Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all 13695 articles
Browse latest View live

የሕወሐት ባለስልጣናት የአሜሪካ ቆይታ፤ የከዱ አሉ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

በአባይ ወልዱ የሚመራውና ሰባት ከፍተኛ የሕወሐት ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን በአሜሪካ አራት ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠመው በስፍራው የተገኙ ምንጮች አስታወቁ። ቡድኑ በዋሽንግተን ኢትዮጲያ ኤምባሲ በጀመረውና በመቀጠል በላስቬጋስ፣ ሲያትልና ካሊፎርኒያ ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ “አላማ” አድርጎ የያዛቸው ጉዳዮች እንደነበሩ የጠቆሙት ምንጮች፣ እነሱም፥ “የመለስ ፋውንዴሽን፣ የአባይ ግድብና የ40/60 የቤቶች ግንባታ.” ሲሆኑ፣ ለነዚህ ማስፈፀሚያ “ገንዘብ አዋጡ” የሚለው ዋናው ግብ እንደነበር አስረድተዋል። በተለይ ደግሞ « በትግራይ ተወላጁ ዘንድ ሕወሐት የለም፣ ተከፋፍሏል፣ ተዳክሟል፣ ፓርቲው ሰው የለውም፤» የሚለውን እራሱ ቡድኑ በማንሳት ለገዛ ጥያቄው መልስ ሲሰጥ « ሕወሐት አሁንም ሃይል አለው፤ አልተዳከመም» በማለት አድራጊ- ፈጣሪ በመሆን ስልጣኑን በበላይነት ተቆጣጥሮ እንደያዘና ቡድኑ የመጣውም “አይዟችሁ” ለማለት እንደሆነ መገለፁን በቅርብ የተከታተሉት ምንጮች አስታውቀዋል። ቡድኑ በተጨማሪም ፥ « ልማት አልምተናል፤ ትግራይ እየለማ ነው፤ ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረገነው ነው» ከማለቱ ባሻገር « በትግራይ ተወላጁ ላይ አደጋ ተደቅኗል፤ የሙስሊሙ፣ የትምክህተኞችና የሽብርተኞች አደገኛ እንቅስቃሴ እያንዣበበ መሆኑን፣…የተደቀነብህን አደጋ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤ ያለበለዚያ ግን ሊያጠፉህ ነው፤» ሲሉ መናገራቸውን የገለፁት ምንጮች አክለውም፣ « አባላት የሆናችሁ ተወደደም ተጠላ መሬትና መኖሪያ ቤት እንሰጣችኋለን፤ ለዚህም ከእኛ ጎን መሰለፍ አለባችሁ» በማለት ሊሸነግሉ መሞከራቸውን ጠቁመዋል።

ከዋሽንግተን ስብሰባ (ለሁለት ተከፍሎ ነው የተካሄደው) በኋላ ወደ ሶስቱ ከተሞች ተከፋፍለው እንደሄዱ ሲታወቅ፥ ሲያትል አቶ ብርሃነ ማረት፣ እንዲሁም ላስቬስጋስ አባይ ወልዱና ተክለወይኒ አሰፋ መሄዳቸው ታውቋል። በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ የገጠማቸው እነአባይ ስብሰባው ከቀኑ 2፡00 ሰዓት ይጀመራል ተብሎ ከአራት ሰዓት በኋላ ዘግይቶ አመሻሽ ላይ መጀመሩን ምንጮች ገልፀዋል። ስብሰባው ሲጀመር ከላይ የተገለፁትን ጉዳዮች ያደመጠው ተሰብሳቢ ተከታዮቹን ጥያቄ አቀረበ፤ « ዴሞክራሲ አለ ትላላችሁ፣ ነገር ግን ዴሞክራሲ የለም፤ በሃሳብ የሚቃወማችሁን ታስራላችሁ፣ ታንገላታላችሁ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ ታካሂዳላችሁ፤ ከእናንተ የተለየ ሃሳብ ያለውን ትፈራላችሁ፤ ለምንድነው ይህን ሁሉ የምታደርጉት?….በማ.ረ.ት.(ማህበር ረድኤት ትግራይ) በትግራይ ሕዝብ ስም የምትሰበስቡትን ገንዘብ ለአራጣ ብድር እና ለፖለቲካ መጠቀሚያ በመሳሪያነት እያዋላችሁት ነው። ለምን?….ትእምት (ኤፈርት) ማነው ባለቤቱ?..በማን ነው የሚመራው?..ማነው የሚቆጣጠረው?..ለመሆኑ ኦዲት ተደርጎ ያውቃል ወይ?..እነማናቸው እየተጠቀሙበት ያለው?» የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ጥያቄዎች እንደነበሩ ምንጮቹ የጠቆሙ ሲሆን፣ አባይ ወልዱ « እኔ አልመልስም፣ ተ/ወይኒ መልስ ይስጥበት» ቢሉም ነገር ግን ግልፅና አግባብ ያለው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ወደ ማመናጨቅና ቁጣ ያመሩት ተ/ወይኒ በዚህ ድርጊታቸው በርካታ ተሰብሳቢዎችን እንዳሳዘኑ አስረድተዋል። በዚህ የተበሳጨው ተሰብሳቢ « ጥያቄያችን አልተመለሰም» በማለቱና ሁከትና ያለመደማመጥ በማየሉ ስብሰባው እንዲቋረጥ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮች፣ የጥያቄና ተቃውሞው መብዛት ያስደነገጣቸው ባለስልጣናቱ የመረጡት ማምለጫ በላስቬጋስ ተወካያቸው በሆነውና መድረክ ሲመራ በነበረው አቶ ተወልደ በኩል፥ « አዳራሹን የተከራየንበት ሰአት አብቅቷል፤ ስለዚህም ስብሰባው አብቅቷል » በማለት በአስቂኝ ሰበብ መቋረጡን አያይዘው ገልፀዋል። እነአባይ ከአዳራሹ ሲወጡ ቀድሞ ውጭ ሆኖ ይጠብቃቸው በነበረው ተሰብሳቢ ውግዘትና ስድብ እንደደረሰባቸው ያስታወቁት ምንጮች « ሌባ..ሌባ…ሙሰኞች..» የሚሉ ተቃውሞዎች ጎላ ብለው እንደተሰሙ አመልክተዋል።

ስብሰባዎቹን የታዘቡ ወገኖች በሰጡት አስተያየት እንዲህ ብለዋል፤ « በአንድ በኩል ልማት እያካሄድን ነው፤ እያሉና ገንዘብ እየጠየቁ በሌላ በኩል “ትግራዋይ አደጋ ተደቅኖብሃል፣ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤” ማለት እርስ በርሱ የሚጋጭና ድጋፍ የማግኛ የፖለቲካ የፖለቲካ ቁማር ነው። ያልተጠየቁትን የፓርቲውን ህልውና (ስለ ሕወሐት) አንስቶ መነገሩም አስገራሚና አጠያያቂ ነው።» ሲሉ ትዝብታቸውን የጀመሩት እነዚህ ወገኖች በማያያዝም፥ « እነዚህ ሰባት ባለስልጣናት ወደ አሜሪካ የመጡት ከነዘመዶቻቸው፣ ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ሲሆን፣ ባለስልጣናቱ የመንግስት ወኪሎች እንደመሆናቸው – በማን ገንዝብ ነው የሚንቀሳቀሱት?..የሚለው መጠየቅ አለበት። በሕዝብ ገንዝብ እየተንፈላሰሱ እንደሆነ ግልፅ ነው። የትግራይ ተወላጁን ብቻ ለይተው ስብሰባ የሚጠሩት ለምንድነው?…በእርግጥ ስላሰቡለት ነው?…የሚሉት ሲፈተሹ .መልሱ በጭራሽ አይደለም ነው። አላማቸውና ትኩረት የሰጡት የትግራይ ተወላጁን እየተንከባከቡት እንደሆነና ተጠቃሚ መሆኑን ለማሳየት በመፈለግ፣ እግረ-መንገዳቸውን ከቀሪው ኢትዮጲያዊ ወገኑ ጋር በመነጠል..ድጋፍ ለማግኘትና በውስጣቸው የተፈጠረውን ቀውስ በዚህ በኩል ቀዳዳውን ለመድፈን የሚደረግ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ስልት ነው። ..ደግሞስ ሕወሐት “አጋር” ከሚላቸው ብ.አ.ዴ.ን፣ ኦ.ህ.ዴ.ድ.፣ ደቡብ ሕዝቦች ተለይቶ፣ በሕዝብ ገንዘብ ስብሰባ የሚጠራበትና ያሻውን የሚያደርግበት አግባብ ምንድነው?..የሚለው ከዚህ ጋር መታየት ያለብት ነው። ፖለቲካዊ ፍጆታና ማንአለብኝነት በፓርቲው በመነገሱ እንደሆነ ደግሞ ግልፅ ነው።» ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ አሜሪካ ከመጡት ሰባት የሕወሐት ባለስልጣናት መካከል- ማለትም አባይ ወልዱ፣ ብርሃነ ኪ/ማሪያም፣ ተ/ወይኒ አሰፋና ዳንኤል አሰፋ በዋነኛነት ሲጠቀሱ፣ ከሰባቱ ሶስቱ ስብሰባውን ሳያካሂዱ ከቡድኑ ተገንጥለው በአሜሪካ መቅረታቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል። ቤተሰቦቻቸውን ይዘው (ልጆቻቸውን ጭምር) በመምጣት አሜሪካ ጥገኝነት ጠይቀው መቅረትን የመረጡት ባለስልጣናት ውስጥ የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባላት እንዳሉ ያረጋገጡት ምንጮች በቅርቡ ዝርዝሩን ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።


በብሔርተኝነት ስም ታሪክንና የኢትዮጵዊነትን መንፈስ ማጣጣል ተቀባይነት የለውም በፍቅር ለይኩን

$
0
0

በአንድ ወቅት በደቡብ አፍሪካዊቷ ከተማ በኬፕታውን የሚኖር አንድ በንግድ ሥራ የሚተዳደር ኢትዮጵያዊ ጎልማሳ አንድ አሳዛኝ ገጠመኙን እንዲህ አጫውቶኝ ነበር፡፡ ይህን ታሪኩን ያካፈለኝ ኢትዮጵያዊ ጎልማሳ የሥራ ቦታው ላይ ከአንድ ከኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ጋር በተነሳ ጠብ በተፈጠረ ግጭት የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆነው ጓደኛውን አንድ የፊቱን ጥርሱን በቦክስ ያወልቀዋል፡፡ የጥርሱን መውለቅ የሰሙ የዚህ ሰው ጓደኞችም ተሰባስበው ይህን ሰው ካልገደልን በማለት ሲጋበዙ ነገሩ በሰላም ያልቅ ዘንድ አንዳንድ የሚያውቋቸው ሰዎች ለሽምግልና ጣልቃ ይገባሉ፡፡

በሽምግልና ድርድር ላይ እያሉም የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆነው ጓደኛውን ጥርስ ያወለቀው ሰው የአያቱ ስም የኦሮሞ ስም ሆኖ ይገኛል፡፡ እነዛም በእንዴት ተደፍረን፣ ይህን ሰው ካልገደልን በማለት ሲዝቱ የነበሩ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችም፣ ይኽ ሰው ለካ ወገናችን ነው በማለት ለበቀል ያነሱትን ሰይፋቸውን ወደ ሰገባው ይመልሳሉ፡፡ ሐሳባቸውን በመቀየር ጉዳዩ በሰላም ተቋጭቶ፣ በሃያ ሺሕ የደቡብ አፍሪካ ራንድ ካሳ ክፍያ እንዲጠናቀቅ ተስማምተው እርቅ ማውረዳቸውንና አያቴ ስም የኦሮሞ ስም በመሆኑ ከጉድ ወጣሁ ሲል በግርምት መንፈስ ሆኖ ገጠመኙን አጫወተኝ፡፡

ይህ ሰው እስከዛች ቀን ድረስ ስለ አያቱ ኦሮሞነትም ሆነ ስለመጣበት ብሔር ወይም ጎሳና ማንነት በቅጡ አስቦ ወይም ትዝ ብሎት እንደማያውቅና ይህ ገጠመኙ ግን ከሚኮራበት ከኢትዮጵያዊነት ማንነቱ ባሻገርም ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ስለሰኟት ሕዝቦቿ ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ቅርስ ለማጥናት የማንቂያ ደወል ሆነኝ ሲል ነግሮኛል፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ሰው በተለያዩ ጊዜያት ወደ ደቡብ አፍሪካ በስደት የገቡና ኖሮአቸውን በዛው ያደረጉ የኦሮሞ ተወላጆች ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ በሚያቀርቡበት ወቅት የተፈጠረውን እሰጥ አገባም እንዲህ ጨምሮ ተርኮልኛል፡፡

የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ሆኑ ስደተኞች ለፖለቲካ ጥገኝነት ብቁ የሚያደርጋቸውን ቅፅ በሚሞሉበት አጋጣሚ አብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች ዜግነት ወይም አገር በሚለው ክፍት ቦታ ላይ ‹‹ኦሮሚያ›› በማለት በመሙላታቸው የደቡብ አፍሪካ ‹‹ሆም አፌር ቢሮ›› የሥራ ባልደረቦች እኛ ‹‹ኦሮሚያ›› የሚባል አገር አናውቅም በማለታቸው በተነሳ ክርክር፣ እነዚህ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆኑ የፖለቲካ ጥገኝነት ፈላጊዎች፣ ‹‹ኦሮሚያ በቀድሞዋ አቢሲኒያ በአሁኗ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ስር ምትማቅቅ አገር ናት፡፡›› በማለት በማስረዳት ዜግነት በሚለው ክፍት ቦታ ላይ ‹‹ኦሮሚያ›› የሚለው ማንነታቸው እንዲሞላላቸው ቢጠይቁም ተቀባይነት በማጣታቸው እየጎመዘዛቸው ቢሆንም የማያምኑበትን የኢትዮጵያዊ ዜግነት በክፍት ቦታው ላይ ይሞሉ እንደነበር ይህ ሰው ጨምሮ ነግሮኛል፡፡

ይህንና ይህን የመሳሰሉ ብሔርን ማእከል ያደረጉ አሳዛኝ ገጠመኞች በኢትዮጵያም ሆነ በውጭ አገር ተደጋግመው የሚከሰቱ መሆናቸው ደጋግምን ያየነውና የሰማነው እውነታ ነው፡፡ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ በአውስትራሊያና በደቡብ አፍሪካ ዛሬ ዛሬ በትግሬ፣ በአማራ፣ በኦሮሞ … ወዘተ ስምና ማንነት የራሳቸውን ወሰን ወስነውና አጥር ከልልው የሚኖሩና ይህና ያ ብሔር በእኔና በዚህ ብሔር ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል፣ ግፍና ጭቆና አድርሶብናል በሚል የየራሳቸውን የጭቆና ታሪክና የተጋድሎ ገድል ጽፈውና አጽፈው ያሉ፣ ከዚህም የተነሳ ደግሞ ለበቀል የሚፈላለጉና በጎሪጥ የሚተያዩ ሕዝቦች ኢትዮጵያ በምትባለው ምድር ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው፡፡

