Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all 13695 articles
Browse latest View live

መንግስታዊ ሽብርተኝነትን የሚሸከም ትከሻ አይኖረንም!!!

$
0
0

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም
የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎችን በማፈንና በማሰቃየት ብሎም በመግደል የአፈና አገዛዙን ለረጅም ጊዜ ሲያራምድ መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እስራትና ግድያውን ህጋዊ ለማስመሰል የተለያዩ አፋኝ አዋጆችን አውጥቷል፡፡ እነዚህን አዋጆችንም ተገን አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባለትን፣ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን፣ እንዲሁም የእምነት ተቋማት መሪዎችን እና በአገዛዙ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ማሰሩን፣ ማሰቃየቱንና ግድያውን ተያይዞታል፡፡ በህገ መንግስቱ የተካተቱ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በሙሉ የሚጥሰውና የአምባገነንነት ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ያፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ ከፀደቀበት እለት አንስቶ ኢህአዴግ ለስልጣኔ ያሰጉኛል የሚላቸውን ፍፁም ሰላማዊ ታጋዮችንና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው በድፍረት የፃፉ ጋዜጠኞችን ብሎም የእምነት ነፃነታችን ይከበር ብለው የጠየቁ የሀይማኖት መሪዎችን በጠራራ ፀሃይ ያለምንም ወንጀል በዚሁ ህገ ወጥ አዋጅ ‹‹የፀረ ሽብር ግብረ ሀይል›› በሚባል ማንነቱ በማይታወቅ የጨለማ ቡድን ወደ እስር ቤት እያጋዘ ይገኛል፡፡

ይህን የሚያጋልጡ ሚዲያዎችንም ለማፈን እስር ቤቶችን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያፈሰሰ የአየር ሞገድ ያውካል፤ በዚህ ሳያበቃ በሀገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ ፖለቲከኞችን ለማሸማቀቅ እንደ ኢሳት ያሉ ሚዲያዎችን የአሸባሪ ልሳን ብሎ በመፈረጅ ሚዲያውን የሚጠቀሙትን ደግሞ ከአሸባሪዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው አድርጎ መወንጀሉን ቀጥሎበታል፡፡ እንደሰማያዊ እምነት ማንም አካል መልእክት የሚያስተላለፍበትን የሚዲያ ተቋም ሊመርጥለት እንደማይችል መንግስት እንዲገነዘበው ከዚህ በፊት በግልፅ ያሳወቀ ሲሆን አሁንም ፓርቲው በዚሁ የፀና አቋሙ እንደሚቀጥል በድጋሚ ይገልፃል፡፡

ባጠቃለይ የዚህን ገዢ አካል የእውር ድንብር ሀገር የማስተዳደር ጉዞ ለመታገል በርካቶች በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም በህወሓት/ኢህአዲግ ግፍና መከራ ተገፍተው ስርዓቱን በሃይል እናስወግዳለን ብለው ሀገር ጥለው የተሰደዱ ዜጎችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የህወሓት/ኢህአዲግ ማናለብኝነትና የስልጣን ጥመኝነትም በግለሰቦች ላይ ከሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ በላይ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትን አስከትሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ይህ ገዢ ፓርቲ የፈጠረው ስርዓት የሀገሪቷን ሰላማዊ የፖለቲካ ምህዳር በማጥበብ ሀገራችንን ወደ አልተፈለገ አለመረጋጋትና ቀውስ እየመራት ይገኛል፡፡ፓርቲያችንም እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም በቅርቡ እየተፈፀሙ የሚገኙ ህገ ወጥ ድርጊቶች ስላሳሰበው ይህን መግለጫ ለማውጣት ተገዷል:-

