የኛ ሰው በካንጋሮ ምድር
ESAT News 21 August 2013
…
ዋ! እዮብ መኮንን! – ‹‹እግዚአብሔርን ባገኘው የምጠይቀው የዘላለም ሕይወት እንዲሰጠኝ ነው››
ጊዜው ከአምስት ዓመት በፊት ነው፤ በሚሊኒየሙ፣ ሚያዚያ ወር የመጀመሪያ ሳምንት፡፡ ሠራበት በነበረው ጐግል ጋዜጣ ‹‹ጥበብ›› አምድ ላይ እንግዳ ላደርገው ረፋድ ላይ ወደ እዮብ መኮንን የእጅ ስልክ መታሁ፡፡ መልካም ፈቃዱን ገለጾ… አንጃ ግራንጃ ሳያበዛ ‹‹ከተመቸህ ዛሬ መገናኘት እንችላለን›› አለኝ፡፡ ትንሽ መዘጋጀት እንዳለብኝ ነግሬው ዛሬ ከሆነ ምሽት ላይ መገናኘት እንደምንችል ነገርኩት፡፡ ጥያቄዎች ሳሰባስብ እና ሳሰላስል ዋልኩ፡፡ የቀጠሮ ቦታ ስላልቆረጥን ከመገናኘታችን በፊት ልደውልለት ተስማማን፡፡ ደወልኩለት!
‹‹ፒያሳ አካባቢ ነኝ፡፡ እዚህ መምጣት ትችላለህ?›› (እዮብ)
‹‹መልካም ግን ትንሽ እንዳልቆይብህ መገናኛ አካባቢ ነኝ፡፡ መሀል ላይ መገናኘት ከቻልን መልካም ነው፡፡ አለበለዚያ ግን ልምጣ››
‹‹እሺ! የት እንገናኝ? መኪና ይዘሀል?››
‹‹መኪና? ይሄ አራት ጎማ ያለው ነገር?››
‹‹ይስቃል››
‹‹አለኝ ግን butter fly ነው፡፡ (የልብስ ስፌት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡) ከቤት ውጪ አልነዳውም››
እየሳቀ ‹‹እሺ! የት ልምጣልህ››
‹‹ዑራዔል አካባቢ አማካይ ስፍራ ነው፡፡ ፕላዛ ሆቴል እንገናኝ?›› እውነት ለመናገር እኔ የነበርኩት ፕላዛ አካባቢ ይገኝ የነበረው ቢሯችን ውስጥ ነበር፡፡ የጀመርኩትን ሥራ ሳጠናቅቅ፣ ኮምፒውተር ስዘጋጋ፣ እንዳልቆይበት ብዬ ግርጌዬ ላይ እንዲመጣ ጨከንኩበት፡፡ የሚገርመው እኔ ቢሮ ስድበሰበስ እሱ ቀድሞ ፕላዛ ደረሰ፡፡ ሮጥ ብዬ ስደርስ ሆቴሉ ግቢ ውስጥ ጥቁር ቪታራ መኪናውን እየዘጋጋ ነበር፡፡ ሆቴሉ ምግብ አዳራሽ ውስጥ ገበታ ሳይቆርሱ መስተናገድ ባይፈቀድም ቃለ ምልልስ ለመስራት ሳስፈቅድ ይሁንታ አገኘሁ፡፡ የሆቴሉ ባልደረቦች ድሬድ ጸጉሩን የተሸለተውን እዮብን እያዩ ‹‹እሱ ነው/አይደለም›› እየተባባሉ ነበር፡፡
አማርኛ፣ ትግሪኛ፣ ኦሮምኛና ሱማሊኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ እንደሚናገር የነገረኝ እዮብ ቃለ ምልልሱን ከመጀመሬ በፊት ማስጠንቀቂያ አስቀመጠ፡፡
‹‹በድምጽ መቀዳት ስለማልፈልግ፣ ወረቀት እና እስክሪብቶ አውጣ››
‹‹ለምን››
‹‹ከዚህ በፊት ያላልኩትን ብለው መጽሔት ላይ ስላወጡ ይሄን ስህተት መድገም አልፈልግም፡፡ ስለዚህ እየጠየቅከኝ መልሱን ጻፍ!››
‹‹እኔ እንዲህ እንደማላደርግ ከመቶ ፐርሰንት በላይ ቃል ልገባልህ እችላለሁ››
‹‹ኖ! አይሆንም››
ላሳምነው ሞከርኩ፡፡ ሊዋጥለት አልቻለም፡፡ በዚያው ሰሞን አንድ መጽሔት ያልዘፈነውን ራጋ ‹‹የራጋ ስልት ያለው እንትን የተሰኘ ዘፈኑ›› እያለ አልበሙን ጥንብ ርኩሱን አውጥት ስለነበር ፕሬሱ ላይ ያለው እምነት የበለጠ እንዲሸረሸር አድርጎታል፡፡ የመጨረሻ አማራጭ ልሰጠው ጉሮሮዬን ጠረግኩ፡፡
‹‹እውነት ለመናገር መልስህን በቃል እየጻፍኩ አልዘልቀውም፡፡ በዚህ ላይ እኔ እስክፅፍ ስትጠብቅ ሃሳብህ ይቆራረጣል፡፡ ለዛ ቢስ ቃለ ምልልስ ይሆናል፡፡ ማድረግ ያለብኝ [ተገቢ ነው ብዬ ባላምንም] እስከዛሬም ለማንም አድርገነውም ባናውቅም ድምጽህን ወደ ወረቀት ከገለበጥኩ በኋላ (After transcription) አምጥቼ ላሳይህ እችላለሁ፡፡ አለበለዚያ ግን በቃል…››