ይህን ከላይ በመግቢያችን የገለጽኩትን አሳዛኝ ገጠመኝ ወይም ታሪክ ለዚህ ጹሑፍ መግቢያ ይሆነኝ ዘንድ የመረጥኩት ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ስለ ኢትዮጵያዊነትና ኦሮሙማ (ኦሮሞ ናሽናሊዝም) በተመለከተ ‹‹በገዳ ዶት ኮም›› እና በሌሎች በተለያዩ ድረ ገጾች ሰፋ ያለ ውይይትና ክርክር ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህ ከስምንት የማያንሱ ማእከላቸውን አውሮፓና አሜሪካ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የኦሮሞ ምሁራን ባደረጉት ውይይትና ክርክር ከተሳተፉት ፖለቲከኞችና የኦሮሞ ምሁራን መካከል ዶ/ር በያን አሶቦና ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ይኸው የኢትዮጵያዊነትና የኦሮሙማ ሙግትም የፓል ቶክ ዋና የመወያያ ርዕስ ሆኖ ነበር፡፡ ይህ ውይይትና ክርክር ገና ሳይበርድና ሳይቋጭ ነበር በዛው ሰሞን ወጣቱ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና ተንታኝ ጃዋር ሙሐመድ ከአልጄዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ለዓመታት በዘለቀው የኦሮሞ ጥያቄ፣ የነፃነት ትግል ታሪክ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ የሰጠው፡፡ ጃዋር I am First Oromo. Ethiopia is imposed on me የሚለው አቋሙን ግልጽ ካደረገ በኋላ የኦሮሞን ታሪክና የኦሮሞን የዓመታት ጥያቄ በተመለከተ የፖለቲካ ተንታኙን የጃዋርን ትንታኔና አቋም በመቃወምም ይሁን በመደገፍ የተለያዩ ሐሳቦች መንሸራሸር ጀመሩ፣ አሁንም ድረስም እየተንሸራሸሩ ነው፡፡

ባለፉት ሰሞናትም በተለያዩ በይነ መረቦችና በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይም የጃዋርን ሐሳብ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች በየበኩላቸው አቋማቸውን ለመግለጽ ሞክረዋል፡፡ አንዳንዶችም ስድብ ቀረሽ በሚመስል ጨዋነትና ቅንነት በጎደለው መንፈስ ጃዋር ባነሳው ሐሳብ ላይ የውይይት መድረኩን የሚያጠለሹና የሚበርዙ እሳቤዎችን ከስድብ፣ ከዛቻና ከማስፈራሪያ ጭምር ሲያዘንቡም ታዝበናል፡፡ ከዚህ ውጪ ደግሞ ሰብአዊ ፍቅር፣ ጨዋነትና ቅንነት በተሞላበት መንፈስ ከኦሮሞም ይሁን ከሌላ ብሔር ተወላጆች ዘንድ፣ ሚዛናዊ የሆነ፣ ከጭፍን ጥላቻና ከበቀል ስሜት በጸዳ መንፈስ ሐሳባቸውንና አቋማቸው የገለጹም ጥቂት ጸሐፊዎችና ተንታኞችም ብቅ ብቅ ብለው ነበር፡፡

እኔም በዚሁ ሰሞነኛ በሆነው የኦሮሞ ሕዝብን ታሪክና ጥያቄ በተመለከተ ለኦሮሞ ሕዝብ ነፃነትና መብት ቆመናል በሚሉ አንዳንድ የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች ዘንድ በኦሮሙማ (በኦሮሞ ናሽናሊዝም)፣ በኢትዮጵያ ታሪክና በኢትዮጵያዊነት ላይ በሚያነሷቸው አንኳር ሐሳቦችና በሚያራመዱት አቋሞቻቸው ዙሪያ ላይ ጥቂት የመወያያ ሐሳቦችን ለማጫር ወደድኩ፡፡
በእርግጥ ይህ ለውይይት ማጫሪያ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ አጭር ጽሑፍ የኦሮሞ ተወላጅ ምሁራንና ፖለቲከኞችን፣ አሊያም ደግሞ በኦሮሞ ሕዝብ ስም ተቋቋመው እየተንቀሳቀሱ ያሉ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ታሪክና በኢትዮጵያዊነት ላይ ያላቸውን አቋማቸውንና ለኦሮሞ ሕዝብ አለን ስለሚሉት የትግል አቅጣጫዎቻቸውን ለመተንተን፣ ለመተቸትና ለመገምገም አይደለም አነሳሱ፡፡ ይህን ለማድረግ እንሞክር ቢባል እንኳን በእነዚህ ጥቂት ገጾች ለመሞከር የሚታሰብ አይሆንም፡፡

ለዚህም እንደ ዋና ሆነው ከሚነሱት ዐበይት ምክንያቶች መካከል ደግሞ በኦሮሞ ሕዝብ ስም እየተንቀሳቀሱ ያሉ በዓላማም በአቋምም የተለያዩ ፓርቲዎች መኖራቸው፡፡ እንዲሁም እነዚሁ ፓርቲዎችም የኦሮሞን ሕዝብን ታሪክና ጥያቄ በተመለከተ የሚያራምዷቸው አቋሞችና ጥያቄዎች ‹‹ከባርነት ወይም ነፃነት›› ወይም ደግሞ ‹‹ከአቢሲኒያ/ከዛሬዋ ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነፃ የመውጣት ጥያቄ ነው፡፡›› ከሚለው ፖለቲካዊ አቋም አንስቶ በተለያዩ የኦሮሞ ተወላጅ ምሁራንና ፖለቲከኞች ዘንድ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ባሉ የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ፣ ባህል፣ እምነትና ቅርስ አኳያ ያሉት አመለካከቶችና ትንታኔዎች መንገዳቸው የየቅል መሆኑን ነገርዬውን ቀላል አያደርገውም ብዬ ስለምገምት ነው፡፡

ለአብነትም ያህል የኦሮሞን ብሔርተኝነት በእጅጉ ያራምዱና ‹‹የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የነጻነት ጥያቄ ነው፡፡›› ሲሉ የነበሩ አንዳንድ የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች በጊዜ ሂደት ኦሮሞ በኢትዮጵያ በቆዳ ስፋት ትልቁና የሕዝቡም ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ውስጥ ግዙፍ ሆነ ቦታ ሊሰጠው ይገባል፣ የኦሮሚፋም በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግሥት ፖለቲካ አሥተዳደር ውስጥ የፌዴራል መንግሥቱ ቋንቋ መሆን የሚችልበት መንገድ ሊታሰብብት ይገባዋል፣ የሚሉ የተለሳለሱ አቋሞችን የሚያራምዱ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ፖለቲከኞችም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብቅ ብቅ ማለታቸውንም ታዝበናል፡፡
ስለሆነም በዚህ ጽሑፍ የኦሮሞን ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነት፣ የኦሮሞን የመብት ጥያቄና ትግል ተመለከተ በፊትም ሆነ በተለይም ደግሞ ከሰሞኑን የፖለቲካ ተንታኙ ጃዋር ሙሐመድ ባነሳው የኢትዮጵያዊነትና የኦሮሙማ አንኳር እሳቤዎች ላይ ተመርኩዤ ጥቂት ነገሮችን ለማለት ወደድኩ፡፡

እንደሚታወቀው ባለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት ውስጥ የእከሌ ብሔር ወይም ጎሳ በዚህኛው ብሔር ወይም ጎሳ ላይ ለፈጸመው በደልና ጭቆና በሚል ያልተወራረዱና ጊዜ እየጠበቁ ቦግ እልም የሚሉ ምሬቶችን፣ ቁጣዎችንና የበቀል ሰይፎችን በተለያዩ የአገራችን ክልሎች መከሰታቸውን ታዝበናል፡፡ ይህን እኩይ የሆነ የበቀል ሒሳብ በማወራረድ የተጠመዱ አንዳንድ ፓርቲዎች፣ ፖለቲከኞችና ግለሰቦችም ሆን ብለውና ያልተገባ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግበስበስ ሲባል እውነታን በማጣመም በሚጻፏቸውና በሚያጽፏቸው የተዛቡ የታሪክ ድርሳናትና ገድሎቻቸው፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ትናንትና ያልነበረ ዛሬም የሌለ ቅዠት ወይም ሕልም ነው እስኪባል ድረስ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በርካታ ትንታኔዎቻቸውን ሰምተናል፣ የዳጎሱ ጥናታዊ ጽሑፎቻቸውንም አስነብበውናል፡፡
በዚህ እነዚሁ የብሔር ፖለቲካ ጽንፈኞች፣ በቀልን ሰባኪዎች፣ የብሔራዊ መግባባትና እርቅ ተቀዋሚዎች በተጻፉ የተዛቡ ታሪኮችና ያልተወራረዱ የበቀል ሒሳቦች ክፉ ስብከት የተነሣም ለዘመናት ተዋደውና ተከባብረው፣ በጋብቻና በአምቻ ተሳስረው፣ እኔ ትብስ አንተ ትብስ ብለው የኖሩ ሕዝቦች የተሳሰሩበትን የአንድነት ድርና ማግ ለመበጠስ ሲባል የተደረጉ አያሌ ዘመቻዎችንም በዘመናችን በሐዘንና በግርምት ሆነን አስተውለናል፡፡
ዛሬም ድረስ ለኦሮሞ ሕዝብ መፍትሔው የእኔ የፖለቲካ አቅጣጫ ነው የሚሉ በርካታ የኦሮሞ ምሁራን፣ ፖለቲከኞችና ፓርቲዎች በአገር ውስጥና በውጭ አገር ሆነው ለኦሮሞ ሕዝብ ይጠቅማል በሚሉት መንገድ የራሳቸውን አቋም በማራመድ ይጻፋሉ፣ ይወያያሉ፣ ይከራከራሉ፣ ይሟገታሉም፡፡

ይሁን እንጂ እስካሁኗ ቅጽበት ለኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት፣ መብትና ጥቅም ቆመናል በሚሉት በበርካታ የኦሮሞ ፖለቲከኞች፣ ምሁራንንም ሆነ ፓርቲዎች ዘንድ ቢያንስ ባለፉት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት የኦሮሞን ሕዝብ ታሪክና ጥያቄ በማስተጋባትና በመፍትሔ አቅጣጫዎችም ዙሪያ በሚያራምዱት አቋማቸው እርስ በርሳቸው የተለያዩና የተከፋፈሉ መሆናቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች ዐይተናል፡፡ በዋነኝነት የኦሮሞ ሕዝብን ጥያቄ ለመፍታት ከእኔ ወዲያ ለአሳር በማለት ሲምል ሲገዘት የነበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በዕድሜ የሚያክለውና የሚስተካከለው ባይኖርም ዛሬም ድረስ በተለያዩ ታሪካዊና ፖለቲካዊ ውስብስብ ችግሮች ተተብትቦ እየዳከረ ያለ ፓርቲ መሆኑን የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡

በተጨማሪም ባለፉት ዓመታት በፓርቲው አመራሮቹ መካከል በተፈጠረ ልዩነትና ውዝግብ የፓርቲው ህልውና አበቃለት እስኪባል ድረስ የነበረውና አሁንም በያዝ ለቀቅ በፓርቲው ውስጥ የሚነሱት ወጀብና ዐውሎ ንፋሶች ዛሬም ድረስ ገና መፍትሔና መቋጫ ያገኙ አይመስሉም፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው፣ ነፃነትን የማወጅ፣ ሉዓላዊነትን የማስከበር፣ የማንነት፣ የታሪክና ፖለቲካ ጥያቄ ነው፣ በማለት ጽንፈኛ አቋሙን በሚያራምደው ኦነግና ደጋፊዎቹ ዘንድ ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በሸዋው ንጉሥ በምኒልክ ሰይፍ ተቀጥቅጦ በአማራ ታሪክና ማንነት ላይ የተገነባ ነው የሚለው መከራከሪያቸው አሁንም ድረስ በአቋም ደረጃ በግልጽ የሚንጸባረቅ ነው፡፡

ወጣቱ የፖለቲካ ምሁርና ተንታኝ ጃዋር ሙሐመድም ይህንኑ ሐሳብ በመድገም እንዲህ ብሎአል፡- ‹‹ … ኢትዮጵያን የመሠረታት የሦስትዮሽ ጦርነት ግብግብ ነው፡፡ በአማራው፣ በኦሮሞው፣ በትግሬው ግብግብ ውስጥ ወደ መጨረሻ ላይ በአመራር ስር የበላይነቱን የያዘው አማራው ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ አሁን የምናያት ኢትዮጵያ ማንነቷ በአማራ ባሕላዊ ሥርጭትና በአማራ ፖለቲካ የተገነባች ነች፡፡ … የኢትዮጵያ አገራዊ ማንነት የምንለውም የአማራ ባህላዊ ማንነት ነው፡፡›› ሲል ከኢትዮጵያ ታላቅ ሥልጣኔ፣ ታሪክና ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ወይም ማንነት ጋር የሚጣረስ ድምዳሜን ሰጥቶአል፡፡
ይህ ዓይነቱ ትንታኔ የኢትዮጵያን ታሪክ በአግባቡ ያለመረዳት ቀውስ ወይም ደግሞ ሆን ብሎ የታሪክ እውነታን የማዛባት ዘመቻ ነው የሚመስለው፡፡ ኢትዮጵያ የምትባለው ምድርና ሕዝቦቿ ትናንትና ከመቶ ዓመት በፊት ምኒልክና ተከታዮቹ በኃይልና በሰይፍ በሚፈልጓት ቅርፅና ይዘት ቀጥቅጠው የፈጠሯት እንጂ የሚለው መከራከሪያ ሐሳብ በምንም መንገድ ውኃ ሊያነሳ የሚችል ሐሳብ አይመስለኝም፡፡ ይህ ዓይነቱ አመለካከት ከሺሕ ዓመታት በፊት ጀምሮ በገናና ሥልጣኔዋና ታሪኳ በዓለም መድረክ ስሟ ገኖ የወጣውን፣ ከአፍሪካ አልፎ በሰሜን አሜሪካና በካረቢያን በባርነትና በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር ተይዘው ሲማቅቁ ለነበሩ ሕዝቦች የነፃነት ምድር፣ የጥቁር ሕዝቦች ተስፋ ‹‹የጥቁር ሕዝቦች የከነዓን ምድር›› በሚል በሰቀቀንና በናፍቆት ሲያስቧትና ሲዘክሯት የኖረችውን ኢትዮጵያን ህልውና የመካድ ያህል የሚቆጠር ይመስለኛል፡፡

ኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የነፃነት ተምሳሌት፣ የአንድነትና የፍቅር ኪዳን ሆኖ በብዙዎች ልብ ውስጥ ሲንቀለቀልና ለዘመናት ሲያበራ የኖረ እውነት መሆኑን መካድ አንችልም፡፡ ከአፍሪካ አስከ አሜሪካ፣ ካረቢያና ጃማይካ ይህ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ በእውቁ የነፃነት ታጋይ በእነ ማርከስ ጋርቬይ፣ በሬጌው ንጉሥ በእነ ቦብ ማርሌይ፣ በእነ ፒተር ቶሽ፣ በአፍሪካውያኑ የነፃነት አባቶች፣ በእነ ጆሞ ኬንያታ፣ በንኩርማ፣ በማንዴላና በበርካታ የነፃነት ታጋዮች ዘንድ የሞራልና ወኔ ስንቅ ሆኖ ያገለገለ፣ ክቡር ታሪክ፣ ሕያው አሻራና ቅርስ መሆኑን መዘንጋት ከታሪክ ሐቅ ጋር መጣላት ነው የሚሆነው፡፡
በተጨማሪም ለዚህችው በሺሕ ዘመናት ገናና ሥልጣኔዋ፣ ነፃነቷ፣ ታሪኳና ሉዓላዊነቷ ሲሉ በዐድዋ ጦር ግንባር ከወራሪው የአውሮጳ ኃይል ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለሕዝቦቿም ነፃነት ዋጋ የከፈሉትን የኦሮሞ ተወላጆቹን የእነ ባልቻ አባ ነፍሶን፣ የእነ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪን፣ የእነ ራስ አበበ አረጋይን፣ አውሮጳ ምድር ድረስ ዘልቆ በሮማ አደባባይ የኢትዮጵያውያንን አይበገሬነትና ለነፃነታቸው ቀናኢ ሕዝብ መሆናቸውን ያሳየውን የአብዲሳ አጋንና የበርካታ እልፍ የሚሆኑ የኦሮሞ ልጆችን ለሰው ልጆች ነፃነት የፈሰሰ ደምና መሥዋዕትነት ማራከስ ነው የሚሆነው፡፡
ከሰሞኑን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩና አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕ/ር መረራ ጉዲና፡- ‹‹የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች፡- ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ እስከ ኢህአዴግ›› በሚል ርዕስ በጻፉት መጽሐፋቸውም በዓድዋው ጦርነት ከየትኛውም ሕዝብ ይልቅ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ጦር አዝማቾችና ጀግኖች ታላቅ መሥዋዕትነት መክፈላቸውን በመግለጽ የዓድዋ ድል የምኒልክን ቅኝ ግዛት ዘመቻ ያጠናከረ ዓውደ ግንባር ነው የሚለውን ሐሳብ አጣጥለው በመከራከር ጽፈዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ታላቅነትና አይበገሬነት በኦሎምፒክ መድረክ ከፍ ያደረጉ አበበ በቂላ፣ ዋሚ ቢራቱ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ደራርቱ ቱሉ … እነዚህ ሁሉ በሮጡበት መድረክ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ብሔርና ሃይማኖት ሳይለዩ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ አብረው ሮጠዋል፣ ስለ ኢትዮጵያ ክብርና ድልም አብረው አምጠዋል፣ ተጨንቀዋል፡፡ በባርሴሎና ኦሎምፒክ መድረክ አበባችን ደራርቱ ቱሉ በአሥር ሺሕ ሜትር የመጀመሪያቱ አፍሪካዊት ሴት ወርቅ ሜዳሊስት በሆነችበት ድሏ የአገሯ ብሔራዊ መዝሙርና ሰንደቅ ዓላማ በስፔን ሰማይ ላይ ሲናኝና ከፍ ብሎ ሲታይ በጉንጯ ላይ ኮለል ብሎ የፈሰሰውን ዕንባዋን የታዘብን ሁሉ፣ በኢትዮጵያዊነት ኩራትና አይበገሬነት መንፈስ አብረናት በደስታ ሲቃ አንብተናል፣ መሬት ስመናል፡፡
ይህን ታሪክ በወርቅ ቀለም የጻፈውን የበርካታ ኦሮሞ ጀግኖችን ገድልና ለኢትዮጵያዊነት የተከፈለ መሥዋዕትነትን ማቃለልና ታሪክን ማዛባት ጤነኛ አካሄድ አይደለም፡፡ በዘመናችን ኦሮሙማን/የኦሮሞን ብሔርተኝነት በእጅጉ የሚሰብኩና የሚያራግቡ ሰዎች በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ኦሮሙማን ወይም የኦሮሞ ብሔርተኝነነትን ለመገንባት ሲሉ የኢትዮጵያን የሺሕ ዘመናት ታሪክ፣ ሥልጣኔ፣ ቅርስና የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ ማጣጣልና መንኳሰስ ጤነኛ አካሄድ አይመስለኝም፡፡

ኢትዮጵያዊነት እንደ ኮሶ ተበጥብጦ በግድ እያነገፈገፈን የተጋትነው፣ እየቀፈፈንና እየኮሰኮሰን የተደረበብን ማንነት ብለው ለሚከራከሩ ሰዎች በእርግጥም በግድ ሳይወዱ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ተቀበሉ ብሎ ማስገደድ እንደማይቻል አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ኢትዮጵያዊ ለመሆን ያለመፈለግ መብታቸውንም በግሌ አከብራለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ታሪክን በማዛባት ጥቁር ሕዝቦች፣ መላው አፍሪካና በአጠቃላይ ነፃነትን አፍቃሪ የሆኑ ሕዝቦች ልብ ውስጥ ትልቅ ዋጋና ክብር ያለውን የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ ማራከስ፣ በኢትዮጵያና በሕዝቦቿን ታሪክ፣ ቅርስና ማንነት ላይ መዘባበት ጤነኛ አካሄድ እንዳልሆነ አሁንም በድጋሚ አስረግጬ ለመናገር እወዳለሁ፡፡

ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ ዳዊት ከበደ ወየሳ

$
0
0

የኢትዮጵያ ጀግኖች ታሪክ ሲነሳ፤ በግንባር ቀደም ከሚጠቀሱት መካከል ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ በዋናነት ይጠቀሳሉ። – በአባታቸው ኦሮሞ፣ በናታቸው የጉራጌ ተወላጅ የሆኑት ባልቻ ሳፎ (ባልቻ አባ ነፍሶ) በተለይ በ1888 ዓ.ም. በአድዋ ጦርነት ወቅት በአጼ ምኒልክ ስር ሆነው በመድፍ አስተኳሽነት በሰሩት ጀግንነት ይታወሳሉ። እኚህ ታላቅ ኢትዮጵያ ለአገራቸው እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ያደረጉት ታላቅ ጀብዱ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ ይኖራል። ስለስራቸውም ክብር ታላላቅ ቦታዎች በስማቸው ተሰይመዋል። ከነዚህም መካከል በሩስያውያን እርዳታ የተገነባው ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል፣ ደጃዝማች ባልቻ መንገድ፣ ደጃዝማች ባልቻ ትምህርት ቤት ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው። ጀግኖች ሲፈክሩና ሲያቅራሩ ስማቸውን እየጠሩ… “ዘራፍ የባልቻ አሽከር!” ብለውላቸዋል። በስማቸው መጽሃፍት ተጽፈዋል። ድምጻውያን አንጎራጉረውላቸዋል።

አሁን ወሊሶ በሚባለው ቦታ፣ በነሃሴ ወር የመጨረሻ ሳምንት፣ በ1854 ዓ.ም. ነበር የተወለዱት። እናም ይህ ሳምንት የልደት ቀናቸው የሚከበርብ ሳምንት ስለሆነ፤ ወደ ኋላ ተመልሰን ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶን እናስታውሳቸዋለን።

የትውልድ ዘር ሃረጋቸው ጉዳይ ብዙ ጊዜ አነጋጋሪ ስለሆነ፤ እዚህ ላይ መልስ ሰጥተንበት እናልፋለን። ባልቻ ሳፎ በአባታቸው የኦሮሞ ተወላጅ ሆነው የሮቢ የልጅ ልጅ ሲሆኑ፤ በናታቸው በኩል ደግሞ ጉራጌ የጭረት ከንፈሴን ናቸው። እኚህ ታላቅ ጀግና ገና በልጅነት እድሜያቸው በጦር ሜዳ ውስጥ የተገኙ ሰው ነበሩ። ነገሩ እንዲህ ነው። በድሮ ጊዜ ጦርነት ሲደረግ፤ አሸናፊው ወገን የተሸናፊውን ብልት መስለብ እንደጀግንነት ይቆጠራል። ምንም እንኳን ምኒልክ እንዲህ አይነቱን እርምጃ የሚደግፉት ባይሆንም፤ ከአቅማቸው በላይ በሆነ ሁኔታ ወታደሩ በጦርነቱ ወቅት ያገኛቸውን ወንዶች፤ የሚገደሉትን ገድለው በህይወት የተረፉትን መስለባቸው የተለመደ የጦርነት ባህል ሆኖ ቆይቷል። በዚህም ጦርነት ወቅት በታዳጊው ወጣት ባልቻ ላይ የደረሰበት ይህ አስከፊ ቅጣት ነበር።

በጦርነቱ የምኒልክ ሰራዊት ማሸነፉ ሲበሰር፤ ስለሞቱት እና ስለተማረኩት ሰዎችም ተነገራቸው። ከነዚህ ምርኮኞች መካከልም ብልቱን ተቆርጦ የተገኘ ብላቴና መኖሩ ሲነገራችው ምኒልክ እጅግ አድርገው አዘኑ። ከነዚያ ሁሉ ምርኮኞችም መካከል ይህንን ልጅ ወደሳቸው እንዲያቀርቡ አደረጉ። ብዙዎቹ ምርኮኞች በምህረት ሲፈቱ፤ ባልቻ አባ ነፍሶን ግን ምኒልክ ሊያሳድጉ ሃላፊነት ወስደው ወደ አዲስ አበባ ይዘውት መጡ። በዚህ አይነት ሁኔታ… ባልቻ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ በምኒልክ ቤተ መንግስት የአጼ ምኒልክ የቅርብ አንጋች ሆኖ፤ በጦር ሞያ ተኮትኩቶ አደገ። በጎልማሳነቱም ወቅት የመድፍ ተኩስ ተምሮ… አጼ ምኒልክ ከፈረንሳይ አገር የተሰጣቸውን መድፎች የሚተኩስ እና የሚያስተኩስ ጎበዝ ጀግና ወጣው።
(ባልቻ የሚለው የኦርምኛ ስማቸው ትርጉም “ምትክ” ማለት መሆኑን እዚህ ጋር ጠቅሰን ብናልፈውስ)

በኢትዮጵያ ውስጥ በተደረጉት ጦርነቶችም፤ መድፉን ወደ ጠላት ወረዳ ተኩሶ… ጠላትን የሚያርበደብድ ጀግና ሆነ። በተለይም ኢትዮጵያ ከጣልያን ጋር ባደረገችው የ1888 ዓ.ም. ጦርነት ወቅት፤ በመቀሌ፣ በአዲግራት እና በአድዋ ተራሮች መድፉን ጠምዶ፤ የጣልያንን ጦር ከርቀት በመምታት ዝናን ያተረፈ ጎበዝ ተሰኘ። በማዕረግ ላይ ሌላ ማዕረግ ተጨምሮለት… ደጃዝማች ተብሎ ስማችው በወርቅ ቀለም ከተጻፈላቸው ጀግኖች መካከል አንዱ ሆኖ ተጠራ። ከጦርነት እና ከጀግንነት ውጪ ሌላ ህይወት ለሌላቸው ለነደጃች ባልቻ አይነቶቹ ጀግኖች እንዲህ ተባለላቸው።

ለበኑም፥ መውዜሩም፥ መድፉም፥ መትረየሱም፥ አንድ ነው ብረቱ፤
ቈራጥ ያስፈልጋል ክትት ያለ ዐሞቱ።
————————————————
ጦር መጣ፤ ጦር መጣ፤ ጫፉን ነቀነቀው፤
ጐበዝን ደስ አለው፤ ፈሪንም ጨነቀው።” ተብሎላቸዋል— የዘመኑ ጀግኖች።

ሊቀመኳስ አባተና ባልቻ አባ ነፍሶ በመድፍ ስላደረጉት ፍልሚያ ቤርክሌይ ሲጽፍ፤ “ጣሊያኖች እንዳስላሴ ወጥተው ‘የእየሱስ ቤተ ክርስቲያንን ልቀቁ፤ ጦርነቱ ሲያልቅ በትልቅ ህንጻ እንሰራላችኋለን።’ አሏቸውና አንድ ሺህ ብር ሰጧቸው። ሁሉም ቤተክርስቲያኑን ሲልለቁ አንድ የሃምሳ አመት ቄስ ግን እምቢ አሉና ወዲያውኑ ተገደሉ። ከዚያም ቤተ ክርስቲያኑንና ቦታውን ጣልያኖች ተቆጣጠሩት። ሆኖም ክርስቲያን የሆኑ የጣሊያን ወታደሮች ‘ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብተን አንዋጋም’ በማለታቸው ክርስቲያን ያልሆኑ ወታደሮች እዚያ ገብተው ጦርነቱ ቀጠለ… ያ ቀን መጥፎ እለት ነበር። በጣሊያኖቹ ወገን ከእንዳስላሴ የሚተኮሰው መድፍ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ጨረሰ። በኢትዮጵያ በኩል የተተኮሰው የመድፍ ጥይት፤ የጣሊያኑ መድፍ አፍ ውስጥ ገብቶ ሁለት ወታደሮች አቆሰለ… እሳትም ተነስቶ አፈር የተሞሉ የምሽግ ጆንያዎች ተቃጠሉ።” ብሏል።
በነገርዎ ላይ አሁን አሁን በዘፈን፤ “ባልቻ አባ ነፍሶ መድፉን ጣለው ተኩሶ” ቢባልም፤ በትክክል መድፍን በመድፍ ተኩሶ የጣለው ግን ያኔ 25 አመት ወጣት መድፈኛ የነበረው አባተ ቧያለው (አባ ይትረፍ) ነበር። በዚያን ጊዜ ነው፤
“አባተ አባ ይትረፍ፣ ነገረኛ ነው፤
ይህን መድፍ፣ ከዚያ መድፍ፣ አቆራረጠው።” ተብሎ የተገጠመው።
(ደጃች ባልቻ በወቅቱ የ36 አመት ጎልማሳና የሊቀ መኳስ አባተ አዛዥ ነበሩ)
የካቲት 23 ቀን፣ 1888 ዓ.ም. የአድዋ ጦርነት እለት…. የጦሩ ዋና ፊታውራሪ ገበየሁ አባ ጎራው በጦርነቱ ላይ ሲሰዉ አጼ ምኒልክን ጨምሮ ብዙዎች አዘኑ። በዚህን ጊዜ ምኒልክንም ሆነ ህዝቡን ለማጽናናት፤ “ገበየሁ ቢሞትም ባልቻ አለልዎ” ለማለት ጭምር እንዲህ ተባለ።

