ESAT Radio: Aug 22
አዲስ አበበ ቢቂላ፣ አዲስ ምሩፅ ይፍጠር፣ አዲስ መሐመድ አማን
አዲስ አበበ ቢቂላ፣ አዲስ ምሩፅ ይፍጠር፣ አዲስ መሐመድ አማን –ኦገስት 23, 2013
ሰማያዊ ስሞታ አለው፤ መስተዳድሩ “ጥፋቱ የራሱ ነው” ይላል –ኦገስት 23, 2013
የሥላሴዎች እርግማን (ሦስት) ፦ አዳክሞ ማደህየት – ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ሐምሌ 2005
አንድ በጣም የተገረመ ደቡብ አፍሪካዊ ይህንን ሁሉ መንገድና ሕንጻ በአንድ ጊዜ ለማሠራት ገንዘቡን ከየት ነው የምታገኙት? ብሎ ጠየቀኝና ከወርቅ-ቡና አልሁት፤ ሳቅ አለና እኔኮ ከልቤ ነው የምጠይቅህ አለኝ፤ እንግዲያው ዘክዝኬ ልንገርህ አልሁት፤ ለወትሮው ብዙ የምክር ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም ለመንግሥትህ እንዳትናገርና የዚሁ ዓይነት ሥራ በደቡብ አፍሪካ እንዳይጀመር ቃል ግባልኝ አልሁትና ቀጠልሁ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በመንግሥት ባንኮች ደጃፍ ላይ የነበረውን መጨናነቅ አይተሃል ወይ? ብዬ ጠይቄው ማየቱን ካረጋገጥሁ በኋላ ጉዳዩን እንደሚከተለው አስረዳሁት፡፡
አገዛዙ መሬቱንም ሆነ ቤቶችን የራሱ ካደረገና ባለቤትነቱን ካረጋገጠ በኋላ በየመንገዱ ዳር እንጀራ፣ ዳቦ፣ ቆሎ፣ ጠላና ትናንሽ ነገር እየሸጡ ልጆቻቸውን የሚያሳድጉ ሴቶች፣ በየቤቱ እየሠሩ በነዚህ ቤቶች ተዳብለው ኪራይ እየከፈሉ የሚኖሩ ሴቶች በብዛት ነበሩ፤ በነዚህ ደሀዎች ላይ ቀበሌዎች በየጊዜው እየዘመቱ ቤቱ እንደሚፈርስባቸው እያስፈራሩ ደሀዎችን ያሸብራሉ፤ በዚህ ዓይነት ፍርሃትና ስጋት ውስጥ ለጥቂት ወራት ካቆዩአቸው በኋላ ክረምትን ጠብቀው በግድ ያስለቅቁአቸዋል፤ በዚህ ምክንያት በአዲስ አበባ ውስጥ የተፈናቃይ ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ በአንዲት ትንሽ ክፍል ውስጥ የሚኖረው ሰው ቁጥር እየበዛ ለጤንነት ክፉ ጠንቅ እየሆነ ነው፤ ይህ ችግርና ስቃይ ትልቅ የሀብት ምንጭ ሆኖአል፤ ደሀ የሚበላው አንጂ የሚከፍለው አያጣም፤ ነጭ ደሀ ነጭ ማር ይከፍላል፤ እነዚህ ባህላዊ አነጋገሮች ተጠንተው በተግባር ላይ እየዋሉ ነው።
እንዴት? ማለት ጥሩ ነው፤ እነዚህ (ቤቶቻቸው ከማለት ይልቅ) መጠለያዎቻቸው የፈረሱባቸው ሰዎች ከረሀቡ ሌላ በብርድና በጸሐይ በመጉላላታቸው የመጠለያ ችግራቸው በጣም ከባድ ስለሆነ በቀላሉ የሚበዘበዙ ናቸው፤ ችግሩን መፍቻ የሚመስል የደሀውን ነፍስ በጉጉት ሰንገው የሚይዙበት ኮንዶሚንየም የሚባል ማቁለጭለጫም አለ፤ ደሀ ሁሉ ኮንዶ አግኝቶ የሚያልፍለት ይመስለዋል፤ ስለዚህ ሁሉም ይፈልጋል፤ ስለዚህ የኮንዶ ፈላጊው ሰልፍ በጣም ረጅም ነው፤ ስለዚህ በመስገብገብ እየተተኮሰ ዋጋው በጣም ከፍ ያለ ነው።
