Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all 13695 articles
Browse latest View live

ይድረስ ለአባይ ባለበት…

$
0
0

ጉዳዩ፤ በጣም አበዛኸው…!

The Nile River has become a point of contention between Egypt and Ethiopia.

The Nile River has become a point of contention between Egypt and Ethiopia.

ይቺ ለአባይ የተፃፈች ደብዳቤ ናት፡፡ አፃፃፏ “ስዲ ወ ግጥሚ” አይነት ናት፡፡ ትንፋሽ ያለው ሰው እንደ ግጥም ቢወርዳት ግጥም ግጥም ትመስላለች፡፡ ትንፋሽ የሌለው ሰው ደግሞ እንዲሁ ቢዘልቃት ስድ ንባብ ትሆናለች፡፡ እስቲ እንደዚህ አዳዲስ ፈጣራዎችን እናስተዋውቅ… ብዬ አካብጄ በአዲስ መስመር እጀምራታለሁ ትድላችሁ…!!

ውድ አባይ፤ ከእናታችን ማህጸን ተገኝተህ ገና በቅጡ ሳትጠና እና ሳትጠናና በልጅነት አፍላ ፍቅር ድንገት አየተሃት ከወደድካት ግብጽ ጋር ከተጋባህባት ዕለት አንስቶ ለጤናህ እንደምን አለህ… ከቶ!

እኛስ እንዳለን አለነው፡፡ አንተን ያኽል ወንድም፤ አንተን ያኽል አጋር፤ ውጪ ሀገር የሚኖር ታላቅ፣ እጅግ ታላቅ፣ ሃብታም የናጠጠ፤ ጥሩ ስርፋ ደህና ቦታ ይዞ የተቆናጠጠ፤ ዘመድ ቢኖረንም ዛሬም አልጠገብንም፡፡ ዛሬም አልወዛንም፡፡ ዛሬም አልወፈርንም፡፡ እንዲሁ እንደቀጠን፣ እንዲሁ እንደራበን፣ አመድ እንደመሰልን አለን አባይ፡፡ እንዲሁ አለን፡፡

ያዩህ ሲነግሩን፤ ከግብፅ ጋር ተኝተህ፤ ት……ልቅ አልጋ አንተው ተዘርግተህ፣ ት……ልቅ ፍራሽ አንተው ተከምረህ፣ ት…ልቅ አንሶላ አንተው ተነጥፈህ፣ ት…ልቅ ብርድ ልብስ አንተው ተደርበህ፣ ት…….ልቅ እንትን አንተው እንትን ሆነህ፤ “አቤት ፍቅራችው ሲያስቀና” እያሉ ብዙ ሰዎች ያወራሉ፡፡

“አምሮበታል፣ ዘንጧል፣ ቢጠሩትም አይሰማ! ከርሷ በቀር አይለማ፣ ከርሷ በቀር… እንዴት የሚያስቀና ፍቅር እንዴት የሚያስቀና ትዳር መስርቷል” ይሉሃል፡፡

ለመሆኑ ከእናት ከአባት ፈቃድ ውጪ፤ የማንአለብኝነት ጋብቻ እንዴት ደስስስስ አሰኘህ እንዴት አሞቀ ጉልቻ…? ሽማግሌ እንኳን ሳይላክ በቅጡ እንዲሁ እንደዋዛ፤ ጎጆ ስትወጡ እሷስ እንዴት ዝም አለች? ቤተሰቦቿስ ምን አሉ? ገሌ ገብተህ ስትቀር “እሰይ አበጀህ” ነው የሚሉ…?

እንደው የሚገርመኝ እንደው የሚደንቀኝ ይቺ ግብፅ ብሎ ሴት፤ ገና በአፍላነት ያየሃት፣ በህጻንነትህ የወደድካት፣ በልጅነትህ የተኛሃት፣ በአደባባይ እንትን ያልካት፣ እናትህን አስረስታ፣ ቀልብህን ሁሉ አስታ፣ ያሳጣችህ ይሉኝታ፤ ብትሰጣት ብትሰጣት፤ “አረ በቃህ… እስቲ ደግሞ ለእናትህ… ካፈራነው ባትልክ እንኳ ካፈራችው አስቀርላት ዝም ብለህ አትንጠቃት እርሷስ ቢሆን ማን አላት…?” የማትልህ እንዴት ያለችው ሚስት ናት!

አባ…ዬ!

ድሮ አፈሩን አጥበከው ከራስህ ጋር በጥብጠከው ቀይ ቀለም አስመስለህ፤ ለዛች ለሚስትህ ይዘህ ሽው ስትል ብቻ ነበር የምናውቀው፡፡

አሁን ደግሞ በቅርቡ ይዘሃል አሉ አዲስ ውሽማ፤ ከራሷ በቀር ሌላ እግዜርን እንኳ የማትሰማ! እርሷ እንዳለችህ ደግሞ፤ ገንዘባችንን፣ ብራችንን፣ ባላረንጓዴ ቀለሙን፤ የቁርስ ምሳ እራት የልጆቻችን ቀለቡን፤ እፍስፍስ አድርገህ እየወስድህ “ግዴየለም እመልሳለሁ” እያልህ ይዘህ ሽውውውው ትላለህ፡፡

እኛም እንደ ትላንቱ ዛሬም እየዘፈንን፤ እያልን እልል ዝም ብቻ ነው የምንል፡፡ “አባይ ማደሪያ የለው ደሞዝ ይዞ ይዞራል፤ አባወራው ከነልጁ ጾሙን ጥቅልል ብሎ ያድራል፡፡ አባይ ወንዛ ወንዙ ብዙ ነው ደም ወዙ” እያልን እየዘፈን ዝም ብቻ ነው የምንል፡፡

አረ ለመሆኑ፤ ስንት ድረስ ነው የሚበቃህ…? ስንት ድረስ ነው የሚያጠግብህ…? መቼስ ነው የምትመልሰው…? አፈር አንሶህ፣ ውሃው አንሶህ፣ ደሞዝ ደግሞ የምትወስደው… እስቲ ንገረኝ አባይ መቼ ነው እዳህን የምትከፍለው…? ምንስ አድርገህ ምን ሰርተህ ነው የእናትህን እና የእኛን ሀቅ እንትፍ ብለህ፤ ምትመልሰው…? እስቲ ንገረኝ አባይ! አህያ እንኳ በወለደች አረፈች ይላል ያገሬ ሰው፤ እናታችን አንተን ወልዳ ቢቀርላት እንኳ ማረፉ፤ ምናል እፎይ ባለች በቀረላት ዘረፋ…?

አንተ!

ምንድነው እንዲህ የሚያደርግህ? በቃኝ ማለትን የማታውቀው፤ ትንሽ ይሉኝታ የሌለህ፤ አረ በማን ወትተህ ነው…!? እልፍ ሲሰጡህ ስንዝር፤ አፈር ሲሰጡህ ብር፤ ደሞ ይዘህ ብርርር! የምትለው አረ ከየት ተማርከው…!

አባይ…

በልጅነትህ ግብጽን አግብተህ ከሱዳን ተዳርተህ፤ በስተርጅናህ ደግሞ እንትናን ወሽመህ ሁሉም አምጡ አምጡ ይላሉና፤ አንተም ስጡ ትላለህ? ለእኛ እና ለእናትህ ለኢትዮጵያስ እስቲ ቁርጥ ቀን ንገረኝ መቼ እንኩ ትለናለህ…?

እስከዛሬ የምትወስደው አፈሩም ሆነ ብሩ፤ “እሱ ካለ ምን ይደረግ” ብለን እንጂ ኖሮን ተርፎን አይደለም ካገሩ፤ ይሄንን አንተም ታውቃለህ፤ ቁባቶችህም ያውቃሉ! ዝም ብለው እንጂ እየወሰዱ ዝም የሚሉ፤ አዎ… እንደሌለን ያውቃሉ፡፡

ግድ የለም “ከሌለው ላይ የሚሰጥ እርሱ የተባረከ ነው” ይላል እና መፃፉ ባትከፍሉንም አንኳ እንዳሻችሁ ብታጠፉ፤ ትዝብት ሆኖ ትርፉ… ግዴለም ውስዱ ግዴየለም ዝረፉ፡፡ ገንዘብ አላፊ ነው አፈርም ጠፊ ነው ተብሎ ባጻፍም ያው እኔ ብያለሁ፡፡

ግና አባይ…

የአሁን ዳር ዳርታችሁ ምንም ደስስስስ አላለኝ፤ እንደው ትከሻዬን ሩሄን ነው የቀፈፈኝ፡፡ ውሽማ እና ሚስትህ እዛ እና እዚህ ሆነው ያለንን ሲወስዱ፤ በእኛው ሲነግዱ በእኛው ሲያረግዙ በእኛው ሲወልዱ ጸጥ ብንላቸው፤ አሁንም አርግዘው ሌላ እንዳማራቸው ሌላ እንዳሰኛቸው ወዲህ እና ወዲያ ሆነው ሲያወጉ ሰማናቸው፡፡

አበዛከው አባይ፤ ያለንን ብንሰጥህ፣ ፀጥ ዝም ብንልህ፣ አክብረን ነው እንጂ፤ ፈርተንህ መሰልንህ…? ነፍሰጡር ሚስትቶችህ፤ ያለ ዕቅድ አርግዘው፣ ነፍሰ ጡሮች ሆነው፣ ነፍስ ነፍስ ሸቷቸው፣ ነፍስ አምጡ ቢላቸው፤ አንተም ይሉኝታ አልባው ብትወስድ የማይበቃህ የቀደመው አንሶህ አሁንም ከጀለህ!

አበዛኸው አባይ

በጣም አበዛኸው…!

ወዳጅህ

ማስታወቂያ፤


ኢሕአፓ በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች በህቡዕ ወረቀት በተንኩ አለ

$
0
0

eprp1በስውር የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)አባላት በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች ረቡዕ ሌሊት ሰኔ 5/2005 ዓ.ም. /June 12, 2013/  ተነሥ  በሚል ርዕስ የተዘጋጁ ቀስቃሽ ፅሑፎችን የበተኑ ሲሆን በዋናነት በቦሌ፣በካዛንቺስ፣በአራት ኪሎ፣በሽሮ ሜዳ፣በቄራ፣በፈረንሳይ ለጋሲዪን፣በሜክሲኮ፣በፒያሳ፣በመገናኛ፣በኮልፌ፣በመርካቶ፣በጎፋ እና በመሳሰሉት ዋና ዋና የከተማዋ ክፍል በሚገኙ የማስታወቂ ቦርዶች ላይ ተለጥፈው የታዩ ሲሆን በተለይ ሐሙስ ሰኔ 6/2005 ዓ.ም. በርካታ ነዋሪዎች ጽሑፉን ማንበብ ችለዋል።ይሁን እንጂ ይህ ዜና የደረሳቸው የገዢው ፓርቲ አመራሮች ወዲያው የፌደራል ፖሊሶችን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላትን በማሰማራት በዋና ዋና ቦታዎች ላይ የሚገኙትን ያነሱ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢ ግን ጽሑፎቹ እስከ ቀትር ሳይነሱ በበርካታ ሰዎች መነበብ ችለዋል።


የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በ5ለ1 አደረጃጀት ጠርንፎ እንደያዘ የሚነገርለት ኢህአዴግ ይህ አይነቱ ድንገተኛ ክስተት ዛሬም ድረስ ከህዝብ ጋር ሆድ እና ጀርባ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ሲሉ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ትዝብታቸውን የገለፁ ሲሆን የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የአዲስ አበባ ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ የወጣቶች ሊግ አመራሮች አስቸኳይ ስብሰባ ሐሙስ ዕለት እንደተቀመጡ ከስፍራው መረዳት ተችሏል።

eprp2

ተነሥ  በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የዚህ ጽሑፍ ይዘት የሚከተለው ነው፦ “እጅግ የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፦ የአኩሪ ታሪክ ባለቤት፤ይልቁንም ለጥቁር ህዝቦች የነፃነት ጮራን የፈነጠቅህ ፋና ወጊ የነፃነት አርበኛ መሆንህ የአደባባይ ምስጢር ነው።ይሁን እንጂ የዚህ ሁሉ ጥንካሬህ መሠረት የሆነው አንድነትህ በጎጠኛው የወያኔ ቡድን የዘውጌ አስተዳደር ተሸርሽሮ ዛሬ በሀገርህ ተንቀሳቅሰህ የመስራት መብትህ ተገድቦ፣ከችሎታህና ከግለሰባዊ ክህሎትህ ይልቅ በዘር ማንነትህ እየተመዘንክ የኢኮኖሚ መገለል እየደረሰብህ ህይወት ብርቱ ሠልፍ ሆናብህ ሀገርህን ጥለህ እንድትሰደድ በተሰላ ስሌት በመኖርና ባለመኖር ቅርቃር ውስጥ እንድትባዝን ተደርገህ፣ሰብዓዊና ዴሞክራሲዊ መብትህ ተገፎ የመናገርና ሃሳብህን በነፃነት የማራመድ መብትህን ከመነጠቅህ ባሻገር በአጠቃላይ ህልውናህ በወያኔ የግፍ መዳፍ ውስጥ ወድቋል።ስለሆነም እንደመዥገር በላይህ ላይ ተጣብቆ በደምህ የሰባውን ይህን ዘረኛ ቡድን ከጫንቃህ ላይ አራግፈህ በፍትህ አደባባይ የምታቆምበት ጊዜው አሁን ነው።ሀገርህንና ራስህን ለማዳን ተነሥ!!!”

By: Beyene Mesfin.                   

ገብረኪዳን ደስታ በትግርኛ “አጼ ምኒልክን ለሸዋ እንጂ ለኢትዮጵያ አልቆሙም ነበር” በሚል በጻፉት መጽሐፍ ላይ የሕዝብ አስተያየት ይፈለጋል

$
0
0

መምህር ገብረኪዳን ደስታ በትግርኛ በጻፉት ባለ533 ገጽ መጽሐፍ የአጼ ዮሐንስን ታሪክ ከፍ አድርገው፤ የአጼ ምኒልክን ታሪክ በሚያንኳስ መልኩ ማቅረባቸውን በርከት ያሉ ታዛቢዎች እየተቃወሙ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ እየገለጹ ነው። መምህሩ በቪኦኤ ላይ ቀርበው በድፍረት ወይም እኔ የማውቀውን ታሪክ ነው የምጽፈው በሚል “ምኒልክ የሸዋ እንጂ የኢትዮጵያ አመለካከት አልነበራቸውም” እንዲሁም ‘ምኒልክ ሰሜኑን የኢትዮጵያ ክፍል ሃገሩ አድርጎ አይመለከትም ነበር’ ሲሉ መናገራቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ይህን ተከትሎ ሃገር ወዳዱ ዶ/ር ሹመት ሲሳይ ምላሽ ሰጥተዋቸዋል። የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች በቪኦኤ ላይ የቀረበውን የመምህር ገብረኪዳን ደስታን አስተያየት እና የዶ/ር ሹመት ሲሳይን ምላሽ አድምጠው አስተያየት እንዲሰጡ ተጋብዘዋል። ቃለ ምልልሱ እንደሚከተለው ተሰተናግዷል።


Menelik_II_ethiopia

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከዓመት ከስድስት ወር እስር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቃሊቲ ሰው ገብቶ እንዲጠይቀው ተፈቀደ

$
0
0

ከሕግ ውጪ መታሰሩን ተረድተው በያሉበት ድምፃቸውን ለሚያሰሙ ምስጋና አቅርቧል

"ስላደረጋችኹልኝ እና ስለምታደርጉልኝ ኹሉ አመሰግናለሁ!" እስክንድር ነጋ

"እስክንድር ለዚህን ያህል ወራት እስር ቤት መቆየቱን ተጠራጠርኩ፤ ጥንካሬው አሁንም አብሮት አለ" ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ Jornalist Eskinder Nega

Ethiopia Zare (ዓርብ ሰኔ 7 ቀን 2005 ዓ.ም. June 14, 2013)፦ ላለፉት አስራ ስምንት ወራት በእስር ላይ ያለው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በዚህ ሣምንት መፈቀዱን ለመረዳት ችለናል። ዛሬ ጠዋት ቃሊቲ ሄደው ከጠየቁት ውስጥ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ አንዷ ስትሆን፤ አላግባብ ከሕግ ውጪ መታሰሩን ተረድተው በያሉበት ድምፃቸውን ላሰሙና ለሚያሰሙ ሁሉ በያሉበት ምስጋናዬ ይድረሳቸው ብሏታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መከራ

$
0
0

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ግንቦት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. (June 6, 2013) ባሰራጨው ፕሮግራም የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መከራ አስመልክቶ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የበደሉ ገፈት ቀማሽ የሆኑት ተጎጂ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶች፣ የኃይማኖት ተቋማት አባቶች፣ ባለሀብቶች፣ የበጎ አድራጎት ተቋማት ኃላፊዎችና በስደትና ተጓዳኝ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎችን በመጋበዝ አወያይቶ ነበር። ዝግጅቱ በሁለት ክፍል የተከፈለ ሲሆን፣ ሁለቱንም ከዚህ በታች ያገኙዋቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ አብርሃም ያዬህ የምላስዎትን አፈሙዝ በአቶ ገ/መድኅን አርአያ ላይ አያዙሩ!

