፈልገውን ነገር በማድረጓ ከውድድሩ መውጣት አለባት ብሎ መፍረድ ምን አይነት ፍርድ እንደሆነ ለአድማጭ እተወዋለሁ:: ሲሆን ሲሆን ስህተቶቿን እያስተካከለች ለማሸነፍ እንድትጣጣር መገፋፋት ይገባል እንጂ ወደ ኋላ እንድታፈገፍግና እንድትሸማቀቅ ማድረግ ተገቢ አይመስለኝም:: የሄደችውስ ከተሳካ አሸንፋ ለመመለስ እንጂ በትንሽ መዘናጋት በተፈጠረ ጉዳይ ተስፋ ቆርጣ ለመመለስ ነው እንዴ? አለምነህ ንግግሩን ሲያሳርግ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ቆንጆዎች ናቸው ሲባል እንደ ቤቲ ማለት አይደለም ሲል የቤቲን ቁንጅና ከኢትዮጵያውያን ቁንጅና ለመለያየትም ጥረት ሲያደርግ ይታያል:: ያንተ ያለህ ጆሮ መቼም አይሰማው የለም:: አይ አለምነህ የኢትዮጵያውያን ቁንጅና እንደ ቤቲ ካልሆነ ታድያ እንደማን ነው? እንዳንተ ይሆን? ለመሆኑ አንተ ያልጣመህን ወይንም ያልተመቸህን ነገር ያደረገ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ቁንጅናው ይገፈፋል ማለት ነው? ለካስ ከጋዜጠኝነትህም በተጨማሪ ቁንጅና ሰጭና ነሺም ሆነሃል? ቤቲማ ልቅም ያለች ኢትዮጵያዊት ቆንጆ ናት በተለያዩ ምክንያቶች በመዘናጋት በአንድ ውድድር ላይ ትንሽ መጠኑን ያለፈ ድርጊት የፈጸመ ግለሰብ ቁንጅናው ይነጠቃል የሚል ህግ ካለ እራሱ አልምነህ ያስረዳን::
ጋዜጠኛ አለምነህ ለመሆኑ ኢትዮጵያ የተዋረደችው በቤቲ የአጋጣሚ መጠኑ ያለፈ ድርጊት ነው እንዴ? ፍጹም በሆነ የአስተዳደር ብልሹነት፣ ፍትሃዊ ባልሆነ የሃብት ክፍፍልና አምባገነናዊ አገዛዝ በሃገራቸው የመኖር ተስፋ አጥተው በሱዳን እና በ ሊብያ በረሃ የማንም አረብና ጥቁር መጫወቻ ሰለሆኑት እህቶቻችን ምነው ዝም አልክ? አለም ደቻሳ በኢትዮ. ኢምባሲ በር ላይ በአረቦች ስትደበደብና ስትጎተት ለዚህ ሁሉ የዳረገንን የአስተዳደር ብልሹነት መሆኑን እያወቅክ ምነው ልሳንህን ያዘው? ዛሬ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተሞች የውጭ ዜጋ የሆነ ጥቁር ይሁን ነጭ እንዲሁም ካገሬውም ሰው ቢሆን ትንሽ ገንዘብ ለማግኘት ለስጦታ እንደተዘጋጀ የገበያ እቃ ራሳቸውን አሳምረውና ተሽቀርቅረው ሰለሚቀርቡት በሺዎች ለሚቆጠሩ የእህቶቻችን ጉዳይስ ዜናው አልደረሰህ ይሆን? እዛው አፍንጫህ ስር በአለቆችህ ቀጭን ትእዛዝ ጋዜጣ ላይ ሃሳባቸውን ስለገለጹ ብቻ በአሸባሪነት ተከሰው ወህኒ ስለተወረወሩት ስለ እነ እስክንድር ነጋ ፣ ርእዮት እና ሰለብዙ የግፍ እስረኞች ጉዳይስ ትንሸ አቆጠቁጥህም? ከእነዚህና ከመሳሠሉት በላይስ ሃገራዊ ውርደት አለ?
ለቤቲ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ ዘመዶችና ለመለው ህብረተሰባችን በሙሉ
ቤቲ አንዲት ኢትዮጵያዊ እህታችን በሃገራችን ያለውን ባህላዊ፣ ማህበረሰባዊ እና ስነልቦናዊ ጫናዎችን ተቋቁማ በዚህ መድረክ ላይ በመሳተፏ አድናቆት ይገባታል:: በመዘናጋት ትንሽ መጠኑ ከፍ ያለና ባታደርገው ሁላችንም የምንመርጠው ነገር ግን ሁሌም እኛ ባሰብነው ብቻ ሳይሆን ባላሰብነው መንገድ ነገሮች ተከስተው ቤቲ ይህንን ነገር ብታደርግም ምንም ማለት ያልሆነና ቀጣይ ቆይታዋ የተሳካ ሆኖላት ጥሩ ውጤት እንድታመጣ ሁላችንም ከሆኗ ልንሆንላት ይገባል:: ወደድንም ጠላንም ቤቲ የኛው እህት፣ የኛው ልጃችን ናት:: እንደስህተትም ከተቆጠረባት የሚሰራ ሰው ይሳሳታልና ስህተቷን አስተካክላ ነገ የተሻለ ስብእና እንዲኖራት ሁላችንም ከሆኗ እንሁን:: ስሜቷን ከሚጎዱ መንፈሷን ከሚረብሹ ድርጊቶች ተቆጥበን በሰላም ተቀብለን የቀድሞ ህይወቷን ምንም ባለመሳቀቅ እንድትቀጥል እንርዳት እላለሁ ::
አመሰግናለሁ::
የምልህ አለኝ የሚለኝ ካለ ይሄው መገኛዬ…. fasil_ayal@yahoo.com