ማፍረስ ከመገንባት የቀለለ ቢሆንም በአዲስ አበባ የሚካሄደው አብዛኛው የመገንባት ሥራም ከማፍረሱ ሥራ የተሻለ መሆኑ በጣም ያጠራጥራል፤ እንዲያውም የማፍረሱንም ሆነ የመገንባቱን ሥራ የሚመሩት የውጭ አገር (ምናልባትም የቻይና) ሰዎች ናቸው ለማለት ያስደፍራል፤ በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ነፍስ ውስጥ መሬት እንዳለ፣ በኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዓመታት ውስጥ መሬት እንዳለ፣ በኢትዮጵያ የተጋድሎ ጀግንነት ውስጥ መሬት እንዳለ፣ በኢትዮጵያ የአገር ፍቅር ውስጥ መሬት እንዳለ የውጩ አገር ሰው በምን መንገድ ሊያውቅ ይችላል? አንድ ኢትዮጵያዊ በአገሩ ውስጥ ባለው ቤት ውስጥ ምን ምን ይሠራል? አንዴት ይሠራል? በዚህ ጉዳይ ላይ የውጭ አገሩ ሰው ምንም ያህል አያውቅም፤
ስቱድዮ በወር አንድ መቶ ዘጠና አምስት ብር፣ ባለአንድ መኝታ ሁለት መቶ ሰባ አራት ብር፣ ባለሁለት መኝታ አምስት መቶ ብር እንደሚከፈል ተወስኖአል፤ ይህ ኪራይ ሁላችንም እንደምናውቀውና እንደለመድነው ዓይነት ያለ ኪራይ አይደለም፤ ልዩ ነው፤ አንዱ ልዩ የሚያደርገውም መጠለያዎቹን ሁሉ ያፈረሱትና ችግሩን የፈጠሩት ራሳቸው ኪራይ ሰብሳቢዎች መሆናቸው ነው፤ ዋናው ልዩ የሚያደርገው ግን ለኮንዶዎቹ ኪራይ መክፈል የሚጀመረው ሕንጻዎቹ ተሠርተውና አልቀው ተከራዮቹ ከገቡ በኋላ አይደለም፤ የሕንጻዎቹ ሥራ የሚጠናቀቀው ቢያነስ ከአምስት ዓመት በኋላ ሲሆን ኪራይ መክፈል የሚጀመረው ዛሬ ነው! ደሀዎች ለማይኖሩበት ቤት ኪራይ ይከፍላሉ! ማንም አላስገደዳቸውም፤ ያስገደዳቸው ደካማነታቸውና መናጢ ደሀነታቸው ነው፤ መስገብገባቸው ነው።
ከቀረበው መረጃ ተነሥተን እስቲ ትንሽ ስሌት እንሥራ፤ በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ውስጥ ስምንት መቶ ሺህ ያህል ሰዎች ለኮንዶ ተመዝግበዋል እንበል፤ በስቱድዮ፣ በአንድ መኝታ፣ በሁለት መኝታ፣ በሦስት መኝታ በእያንዳንዳቸው የቤት ደረጃዎች ሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ቢመዘገቡ ከነዚህ ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት በዝቅተኛ የደሀነት ደረጃ ላይ ቢሆኑ፣ ሢሶ የሚሆኑት ደግሞ የደሀነት መሀከለኛ ደረጃ ላይ ቢሆኑ፣ ሌሎቹ ማለትም አንድ አምስተኛ የሚሆኑት በተሻለ ደረጃ ላይ ያሉ ደሀዎች ቢሆኑ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በያመቱ የሚሰበሰበው ገንዘብ እንደሚከተለው ይሆናል፤