1. ሰኔ 16 2006 ዓ.ም የየመን መንግስት የዓለም አቀፍ ስምምነቶችንና ድንጋጌዎችን በመጣስና በሰው ሀገር የውስጥ ጉዳይ በመግባት የአማፂ ቡድን ግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዟ ይታወሳል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ለህወሓት/ ኢህአዴግ ተላልፈው መሰጠታቸውን ከ16 ቀናት በኋላ መታወቁና ይህንንም ሁለቱ ሀይሎች ማመናቸው ተሰምቷል፡፡ ነፃነት በሌለበት ሀገር ዜጎች ሰብዓዊ ክብራቸውን ለማስጠበቅ የሚያደርጉት ጥረት የሌሎች ሀገር መንግስታት የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በዓለም አቀፍ ስምምነቶችም ሆነ በተለይ በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ጥላ የሚያጠላ መሆኑን ግንዛቤ አለመወሰዱ እጅግ የሚያሳዝን ድርጊት ነው፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከተያዙ በኋላ ላለፉት 16 ቀናት በምን አይነት ሁናቴ እንደቆዩ ህዝብና ቤተሰቦቻቸው እንዲያውቁት አለመደረጉ፤ ስለ አያያዛቸው ሁኔታም በማህበረሰቡና በፓርቲያችን ውስጥ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዲኖር አድርጓል፡፡ሰማያዊ ፓርቲ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሰብዓዊ አያያዝ እያሳሰበው ህወሓት መራሹ የኢህአዴግ አገዛዝ አያያዛቸውን ግልፅ እንዲያደርግ ሰብዓዊ ክብራቸውም እንዲጠበቅ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
2. በዚሁ ሳምንት ገዢው ፓርቲ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የአምባገነኑን መንግስት ህወሓት/ኢህአዲግን ሲታገሉ የነበሩ ፖለቲከኞችን በስመ አሸባሪ ከያሉበት እየለቀመ ህገ-ወጥ እስራት መፈፀሙ ይታወቃል፡፡ ህወሓት/ኢህአዲግ ይህ ግብታዊ ተግባሩ ምንም እንኳን አዲስ ባይሆንም በአሁኑ ወቅት ለውጥን ለማምጣት በቆራጥነት እየታገሉ ያሉ ሰላማዊ ታጋዮችን ማሰሩ በሀገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ፓርቲዎችን ከአማፂ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው በማስመሰል ሰላማዊ ትግሉን ለማዳከምና መጪውን 2007 ዓ/ም ምርጫ ያለ ተቀናቃኝ ለማለፍ የሚደረግ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ የፓርቲያችን ብ/ም/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሺዋስ አሰፋ በሰላማዊ ትግሉ በቁርጠኝነት እየተሳተፈ ባለበት ሁኔታ ለእስር መዳረጉ፤ የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄን በመፍጠር ላይ ያለው የአረና /ትግራይ/ ፓርቲ አመራር አባል የሆኑትን አቶ አብረሃ ደስታ ለእስር መዳረጋቸው ህወኃት/ኢህአዴግ የመጨረሻው መጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ያረጋግጣል፡፡ በመሆኑም አገዛዙ እያካሄደ ያለውን መንግስታዊ ሽብር አቁሞ ለሀገርም ሆነ ለራሱ የሚበጀውን መንገድ እንዲከተል እያሳሰብን የታሰሩት የፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡

በመጨረሻም ፓርቲያችንን መንግስት እያደረገ ያለው ሽብርን የመንዛትና ህግን የመጣስ ተግባሩ መቼም ቢሆን ከሰላማዊ ትግሉ እንደማያቆመውና ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በአፅንኦት እየገለፀ እነዚህንና ከላይ የተጠቀሱትን የገዢውን ፓርቲ መርህ አልባነት፣ ህገ-ወጥነት እና የለየለት አምባገነንነትን አሁን ካለው ነባራዊ እውነታ ጋር አጣምሮ የትግል ስልቱን ደረጃ ከፍ ወዳለ ምዕራፍ ማሸጋገር እንዳለበት አምኗል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ለምናደርጋቸው ሀገር አቀፍ ንቅናቄዎች መላው የሀገሪቱ ህብረተሰብ በንቃት ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ ጥሪውን እያስተላለፈ ለዚህም ቁርጠኛ አመራር ለመስጠት ዝግጁነቱን ለመግለፅ ይወዳል፡፡በዚህ አምባገነንነትን ለመታገል በሚደረገው ንቅናቄም በሀገር ውስጥ የሚገኙ ህጋዊና ሰላማዊ ፓርቲዎች፤አለም አቀፍ ተቋማት፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ሲቪክ ማህበራት፤መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሰላማዊ ትግሉ ጎን በጋራ እንድንቆም እንጠይቃለን፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
ሰማያዊ ፓርቲ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም


Early Edition –ጁላይ 10, 2014

የመንግሥት ድጎማ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ወቀሳ

$
0
0
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ መንግሥት ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ላይ አድሎአዊ አሰራር ይታይበታል፣ ሕጋዊም አይደለም ሲል ቅሬታውን አሰማ።…

የተባባሰዉ የእስራኤል የፍልስጤም ግጭት

$
0
0
የእስራኤል የጦር አዉሮፕላኖች በፍልስጤም ግዛት ጋዛ ላይ ዛሬ ደጋግመዉ ባደረሱት ድብደባ የተጎዱ ሲቪሎች ቁጥር መጨመሩን ዘገባዎች ያመለክታሉ። የተመድ የፀጥታዉ ምክር ቤት እስራኤል ከሃማስ ጋ የገጠመችዉን ፍጥጫ ለመመልከት አስቸኳይ ስብሰባ ያደርጋል።…

