Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all 13695 articles
Browse latest View live

ወግ ቀማሪው ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም አረፉ

$
0
0

ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም Mesfin HabtemariamEthiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. July 15, 2014)፦ ከአቶ ሀብተማርያም ሞገስ እና ከወ/ሮ ደስታ አየለ በ1935 ዓ.ም. የተወለዱት ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም እሁድ ሐምሌ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. በ71 ዓመታቸው በአዲስ አበባ ከተማ አረፉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...


ኡመተ ፈናን ኡመተ ቀሽቲ ዲሬ ዳዋ

$
0
0
(አርቲስቱና ሽቅርቅሩ የድሬዳዋ ሕዝብ)

ደራሲ፡- አፈንዲ ሙተቂ
የገጽ ብዛት፡-191
ዋጋ፡- 60 ብር
የኅትመት ዘመን፡- 2006 ዓም
አፈንዲ ሙተቂ ያበረከተልንን መጽሐፍ አነበብኩት፡፡ ከአዋሽ ወዲያ ማዶ ያለውን ሀገራችንን ሙልጭ አድርገን ለማወቅ የሚጎድለን ነገር መኖሩን የምንረዳው የእርሱን መጽሐፍ ስናነብ ነው፡፡ እንኳን እንደ እኔ በጎብኝነት የሚያውቀው ቀርቶ ተወልጄበታለሁ አድጌበታለሁ የሚለው ሁሉ የቀበሌ መታወቂያውን እንደገና እንዲያወጣ የሚያደርግ መጽሐፍ ነው፡፡
ሰው የሚያውቀውን ሲጽፍ ወይም የሚጽፈውን ሲያውቅ እንዲህ ያለ መጽሐፍ ይገኛል፡፡ ባሕሉ አልቀረ፣ ትውፊቱ አልቀረ፣ አባባሉ አልቀረ፣ ታሪኩ አልተዘለለ፣ መልክዐ ምድራዊ መረጃው አልተዘነጋ፣ አፈ ታሪኩ ቦታውን አልሳተ፣ ሁሉም በመልክ በመልኩ ተሰድሮ እንደ መልካም የወታደር ሠልፍ የቀረበበት መጽሐፍ ነው፡፡

አፈንዲ ለአካባቢው ወግና ታሪክ ቅርበት ብቻ ሳይሆን ፍቅርም እንዳለው፣ ፍቅር ብቻም ሳይሆን ጥናትም እንዳለው፣ ጥናትም ብቻ ሳይሆን ትኩረትም እንዳለው መጽሐፉ ያሳየናል፡፡ የሕዝቡን ፍቅርና አንድነት፣ መተሳሰብና አብሮነት፣ የቆየውን የመተጋገዝ ልማድና ተግባቦት ያሳየባቸው ወጎቹ የመለያየት ጥላ ላጠላበት ህልውናችን ፈዋሾ ናቸው፡፡
በተለይም የሐረርጌ ኦሮሞን ትውፊትና ባሕል፣ የአስተዳደር ታሪክና ዕምቅ ብቃት ያሳየበት ጹሑፉ እዚያው ሕዝቡ ውስጥ ያለን ያህል እንድንረዳው የሚያደርግ ነው፡፡ አፈንዲ የአካባቢውን ነገር ሲነግረን በአንዳንዶች ዘንድ እንደሚታየው እንድንጠብ አድርጎ ሳይሆን እንድንሰፋ አድርጎ ነው፡፡ ያንን አካባቢ ከእኛ ውጭ አድርገን እንድናየው አድርጎ ሳይሆን ውስጡ እንድንገባበት አድርጎ ነው፡፡
አፈንዲ ሦስት ነገሮች አሉት፡፡ ርትዕ፣ ዕውቀትና የኃላፊነት ስሜት፡፡ ነገሮችን ያየበት መንገድ ርትዕ እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡ በአካባቢው ለተደረጉ ነገሮች ሁሉ ሃይማኖትና ዘርን ሳይለይ ለሁሉም የድርሻውን ሰጥቷል፡፡ የተለያዩ እምነቶች፣ ባሕሎችና ግለሰቦች በአካባቢው የነበራቸውን በጎ ሚና ለማጉላት፣ ክፉውንም በጨዋነት ለማረም ያደረገው ጥንቃቄ የሚያስመሰግነው ነው፡፡
አፈንዲ በተለይ ከአዋሽ ማዶ ስላለው ታሪክ፣ ባሕል፣ ትውፊትና መልክዐ ምድር ለሌላውም ሊተርፍ የሚችል ዕውቀት ስላለው የሚጽፈው የቃላት ስብስብ አይደለም፡፡ በእያንዳንዱ ቃል ላይ ዕውቀት ያዘለ ነገር አለው፡፡ የሚጽፍ ሰው የሚጽፈው ነገር የት እንደሚደርስ አያውቅምና በኃላፊነት ስሜት እንዲጽፍ ይመከራል፡፡ አፈንዲ በዚህ መጽሐፉ በእምነቶች፣ በሕዝቦች፣ በጎሳችና በፖለቲካ መሪዎች መካከል ተግባቦት ይፈጠር ዘንድ፣ መደናነቅና መከባበር እንዲኖር የሚያደርጉ ሐሳቦችን በኃላፊነት መንፈስ ጽፏል፡፡ ‹‹እንዴው ዘራዋ›› የሚል ነገር አላየሁበትም፡፡ ታላቅ ችሎታና ብስለት ነው፡፡
አንቡት፡፡ ታውቃላችሁ፣ ትዝናናላችሁ፣ ትጨምራላችሁ፡፡