ደሀነት ሲበዘበዝ
ኮንዶ | የተመዘገቡ | የወር ኪራይ በደሀነት ደረጃ | የዓመት ኪራይ |
ስቱድዮ |
200 000 |
200 000 x 195= 39 000 000 |
468 000 000 |
1 መኝታ |
200 000 |
200 000 x 274= 54 800 000 |
657 600 000 |
2 መኝታ |
200 000 |
200 000 x 500= 100 000 000 |
1 200 000 000 |
3 መኝታ |
200 000 |
200 000 x 750= 150 000 000 |
1 800 000 000 |
ድምር | 1 000 000 | 279 700 000 | 4 125 000 000 |
እንግዲህ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከመጠለያ ማጣት ጭንቀት ለማምለጥና ያደረባቸውን የኮንዶ ጉጉት ለማሳካት ከአራት ቢልዮን ብር በላይ እየተራቡ ይገብራሉ፤ በአምስት ዓመታት ውስጥ ገና ኮንዶው ውስጥ ሳይገቡ ላባቸውን ያንጠፈጠፉበትን 20 625 000 000 ብር ይከፍላሉ ግፍ ሌላ ትርጉም የለውም።
ማፍረስም በጣም ትርፋማ ሥራ ሆነ።
በፈረሰው ላይ የሚገነባውስ? ስለኮንዶው ሕንጻ አንዳንድ ጥያቄዎችን ማንሣት በግድ ያስፈልጋል፤ አንደኛ የኮንዶው ሥራ መቼ ተጀምሮ መቼ ያልቃል? ያልቃል ሲባልስ ለመኖሪያ ብቁ የሆነ፣ በሮችና መስኮቶች ተገጥመውለት፣ ወለሉና ጣራው፣ የመታጠቢያ ቤቱ ሁሉ ተሟልቶ ነው ወይስ ባለቤት የሚሆኑት ሰዎች የሚጠብቃቸው ሥራ አለው? ሁለተኛ የኮንዶው ሕንጻ ስንት ክረምትና ስንት በጋ የሚችል ይሆናል? ሦስተኛ ኮንዶው ሰዎችን ወደከፍተኛው ፎቅ የሚያደርሳቸው ‹ሊፍት› አለ ወይስ ሰዎች በእግራቸው በደረጃ ሊወጡ ነው? ይህ ከሆነ ለሽማግሌዎችና አሮጊቶች ምን ዝግጅት ተደርጎላቸዋል? ሽማግሌዎችንና አሮጊቶችን ወደምድር ቤቱ አካባቢ ለመደልደል ታስቦአል ወይ? አራተኛ የውሀ አቅርቦቱ ምን ያህል አስተማማኝ ነው? ውሀ በሚጠፋበት ጊዜ ነዋሪዎቹ ሊጠቀሙበት የሚችሉበት የመጸዳጃ ቦታ ካልተዘጋጀ በጥቂት ጊዜ ውስጥ አካባቢው ለጤና ጠንቅ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፤ ‹‹የአበሻ ኑሮ›› የሚባል ነገር ያለ ይመስለኛል፤ ቡናና ጌሾ መውቀጡ፣ ብቅልና በርበሬ ማስጣቱ፣ ዶሮና በግ ማረዱ፣ አንጀራ መጋገሩ፣ ማኅበሩ፣ ለቅሶው — እነዚህና ሌሎችም ማኅበራዊ ግዴታዎች ኮንዶው ሲሠራ ታስበው ነበር ወይ?
ደሀው ራሱን በማፈራረስ፣ ይበልጡኑ በሚደኸይበት ሥራ እንዲጠመድ፣ በፍርስራሽ እንዲነግድ በምናምን ተይዞአል! የሥላሴዎች እርግማን!