ገበይሁ ቢሞት፣ ተተካ ባልቻ፤
መድፍ አገላባጭ፣ ብቻ ለብቻ። ተብሎ ተፈከረ።

እንግዲህ የደጃዝማች ባልቻ የጀግንነት ታሪክ በተለይ ከአድዋ ድል በኋላ እየገነነ መጥቶ የመድፈኛ ክፍል ሃላፊ ከመሆን ጀምሮ፤ በኋላም በአጼ ምኒልክ ዘመን የጦር መሳሪያ ግምጃ ቤት ሲቋቋም፤ የግምጃ ቤቱ ኃላፊ ሆነው ዛሬ ከበቅሎ ቤት በታች ይገኝ ከነበረው ስፍራ ላይ፤ የኢትዮጵያን ጦር መሳሪያ በአይነት ባይነት ማቀመጥ መጀመራቸው ይታወቃል።

(የጦር ግምጃ ቤቱ ከምኒልክ ጀምሮ እስከ ደርግ ዘመን ድረስ የነበሩ መድፍ እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን እንደያዘ፤ ግንቦት 27፣ 1983 ዓ.ም. መቃጠሉ ይታወሳል – የበቅሎ ቤቱ ፍንዳታ መሆኑ ነው)

እዚህ ላይ አንድ ሌላ ታሪክ እንጨምርልዎ። የደጃች ባልቻ ታሪክ ሲነሳ ይህ ታሪክ ሁሌ ይነሳልና… ይህን ፈገግ የሚያሰኝ ገጠመኝ ሳንነግራችሁ እንዳንቀር በሚል እነሆ አቅርበነዋል። ታሪኩ እንዲህ ነው።

ቀደም ብለን እንደገለጽነው…. ባልቻ አባ ነፍሶ በልጅነታቸው ብልታቸውን ጦር ሜዳ ላይ ስላጡ፤ ውስጥ ውስጡን ሚስጥሩ መወራቱ አልቀረም። ደግሞም መሞት የፈለገ ካልሆነ በቀር፤ ማንም ደፍሮ ይህን ጉዳይ እሳቸው ፊት አያነሳም። አንድ ቀን የሚነሳበት አጋጣሚ ሊፈጠር ሆነ።

አዎ ከእለታት በአንዱ ቀን አጼ ምኒልክ…. ደጃዝማች ባልቻን ምርጥ የሆነ ጎራዴ ሸለሟቸው። የቤተ መንግስት ሰዎችም ጎራዴውን አደነቁላቸው። አንዳንድ ጓደኞቻቸው ግን፤ “ይህንን የጎራዴ ስጦታ የማያደንቀው አለቃ ገብረ ሃና ብቻ ነው።” አሏቸው። ባልቻ አባ ነፍሶም “ጃንሆይ የሰጡኝን ጎራዴ እንዴት ነው የማያደንቀው?” ብለው ተቆጡ። አለቃ ገብረሃና እቤታቸው ድረስ እንዲመጡ አደረጉና… ከጋበዟቸው በኋላ፤ “ሰው ሁሉ የምኒልክን ስጦታ ሲያደንቅ አንተ የማታደንቀው ለምንድነው?” አሏቸው።
አለቃ ገብረሃናም “የታለ ስጦታው?” ይላሉ።

ደጃች ባልቻም ጎራዴውን መዘው ለአለቃ ገብረሃና ሰጧቸው። በአሽሙር ንግግራቸው የሚታወቁት አለቃ ገብረሃናም ጎራዴውን ተቀብለው አገላብጠው ካዩ በኋላ፤ “አይ ጎራዴ! አይ ጎራዴ! ጥሩ ጎራዴ!” ካሉ በኋላ ጎራዴውን መለሱላቸው። ደጃች ባልቻም በአለቃ ገብረሃና ንግግር ተደስተው ተለያዩ።
በኋላ ላይ የደጃዝማች ወዳጆች፤ “አለቃ ገብሃና ምናለ?” ይሏቸዋል።

ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶም «በደንብ ነው ያደነቀው» ብለው ይመልሳሉ፡፡
«እስኪ ምናለ?» ይላሉ ወግ ፈላጊዎቹ፡፡
«አይ ጎራዴ፣ አይ ጎራዴ ብሎ አደነቀ» ይሏቸዋል፡፡

ያ ሁሉ ሰው በሳቅ ያወካና «እንዴ ደጃዝማች ባልቻ … በቅኔ እርስዎን እኮ ነው የተናገረው» ብለው …አለቃ… ‘ጎራዴ’ ያሉት ደጃዝማቹን መሆኑን ያስረዷቸዋል፡፡ ያን ጊዜ ጀግናው ደጃች ባልቻ፤ አለቃ ገብረሃናን እገላለሁ ብለው ተነሱ። የአገር ሽማግሌዎችም በስንት አማላጅ እና ልመና “በመጀመሪያ ደረጃ አለቃን ቤትዎ ድረስ የጠሩት እርስዎ ነዎት። አሁን የናንተ መጣላት ወሬውን ላልሰማ ማሰማት ነው” ብለዋቸው፤ ደጃች ባልቻም የሽማግሌዎቹን ምክር ሰምተው አለቃ ገብረሃናን እንደሸሹ ኖሩ ይባላል። ለነገሩ ደጃች ባልቻ በኋለኛው ህይወታቸው ዘመን፤ ከነገር እና ከርስ በርስ ጸብ ሲርቁ እንደኖሩ ቀጣዩ የህይወታቸው ታሪክ ያመለክታል።

በእድሜ እና በእውቀት መጎልበት ሲመጣ… በመጀመሪያ ሲዳሞን እንዲያስተዳድሩ ተደረገ። በኋላም የራስ መኮንን የመጀመሪያ ልጅ ደጃች ይልማ ሲሞቱ፤ የሃረር ገዢ ሆነው ሐረርጌን እንዲያስተዳድሩ… በልጅ እያሱ አማካኝነት ተሾሙ። ተፈሪም ከሲዳሞ ማዶ ያለውን የጊሚራ መሬት እንዲያስተዳድር፤ በልጅ እያሱ አማካኝነት ተሾመ። በእርግጥ ልጅ እያሱ ይህንን ያደረጉት ገና ከመጀመሪያው በተፈሪ እና በባልቻ መካከል ቅሬታን በመፍጠር፤ ሁለቱን ትላልቅ ሃይሎች ከፋፍለው መግዛት እንዲችሉ ነበር።

እናም ደጃች ባልቻ አባ ነፍሶ ሐረርጌን ለአራት አመታት ሲያስተዳድሩ፤ ተፈሪ ደግሞ፤ “የአባቴ አገር ሐረርጌን ላስተዳድር?” የሚል ጥያቄ ለእቴጌ ጣይቱ እያቀረቡ፤ ወደተሾሙበት ደቡብ ኢትዮጵያ ሳይሄዱ አዲስ አበባ ላይ ከረሙ። በርግጥም… ሐረርጌ ሊሰጥ የሚገባው ለሌላኛው የራስ መኮንን ልጅ፤ ለደጃች ተፈሪ መሆን ሲገባው ለባልቻ አባ ነፍሶ መሰጠቱ፤ በኋላ ራስ ተፈሪ ቀጥሎም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት በሆኑት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መካከል ቅሬታን ፈጠረ።

በስተበኋላም ላይ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የንጉሠ ነገሥትነቱን ዙፋን ሲይዙ፤ ባልቻ አባ ነፍሶን ከቀድሞ የአገር አስተዳዳሪነት ሹመት አነሷቸውና ደጃች ብሩ ወልደገብርኤልን ሾሟቸው። ይህም ሆኖ ግን ባልቻ አባ ነፍሶ በወቅቱ በነበሩት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ጭምር እንደተከበሩ፤ በዘመዶቻቸው አገር ተቀመጡ። ከዚህ በኋላ ደጃዝማች ባልቻ ከነ ሙሉ ክብራቸው፤ በአካባቢው ህዝብ እንደተወደዱ፤ ከንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለስላሴም ጋር ወደ ሌላ ጸብ ሳይገቡ፤ ከነልዩነታቸው በሰላም ተለያይተው መኖር ጀመሩ። ቀዳማዊ ኃይለስላሴም አገር እያስተዳደሩ፤ ደጃች ባልቻም የተጣላ እያስታረቁ፤ እስከ ሁለተኛው የጣልያን ወረራ 1928 ዓ.ም. ድረስ ዘለቁ።

ጣልያን ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያን ሲወር፤ ከአጼ ምኒልክ ጋር ሆነው በጀግንነት የተዋጉት፤ አሉላ አባ ነጋ፣ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ፣ ራስ አባተ እና ሌሎችም ጀግኖች በእርጅና አንድ በአንድ ሞተው አልቀው ነበር። ከዚያን ዘመን ጀግኖች መካከል የቀሩት… አንድ ሰው ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ ብቻ ነበሩ። እሳቸውም ቢሆን አርጅተዋል። በዚያ ላይ ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ጋር በነበራቸው ጸብ ምክንያት ንጉሠ ንገሥቱ ኢትዮጵያን ለቀው ወደ ጄኔቭ ሲሄዱ፤ ደጃች ባልቻ ከጣልያን ጎን ሊሰለፉ እንደሚችሉ የጣልያኖች ግምት ነበር። ደጃች ባልቻ ግን በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ላይ ቅሬታ ቢኖርባቸውም፤ በአገር ጉዳይ ሌላ ድርድር ውስጥ መግባት አልፈለጉም። ስለሆነም ጦራቸውን ማሰባሰብ ጀመሩ። እናም ከነደጃች ኃይለማርያም ማሞ፣ አበበ አረጋይ እና አቡነ ጴጥሮስ ጋር የሚስጥር ደብዳቤ መለዋወጣቸውን ቀጠሉበት።

በወቅቱ አዲስ አበባ ሙሉ ለሙሉ በጣልያን አገዛዝ ስር ወድቃለች። ንጉሠ ነገሥቱም በአገር የሉም። በማይቸው ጦርነት ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን በጣልያን አውሮፕላን፤ በአየር በሚጣል ቦንብ እና የመርዝ ጢስ አልቀዋል። ከዚያ የተረፉት ግን እጃቸውን ለመስጠት አልፈለጉም። ጣልያን የከተመበት አዲስ አበባ ድረስ መጥተው ለመፋለም ወሰኑ። በእቅዳቸውም መሰረት የራስ ካሳ ልጆች ከፍቼ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ፤ ደጃዝማች ኃይለማርያም ማሞም ጦሩን ይዞ ከነ አቡነ ጴጥሮስ ጋር ሆኖ አዲስ አበባ እንዲገባ፤ ደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶም አምስት ሺህ ያህል ጦራቸውን ይዘው በአዲስ አበባ ደቡብ በኩል በእኩል ቀን ገብተው የጣልያንን ጦር ለመምታት ተዘጋጁ። ደጃች ባልቻ ጦራቸውን አምጥተው አሁን “አየር ጤና” ከሚባለው ሰፈር ማዶ ካለው ረጲ ጋራ ላይ መሸጉ።
ይህን ታሪክ ለማሳጠር ያክል የሆነውን በአጭሩ እንዲህ ልግለጸው። …የራስ ካሳ ልጆች አዲስ አበባ ሳይገቡ ሶስቱም ተገደሉ። ደጃዝማች ኃይለማርያም ማሞ አዲስ አበባ ዘልቀው፤ አሁን እንግሊዝ ኢምባሲ ያለበትን አካባቢ አልፈው እስከ ቀበና ድረስ ዘልቀው፤ ብዙ ወታደሮቻቸው አልቀው እሳቸው ተሰዉ። አቡነ ጴጥሮስ በጣልያኖች ተይዘው ታሰሩ (በርግጥ በኋላ ላይ በጥይት ተደብድበው ተገደሉ)… ደጃዝማች ባልቻ ከትውልድ መንደራቸው… ከአገምጃ ሶዶ ተነስተው አዲስ አበባ ደረሱ። ከዚያም ረጲ ጋራ ላይ ሆነው፤ መድፋቸውን ጠምደው የሌሎቹን አርበኞች ሁኔታ እና መልዕክት መጠባበቅ ጀመሩ። ሁኔታውን ለመሰለል ለሊቱን ወደ አዲስ አበባ የላኳቸው ወታደሮቻቸው፤ ጣልያኖቹ ጋር ሳይደርሱ በባንዳዎች ተይዘው ተገደሉባቸው። ሲነጋ ጣልያን በአውሮፕላን ሆኖ፤ የደጃች ባልቻን ጦር እየተከተለ በጣም ብዙ ሰው ፈጀባቸው። በህይወት ዘመናቸው ጣልያንን ሁለት ጊዜ የተዋጉትና ብዙ ሺህ ተከታይ የነበራቸው ባልቻ አባ ነፍሶ ብቻቸውን ቀሩ። በመጨረሻ ጥቂት ወታደሮቻቸውን ይዘው ወደ ኋላ አፈገፈጉ።

የደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶ ታሪክ በጣልያኖች ዘንድ ሲወራ ብዙዎችን አስገረመ። የጣልያን ጋዜጦች… “በአድዋ ጦርነት ወቅት ከምኒልክ ጋር ሆኖ ከተዋጉት ሰዎች መካከል ባልቻ አባ ነፍሶ የሚባል የ75 አመት ሽማግሌ ሰው አሁን በህይወት አለ። በደቡብ በኩል ጦር እያደራጀ ነው።” ተብሎ እየተጋነነ ሲወራ፤ የጣልያን መንግስት፤ “ይህን ሰው እንፋረደዋለን። ከነህይወቱ ይዛቹህ እንድታመጡት።” የሚል ትዕዛዝ አስተላለፈ።
በነገርዎ ላይ ደጃች ባልቻ ሁለት ወንድሞች ነበሯቸው። አንደኛው ፊታውራሪ ሳህለሚካኤል ነው። በአድዋ ጦርነት ላይ ተሰውቷል፤ 2ኛውን ፊታውራሪ ገብረመድህንን ደግሞ በሰገሌ ጦርነት ወቅት በጦር ሜዳ ህይወቱ አልፏል። እናም በወቅቱ ብቻቸውን የነበሩት ደጃች ባልቻ….
“ጦር መጣ ይላሉ፤ እኔ ምን ቸገረኝ፤
እናቴም ልጅ የላት፤ ለኔም ወንድም የለኝ።” አሉ ይባላል።