አመነታ፡፡ እንደምንም አሳመንኩትና ‹‹ሽጉጤን›› ተረክ አደረግኳት [ለእንደ እኔ አይነት ጋዜጠኛ ተብዬ ሽጉጡ ድምጽ ማስቀሪያው ነች፡፡] አወራን፡፡ በቀጣዩ ቀን ምሽት ላይ ይሰራበት የነበረው ፋራናይት ክለብ (ልምምድ ላይ የነበረ ይመስለኛል) ወስጄ አሳየሁት፡፡ አነበበውና ምንም ሳያንገራግር በደስታ ሸኘኝ፡፡ ከዚያም የሚያዚያ 10/2000 ዓ.ም ጐግል ጋዜጣ ላይ ጨዋታውን ዳርኩት፡፡ ካወራናቸው ውስጥ ጥቂቱን እንካችሁ፡፡
የተለያዩ አይነት የሬጌ ስልቶች አሉ፡፡ አንተ የምትጫወተው የትኛውን አይነት ነው ትክክለኛ (Pure የሆነውን) ሬጌ ትጫወተዋለህ
ሬጌ የተለያየ አይነት ስታይል አለው፡፡ ሩትስ፣ ስካ፣ ዋን ድሮፕና ሌሎችም አሉ፡፡ የምቱ ሁኔታ ነው ሩት፣ ስካ… ሊያስብለው የሚችለው፡፡ እኔ ሁሉንም የሬጌ ቶን እጫወታለሁ፡፡ ስለ እኔ መናገር ቢከብደኝም ሙዚቃ የሚያውቁ ሰዎች በአብዛኛው በትክክል እንደምጫወተው ይናገራሉ፡፡
‹‹ይዞ የመጣው ለአገራችን አዲስ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊያሰልፈው የሚችል አዘፋፈን ነው፡፡ ሬጌ የሚፈልገው ነገር አለው፡፡›› ተብሎ ስለ አንተ የተጻፈ ጽሁፍ አንብቤያለሁ፡፡ በዚህ ትስማማለህ?
ጸሐፊው ያመነበትን ጽፏል፡፡ እኔ ከምናገር አድማጭ ቢፈርድ ጥሩ ነው፡፡
በሙዚቃ ስራህ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረብህ ሰው አለ?
አሊ ቢራ እና ቦብ ማርሌይ በጣም የምወዳቸው ድምጻዊያን ናቸው፡፡ የእነሱ ተፅዕኖ አለብኝ፡፡ የሁለቱንም ዘፋኞች ዘፈን ከልጅነቴ ጀምሮ እሰማም፣ እዘፍንም ነበር፡፡
ሬጌ ሙዚቃ መጫወት ያለበት ሰው ምን ማሟላት አለበት?
መጀመሪያ ሙዚቃውን ማፍቀር አለበት፡፡ ከዚያም በደንብ መስማትና ደጋግሞ ልምምድ መሥራት ይኖርበታል፡፡
በአልበምህ ላይ የሰራሀቸው ዜማዎች ተመሳሳይነት አላቸው ይባላል፡፡
በፍጹም አይመሳሰሉም፡፡ ለአንድ የውጪ አገር ዜጋ የትግሪኛ ዜማ ብታሰማው ሁሉም አንድ ዓይነት ነው የሚመስለው፡፡ የእኔም እንደዚያው ነው፡፡ አሰማማችን ነው እንጂ ዜማዎቹ አይመሳሰሉም፡፡
አልበምህ ያሰብከውን ያህል ተደምጧል?
ገና ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ ሰውም በበቂ ሁኔታ የሰማው አይመስለኝም፡፡ የተወሰነ ሰው ግን ሰምቶታል፡፡
ለምሳሌ የሚካያ በኃይሉ አልበም ከወጣ ጀምሮ (1999 ዓ.ም.) የወደዱት ቢሆንም ይበልጥ የተሰማው እየቆየ ሲሄድ ነው፡፡ ያንተም አልበም እንደዚያ…
እመኛለሁ ግን እንደዚያ ይሆናል ብዬ አላስብም፡፡ አምላክ ነው የሚያውቀው፡፡
‹‹እዮብ በአብዛኛው የሚጫወተው የሬጌ ዘፈኖችን ስለሆነ ጸጉሩ መለያው ነበር፡፡ ሲቆረጠው ዘውዱን የተገፈፈ ንጉስ መስሏል ያሉኝ አሉ፡፡
ለእነሱ የሚታያቸው እንዳልከው ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ ግን በመቆረጤ ደስተኛ ነኝ፡፡
መቼና ከማን ጋር ስትሆን ደስ ይልሀል?
ለብቻዬ፣ ከጓደኞቼ ጋር ስሆንና መጽሐፍ ቅዱስ ሳነብ ደስ ይለኛል፡፡ ሁሌም አዲስ ስለሆነ ባነበብኩት ቁጥር ይገርመኛል፡፡ ያነበብከውን መተግበር ስትጀምር ይበልጥ አዲስ ይሆንብሀል፡፡ ሌላ መጽሐፍ ማንበብ ትቼያለሁ፡፡
ትልቁ ራዕይህ ምንድን ነው?