ESAT News 22 August 2013
…
የልማታዊ ጋዜጠኞች አንዝህላልነት እና የአብርሃ ደስታ እማኝነት “የኢትዮዽያውያን ህይወት በዓረብ ሀገሮች “
ባሳለፍነው ሳምንት በሳውዲ አረቢያ ግፍ ተፈጸሞባቸው ወደ ባገር ቤት የሚሸኙ እህቶች የመኖራቸው መረጃ ደረሰኝ ። በተለይም በቅርብ እከታተላቸው የነበሩ አህቶች እንግልት በመጠቆም በዚው በፊስ ቡክ የማለዳ ወግ ዳሰሳየ ላይ አንድ መልዕክት አስላልፊ ነበር! መልዕክቱም ለልማታዊ የሃገር ቤት ጋዜጠኞች ሲሆን የመልዕክቱ ፍሬ ሃሳብ ” የምንናገረውን ማመን መቀበል አቅቷችሁ እንደ ጠላት ከምታዩን ረቡዕ ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ ሂዱና ከፍተኛ ግፍ ተፈጸደሞባቸው ከሳውዲ ተጠርፈው ወደ ባገር የሚገቡትን የኮንትራት ሰራተኞችን ተመልክቱ !”የሚል ነበር።
ንቁ እዝነ ልቦንና ያልታደሉት ልማታዊ ጋዜጠኞች በቦታው ሄደው ከቤሩት የተመለሱትን ሻንጣ የደረደሩ እህቶች በቴሌቪዥኑ መስኮት ብልጭ አድርገው ከማጥፋታቸው ባለፈ ከሳውዲ ያለጫማና የረባ ልብስ ተደብድበውና ተደፍረው የተመለሱትን ግፉአን ሊያሳዩን እንኳ አልፈቀዱም! ጋዜጠኞቻችን አልተሳሳቱም!!! የተሳሳትኩት እኔ ነኝ!!! ያን ሰሞን “ስደት ይቅር ” ምንቴስ ሰፊ ሽፋን በየሚዲያው እየሰጡ ፣ የደበቁትን መከራችን እያሳዩ እያሉ ህዝበ አዳም ፣ ሃገሬውን ሲያስለቅሱን የከረሙት ወደ ነፍሳቸው ተመልሰዋል ብየ በማሰቤ ስህተቱ የእኔ ግምት ነው!!! ጉዳታችን እዩት ቀሪው እንዲማርበት ፣ ሃላፊዎቻችን ይዩትና ወደ ዘነጉት የዜጎች ጉዳይ ያተኩሩ ዘንድ የተገፊ ግፉአኑን ጉዳይ ተከታትየ መጠቆሜ በአደባባይ ቃል የገቡትን ይፈጽማሉ ብየ በማሰቤ የተሳሳትኩት እኔ ነኝ!!! ስህተቴ አንድና አንድ ነው!!! የአረብ ሃገሩን የስደት መከራ የሚፈልጉት ለፕሮፖጋንዳ እንጅ ቀሪውን ማስተማርን እንደልሆነ አለማሰቤ ነው ስህተቴ ! በእንዝህላል ልማታዊ ጋዜጠኞቻችን አዝኘም ብቻ ሳይሆን አፍሬ ዝም ማለቴ ግን እውነት ነው! ዛሬ ማለዳ ግን መልካም መረጃም የሚየ ስፈነጥዝ ባይሆንም መረጃው በመሰራጨቱ የተደሰትኩበትን መጣጥፍ ተመለከትኩ ።
ሮብ ነሓሴ 15, 2005 ዓም ከአረብ ሃገር ወደ ሃገር የገቡትን እህቶች አብርሃ ደስታ አግኝቷ እንዳነጋገራቸው በማህበራዊ ድህረ ገጽ ካስተላለፈው መልዕክት ለመረዳት በመቻሌ ደስ አለኝ ! በገዥው የኢህአዴግ መንግስት አስተዳደር ላይ በተለይም ስለ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከመቀሌ ሆኖ በሚያሰራጫቸው የሰሉ ሚዛናዊ ሂሶች ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣው አብርሃ ድስታ ግፉአን እህቶቸችን ቦሌ አየር ማረፊያ አግኝቷቸው ያየውን የሰማውን እጥር ምጥን ባለው የለመድነው መረጃ አቀባበል እንካችሁ ብሎናል ። የአብርሃ እማኝነት አስደስቶኝ እኔም ለዛሬ ወግ ዳሰሳ አበቃሁት ! ወዳጃችን አብርሃ ደስታ ሆይ ! የአረብ ሃገሩ የብዙሃን የኮንትራት ሰራተኞች አስከፊ ህይዎት ያጫዎቱህ ወደ ሃገር ለመግባት የታደሉት መሆናቸውን አስረግጨ እነግርሃለሁ ! ያየሃቸው የታደሉት ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው ! የመንግስት ተወካይ አለን ለማለት አልደፍርም ! እውነቱ ይህ ነው ! አንተም እንኳን ከግፉአኑ ሰምተህ አሰማህን ! ይህ የማናችንም ሃላፊነት መሆን ሲገባው እያደረግነው አይደለም! የእህቶቻችን ህይዎት በአረብ ሃገር ምስክርነቱ ይህ ነው ! እንዲህ ይኖራል ! የእኔን በዚህ ላብቃና እጥር ምጥን ወዳለችው የአብርሃ ደስታን እማኝነት ከዚህ በታች እንድትመለከቱ ስጋብዝ ለአብርሃ ምስጋና በማቅረብ ጭምር ነው! እነጰ አበቃሁ ! ቸረወ ያሰማን !