ከዚህ በኋላ የሆነውን እኛ ከምንተርከው ይልቅ፤ በወቅቱ በአርበኝነት ጫካ ገብተው ሲዋጉ ከነበሩት መካከል ሻለቃ መስፍን ስለሺ የጻፉትን ደብዳቤ እናካፍላቹህ። ሻለቃ መስፍን ስለሺ ደብዳቤውን የጻፉት እንግሊዝ አገር ለነበሩት ለቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ነበር።
“…የጠላት ጦር ደጃዝማች ባልቻ ወድሚኖሩበት እስከ ጉራጌ አገር ድረስ በመዝለቅ በሳቸው ላይ ዘመተባቸው። ህዝቡ ከዳቸው፤ ወታደሮቻቸውም ለህይወታቸው ሲሉ ሸሹ። እሳቸው ደጃች ባልቻ እና ሁለት አሽከሮቻቸው፤ ከሳቸው ጋር ሶስት ሰዎች ብቻ ቀሩ። ያ ሁሉ የጣልያን ጦር ከበባቸው። ወዴትም መሄድ አልቻሉም። በመጨረሻም አንድ ነጭ ፈረንጅ ወደጃች ባልቻ ዘንድ መጣ። ከዚያም… “ደጃዝማች ባልቻ ማለት አንተ ነህ?” አላቸው።

ደጃዝማቹም “አዎ እኔ ነኝ!” ሲሉ፤ ፈረንጁ “በሉ ይማረኩ። ሽጉጥዎትንም ያስረክቡኝ።” አላቸው።

ደጃዝማች ባልቻም፤ “እኔ እጅ የምሰጥ ሰው አይደለሁም። ትጥቄንም አልሰጥህም!” ብለው ሽጉጣቸውን አውጥተው፤ ነጩን የጣልያን ጦር መኮንን ገደሉት። ከዚያም በራሳቸው ሽጉጥ የራሳቸውን ህይወት አጠፉ። ከደጃዝማች ባልቻ ጋር አብረው የነበሩትም ወታደሮች ስቃይ ሳይበዛባቸው በየተራ ወደቁ።” በማለት በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ ገልጿል።
እናም የጣልያን ጦር በቾ አበቤ ድረስ ዘምቶ ከደጃች ባልቻ አባ ነፍሶ ጋር ተዋግቶ፤ ሳያሸንፍ ተሸነፈ። እጃቸውን ይዞ ሊወስዳቸው ቀርቶ፤ ህይወታቸውን እንኳን ሳያጠፋው በራሳቸው ጥይት ራሳቸውን ሰዉ – ጥቅምት 27፣ 1929 ዓ.ም.።

በሁለተኛው የጣልያን ጦርነት ወቅት ብቻቸውን መሆናቸውን የተመለከተ አዝማሪ….
የባልቻ ወንድሞች ጥይቶቹ ናቸው፤
እዚህ ተቀምጦ፣ እዚያ የሚልካቸው፡” ብሎ ገጥሞላቸው ነበር።

በነገርዎ ላይ ደጃች ባልቻ በሞቱ በ11ኛው አመት፤ አሁን ከልደታ ማዶ የሚገኘውና በስማቸው የተገነባው ዘመናዊ ሆስፒታል በጥቅምት ወር መጨረሻ 1940 ዓ.ም. ተመርቆ ተከፈተ። ሆስፒታሉ በመጪው ጥቅምት ወር 45 አመት ይሞላዋል። (በዚያው አጋጣሚ ደጃች ባልቻን ቢያስቧቸው መልካም ነበር)

የታሪክ ወጋችንን ልናጠናቅቅ ነው።
በአምስቱ አመት የአርበኞች ትግል ወቅት… አንበሳው የኢትዮጵያ ጦር ተመልሶ አገሩን እንደሚያስተዳድር የታወቀ ነበር። አርበኞችም እንዲህ እያሉ ይፎክሩ ነበር።
“ባንበሳው መኝታ፣ ጅቡ ተኝቶበት፥
ብንን ብንን ይላል፣ በ’ልሙ እየመጣበት።”

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በ1933 ዓ.ም. በድል አድራጊነት አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ፤ የሞቱትን የኢትዮጵያ ጀግኖች አሰቧቸው። ለሰማዕታቱ መታሰቢያ ሃውልት ቆመ። አቡነ ጴጥሮስ ከተገደሉበት ስፍራ ጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ሃውልት በስማቸው ተቀርጾ ቆመላቸው (አሁን ለጊዜው ተነስቷል)። ለደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶም በስማቸው በተወለዱበት ወሊሶ፤ ባደጉበት አዲስ አበባ በስማቸው ትምህርት ቤቶች ተከፈቱላቸው፤ መንገድ ተሰየመላቸው፤ ሆስፒታልም ተሰራ። በነዚህ ጊዜያት በሙሉ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በስፍራው እየተገኙ መንገዱን መርቀዋል፤ ሆስፒታሉ ሲከፈትም ንግግር አድርገዋል። ይህ ብቻ አይደለም። ባልቻ አባ ነፍሶ በተወለዱበት ስፍራ ጭምር ሃውልት ተሰርቶላቸዋል።

ባልቻ አባ ነፍሶ በአካል ጉድለት ምክንያት፤ ልጅ ወልደው ዘራቸውን ባይተኩም፤ የጀግናን ውለታ የማይረሳው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ልጅ ሆኗቸዋል። አጼ ምኒልክ “ከትልቅ መወለድ ሳይሆን፤ ራስን ከትልቅ ነገር መውለድ ሞያ ነው” እንዳሉት፤ ደጃች ባልቻ ከትልቅ ስለተገኙ ሳይሆን፤ ትልቅ ስራ ስለሰሩ… በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በስማቸው መንገድ፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤት ከተሰራላቸው ሌሎች ጀግኖች ይልቅ ብዙ የተባለላቸው – ባልቻ አባ ነፍሶ ናቸው።

ይህ ሳምንት ባልቻ አባ ነፍሶ የተወለዱበት ቀን ነው…. እናም “መልካም ልደት። እንኳንም ተወለዱልን!” እንበላቸው!!

በብርሀኑ ተበሳጨሁ፤ በሰማያዊ ተጽናናሁ፡ በአንድነት ደግሞ ተስፋ አደረግሁ ልጅ ተክሌ

$
0
0

1-ይህ ጽሁፍ ዓላማው አድናቆት፡ ትችትና ግብዣ ነው። የአንድነት ምሽት በቶሮንቶ ግብዣ። ከአድናቆትና ከግብዣው በፊት ስለፖለቲካ መሪዎችና ስለፖለቲካ ተንታኞች አትቶ፤ የብርሀኑ ነጋን (ዲባቶ) አቀራረብ ይተቻል። የሰማያዊ ፓርቲን ርምጃ ያደንቃል። የአንድነት ዘመቻን ስለማገዝ ያሳስባል። እንደው ተገጣጥሞ ነው እንጂ፤ አንዱን ለማሞገስ ሌላው መኮሰስም መከሰስም የለበትም። ግን አንዳንዴ ደግሞ፤ በጊዜ ያልተተቸ፤ ይለመዳል። አጉል ልማድ ይሆናል። ሁሉንም ለያይቶ ለመጻፍ ደግሞ፤ ጊዜ የለም። ስለዚህ ባንድ ወንጭፍ ሶስት ወፍ ነው ለመማረክ የምጥረው። ከሀተታ ልጀምር።

የፖለቲካ ተንታኝና የፖለቲካ መሪ

2-የፖለቲካ መሪ ከፖለቲካ ተንታኝ መለየት አለበት። የፖለቲካ መሪ የፖለቲካ ተንታኝ ሲሆን፤ የጋዜጠኞችንና የፖለቲካ ተንታኞችን/የምሁራንን ስራ ይጋፋል። ያ ብቻም አይደለም። መምራት አቅቶት፤ ወይም መምራት ጠፍቶት፡ በአካልና በስም የፖለቲካ መሪነቱን ወንበር ተቆናጦ፤ በግብር ግን የፖለቲካ ተንታኝነትን ቦታ ይዞ፤ የፖለቲካ መሪነትን ስራ በፖለቲካ ትንታኔ ሊያካክስ ይሞክራል። ያም ብቻ አይደለም፡ የፖለቲካ መሪነት ሚናን ከፖለቲካ ተንታኝ ጋር ያደባለቀ መሪ፤ የያዘውን የፖለቲካ መሪነት ሀላፊነት ከተንታኝነት ሲለሚቀይጠው፤ ትንታኔው ንጹህ አይሆንም። ስለዚህ የፖለቲካ ትንታኔውን መቀበል ይከብዳል። ባይከብድም ትንታኔው ጎዶሎና ወደሁዋላ የሚጎትት፤ ወይንም ወደፊት የማያራምድ ይሆናል። ወይም ትንታኔው ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የሚደረግ ጥልቅ ያልሆነ ትንታኔ ይሆናል።

3-ለምሳሌ ብርሀኑ ነጋ ባለፈው የኢሳት ስብሰባ ላይ ያቀረበውን የንግግሩን ገጽ 16 መጨረሻና ገጽ 17 መጀመሪያ ብንመለከት ሀሳቡ ጥልቅ ወይም ሀቀኛ አለመሆኑን በቀላሉ ለመረዳት ይቻላል። http://www.ethiomedia.com/2013report/haimanot_ena_poletika.pdf ለዚህም ነው ምሁር ፖለቲከኛ መሆንን ከመረጠ፤ ምሁርነቱን ቀንሶ መሪነቱን እንዲያጠብቅ ግድ ነው የምንለው። ኦባማን ውሰዱ። ኦባማ ሲመረጥ ምሁር ነበር። ከአራት አመት በሁዋላ ግን ምሁርነቱ እየቀነሰ፤ ወደቡሽነት እየተጠጋ መጥቷል። የኦባማ የሶሪያ አቋም፤ ከቡሽ የኢራቅ አቋም ብዙ አይለይም። አሳድን እንበለው ወይም እንብላው እያለ ነው። ኢሳት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ብርሀኑ ነጋ (ዲባቶ) ያንን መለየት ነው የተሳነው። በፖለቲካ መሪነት መጥቶ (በግንቦት ሰባት ሊቀመንበርነት) የፖለቲካ መሪነቱን ግን ትቶ፤ ምሁር ለመሆን ሞከረ። ተንታኝ። የፖለቲካ ተንታኝ በመሆን የጋዜጠኞችንና የምሁራንን ስራ መሻማት ብቻ ሳይሆን፤ ሁለቱንም ሳይሆን ቀረ። በዚህ ረገድ ጃዋር ይሻላል። እንደተንታኝ በደንብ ይተነትን ነበር። የተንታኝነቱን ሚና ትቶ ባለፈው ሰሞን የራሱን የፖለቲካ አቋም ሲያንጸባርቅም፤ ብዙ ሰዎችን ቢያበሳጭም፤ እቅጩን ነው ያስቀመጠው። ብሬ አድበሰበሰው። በእስር ላይ የሚገኙትም ይሁኑ በነሱ የተተኩትን ከነሱም የቀደሙትን ሙስሊሞች አካሄድና እንቅስቃሴ የሚጠራጠሩ ካሉ፤ ጥርጣሬያቸው በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ነው የተፈጠረው ለማለት ይከብዳል። በወያኔ ፕሮፓጋንዳ የማይበገሩም ከተጠራጣሪዎቹ ተርታ ውስጥ አሉበትና።

4-የዲባቶ ብርሀኑ ነጋ ያልጠራ ትንታኔ የመነጨው፤ ፖለቲካዊ መሪ መሆንና ፖለቲካዊ ምሁር/ተንታኝ መሆንን አጣምሮ ለመሄድ ከመሞከር ነው። የፖለቲካ ተንታኝ የምለው፤ በፖለቲካ ውስጥ በቀጥታ በአድራጊ-ፈጣሪነት ሳይሳተፍ ወይም መሳተፍ ሳይጠበቅበት፤ የአንድን ፖለቲካዊ ስብስብ/ማህበረሰብእ ፖለቲካዊ ሁኔታ እየቃኝ፤ ከአካባቢያዊና አለማቀፋዊ ሁነቶች ጋር እያጣቀሰ፡ የሁነቶቹን ምክንያት የሚያብራራ፤ ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮችን የሚጠቁም፤ አደጋዎችን የሚተነብይ፡ ተመልካችና ተናጋሪ ማለት ነው። የፖለቲካ መሪ የፖለቲካ ተንታኝ ሲሆን፤ አደናጋሪ ነው የሚሆነው። የፖለቲካ መሪዎች የፖለቲካ ተንታኝ መሆን የለባቸውም እያልኩ አይደለም። እኔ የምለው፤ አንደኛ ፖለቲካ መሪዎች የፖለቲካ ትንታኔ ችሎታቸው የሚገለጸው በፖለቲካዊ አመራራቸው በሚወስዱት ፖለቲካዊ እርምጃ ውስጥ መሆን አለበት ነው። ሁለተኛ፡ ፖለቲካን መተንተን የፖለቲካ መሪዎች ዋና የአደባባይ ስራ መሆን የለበትም ነው። እዚያው ድርጅታቸው ውስጥ እንደፍጥርጥራቸው። ይፋዊ ፖለቲካዊ ስራቸው ግን፤ መምራት እንጂ መተንተን አይደለም። አቶ መለስ ከሞቱ በሁዋላ ብቻ ያለውን ሁኔታ እንኳን ብንለመከት ግን፤ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ብርሀኑ ነጋ፤ ከሲሳይ አጌና ጋር ያደረጋቸውን ቃለምልልሶች ወይንም ያለፈው ሰሞንን የኢሳት መድረክ ጨምሮ፤ በቀረበባቸው መድረኮች ላይ የሚናገራቸወን ስንለመከት አድራጊ የፖለቲካ መሪ ሳይሆን፤ ተንታኝ ጋዜጠኛ ወይንም እዚህ አገር እንደሚሉት ጠቢብ ምስክር ለመሆን ነው የጣረው።

5-ያ ብቻም አይደለም፤ አሁን በእመ-ብርሀን፤ ሰላሳ ድርጅቶች የኢትዮጵያን እጣፈንታ ከህዝብ ጋር ሊመክሩ በተሰበሰቡበት መድረክ ላይ ለመነሻ የሚሆን የአስር ደቂቃ ንግግር አድርጎ የተቀረውን ሰዓት ለህዝብ ውይይት መተው እንጂ፤ የ55 ደቂቃ ድርሳን ማንበብ ምን የሚፈይደው ነገር አለ? ብርሀኑ ነጋ ባለፉት ሶስት ወራት በኢሳትም ይሁን በተለያዩ መድረኮች ያገኘውን እድልና ሰዓት ስንመለከተው ደግሞ የንግግሩ መርዘም ስህተትነትና አበሳጭነት ይጎላል። ያ ብቻም አይደለም፤ ሶስት ሺህ ምናምን አመት፤ መጀመሪያ በጸሀዩም በጨረቃውም በማምለክ፤ ከዚያ ብሉይን በመቀበል፤ ከዚያ ክርስትናን፤ ከዚያ እስልምናን፤ ከዚያ ካቶሊክን፤ ከዚያ ፕሮቴስታነንስዝምን፤ በመቀበልና በማቻቻል ለኖረች አገር፤ የሊበራሊዝምና ዴሞክራሲ መፍትሄ ለሀይማኖት ነጻነት የሚል የአንድ ሰዓት ስብከት ያስፈልጋታል? ቢቀርብንስ?