አማርኛ ቋንቋን ከባዕድ ቋንቋ የመቀላቀል አባዜ

$
0
0
ተማርን የሚሉ ሰዎች አማርኛን ቋንቋ ዉስጥ አንዳንድ የእንግሊዘኛ ቋንቋን እየሰነቀሩ ቋንቋዉ እንዲመነምን እየዳረጉ ናቸዉ ይላሉ ምሁራን። በሌላ በኩል ሃሳብን ለመግለፅ አማርኛ ቋንቋ አስቸጋሪ ነዉ የሚሉም አልጠፉም!የባዕድ ቃላትን የመዋስ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ፤ እንግሊዘኛ ቃላትን ጣል እያደረጉ የመናገር አባዜ የተለመደ ይመስላል…

We cannot Tolerate TPLF/EPRDF’s State Terror!

$
0
0

Press Release by Blue Party Ethiopia / Semayawi Party- Ethiopia/
It is a well known fact that TPLF/EPRDF has slaughtered and oppressed Ethiopian citizens since it came to power. In order to oppress the peaceful struggle, especially within the last 10 years, the regime acclaimed several repressive proclamations and laws to legalize its butchery and tyranny. Many politicians, journalists, bloggers, religious leaders and people who raised question against the regime are victims of these proclamations. Since these controversial laws have been applauded by TPLF/EPRDF, the security institutions that serve the regime have put a lot of politicians, journalists, activists and many who issue its power to jails. The regime also tries to label Medias such as ESAT as terrorists’ medium to threaten politicians in relation to terror act which is ridiculous. Blue likes to stress out that no one should not and cannot choose Medias for anyone in regards to freedom of speech and press.

Accordingly, TPLF/EPRDF’s obsession of power and its negligence to accountability is leading the country in a wrong and chaotic situation. Particularly the last four years have been difficult and the arrest of many peaceful citizens made the political atmosphere very constricted. Nevertheless, countless people are struggling peacefully within the rule of law; many flee abroad to over throw the dictatorial government with whatever way they thought is possible. Thus, Blue Party /Semayawi/ finds it very significant to take this firm position due to the above reasons and more that hasn’t been mentioned here:

1- On June 24 2014, the rebel group Ginbot 7’s General Secretary, Andargachew Tsege was detained by the Yemeni intelligence officers in collaboration with Ethiopian intelligence officers. The officials of both countries knowingly violated international conventions. It is not legal or convenient to intervene in eternal matters of a sovereign country whatsoever. Consequently, the act of Yemeni officials will sure distress the upcoming relationships of the countries. Nonetheless, as the regime didn’t let the public and his family know his whereabouts for 16 days, the matter has been viewed suspiciously in our party, in the public at large and in the international community. It is our concern that he could be ill treated and more. Therefore, Blue Party strongly demands that Andargachew Tsege must be treated moderately and that all his rights under custody are respected.

2- The regime also illegally arrested prominent figures of Ethiopian politicians on July 8. The detainees are members and leaders of parties who are engaged in peaceful struggle. In fact it is not surprising to hear such news; however, we have learned that the regime is anxious and is trying to connect the detainees with rebel forces so that it hopes it can crack down the peaceful struggle before the 2015 election for they could be a threat to its power. It is clear that the dictatorial rule wants to stay in power more through spreading fear among the society. Thus its desperation is leading its ego to arrest one of our members and three other party leaders. Blue Party’s National Council Vice Chairperson Mr. Yeshiwas Assefa, Mr Habtamu Ayalew(Head of Public Relations Affairs of UDJ), Mr. Daniel Shibeshi(Vice Chairman of Organizational Affairs of UDJ) and Arana Tigray’s executive committee member and activist Mr. Abraha Desta are detained for activism and peaceful struggle. All these figures have been engaged in promoting peaceful struggle within the rule of law. Their arrest boldly hints that the regime’s final days in power are counted and change is inevitable in the near future. Hence, Blue Party demands an immediate release of the detainees and as well advocate the regime to stop the state terror. We condemn that TPLF/EPRDF comes to its sense and do what’s right for themselves and the country before it’s too late.
Finally we make sure that the act of state terror by TPLF/EPRDF will not hinder us for an inch from the none-violent struggle we are committed to. We have come into the decision that the offensive and atrocious act of TPLF/EPRDF required us to bring the struggle to the next level. Hence, we call upon the Ethiopian people to be ready to a nationwide movement and make sure that Blue Party is fully committed to provide the leadership needed at its unsurpassed. The Party also calls the peaceful parties, international institutes, human right activists, civic societies for all Ethiopian born and Ethiopians to stand together.