አላውቀውም፡፡ ዛሬን ብቻ መኖሬን ነው የማውቀው፡፡ በፕሮግራም ነገ እንዲህ አደርጋለሁ አልልም፡፡ አስተማሪና መካሪ ዘፋኝ ብሆን ደስ ይለኛል፡፡ ስለ ነገ የሚያውቀው እግዚአብሔር ነው፡፡
አሁን የምትኖረው ሕይወት እና ያለህበት ደረጃ የምትፈልገውን ዓይነት ነው?
ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት ትልቅ ነገር ነው፡፡ ደስተኛ ነኝ፡፡ ሕይወት ደግሞ የምትጣፍጠው አማራጭ ስታጣ ነው፡፡ በሕይወቴ ከዚህ በላይ ብሆንም ካለሁበትም ዝቅ ብልም ምንም አይመስለኝም፡፡ አማራጩ እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡
በቆይታችንየእግዚአብሄርንስምደጋግመህአንስተሀል፡፡ብታገኘውበቀዳሚነትየምታነሳለትጥያቄምንድንነው?
የዘላለም ሕይወት እንዲሰጠኝ ነዋ!
በደረሰበት ደንገተኛ ህመም ቅዱስ ገብርዔል ሆስፒታል ሲታከም የነበረው ከዚያም ለተሻለ ሕክምና ወደ ናይሮቢ አቅንቶ ሳይነቃ በሳምንቱ መጨረሻ ሕይወቱ ያለፈው ተወዳጁ ድምጻዊ እዮብ መኮንን ጋ ያኔ በተገናኘንበት ወቅት አልበሙ እንዲህ ይገናል ብሎ አላሰበም፡፡ ‹‹ታያለህ እንደ ሚካያ አልበም ነው የሚሆነው›› ብዬ ‹‹ስጠነቁል›› አልመሰለውም ነበር፡፡ ሥራው ከገነነ በኋላ ‹‹አላልኩህም ነበር!›› ብዬ ከመፎከር አልቦዘንኩም፡፡ አንድ ቀን አጋጣሚ ቦሌ አካባቢ አግኝቼው አንድ ካፌ ትንሽ ተቀምጠን አወራን፡፡ አወራን ከማለት ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ ሲሰብከኝ ነበር ማለት ይቀላል፡፡ ልቡ ተሰብሮ፣ ግንኙነቱ ከአምላኩ ጋር ብቻ ይመስል ነበር፡፡ ዛሬ በ9 ሰዓት በሥላሴ በተፈጸመው የቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ ጥቅምት 12/1967 ዓ.ም. መወለዱ የተነገረው እዮብን ሁኔም በማይሰለቹ ዜማዎቹ እናስታውሰዋለን፡፡ በርካታ ሰውም በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ሀዘኑን ገልጿል፡፡ እንደተመኘውም በላይኛው ቤት ‹‹የዘላለም ሕይወት እንዲሰጠው›› እመኛለሁ፡፡ ዋ! እዮብ! ከልቤ አዝኛለሁ! ነፍሱን ይማረው!
መለስና ደሃ ዘመዶቹ
ክፍሉ ግርማ
ሰሞኑን የቀድሞውን የዲክታትር መለስ ዜናዊ የሞተበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት በየድረገጹ የተለያዩ የተቃውሞም የድጋፍም ጽሁፎች እየወጡ ነው ከሁሉ ግን አውራምባ ታይምስ በተሰኘው ድረገጽ ላይ አንድ ስለ መለስ ወንድምና እህት የሚገልጽ ፊልም አየሁ ነገሩ ሁሉ በጣም ገረመኝ ብዙ አስተያየቶችንም አነበብኩ ለእኔ ግን የማይውጥ ነው!! በጣም ስለድሃ ይሚያስብ ታላቅ መሪ…. ዘመዶችን እንኳን ለሃገሩ ሲል የረሳ መሪ…..ወ.ዘ.ተ እነዚህን የመሳሰሉ ውደሳዎችን የሚወዱት ኮሚኒስቶች ብቻ ናቸው
አንድ ሃይማኖት ያለው ወይም በትክክል የሚያስብ ሰው እንዴት ዘመዶችን ይረሳል በክርስትናም ሆነ በሙስሊሙ እምነት እናትና አባትን ከዚያም ወንድምና እህትን ማክበር መረዳዳትም እንዳለብን ያስተምራል.. አሁን እስቲ ይታያችሁ የመለስ እህት ጠላ መሸጥ ማለት መለስ ታላቅ መሪ ማለት ነው ? እዚህ አሜሪካን ሃገር በቀን 16 ሰዓት ከባድ ስራ እየሰሩ ወይም በአረብ አገር እህቶቻችን 24 ሰዓት በሰው ሰራተኛነት እይተቃጠሉ ወንድምና እህቶቻቸውን የሚስተምሩ ከቻሉም በብዙ ሺ የሚቆጠር ብር እየከፈሉ ከሃገር ወጥተው ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያደርጉት ቤተሰባቸውን ለመቀየር አይደለምን? በሃገራችንም አንዱ ከቤተሰብ የተሻለ ቦታ ካለ ሌላውን መርዳትም የተለመደ ባህላችን ነው ወደ ቁም ነገሩ ለመለስና በእኔ እምነት መለስ እነዚህን ደሃ ወንድምና እህቱን አይውዳቸውም ወይም ያፍርባቸዋል ያልተማሩና ደሃ ስለሆኑም ይሆናል ወይም ሌላ ሚስጢር አለ እንጂ ለነዚህ ሚስኪን ሰዎች መለስ ትንሽ ቦታ አጥቶ አይደለም ለመሆኑ እነዚህ ወንድምና እህት ቤተመንግስት ለቅሶ ለመቀመጥ ተፈቅዶላቸው ይሆን በቀብር ስነ ስረአቱ ላይስ….ወ/ሮ አዜብስ ኤፈርት ካሰራቸው ብዙ ፋብሪካዎች በአንዱ ተቀጥረው ትንሽ ከጠላ ሻጪነት ብትገላግላቸው ጥሩ ነበር ኤፈርት የትግራይ ህዝብ ሀብት አይደለም እንዴ? ለመለስ እህት ያልሆነ ለማን ሊሆን ነው?