6-በዚህ ኢሳት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ፤ ግንቦት ሰባትን ወክሎ ንግግር ካቀረበው ብርሀኑ ነጋ ይልቅ፤ የሽግግር ምክርቤቱ እጥር ምጥን ባለች ባለአራት ገጽ ወረቀቱ፤ የተሻሉ የሽግግር ሀሳቦችን አቅርቧል። http://etntc.org/ENTC/wp/wp-content/uploads/ESAT-Presentation-0818.pdf። እነሱ የሚመኟት ኢትዮጵያ ምን መምሰል እንዳለበት፤ ሽግግሩ ምን እንደሚመስል፤ የሽግግር ሰነድ የሚያረቅ ኮሚቴ ስለማዋቀራቸው፤ አለማቀፍና አገርአቀፍ የእምቢተኝነት ቡድን ስለማቋቀም፤ ድርጅታቸው ምን እየሰራ እንደሆነ ተናግሯል። ከሽግግር ምክርቤቱ አራት አመት ቀደም ብሎ የተቋቋመው ግንቦት ሰባት ግን ጥምረት ከተቋቋመ ከሶስት አመት በሁዋላ፤ የከማል ገልቹ ኦነግ ከተመለሰ ከሁለት አመት በሁዋላ፤ ገና ስለድርጅቶች አንድነት፤ በጋራ ትግል ወያኔን ስለማስወገድ አጣዳፊነት ይሰብካል። የዛሬ አመት፡ የዛሬ ሁለት አመት፡ የዛሬ ሶስት አመት ከነበርንበት ብዙም ፈቀቅ አላልንም።

7-ኢሳት ይሄንን ስብሰባ ማዘጋጀቱ ይደነቃል። ይሁን እንጂ፤ የኢሳት አስተዳዳር የሆነው ወዳጄ ነአምን ዘለቀ የዛሬ አመት አካባቢ እንዲህ ያለው ተመሳሳይ ስብሰባ ሲዘጋጅ፤ (ያኔ ስብሰባው የተዘጋጀው በኢሳት ሳይሆን በግንቦት ሰባትና በነኑሮ ደደፎ (ዲባቶ)/ከማል ገልቹ ኦነግ ነበር)፤ እባክህን መሪዎቹ ንግግር ያሳጥሩና ለሰዉ እንዲተነፍስ ግዜ ይስጡት ብዬ አሳስቤው ነበር። ነአምን አንዳንዴ አይሰማም። ወይም ቢሰማም አያደምጥም። እነሆ፤ ባመቱ፤ ሌላ ውድ መድረክ ባከነ። የብርሀኑ ነጋ ጽሁፍ፤ የመጀመሪያው አስራሶስት ገጽ ለዚያ መድረክ አስፈላጊ አልነበረም። ነገር መቁረጥና ማሰጠር፤ እንዲሁም መድረክ ላይና ምድር ላይ የምናቀርበውን መምረጥ አለብን። ያለበለዚያ ትክክለኛና ውጤታማ ሚናችንን መለየት አለብን።

ተስፋ፡ አድናቆትና፤ ግብዣ

8-መቼም ተቃጥላችሁ አትሙቱ ያለን ፈጣሪ መጽናኛ አያሳጣንም፤ በግንቦት ሰባት ሊቀመንበር አቀራረብ ብንበሳችም፤ አላህ የሚያጽናናን አላሳጣንም። የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ እኛ በምናደርገው ነገር ምንም ቀስቀስ በማይልበት፤ ፖለቲካዊ አየሩ ጸጥ ረጭ ባለበት ሁኔታ ነው፤ የዛሬ ሶስት ወር አካባቢ፤ ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የተሳካ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ። ላለፉት ስምንት አመታት ሰልፍ አይታ ለማታውቀው አዲስ አበባ ሀያ መቶም የሁን ሀያ ሺህ ሰው ያስወጣ ሰልፍ ተከሰተ። ያ ያጽናናል። እነሆ ያኔ በያዙት ቀጠሮ መሰረት፤ ሁለተኛው የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በመጪው እሁድ ይቀጥላል። መቼም ብዙዎቻችን ፈሪዎችና ሸሺዎች በሆንበት ሁኔታ፤ ጥቂት ዠግኖች አልጠፉምና፤ የሰማያዊ ፓርቲዎች ድፍረትና ቁርጠኝነት የሚያስደንቅ ነው። የህወሀት ኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት፤ በአዲስ አበባ መስተዳድር በኩል ሰልፉ ህገወጥ ነው ቢሉም፤ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች ግን ሰልፉ ህጋዊ ነው፤ እንገፋበታለንም እያሉ ነው። የመጪው እሁድ ትልቅ ተጋድሎ ዋዜማ ላይ ነን።

9-እንዲህ ያለውን ትእይነት ቆሞ መመልከት ብቻ ግን ነውር ነው። መቼም አንዴ ሸሸተን ወጥተናል፤ በወጣንበትም ቢሆን ግን፤ የምንችለውን እንኳን በማድረግ ተዋናይ መሆንም አለብን። የኛ የተቀናቃኙ/ተፎካካሪው/ተቃዋሚው ጎራ፤ በተለይ በውጪ የምንኖረው ተቃዋሚዎች ትልቁ ችግር፤ ማድረግ የምንችለውን እንኳን ማድረግ አለመቻላችን ነው። በሰላማዊም ይሁን ደማዊ መንገድ፤ በአመጽም ይሁን በጸሎት ለሚታገሉት ስንቅና ትጥቅ ማቀበል። ስንቅና ትጥቅ ላለማቀበል ብዙ ምክንያት መደርደር ይቻላል። ምንም ምክንያት ግን አጥጋቢ አይሆንም። ቅዳሜና እሁድ የዱለትና የቁርጥ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን ጉዳይ እያብራራ የሚተነትነው፤ የምእራባዊያንን ሴራ የሚመሰጥረው ወዳጄ፤ የኢሳት ዝግጅትን የ20 ብር ትኬት ስሰጠው ፊቱን እንዳጨፈገገው መሆን የለብንም። ለሰማያዊ ፓርቲ ሁለተኛ ሰልፍ መሳካት እንጸልያለን። በጸሎት ብቻ አናበቃም። በግብርም እንከተላለን።

10-መቼም በየከተማው ብዙ የማይደክማቸው ሰዎች አሉ። እነሆ በመጪው ቅዳሜ ማታ፤ በዚህ በኛ ከተማ ትንሽ ተንፈስ እንላለን። ተሰብስበን ኢህአዴግን ከመዘልዘል ባሻገር፡ የትግሉ በረከት እንጥፍጣፊ ይደርሰን ዘንድ የአንድነት ምሽት ያዘጋጁ አሉ። “የአእላፋት ድምጽ ለነጻነት” የተሰኘውን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ዘመቻ በመደገፍ እዚህ ቶሮንቶ ከተማ፤ እንደፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር፤ ቅዳሜ ኦገስት 31 ማታ ከ6ሰኣት ጀምሮ’፤ 2050 ዳንፎርዝ ጎዳና በሂሩት ሬስቶራንት የቤተሰብ አዳራሽ የእራት ምሽት ተዘጋጅቷል። በሰሀን $ 50 ብቻ። ለጥንዶች $ 60። ለኔቢጤው ደሀ ደግሞ $ 30 ብቻ። ገቢው፤ ከወጪ ምላሽ ለአንድነት ፓርቲ የሚሄድ ነው።

11-እነሆ፤ በአካል ከግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይል ጋር ላንዘምት እንችላለን። በአካል ከሰማያዊ ፓርቲም ጋር አንሰለፍ ይሆናል። ከአንድነት የነጻነት ድምጾች ጋር ለመጮህ ግን አይሳነንም።ለሚጮሁት ጉልበት፤ ለሚሰለፉት ብርታት፤ ለሚዘምቱትም ጽናት ልንለግስ እንችላለን። በያለንበት አካባቢ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች እንርዳ። እዚህ ቶሮንቶ ያለን፤ ቅዳሜ ሂሩት ሬስቶራንት ብቅ እንበል። ቅዳሜ እንኩዋን፤ ላሊበላና ብሉናይል፤ ዞብልና ራንዴቩ ይቅሩብን። ቅዳሜ ማታ፤ ሂሩት ጋር እንገናኝ።
እኛው ነን። ከቶሮንቶ። ነሀሴ፡ 2005/2013።

ቅ/ሲኖዶስ እና ፓትርያሪኩ የአቡነ ያዕቆብ የመላው አፍሪካ አህጉረ ስብከት አስተዳደር እያስከተለ ለሚገኘው ጉዳት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጡ ተጠየቀ

$
0
0
  • ለወራት በአ/አ የተቀመጡት ሊቀ ጳጳሱ ትላንት ምሽት ወደ ደ/አፍሪካ ተጉዘዋል
  • በሊቀ ጳጳሱ አስተዳደር የተማረሩና አስቸኳይ መፍትሔ የሚሹ አቤቱታዎች ለውጭ ግንኙነት መምሪያውና ለፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት እየጎረፉ ነው

ከዚህ በታች የምናቀርበውና ‹‹የአቡነ ያዕቆብ ሲሞናዊነት[ስምዖናዊነት] ሲገለጥ›› በሚል ርእስ የተጠናቀረው መልእክት የደረሰን በኬንያ – ናይሮቢ ከሚገኙ ምእመናን ነው፡፡ መልእክቱ÷ የመላው አፍሪቃ አህጉረ ስብከትን የተመለከተ ዘገባ በጡመራ መድረኩ ለንባብ ከበቃበት ጊዜ ጀምሮ ከሚደርሱን በርካታ አስተያየቶች መካከል ለማለዘብ የተገደድናቸውንና በተለይ ሊቀ ጳጳሱን የሚመለከቱ ግልጽ የወጡ መረጃዎችንና ትችቶችን መልሰን እንድናጤናቸው፣ ደጋግመን እንድናጣራቸው አግዞናል፡፡

መልእክቱን መሠረት ያደረጉ ዋና ዋና ነጥቦችን በቅድሚያ ያስቀመጥን ሲኾን ምእመናኑ ከናይሮቢ ያደረሱን መልእክትም መጠነኛ ማለዘቢያ ተደርጎበት ተያይዞ ቀርቧል፡፡ ቁም ነገሩ÷ በቀደሙት ዘገባዎቻችን እንዳመለከትነው፣ ቤተ ክርስቲያናችን በብዙ በምትጠበቅበት የአፍሪቃ አህጉር ሐዋርያዊ ተልእኮዋ በምን ደረጃ እየተፈጸመ እንዳለ ለማሳየትና ከዚያም በመነሣት ለችግሮቹ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ፣ ለተግዳሮቱም የሚመጥን የአገልግሎት ዝግጁነት እንዲኖር ለማትጋት ነው፡

 

ዐበይት የትኩረት ነጥቦች

  • የማጥመቅ ሥርዐታቸውና የሚታሙበት ጥንቆላ ለምእመናን እምነት፣ ጤንነትና ማኅበራዊ ኑሮ ፈተና ኾኗል፤ ይህን የሚቃወሙ ካህናትም በደል ይፈጸምባቸዋል፡፡
  • በአብያተ ክርስቲያን ቅጽር ማረፊያ ቤት እያለ በቀን 150 የአሜሪካን ዶላር የሚከፈልበትን ‹ገስት ሃውስ› እና የግለሰብ ቤት ለማረፊያነት መምረጣቸው ከአዋኪው የማጥመቅ ሥርዐታቸውና ከሚታሙበት የጥንቆላ ተግባር ጋራ ተያይዞ ለከፋ ሐሜትና ትችት ዳርጓቸዋል
  • አዲስ አገልጋዮችን በመቅጠር አመካኝተው ገንዘብ ለመቀበል ሲሉ በአገልግሎት ላይ ያሉ ካህናት አገልግሎታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ይገፋፋሉ፤ የሚቃወሟቸውን ካህናት ከምእመናን ያጋጫሉ፤ ምእመናንን በካህናት ላይ ያነሣሣሉ፡፡
  • የውጭ ግንኙነት ጽ/ቤት ሳያውቀው በጎጠኝነትና ጥቅመኝነት ላይ ተመሥርተው ለሚፈጽሙት ቅጥር በአዲስ አበባ በደላላነት የሚያገለግሏቸው ቀሲስ ግሩም ታዬ ናቸው፡፡

*            *            *

  • በዑጋንዳ፣ ታንዛንያና ሌሎችም የአህጉሪቱ ክፍሎች አብያተ ክርስቲያን እንዲስፋፉ ለሚማፀኑ በጎ አድራጊ ምእመናን ቀናና አፋጣኝ ምላሽ አይሰጡም፤ ይልቁንም የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳደርን በመጋፋት ያለገደብ በሚጠይቁት የገንዘብ ወጪ አድባራቱን ለብኩንነት እየዳረጉ ማደኽየታቸ በፈጠረው ምሬት ከአንድነት መዋቅር የመለየት ስጋት የተጋረጠባቸው ነባር አድባራት አሉ፡፡
  • ይህ ምሬትና ስጋት ከተጋረጠባቸው አድባራት አንዱ የናይሮቢ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የደብሩን ይዞታ ንብረቷ ያደረገችው በሦስተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አስተዳደር ወቅት ነው፡፡ የባዕለጸጎች መኖርያ ነው በሚባለው የከተማዪቱ ዕንብርት የሚገኘው ደብሩ ሁለት ዐበይት ችግሮች ተጋርጠውበታል፡፡
  • አንደኛው÷ የልማት ዕቅዶች ጅምር ቢኖሩትም ሊቀ ጳጳሱ በመስተንግዶና መጓጓዣ ስም የሚጠይቁት ያልተገባ ወጪ ፋይናንሳዊ አቅሙን እየተፈታተነው መኾኑ ነው፡፡ የኮፕት ቤተ ክርስቲያንና ካቶሊኮች ታላላቅ ገዳማትን በመመሥረት፣ ሆስፒታሎችንና ሌሎች ማኅበራዊ ተቋማትን በማስፋፋት የሚያካሂዱት ልማት መንፈሳዊ ቅንዐት የማይፈጥርባቸው ሊቀ ጳጳሱ የቀደሙት ሊቃነ ጳጳሳት (ብፁዕ አቡነ ዳንኤል፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ) የፈጸሟቸውን ሐዋርያዊ ክንውኖች እንኳ ለማስጠበቅ ተነሣሽነቱም ብቃቱም የላቸውም፡፡
  • ሁለተኛው÷ ሊቀ ጳጳሱ በርቱዐ ሃይማኖት እና በሞያ ብቃት ሳይኾን በጎጥና ጥቅመኝነት ላይ ተመሥርተው በሚያካሂዱት ቅጥር አንድ ቀሳጢ ‹መነኩሴ› በቀዳሽነት ለማስቀጠር ከደብሩ አስተዳደር ጋራ ውዝግብ መፍጠራቸው ነው፡፡ በውጭ ግንኙነት ጽ/ቤትና በፓትርያሪኩ ዕውቅና የተላኩት ካህን በግፍ ቦታውን ጥለው እንዲሰደዱ ካደረጉ በኋላ ሊቀ ጳጳሱ በግል ውሳኔያቸው ሊያስቀጥሩት የነበረው ይህ የሃይማኖት ቀሳጢ ማንነቱ በማስረጃ ተጋልጦ ቅጥሩ ቢከሽፍም ሊቀ ጳጳሱን ተስፋ አድርጎ በዚያው የሚገኝ በመኾኑ ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም ስጋት ፈጥሯል፡፡ ውዝግቡ፣ በለቀቁት ባለሞያ ካህን ቦታ ተተኪ እንዳይቀጠርና ባሉት ጥቂት አገልጋዮች ላይ ጫና እንዲፈጠር አድርጓል፡፡