$
0
0

ሸግዬ ነብሮ

Abraham11-271x300 የዚህ ጽሑፍ መነሻ በቅርቡ አውራምባ ታይምስ የተባለው ድረ-ገጽ ከአቶ አብርሃም ያዬህ ጋር ያደረገው ቃለ-ምልልስ ነው።
ወደ አቶ አብርሃም ቃለ – መጠይቅ በዝርዝር ከመግባታችን በፊት “ማን ያርዳ የቀበረ፣ ማን ይናገር የነበረ” የሚለውን የሀገራችንን ብሂል በማጤን አቶ አብርሃም ያዬህንም ሆነ አቶ ገ/መድኅን አርአያን በተመለከተ በቅርብ የማውቀውን አቀርባለሁ። በዚህ አጋጣሚ አቶ አብርሃም ወደ ሀገር ቤት በገቡበት ጊዜ የነበሩ እማኞች በሙሉ በሕይዎት የሉም፤ ወይም ቢኖሩም እንኳን ምንም አይሉም ብለው አስበው ከሆነ መሳሳታቸውን አስቀድሜ ልጠቁማቸው እወዳለሁ።
አቶ አብርሃምያዬህ የመለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስዩም መስፍንና አባይ ፀሐዬ የሕወሓት ማፊያ ዘራፊ ቡድን ቁንጮ አባላት የቅርብ ጓደኛና የአንዳንዶቹም የሥጋ ዘመድ ናቸው። ግለሰቡ ኢትዮጵያ ውስጥ በሥራ ዓለም በቆዩበት ዘመን ምንም በደል ያልደረሰባቸውና የተደላደለ ኑሮ የነበራቸው ሲሆን፣ ግብር እየከፈለ ያስተማራቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በመክዳት እንደ ዘመዶቻቸው የጎጠኝነት ህመም (Narrow Tribal Mentality) ተጠናወቷቸው ትግራይን ከኢትዮጵያ ለማስገንጠልና የትግራይ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከተመሠረተ በኋላ የአመራር ቦታ እይዛለሁ በሚል ቀቢፀ ተስፋ ሀገር ጥለው የፈረጠጡ ደካማ ፍጡር ናቸው። (እንደ ቀድሞ ታጋዮች፣ የአሁን ሀገር ዘራፊዎች የናጠጠ ዲታ እሆናለሁም ብለው ሊሆን ይችላል።)
አቶ አብርሃም እጀ ለስላሳ፣ ባለረጅም ምላስ፣ ለሜዳ ትግል የማይበቁና የወንድነት ሀሞት የሌላቸው በመሆናቸው ከመከረኛው የትግራይ ሕዝብ በሚገኘው የድርቅ እርጥባን ፍርፋሪ ካርቱም ውስጥ እየተንደላቀቁ የኖሩ ቅምጥል “ታጋይ” ናቸው። የአቶ አብርሃም የውጭ የሥራ ተልዕኮ ከዚህ በፊት እርሳቸው ለማናፈስ እንደሞከሩት የሕወሓት የመረጃ መኮንንነት አይደለም። የመረጃ መኮንንነት መለፍለፍን ሳይሆን ማዳመጥንና ማመዛዘንን የሚጠይቅ እነ ምን ይዤ ልቅረብ ብለው የሚሠሩት ሞያ ሳይሆን፣ የሰከነ አዕምሮ የሚጠይቅና በተክለፈለፈ የአብርሃም ያየህ ዓይነት ፍጡር የሚከናወን ተግባር አይደለም። ስለሆነም የግለሰቡን ፀባይ የተረዱት ጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸው የአብርሃም ምላስ ይጠቅማል ባሉት የአገናኝነት (Laison Officer) ተግባር ላይ መደቧቸው። ለግል ጥቅም የቆሙ የሱዳን ባለሥልጣኖችን በገንዘብ በመያዝ ድጋፍ ማስገኘት፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባንኮች ወያኔ በዘረፈው ገንዘብ የምዕራቡ ዓለም ሆዳም ጋዜጠኞችን በመደለል በየሆቴሉ በመጋበዝና ውስኪ በማጠጣት የድለላ ሥራ በመሥራት ትግራይ ገብተው ድርቅን በተመለከተ ቪዲዮና ፎቶ በማንሳት በድርቅ ዕርዳታ ስም ለወያኔ እኩይ ተግባር የሚውል ገንዘብ የሚያስገኝ የፕሮፓጋናዳ ሥራ እንዲሠሩ ማድረግ ነው።
በሌላ በኩልም የዛሬ የሕወሓት መኳንንቶች ወደ ሱዳን ብቅ ሲሉ ማረፊያና ቆነጃጅቶችን በማዘጋጀት፣ የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበትን መንገድ በማመቻቸት ይላላኩ እንደነበር ከጤፍ የማይቆጥሩዋቸውና የሚንቁዋቸው ዛሬ በሸራቶን ልዩ ክፍል ተዘጋጅቶላቸው የሚንደላቀቁት የሕወሓት ማፊያ ቡድን ዘራፊ ቢሊዬነሮች ሁሌም የሚሉት ነው። አቶ አብርሃም የትግራይን በረሃ ያልረገጡና የስሚ ስሚ ከሌላ ያዳመጡትን ሽንኩርትና ቅመም ጨምረው አጣፍጠው የሚያቀርቡ ጥሩ የሸክላ ድስት ናቸው። የአቶ አብርሃም ምላስ ረዥም ከመሆኑ የተነሳ መቋጠሪያ ሸምቀቆ ስለሌለው እነ ስብሃት ነጋ ወደ ሚስጥሩ ጓዳ ሳያስገቡ በጥንቃቄ በገደብ በሩቅ የያዙዋቸው አገልጋያቸው (Servant) ነበሩ።
ማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ (ማሌሊት) ሲመሠረት አቶ አብርሃም በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ቀርቶ በተራ አባልነት እንኳን ያልታጩ ጀሌ መሆናቸውን ሲገነዘቡ ነው “እኔ ከማን አንሼ ነው” በማለት ተቆጥተው እና መለስና ስብሃት ጋ ካልቀናኝ የመንግሥቱ ኃይለማርያምን ልብ እሰርቃለሁ፤ የናቀኝንም እበቀላለሁ ብለው በማስላት ነበር ወደ አዲስ አበባ የገቡት።
አቶ አብርሃም ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ የተቀበላቸው የመረጃ መሥሪያ ቤቱ ቢሆንም የግለሰቡን ፀባይ በመረዳቱ ያሠማራቸው በፕሮፓጋንዳ ሥራ ብቻ ነው። አቶ አብርሃም ስለሕወሓት ወያኔ የሆነውን ታሪካዊ መረጃ ከማነብነብና ከተለያዩ ጽሑፎች ካገኟቸው መረጃዎች በስተቀር ትግራይ በረሃ ውስጥ ስላለው ሁኔታ የሚያውቁት የስሚ ስሚ ካልሆነ በስተቀር አንድም ነገር የለም። ስለትግራይ በረሃና ጓዳ ጎድጓዳ የእጃቸውን መዳፍ ያክል የሚያውቁትና ለመረጃው መ/ቤት እጅግ ጠቃሚ መረጃ የሰጡት ግን አቶ ገ/መድኅን አርአያ ነበሩ። ሆኖም ግን ሚስጥሩ ያልገባቸውና የአብርሃም ያየህን ንግግር በቴሌቭዥን መስኮት ያዳመጡና አሁንም ወያኔ በሀገራችን ላይ ከሚፈፅመው ጋር እያዛመዱ ሰውየውን እንደትንቢተኛ የሚያዩዋቸው አሉ። ሀቁ ግን በመረጃ መሥሪያ ቤቱ ቢሮ አብርሃም ያየህን ተዋናይ አድርጎ የተሠራ ድራማ ነው። መረጃው የተገኘው ከአቶ ከአቶ ገብረ መድኅን አርአያና ከመረጃ መ/ቤቱ ነው።
ወያኔ ኢትዮጵያን ሲወር አቶ አብርሃም የፈረጠጡት ወደ ዩጋንዳ ነው። በዩጋንዳ ቆይታቸውም ወያኔን እታገላለሁ በሚል ከኮሎኔል መንግሥቱ ገንዘብ ለመቦጨቅ ያደረጉት ሙከራ ባለመሳካቱ ግለሰቡ ባላቸው የሲጋራ፣ የመጠጥና የሴሰኝነት ባህሪ ገንዘብ ስለማይበቃቸው ወደ ተራ ሌብነት በመዝቀጥ በንጉሡ ጊዜ የፖሊስ ጄኔራል የነበሩትን የጄኔራል ጋሻው ከበደን ሴት ልጅ ለመዝረፍ ሲሞክሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘው አራት ዓመት ተፈርዶባቸው ካምፓላ ውስጥ ሉዚራ ወደተባለው ወህኒ ቤትና ከባድ ወንጀለኞች በሚታሰሩበት Block A ተወርውረው ሳለ በዩጋንዳ፣ አሜሪካና መላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከእሥር እንዳስፈቷቸውና ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለሱ እንደረዷቸው ይታወሳል።
ውለታ ቢሱና በልቶ ካጁ አብርሃም ያዬህ ግን በዴንማርክ ኑሯቸውን ካደላደሉ በኋላ ቅንጅትንና የረዷቸውን ኢትዮጵያውያን ለምን እኔን በትግል አመራርነት አላቀፉኝም በሚል በተለያዩ ጊዜያቶች ሲያንቋሽሹና የመለስ ዜናዊን ታላቅነት ሲለፍፉ የወያኔ ድረ-ገጽ በሆነው በአይጋ ፎረም ሳይቀር ተስተውለዋል።
በቅርቡም በለመደ አፋቸው አውራምባ ታይምስ በተባለው ድረ-ገጽ ላይ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ በጊዜው የነበሩት ሰዎች ያለቁ መስሏቸው “ላም ባለዋለበት ኩበት ለቀማ” እንዲሉ እራሳቸውን አዋቂ አድርገው አቶ ገብረ ምድኅን አርአያን አንቋሽሸዋል። በደርግ ዘመን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በቀረበው ቃለመጠይቅ ላይ አቶ ገብረ መድኅን ለመሳተፍ ፈቃደኛ እንዳልነበሩና እንዲያውም ፊታቸውን ለማሳየት እንዳልፈለጉ፣ ወደ መገናኛ ብዙሐን ያመጧቸው እርሳቸው እንደሆኑ፣ ሰዎች ከአቶ ገ/መድኅን ጋር በአንድ ላይ መቅረብ እንደሌለባቸውና ነገርም ስለሚያበላሹ እንደመከሯቸው፣ አቶ ገ/መድኅን ከእርሳቸው በፊት ሁለት ዓመት ቀድመው የገቡ ቢሆንም ጠቃሚ ሆነው ባለመገኘታቸው ተጥለው እንደተቀመጡ፣ በሐውዜን ጉዳይ ላይ የተናገሩት ሁሉ ሀሰት እንደሆነና እንዲያውም ሐውዜን ሲደበደብ አዲሰ አበባ እንደነበሩ፣ አብርሃም ያዬህ ዓይናቸውን በጨው አጥበው ቀባጥረዋል።
አቶ ገ/መድኅን አርአያ የወያኔ በጅሮንድ ወይም ገንዘብ ያዥ የነበሩ፣ ሕወሓት ሲመሠረት ጀምሮ አብረው የነበሩ፣ የወያኔን ገመና ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ከካርቱም መሸታ ቤት ሳይሆን ከትግራይ በረሃ የመጡ፣ የረጋ መንፈስ ያላቸው፣ አስተዋፅዎአቸው (ክሬዲታቸው) በከፊል በአፈ-ጮሌው አብርሃም ያዬህ የተሰረቀባቸው ሀቀኛና ጥሩ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ናቸው። ከላይ እንደተገለፀው በአቶ አብርሃም አፈ-ጮሌነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቀረበው ገለፃ መረጃው የተገኘው ከአቶ ገ/መድኅንና ከደኅነነቱ መ/ቤት የመረጃ ዘገባ (Intelligence Analysis) ነው።
በእንግሊዝ ሀገር በለንደን ከተማ የወያኔ የመረጃ ሠራተኛ ተባባሪ ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኘው ኃይለ ሥላሴ ግርማይ የተባለው ቅጥረኛ እየተከፈለው አቶ አብርሃም በኢትዮጵያ ቴሌቨዥን ሲለፈልፉ ከጀርባ ሆኖ መረጃ ሲያቀብልና ጽሑፍ ሲሰጥ የነበረ ነው። የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንዲሉ ኃይለ ሥላሴ ግርማይ የአቶ ገ/መድኅን አርአያ የእናታቸው ልጅ ታናሽ ወንድማቸው ሲሆን፣ በተለያዩ ጉዳዮች በተለይም እነ ተክሉ ሐዋዝ በእነ ስብሓት ነጋ በመገደላቸው ተጣልቶ እየተከፈለው ለደኅንነቱ መ/ቤት መረጃ ሲያቀብል የነበረ ግለሰብ ነው። ሮም ላይ በጣሊያን መንግሥት አማክኝነት የደርግና የወያኔ የእርቅ ስብሰባ በተደረገበት ወቅት የአውሮፕላን ቲኬትና የልዩ ልዩ ወጭ ተልኮለት ከለንደን ወደ ሮም በመሄድ ከረጅም ዓመታት በኋላ ከአቶ ገ/መድኅን ጋር እንዲገናኝ ተደርጓል። (አቶ አብርሃም አዲስ አበባ በቴሌቭዥን ሲለፈልፉ የአቶ ገ/መድኅንን የሮም ጉዞ እንኳን አያውቁም ነበር።)
ህምባባ ሼዊት በተባለ ኦፕሬሽን ወያኔ አቶ ገ/መድኅንንና አቶ አብርሃም ያዬህን ለማጥፋት ያደረገው ዝግጅት ተደርሶበት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲነገራቸው መሬት ተቀድዳ በዋጠችኝ ሲሉ የነበሩት አቶ አብርሃም ስንት ማደሪያ እንደቀያየሩና ያሳዩት የባህሪ መለወጥ ማንነታቸውን አስመስክሯል። በአንፃሩ ግን አቶ ገ/መድኅን በመገናኛ ብዙሐን ከመቅረባቸው በፊት በአንድ የመንግሥት መ/ቤት እንደ ማንኛውም ሰው ሳይፈሩ ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩና እንኳን ሸፍኑኝ ሊሉ ግምባር ቀደም ሆነው ደረታቸውን ሰጥተው ወያኔን ፊት ለፊት የመፋለም ቁርጠኛ አቋማቸውን እጃቸውን ለመንግሥት ከሰጡ ቀን ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ያስመሠከሩ ሀቀኛና ቀጥተኛ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
አቶ ገ/መድኅን አርአያ አቶ አብርሃም እንደሚሉት ከእርሳቸው በፊት ሁለት ዓመት በኢትዮጵያ ካለሥራ ተጥለው የቆዩ አይደሉም። አቶ ገ/መድኅን ከአቶ አብርሃም በፊት ኢትዮጵያ ውስት የቆዩት ለዘጠኝ ወራት ሲሆን ስለ ሕወሓትም ሆነ በትግራይ በረሃ የውሃ ኩሬ ሳይቀር የት እንዳለ የማስታወስ ከፍተኛ ችሎታ ስለነበራቸው ሳይጋለጡ ለእናት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ሲሠሩ የቆዩ እንጅ በሬዲዮና በቴሌቭዥን የሚያቅራሩ የድል አጥቢያ አርበኛ ወይም የከተማ ፋኖ አልነበሩም።
ለመሆኑ አቶ አብርሃም ቀን በቴሌቭዥን ሲጮሁና ማታ ማታ ደግሞ ከአዲስ አበባ እስከ ናዝሬት በሚገኙ መሸታ ቤቶች “አሆይ ላሎዬ” ሲሉ፣ ጀግናውና ሐቀኛው አቶ ገ/መድኅን ግን ትግራይ በረሃ ድረስ እንደገና ገብተው አመርቂ ሥራ ሠርተው መውጣታቸውን ብነግረዎት ምን ይላሉ!? አቶ አብርሃም ያዬህ የት እንደነበር ሊያውቁት ቀርቶ ምንነቱን እንኳን ሰምተው የማያውቁትና የወያኔ ሬዲዮ ጣቢያ የነበረበት ክሳድ ግመል የተባለ ተራራማ ቦታ ድረስ በመሄድ ገ/መድኅን አርአያ ኢትዮጵያዊ ግዴታቸውን ተወጥተው የተመለሱ ጀግና መሆናቸውን በሕይዎት ኖሬ ስመሠክርላቸው ክብርና ኩራት እየተሰማኝ ነው። ይህንና ሌሎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሊነገርላቸው የሚገባቸውን ድንቅ ሥራዎች አንድ ቀን በሕይዎት ያለን ምሥክሮች በአካል ቀርበን የመንመሠክረው ሀቅ ስለሆነ አቶ አብርሃም ዛሬ አፍዎ እንዳመጣ መዘላበዱ ነገ ትርፉ ውርደት ይሆናልና ቢታቀቡ እመክረዎታለሁ።
በዚህ አጋጣሚ ዕውነታውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ወደፊት ሊያቀርቡ የሚችሉ ብዙ ሰዎች ስላሉ አቶ አብርሃም ያዬህ የምላስዎትን አፈሙዝ ከጀግናውና ሀቀኛው ገ/መድኅን ይልቅ ወደ ሀገር አጥፊው ወያኔ እንዲያዞሩ ስመክር፣ ሌሎችም እበላ ባይ ሆድ አደሮች ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ስማቸውንና ታሪካቸውን ባይለውጡ መልካም ነው እላለሁ።

አንድነት ፓርቲ ለመድረክ ምላሽ ሰጠ፤ የተደበቀውን አፍረጠረጠው

$
0
0

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

UDJበመሠረቱ ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) መድረክ እንዲመሠረትና አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ድርጅት ነው፡፡ ለመድረክ መፈጠርና መጎልበት በአደረገው ጉልህ ተሳትፎ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለበት መሆኑን መድረክም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡

የግምገማው ግኝቶች በየትኛውም ገጽና ቦታ የመድረክ ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብና የስምምነት ሰነድ በመድረክ አባል ድርጅቶች በጋራና በሙሉ ስምምነት መጽደቃቸውን አላስተባበለም፡፡ አልካደምም፡፡ በተጨማሪም መድረክ እንደ አንድ የፖለቲካ ኃይል በኢትዮጵያ ሕዝብ ህሊና ውስጥ ከፍተኛ ተስፋን የፈጠረ ብቻ ሳይሆን አዲስ የጉዞና የአሠራር አቅጣጫን የቀየሰ መሆኑን ጭምር አንድነት ያውቀዋል፡፡ ያምንበታልም፡፡

መድረክ ከመቀናጀት ወደ ግንባር የተሸጋገረበት ሂደትም ብዙ ችግሮችና ድክመቶች ቢኖሩትም በአባል ድርጅቶች ሙሉ ስምምነትና ፍቃደኘነት መሆኑን አንድነት አምኖ የሚቀበለው እውነታ ነው፡፡ በመሆኑም የመድረክ ድክመቶች፣ ስህተቶችና ችግሮች በሙሉ አንድነት ፓርቲም አብሮ የሚጋራውና የሚጠየቅበት ነው፡፡ የግምገማው ዓላማ ችግሮችንና ድክመቶችን ወደ ሌሎች የመግፋት (blame-shifting) አባዜ አለመሆኑን አበክረንና አጠንክረን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን፡፡

በአባል ድርጅቶች መካከል ስምምነት ያልተደረሱባቸው የፕሮግራምም ሆነ የህገ-ደንብ ጉዳዩችም በቀጣይ ውይይቶች ለማቀራረብ እንደሚሞከርና ይህ ካልተሳካም መድረክ የመንግሥት ሥልጣን ሲይዝ በሕዝብ ውሳኔ መፍትሔ እንዲያገኙ እንደሚደረግም ሙሉ ስምምነት ያገኘ ጉዳይ መሆኑ እውነት ነው፡፡

የመድረክ መግለጫ፣ ችግርች የሚጀምረው በመጀመሪያ ያልተካሄዱ ጉዳዩችን እንደተካሄዱ አርጎ ከማቅረቡ ላይ ነው፡፡ ሁለተኛውና መሠረታዊው ችግር ደግሞ ድርጅቶች በአንድ ወቅትና ሁኔታ ተስማምምተውና ወደው የተቀበሉት ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ግምገማ ማካሄድ የለባቸውም የሚለው ነው፡፡ በሌላ በኩልም በአንድ ወቅትና ሁኔታ የተወሰኑ ሰነዶችን ፓርቲዎች በስምምነት ስለተቀበሉት ብቻ ሰነዶችን ትክክል ያደርጋቸዋል የሚለው ግንዛቤ ነው፡፡ ባጠቃላይ ሕይወትና በውስጡ ያሉ ክስተቶች በሙሉ የማያቋርጥ የለውጥ ሂደትና እንቅስቃሴ አካል ናቸው፡፡ በመሆኑም በማንኛውም ሥነ አመክኖ (Logic) ሰነዶች ከወቅት፣ ከጊዜና ከሁኔታዎች አኳያ (አንፃር) ይፈተሻሉ፣ ይገመገማሉ ይሻሻላሉ፣ ይለወጣሉም፡፡

በመግቢያው ላይ እንደተቀመጠው የግምገማው ዓላማ የመድረክ ድክመቶች የሚስተካከሉበትና ጥንካሬዎቹ የሚጎለብቱበት ሁኔታ እንዲፈጠርና ብሎም ትግሉ የሚፈልገውን ሁለንተናዊ አቅም ለመፍጠር እንዲቻል ነው፡፡ በዚህ ረገድ የአንድነት ፓርቲ ምን ዓይነት ሚና መጫወት ይገባዋል የሚለውን ጭምር ለመፈተሽ ነው፡፡ በግምገማው ሂደትም የታዩት ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ) ለአለፉት በርካታ ዓመታት በተቃዋሚ ጎራ አብሮ ላለመስራት ፈታኝ ሆኖ የቆየውን የኢትዮጵያ ብሔርተኘነትና ብሔር ላይ በተመሰረቱ ፓርቲዎች መካከል የነበረውን ክፍተት በተወሰነ መልኩ ማጥበቡ በአዎንታነት የሚታይ ቢሆንም፤ መድረክ ከተመሠረተ አራት ዓመት ቢያልፈውም በፕሮግራም ልዩነቶች ላይ አንድም ቀን ውይይት አለማካሄዱና ደንበቦችንም ቢሆን አብረን የቆየንባቸውን ጊዜያት ያገናዘበና ትግሉ የሚጠይቀው ደረጃ የሚመጥን ለውጥ አለማድረጉን ነው፡፡ ይህም አንዱ ዋና ምክንያት በመሆኑ መድረክ ከተመሠረተ ጀምሮ ፓርቲዎቹ የመድረክ አባል ለመሆን ያለመቻላቸው ነው፡፡

ለ) የመድረክን ሕገ-ደንብ በኢ-ዴሞክራሲያዊነት ለማስቀመጥ አስገዳጅ የሆነው አንዱ ምክንያት ፓርቲዎች የመተማመንና የአብሮ የመስራትን መንፈስ መፍጠራቸውና ከ4 ዓመት በኋላም በሙሉ ድምጽ ስምምነት ማለፍ ያለባቸው ጉዳዮች መኖራቸው ጭምር ነው፡፡ የቪቶ ሥልጣን የተሰጠውም የፓርቲዎችን ፍላጎትና ስጋቶች ለማስተናገድ ነው የሚለውም በግምገማው ተገቢ ሆኖ ባለመገኘቱ ነው፡፡ ትልቅ ቦታም ሊሰጠው ይገባ የነበረው ለሕዝብና ለአገር ፍላጎትና ስጋቶች ስለ ነበር ነው፡፡

ሐ) በግንባሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት እያንዳንዱ የመድረክ አባል ፓርቲዎችና አመራሮች በአባል ድርጅቶች ላይ አፍራሽ አስተያየት ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው የሚል ሆኖ ሳለ በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ በአንድነት ፓርቲና በአመራሮቹ ላይ የተሰነዘሩ አፍራሽና ጎጂ አስተያየቶችን በግልጽ በማስቀመጥ ፓርቲዎችና አመራሮች ወደ ትክክለኛው አቅጣጫና መስመር ይመለሱ ዘንድ አባሎችና ሕዝቡም የራሱን ገንቢ አስተዋጽአ እንዲያደርግ ነው፡፡ ከሁሉም በጣም ቅር የሚያሰኘው የመድረክ መግለጫ አፍራሽ አስተያየቶችን ሃሳብን በነፃነት ከመግለጽ መብት ጋር ማያያዙ ነው፡፡ በምን መመዘኛ ነው፡-

‹‹አንድነት ዶ/ር ነጋሶን ሊቀመንበር አድርጎ ቢመርጥም የአማራ ፓርቲ ወይም የአዲስ አበባ ልሂቃን ፓርቲ መሆኑን መካድ አያስፈልግም››
‹‹የአንድነት አዝማሚያ በደቡቦች፣ በአረና እንዲሁም በኦሮሞ ላይ የበላይነትን ለማሳየት ነው››
‹‹ አንድነቶች ፌዴራሊዝምን አይወዱም ፌዴራሊዝሙን የሚጠሉት አማራሮች ናቸው››
‹‹ ከዶ/ር ነጋሶ ውጭ መሪዎቹ አማሮች ናቸው፡፡ ይህን የምለው ስለማውቀው ነው››
‹‹ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ ሲዳማ ወለጋ ወ.ዘ.ተ ሄዶ ድምጽ ማግኘት አይችልም››
‹‹ ኦሮሞ አማራ ክልል ሄዶ ምረጡኝ ቢል ድምጽ አያገኝም፡፡ ኦሮሞ ከሆነ
ለምን ኦሮሞ ፓርቲ አይገባም አማራው ኦሮሞ አገር ሄዶ አይመረጥም››

ይህን የተናገሩት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ናቸው፡፡ በሌላ በኩልም ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በተደጋጋሚ፡-

1. የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉን መመረጥ የሚያውቀው ኢህአዴግ ነው፡፡ የእሳቸው መመረጥ የኢህአዴግ አሻጥር ነው፡፡

2. ስንትና ስንት የዴሞክራሲ አርበኞች ባሉበትና ደጋግመው በምርጫ ያሸነፉ ሰዎች እያሉ አንድ ተወዳዳሪ ብቻ አሸንፋል መባሉ አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡

የደቡብ ህብረት ፓርቲ በአቀረበው የክስ ማመልከቻ፡-

አንድነቶች ‹‹በአቋራጭ ሥልጣን የሚልፈጉ የነፍጠኛ አቋም ያላቸው ናቸው›› እነዚህ አነጋገሮች አፍራሽና አጥፊ ፕሮፓጋንዳ አካል ናቸው፡፡ ከላይ በአንድነት ፓርቲ ላይ ከተሰጡ አስተያየቶች መካከል የተወሰኑቱ ‹‹ጠባብ ብሔርተኝነት›› ባህሪያት የማያመላክቱ ከሆነ ምንን ነው የሚያመላክቱት? ሌሎችንም ምሳሌዎችንና ድርጊቶችንም መጨመር ይቻል ነበር፡፡ ሁኔታው በአጭሩ ለመተው ሲባል እንጂ፡፡
መ) ግምገማው የአንድነትን ብሔራዊ ምክር ቤትን፣ የሥራ አስፈፃሚውንና በመድረክ የአንድነት ተወካዮች ሚና በትኩረት የተመለከተውና የሰሉ ሂሶችን እንደየ ተጠያቂነታቸው ደረጃ የአሳረፈባቸው እንጂ እንዲያው ችግሮችን ወደ መድረክና አባል ፓርቲዎች የወረወረ አይደለም ወደ ውጭ እንዳየ ሁሉ ወደ ውሰጥም አይቷል፡፡

ሠ) በመጨረሻም ግምገማው የመፍትሔ አሳቦችን በአጭር ጊዜና በረጅም ጊዜ በመከፋፈል ጠቃሚ አስተያየቶችን ሰጥቷል፡፡ በተለይም ተቀዋሚ ፓርቲዎች አሁን የሚንቀሳቀሱበት የፖለቲካ ምህዳር እጅግ ፈታኝ የሆነበት ወቅት በመሆኑ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ በአገራችን ጠንካራ መሠረት እንዲይዝ የተቃዋሚ ኃይሎች የመጠላለፍ፣ የመጠፋፋት ፖለቲካ የትም እንደማያደርስ በመገንዘብ በመተጋገዝ በአብሮ መስራት መንፈስ አብሮ መቆም እንዳለባቸው ነው፡፡ የሚያሳየው ከአብሮ መሥራት ውጭ በአገራችን ውስጥ ለውጥ ሊመጣበት የሚችልበት እድል ዝግ እንደሆነ ነው ያመላከተው፣ ያሳየው፡፡ ማንኛውም ፓርቲ የቱንም ያህል ትልቅነኝ ቢልም፣ ትልቅ ቢሆንም ዛሬ ኢትዮጵያ ያለችበትን ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ብቻውን ሊወጣው እንደማይችል ነው የታመነበት፡፡

እውነታውና የግምገማው ዓላማና ግኝቶች ይህ ሆኖ ባለበት ሁኔታ አንድነትን በመድረክ አፍራሽነት ለመፈረጅ መሞከር ‹‹ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ›› ያስመስለዋል፡፡ ይልቁንም አንድነት ለግምገማውም ሆነ በተግባር ያረጋገጠው ለመድረክ ጥንካሬ ብርታትና ወደ ፊት መራመድ እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ አሁንም በትጋት እንደሚሰራ በድጋሚ ያረጋግጣል፡፡ ግምገማዎችን ማካሄድና ውስጣዊ ድክመቶች አንጥሮ በማውጣት ከዚያም ትምህርት አግኝቶና እርምት አድርጎ መራመድ ‹‹ኢህአዴግን ነው የሚጠቅመው፤ ሕዝብን ያሳዝናል›› በሚል መርህ በሽፍንፍን መጓዝ ከአገኘነው ተሞክሮ አፃር ሲታይ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

በመጨረሻም ለመድረክ የምናሳስበው ቁም ነገር የተፈፀሙን የአካሄድ ስህተት ምክንያት በማድረግ የግምገማውን ይዘት አልቀበልም ማለቱ ማንንም እንደማይጠቅም በድጋሚ ተመልክቶ በይዘቱ ላይ ውይይት እንዲከፈት እንዲያደርግ በአጽኖት እንጠይቃለን፡፡ ይህ እስከሆነ ድረስ የአብሮ መስራቱና መተባበሩ ተግባር አሁንም ይቀጥላል፡፡

ሰኔ 5 ቀን 2ዐዐ5 ዓም

አዲስ አበባ

ሁሉንም ነገር ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የቆረጠ ፓርቲ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ መጣሉ የማይቀር ነው!!! ከአአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ የታደለች፤ በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ ለብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች  የተጋለጠች አገር ናት፡፡ በአንፃራዊነት ሲታይም ምንም እንኳን በተፈጥሮ ሀብት የታደለች ብትሆንም ዜጎቿ በርሃብ የሚሰቃዩባት፤ ከሞት ጋር ተጋፍጠው ስደትን የሚመርጡባት፤ በሙስና ተግጣ ያለቀች፣ መልካም አስተዳደር የናፈቃት የምታስቆጭ ሀገርም ናት፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ከራሱ ስልጣን ይልቅ የህዝብን ጥቅም የሚያስቀድም፣ ለህዝብ ጆሮ የሚሰጥ አስተዋይ መሪ አግኝታ አታውቅም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ለዘመናት ያልተፈቱ ችግሮችና በመሪዎቹ የሚፈጠሩ ችግሮች ትከሻውን ያጎበጡት የኢትዮጵያ ህዝብም ሉዓላዊነቱን ለማንምና ለምንም ሰጥቶ አያውቅም፣ ወደፊትም ሊሰጥ አይችልም፡፡  ይህም ስለሆነ ሀገራችን ሉዓላዊነቷ ሳይደፈር ለብዙ ሺ ዓመታት ቆይታለች፡፡

ከዚህ በፊትም አቶማን ቱርኮች፣ ግብፆች፣ ድርቡሾች፣ ጣሊያኖችና ሶማሊያ ባደረጉት የሉዓላዊነት መድፈር የጨቋኞችን ክፉ ድርጊት ወደ ጎን በማለት፣ ‹‹ጨቋኝ ገዢዎች እንጂ ሀገሬ አይደለችም›› በሚል እሳቤ ደሙን አፍስሷል፡፡ አጥንቱን ከስክሷል፡፡ ለባለፉት ሃያ ሁለት አመታት ግን ብሔርንና ጎሳን መሰረት ባደረገው ከፋፋይ ሥርዓት ኢትዮጵያዊ አንድነትን በማደብዘዝና የጋራ ህብረ ቀለምና እሴቶችን ወደ ቡድን ህብረ ቀለምና እሴት በመቀየር፣ ተከብሮና ታፍሮ የኖረ ሉዓላዊነታችንን ከግራና ከቀኝ እንዲቆረስ በማድረጉ ከቀደሙት አገዛዞች ለየት ያደርገዋል፡፡

በተጨማሪም ይሄን ሥርዓት ከሌሎች የቀደሙ አምባገነን ሥርዓቶች ለየት የሚያደርገው ‹‹ሁሉንም ነገር ለፖለቲካ ሥልጣን መጠቀሚያ ማዋል›› የሚለው ተግባሩ ነው፡፡ ሌላው ሁሉ ቀርቶ የአንድ መንግሥት ግዴታዎች የሆኑት ተግባራት መንገድ፣ መብራት፣ ውሃ፣ ቤት የመሳሰሉት መዳረሻቸው የፖለቲካ ሥልጣንን ማራዘም ነው፡፡ እነዚህንም ስለሞከረ አመስግኑኝ፣ ዘምሩልኝ የሚል መንግሥት የኢህአዴግ መንግሥት ብቻ ነው፡፡ በመሰረቱ መንግሥት አይመሰገንም፡፡ በሰለጠኑት እና እድለኛ በሆኑት ሀገሮች ህዝቡ መንግሥቱን እንዳመሰገነ የሚቆጠረው የምርጫ ካርዱን ሲሰጠው ብቻ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ያለው የመንግሥት ግዴታ ነው፡፡

ፓርቲያችን አጥብቆ እንደሚያምነው ለፖለቲካ ፍጆታ የማይውል ንፁህ ልማት እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡ ለፖለቲካ መጠቀሚያ የማይውል የመሠረተ ልማት ግንባታ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል ትላልቅ ግድቦችን መገንባት፣ ለመስኖና ለተለያዩ ጉዳዮች  መጠቀም እንደ ኢትዮጵያ በርካታ ህዝብ ላለው ሀገር አስፈላጊነቱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚገባ አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት ዛሬ ኢህአዴግ እንዳዲስ ያነሳው በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ መስራትና የማልማት አስፈላጊነት ለዘመናት ሲነሳ የነበረ ጉዳይ ነው፡፡