ከክፉ ውንድም ይጠብቅዎ
ፍልሙን ለማይት
ታንዛንያና ባህሏ
ሙጋቤ ቃለ መሐላ ፈጸሙ
የካንሰር ምርምር በኢትዮጵያ
የግብፅ ቀውስና የአውሮፓ ሕብረት
220813 ዜና 16:00 UTC
ሕዝባዊ ስብሰባ በሲያትል በአካባቢው ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
Amharic News 1800 UTC –ኦገስት 22, 2013
ሕዝባዊ ስብሰባ ፤ በሲያትል እና በአካባቢዋ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
ሆስኒ ሙባረክ ተፈቱ
ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር ተፈተው በሄሊኮፕተር ወደ ጦሩ ሆስፒታል ለምርመራ ተወስደዋል፣ ጊዚያዊው መንግስት ከቤታቸው እንደማይወጡ አስታውቋል።
ፕሬዚዳንቱ ከቀረረበባቸው የሙስና ክስ ነጻ በመሆናቸው መፈታታቸው ተገልጿል። ይሁን እንጅ ከሁለት አመት በፊት በግብጽ ከተካሄደው አብዮት ጋር በተያያዘ አሁንም ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸዋል።
ደጋፊዎቸቻቸው ደስታቸውን ቢገልጹም፣ የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎች ደግሞ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
ግብጽ አሁንም በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ ብዙ የፖለቲከኛ ተንታኞች ይናገራሉ።
በአማራ ክልል በአንድ ሰምንት ጊዜ ውስጥ በጎርፍ ከ45 ሰዎች በላይ ሞቱ
ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢው በሚጥለው ከባድ ዝናም የተነሳ በክልሉ በሚገኘው ኦሮሚያ ዞን ባለፈው ሳምንት ከ30 ያላነሱ ሰዎች የተገደሉበትን ክስተት ጨምሮ ፣ በደቡብ ወሎ ዞን በአንባሰል ወረዳ አንዲት ሚኒ ባስ በጎርፍ በመወሰዷ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በጎርፍ የተወሰዱ ሰዎችን አስከሬን ለማግኘት በተደረገ ጥረት የ14 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል። የአካባቢውን ፖሊስ አዛዥ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
በክልሉ እየጣለ ያለው ሀይለኛ ዝናብ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ መሆኑን ከክልሉ የሚደረሱን ዘገባዎች ያመለክታሉ። በአንዳንድ አካባቢዎች ትራንስፎርመሮች በመቃጠላቸው መብራት ለሳምንታት መቋረጡም ታውቋል።
ሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች -ሰማያዊ ፓርቲን ከፓርቲዎች የትብብር መድረክ አሰናበቱ።
ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ33ቱ ፓርቲዎች የትብብር መድረክ -ሰማያዊ ፓርቲን ያሰናበተው፤የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ሰሞኑን ለ ሰንደቅ ጋዜጣ የሰጡት ቃለምልልስ የሌሎች ፓርቲዎችን ክብር የነፈገ ነው በሚል ነው።
በዚህም መሰረት ፓርቲዎቹ ባደረጉት ስብሰባ ሰማያዊ ፓርቲ ከስብስቡ እንዲወጣ መወሰናቸውን የቪኦኤ ዘገባ ያስረዳል።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፀሀፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ውሳኔው የተላለፈው ባለፈው እሁድ በተካሄደ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሆነ ገልጸዋል።
አቶ ይልቃል ለሰንደቅ በሰጡት ቃለ ምልልስ በዚህች አገር ከሰማያዊ ፓርቲ ውጪ ሌላ ተቃዋሚ ፓርቲ አለ ብለው እንደማያምኑ መገለፃቸው ይታወሳል።