*            *            *

  • መላው አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ያላቸውን የምክትል ፕሬዝዳንትነት ሓላፊነት በአግባቡ እየተወጡ አይደለም፡፡ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደውን የቅዱስ ሲኖዶሱን የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባዎች መንፈሴ አላዘዘኝም እያሉ በተለያዩ ሰበቦች እንደሚቀሩት ሁሉ፣ መሳተፍ የሚገባቸውን የምክር ቤቱን ስብሰባዎችም ኾነ ብለው በማስተጓጎላቸው በአህጉር ደረጃ የተወከሉበትን የቤተ ክርስቲያናችንን ሚና ከሌሎች አብያተ እምነት መሪዎች ሚና አሳንሰዋል፡፡
  • ‹‹ለመላው አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ርዳታ መስጠት››፣ ‹‹በደቡብ አፍሪካና በኢትዮጵያ የማሳድጋቸው ሕፃናት አሉ›› በሚሉ ሰበቦች መጠኑ ያልታወቀ የበጎ አድራጊ ምእመናንን ገንዘብ ለግላቸው አካብተዋል፡፡ ለዚህ ዓላማ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ስታፎችንና ባዕለጸጋ ነጋድያንን በጥቅመኝነት በቀጠሯቸው አገልጋዮች ደላላነት ዒላማ አድርገዋቸዋል፡፡
  • ‹‹ኤርትራዊ ነኝ›› በሚል ከኤርትራውያን ምእመናን ገንዘብ ለግላቸው ይሰበስባሉ፡፡ ሊቀ ጳጳሱ÷ ኤርትራዊ ተወላጅ ሲያገኙ ኤርትራዊ ነኝ፤ የኢሕአዴግ ደጋፊ ሲያገኙ ኢሕአዴግ ነኝ በሚል ጥቅም የሚያጋብሱበትን ኹኔታ በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በትኩረት እየተከታተለው መኾኑ ተጠቁሟል፡፡

*            *            *

 


Ancient Ethiopian math

Amharic News 1800 UTC –ኦገስት 31, 2013

$
0
0
News, Call-in show or special interviews and Ye Musica Qana…

ESAT Radio Aug 31


ሚድያና መዘዙ: ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብር ኤል

$
0
0

ከዚህ ቀደም ያልሆነ ወይንም ያልበረ ሆኖ ሳይሆን እንደው በዓይነቱም ሆነ በይዘቱ ከዕለት ወደ ዕለት በከፍተኛ ፍጥነት እየተለዋወጠ የሚገኘው የዓለማችን ገጽታ ሳያሳስቦት አይቀርም። እውነት ነው የቴሌቪዥን መስኮት በከፈቱ ቁጥር ነውጥና ሁከት እንጅ ሰላምና ልማት የማይታሰቡ ሆነዋል። ሕዝብ በሕዝብ፣ ሕዝብ በመንግሥት፤ መንግሥት በመንግሥት ላይ የሚያምጽበትና የሚነሱበት አስደንጋጭ ክስተቶችም የመገናኛ ብዙሐን ሁለመና ቀስፈው ወደ ሰፊው ውቅያኖስ ይዘው ከመውረዳቸው በተጨማሪ የሰው ልጅ እልቂትና ደም መፋሰስ ሰበር ዜና ሆኖ ሰሚ ጆሮ ማጨናነቅ ተጣጥፎ ቀጥለዋል። ይሁንና በዚህ ሁሉ ሁከት፣ ትርምስና ብጥብጥ የዓለም ማህበረሰብ ልብ በመስለብ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ የሚገኘው የሚድያ ድርሻ ልብ ብለው አስተውሎዋል?

በኢንተርኔት አገልግሎት ብቸኛ ተጠቃሚና ደስተኛ የሆነው ሰፊው ሕዝብ ብቻ ለመሆኑ ስንቶቻችን እንደምንስማማ እርግጠኛ ባልሆንም የኢንተርኔት አገልግሎት ለሰፊው ሕዝብ ጉልበት ሲሆን ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የዓለማችን ግዛት በፖለቲካ ወንበር የተቀመጡ ባለ ስልጣናት ደግሞ የእግር አሳት ሆኖ የሚይዙት የሚጨብጡት ሲያሳጣቸው እየተመለከትን ነው። የኢንተርኔት አገልግሎት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚ ያደረገ ያክል ከአሜሪካ እስከ አውሮፓ ከኤሽያ እስከ አፍሪካ የሚገኙ ዲሞክራቱም አምባገነኑም እኩል እያርበደበደ፣ እያንጰረጰረ፣ ጉልበት እየፈታና አዳራሻሾቻቸውም እያናወጠ ይገኛል ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ተራርቆና ተቆራርጦ የነበረው የዓለም ማሕበረሰብ፤ የአንዲት አገር ሕዝቦች ከኢንተርነት አገልግሎት የተነሳ እርስ በእርስ መነጋገር ወደሚችልበት ደረጃ ቢመጣም መንግስታት ደግሞ በፊናቸው ይህን መነጋገር ተከትሎ የሚመጣ አንድነትንና ሕዝብረት ለመስበር ብሎም ለመበጣጠስ “ሚድያ” በመባል የሚታወቀው ጉልበታም መሳሪያ በመጠቀም የሚመሩት ሕዝብ ወደሚፈልጉት አቅጣጫ የሚዘውሩበትና የሚፈልጉትን ብቻ የሚመግቡበትን አስተማማኝ ጡንቻ ከመጠቀም የባዘኑበት ደቀቃ የለም። የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ጠንካራ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁ አሜሪካዊ የታሪክ ተመራማሪና ጸሐፊ “Propaganda is to a democracy what violence is to a dictatorship.” ሲሉ እንደገለጹት።

አሁን ባለው ነባራዊ የዓላማችን ሁኔታ “ሚድያ” ጸረ ሕዝብ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ሚድያ መንግስታት የሚመሩትን ሕዝብ የሚገርፉበት ጅራፍና አልፎ ተርፎም ጦርነት አብሳሪ፣ ኃያላኑ የሰው ሀገር ለመውረር ሲነሱም “ሚድያ” እንደ ጠቋሚ ኮምፓስና የጦርነት ፊት አውራሪ ሆኖ ሲያገለግል ያየነውና እያየነው ያለ የባለ ስልጣናት አፍ ነው ቢባል ያንሰዋል። ስለሆነም “ሚድያ ንብረትነቱ የሕዝብ ነው!” የሚለው የነቀዘ አባባል ከእውነት የራቀ አባባልና ከመፎክር አልፎም እውነትነት የሌለው ሕጋዊ ውሸት ነው። ሚድያ (መንግስትም ሊሆን ይችላል ላይሆንም ይችላል) ብቻ ግን ኃያላን/ባላሀብቶች በሕግ የሚዋሹበት መሳሪያ ነው።  ለነገሩ “Mainstream Media” ተብሎ መጠራቱ ቀርቶ “Mass Murdering Media” ከተባለ ዓመታት አስቆጥሮ የለ።

ወደ ወቅታዊው ሁኔታ ስንመለስ ባሳነፍነው ሳምንት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስተር ዴቭድ ካመሮን ጋር አርባ ደቂቃዎች የፈጀ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውንና በደማስቆ የኬሚካል የጦር መሳሪያ (Biological Weapon) ጥቃት ሰለባ የሆኑ አንድ ሺህ አራት መቶ የሚደርሱ የዶማስቆ አከባቢ ነዋሪዎች የስሪያ መንግሥት በሻር አል አሳድ ኃላፊነቱን ይወስዳል በሚል መተማመናቸው፤  የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሐላፊ የሆኑት ጆን ኬሪ የስሪያ መንግሥት ባዮሎጂካል ጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል ሲሉ ደጋግመም መግለጫ መስጠታቸው፤ የእንግሊዝ ፓርላመትን እንግሊዝ በስሪያ ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንድትወስድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ ማድረጉ፤ በዛሬው ዕለት ደግሞ የራሽያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ አለኝ የምትለውን ማስረጃ በተባበሩት መንግሥታት ለጸጥታ ምክር ቤት ማስረጃዋን እንድታቀርብ መጠያቀቸው፤ አጀንስ ፍራንስ ፕረስ ስማቸው ያልተገለጸ አንድ የስሪያ የመንግስት የደህንነት ባለሥልጣን ጠቅሶ እንደገለጸው ስሪያ በማንኛውም ቅጽበት ለሚሰነዘርባት ማንኛውም ዓይነት ጥቃት አጸፌታ ምላሽ ለመስጠት/ራስዋንም ለመከላከል በተጠንቀቅ እንደምትገኝ የተገለጸበት ሁኔታ እንዲሁም ረፋዱ ከብዙ ግርግር በኋላ ፕሬዝዳን ባራክ ኦባማ የኮንግረሳቸው ፍቃድ እንደሚሹ ማሳወቃቸውን ሁኔታው እያጋጋለውና እያወሳሰበው ይገኛል።

ጥያቄው እውነት የስሪያ መንግሥት በገዛ ሕዝቡ ኬሚካላዊ የጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል ወይ? የሚለው ጥያቄ ለመመለስ ምዕራባውያን መንግሥታት በማዕከላይ ምስራቅ የሚከተሉትን ፖሊሲና የተያያዙት የፖለቲካ አካሄድ በጥሞና ከማየትና ከማጥናት አልፎ ስሪያ ምድር ድረስ በመሄድ ነገሩን ማጣራት የሚጠይቅ ነው ብዬ አላምንም። ይህ ደግሞ በግሌ ያመጣሁት መገለጥ ሳይሆን በሞያው የተካኑ የፖለቲካ ተንታኞች የሚሉትንና የሚስማሙበት እውነታ ነው። “ሚድያ” በስሪያ ጉዳይ ላይ እየተጫወተው ያለው ከፍተኛ ሚናና መጠነጠ ሰፊ ዘመቻ ከማየታችን በፊት ግን እየሆነ ስላለው ሀገራትና መንግስታት የማውደም ዘመቻ በአግባቡ ለመረዳት ያክል ቀደም ብለው የምዕራባውያን መንግስታት ሰለባ የሆኑ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች (በነዳጅ) ሀገረ ሳዳም ሁሴን ኢራቅ ጨምሮ በአፍጋኒስታንና በሊብያ የሆነውን ከብዙ በጥቂቱ ማየቱ መልካም ይመስለኛል።

በፖለቲካ ሊቃውንት ዘንድ በአህጽሮተ ቃል PRS/N-PRS በማለት የሚታወቀው (Problem-Reaction-Solution/ NoProblem-Reaction-Solution) ጥቅምን የማግበስበስ ስልት በምዕራባውያን ዘንድ በተለይ በአሜሪካና በእንግሊዝ መንግስታት በሚገባ ተግባራዊ ለመሆኑ ምንም አያጠራጥርም። ይህ ማለት መስከረም  11/2001 በአሜሪካ በኒውዮርክ ከተማ ግዙፉ ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል በደረሰ ጥቃት የአሜሪካ መንግሥት ቀደም ብሎ በአፍጋኒስታን ጸረ ሶቬት ሕብረት ያሰለጠነው፣ ያስታጠቀውና ወልዶ ያሳደገው በኦሳማን ቢንላደን የሚመራ አልቃይዳ ነው በማለት በይፋ ሲያሳውቅ ድርጊቱም በአሜሪካውያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ በመቀስቀሱ የአሜሪካ መንግሥት ይህን የሕዝብ ቁጣና ከፍተኛ ድምጽ በመጠቀም (የሚፈለገውም ይህ ነበርና) አልቃይዳ ፍለጋ ተብሎ አፍጋኒስታን እንዳልነበረች አድርጓታል። (የመስከረም 11 ክስተት የአሜሪካ መንግሥት የልቡን ለማድረስ ራሱ የፈጸመው ድርጊት ነው አላልኩም።)

እንደ ጀስ ቨንቱራ (ከ 1999 – 2003 እ.አ.አ የሚንሶታ አገረ ገዢ ነበር ፖለቲከኛና ጸሐፊ) እምነትና ትንተና አሜሪካ አፍጋኒስታን የወረረችበት ምክንያት ለCNN በሰጠው ቃለ ምልልስ እንዲህ ይላል “we are in Afghanistan because there is a Trillion dollars worth of Lithium there.” አክሎም ንጥረ ነገሩ የሚሰጠውን ጥቅም እንደሚከተለው ያብራራዋል “Now, what is lithium used for? Every cell phone, every computer, and soon to be electric cars.”