Long live Ethiopia
Blue/Semayawi Party Ethiopia
July 10, 2014

የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር

$
0
0
በብራዚል በመካሄድ ላይ ባለውና ፣ የፊታችን እሁድ በሚያከትመው የዘንድሮው የዓለም የአግር ኳስ ዋንጫ ውድድር፣ ትናንት ማታ በተካሄደው ሁለተኛው የግማሽ ፍጻሜ ውድድር አርጀንቲናና ኔደርላንድ በ9o ው ደቂቃ ጨዋታና 30 ደቂቃም ተጨምሮ ባለመሸና…

የሶማልያ የፀጥታ ኀላፊዎች ሹም -ሽር

$
0
0
የሶማልያ ጠ/ሚንስትር አብዲዋሊ ሼክ አህመድ ሙሐመድ፣የብሔራዊ ደኅንነት ድርጅት ሹም የነበሩትን በሺር ጉቤንና የፖሊሱን ኃይል አዛዥ አብዲከሪም ዳሒርን በመሻር በምትካቸው፤ በብሪታንያ የሶማልያ አምባሰደር የነበሩት…

የህወሃቱ የስለላ ሃለፊ ታሰረ

$
0
0

ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት አባል የሆነውና በሶማሊ ክልል የደህንነት ሃለፊ በመሆን ሲሰራ የነበረው መቶ አለቃ አወጣሃኝ በክልሉ ፕሬዚዳንት ትእዛዝ እንዲታሰር ተደርጓል።

ግለሰቡ በምን ምክንያት እንደታሰረ ለማወቅ ባይቻልም፣ በክልሉ ፕሬዚዳንት እና በህወሃት የጸጥታ ሰራተኞች መካከል እየተካረረ የመጣው አለመግባባት ማሳያ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

ታዋቂዎቹ ፖለቲከኞች በማእከላዊ እስር ቤት መታሰራቸው ታወቀ

$
0
0

ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌደራል ፖሊሶች እየተደበደበ ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስዶ የነበረው ታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ ማእከላዊ እስር ቤት መታሰሩ ታውቋል። የአብረሃ መኖረያ ቤት በፖሊሶች እንደተፈተሸም ለማወቅ ተችሎአል።

የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ዳንኤል ሽበሺ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ሲገለጽ፣ ዜናውን እስካቀረብንበት ጊዜ ስለተከፈተባቸው ክስ ለማወቅ የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

በኢትዮጵያ ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው እንዲሁም የተቃውሞ የፖለቲካ ድርጅቶችን በመቀላቀላቸው የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከመቼም ጊዜ በላይ ጨምሯል።

አቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ተከትሎ ኢትዮጵያውያን  ቁጣቸውን መግለጽ ቀጥለዋል

$
0
0

ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ሰሞኑን ከአገር ቤት በሚደወሉ ስለኮች የተጨናነቀ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ደዋዮች የኢህአዴግን

ስርአት በሃይል ለመፋለም መቁረጣቸውን የሚገልጹ ናቸው።

እንደሰሞኑ ሁሉ ” መንገዱን አሳዩን እና አቶ አንዳርጋቸው ይዘውት የተነሱትን ራእይ እውን እናድርገው ” የሚሉ ወጣቶች እየተበራከቱ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ ህዝቡ

ራሱን እያደራጀ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባው እያሳሰቡ ነው።

አንድ አስተያየት ሰጪ መንግስት ህዝቡን ለማረጋጋት በሚል አቶ አንዳርጋቸውን በቴሌቪዥን ማሳየቱን ገልጸው፤ ህዝቡ በዚህ ሳይዘናጋ ፣

ባርነትን ከራሱ ለማውረድ ከፈለገ የራሱን እርምጃ መውሰድ መጀመር አለበት ብለዋል።

ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በየትና እንዴት እንደሚታገል ፍንጭ ነው ያጣው ካሉ በሁዋላ፣ ስራውን መጀመር አማራጭ የሌለው ነገር ሲሉ አክለዋል።

“አንድ ቀን ቀን ይወጣል ብለን” ስንጠብቅ ከርመናል ያሉት አንድ አስተያየት ሰጪ፣ ከእንግዲህ የምንጠብቀው ምንም ነገር የለም፣ ሁሉም ደምቷል ብለዋል።

“እኛም ሴቶች ብንሆን ለትግሉ ብዙ የምናግዘው ነገር ይኖራል” ያለችው አንዲት የራያ ቆቦ ነዋሪ፣ ለነጻነት የሚደረገው ትግል ወደፊት መቀጠል እንዳለበት ገልጻለች።

በሌላ በኩል ደግሞ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መግለጫዎችን ማውጣት የቀጠሉ ሲሆን፣ የተቃውሞ ሰልፎችም በተለያዩ አካባቢዎች እየተደረጉ ነው።

የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ህብረት ግንባር ወይም በእንግሊዝኛው አርዱፍ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ቁጣውን ገልጿል።

የመን ህገወጥ በሆነ መንገድ አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፋ መስጠቷን በጽኑ ያወገዘው አርዱፍ፣ የመን በፈጸመቸው ህገወጥ ተግባር ተጠያቂ መሆን አለባት ብሎአል።

አቶ አንዳርጋቸውን የመሰሉ የነጻነት ታጋዮችን በማሰር የነጻነት ትግሉ እንደማይቋረጥ የገለፀው አርዱፍ ፣ እንዲያውም ትግሉን የበለጠ እንድናጠናክር ያደርገናል ሲል አክሏል።

የአለማቀፍ ማህበረሰቡ፣ የእንግሊዝ መንግስትና  የኢትዮጵያ ሃይሎች በሙሉ ለአቶ አንዳርጋቸው መለቀቅ አበክረው እንዲሰሩ አርዱፍ በመግለጫው ጠይቋል።

በብሪዝበን አውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን ጋዜጠኛ ኤልሳ ይመኑ ከስፍራው ዘግባለች።

በፊንላንድየሚገኙኢትዮዽያውያንእናትውልደኢትዮዽያውያን ደግሞ ሄልሲንኪ  በሚገኘው የ እንግሊዝ

ኤምባሲ በመገኘት ያዘጋጁትን ደብዳቤ አስረክበዋል። ኢትዮጵያውያኑ በደብዳቤው የየመን መንግስት የፈፀመውን ታሪካዊና ይቅርታ  የማያሰጥ ተግባር በጽኑ አውግዘው

የየመን መንግሥት አለም አቀፍን ሕግ ጥሶ ለፈፀመው ሕገወጥ ተግባር በተለያዩ መንገዶች እና  ግዜያት ዋጋ እንደሚያስከፍለው አስታውቀዋል ።

የእንግሊዝ  መንግስትም  አቶ አንዳርጋቸው  ጽጌ ዜጋው  ስለሆኑ ፣ ሰብአዊ   መብታቸው  ስለተገፈፈ እንዲሁም የህወሓት አገዛዝ በቶርቸር እና ሰብአዊ መብት ረገጣ  አለም አቀፍ

ድርጅቶች ባረጋገጡት መሠረት የታወቀ በመሆኑ ባስቸኳይ ተለቀው እንግሊዝ ሀገር ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ የእንግሊዝ  መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ ባፋጣኝ እንዲሰሩ ጠይቀዋል ።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አምባገነን አገዛዝ፣የሰብአዊ መብት ረገጣ ፣ግድያ የሚዲያ አፈና፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አለመከበር የእንግሊዝ መንግሥት ዝም

ብሎ ማየቱን ከቀጠለ ወይንም ጠንካራ አቋም የማይወስድ ከሆነ ለጊዜያዊ ጥቅም ብሎ ዘለቄታዊ

የሆነውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና የእንግሊዝ ብሔራዊ ጥቅም ስለሚጎዳ እንግሊዝ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን የውጭ ጉዳይ ፓሊስ እንደገና ባትክሮት እንድትመረምረው ጠይቀዋል ።

ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና –ጁላይ 10, 2014

$
0
0
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

UTC 16:00 የዓለም ዜና 10.07.14

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎችን በማፈንና በማሰቃየት ብሎም በመግደል የአፈና አገዛዙን ለረጅም ጊዜ ሲያራምድ መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እስራትና ግድያውን ህጋዊ ለማስመሰል የተለያዩ አፋኝ አዋጆችን አውጥቷል፡፡ እነዚህን አዋጆችንም ተገን አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባለትን፣ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን፣ እንዲሁም የእምነት ተቋማት መሪዎችን እና በአገዛዙ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ማሰሩን፣ ማሰቃየቱንና ግድያውን ተያይዞታል፡፡

በህገ መንግስቱ የተካተቱ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በሙሉ የሚጥሰውና የአምባገነንነት ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ያፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ ከፀደቀበት እለት አንስቶ ኢህአዴግ ለስልጣኔ ያሰጉኛል የሚላቸውን ፍፁም ሰላማዊ ታጋዮችንና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው በድፍረት የፃፉ ጋዜጠኞችን ብሎም የእምነት ነፃነታችን ይከበር ብለው የጠየቁ የሀይማኖት መሪዎችን በጠራራ ፀሃይ ያለምንም ወንጀል በዚሁ ህገ ወጥ አዋጅ ‹‹የፀረ ሽብር ግብረ ሀይል›› በሚባል ማንነቱ በማይታወቅ የጨለማ ቡድን ወደ እስር ቤት እያጋዘ ይገኛል፡፡