አንድነት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአባይ ወንዝ ላይ የመጠቀም ተፈጥሮአዊና መብት እንዳለውና ይሄ የኢትዮጵያውያን መብት ለማንም ተላልፎ የሚሰጥ  እንዳልሆነ በጽኑ ያምናል፡፡ በአባይ ላይ በፍትሓዊነት የመጠቀም መብት ከፓርቲዎች ወይም ገዢ ከሆነው ፓርቲ ለህዝቡ የሚሰጥ ሳይሆን የህዝቡና የህዝቡ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ እንዳነሳነው ችግሩ የሚመነጨው ገዥው ፓርቲ አባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመስራት መነሳቱ ሳይሆን የአባይን ጉዳይ የኢህአዴግ ጉዳይ ማድረጉ፣ የአባይን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ ራዕይ ማድረጉና ከእለት ጉርሱ ቀንሶ ቦንድ እየገዛ ያለውን ህዝብ የግድቡ ባለቤት ማድረግ አለመቻሉ ነው፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆነን ግድቡ በጊዜያዊነት አቅጣጫ እንዲቀይር የተደረገበትን ቀን ከግንቦት ሃያ በዓላቸው ጋር ሆን ብለው ለማገጣጠም መፈለጋቸው ነው፡፡ ግድቡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግድብ ይሁን የኢህአዴግ በውል አልለዩትም፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የፖለቲካ መጠቀሚያ ጉዳይ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአባይ ላይ ግድብ ከመሰራቱ በፊት ማለቅ የሚገባቸው የዲፕሎማሲ ስራዎችና ሌሎች ጉዳዮች በውል ታይተዋል ወይ የሚል ጥያቄ ማንሳትም ተገቢ ነው፡፡ ምክንያቱም ግድቡ ላይ ከእያንዳንዱ ኪስ የተወሰደ ገንዘብ አለና ነው፡፡

ስለዚህ ገዢው ፓርቲ ሁሉን ነገር ለፖለቲካ ፍጆታ በማዋል ሥልጣንን ማስረዘም በሚል መርህ ተቀይዶ የዘነጋቸው ብዙ ሀገራዊ ተግባራት እንደነበሩና እንዳሉ ለመገመት ይቻላል፡፡ ከነዚህም ዋነኛው በቂ የዲፕሎማሲ ስራ  አለመስራት፤ ከዓባይ ተጋሪ ሀገሮች ጋር በቂና አስተማማኝ ውይይት አድርጎ ስምምነት አለመድረስ፤ በዚህ ረገድ ሀገሪቱ የጦርነት ስጋር ቢገጥማት ለመቋቋም በቂ ዝግጅት አለማድረግ፤ የገንዘብ ቁጥጥርና ሙስና የመሳሳሉት ይጠቀሳሉ፡፡

ሌላው አብይ ጉዳይ ሁሉም ነገር እኔ አውቀዋለሁ በሚል ትእቢት ኢህአዴግ ብሔራዊ መግባባት (National Consensus) እንዲፈጠር ምንም አይነት እንቅስቃሴ ለማድረግ አለመፈለጉ ነው፡፡ ይልቁንም ገዢው አካል ብሔራዊ መግባባት እንዳይፈጠር በመስራት የሚታወቅት ነው፡፡ ሀገራዊ ጉዳይ ያነሱ ፖለቲካኞችንና ጋዜጠኞችንና ባዘጋጀው የማጥቂያ ህግ ‹‹ሽብርተኛ›› በማለት የሚፈርጅ፣ ለመነጋገርና ለመግባባት ዝግጁነት የሌለው፣ በልማት ስም ጭቆና የሚያካሂድ፣ ይቀናቀነኛል የሚላቸውን ኃይሎች ሁሉ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለባቸው ብሎ የሚያስብ አምባገነን ሥርዓት ነው፡፡ በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ብሔራዊ መግባባትን የሚፈታተን በማጥቃት ላይ ብቻ የተመሰረተ አገዛዝ ነው፡፡ ስለዚህ አጣብቂኝ ውስጥ በወደቀበት ጊዜ እንኳን ሀገራዊ አጀንዳ ካላቸው ተቃዋሚዎች ጋር የመመካከር ሃሳብ የለውም፡፡ ይሄም የሆነው ከሀገር ይልቅ ስልጣንንና ለስልጣን ብቻ ከማሰብ የሚመነጭ በመሆኑ ነው፡፡ ታዲያ የታቀደው ትልቅ ፕሮጀክት ያለ ሀገራዊ መግባባት እንዴት ሊሳካ ይችላል?

ከተመረጡ አንድ ዓመት የሚሆናቸው የግብፁ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ ያቀረቡት ሃሳብ ቅቡልም ሆነ የማይረባ ከተቃዋሚዎች ጋር ተነጋግረዋል፤ የሱዳን መንግሥት የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት የተሻለ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር እየጣረ ይገኛል፡፡ በአንፃሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን በግትርነት ማሰርና መፈረጁን በመቀጠል የሀገራዊ መግባባት አደጋ እየሆነ ይገኛል፡፡ በሀገራችን ያሉ ችግሮችን ተነጋግሮ ለመፍታት ፈቃደኛም፣ ቁርጠኛም አይደለም ስለዚህ ራሱ መንግሥት ተጠያቂ የሚሆንበት ጉዳይ ብዙ ነው፡፡

በመዚህም መሠረት የአንድነት አቋም የሚከተለው ነው፡-

1.  የግብጽና የኢትዮጵያ መንግሥት ከፀብ አጫሪ ድርጊት በመቆጠብ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ከሚያበላሹ ፕሮፓጋንዳዎችን ከመንዛት እንዲታቀቡና ለዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጠረጴዛ ዙሪያ ንግግሮች ላይ እንዲያተኩሩ እናሳስባለን፤

2.  አባይን መጠቀም የኢትዮጵያ ተፈጥሮዊ መብት መሆኑ እንዲታወቅ፣

3.  ሁለቱ ሀገሮች የአባይን ጉዳይ የውስጥ ፖለቲካቸው ማብረጃ ከማድረግ እንዲቆጠቡ፣

4.  ሀገራዊ መግባባት አሁኑኑ እንዲፈጠር መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ፣

5.  የአባይ ጉዳይ የፖለቲካ  መጠቀሚያ መሆኑ እንዲያበቃ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ሰኔ 6 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም

አዲስ አበባ


ሰማያዊ ፓርቲ በግብጽ ጉዳይ መግለጫ ሰጠ

$
0
0

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
June 14, 2013

semayawi partyግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ወረራና ደባ መፈፀም የጀመረችው ኢትዮጵያ ዛሬ በአባይ ላይ ግድብ ለመስራት ከመነሳቷ እጅግ በርካታ አመታት በፊት ጀምሮ ነው፡፡ ሀገራችን ከግብፅም ሆነ ከሌሎች የተቃጣባትን ተደጋጋሚ ወረራዎች በመመከትና ጠላቶቿንም ድባቅ በመምታት ነፃነቷን ጠብቃ መኖሯ ለጠላቶቿ መራር የሆነ እውነት ነው፡፡ በተለይም ከጥንት ጀምሮ የአባይን ምንጭ ለመቆጣጠር ጥልቅ ምኞት የነበራት ግብፅ በሃገራችን ላይ የፈፀመችውን ግልፅና ድብቅ ወረራ በመመከት ተደጋጋሚ ሽንፈትን አከናንበን መልሰናታል፡፡

ሀገራችንን በጦር አውድማዎች ማሸነፍ እንደማትችል በቂ ትምህርት የወሰደችው ግብፅ ከቅርብና ሩቅ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር ዛሬ በኤርትራና በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ የተቀመጡ አማፅያንን በማስታጠቅና ሁለንተናዊ ድጋፍ በመስጠት ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠልና ኢትዮጵያም እንድትዳከም ከፍተኛ ደባ ፈፅማለች ፡፡ ግብፅ ይህን ሁሉ ግልፅ እና ስውር ደባ የምትፈፅመው ኢትዮጵያ በወንዞቿ መጠቀም የማትችል ደካማ ሐገር እንድትሆን ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ጥረቷ ግን ደካማ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ከመሞከሯ ውጭ የምኞቷን ያህል አልተሳካላትም፡፡ ቢሆንም እኛን ኢትዮጵውያንን እርስ በእርሳችን በማናከስ በጦርነትና በክፍፍል ተጠምደን ወንዞቻችንን የመጠቀም አቅም በማሳጣት ለዘለዓለም ብቸኛ ተጠቃሚ ሆና መኖር ትፈልጋለች፡፡ ይህ ካልተሳካላት ቀጥተኛ ወረራ በመፈፀም የወንዞቻችን ምንጮች ለመቆጣጠር እንደምትመኝ የየዘመናት ሙከራዎቿ ያረጋግጣሉ፡፡

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የጀመረችውን ግድብ አስመልክቶ ሰሞኑን ከግብፅ በኩል የሚሰማው ዛቻና ማስፈራሪያም ከላይ የተገለፁት እውነታዎች ነፀብራቅ ነው፡፡ በመሠረቱ በአባይ ወንዝ ላይ የተጀመረው ግድብ ከሐገራዊ ጠቀሜታው ይልቅ የገዥውን ፓርቲ የስልጣን እድሜ ለማራዘም የታለመና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚደለቅ ከበሮ መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ የግድቡ ሥራ የገዥውን ፓርቲ የተለየ አሣቢነትና ተቆርቋሪነት የሚያሳይ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው ልፈፋ ከተራ ጩኸት በዘለለ የዜጎችን ልብ የሚያማልል አይደለም፡፡ በአንፃሩ ከገዥው ፓርቲ አመለካከት ውጭ ያሉ ዜጎችን የግድቡ ሥራ የማይመለከታቸው አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው የወሬ ክምር ልብን የሚሰብር ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ በመሆኑም ለኢትዮጵያ ክብርና ኩራት መሠዋት ለዜጎችም ጥቅም መጠበቅ እነማን ምን እንደከፈሉና እንደሚያስቡ ለታሪክ በመተው ሃገርን መክዳትና መጥላትን በሌሎች ላይ ለመለጠፍ የሚደረገው ሩጫ ግን እንዲታሰብበት እንመክራለን፡፡

የግድቡ ሥራ ከስም አወጣጥ ጀምሮ የፕሮጀክቱ አነዳደፍ፤ የፋይናንስ አሰባሰብ፣ ግንባታውን የሚያካሂዱ ድርጅቶች አመራረጥና ሌሎችም ጉዳዮች እጅግ ግልፅነት የጎደላቸውና ባለቤትነታቸውም ከኢትዮጵያ ህዝብ ተነጥቆ ለተወሰኑ ቡድኖች በተለይም ለገዥው ፓርቲ ፍላጎት ማሳኪያ እየዋለ መሆኑ ቀርቶ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በሚያስማማ ሁኔታ እንዲካሄድ ፓርቲያችን አጥብቆ ይጠይቃል፡፡

ሐገራችን ለሚያስፈልጋት ዓላማ ሁሉ በወንዞቿ መጠቀሟን በመቃወም በግብፅም ሆነ በሌላ በማንኛውም አካል የሚፈፀሙ ዛቻም ሆነ ሌሎች አሉታዊ ድርጊቶችን ፓርቲያችን አጥብቆ ያወግዛል፡፡ የሃገራችንን ጥቅም ለማስጠበቅም ማንኛውንም መሰዋዕትነት መክፈልን ከጀግኖች አባቶቻችን የወረስነው አኩሪ ታሪካችን በመሆኑ ይህን ቃል ኪዳን ማክበርና መጠበቅ የፓርቲያችን የፀና አቋም ነው፡፡

በመጨረሻም አሁን የተፈጠረው ውጥረት በውይይት እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲያደርግ እያሳሰብን ነገር ግን ግብፅ ይህን አልቀበልም በማለት ፍላጎቷን በሃይል ለማስፈፀም የምትፈልግ ከሆነ የአባቶቻችንን ታሪካዊ አሸናፊነት የምንደግመው መሆኑን ከታሪክ እንድትማር ለማስታወስ እንገደዳለን፡፡

ሰኔ 7 ቀን 2005 ዓ.ም

ከፍተኛ የደህንነት ሹም ከስልጣን ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0
tplf-rotten-apple-245x300የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ አቶ ወልደስላሴ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ወ/ስላሴ ከስልጣን እንዲነሱ ያደረጉት የደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል። የሁለቱ ሹማምንት ፀብ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ ቆይቶ መጨረሻ መፈንዳቱ ታውቋል። በመቀሌ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ አቶ ጌታቸው የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል ሆነው እንዳይመረጡ ሰፊ ቅስቀሳ ሲካሂድ የቆየው ወ/ስላሴ በመጨረሻም የአባላት ምርጫ ሲካሄድ ባቀረበው ተቃውሞ ላይ « ..ጌታቸው የተሰጠውን የፓርቲና መንግስታዊ ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ አይደለም፤ የአልሙዲ ተላላኪና አሽከር ሆኗል…የአላሙዲ አገልጋይ ሆኖዋል…ስለዚህም በማ/ኮሚቴ አባልነት መካተት የለበትም..» ሲል መናገሩን ያወሱት ምንጮቹ፣ የወ/ስላሴ ተቃውሞ ተቀባይነት ባለማግኘቱ አቶ ጌታቸው በማ/ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ መደረጉን አያይዘው ገልፀዋል። ..
አቶ ጌታቸው በቅርቡ በወሰዱት የአፀፋ እርምጃ ወ/ስላሴ ከአገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊነታቸው እንዲነሱ በማድረግ እንደተበቀሏቸው ማወቅ ተችሏል። በጎንደር ተወልደው ያደጉትና በሰባዎቹ መጀመሪያ አመታት ሕወሐትን የተቀላቀሉት አቶ ጌታቸው በአብዛኛው አመራር « ጥሩ ሰው ነው፣ ላመነበት ነገር ወደኋላ የማያፈገፍግ..» ተብሎ እንደሚነገርላቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል። በሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን ተተክተው በ1994ዓ.ም ወደስልጣን የመጡት ጌታቸው በተጨባጭ ሙስና ፈፅመዋል የሚል መረጃ እንደሌለ ያመለከቱት ምንጮቹ ነገር ግን በአብዛኛው ባለስልጣናት የሚፈፀመው መጠነ ሰፊ ዘረፋና ሙስና በተመለከተ በርካታ መረጃና ማስረጃ በጌታቸው እጅ እንደሚገኝ አያይዘው ገለፀዋል። በሌላም በኩል በ1994ዓ.ም በደህንነት ቢሮ የበታች ሹማምንት ሆነው በአቶ መለስ ከተመደቡት መካከል ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስና ወ/ስላሴ እንደሚገኙበት ያስታወሱት ምንጮቹ፣ አክለውም ሁለቱ የሕወሐት አባላት ከስር ሆነው ፈላጭ ቆራጭ አመራር ይሰጡ እንደነበረና በዚህ ተግባራቸው ከጌታቸው ጋር የከረረ ውዝግብ ውስጥ ገብተው መቆየታቸውን አስታውቀዋል። ኢሳያስ ከአቶ መለስና ስብሃት ጋር ስጋ ዝምድና እንዳለው ማወቅ ተችሏል። በተለይም በዚህ ጣልቃ ገብ አሰራር ተማረው የቆዩት አቶ ጌታቸው ከቅርብ አመት ወዲህ ከአቶ መለስ ጋር ጭምር አለመግባባት ፈጥረው እንደነበረ ሲታወቅ፣ አቶ መለስ የጤና ችግር ተፈጥሮቦቻው እንጂ በዛው ወቅት ከስልጣን ሊያነሷቸው ከወሰኑት ባለስልጣናት አንዱ ጌታቸው እንደነበሩና ከመለስ ህልፈት በኋላ የደህንነቱ ሹም የታቀደባቸውን እንደደረሱበት ምንጮቹ አስታውቀዋል። የጠ/ሚ/ሩን ህልፈት ተከትሎም አቶ ጌታቸው ስልጣናቸውን በማደላደል ጎልተው መውጣቸውንና በወ/ስላሴ ላይ የወሰዱት እርምጃ ማስረጃ እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ የአቶ ጌታቸው ወንድም ዳንኤል አሰፋ የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባል ተደርጎ ባለፈው ጉባኤ መመረጡ ሲታወቅ፣ የዳንኤል ባለቤት የስብሃት ነጋ ዘመድ እንደሆነች ተጠቁሞዋል።
ከስልጣን የተነሳው ወ/ስላሌ ከበረሃ ጀምሮ በርካታ የድርጅቱን ታጋዮች በመረሸን እንደሚታወቅ ያስታወሱት የቅርብ ምንጮቹ « ፆታዊ ግንኙነት ስታደርጉ ተገኝታችኋል…» በሚሉና ሌሎች ተልካሻ ምክንያቶች እንዲረሸኑ በበላይ አመራር ውሳኔ የተላለፈባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የፓርቲው አባላት (ታጋዮች) ለመግደል ይጣደፉ ከነበሩት መካከል ኢሳያስና ወ/ስላሴ ዋናዎቹ ነበሩ ሲሉ ያስረዳሉ። አቶ መለስ ሁለቱን አባላት ወሳኝ በሆነው የደህንነት ቢሮ ቁልፍ ስልጣን የሰጧቸው « አድርጉ » የተባሉትን ያለማመንታት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው ብለዋል። ወ/ስላሴ ስልጣን በጨበጠ ማግስት በአንድ ቀን አርባ የቢሮው አባላትን ( መኮንኖች ተብለው ነው የሚጠሩት) እንዳባረረ የገለፁት ምንጮቹ፣ በየጊዜው በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላትን « ተሃድሶውን አልተቀበላችሁም፣ የቅንጅት ደጋፊዎች ናችሁ..» በሚሉና ሌሎች ምክንያቶች ከማባረር – እስር ቤት እስከመወርወር የደረሰ እርምጃ ሲወስድ መቆየቱን አስታውሰዋል። ከመለስ ጋር በሃሳብ ያለተስማሙ ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናትን በገዛ መኖሪያ ቤታቸው በገመድ በማነቅና በስለት በማረድ የጭካኔ ተግባር ያስፈፀሙት ወ/ስላሴና ኢሳያስ መሆናቸውን ምንጮቹ አጋልጠዋል። በግፍ የተገደሉት የመገናኛ ሚ/ሩ አቶ አየነውና የቤተመንግስት የደህንነት ሹም አቶ ዘርኡ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አዜብ መስፍን በቅርቡ ቨርጂኒያ መጥተው እንደነበረ ምንጮች ገለፁ። ድምፃቸውን አጥፍተው የመጡት አዜብ በተጠቀሰው ከተማ እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ የገዙት መኖሪያ ቪላ ውስጥ ለጥቂት ቀናት እንደቆዩና ወደአገር ቤት እንደተመለሱ ምንጮቹ አስታውቀዋል። ከቪላው ጋር በተያያዘ ተጨማሪ መረጃዎች እየተጠናከሩ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።