“ገዥው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ የሰጡንን ዕውቅና ሳይቀር አቶ ይልቃል ነስተውናል”ያሉት የመኢአድ ፀሀፊ፤ህዝቡ በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ እምነት እንዳያድርበት ደባ ስለፈጸሙ፤ ድርጊታቸውን እንዲያርም ጊዜ ቢሰጣቸውም ሊያርሙ ስላለረቻሉ፤ ይባስ ብለውም ያንኑ ሃሳባቸውን ፡”የኛ ፕሬስ”በተሰኘ ጋዜጣ ላይ በማንፀባረቃቸው እና አቋሙ የ እርሳቸው ብቻ ሳይሆን የፓርቲያቸው ጭምር እንደሆነ በመረጋገጡ ከስብስቡ እንዲሰናበቱ ወስነናል ብለዋል።
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል በበኩላቸው “የሰጠሁት አስተያየትና ያንፀባረቅኩት ሃሳብ አዲስ አይደለም፤ እውነትም ነው”ብለዋል።
እስካሁን ሌሎች ፓርቲዎች የከፈሉትን መስዋዕትነት እርሳቸውና ፓርቲያቸው እንደሚያደንቁ ለቪኦኤ የተናገሩት አቶ ይልቃል፤ይሁንና ተቃዋሚዎች በአሁኑ ጊዜ የህዝብን የለውጥ ጥያቄ ለመመለስ በሚያስችል ጥንካሬና አቋም ላይ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።
“እኔ ስህተተኛ ብሆን ደስታዬ ነበር”ያሉት አቶ ይልቃል፤”እነዚህ ፓርቲዎች ነን እንደሚሉት ቢሆኑ እኔና ጓደኞቼ ሰማያዊ ፓርቲን አፍርሰን ወደየሌሎች ፓርቲዎች እንገባለን፤ወይም ወደየቤታችን እንሄዳለን”ብለዋል።
“ግን እውነቱ ሌላ ነው። የኢትዮጵያን ችግር መጋፈጥ አለብን ካልን እውነቱን ማድበስበስ የለብንም” በማለት ቀደም ሲል በሰጡት አስተያዬት እንደሚያምኑ በድጋሚ አረጋግጠዋል።
የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎችን ቤት ለማዳረስ ከ20 ዓመታት በላይ እንደሚፈጅ አንድ ሰነድ አመለከተ
ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከንቲባ ድሪባ ኩማ የሚመራው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ረቂቅ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ የኮንዶሚየም ቤት ፈላጊዎችን ለማስተናገድ ከ20 ዓመታት በላይ ጊዜ እንደሚወስድ ጠቆሟል።
አስተዳደሩ ለኮንዶሚየም ቤቶች ብቻ ከ800ሺ በላይ ዜጎችን ቢመዘግብም በቀጣይ አምስት ዓመት ለመስራት ያቀደው 178 ሺ ቤቶችን ብቻ ነው፡፡
አስተዳደሩ ከ2006 እስከ 2010 ዓ.ም ሥራ ላይ አውለዋለሁ ባለው የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ የቤቶች ልማትን በተመለከተ የያዘው ዕቅድ እጅግ አነስተኛ ሆኖ መገኘት በየደረጃው ያሉ አባላትና ካድሬዎችን ጭምር አስደንግጦአል፡፡
በአሁኑ ወቅት 20 በ80 በሚባለው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ባለቤት ለመሆን ከ800ሺ በላይ
ነዋሪዎች ተመዝግበው እየተጠባበቁ ባሉበት ሁኔታ በአምስት ዓመት 178ሺ ቤቶችን ብቻ እገነባለሁ በሚለው ስሌት ሲታሰብ 800ሺ ተመዝጋቢውን ለማዳረስ ከ20 ዓመታት በላይ ጊዜ የሚፈጅ መሆኑ ሕዝቡን በከፍተኛ ደረጃ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው ተብሎ ተሰግቶአል፡፡
የቤቶች ልማት ቢሮው ይህን ዕቅድ የያዘው የአስተዳደሩን አቅምና የእስካሁኑን የግንባታ ልምድ ግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡ የኩማ አስተዳደር በአምስት ዓመት ቆይታው 36ሺ700 ከባለአደራ አስተዳደር የተረከበውን ቤቶች ጨምሮ በጠቅላላው በሰልጣን ጊዜው መገንባት የቻለው 175ሺ246 ያህል ቤቶችን ብቻ ነው፡፡
ፕሮግራሙ ከተጀመረ ባለፉት ስምንት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለተጠቃሚዎች የተላለፉ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ብዛት 100 ሺ 559 ያህል ነው፡፡ አዲሱ ዕቅድም ሲሰራም ይህን የመገንባት አቅም ታሳቢ አድርጎ መሆኑን ታውቋል፡፡