ነቢዩ ሲራከ
By Abraha Desta የኢትዮዽያውያን ህይወት በዓረብ ሀገሮች ——————————————— ሮብ ነሓሴ 15, 2005 ዓም ጠዋት ቦሌ ኤርፖርት ነበርኩ። ኢንተርናሽናል ተርሚናሉ ከዓረብ ሀገራት በተመለሱ እንስት ኢትዮዽያውያን ተጥለቅልቋል። የተከፉና የተረበሹ ይመስላሉ። ከሰዓት በኋላ ወደ መቐለ ለመመለስ ወደ ሀገር ውስጥ ተርሚናል ገባሁ። ከነዚህ ጠዋት ረጅም ሰልፍ ይዘው ያየኋቸው ተመላሾች የተወሰኑ አገኘሁ። ስለ ህይወታቸው፣ ስለሚደርስባቸው እንግልት ወዘተ አጫወቱኝ። በዓረብ ሀገሮች የሚኖሩ ኢትዮዽያውያን እንደሰው አይቆጠሩም፤ ብዙ አካላዊና ስነ አእምራዊ ችግር ይደርሳቸዋል። ብዙዎቹ አብደዋል፣ ራሳቸው አጥፍተዋል። ኢትዮዽያውያን በመሆናቸው ራሳቸው ይረግማሉ፤ በመፈጠራቸው ያዝናሉ። የኢትዮዽያ ኤምባሲ ግን ምንድነው የሚሰራው? የዜጎች ደህንነት መጠበቅ’ኮ የመንግስት ሐላፊነት ነው። የኢትዮዽያውያን ስደትና ግፍ ሀገራችን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ሊመራት ይችላል።
የመለስ ዜናዊ “የሁለት አሐዝ ዕድገት” እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ኑሮ ***
ከበፍቃዱ ዘ ኃይሉ
“ለ7 ዓመታት በተከታታይ 11·6 በመቶ አድጓል” የተባለው የመለስ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፥ የዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍም ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሚገኘው መረጃ ላይ ቢመሠረቱም “የለም፤ ከ6 እስከ 8 በመቶ ነው ያደገው፣ ቢሆንም ቀሽት ነው” ይላሉ።
“ኢኮኖሚው ሲመነደግ” የሕዝቦች ኑሮ ደረጃስ እንዴት ነው?