የታማኝ በየነ ሾው – በኢሳት

Sport: በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 10ሩ አክሳሪ ተጫዋቾች

$
0
0

FBL-EUR-C3-TOTTENHAM-PANATHINAIKOS
ከይርጋ አበበ
እለታዊው የእንግሊዙ ዘሰን ጋዜጣ በስፖርት አምዱ ላይ ባለፉት አሥር ዓመታት ቀጣሪዎቻቸውን ለከባድ ኪሳራ ያጋለጡ አሥር ከዋክብት ብሎ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተጫዋቾች አቅርቧቸዋል። ተጫዋቾቹ ክለቦቹን ሊያከስሩ የቻሉት ከተገዙ በኋላ ጥሩ መጫወት ባለመቻላቸው እንደገና ለገበያ ሲቀርቡ የተሸጡበት ዋጋ መጀመሪያ ከተገዙበት በእጅጉ ያነሰ በመሆኑ ነው ሲል ዘገባው ይገልጻል። ከአስሩ አክሳሪ ተጫዋቾች በተጨማሪ በቅርቡ የቼልሲው ስፔናዊ ኮከብ ፈርናንዶ ቶሬዝ ወደ ባርሴሎና ዝውውር ካደረገ የመጀመሪያውን ቦታ የሚይዝ ይሆናል። ለጊዜው ግን ዘሰን አክሳሪ ብሎ የሰየማቸውን ለአንባቢያን በሚመች መልኩ ከዚህ በታች አቅርበናቸዋል።
10. ሽዋን ራይት ፍሊፕስ
እንግሊዛዊው ፈጣን የመስመር ተጫዋች የሮማን አብራሞቪችን ካዝና ሃያ አንድ ሚሊዮን ፓውንድ ካስወጣ በኋላ ለሦስት ዓመታት በስታንፎርድ ብሪጅ የመጫወት እድል ቢያገኝም የተጠበቀውን ያህል ለክለቡ መጥቀም ባለመቻሉ በጆዜ ሞሪንሆ የመውጫ በር ተከፍቶለት ወደ ቀድሞ ክለቡ ማንቸስተር ሲቲ በስምንት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ፓውንድ ተዘዋውሯል።
9. አልቤርቶ አኩይላኒ
ዣቪ አሎንሶን ለሪያል ማድሪድ አሳልፈው የሰጡት ራፋኤል ቤኔቴዝ ቦታውን ለመድፈን ዓይናቸው ያረፈበት የሮማው መልከ መልካም ወጣት አልቤርቶ አኩይላኒ ነበር። ለእዚህ ጥበበኛ ጣሊያናዊ ሃያ ሚሊዮን ፓውንድ ከፍለው የኮፕሶቹ ቢያደርጉትም ከእንግሊዝ ጋር መላመድ አለመቻሉ ለድጋሚ ሽያጭ እንዲቀርብ ሆነ። በጁቬንቱስ ለአንድ ዓመት በውሰት ከቆየ በኋላ ወደ ፍዮሬነቲና በሰባት ሚሊዮን ፓውንድ በቋሚነት ፈርሟል።
8. ሮቢንሆ
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ባለሀብቶች ማንቸስተር ሲቲን እንደተረከቡ በ32ሚሊዮን ፓውንድ ከሪያል ማድሪድ በ2008 አስፈረሙት። ወጣቱ ላቲን አሜሪካዊ ለሰማያዊ ለባሾቹ ብዙ አገልግሎት መስጠት ባለመቻሉ ወደ ሳንቶስ ለውሰት በመሄድ ለአንድ ዓመት ተጫወተ። የውሰት ውሉ ተጠናቅቆ ወደ እንግሊዝ ቢመለስም የታሰበውን ያህል መጥቀም ባለመቻሉ አስራ አራት ሚሊዮን ፓውንድ ከስረው በ18ሚሊዮን ፓውንድ ለኤሲ ሚላን ለመሸጥ ተገደዋል
7. ሔርናን ክሬስፖ
አርጄንቲናዊው ጸጉረ ሉጫ አጥቂ በ2003 የክረምት የተጫዋቾች ዝውውር ሲከፈት አስራ ስድስት ሚሊዮን ፓውንድ ተከፍሎበት በክላውዲዮ ራኒየሪ ዘመን ለቼልሲ ፈረመ። ራኒየሪ ተነስተው ጆዜ ሞሪንሆ ክለቡን ማሰልጠን ሲጀምሩ ላንተ የሚሆን ቦታ የለኝም ብለው ወደ ኤሲ ሚላን በውሰት ሸኙት። ሁለት ዓመታትን በሳንሲሮ ከቆየ በኋላ በነጻ የዝውውር ሂሳብ ለሌላው የሚላን ክለብ ኢንተር ሚላን በነፃ ፈረመ።
6. ማይክል ኦውን
የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ እፈልጋለሁ ብሎ ከሊቨርፑል ወደ ሪያል ማድሪድ ላቀናው አጭሩ እንግሊዛዊ አጥቂ በስፔኑ ክለብ የሮናልዶና ራኡል ጎንዛሌዝን ክፍያ የከፈለው ኒውካስትል ዩናይትድ ነበር። ነገር ግን ተደጋጋሚ ጉዳቶች ከሜዳ ያራቁት ኦውን ከአራት ዓመታት ቆይታ በኋላ ሴንት ጀምስ ፓርክን በነጻ ተሰናብቶ ኦልድ ትራፎርድ ደረሰ።
5. ኦውን ሃርግሬቭስ
ትውልደ ካናዳዊ የሆነው እንግሊዛዊው የቀድሞ የባየር ሙኒክ አማካይ በ17 ሚሊዮን ፓውንድ ክፍያ ኦልድትራፎርድ የደረሰው በ2006 የውድድር ዘመን ነበር። ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ክፍተቴን በደንብ ይሸፍንልኛል ያሉት ይህ አማካይ ተከላካይ ለጉዳት ቅርብ መሆኑ ብዙውን ጊዜውን በማገገሚያ ክፍል ማሳለፉ ነበር ለከተማ ተቀናቃኛቸው በነፃ ዝውውር አሳልፈው እንዲሰጡት ያስገደዳቸው። የግሌዘር ቤተሰቦችም በልጁ አስራ ሰባት ሚሊዮን ፓውንድ ከስረዋል።
4. ጆ
የስሙ ሆሄያት አጭር የሆነው መለሎው ብራዚላዊ ሲኤስ ሲ ሞስኮን ለቆ ለማንቸስተር ሲቲ የፈረመው በ2008 የውድድር ዘመን በ18 ሚሊዮን ፓውንድ ክፍያ ነበር። ነገር ግን እንደተጠበቀው ክለቡን ማገልገል ባለመቻሉ ለሃገሩ ክለብ ኢንተር ናሲዮናል በነፃ ዝውውር ሊፈርም ችሏል። አስራ ስምንት ሚሊዮን ፓውንድ ያከሰረው ብራዚላዊ አራተኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጥ ተገዷል።
3. ኢማኑኤል አዲባዮር
ዌለሳዊው የቀድሞ የማንቸስተር ሲቲ አሰልጣኝ ማርክ ሂውዝ በአርሴናል የተገፋውን አፍሪካዊ ግዙፍ አጥቂ በሃያ አምስት ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ወደ ክለባቸው ያዘዋወሩት በ2009 ነበር። ግዙፉ አጥቂ በኢቲሃድ ጅማሮው ጥሩ ቢሆንም ማርክ ሂውዝን ተክተው ክለቡን የተረከቡት ሮቤርቶ «ማንቺኒ አልፈልግም »ስላሉት በተለያዩ ክለቦች በውሰት ሲንከራተት ቆይቶ በመጨረሻም ለሰሜን ለንደኑ ቶተንሃም በአምስት ሚሊዮን ፓውንድ ክፍያ በቋሚነት ፈረመ። ሃያ ሚሊዮን ፓውንድ በማክሰሩ የሶስተኛነት ደረጃን በብቸኝነት ተቆናጠጠ።
2. ዲሚታር ቤርባቶቭ
ቡልጋሪያዊው አጥቂ ካረሎሰ ቴቬዝ ትቶት የሄደውን የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ክፍል ሊደፍን 31 ሚሊዮን ፓውንድ ተከፍሎበት ኦልድትራፎርድ ደረሰ። ለኦልድትራፎርዱ ክለብ በአራት ዓመት ቆይታው ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ጨምሮ የተለያዩ ክብሮችን ቢጎናጸፍም የሮቢን ቫንፔርሲን ለማንቸስተር መፈረም ተከትሎ ከክለቡ እንዲለቅ ሲደረግ በቶተንሃም ቆይታው የሚያወቁት ሆላንዳዊ አሰልጣኝ ማርቲን ዮል በአምስት ሚሊዮን ፓውንድ ለፉልሃም አስፈረሙት። ሃያ ስድስት ሚሊዮን ፓውንድ ክለቡን ለኪሳራ ዳረገ ብሎ ዘሰን ጋዜጣ ሁለተኛው አክሳሪ ሲል ሰይሞታል።
1. አንድሪ ሸቪቼንኮ
ዩክሬናዊው አጥቂ በኤሲ ሚላን ቆይታው የባሎን ዶር ሽልማትንና ተደጋጋሚ የሴሪአው ኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ክብርን ተጎናጽፎ ነበር። ሩሲያዊው የቼልሲ ባለቤት የጎረቤት ሀገራቸውን ልጅ ወደ ክለባቸው እንዲመጣላቸው የሳንሲሮ አቻዎቻቸውን በተደጋጋሚ ደጅ መጥናታቸው በ30 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ፓውንድ ይሸጡላቸዋል ። ነገር ግን በክለቡ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ስላልተፈለገ የተጠባባቂ ወንበር አሟቂ ሆነ። «የመጫወት እንጂ ወንበር ላይ የመቀመጥ ልክፍት የለብኝም » እያለ ምሬቱን ደጋግሞ ሲገልጽ የቆየው አጥቂ ፣ለቀድሞ ክለቡ ኤሲ ሚላን በውሰት ሲጫወት ቆይቶ በመጨረሻም የሮማን አብራሞቪችን 30 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ፓውንድ እንደ ጉም ብን አድርጎ ወደ አሳዳጊ ክለቡ ዳይናሞ ኬቭ በነጻ ዝውውር ሄደ ። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአስር መቱ ቁጥር አንድ አክሳሪ ተጫዋች ለመባልም ተዳረገ ።

ቡድናችንና ግብፃዊ ዳኛ …… (አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)

$
0
0

ethiopia football

ዛሬ እሁድ ማታ ለሚካሄደው የዋልያዎችና የባፋናዎች የእግርኳስ ግጥምያ መቐለዎች ለድጋፉ ካሁኑ ሽርጉድ ጀምረዋል። የሀገራችን ባንዲራ የያዙ ወጣቶች በብዛት ይታያሉ። የተወሰኑ ወጣቶች እንደነገሩኝ የዛሬ ጨዋታ አስጨናቂ ነው። ምክንያቱም

(1) ለዓለም ዋንጫ የምናልፍበት ወሳኝ ጨዋታ ነው። (2) የመሃል ዳኛው ግብፃዊ ነው (በግብፅና ኢትዮዽያ መካከል ያለው የፖለቲካ ውዝግብ የዳኛው ውሳኔ …. ከሚል ስጋት ነው)።

የኔ ስጋት ግን ‘ዋልያዎቹና ባፋናዎች ይመጣጠናሉ ወይ?’ የሚል ነው። የስፖርት ትንተናው ለባለሙያዎቹ ልተወውና ስለ ግብፃዊ ዳኛና የተገመተው የፖለቲካ ተፅዕኖ ትንሽ ልበል።

ግብፃዊው የመሃል ዳኛ (የፖለቲካ ሁኔታችን እየታወቀ ለምን ግብፃዊ ዳኛ እንደተመረጠ አልገባኝም) ያሰብነው ችግር ይፈጥራል ብዬ አላምንም። ምክንያቱም

(1) የስፖርትና የፖለቲካ የጨዋታ ሕጎች የተለያዩ ናቸው። የእግርኳስ ጨዋታ የራሱ የሆነ ደምብ አለው። ደምቡ ሳይንሳዊ ነው፤ አብዛኛው የእግርኳስ አፍቃሪ ሕጉ ያውቀዋል። ጨዋታው ህዝብ ያየዋል፤ አይቶም የየራሱ ፍርድ ይሰጣል። ዳኛው ጨውታውን ይዳኛል፤ ህዝቡ ደግሞ ዳኛውን ይዳኛል። በስፖርት ሕግና ዳኝነት (ከፖለቲካ ጋር ሲነፃፀር) የተሻለ ግልፅነት አለ። በፖለቲካ እውነታውን መጠምዘዝና በውሸት ‘ትክክል’ መሆኑ ለህዝብ መሸወድ ይቻላል። ይህን የሚደረገው ግልፅነት በማጥፋትና መረጃ በማሳሳት ነው። ግልፅነትና መረጃ ማሳሳት የሚቻለው ነፃ የግል ሚድያ በማፈን ነው።

ፖለቲካ ስለስነግባር አይደለም። የስፖርት ዳኝነት ግን ከስነምግባር ጋር የተያያዘ ነው። ስለዚህ ዳኛው ውሳኔ ያበላሻል ብዬ አላስብም። ደግሞ አበላሽቶ ምን ይጠቀማል? ጉዳት ብቻ ነው ያለው። ካበላሸ በስነምግባር ጉድለት ከዳኝነት ሙያው ሊታገድ ይችላል።

(2) እንበልና ዳኛው የፖለቲካ ዓላማ ይዞ ወደ ሜዳው ገብቷል። በጦርነት ወይ ግጭት ለማሸነፍ ፕሮፓጋንዳ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ከፕሮፓጋንዳዎች አንዱ የሌላውን ህዝብ ቀልብ መሳብ (public diplomacy) ነው። ስለዚህ ግብፅዊው ዳኛ ለሀገሩ ማበርከት የሚፈልገው ፖለቲካዊ ሚና ካለው ለኢትዮዽያ ብሄራዊ ቡድን በተቻለ መጠን ማገዝና (ወይም ፍትሓዊ ዳኝነት በመስጠት) ኢትዮዽያውያንን ማስደሰት ነው። ኢትዮዽያውያን ስለ ግብፃውያን ‘ጥሩ’ አመለካከት እንዲኖራቸው ጥረት ካደረገ ለሀገሩ ጥሩ ነገር ሰራ ማለት ነው።

(3) ሆን ብሎ የኢትዮዽያ ብሄራዊ ቡድን ለመበደል ካሰበና ካደረገ ግን እንደ የፖለቲካ መሪዎቹ ፖለቲካ አያውቅም ማለት ነው። የኢትዮዽያ መንግስት (ከዳኛው ስሕተት) ፖለቲካዊ ጥቅም ያገኛል ማለት ነው። ባጭሩ ግን ዳኛው ፍትሓዊ ዳኝነት ከመስጠት እንጂ ከማበላሸት ምንም አይጠቀምም። ስለዚህ ‘ትክክለኛ ዳኝነት’ ይሰጣል ብዬ አስባለሁኝ።

በመጨረሻም

አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ተጫዋቾቹን በትእግስት፣ ስነምግባር በተሞላበት ጥሩ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ እንጂ አንዳንዴ ከሚፈፅሙት ጥፋት (በዳኛም በሌሎች ተጫዋቾችም) እንዲጠነቀቁ መምከር አለበት። የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌደሬሽንም የቡድኑ ደጋፊዎች (አንዳንድ ችግሮች ቢፈጠሩ) በዳኛውና በሌሎች ተጫዋቾች ችግር እንዳይፈጥሩ (ሊጣልብን ከሚችል ቅጣት አንፃር) ጠንከር ያለ መልእክት ማስተላለፍ ይገባዋል።

ድል ለብሄራዊ ቡድናችን!!!

It is so!!!