ይህ ረቂቅ ዕቅድ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በተገኙበት ሰሞኑን በየደረጃው ላሉ
የአስተዳደር አካላት ለውይይት በቀረበበት ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ አንዳንድ ተሰብሳቢዎች በዚሁ መድረክ ላይ ይህን ዕቅድ ሕዝቡ አይቀበለንም፣ ማሳመንም አንችልም በሚል ተሻሽሎ እንዲቀርብ ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም በአዲሱና አወዛጋቢ በነበረው የሊዝ አዋጅ መሠረት በቀጣይ አምስት ዓመታት በአዲስአበባ ብቻ ካሉ ነባር ባለይዞታዎች ግማሽ ያህሉን ወደሊዝ ሥርዓት ለማስገባት የተያዘው ዕቅድም በተመሳሳይ ሁኔታ በራሱ አመራር አባላት ተቃውሞ ገጥሞታል።
የሊዝ አዋጁ ነባር ይዞታን በተመለከተ ይዞታዎች ሲሸጡ ወደአዲሱ የሊዝ ሥርዓት እየገቡ እንደሚሄዱ ቢደነግግም አስተዳደሩ በምን መልኩ 50 በመቶ ያህል ነባር ይዞታዎችን ወደሊዝ ሥርዓት
ለማስገባት እንዳቀደ ግልጽ አይደለም ፡፡
የስብሰባው ተካፋዮችም ይህ የሊዝ ጉዳይ አገር አቀፍ ሕግ ሆኖ ሳለ በአዲስአበባ ይጀመር የመባሉ ጉዳይ እና የአፈጻጸሙ ሁኔታ የህዝብን ድጋፍ ያሳጣል በሚል ሳይቀበሉት ቀርተዋል፡፡ ይህ የአምስት ዓመት የስትራቴጂክ ዕቅድ በቀጣይ ህብረተሰቡ ተወያይቶበት ስራ ላይ ይውላል ተብሎአል፡፡
የቁጫ የአገር ሽማግሌዎች በጠቅላይ ሚ/ሩ ጽህፈት ቤት ተገኙ
ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 60 የሚጠጉ የወረዳዋ ሽማግሌዎች በዛሬው እለት ለ7ኛ ጊዜ በጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽሀፈት ቤት ቢገኙም ጠ/ሚኒስትሩን ሊያገኙዋቸው እንዳልቻሉና በተወካያቸው በአቶ ወርቁ በኩል መንግስት ጉዳዩን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሳውቃል የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ለኢሳት ገልጸዋል።
በመንግስት መልስ ደስተኞች ያለሆኑት የአገር ሽማግሌዎች፣ እንደገና ተመልሰው ወደ ክልሉ ዋና ከተማ አዋሳ ማቅናታቸው ታውቋል። ሽማግሌዎቹ ለጠ/ሚንስትር ሀይለማርያም ተወካይ ፣ ወደ ቦታችን ስንመለስ እንደማንታሰር ዋስትና ይሰጠን በማለት ቢጠይቁም፣ ተወካዩ የሚያስሩዋችሁ ከሆነ በቀጥታ ደውሉልኝ ብለው ስልካቸውን እንደሰጡዋቸው ገልጸዋል።
የአገር ሽማግሌዎች ወደ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጽ/ት ቤት ለመሄድ ያስገደዳቸው በወረዳው የሚታሰረው ሰው ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱና ይህን ተከትሎም ግጭት ሊነሳ ይችላል የሚል ስጋት በመኖሩ አስቀድሞ ለማሳወቅ ነው ብለዋል።
በአካባቢው እየደረሰ ያለው የመብት ጥሰት ፣ በአገሪቱ መንግስት አለ ወይ የሚያስብል መሆኑን ከሽማግሌዎቹ አንዱ ተናግረዋል።
እስካሁን ድረስ ቁጥሩ በትክክል ባይታወቅም ከ90 እስከ 100 የሚደርሱ ሰዎች መታሰራቸውን ሽምግሌዎቹ ይናገራሉ።
መረጃውን ከቀበሌ ቀበሌ በማመላለስ ግጭት እንዲፈጠር ያደርጋሉ የተባሉ 160 ባጃጅ የሚባሉ ተሽከርካሪዎች አሁንም ፖሊስ ጣቢያ ቆመዋል። ከ30 በላይ ሰራተኞችም ተባረዋል።
የቁጫ ወረዳ ነዋሪዎች በቋንቋችን እንጠቀም፣ ሌሎች መብቶቻችን ይከበሩልን የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸው ይታወቃል።
አምስተኛው ባርነት – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)
በጥንቱ ስርዓት፣ አንድ ሰው ከአራቱ በአንዱ መንገድ ባሪያ ይሆናል። የመጀመሪያው በጦርነት ተሸንፎ ከተማረከ ፣ ሌላው እዳውን መክፈል አልችል ብሎ በእዳ ከተያዘ ፣ ሶስተኛው ከባሪያ ቤተሰብ የተወለደ ከሆነ በውርስ፣ አራተኛው ደግሞ ባሪያ ፈንጋዮች ይዘው ከሸጡት ነው። በዚህ ዘመን የባሪያ ንግድ ቢጠፋም፣ ባርነት ግን አልጠፋም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንዲያውም አምስተኛውን የባርነት መንገድ እያየን ነው፤ ይሄ ባርነት በባህሪው እስከዛሬ ከታዩት ሁሉ የተለየና አስገራሚም ነው። እመለስበታለሁ።