ይህን የሚያጋልጡ ሚዲያዎችንም ለማፈን እስር ቤቶችን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያፈሰሰ የአየር ሞገድ ያውካል፤ በዚህ ሳያበቃ በሀገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ ፖለቲከኞችን ለማሸማቀቅ እንደ ኢሳት ያሉ ሚዲያዎችን የአሸባሪ ልሳን ብሎ በመፈረጅ ሚዲያውን የሚጠቀሙትን ደግሞ ከአሸባሪዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው አድርጎ መወንጀሉን ቀጥሎበታል፡፡ እንደሰማያዊ እምነት ማንም አካል መልእክት የሚያስተላለፍበትን የሚዲያ ተቋም ሊመርጥለት እንደማይችል መንግስት እንዲገነዘበው ከዚህ በፊት በግልፅ ያሳወቀ ሲሆን አሁንም ፓርቲው በዚሁ የፀና አቋሙ እንደሚቀጥል በድጋሚ ይገልፃል፡፡

ባጠቃለይ የዚህን ገዢ አካል የእውር ድንብር ሀገር የማስተዳደር ጉዞ ለመታገል በርካቶች በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም በህወሓት/ኢህአዲግ ግፍና መከራ ተገፍተው ስርዓቱን በሃይል እናስወግዳለን ብለው ሀገር ጥለው የተሰደዱ ዜጎችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የህወሓት/ኢህአዲግ ማናለብኝነትና የስልጣን ጥመኝነትም በግለሰቦች ላይ ከሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ በላይ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትን አስከትሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ይህ ገዢ ፓርቲ የፈጠረው ስርዓት የሀገሪቷን ሰላማዊ የፖለቲካ ምህዳር በማጥበብ ሀገራችንን ወደ አልተፈለገ አለመረጋጋትና ቀውስ እየመራት ይገኛል፡፡ፓርቲያችንም እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም በቅርቡ እየተፈፀሙ የሚገኙ ህገ ወጥ ድርጊቶች ስላሳሰበው ይህን መግለጫ ለማውጣት ተገዷል:-

1. ሰኔ 16 2006 ዓ.ም የየመን መንግስት የዓለም አቀፍ ስምምነቶችንና ድንጋጌዎችን በመጣስና በሰው ሀገር የውስጥ ጉዳይ በመግባት የአማፂ ቡድን ግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዟ ይታወሳል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ለህወሓት/ ኢህአዴግ ተላልፈው መሰጠታቸውን ከ16 ቀናት በኋላ መታወቁና ይህንንም ሁለቱ ሀይሎች ማመናቸው ተሰምቷል፡፡ ነፃነት በሌለበት ሀገር ዜጎች ሰብዓዊ ክብራቸውን ለማስጠበቅ የሚያደርጉት ጥረት የሌሎች ሀገር መንግስታት የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በዓለም አቀፍ ስምምነቶችም ሆነ በተለይ በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ጥላ የሚያጠላ መሆኑን ግንዛቤ አለመወሰዱ እጅግ የሚያሳዝን ድርጊት ነው፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከተያዙ በኋላ ላለፉት 16 ቀናት በምን አይነት ሁናቴ እንደቆዩ ህዝብና ቤተሰቦቻቸው እንዲያውቁት አለመደረጉ፤ ስለ አያያዛቸው ሁኔታም በማህበረሰቡና በፓርቲያችን ውስጥ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዲኖር አድርጓል፡፡ሰማያዊ ፓርቲ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሰብዓዊ አያያዝ እያሳሰበው ህወሓት መራሹ የኢህአዴግ አገዛዝ አያያዛቸውን ግልፅ እንዲያደርግ ሰብዓዊ ክብራቸውም እንዲጠበቅ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

2. በዚሁ ሳምንት ገዢው ፓርቲ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የአምባገነኑን መንግስት ህወሓት/ኢህአዲግን ሲታገሉ የነበሩ ፖለቲከኞችን በስመ አሸባሪ ከያሉበት እየለቀመ ህገ-ወጥ እስራት መፈፀሙ ይታወቃል፡፡ ህወሓት/ኢህአዲግ ይህ ግብታዊ ተግባሩ ምንም እንኳን አዲስ ባይሆንም በአሁኑ ወቅት ለውጥን ለማምጣት በቆራጥነት እየታገሉ ያሉ ሰላማዊ ታጋዮችን ማሰሩ በሀገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ፓርቲዎችን ከአማፂ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው በማስመሰል ሰላማዊ ትግሉን ለማዳከምና መጪውን 2007 ዓ/ም ምርጫ ያለ ተቀናቃኝ ለማለፍ የሚደረግ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ የፓርቲያችን ብ/ም/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሺዋስ አሰፋ በሰላማዊ ትግሉ በቁርጠኝነት እየተሳተፈ ባለበት ሁኔታ ለእስር መዳረጉ፤ የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄን በመፍጠር ላይ ያለው የአረና /ትግራይ/ ፓርቲ አመራር አባል የሆኑትን አቶ አብረሃ ደስታ ለእስር መዳረጋቸው ህወኃት/ኢህአዴግ የመጨረሻው መጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ያረጋግጣል፡፡ በመሆኑም አገዛዙ እያካሄደ ያለውን መንግስታዊ ሽብር አቁሞ ለሀገርም ሆነ ለራሱ የሚበጀውን መንገድ እንዲከተል እያሳሰብን የታሰሩት የፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡

3. በመጨረሻም ፓርቲያችንን መንግስት እያደረገ ያለው ሽብርን የመንዛትና ህግን የመጣስ ተግባሩ መቼም ቢሆን ከሰላማዊ ትግሉ እንደማያቆመውና ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በአፅንኦት እየገለፀ እነዚህንና ከላይ የተጠቀሱትን የገዢውን ፓርቲ መርህ አልባነት፣ ህገ-ወጥነት እና የለየለት አምባገነንነትን አሁን ካለው ነባራዊ እውነታ ጋር አጣምሮ የትግል ስልቱን ደረጃ ከፍ ወዳለ ምዕራፍ ማሸጋገር እንዳለበት አምኗል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ለምናደርጋቸው ሀገር አቀፍ ንቅናቄዎች መላው የሀገሪቱ ህብረተሰብ በንቃት ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ ጥሪውን እያስተላለፈ ለዚህም ቁርጠኛ አመራር ለመስጠት ዝግጁነቱን ለመግለፅ ይወዳል፡፡በዚህ አምባገነንነትን ለመታገል በሚደረገው ንቅናቄም በሀገር ውስጥ የሚገኙ ህጋዊና ሰላማዊ ፓርቲዎች፤አለም አቀፍ ተቋማት፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ሲቪክ ማህበራት፤ መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሰላማዊ ትግሉ ጎን በጋራ እንድንቆም እንጠይቃለን፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
ሰማያዊ ፓርቲ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም

በወጣት ሰላማዊ ፖለቲከኞች መታሰር ዙሪያ ኢትዮጵያዉያን ከሰጡት አስተያየት ጥቂቶቹ

$
0
0

ሰላማዊ ሰዎችን ማሰር ቀለቡ ያደረገው መንግስት፣ በትላንትናው እለት ከአንድነት ፓርቲ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ ከአረና አቶ አብርሃ ደስታ እንዳሰራቸው ተነግሯል። ይህንን በመቃወም በፌስቡክ ኢትዮጵያዉያን ካሰፈሩት መካከል ጥቂቱን እንደሚከተለው ቀንጭበን አቅርበናል፡

ያሬድ አማረ፡
«ወደኋላ አንመለስምዘመን ተሻጋሪ ወጣቶች በቅለናልና በምንም መልኩ ለሚደረግ ማዋከብ፤እስራት እና ግድያ ከጀመርነው የሰላማዊ ትግል መስመር ስንዝር አንዛነፍም፡፡ደግሞም አምባገነኖች ባሉበት ሀገር የጀግና ቤቱ እስር ቤት አልያም መካነ መቃብር ውስጥ ሊሆንም እንደሚችል ስንጀምር ያለአስረጂ እናውቃለንና»

Beyo Te ፡
«አብረሃ ደስታ ለዲሞክራሲ ተሰዋ!!!… ሺ የምትወልድ እናት አትንጠፍ!!! ትግሉ ይቀጥላል ኢህአዴግ ይወድቃል!!»

Tigist Alemneh፡
«እንዴት ቢያሰፉት ነው፣ እንዴት ቢገነባ፤
ጉሮኖው ‘ማይሞላ፣ እልፍ ሠው ሲገባ? »

Jomanex Kassaye
«ኢህአዴግ አበቃለት ስለተባለ አያበቃለትም ዛሬ ለእስር ፊት ከሰጠኸው ነገ ከመግደል ላለመመለሱ መተማመኛ የለንም፡፡»

Abebe Tolla
«ኢሃዴግ አበደች ጨርቋን ቀዳደደች
ያንንም ይሄንም ሁሉን ልያዝ አለች፤
እንጃልኝ መዳኗን
ከንግዲህ በኋላ…
ምንም ደስ አላለኝ
እንደው አኳኋኗ… »

Tewodros Belay
«በነውሩ የሚኮራ አገዛዝ ዜጎቼን አሰርኩ እያለ ሲፎክር ያመሻል። የጉድ ሀገር !»