ኢትዮጵያ በየአረብ አገራቱ የቤት ሠራተኛ አቅራቢነት ከፍተኛ ደረጃ የደረሰችው በመለስ ዘመን ነው። (ለምሳሌ አሁን ኢትዮጵያውያንን አልቀበልም ያለችውን ሳውዲ አረቢያ የቤት ሠራተኛ ፍላጎት 10 በመቶ ኢትዮጵያ ትሸፍን ነበር።) በየአረብ አገራቱ የኢትዮጵያውያን ስም ከሌብነት እና ሴተኛ አዳሪነትጋ የተያያዘ ነው።
ከኢትዮጵያ ውጪ መውጣት ለሁሉም ዜጋ ቢፈቀድ ዐሥር ሚሊዮን ሰው እንኳን ይቀራል ብዬ መገመት ይከብደኛል። ከተሜውም ገጠሬውም ወደቻለው ቦታ ይፈልሳል። የተማረውም፣ ያልተማረውም ኢኮኖሚያዊ ስደትን የመምረጡ እውነት የኢኮኖሚያዊ ዕድገቱን እውነተኝነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይከተዋል።
የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በተለይ የመንገድ ሥራዎች ሲነቃቁ የግሉ ዘርፍ (ከኢሕአዴግ “የኢንዶውመንት” ቢዝነሶች በቀር) ተዳክሟል። ያሉትም የግል ቢዝነሶች ቢሆኑ በፖለቲካ ጥቅም የሚለመልሙ በመሆናቸው በከተሞች መሐል የሚበቅሉ ብልጭልጭ ሕንፃዎች የሙስና ሲሳይ ናቸው። ከሕንፃዎቹ ጀርባ ያሉት ያው የድሮዎቹ ቆሼ ሰፈሮች ናቸው። እንደ HDI ያሉ የUN የሰብኣዊ ልማት መለኪያዎችም የሚያሳዩን ኢትዮጵያውያን ዛሬም በድህነት እየማቀቁ መሆኑን ነው።
“ስኳር የተወደደው ድሃው ስኳር መብላት ጀምሮ ነው” ያሉት መለስ ስኳሩን የሚልሱት እነማን እንደሆኑ እንኳ ሳይረዱ ያለፉ ይመስለኛል።
አቶ መለስ ምንጩንና መጠኑን ማንም ያልገመተው፣ የባለብዙ ሀብት ባለቤት፣ የትዳር አጋራቸውን ጨምሮ ሌሎች ጥቂት ሀብታሞች ያሉበት የጥቅመኞች ክበብ እየዳጎሰ ብዙኃኑ የሚቀጭጩበትን የቢዝነስ ስርዓት በመፍጠር በቁጥር ጫወታ አድጋችኋል ይሉናል። ድሃ ተኮር ፖሊሲ ቀርጫለሁ፣ ለልማቱ ብዬ ነው ዴሞክራሲን የበደልኩት ብለው ያተረፉልን ነገር ቢኖር አገርክን ጥለህ ብረር፣ ብረር የሚያሰኘው ምስኪን፣ ድሀ ትውልድ ብቻ ነው።
23.08.2013 ዜና 16:00 UTC
ሶሪያ፥ ዩናይትድ ስቴትስና «ቀዩ መስመር»
ጣምራ የሥነ ተዋልዶ ጤናና ልማት ድርጅት
የሙባረክ መፈታትና የአረቡ ዓለም አስተያየት
ተገን ጠያቂዎችና የቀኝ አክራሪዎች ተቃውሞ
Amharic News 1800 UTC –ኦገስት 23, 2013
ዜና ከባሌ ሮቤ፤ ፍኖተ ነጻነት
ሀሙስ ነሃሴ 16 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ከሮቤ ከተማ ከንቲባ፣ ምክትል ከንቲባ፣ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊና ከከተማው ካቢኔዎች ጋር 3 ሰዓት የፈጀ ውይይት አድርገዋል፡፡ ባለስልጣናቱ “አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን ማድረግ አይችልም፤ እኛ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ስጋት አለብን፡፡ የቀድሞው ጠ/ሚር መለስ በፓርላማ እንደተናገሩት በአካባቢያችን የአልቃይዳ ክንፍ አለ” ብለዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች በበኩላቸው “በባሌ አካባቢ ያለውን የፀጥታ ችግር የምታውቁት እናንተ ናችሁ፤ አልቃይዳ ባሌ ውስጥ አለ ካላችሁ፣ ይሄንኑ የሚያረጋግጥ ይፋዊ ደብዳቤ ስጡን፤ይህ ካልሆነ ግን ሰላማዊ ሰልፉን እንቀጥላለን፡፡” የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ ዛሬ ወደ ከንቲባው ጽ/ቤት የተጠሩት የአንድነት ተወካዮች “እሁድ በባሌ ሮቤ የገበያ ቀን ስለሆነ ሰልፍ ማድረግ አትችሉም፡፡” የሚል ምላሽ አግኝተዋል፡፡ ተወካዮቹም አንድነት ፓርቲ እሁድ ሰላማዊ ሰልፉን ከማድረግ የሚከለክለው ህጋዊ ምግንያት እንደሌለ አስረግጠው አስረድተው ወጥተዋል፡፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ
Ethiopia-Press-Review-8-23-13 –ኦገስት 23, 2013