የዞን 9 ጦማርያን አና ጋዜጠኞች የማእከላዊ ምርመራ የተፈጻመባቸው ምርመራ መጠናቀቅ

$
0
0


#Ethiopia #FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw #FreeAllPoliticalPrisoners

ትላንትና ያለምንም ክስ ድፍን 80 ቀን የሞላቸው የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ጓደኞቻቸን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ ያካሄደውን ምርመራ መጨረሱን ፓሊስ በጓሮ በኩል ፍርድ ቤትበመቅረብ አሳውቋል፡፡ ቅዳሜ እለት 28 ቀናት የምርመራ ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደፍርድ ቤትከመሄዳቸው ከቀናት አስቀድሞ ከነበሩበት የጨለማ ክፍል እስር በተለምዶው ሸራተን ወደሚባለው ቦታ የተዘዋወሩት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላለፉት ጥቂት ቀናት በወዳጅ እና ጓደኛም ጭምር መታየት ችለዋል፡፡ 

ቅዳሜ በመቶዎች ተሰብስበው የሚጠበቁበት ችሎት ላይ ፓሊስ ብቻውን በመገኘት እና ጠበቃውን ባላካተተ ከዳኛ ጋር የተደረገ ንግግር የፓሊስ የምርመራ ፋይሉን በማጠናቀቁ ወደ አቃቤ ህግ ማስተላለፉን እና ክሱም በከፍተኛውፍርድ ቤትአንደሚታይ በማመልከት የጊዜ ቀጠሮ ፋይሉ አንዲዘጋ ጠይቋል፡፡ ታሳሪዎችም ሆነ የህግ ጠበቃቸው ባልተገኙበት ፍርድ ቤቱ የፓሊስን ጥያቄ ተከትሎ ፋይሉ የተዘጋ ሲሆን ከሰአታት ጥበቃ በኋላ በመዝገብ ቤት በኩል ጠበቃቸውና ወዳጆች ፋይሉ መዘጋቱን ለማወቅ ችለዋል፡፡ 