Homa Keno
«ኢህአዴግ ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱን በኃይል ሊንዱ ነበር እያለ ንፁሃንን ዘብጥያ ባወረደ ቁጥር በለየለት ውንብድናና እብሪት ላይ የመሰረተው ሥርአት እየተናደ መሆኑ የገባው አይመስልም …. ደሞ አያፍርም ብሶት ወለደኝ ይለናል» Eshetu

Joe Man Mergu
«የሺ ሰው ግምት! እኔ አብርሃ ደስታን አሰሩት አልልም፤ አሰሯቸው እንጂ»

Beti Abrhem
«ጧት ማታ ሲጠጉን ከተሰማን ሽብር
“ሀገር ” ምን ሊረባን አለን ማለት ይቅር»

Ya Red
«ማእከላዊ ተወስደህ ቶርች ስትገለበጥ አይደለም ግንቦት 7 ‘ዿግሜ 7 ነህ’ ካሉህ ታምናለህ»

Nebiyu Hailu
«ጨቋኞችን መታገል ፅድቅ እንጂ ኩነኔ እንደሌለው አምናለሁ፤ ጭቆናን እምቢ በማለቴ የምጠጣት እያንዳንዷ ፅዋ በፈጣሪ ዘንድ ወሮታ እንደምታከማችልኝም አምናለሁ፡፡ ፍርሀትን ብቻ እፈራለሁ » Nebiyu Hailu

Emmii Solomon
«ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ለምን ጻፋቹህ ለምን ያገባናል አላችሁ ተብለው አሁን በየስር ቤቱ የታጎሩትና በየጊዜው እያጠለጠሉ የሚወስዷቸው ስንት ናቸው ? ስንቱን ከሃገር አሰደዱ ? ማነው አሸባሪው ታዲያ ?» Emmii Solomon

Jeremiah De II
«ውሻው ከእብደቱ ሊድን ባለመቻሉ ንክሻውን እንደቀጠለበት ነው!! »


አቶ ብዙነህ ፅጌ (የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ወንድም) ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ ሙሉ ቃል –ጁላይ 10, 2014

አቶ ብዙነህ ፅጌ (የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ወንድም) ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ –ዘገባ –ጁላይ 10, 2014

የተቃዋሚዎቹ መሪዎች ዛሬም ፍርድ ቤት አልቀረቡም –ጁላይ 10, 2014

$
0
0
arrested opoosition leaders not taken to court  …

አቡጊዳ – አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታፈኑት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሳይነገራቸው ነው ተባለ

$
0
0

ኢትዮጵያ ሪቪው ምንጮቹን ጠቅሶ ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የታፈኑት፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሳያወቁት ፣ በአቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የሕወሃት ደህንነት ጽ/ቤት እና በአቶ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ዉሳኔ እንደሆነ ዘገበ። ሁለቱ የሕወሃት ባለስልጣናት፣ የሆነውን ነገር ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ለመንገር እንኳን ደንታ እንደልነበራቸው ኢትዮጵያ ሪቪው፣ እነ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን እንደ አለቃቸው ሳይሆን እንደ «አህያቸው» እንደሚመለከቷቸው በዘገባው አስፍሯል።

«ያለ እንግሊዞች ትብብር፣ የየመን ደህንነቶች የእንግሊዝ ፓስፖርት ያለው ሰው፣ ያለ እንግሊዞች አዎንታ የመያዙ እድል በጣም ትንሽ ነው» ሲልም የእንግሊዝ ደህንነት በጉዳዩ ላይ እጁ ሊኖርበት እንደሚችል ኢትዮጵያ ሪቪዉ አክሎ ገልጿል።

የእንግሊዞች እጅ እንዳለበት በኢትዮጵያ ሪቪዉ የቀረበው ግምት እንደተጠበቀ፣ በተለያዩ መድረኮች ሌሎች ግምቶችም እየተሰጡ ነው። የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ወይንም አስመራ ባለው የግንቦት ሰባት መዋቅር ዉስጥ ያሉ አመራሮች፣ የአቶ አንዳርጋቸውን የጉዞ መረጃ አስቀድመው ለሕወሃት ደህንነቶች በመስጠታቸው፣ አቶ አንዳርጋቸው ሊያዙ እንደቻሉም የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም።

«አቶ አንዳርጋቸውን ማን አስያዛቸው ? » ለሚለው ጥያቄ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለበት መልኩ የግንቦት ሰባት ድርጅት፣ ምላሽ መስጠት እንዳለበትም ብዙዎች ይናገራሉ።

የኢትዮጵያ ሪቪዉን ዘገባ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !

የተቃዋሚ ፓርቲዎች አራት አመራር አባላት መያዝ – የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘገባ

Viewing all 13695 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>