ዜና ፍትሕ ከትግራይ ክልል፡ የ12 ሰዎች አስከሬን በአንድ ቤተክርስትያን በጅምላ ተቀበረ… እና ሌሎችም

$
0
0

Abrham Destaአብርሃ ደስታ ከመቀሌ

አንድ

በአፅቢ ወረዳ (ጣብያ ሩባ ፈለግ፣ ቁሸት ደብረሰላም) የሚኖሩ አርሶ ኣደሮች በግጦሽ መሬት ይገባኛል ምክንያት ከመንግስት ጋር ተጣሉ። መንግስት በፓኬጅ ፕሮግራም (‘ፓኬጃዊ ምትእትታው’) መሰረት በ’ፍትሓዊ ልቃሕ’ (‘ፍትሓዊ ብድር’ መሆኑ ነው) አማካኝነት ገበሬዎቹ ብድር ወስደው ከብቶች ይገዛሉ። በተመሳሳይ ግዜ በአከባቢው የሚገኝ የሳር (ግጦሽ) መሬት እንዲከበርና ገበሬዎቹ እንዳይጠቀሙት ይወሰናል።

አርሶ አደሮቹ ከብቶች ገዝተው አርብተው ዕዳቸው (የወሰዱት ብድር) ለመመለስ ሲፈልጉ ከብቶቻቸው የሚበላ አስፈለጋቸው። የሳር መሬቱ መጠቀም ፈለጉ። መንግስት አልፈቀደላቸውም፤ ከለከላቸው። ህዝቡ ዓመፀ (ወይ ዕዳው ይሰረዝ ወይ ከብቶቹ የሚበላ ይኑራቸው ብለው)። መፍትሔ አላገኙም። የተወሰኑ አርሶ አደሮች የራሳቸው የነበረ (በኋላ የተከበረ) ሳር መጠቀም ጀመሩ። የወረዳው ምልሻዎች ሰዎቹን ማስፈራራት ጀመሩ። ሁሉም የአከባቢው ገበሬዎች የየራሳቸው ግጦሽ መጠቀም ጀመሩ። የወረዳው ፖሊሶች መተው (አቶ ወልደገብርኤል ሃይሉና አምሳ አለቃ አታክልቲ የተባሉ ሁለት ሰዎች) ለማሰር ሲሞክሩ ህዝቡ ተሰብስቦ ‘ከፈለጋቹ ሁላችን እሰሩን’ ብለው ይጮሃሉ። ፖሊሶቹ በዱላ መደብደብ ጀመሩ። ህዝቡም ድንጋይ እየወረወረ ከፖሊሶቹ ይጋጫል። ተኩስ ተከፈተ፤ በድንጋይ የቆሰሉ ብዙ ሰዎች አሉ።

ያልተመጣጠነ ሃይል በመጠቀም ሰባት አርሶ አደሮች (ከነከብቶቻቸው) ታስረዋል። ከብቶቹ እንዴት እንደታሰሩ ግልፅ አይደለም። ዛሬ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች እንዲታሰሩ ስም ዝርዝራቸው ይፋ ሆነዋል። በአከባቢው ውጥረት ነግሷል። ከነከብቶቻቸው የታሰሩ ሰባት ሰዎች የድሮ የህወሓት ታጋዮችና እስከ ቅርብ ግዜም የሕወሓት አባላት የነበሩ ናቸው። በደርግ ዘመን ‘ከህወሓት ታጋዮች ግንኙነት አላቸው’ ተብለው ከነከብቶቻቸው ታስረው እንደነበርና በዛ ምክንያት ወደ ትግሉ እንደተቀላቀሉ ለማወቅ ችያለሁ። የአከባቢው ኗሪዎች አሁንም ከነከብቶቻቸው መታሰራቸው ግርምት ፈጥሮባቸዋል። ግጭቱ የተጀመረው ግንቦት 10 ሲሆን ተኩሱና እስሩ የተፈፀመው ግን ሰኔ 6, 2005 ዓም ነው።

ሁለት

በሰሓርቲ ሳምረ ወረዳ (ጣብያ አዲሳለም፣ ቁሸት ሓንጣባት) የመንግስት ሰዎች የአከባቢው አርሶአደሮች በማስገደድ መዳበርያ እንዲወስዱ በሚያስፈራሩበት ግዜ ሁለት ሰዎች (አቶ ግርማይና መምህር ገብረህይወት የተባሉ ነዋሪዎች) ‘ህዝብ ማስፈራራት ተገቢ አይደለም’ ብለው ስብሰባ ረግጠው በመውጣታቸው እንዲታሰሩ ሲወሰን ህዝቡ (በሙሉ) ‘ሁላችንም እሰሩን’ ብሎ ፖሊስ ጣብያ ድረስ በመሄዱ ሁለቱም ሰዎች ሳይታሰሩ ቀርተዋል። መተባበር እንዲህ ነው። ህዝቡ ካበረ የካድሬዎች መጫወቻ አይሆንም።

ሦስት

በእንደርታ ወረዳ (ጣብያ ማይፀዶ፣ ቁሸት እግሪሓሪባ) በመሬት ጉዳይ በህዝቡና ካድሬዎች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ለሁለት ዓመት ያህል የመንግስት አገልግሎት (የመንግስት አስተዳደር) ተቋርጧል። በዛ አከባቢ የመንግስት አካል የለም። ክሊንኮች አይሰሩም። የአከባቢው አስተዳደር የለም። ለምሳሌ በአከባቢው የሚገኘው ‘ተከስተ ሃይሉ ትምህርትቤት’ በሚል ስም የሚታወቅ ትምህርትቤት ከተዘጋ ዓመት ሁኖታል። ከዛ አከባቢ የሚመጡ ተማሪዎች የትምህርት ዕድል ተነፍገዋል (‘ወላጆቻቹ ለመንግስት አልታዘዙም’ በሚል ሰበብ)። ለመንስግት አለመታዘዝ አገልግሎት ያሳጣል።

አራት

በዚህ ሳምንት በመቀለ ከተማ የአስራ ሁለት ሰዎች አስካሬን በአንድ ቤተክርስትያን በጅምላ እንዲቀበሩ የተሞከረ ሲሆን የቤተክርስትያኑ ሓላፊዎች ከመቀበራቸው በፊት የአስካሬኖቹ ማንነት እንዲታወቅ ጠይቀው የመንግስት አካላት መልስ መስጠት ስላልፈለጉ ቤተክርስትያኒቱ እንደማትቀበል አሳውቃ ነበር። ትናንት ባገኘሁት መረጃ ግን አስካሬኖቹ በእንዳጋብር ቤተክርስትያን በጅምላ (በምስጢር) መቀበራቸው ነው። ሰዎቹ በፖለቲካ ምክንያት የተረሸኑ ሳይሆኑ አይቀሩም (ተጨማሪ መረጃ ግን ያስፈልጋል)።

ህዝብ ግን ፍትሕ ያስፈልገዋል።

በአ.አ 6 መምህራን በህፃናት ላይ ግብረሰዶም ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው ታሰሩ

$
0
0

Child-abuse-በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ሩዋንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ካራክተር ሆልማርክ አካዳሚ በሚባል ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ፣ በሁለት ወንድ ሕፃናት ላይ ግብረሰዶም ፈጽመዋል የተባሉ ስድስት መምህራን ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ።
ተጠርጣሪዎቹ የአካዳሚው ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ኃይለየሱስ፣ የአካዳሚው ሱፐርቫይዘር አቶ የኔዓለም ጌታቸው፣ መምህር ዓለማየሁ ገብሬ፣ መምህር ደበበ ጥሩነህ፣ አቶ መልካሙ ቀለብና አቶ ሳምሶን መኩሪያ ሲሆኑ፣ አካዳሚው ካራክተር ሆልማርክ አካዳሚ አክሲዮን ማኅበርም መከሰሱን የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ለሰባተኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ ያስረዳል ያለው የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ጨምሮም ተጠርጣሪዎቹ የ10 እና የ11 ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ሁለት ወንድ ሕፃናትን ከጥቅምት ወር መጀመሪያ 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በምሳና በዕረፍት ጊዜ ተማሪዎች ከክፍል ሲወጡ፣ ወደ ባዶ ክፍል በመውሰድ በተደጋጋሚ እየተፈራረቁ የግብረሰዶም ድርጊት እንደፈጸሙባቸው ክሱ ያስረዳል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ዳይሬክተሩንና ሱፐርቫይዘሩን ጨምሮ ሌሎቹም መምህራንም በየካቲት ወር ሁለት ቀናት፣ እንዲሁም በሚያዝያ ወር በሕፃናቱ ላይ ድርጊቱን ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው፣ የሕፃናት ክብር ድፍረት ወንጀል ተካፋይ በመሆን መከሰሳቸውን ክሱ ያብራራል ሲል ዘግቧል።

ካራክተር ሆልማርክ አካዳሚ አክሲዮን ማኅበር በሥሩ ያሉትን ሠራተኞችና ኃላፊዎች በአግባቡ መቆጣጠርና የሕፃናትን ጤንነትና አካልን በአግባቡ መጠበቅ ሲገባው ባለመፈጸሙ፣ በወንጀል ድርጊቱ ተካፋይነት ተጠርጥሮ መከሰሱን ክሱ እንደሚገልጽ ያስታወቀው ጋዜጣው ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን በመግለጽ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ቢጠይቁም፣ ድርጊቱ ከባድ መሆኑን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን ውድቅ በማድረግ፣ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለሰኔ 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ተጠርጣሪዎቹም በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ አዟል ሲል ዘገባውን ቋጭቷል።


ስለዐባይ መገደብ ጉዳይ እኔም የምለው አለኝ ( ተክሌ የሻው)

$
0
0

The Nile River has become a point of contention between Egypt and Ethiopia.

The Nile River has become a point of contention between Egypt and Ethiopia.


ሰሞኑን ኢትዮጵያውያንን አነጋጋሪ ሆኖ ያለው የዐባይ መገደብ ጉዳይ ነው፡፡ አንዳንድ ወገኖች ሁኔታውን ከቀኝ ከግራ፣ከፊት ከኋላ ሳያዩ ከመለስ ዜናዊ ድንክዮች ባላነስ መንገድ መገደቡ ትክክልና ተገቢ እንደሆነ ሲጸፉና ሲናገሩ ይሰማል፡፡ ይህ ሊደንቀን አይገባም፡፡ የነዚህ ዓይነት ሰዎች አቋም አንድም ግድቡ ስለሚኖረው ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊና በህላዊ ጉዳዮች ባይተዋሮች ናቸው፡፡ ሁለትም “እናቴን ያገባ ሁሉም አባቴ” ነው በሚል እሳቤ ወያኔን ኢትዮጵያዊ መንግሥት አድርገው የተቀበሉ ናቸው፡፡ ሦስትም የስደት ኑሮ ከብዷቸው ከወያኔ ጋር መግባቢያ መሰላል እየሠሩ ናቸው፡፡ ይህን ያልተገነዘቡና የወያኔን የቆረጣ የትግል ሥልት ያልተረዱ ወገኖች ለምን በዚህ ወቅትና ሰዓት የዐባይ መገደብ ጉዳይ አጀንዳ ሆኖ ቀረ? ብለው ሳይጠይቁና ዕውነታውን ሳይረዱ፣ ዐባይ መገደቡን መደገፍ አለብን ይላሉ፡፡
በሀሳብና በአመለካከት ደረጃ ዐባይ መገደብ የለበትም የሚል ኢትዮጵያዊ ይኖራል ተብሎ አይገመትም፡፡ ጥያቄ የሚነሳው ዕውን ወያኔ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ለሕዝቡ ሉዐላዊነት፣ብሔራዊ ጥቅምና ብልጽግና የቆመ ነው? ይህን ግንባታ ለመገንባት የተነሳሳው የኢትዮጵያን ሕዝብ በዐባይ ተጠቃሚ ለማድረግ አስቦ ነው? ወይስ ከኋላው ሌላ ምክንያቶች አሉ? የኢትጵዮጵያን የባሕር በር ፈቅዶ የሰጠ፣የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት ድል በአልጀርስ ስምምነት አሳልፎ የሰጠ፣የአገሪቱን ምዕራባዊ ዳርቻ 160 ኪሎሜትር ርዝመት፣50 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ለሱዳን አሳልፎ የተሰጠ፣ከ7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በላይ ለቱርክ፣ለሳውዲ ዐረቢያ፣ለቻይና፣ወዘተ ባለሀብቶች ለሄክታር በአንድ ዶላር ሂሳብ ለ99 ዓመታት የሸጠ፣የአገሪቱን ታሪክና አንድነት የካደ፣የመነጣጠያ ሕገ-መንግሥት ያዘጋጀ፣ባገሪቱ ካሉ ከፍተኛ ቁጥር ካላቸው ነገዶች መካል አንዱ የሆነውን የዐማራ ነገድ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸመ አካል ዐባይን በመገደብ እንዴት ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ያደርጋል ብሎ ማሰብና ማመን ይቻላል ? በአሁኑ ወቅት ወያኔ እየደረሰበት ያለውን የሕዝብ ተቃውሞ አቋም ለማብረድ የአቅጣጫ ማስለወጫ አጀንዳ አለመሆኑን በእርግጠኝነት እናውቃለን ወይ ? ወደ ውሳኔ ከመድረሳችን በፊት ለእነዚህ ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ማግኘት ያለብን ይመስለኛል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ዐባይ ይገደብ አይገደብ ከሚለው መደምደሚያ ከመደረሱ በፊት ለሚከተሉት መሠረታዊ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልሶች ማግኘት ያለብን ይመስለኛል፡፡ እነዚህም፡-
1. ኢትዮጵያ ተብላ ለዘመናት በዓለም ካርታ የምትታወቅ አገር ዛሬ በድሮ ወርድና ቁመቷ አለች?
2. የአንድን አገር ምላተ ሕዝብ ተሳትፎ የሚጠይቅን ተግባር ለማከናወን በቅድሚያ ከዕቅድ ዝግጅ እስከ አፈጻጸም ሕዝቡ መሳተፍ የለበትም ?
3. የሕዝቡን ቁሳዊና ኅሊናዊ ሀብት በሚፈለገው ደረጃ ለማግኘት ሕዝቡ የኔ የሚለው የመንግሥት አደረጃጀትና አመራር አለ ብሎ ያምናል?
4. ዐባይን ለመገደብ የታሰበው በዕውነት ለልማት ታስቦ ነው? ወይስ የሰሜን አፍሪካ ሕዝብ አመጽ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሸጋገር የአመለካከት ለውጥ ለመፍጠር ነው?
5. ዐባይ ይገደብ ከተባለስ መገደብ ያለበት ቦታ የት ቢሆን ነው ለሕዝቡ ዕከል ተጠቃሚ፣ለግድቡ ደህንነት አስተማማኝ የሚሆነው?
6. ዐባይን ያህል ግዙፍ ግድብ ከመገደብ መካከለኛና ዝቅተኛ ግድቦችን መገደብ የበለጠ ውጤታማ መሆን አይቻልም ነበር ወይ?
7. የጣና በለስን ፕሮጀክት ዘርፎና አውድሞ ቤንሻንጉል ጉምዝ ላይ ከሱዳን ደንበር የቅርብ ርቀት ላይ ይህን ያህል ግዙፍ ግድብ ለመገደብ የታሰበው ዕውነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሌሎች አማራጭ ቦታዎቸ ጠፍተው ነው ? ወይስ በግንባታው ሊጎዳ የተፈለገ አካባቢ አለ?
8. ከለጋሽ እና አበዳሪ መንግሥታና ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ያገኘውን ብድርና ዕርታ በሙስና የወያኔ አባሎችን ተጠቃሚ ያደረገ አመራር መሆኑ እየታወቀ ለግድቡ ሥራ ከሕዝብ የሚሰበሰበው ገንዘብለተባለለት ዓላማ ስለመዋሉ ምን ዋስትና አለ?
9. የዐባይ ገባር ወንዞች በአመዛኙ ከጎጃም፣ከጎንደር፣ከሰሜን ሸዋ እና ከወሎ የሚነሱ ናቸው፡፡ ግድቡ እንዲሠራ የተፈለገው ከእነዚህ ክልሎች ብዙ እርቆ ነው፡፡ በግድቡ መሠራት ምክንያት እነዚህ የዐባይ ገባር ወንዞች ባለመብት የሆኑ አካባቢዎች በገባር ወንዞቹ ላይ የመጠቀም መብታቸውን አይከልልም ወይ?
ለእነዚህና መሰል ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ሳንሰጥ፣ ዐባይ ይገደብ ወይም አይገደብ ብለን አቋም መያዝ ተገቢም ትክክልም አይመስለኝም፡፡ ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ሳንሰጥ በስሜት ዐባይ ይገደብ ብንል ሁለት መሠረታዊ ስሕተቶችን እንሠራለን፡፡ አንድ ለወያኔ ዕድሜ ማራዘሚያ እንሆናለን፡፡ ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ድጋፍ ትምህርት መቅሰም ያለብን ይመስለኛል፡፡ በወያኔ አመራር የኢትጵዮያ ብሔራዊ ጥቅምና የሕዝቡ መብት ይጠበቃል ብሎ ማሰብ ሸንበቆ ያፈራል ብሎ መጠበቅ ነው፡፡ ሁለት ወያኔ ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈል እየተጠቀመበት ያለውን ጎዳና እንድንከተል ስለሚያደርግ አገሪቱንና ሕዝቡን እንጎዳለን፡፡

በኢትዮጵያዊያ የመሳፍንት ዘመን አጭር ታሪክ

$
0
0

Menelik_II_ethiopia
ከታክሎ ተሾመ ( አውስትራሊያ)

መምህር ገብረኪዳን ደስታ “ለVOA” ለሰጡት መልስ የግል አስተያየት

ከኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ሳንገባ ለዚህ ጽሁፍ መነሻ እንዲያመች ትንሽ ቀንጨብ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በ1529 – 1543 ዓ.ም ኢማም አህመድ የተባለው የአፋር ተወላጅ በሐረር አካባቢ የሚገኙ ደጋፊዎቹን በማስተባበር በመላው ኢትዮጵያ የእስላም መንግሥት ለመመስረት ከፍተኛ ጦርነት አድርጓል። በጦርነቱ ምክንያት በእሰልሞናዊ ገዥዎችና በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ብዙ እልቂት ደረሰ። በዚህ የተነሳ የያሬድ መንፈሳዊ ኪነት እድገት ሳያሳይ በቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ብቻ ተወስኖ ቀረ።