በተመሳሳይ ሁኔታ ትላንት ሰኞ ይቀርባሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩት ሌሎች ሶስት የዞን 9 ጦማርያንም ፓሊስም ሳይቀርቡ ፓሊስ በጻፈው የሶስት መስመር ደብዳቤ ምርመራ መጨረሱን አና ለአቃቤ ህግ ማስተላለፉን አሳውቋል፡፡ በመሆኑም የጓደኞቻችን ሆኑ ፓሊስ ባልተገኙበት የትላንትናው ሂደትን አስከትሎ የጓደኞቻቸን ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንን ክሱን በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ለደንበኞቻቸው አንደሚሰጥ እነደሚጠብቁና እሳቸው ባሉበት መከናወን እነዳለበት ገልጸዋል፡፡ የፓሊስን አሰራር የወንጀል ስነስርአት ህግን ያልጠበቀ ድብብቆሽ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ጓደኞቻችን ቀድሞ የነበሩት የእስር ቦታ በቀን ሁለት ጊዜ 15 ደቂቃ ወደውጪ ለመናፈስ ከመውጣት ባሻገር ምንም ከውጪው አለም ጋር የመገናኘት እድል ሳይኖራቸው ከሁለት ወራት ከግማሽ በላይ ካሳለፉበት ጊዜ በመገላገል ሊጠየቁ ወደሚችሉበት ቦታ መዘዋወራቸውን ተከትሎ በጠንካራ ሞራል አና አካላዊ ደህንነት ላይ አንደሚገኙ ለመረዳት ችለናል፡፡ በቦታው ለጎበኙዋቸው ወዳጆች አንደተናገሩትም ሁሉም ራሳቸው ላይ ጥፋተኝነትን የሚመሰክር ቃል ላይ የፈረሙ ሲሆን ጦማሪ አቤል ዋበላ ለመፈረም ፍቃደኛ ባለመሆኑ እስካሁን ሌሎች ሊጎበኘት የማይችሉት ቦታ ላይ አንደቆየ ታውቋል፡፡ 

የተከሰሱት አና ምርመራ እየተካሄደባቸው ያለው በጻፏቸው ጽሁፎች አይደለም የሚል ክርክር ሲያቀርብ የነበረው ፓሊስም ጽሁፎቻቸውን ማስረጃ አድርጎ እነዳስፈረማቸው ገልጸውልናል፡፡ ለምሳሌ ያህል ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የሪፓርተር ጋዜጣ ሁለት ዜናዎችን በማጋራቱ ብቻ መስረጃ ተብሎበት አንዲፈርም የተገደደ ሲሆን ዜናው የመከላከያ የብሄር ተዋእጾን አና አዲሱን የይቅርታ አዋጅን የሚመለከት ሲሆን ጦማሪ በፍቃዱ ስለለውጥ የሚለው በዞን9 ላይ የተጻፉ ተከታታይ ጽሁፎቹ እነዲሁም ጦማሪ ዘላለም ክብረት ህግ መንገድ ወይስ ምርኩዝ እና ሳንሱር ድሮና ዘንድሮ የሚሉት ጽሁፎች ይገኙበታል ፡፡ 

የዞን 9 ጦማርያን በጠንካራ አካላዊና መንፈሳዊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን አላአግባብ እስሩን ተከትሎ በተለያየ መልኩ አጋርነታችሁን ላሳያችሁ የዞን 9 ነዋሪያን እና የሰብአዊ መብት ጠበቆች ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በምርመራ ወቅት በተደጋጋሚ የተፈጸመባቸው የመብት ጥሰትም ሃሳባቸውን መግለጻቸው ትክክል መሆኑን ያረጋገጠላቸው መሆኑን አስታውሰው መጪውን የህግ ሂደት ለመከታተል እና ለታሪክ ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ 

ዞን 9 ጦማርያን ስብስብ በምንም ድብቅ ህገ ወጥ ድርጊት ውስጥ ተሳትፈን አንደማናውቅ እና ጦማሪ ጓደኞቻችን አንዲፈቱ መጠየቃችንን እንደማናቆም እያስታወስን መጪውን የህግ ሂደት በሚገባ ለመዘገብ እና የፍትህ ስርአቱን ለመፈተሽ ዝግጁ መሆናችንን በድጋሚ አንገልጻለን፡፡ 
የጦማሪ በፍቃዱና ዘላለም ጽሁፎች ሊንክ ከስር ይገኛል፡፡

--- ኢህአዴግ ሰልጣኑን በምርጫ ይለቃል?