ሰበር ዜና ከአዳማ፤ ፍኖተ ነጻነት
በመጪው እሁድ ነሃሴ 19 ቀን 2005 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሊያደርግ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ጷጉሜ 3 መዘዋወሩን የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረ ኃይል ማምሻውን አስታወቀ፡፡ ግብረኃይሉ እንዳስታወቀው የአዳማ ከተማ አስተዳደር ለአንድነት ፓርቲ በፃፈው ደብዳቤ ነሃሴ 19 በከተማው ስብሰባ በመኖሩና የሀይል እጥረትም ስላለበት አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን እንዲያስተላልፍ ጠይቋል፡፡ አንድነት ፓርቲም የቀረበለትን ጥያቄ ከግምት በማስገባት ሰልፉን ለጷጉሜ 3 ቀን 2005 ዓ.ም መዘዋወሩን የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረ ኃይል ማምሻውን አስታውቋል፡፡
#Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ
በሱዳን ከ300 ሺ ህዝብ በላይ በጎርፍ ተጠቃ
ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው በያዝነው ወር በጣለው ዝናብ ከ50 በላይ ሰዎች ሞተው፣ ከ300 ሺ ያላነሱት ደግሞ ተፈናቅለዋል።
በተለይ በዋና ከተማዋ ካርቱም ላለፉት 25 አመታት ያልታየ ጎርፍ መታየቱን ድርጅቱ አስታውቋል።
በአገሪቱ ካሉ 18 ግዛቶች መካከል በ14 ላይ ከፍተኛ የንብረት መውደምም ተከስታል።
በባህርዳር የኢህአዴግ አባል ያልሆነና በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ያልተደራጀ ስኳዐር አያገኘም ተባለ
ነሃሴ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከባህርዳር የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ ለከተማው ነዋሪዎች አዲስ የአባልነትና አንድ ለአምስት አባልነት መለያ ወረቀት ያዘጋጀ ሲሆን፣ ይህንን ወረቀት ያላሳየ ሰው በመንግስት የሚከፋፈለውን ስኳር አያገኝም። አንዳንድ ነዋሪዎች ችግራቸውን በኤፍ ኤም ራዲዮ ላይ ቢናገሩም ምንም መፍትሄ እንደሌለው እንዳወቁ ለኢሳት ተናግረዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ህዝብ ግንኙነት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
ኢህአዴግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገር ውስጥ ባሉ ተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ እየተደናገጠ መምጣቱ ይነገራል።
ዜና ከአዲስ አበባ ፤ ፍኖተ ነጻነት
በመጪው እሁድ ነሃሴ 19 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መ.ኢ.አ.ድ/ ዋና ጽ/ቤት 33ቱ ፓርቲዎች ለጠሩት ህዝባዊ ውይይት የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የፓርቲዎቹ አባላት በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ አቶ ደመላሽ፣ አቶ አብርሃም ፣ አቶ አታላይ በለው፣ አቶ እዮብዘርና አቶ መላኩ መሰለ የተባሉት አባላት የቅስቀሳ መከናውን ከያዘው ሹፌርና ረዳት ጋር ታስረዋል፡፡ የፓርቲዎቹ አመራሮች አባሎቻቸው ወደታሰሩበት 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ አቅንተው እስሩ ህጋዊ አለመሆኑን አዋጅ በመጥቀስ ቢያስረዱም በስፍራው የነበሩት የፖሊስ አዛዥም
“እኔ በአዋጅ ሳይሆን በትዕዛዝ ነው የምመራው፤ እሰር የሚል ትዕዛዝ ደርሶኝ አስሬያቸዋለሁ”
የሚል ምላሽ ሸሰጥተዋቸዋል፡፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