ባሪያ ማለት፣ የጌታውን እጅ አይቶ የሚያድር፣ በራሱ ነጻነት የሌለው፣ ሰምቶ የመቀበል እንጅ ሰምቶ የመመለስ መብት የሌለው፣ በግዑዝና በነጻ-ሰው መካከል ያለ ፍጥረት ነው። ባርያ ሰውን ሰው የሚያደርገውን ነጻነት ሙሉ በሙሉ የተገፈፈ በመሆኑ፣ ከሰው ተርታ የሚመደበው ስለሚመገብ፣ ስለሚለብስ፣ መጠለያ ስላለው፣ ቋንቋ ስለሚጠቀም እና አውራጣት ስላለው ብቻ ነው፤ ከዚያ በተረፈ ግን የጭነት እንስሳ ማለት ነው። ባሪያ በእግዚአብሄር አምሳል በመፈጠሩ ክፉና ደጉን የመለየት ስልጣን ቢሰጠውም ፣ ስልጣኑን በጌታው በመነጠቁ ፣ ሁልጊዜ የጌታውን ደግ ነገር ብቻ እያየ እና እያመሰገነ የሚኖር ፍጥረት ነው።
በአሁኑ ጊዜ የሚታየው አምስተኛው የባርነት መንገድ 40 በ60 ከሚባለው የቤት ግንባታ ጋር የተያያዘ ነው፤ በዚህ የባርነት መንገድ ለመጓዝ የወሰነው ደግሞ ዲያስፖራው ( በውጭ የሚኖረው) ኢትዮጵያዊ ነው። መንግስት ለዲያስፖራው 40/በ60ን ሲያዘጋጅ ሁለት አላማዎችን ታሳቢ አድርጎ ነው- ዲያስፖራው ጥሮ ግሮ ያገኘውን ሀብት ሰብስቦ ደቋናውን ለመሙላት እና ዲያስፖራው ስለነጻነቱ እንዳይጠይቅ ወይም መንግስትን እንዳይቃወም አፍ ለማዘጋት።
40 /በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራ እናት እና አባቱ፣ እህትና ወንድሙ፣ በአጠቃላይ የአገሩ ሰዎች ቢገደሉ፣ ቢታሰሩ ፣ ቢሰደዱ፣ ቢራቡ ፣ ቢጠሙ፣ ” ለምን?” ብሎ አደባባይ ወጥቶ የመጠየቅ እና የመቃወም ነጻነት አይኖረውም፤ ነጻነቱን በ40/በ60 ተገፎአል። ለሌላው መብት ሊሟገት ቀርቶ፣ በጥፊ ቢመታም እንኳን፣ “ጥፊው እንዴት ይጣፍጣል፣ እባክህ ግራ ጉንጨንም ድገምልኝ” ከማለት ውጭ፣ “ለምን ትመታኛለህ?’ ብሎ የአባትና እናቱን ወኔ ቀስቅሶ ብድሩን የመመለሻ ልብ አይኖረውም። እስክንድር ነጋ፣ አበበ በለው፣ ብርሀኑ ነጋ፣ እና ሌሎችም፣ ከስጋቸው ድሎት ነጻነታቸውን ያስቀደሙ በርካታ ኢትዮጵያውያን፣ ባርነት በቃን በማለታቸው፣ ጥረው ግረው ያፈሩትን ሀብት ተነጥቀዋል።
40/በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራ ስለወገኑ ለመጮህ ከእንግዲህ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ከተሞች እጅግም አይታይም፣ ለይሉንታ ቢታይ እንኳ ፊቱን በወረቀት ሸፍኖ ከሁዋላ ከመሰለፍ የዘለለ ሚና አይኖረውም። በነጻነት አገር እየኖሩ ገንዘብ ከፍሎ፣ በፍላጎት ባርነትን መምርጥ ማለት ይህ አይደለምን? የሚገዛ የለም እንጅ እነዚህ ሰዎች እኮ መንግስት ቢሸጣቸው እንኳ ምንም የሚናገሩ አይደሉም። ገንዘብ ተከፍሎ ባሪያ አድርጉን ብሎ የሚጠየቅበት አሰራር በታሪክ ታይቶ ይታወቃልን?
በአገር ቤት ያለው ህዝብ ለ 20/በ80 ቢመዘገብ አይገርመኝም፤ በባርነት ውስጥ የሚኖር ህዝብ በመሆኑ፣ አንድ ቀን ራሱን ነጻ እስኪያወጣ፣ ለጊዜው ተመችቶት ይኑር። ባሪያም እኮ ልብሱን ይቀይራል፣ የምኝታውን ሳር ተባይ ሲወርበት በሌላ ሳር ይተካዋል፤ ባበርነት ስር ያለው የአገር ቤት ሰው በነፍሱም በስጋውም ሊበደል አይገባውም፤ ቢያንስ እስከ ጊዜው በስጋው ይደሰት። ዲያስፖራው ግን የኢትዮጵያን ምድር ከለቀቀባት ጊዜ ጀምሮ ከባርነት ነጻ ወጥቷልና በነጻነት መኖር የሚችለበት እድል አለው፤ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ነጻነት ለመታገል ሁኔታው ተመቻችቶለታል፤ ይህን ነጻነቱን ግን እራሱ ገንዘብ ከፍሎ ሊሸጠው ይደራደራል። ፍርፋሪ እየተጣለለት ወደ ቄራ የሚወሰድ እሪያ መጨረሻው ሞት እንደሆነው ሁሉ፣ 40/በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራም መጨረሻው ባርነት ነው። አምስተኛው ባርነት!