---ለውጥን መቋቋም እና ለውጥን መፍራት


---የሥርዐት-ለውጥ-እና-ሃይማኖቶች

 

--- -የ66 ቱ አብዪቶች እና የነጻ ማህበራት ፋይዳ  

----ሳንሱር አና ህግ ትላንትና እና ዛሬ

 

--- ሕግ ምርኩዝ ነው ዱላ ? 

--- አብዩት ወይስ አዝጋሚ ለውጥ 





Early Edition –ጁላይ 15, 2014

ደራሲ መሥፍን ተቀበረ

$
0
0
መስፍን ሐብተማርያም በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ የወግ ፀሐፊ ነበር።በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ወጎችን የፃፈና ያሳተመ፤ ተርጓሚ፤ የሥነ-ፅሁፍ ሐያሲ እና አዲስ አበባና አሥመራ ዩኒቭርስቲን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት ያስተማረ የሥነ-ፅሁፍ ሰዉ ነበር።…

UTC 16:00 የዓለም ዜና 150714

የ«ብሪክስ» አባል ሃገራት እና ወቅታዊ ይዞታቸው

$
0
0
የብራዚል፣ ሩስያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪቃ ርዕሳነ ብሔር እና መራሕያነ መንግሥታት ከሁለት ቀናት በፊት የተጠናቀቀውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ባስተናገደችው ብራዚል ዛሬ የሁለት ቀናት ጉባዔ ይጀምራሉ።…

የጋዛ ግጭት

$
0
0
የጋዛ ግጭት ውዝግቡ ካለፈው አንድ ሳምንት ወዲህ ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል፣ ፍልሥጤማውያን ከጋዛ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሳቸውን፣ የእስራኤል ጦርም ጋዛን ማጥቃታቸውን ቀጥለዋል። በዚሁ መሀል እስራኤል እና…

ኤቦላ በምዕራብ አፍሪቃ

$
0
0
በኤቦላ ቫይረስ ወይም ተህዋሲ ከሚያዙ ሰዎች 90 በመቶዉ እንደማይተርፉ ነዉ መረጃዎች የሚያመለክቱት። ተህዋሲዉን የሚከላከልም ሆነ የሚያድን ክትባትም ሆነ መድሃኒት እስካሁን አልተገኘም። ኤቦላ ከዚህ ቀደም በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ፣ ሱዳን፣ ጋቦን፣ አይቮሪኮስትና ዩጋንዳ በተደጋጋሚ ተከስቷል።…

የአሜሪካንና የጀርመን የስለላ ቅሌትና ተፅእኖው

$
0
0
ዩናይትድ ስቴትስ ሁለት የጀርመን መንግሥት ሠራተኞችን ለስለላ መመልመሏ ከተደረሰበት በኋላ በበርሊን የአሜሪካን ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት CIA ተጠሪ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ጀርመን መጠየቋ በሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ ጥላ አጥልቷል። የጀርመን መንግሥት ፖለቲከኞች ጀርመንም ለአፀፋ ስለላ እድትዘጋጅ እየጠየቁ ነው።…

ተጫዋቾቹ በርሊን ገቡ

$
0
0
የቡድኑ አባላት በግልፅ መኪና ተሳፍረዉ ከበርሊን አዉሮፕላን ማረፊያ ዋናዉ ድግሥ-ሥፍራ ብራንደርቡርገር ቶር እስኪደርሱ ድረሥም በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ በመንገዶች ግራና ቀኝ በመሆን የጀግና አቀባበል አድርጎላቸዋል…

ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና –ጁላይ 15, 2014

$
0
0
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ለፀረ-ሽብር ግብረ-ኃይል አዛዥ ትዕዛዝ ተሰጠ –ጁላይ 15, 2014