ነገ ርግን ከኢማም መሃመድ ጥፋት በኋላ የሰለሞናዊ ሥርወ-መንግሥት የቀድሞ ግዛቶቹን አስመለሰ። ቢሆንም በተደረጉ የእርስ በርስ ጦርነቶች የኃይል ክፍተት የተነሳ ከደቡብ እስከ ምስራቅ ድረሰ የኦሮሞዎች ወረራ ተስፋፋ። የኦሮሞ ወራሪዎች ገዳ በሚባል ስርዓት ሉባ በሚባሉ የጦር አበጋዞች አማካኝነት ጋሻና ጦር ይዘው የአዳልን የአካባቢ ነገሥታት እየወጉ፤ ነዋሪውን እያስለቀቁ በራሳቸው ቋንቋና ባሕል ለማዋሃድ ከፍተኛ ጦርነት አካሂደዋል።

እሮሞዎች ያደርጉት ጦርነት ራሳቸውን ችለው መንግሥት አይመስርቱ እንጂ በደቡብ መሀል አገር የሚገኙ እሮሞዎች፤ ገራጌዎች፤ ከምባታዎች፤ ሃዲያዎች፤ ሲዳማና ሌሎችም ብሄር-ብሄረስቦች ተቀላቅለው ግዛታቸውን ለማስፋት ሞክረው ነበር።

በጦርነቶች ምክንያት በአንድ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች እየፈለሱ ከሌሎች ጋር በመቀያየጥ አዲስ የአኗኗል ዘቤዎችን በመለማመድ በአሸናፊዎች ተጽኖ ሥር የመውደቅ እጣ ደርሶባቸዋል። በተለይ በምስራቅ አፋር፤ ሱማሌና እሮሞዎች ጐልቶ ይታይ ነበር።

በዘመነ መሳፍንት በኦሮሞ መሪዎች አማካኝነት ይደረጉ የነበሩ ጦርነቶች ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች ብቻ የተወሰነ አልነበረም። በሽዋ ከነበሩ መንግሥታት ጋር በመመሳሰል አጼ ሱሰንዮስ የተባሉ እሮሞዎችን ይዘው ከጐንደር ነገሥታት ጋር ተዋግተው ጐንደር መንግሥት መስርተው ነበር። በየጊዜው የሚደረጉ የሥልጣን ፉክክሮች የኃይል ሚዛናቸው እያየለ ሲመጣ ዛጉዌዎች የሃይማኖትንና የአገር አመራርን ለሰለሞናዊ ሰርወ-መንግሥት አስተላፉ። በዚህ ጊዜ በሰሜን በኩል አማራና ትግሬ የበላይነት እንዳላቸው በሌሎች ዘንድ ጥርጣሬን እንዳስከተለ ይገመታል።

ከላይ የተጠቀሰውን አጋጣሚ በመጠቀም ቱርክ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ የአካባቢ የጐሳ መሪዎችን በጥቅማጥቅም እየደለለች በ1557 ምጽዋን ተቆጣጠረች። እንዲሁ ግብጽ የሱዳን ወደብ የነበረውን ዘይላን ያዘች። ከዛም እስከ ቀይ ባሕር ድረስ ለመስፋፋት ሞክራለች። በ19ኛው ከፍለ ዘመን ጣሊንና እንግሊዝም ቅኝ ግዛታቸውን ለማስፋፋት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ስላደረጉ አገሪቱ በውጭና በእርስ በርስ ጦርነት ተወጠረች።

በዘመነ መሳፍንት የግዛት ዘመን የአገሪቱ ማዕከላዊ መንግሥት እየተዳከመ ሲመጣ የትግራይ ገዥ የነበሩ ራስ ሚካኤል ስሁል የተባሉ ኢዮአስ 1ኛን በ1769 ከሥልጣን አውርደው አስገደሏቸው። እንዲሁ አጼ ዮሃንስ 2ኛ አጼ ተክለሃይማኖት 2ኛን ሲሾሙ ለዘመነ መሳፍንት የመጀመሪያው ክስተት ሆነ።
የተካሄደው የእርስ በርስ የሥልጣን ሽኩቻ በተራዘመ ቁጥር ግብጽ አጋጣሚውን በመጠቀም 1874 ዓ.ም ሀረርን ተቆጣጥራ ነበር። በ1875 ዓ.ም በሰሜን በኩል ጣሊያኖች ከፍተኛ የመስፋፋት ወረራ አደረጉ። ይሁን እንጂ በአጼ ዮሃንስ አራተኛ የግዛት ዘመን ሥመ ጥሩው አሉላ አባ ነጋ ባደረጉት የተቀነባበረ ጦርነት በ1887 ዓ.ም ዶጋሌ ላይ ጣሊያን መሸነፏ አልቀረም። በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲሁ ጉራአ አካባቢ ግብጽ የላከቸው ጦር በኢትዮጵያ አልበገር ባይነት ድባቅ ተመታች።

በኢትዮጵያ የተማከለ መንግሥት ለመመስረትም ሆነ የበላይነትን ለማሳየት ብዙ ጊዜ የእርስ በርስ ጦርነቶች መካሄዳቸውን ከፍ ሲል አውስተናል። ይህ ሁኔታ ባለበት አጼ ቴዎድሮስ 2ኛ በጐንደር በኩል ሥማቸውና ኃይላቸው ጐልቶ ወጣ። ነገር ግን በአገሪቱ የተማከለ መንግሥት ለመመስረት ከፍተኛ ተጋድሎ በሚያደርጉበት ወቅት የቤተክርስቲያን ሹማምትም ሆኑ አንዳንዶች ሥልጣናቸውን ላለማስነጠቅ ውስጥ ውስጡን በአጼ ቴዎድሮስ ላይ መዶለት ጀመሩ። ከዚህ አድማ ባልተናነሰ ሁኔታ የየጁ ኦሮሞ የሽዋ፤ የጐጃም መሳፍንቶች በጐንደር በኩል የሥልጣን ተፎካካሪ የሆኑ አጼ ቴድሮስን ለመውጋት ተነሱባቸው።

የሰሜኑ የትግሬው በዝብዝ ካሣ (አጼ ዮሃንስ 4ኛ) ሥጣል ከቴዎድሮስ እጅ ነጥቀው ብቸኛ ንጉሥ ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎት ስለነበራቸው የመሣሪያ እርዳታ አገኛለሁ በሚል ከኢንግሊዝ ጋር ተስማሙ። ይሁን እንጅ አጼ ቴዎድሮስ የውጭ ባዕድ ወራሪ ኃይል አገሪቱን እንዳይደፍራት ኃይላቸውን በማጠናከር ብዙ ጊዜ ተዋግተዋል።

ነገር ግን አገር በቀል ባንዳዎች ለእንግዝሊዝ ጦር መረጃ እያቀበሉ የአጼ ቴዎድሮስ ኃይል እንዲሳሳ ማድረጋቸው አልቀረም። ለዚህ ማስረጃ አጼ ዮሃንስ አራተኛን ከእንግሊዝ ጋር ባደረጉት ውል የናፒየርን ጦር ወደ መቅደላ መምራታቸው ነው። በመጨረሻም አጼ ቴዎድሮስ የሚደርስባቸውን ተቃውሞ እየተጋፈጡ ከ1855 1868 በንግሥና ቆይተው መቅደላ ላይ ከኢንግሊዞች ጋር በተከፈተው ጦርነት ለጠላት እጅ መስጠትን እንደነውር ቆጥረው የራሳቸውን ሽጉጥ ጠጥተው ለአገራቸውና ለሕዝባቸው መስዋዕት መሆናቸውን ታሪክ መዝግቦታል።

ከአጼ ቴዎድሮስ በኋላ አጼ ዮሃንስ 4ኛ ኃይላቸው በማጠናከር ከተቀናቃኞቻቸው ጋር ከፍተኛ ውጊያ አድርገዋል። በእንግሊዝ መንግሥት ተባባሪነት የአጼ ዮሃንስ አራተኛ ኃይል ጐልቶ ሊወጣ ቻለ። ይሁን እንጂ የአካባቢ ገዥዎችን ከማስተባበር ባለፈ አገሪቱን በተማከለ መልክ ማስተዳደር አለመቻላቸውን ከታሪክ መረዳት አያዳግትም። በሰሜን ጀግናው አሉላ አባ ነጋ የጣሊያንን ወረራ እየተጋፈጡ ባለበት የአጼ ዮሃንስ ኃይል እምብዛም እንዳልታከለበት የብዙዎች ግምት ነው።

አጼ ዮሃንስ አገራቸውን ለባዕድ ወራሪ አሳልፈው ላለመስጠት መተማ ላይ ከድርቡሾች ጋር ሲዋጉ ሕይወታቸው ልፏል። አንገታቸው ተቆርጦ ካርቱም መሄዱ እውነት ነው። በዚህ ሁኔታ አጼ ዮሃንስ አራተኛ 1872–1889 ድረሰ ሥልጣን ላይ መቆየታቸው የማይታበል የታሪክ ሃቅ ነው።

አጼ ዮሃንስ አራተኛ ኢትዮጵያን በተማከለ መልክ ለማስተዳድር ጥረት በማድረጋቸው ለኢትዮጵያ ባለውለታ ናቸው። ነገር ግን በግዛት ዘመናቸው ሕዝብ አብሯቸው ተሰልፎ እያለ በእስልምና ተከታዮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር ጀመሩ። አጼ ዮሃንስ አራተኛ የአስተዳደር ጉድለት ወይም ብቃት ስላልነበራቸው በእስልምና ተከታይ ሕዝብ በኩል ሊያገኙ ይችሉ የነበረው ድጋፍ አጡ። ጠቅለል ባለ መልኩ አጼ ዮሃንስ አራተኛ በታሪክ መልካም ሥም ቢኖራቸውም አጼ ቴውድሮስ በባዕድ ወራሪ እንዲጠቁ ማድረግ ባልተገባቸው ነበር። በዚህ የተነሳ ይመስላል ብዙ ጊዜ የአጼ ዮሃንስ መንግሥት በባዕዳን የተገነባ እንደነበር የተለያዩ የታሪክ ፀኃፊዎች ዘግበውታል።

በልማት በኩል ያደረጉት አስተዋጽዖ ጐልቶ አልታየም። የእስልምናን ሃይማኖት ጠቅለው ወደ ክርስትና ሃይማኖት ለማስፋፋት ከፍተኛ ሥራ ሰርተዋል። ቢሆንም ከጥቅሙ ጉዳቱ እያመዘነ የሃይማኖት ልዩነት በፈጠረው ክፍተት የሰው ሕይወትና ንብረት ከማለቁም ባሻገር የእስላምና የክርስቲያን አንድነት እንዳይጠነክር የአጼ ዮሃንስ አራተኛ አስተዳደር ምክንያት ሆኗል።

ባጠቃላይ በዛ ዓለም ባልሰለጠነት፤ አገሪቱ በእርስ በርስ የሥልጣን ሽኩቻ እየታመሰች ባለበት አገራቸውን ለድርቡሽ አሳልሆፎ ላለመስጠት ያደረጉት ጀግንነት ለመላ ኢትዮጵያ ዋስትና ነበር ማለት ይቻላል።

ከዝርዝር ጉዳዩ ከመግባቴ በፊት በመጀመሪያ ደረጃ መምህር ገብረ ኪዳን ደስታ ጊዜያቸውን ወስደው የአገር ታሪክ በመፃፋቸው ላንደቃቸው እወዳለሁ። ከዚህ በፊት የተፃፉም ሆነ ያልተፃፉ በታሪክነት እንዲቀመጡ ችሎታ ያላቸው የመፃፍ አገራዊ አደራ አለባቸው። እርግጥ ነው ሰው የማይገሰስ ሰብአዊ መብቱን በመጠቀም መፃፍና መናገር እንደሚችል አምናለሁ። ነገር ግን የአገርና የሕዝብ ታሪክ በዘፈቀደና ክልልን ያማከለ ከሆነ ለትውልዱም ሆነ ለአገር ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ከመምህር ገብረ ኪዳን አንደበት ማድመጥ እንደተቻለው ችግራቸው ከአጼ ምኒሊክ ጋር የተያያዘ ነው። ይህን ካልኩ ዘንዳ ወደ መነሻየ ላምራ።

መምህር ገብረኪዳን ደስታ በቅርቡ ስለአጼ ዮሃንስ አራተኛ ገድል የሚያሳይ መጽሕፍ መፃፋቸው ይታወሳል። ይህን መነሻ በማድረግ የአሜሪካ ሬዲዮ አማርኛ ዝግጅት የትግራይ ቃላቀባይ አቶ ገብራይ ገብሩ የአጼ ዮሃንስን ገድል የሚያወሳ መጽሕፍ መፃፍ ለምን አስፈለገ የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸው ማዳመጥ ችያለሁ።

የመምህር ገብረ ኪዳን ደስታ መልስ፟፦ሌሎች ስለአካባቢያቸው ሲጽፉ እኔም ስለአካባቢየ እጽፋለሁ፤ አጼ ዮሃንስ ለኢትዮጵያ ጥሩ ሰርተዋል፤ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ታሪክ የተባለው ለአንድ ውስን ሰርዓ-ተማኅበር ብቻ በማጠንጠን አንድ አቅጣጫ ይዟል፤ ለማቃናት የሚተጋ ሰው አላጋጠመኝም፤ በአጼ ዮሃንስ ላይ የተሳሳተውን ዘገባ ለማስተካከል ነው አሉ። ጋዜጠኛው ገብራይ ገብሩ አክሎ ለዚህ ምን ማሰረጃ አለዎች የሚል ጥያቄ አቀረበላቸው።
የደራሲ ገብረ ኪዳን መልስ ፦ ስለመረጃ ከትግራይ ሕዝብ በላይ ምንጭ የሚሆነኝ ሌላ ሕዝብ የለም የሚል ነበር።

መምህር ገብረ ኪዳን ማብራሪያቸውን ሰፋ በማድረግ አጼ ምኒሊክ የሽዋ ሰው ብቻ ስለነበሩ ሰሜኑን ክፍል እንደ ኢትዮጵያ አይመለከቱትም፤ ለኮሎኒያሊዝም ምክንያት ናቸው ወዘተ በማለት ደጋግመው ነግረውናል።

አዎ አጼ ምኒሊክ የሸዋ ሰው መሆናቸው አይካድም፤ በዚህ ሁላችን ልዩነት ያለን አይመስለኝም፤ እሽ እንስማማ። ችግሩ ግን የሽዋ ሰው ብቻ ስለነበሩ ሰሜኑን ክፍል እንደ ኢትዮጵያ አይመለከቱትም የሚለውን አምኖ ለመቀበል ህሊናየ አልደፈረም። አባቶቻችና የታሪክ መዛግብት እንደሚያስረዱን ከሆነ አጼ ምኒሊክ የመላ ኢትዮጵያ አካል መሆናቸውን ነው ታሪክ የነገረን።

በዘመኑ መሳፍንታት ሲነሱ መጀመሪያ የአካባቢያቸውን ሕዝብ ይሁንታ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ነው። የአጼ ዮሃንስን፤ የአጼ ቴዎድሮስም የኃይል አደረጃጀት እንዲሁ በአካባቢ ላይ የተገነባ ነበር። የአጼ ምኒሊክም አደረጃጀት ከዚህ የተለይ አይደለም። በዚህ ዓይነት መነሻቸውን አውቀው እያሰፉ ሌላውን አካባቢ ማስተዳደር ችለዋል።

አጼ ምኒሊክ ከአጼ ዮሃንስ ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር አጼ ምኒሊክ አንድ ነገር ከማድረጋቸው በፍፊት አቅምና ችሎታቸውን የማመዛዝን ችሎታ ነበራቸው። በወቅቱ አጼ ዮሃንስ ከእንግሊዝ ባገኙት መሣሪያ የተጠናከሩ ስለነበር ለብቻ ከመዋጋት ይልቅ ኃይል ካለው ጋር በመሆኑ አገሪቱን ማስተዳደር ይቻላል በሚል አጼ ምኒሊክ ከትግሬ ከተወለዱት ከአጼ ዮሃንስ ጋር ወዳጅነት መፍጠር ብቻ ሳይሆ እስከ መጋባት ደርሰዋል። ታዲያ ከሸዋ እስከ ትግራይ ድርሰ ዘር ሳይለዩ በጋብቻ ከተሳሰሩ የሽዋ ብቻ ነበሩ ለማለት አያስደፍርም። ታሪኩ እንደታሪክ ይቀመጥ ከተባለ የጠባብነት ስሜት ያልነበራቸው ምኒሊክ ብቻ ነበሩ ማለት ይቻላል።
የኢትዮጵያን ሉዓዊነት ለማስከበር የተማከለ መንግሥት ለመፍጠር የተለያዩ አካባቢዎችን አንድ እያደረጉ እቅዳቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥ እየተንቀሳቀሱ እያለ ከመሳፍንቶች የእርስ በርስ ጦርነት በከፋ መልኩ የጣሊያን መንግሥት ኢትዮጵያን ለመቀራመት ወረራ ጀመረ። ይሁን እንጅ በአጼ ምኒሊክ ድፍረትና በእትጌ ጣይቱ ብልህነት በ1896 የአድዋን ድል ተጐናጸፉ። ነገር ግን የአገሪቱ ማዕከላዊ መንግሥት በመላላቱ የተነሳ ቀረጥ ወይም ታክስ የሚከፍለው የሰው ቁጥር ቀነሰ። የገቢ ምንጭ በቀነሰበት ሁኔታ እስከ መጨረሻው ከጣሊያን ጋር ጦርነት ቢገጥሙ ውድቀት ሊደርስባቸው እንደሚችል በመገመት ለጊዜው ኤርትራን ከጣሊያን እጅ ማስወጣት አልቻሉም።