ኢሕአፓ፣ እኔ እማውቀው፣
አምስተኛው ባርነት፤ ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)
በጥንቱ ስርዓት፣ አንድ ሰው ከአራቱ በአንዱ መንገድ ባሪያ ይሆናል። የመጀመሪያው በጦርነት ተሸንፎ ከተማረከ ፣ ሌላው እዳውን መክፈል አልችል ብሎ በእዳ ከተያዘ ፣ ሶስተኛው ከባሪያ ቤተሰብ የተወለደ ከሆነ በውርስ፣ አራተኛው ደግሞ ባሪያ ፈንጋዮች ይዘው ከሸጡት ነው። በዚህ ዘመን የባሪያ ንግድ ቢጠፋም፣ ባርነት ግን አልጠፋም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንዲያውም አምስተኛውን የባርነት መንገድ እያየን ነው፤ ይሄ ባርነት በባህሪው እስከዛሬ ከታዩት ሁሉ የተለየና አስገራሚም ነው። እመለስበታለሁ።
ባሪያ ማለት፣ የጌታውን እጅ አይቶ የሚያድር፣ በራሱ ነጻነት የሌለው፣ ሰምቶ የመቀበል እንጅ ሰምቶ የመመለስ መብት የሌለው፣ በግዑዝና በነጻ-ሰው መካከል ያለ ፍጥረት ነው። ባርያ ሰውን ሰው የሚያደርገውን ነጻነት ሙሉ በሙሉ የተገፈፈ በመሆኑ፣ ከሰው ተርታ የሚመደበው ስለሚመገብ፣ ስለሚለብስ፣ መጠለያ ስላለው፣ ቋንቋ ስለሚጠቀም እና አውራጣት ስላለው ብቻ ነው፤ ከዚያ በተረፈ ግን የጭነት እንስሳ ማለት ነው። ባሪያ በእግዚአብሄር አምሳል በመፈጠሩ ክፉና ደጉን የመለየት ስልጣን ቢሰጠውም ፣ ስልጣኑን በጌታው በመነጠቁ ፣ ሁልጊዜ የጌታውን ደግ ነገር ብቻ እያየ እና እያመሰገነ የሚኖር ፍጥረት ነው።
በአሁኑ ጊዜ የሚታየው አምስተኛው የባርነት መንገድ 40 በ60 ከሚባለው የቤት ግንባታ ጋር የተያያዘ ነው፤ በዚህ የባርነት መንገድ ለመጓዝ የወሰነው ደግሞ ዲያስፖራው ( በውጭ የሚኖረው) ኢትዮጵያዊ ነው። መንግስት ለዲያስፖራው 40/በ60ን ሲያዘጋጅ ሁለት አላማዎችን ታሳቢ አድርጎ ነው- ዲያስፖራው ጥሮ ግሮ ያገኘውን ሀብት ሰብስቦ ደቋናውን ለመሙላት እና ዲያስፖራው ስለነጻነቱ እንዳይጠይቅ ወይም መንግስትን እንዳይቃወም አፍ ለማዘጋት።
40 /በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራ እናት እና አባቱ፣ እህትና ወንድሙ፣ በአጠቃላይ የአገሩ ሰዎች ቢገደሉ፣ ቢታሰሩ ፣ ቢሰደዱ፣ ቢራቡ ፣ ቢጠሙ፣ ” ለምን?” ብሎ አደባባይ ወጥቶ የመጠየቅ እና የመቃወም ነጻነት አይኖረውም፤ ነጻነቱን በ40/በ60 ተገፎአል። ለሌላው መብት ሊሟገት ቀርቶ፣ በጥፊ ቢመታም እንኳን፣ “ጥፊው እንዴት ይጣፍጣል፣ እባክህ ግራ ጉንጨንም ድገምልኝ” ከማለት ውጭ፣ “ለምን ትመታኛለህ?’ ብሎ የአባትና እናቱን ወኔ ቀስቅሶ ብድሩን የመመለሻ ልብ አይኖረውም። እስክንድር ነጋ፣ አበበ በለው፣ ብርሀኑ ነጋ፣ እና ሌሎችም፣ ከስጋቸው ድሎት ነጻነታቸውን ያስቀደሙ በርካታ ኢትዮጵያውያን፣ ባርነት በቃን በማለታቸው፣ ጥረው ግረው ያፈሩትን ሀብት ተነጥቀዋል።
40/በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራ ስለወገኑ ለመጮህ ከእንግዲህ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ከተሞች እጅግም አይታይም፣ ለይሉንታ ቢታይ እንኳ ፊቱን በወረቀት ሸፍኖ ከሁዋላ ከመሰለፍ የዘለለ ሚና አይኖረውም። በነጻነት አገር እየኖሩ ገንዘብ ከፍሎ፣ በፍላጎት ባርነትን መምርጥ ማለት ይህ አይደለምን? የሚገዛ የለም እንጅ እነዚህ ሰዎች እኮ መንግስት ቢሸጣቸው እንኳ ምንም የሚናገሩ አይደሉም። ገንዘብ ተከፍሎ ባሪያ አድርጉን ብሎ የሚጠየቅበት አሰራር በታሪክ ታይቶ ይታወቃልን?
በአገር ቤት ያለው ህዝብ ለ 20/በ80 ቢመዘገብ አይገርመኝም፤ በባርነት ውስጥ የሚኖር ህዝብ በመሆኑ፣ አንድ ቀን ራሱን ነጻ እስኪያወጣ፣ ለጊዜው ተመችቶት ይኑር። ባሪያም እኮ ልብሱን ይቀይራል፣ የምኝታውን ሳር ተባይ ሲወርበት በሌላ ሳር ይተካዋል፤ ባበርነት ስር ያለው የአገር ቤት ሰው በነፍሱም በስጋውም ሊበደል አይገባውም፤ ቢያንስ እስከ ጊዜው በስጋው ይደሰት። ዲያስፖራው ግን የኢትዮጵያን ምድር ከለቀቀባት ጊዜ ጀምሮ ከባርነት ነጻ ወጥቷልና በነጻነት መኖር የሚችለበት እድል አለው፤ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ነጻነት ለመታገል ሁኔታው ተመቻችቶለታል፤ ይህን ነጻነቱን ግን እራሱ ገንዘብ ከፍሎ ሊሸጠው ይደራደራል። ፍርፋሪ እየተጣለለት ወደ ቄራ የሚወሰድ እሪያ መጨረሻው ሞት እንደሆነው ሁሉ፣ 40/በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራም መጨረሻው ባርነት ነው። አምስተኛው ባርነት!