$
0
0
Court orders to Ethiopia's Anti-terror chief…

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ እርዳታ ፖሊሲ ተግባራዊነት እንዲፈተሽ ታዘዘ –ጁላይ 15, 2014

$
0
0
Ethioia, villagization, UK High Court, Human Rights Watch…

ግብፅ ውይይቱ እንዲጀመር ጠየቀች –ጁላይ 15, 2014

$
0
0
Egypt requeste resumption of reneissance dam tripartite talks…

ግብፅ ውይይቱ እንዲጀመር ጠየቀች

$
0
0
ተቋርጦ የቆየውን የኅዳሴ ግድብ ግንባታ የሦስትዮሽ ውይይት እንደገና ለመጀመር ግብፅ መጠየቋን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል፡፡…

ለፀረ-ሽብር ግብረ-ኃይል አዛዥ ትዕዛዝ ተሰጠ

$
0
0
        የፌደራሉ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ሁለተኛ የፍትሐ ብሔር ችሎት በቅርቡ የታሠሩትን የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች በአርባ ስምንት ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት ስለማቅረቡ ማስረጃ እንዲያያይዝ ለፀረ-ሽብር ግብረ-ኃይሉ ኃላፊ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የተባለውን ማስረጃ ሐምሌ 10/2006 ዓ.ም እንዲያቀርብ ቀጠሮ መያዙን ጠቅሶ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን መለስካቸው አምሃ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡  

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ እርዳታ ፖሊሲ ተግባራዊነት እንዲፈተሽ ታዘዘ

$
0
0
የእንግሊዝ የባሕር ማዶ ትብብር ኤጀንሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ሲሰጥ ከራሱ የሰብዓዊ መብቶች ፖሊሲዎች ጋር በተጣጣመ መልክ መሆንና አለመሆኑ እንዲፈተሽ አንድ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዋች አድንቋል፡፡…

እስራኤል በጋዛ ላይ ያቋረጠችውን ድብደባ እንደገና ጀመረች

$
0
0

ሐምሌ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃማስና በእስራኤል መካከል የተጀመረው ጦርነት ፣ በግብጽ አደራዳሪነት ለሰአታት ጋብ ብሎ የቆየ ቢሆንም፣ እስራኤል ድብደባውን እንደገና መጀመሯን ቢቢሲ ዘግቧል።

በግብጽ የቀረበውን የሰላም ስምምነት እስራኤል ብትቀበለውም፣ ሃማስ ግን ስምምነቱ ሽንፈትን እንደመቀበል ይቆጠራል በሚል ሳይቀበለው ቀርቷል።

ይህን ተከትሎም እስራኤል የአየር ድብደባውን እንደገና ጀምራለች። እስካሁን በደረሰው ጥቃት ከ192 በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል፤ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩትም ቆስለዋል። በእስራኤል በኩል 4 ሰዎች በሃማስ ሮኬት መቁሰላቸው ታውቋል።

እስራኤል በምትሰነዝረው ወታደራዊ ጥቃት የሞቱት አብዛኞቹ ሲቪሎች መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል። እስራኤል ግን መረጃውን ታስተባብላለች።

የመኢአድና አንድነት ውህደት አመቻች ኮሚቴ የባንክ አካውንቱን ይፋ አደረገ – ፍኖተ ነጻነት

$
0
0

የመኢአድና አንድነት ውህደት አመቻች ኮሚቴ ስራውን በቅልጥፍና እና በትጋት እየተወጣ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚህም መሰረት ለጉባኤው መሳካት ይረዳ ዘንድ መላው ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩ ጥሪ በማድረግ የባንክ አካውንቱን ይፋ አድርጓል፡፡
የባንክ አካውንት ቁጥር UDJ A/C 47
የባንክ አካውንት ቁጥር AEUP SP 235udJAEUP

Viewing all 13695 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>