ለዚህ ዋናው ምክንያት የኢኮኖሚ አቅም ማነስና በሰሜ ኢትዮጵያ አገር በቀሎች ከጠላት ጋር በመወገናቸው ወደ ፊት ቢገሰግሱ ድል ሳይሆን የያዙትን እንደሚያጡ ከግምት በመሳገባት ነው።
የዚህ አይነት የጦርነት እስትራቴጅ በዚህ በ21 ክፍለ ዘመንም ቢሆን አንድ መንግሥት ለውጊያ ሲነሳ መጀመሪያ የጦር ኃይሉን የኢኮኖሚ አቅሙ በማገናዘብ ነው ። ታዲያ የአጼ ምኒሊክ ጥፋት ተምኑ ላይ ነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ይሁን እንጅ አጼ ምኒሊክ ቀስ በቀስ የመሳፍንት ገዥዎችን ወደ አንድ በማምጣት ለማዋሀድና አገሪቱ ከውጭ ወራሪ ጦርነት ተላቃ የቴክኖሎጅ እድገት እንድታሳይ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። የተለያዩ የእምነት ተከታዮች የእርስ በርስ ውጊያን አስቀርተው ወደ አንድ እንዲመጡ አድርገዋል።

አጼ ምኒሊክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የዛሬው ምሁር ያላሳየውን የተራማጅነት ባሕሪ እንደነበራቸው አሳተው አልፈዋል። በአገሪቱ ሰላም የሰፈነ በአጼ ዮሃንስ ዘመን ሳይሆን በአጼ ምኒሊክ የግዛት ዘመን ስለመሆኑ ታሪክ ነጋሪ አያስፈልግም። ድሃው ሰርቶ የመኖር መብቱ ተከብሮ፤ ግብር እንኳን መክፈል ያልቻሉ እርዳታ እየተሰጣቸው በሰላም የኖሩበትን ዘመን ፈጠረዋል። የአግሪቱን የሥልጣኔ ጉዳና ለማፋጠን ገጠሬውን ከከቴሜው፤ የውጩን ከኢትዮጵያ ጋር ለማገናኘት የባቡር መስመር፤ የስልክ አገልግሎት እንዲስፋፋ የመጀመሪያ የእድገት በር ከፋች አጼ ምኒሊክ ናቸው።

በአጼ ዮሃንስ ዘመን ጣሊያን በቀይ ባሕር ሲስፋፋ ነበር። አጼ ምኒሊክ ግን የባድ ወራሪን መስፋፋት ዘመቻ ለመደምሰስ ባደረጉት ጦርነት አድዋ ላይ ድል መቀዳጀታቸው ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ አጼ ምኒልክ ብቻ ናቸው። የአገሪቱን የእርስ በርስ ጦርነት አስወግደው አዲስ አበባን ቆርቁረው ዛሬ ለአፍሪካ አንድነት ጽሕፈት ቤት በር የከፈቱ ምኒሊክ ብቻ ናቸው።

ኢትዮጵያን በሕግ የሚተዳደር ሕዝብ ፈጥረዋል። ዓለም ባልሰለጠነበት በእርስ በርስ ጦርነት ወቅት አጼ ምኒሊክ ሥልጣ ከአንዱ ወሌላው በሰላም እንዲሸጋገር ለመጀመሪያ ጊዜ የዴምክራርሲን ይትባህል አሳይተው አልፈዋል።

ደራሲው ከአንደበታቸው ሲናገሩ እንደተደመጠው ከሆነ በጐጥ ዙሪያ የተሸበቡ መሆናቸውን አሳይቷል።
በጣም አዛዛኝ ሆኖ ያገኘሁት ደግሞ መላውን ኢትዮጵያ በማግለል ምስክሬና የታሪኩ ምንጭ የትግራይ ሕዝብ ብቻ ነው ማለታቸው የደራሲነታቸውን ማንነት በሚገባ አሳይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የህወሐትን የድል ቀን ትግራይ ውስጥ ሲያከብሩ እንኳ ከወርቅ ሕዝብ ተወለድኩ ያሉትን ቃል ያጠናከረ መጽሕፍ መስሎ ታይቶኛል።

ኢትዮጵያ ከመሳፍንት እስከ አሁን ድረሰ ሕዝቦች ተዋደው ተፋቅረው ዘር ሳይለዩ ተጋብተው ተዋልደው አገራችን አቆይተው አስረክበውናል። በመሆኑም ይህ ትውልድም ሆነ ቀጣዩ ትውልድ አንድ በሆነች አገሩ እንዲኮራ ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠነክር የታሪክ መጽሀፍ እንደሚፈልግ አያጠያይቅም።

በመጨረሻ፦መምህር ገብረኪዳን ደስታ በቃለመጥይቁ ላይ የተሳሳትኩት ካለ እታረማለሁ ማለታቸው ኢትዮጵያዊነትን ያሳያል። በመሆኑም መምህር ገብረኪዳን በታሪክነት ያቀረቡትን መጽሀፍ ለአገርና ለሕዝብ አፍራሽ መሆኑን ልብ እንዲሉት ተመልሰው እንዲያነቡትና የሚስተካከለውን በእርምት መልክ ቢያወጡት በሕዝብ ዘንድ ሊኖረዎት የሚገባው ተቀባይነት ቦታ ይኖረዋል። ነገር ግን ወግቶ ይማርህ ከሆነ በታሪክ ማስወቀሱ አይቀርም።

አንባቢያን በዚህ ዙሪያ የተሳሳትኩት ወይም የጐደለ ካለ ለመታረም ዝግጁ ነኝ።

ሁሉም ቀናውን እንዲያሰብ የእግዚአብርሄር ረዴት ይደርብን።

የቤቲ እናት “ልጄ በፍጹም ይህን ድርጊት አልፈጸመችም፤ አትፈጽምም” አሉ

$
0
0

betty-bba-chase-ethiopia(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ በሚሰራጨው በሸገር ራድዮ የታዲያስ አዲስ የራድዮ ፕሮግራም ላይ የቀረቡት ከሰሞኑ ኢትዮጵያውያንን እያነጋገረች የምትገኘው የቤቲ እናት ወ/ሮ አየለች ልጃቸው ከሴኒጋላዊው ጋር አልጋ መጋፈፏንና በቪድዮ ላይ መታየቱን “አላምንም፤ ልጄ በፍጹም ይህን ድርጊት አልፈጸመችም፤ አትፈጽምምም” ሲሉ ተከራከሩ። በፌስቡክ ላይ ስለልጅቷ የሚወራውም የምቀኛ ወሬ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር ቃል የተመላለሱት ወ/ሮዋ ህዝቡ ለልጃቸው ላይ እጁን እንዲያነሳ ጠይቀዋል። ቃለምልልሱን ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ

የድምጻዊት አበበች ደራራ መታሰቢያ ፕሮግራም በእስራኤል የኢትዮጵያ ቲቪ ቀረበ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በቅርቡ ከዚህ ዓለም ያለፈችው ድምጻዊት አበበች ደራራን በማስመልከት በእስራኤል የኢትዮጵያ ቲቪ የመታሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጀ። በዚህ የመታሰቢያ የቲቪ ፕሮግራም ላይ የተለያዩ በ እስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ስለአበበች የሚሰማቸውንና ያሳለፏቸውን መልካም ጊዜያትና የድምጻዊቷን ሥራዎች ዳስዋል። ዘ-ሐበሻ ይህን ፕሮግራም ለአንባቢዎቿ ታካፍላለች። ቪድዮው የሚከተለው ነው፦
AbebechDerara

Sport: የኢትዮጵያን ደስታ የፊፋ ዜና አቀዘቀዘው

$
0
0

ethiopia bafana bfana

ከፍሰሃ ተገኝ

(www.total433.com)

አዲስ አበባ ላይ የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድንን ያስተናገደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጌታሁን ከበደ እና የደቡብ አፍሪካው የፊታ አጥቂ በርናርድ ፓርከር በራሱ ጎል ላይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2 ለ 1 አሸንፏል።

የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን በተላይ በመጀመሪያዎቹ 20 እና 25 ደቂቃዎች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመሀል ክፍል ኳሱን እንዳይቆጣጠር ለማድረግ በሚል ተጭኖ የተጫወተ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ሰባት እና ስምንት የደቡብ አፍሪካ ተጨዋቾችን የኢትዮጵያ ቡድን ግማሽ ሜዳ ላይ ማየት የተለመደ ነበር።

ሆኖም የጨዋታውን የመጀመሪያ የጎል ማግባት እድል የፈጠረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሲሆን ሳልሀዲን ሰኢድ በግንባሩ የገጨውን ኳስ የደቡብ አፍሪካው ግብ ጠባቂ ኩኔ አድኖበታል።

15ኛው ደቂቃ ላይ ሳልሀዲን ሰኢድ ከርቀት በግሩም ሁኔታ የሞከረውን ኩኔ እንደገና ጎል ከመሆን ሲያከሽፍበት፣ ብዙም ሳይቆይ ፓርከር ከሌሾሎንያኔ የተቀበለውን ኳስ መትቶ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰው በግሩም ሁኔታ አድኖበታል።

ጨዋታው ግማሽ ሰአት ያህል እንደተጓዘ ፋላ ከማእዘን ምት ያሻማውን ኳስ ማቶሆ በጭንቅላቱ በመግጨት የሞከረውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰው በቡጢ የመለሰው ኳስ ፓርከር ጋር ደርሶ ለደቡብ አፍሪካው ካይዘርስ ቺፍስ ክለብ የሚጫወተው የፊት አጥቂ ያደረገውን የጎል ሙከራ የግቡ መስመሩ ላይ ቆሞ ሲጠብቅ የነበረው አይናለም ሀይሉ በአስደናቂ መከላከል ጎል ከመሆን አድኖታል።

የጨዋታው የመጀምሪያ ጎል የተገኘው 34ኛው ደቂቃ ላይ ሲሆን በረኛው ኩኔ በረጅሙ ወደ ኢትዮጵያ ሜዳ የመታውን ፓርከር ከኢትዮጵያ ተከላካዮች ፈጥኖ በመሮጥ የመታው ኳስ ጀማል ጣሰውን አልፋ መረብ ላይ በማረፏ ደቡብ አፍሪካ ጨዋታውን 1 ለ 0 እንድትመራ አስችሏታል።

የደቡብ አፍሪካ መሪነት የቆየው ግን ስምንት ደቂቃ ያህል ብቻ ሲሆን የመጀመሪያው ግማሽ የጨዋታ ክፍለ-ጊዜ ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃዎች ያህል ሲቀሩት አዲስ ህንጻ፣ ሽመልስ በቀለ እና ጌታነህ ከበደ ያደረጉት ቅብብል የፈጠረውን የጎል ማግባት እድል ጌታነህ ከበደ በግሩም ሁኔታ ከመረብ አሳርፎ የመጀመሪያው ግማሽ የጨዋታ ክፍለ-ጊዜ 1-1 ተጠናቋል።

በሁለተኛው ግማሽ የጨዋታ ክፍለ-ጊዜም ልክ እንደ መጀመሪያው ሁሉ ደቡብ አፍሪካ ተጭኖ የተጫወተ ቢሆንም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጠንካራ የመከላከል እንቅስቃሴ ጥቃቱን ለመቋቋም አልተቸገረም ነበር። በተለይ ተቀይሮ የገባው ራንቴ ሜዳ ከገባ ብዙም ሳይቆይ ሁለት አደገኛ የጎል ማግባት ሙከራዎችን ቢያደርግም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመከላከል እንቅስቃሴሴ እና የራሱም የአጨራረስ ድክመት ሙከራውን አክሽፎበታል።

70ኛው ደቂቃ ላይ አበባው ቡጣቆ በቅጣት ምት ወደ ደቡብ አፍሪካ የፍጹም ቅጣት ምት ክልል የላከውን ኳስ የደቡብ አፍሪካው ፓርከር በግንባሩ ገጭቶ ባልተጠበቀ ሁኔታ በራሱ ጎል ላይ ግሩም ጎል በማሳረፉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ሊመራ ችሏል።

የጨዋታው የመጨረሻ 15 ደቂቃዎች በአብዛኛው ደቡብ አፍሪካ ጎል ለማግባት በሚያደርገው ማጥቃት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደግሞ ውጤት አስጠብቆ ለመውጣት እና በሚገኙ አጋጣሚዎች ኳሱን ወደፊት ለሳልሀዲን ሰኢድ እና ጌታነህ ከበደ በመላክ በማጥቃቱ ላይ በመሳተፍ በሚያደርጓቸው ጥንቃቄ የተሞላባቸው እንቅስቃሴዎች ከተጓዘ በኋላ በኢትዮጵያ 2 ለ 1 አሸናፉነት የተጠናቀቀው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት፦

“ይሄ ተአምር ነው። ዛሬ በምንም ቃል ሊገለጽ የማይችል ለኢትዮጵያዊያን ታላቅ ቀን ነው። ደቡብ አፍሪካ በመጀመሪያው ግማሽ ተጭኖን ተጫውቷል። ጠንካሮችም ነበሩ። በሁለተኛው ግማሽ ግን የአጨዋወት ለውጥ በማድረግ ሁለቱ የተመላላሽ ስፍራ ተጨዋቾችቼ አጥቅተው እንዲጫወቱ አደረኳቸው።

“ምክንያቱም በሜዳችን እንደመጫወታችን አቻ መውጣት በቂያችን አልነበረም። በደጋፊያችን ፊት ማሸነፍን እፈልግ ነበር። በርግጥ ያሸናፊነቷን ጎል የሰጠን ደቡብ አፍሪካዊ ተጨዋች ነው። ምን አልባት እግርዚአብሄር ድሉን ለኛ ሊሰጠን ስለወሰነ ይሆናል ያ የሆነው” ብለዋል።

የደቡብ አፍሪካው አሰልጣኝ ጎርደን ኢገንሰንድ ቡድናቸው ቢሸነፍም የተጋጣሚያቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና ደጋፊውን ከማድነቅ ወደኋላ አላሉም።

“ኢትዮጵያዊያንን እንኳን ደስ ያላችሁ እላለሁ። በጣም አስቸጋሪ ጨዋታ ነበር። በተላይ ደጋፊዎቻቸው ግሩም ነበሩ” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዚህ ውጤት በኋላ ምድቡን አንድን በ13 ነጥብ በመምራት አንድ የምድብ ጨዋታ እየቀረ በጥሎማለፍ መልክ ወደሚካሄደው የቀጣዪ ዙር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ማለፏን ቢያረጋግጥም የአለም አቀፉ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፊፋ እሁድ ማምሻውን ባወጣው ዜና “የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአለፈው ሳምንት ቦትስዋናን 2 ለ 1 በረታበት ጨዋታ ላይ ተሰልፎ መጫወት ያልነበረበት ተጨዋች አሰልፎ አጫውቷል” በሚል ምርመራ እንደሚደረግበት ማስታወቁ በኢትዮጵያዊያን ላይ የተፈጠረውን ታላቅ የደስታ ስሜት አደብዝዞታል።

ፊፋ ኢትዮጵያን ጨምሮ በቶጎ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ላይ ተመሳሳይ ምርመራ የከፈተው የፊፋ የውድድር እና ስነ-ስርአት መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 55 እና የብራዚሉ አለም ዋንጫ ማጣሪያ መተዳደሪያ ደንብ ላይ አንቀጽ ስምንትን በመጥቀስ ነው።

የፊፋ የውድድር እና ስነ-ስርአት መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 55

የፊፋ የውድድር እና ስነ-ስርአት መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 55

የፊፋ የጨዋታ መዝገቦች እንደሚያሳዩት ከሆነ ምን አልባት መጫወት ሳይኖርበት የተጫወተው ምንያህል ተሾመ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ ጋር 1 ለ 1 በተለያየችበት እና አዲስ አበባ ላይ ቦትስዋናን 1 ለ 0 በረታችበት ጨዋታዎች ላይ የቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርዶች ያየ በመሆኑ በአለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ ወደ ሎባትሴ አቅንታ ቦትስዋናን 2 ለ 1 በረታችበት ጨዋታ መሰለፍ አልነበረበትም።

ምንያህል ተሾመ በየነ የቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርዶች ያየባቸው ጨዋታዎች (ምንጭ - ፊፋ ድረ-ገጽ)

ምንያህል ተሾመ በየነ የቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርዶች ያየባቸው ጨዋታዎች (ምንጭ – ፊፋ ድረ-ገጽ)

ኢትዮጵያ ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች የአለፈው ሳምንቷ ድል ይሰረዝ እና ለቦትስዋና የ 3 ለ 0 አሸናፊነት እና ሙሉ ሶስት ነጥብ የሚሰጥ ሲሆን፣ የምድብ አንድ የደረጃ ሰንጠረዥን ኢትዮጵያ በ10 ነጥብ ስትመራ፣ ደቡብ አፍሪካ በስምንት ነጥብ ሁለተኛ፣ ቦትስዋና በሰባት ነጥብ ሶስተኛ፣ መሀከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ በሶስት ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዘው የሚከተሉ ይሆናል።

ስለዚህ ወደ ቀጣዩ ዙር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የሚያልፈውን የምድቡ አሸናፊ ለመለየት መሀከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ከ ኢትዮጵያ፤ ደቡብ አፍሪካ ከ ቦትስዋና የሚያደርጉት የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታዎች ወሳኝ ይሆናሉ ማለት ነው።

ምንጭ፡ total433.com

Viewing all 13695 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>