ወደ ኢራቅ ልሻገር። ከ2003 እ.አ.አ ጥቃት በኋላ ምድሪቱ የቀረላት ነገር አለ ተብሎ መናገር የሚቻል አይመስለኝም። ወድማለች! ተብሎ በአራት ነጥብ ብንዘጋው የሚያግባባን ይመስለኛል። ግን ለምን? ማለቱ ግን ተገቢ ይመለኛል። እስቲ አሜሪካዊው ባለ አራት ኮከብ ጄነራል ዌስሊ ክላርክ በ2003 እ.አ.አ “Winning Modern Wars” በሚል ርዕስ ለህትመት ባበቁት መጽሐፋቸው በግልጽ ያሰፈሩትን እንመልከት።

“As I went back through the Pentagon in November 2001, one of the senior military staff officers had time for a chat. Yes, we were still on track for going against Iraq, he said. But there was more. This was being discussed as part of a five-year campaign plan, he said, and there were a total of seven countries, beginning with Iraq, then Syria, Lebanon, Libya, Iran, Somalia and Sudan.” ”Winning Modern Wars” (ገጽ 130)

ክላርክ በመጽሐፋቸው እንዳሰፈሩት የዋሽንግተን/የፔንታጎን ባለ ሥልጣናት ሶማሊያን ጨምሮ ሁለት በሰሜኑ ክፍል የሚገኙ የአፍሪካ አገራት፤ አራት የማዕከላይ ምስራቅ መንግስታት በአጠቃላይ በአምስት ዓመት ውስጥ ሰባት መንግስታት የማውደም/የመውረር ዕቅድ እንዳላቸው አስፍረዋል። ይህን ዕቅድ ተግባራዊ የሚያደርጉበት ፕላንም ቀድሞ ያለቀ ነው። እዚህ ላይ N-PRS (No Problem-Reaction-Solution) በኢራቅ ላይ እንዴት እንደሰራና የሚድያ ድርሻም  ምን እንደ ነበር እንደመልከት።

ኢራቅን ለመውረር ሌላ ፍንዳታ አላስፈለገም። ፔንታጎን “የሳዳም መንግስት የጅምላ ጨራሽ አውዳሚ መሳሪያ ባለ ቤት ነው! ይህ ደግሞ ለዓለማችን ሰላም ጠንቅ በመሆኑ የዓለም ማህበረሰብ ዋል እደር በሌለበት ድርጊቱን ያወግዘው ዘንድ ይገባል። አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል!” ሲል በሚድያ የሚያሰጨው ፕሮፖጋንዳ ብቻ የዓለም ማህበረሰብ ቀልብ በመሳብና በጭንቀት በመወጠር ሕዝብ ደግሞ በፊናው ከሰማው አስደንጋጭ ዜና የተነሳ “ምን ነው የዓለም መንግስታት ተባብረው ይህን ሰው (ሳዳምን) ባጠፉልን” ሲል በሰጠው ምላሽ ይሁንታ ያገኙ የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግስታት አገሪቱ እንዳልነበረች የፍርስራሽ ክምር አድርጓታል። የዶላር ከረንሲ በተመለከተ የጠነሰሰው ጥንስስ ብቻም ሳይሆን ድሮም ሰውዬም ለምዕራባውያን አጀንዳ የሚመች ሰው አልነበረምና በሕግ ገመድና አንገቱን አገናኝተው በአደባባይ አሰናብተዉታል። ታድያ ከዚህ ሁሉ ግርግርና ትርምስ በኋላ ሰውዬው የተባለው ጅምላ ጨራሽ አውዳሚ መሳሪያ ተገኘበት ሆይ? ለሚለው ጥያቄ አይደለም ጅምላ ጨራሽ አውዳሚ መሳሪያ ይቅርና መርፌም አልተገኘበትም። እና? እናማ እርስዎ ያልሰሙ እንደሆነ አላውቅም እንጅ በአንድ ወቅት አሜሪካዊ አቦይ ስብሃይ ዲክ ቼነይ “እና ምን ይጠበስ ነው!” በማለት ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

እስቲ ወደ ሊብያ ደግሞ እንለፍ። ሚድያም አለ “በዛሬው ዕለት የሊብያ ታጠቂ ኃይሎች ባልታጠቁ ዜጎች በከፈቱት ተኩስ … የሚያህሉ ጹሐን ዜጎች መቁሰላቸውን የዓይን ምስክሮች አረጋገጡ” ሙቀቱ ጨመር አደረጉትና (ሚድያዎቹ ማለቴ ነው) በሚቀጥለው ቀን ደግሞ “አንባገነኑ የሊብያ ገዢ ጋዳፊ … የሚያህሉ ንጹሐን ዜጎች ገደሉ” ሙቀቱ እንደ ጨመረ ነው “ኧረ የሰው ያለህ! ጋዳፊ ንጹሐን ዜጎች ጨረሱ ኡ ኡ ኡ … ምን ነው የዓለም መንግሥታት ዝም ያሉ?” ወደ ማለት ተደረሰ። የትኛው ዓለም አቀፍ ሕግ ይህን ያደርጉ ዘንድ እንደሚፈቅድ ለጊዜው ለማወቅ ባይቻልም በአሜሪካ የታገዘ የNATO ጦር ሊብያን እስክታስነጥስ ድረስ አጨሳት። ነፍስ ይማር! ጋዳፊም ሸሽተው መሸሽ አልተቻላቸውም ተይዘው መሬት ለመሬት እየተጎተቱ ክፉኛ ተደብድበው ተገደሉ። ተልዕኮ ተሳካ!

“ኧረ ጋዳፊ ንጹሐን ዜጎች ጨረሱ ኡ ኡ ኡ የትድግና ያለህ!” የሚለው የሚድያ ጭኸት አይደል ጋዳፊና መንግሥታቸው ጠራርቆ የወሰደ። ቁምነገሩ በሚድያ እንደተነገረን ጋዳፊን የቀሰቀሰ፣ የተነኮሰና ያነሳሳ “የዓረብ ስፕሪንግ” በመባል የሚታወቀው ሕዝባዊ ዓመጽ ነው ብለው የሚያምኑ ከሆኑ በእውነቱ ነገር “ሚድያ” በእርስዎ ላይም ስራውን ሰርተዋል ማለት ነው። “ይሄው ጋዳፊ ንጹሐን ዜጎች እየገደለ ነው!” ተብሎ ለክስም ሆነ ለወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንዲያመች ጋዳፊን ዕንቅልፍ ለመንሳትንና ዕረፍት ለማሳጣት ቀደም ብሎ እንደተገለጸ “ይሄው” ለማለት እንዲያመች ጋዳፊን በተጨባጭ የሚያሳስት ተኩሶ የሚያስተኩስ ገድሎ የሚያስገድል ልዩ ኃይልማ ተሰማርተዋል! ብለው ከጠራጠሩ ግን ነቄ ኖት ማለት ነው። በሊብያ የሆነው ይህ ነው ይላሉ እንግዲህ ፖለቲካ ማለት ምን ማለት እንደሆነንና እንዴት እንደሚሰራም የሚያውቁበት ሊቃውንቱ። የእኔና የእርስዎ መንቃት ግን አይደለም ላይመለስ ያሸለበውን ጋዳፊ በቁሙ ያለውን አሳድ የሚታደግ ለመሆኑ እጠራጠራለሁ። ለማንኛውም ወደ ስሪያ እናምራ፥

መቼም ተጋብቶ የፌርማው ቀለም ሳይደርቅ መፋታት እንደ ሚድያ ያለ የሚያምርበትና የሰመረለት ማንም የለም። እስቲ አሁን ደግሞ የስሪያና የምዕራባውያን ሚድያ ጊዜያዊ ጋብቻ ምን እንደሚመስል እንመልከት። የእስራኤል የስለላ ድርጅት “ሞሳድ” ደረሰበት እየተባለ ከሚያናፈው የዘለለ ያለ አንዳች ተጨማጭ ማስረጃ/መረጃ የኦባማ አስተዳደር የጦር መርኮቦችን ሲያንቀሳቅስ ሚድያዎች በለው! ደብድበው! ድፋው! አጭሰው! ቀቅለው! ፍለጠው! ቁረጠው! በማለት ነገሩን ከማራገብ በመቆጠብ የአሜሪካ መንግሥት በማዕከላይ ምስራቅ ያለው የረጅም ጊዜ ፖለቲካዊ ዕቅድ በማውሳት ወይም በመምዘዝ በስሪያ ላይ ያንጃበበው የጥፋት ደመና ከመነሻው መንስኤው ምን ሊሆን እንደሚችል ለማጣራት (ለመመርመር) ጥረት ያደረገ አንድም የ“ሚድያ” ተቋም ፈልጎ ለማግኘት አልተቻለም።

“የስሪያ መንግሥት” ቀጥሎ ደግሞ “በሻር አል አሳድ” የሰሙኑ የምዕራባውያን ሚድያ የመግባቢያ ቋንቋ ሆኖዋል። በቀንም በውድቅት ሌሊትም የሚሰሙት ቃል ከተጠቀሱ ቃላቶች የወጣ አይደለም። ሁሉም (ምዕራባውያን የሚድያ ተቋሞች ለማለት ነው) በአንድ ቃል ይስማማሉ ይኸውም፥ “በሻር አል አሳድ የኬሚካል ጦር መሳሪያ በመጠቀም ንጹሐን ዜጎች ፈጅተዋል” በሚል ጭብጥ ላይ ያልተመሰረተ ክስ ይስማማሉ። ሌላ እነዚህ ሁሉ የመገናኛ ብዙሐን አንድ የሚያደርጋቸው ጉዳይም አለ ይኸውም አንዳቸውም ለሚዘግቡት “ዜና” የሚያቀርቡት ተጨባጭ ማስረጃ የላቸው። “በሻር አል አሳድ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል ተጠቅመዋል ነው!” ከሚል ውጭ ሌላ የሚሰሙት “ዜና” የለም። እንዲህ ያለ አቀራረብ ደግሞ ዜና ሳይሆን ፕሮፖጋንዳ ነው።

በዙሪያው ሙያዊ ተመክሮአቸውና እውቀታቸው እንዲያካፍሉ የሚቀርቡ የተለያዩ ግለሰቦች ወደሚሰጡት አስተያየት ያመራን እንደሆነም “የለም ይህ ነገር አሜሪካን አይበጅም” በማለት ተቃውሞአቸውን የሚያሰሙ ሙሑራን ከአስር ሁለት ቢሆኑ ነው የተቀሩት ግን “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” እንዲል ያገሬ ሰው ማንም ይተኩሶው ማን ይህን የመሰለ ጥብስ የሆነ ዕድል ተገኝቶ እያለማ አል አሳድን መጥበስ ነው እንጅ የምን የተባበሩት መንግስታት ውጤት መጥበቅ ነው። ፕሬዝዳንት ጦርነት ለማወጅ ባለ ሙሉ ስልጣን ነው። የኮንግረስ ፈቃድ ወይም እውቅና የሚጠብቅበት ምንም ምክንያት የለውም። በማለት ነገሩን የሚያጋግሉ ስፍር ቁጥርም የላቸው። በዚህ ሁሉ የግለሰቦች የሚመስል አስተያየት ሚድያ ተልዕኮውን እየተወጣ ነው።

ፕሬዝዳንት ኦባማ ከአሜሪካ ኢኮኖሚያዊ ጥቅምም ሆነ ብሔራዊ ደህንነት አንጻር ሲታይ በከፊልም ሆነ በምን ስሪያን የሚወርበትና ወታደራዊ ጥቃት የሚያደርስበት አንዳች ምክንያት እንደሌለው ጠንከር ያለ ተቃውሞ የሚያሰሙ ተንታኞችም አልታጡም። ተንታኞቹ አክለው እንደሚገልጹትም ኦባማ ስሪያን ለመውረር የተውተረተረበት ዋና ምክንያት ይላሉ ስሪያ ለአሜሪካ ደህንነት የምታሰጋ አገር ሆና ሳትሆን አስተዳደሩ በIRS በNSA በባንጋዚ የደረሰበትን ኪሳራና ያጣውን ተአማኝነት ለመመለስ ነው በማለት የኦባማ አስተዳደር በስሪያ ለሚወስደው እርምጃ አሜሪካ ወደከፋ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ አዘቅት የሚከት ነው ሲሉም ተሰምተዋል።

እኔምለው ግን አሜሪካ ሆነች እንግሊዝ እግር አለሁ እያለች የምትገኘው ሀገረ ፈረንሳይ የሰው ሀገር ይወሩና ያወድሙ ዘንድ የፈቀደላቸው ማን ነው? በውኑ ይህን ያደርጉ ዘንድ የሚፈቅድ ሕግ አለ? የተባበሩት መንግሥታት የኬሚካል ጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ ውልዋል አልዋለም የሚለውን ከማረጋገጥ ያለፈ የኬሚካል ጦር መሳሪያው ማን ተኮሰው? የሚለውን ጥያቄ የማጣራትም ሆነ ለጥያቄው መልስ የመስጠት ስልጣኑ የለውም አሉን። እውነት? የራሽያም ሆነ የቻይና ድጋፍ የሌላት አንዲት ድንጋያማ አፍሪካዊት አገር አንዲት ነገር ብታደርግ ግን የተባበሩት መንግስታ ርሃብ እንደጠለፈው ጅብ ዘሎ ማዕቀብ ለመጣልም ሆነ አንድን ነገር ለማድረግ (ውሳኔ ለማስተላለፍ) ማንም አይቀድመውም ነበር። ድግነቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከዋልያ በቀር የዘይትም ሆነ የነዳጅ ባለቤት ባለመሆንዋ ከዚህ ሁሉ ወከባና ቡጢ ተርፈናል። ቢሆንም እንደ የአንዲት ሀገር ልጆች ልዩነቶቻችን በማጥበብ የተባበርንና የተስማማን እንደሆነ የማይለወጥ ታሪክ የለምና ሰርተን የሀገራችን ገጽታ የለወጥን ዕለት “ድሪማችን” ከሚያጨናግፍ ከ“ድሮን” እናመልጣለን ማለት ግን የዋህነት ነው። “ነግ በኔ” ማለት ጥሩ ነው እያልኩ ነው።

ዲን ሙሉጌታ ወልድገብርኤል

E-mail: yetdgnayalehe@gmail.com

United States of America

August 31, 2013

ሽብርተኛው ወያኔ/ኢህአደግ በሀይማኖቶችና በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚያደረገውን እኩይ ሴራ እናወግዛለን! -ENTC

$
0
0

entc-logo-5ባሳለፍናቸው ወራት በኢትዮጵያ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች እየደረሱባቸው ያሉ አፈናዎችንና እስሮችን በመቋቋም ህዝቡ  ለመብቱ እንዲቆም እያደረጉ ያሉትን የማነቃቃትና የማንቀሳቀስ ስራ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም ሳይገድሉ  እየተገደሉ ያለመታከት ከአንድ አመት በላይ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለጥያቄያቸው ምላሽ በመሻት ድምዳቸውን  በማሰማታቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክርቤት ያለውን አድናቆትና አክብሮት ይገልጻል። እንቅስቃሴዎቹም  የሽግግር ምክርቤት ከሚከተለው የህዝባዊ እምቢተኝነት የትግል ስልት ጋር ተዛማጅ በመሆናቸው ሙሉ ድጋፋችንን መግለጽ  እንወዳለን ።ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

“ትግላችን የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር ተሸጋግሯል!” – ሰማያዊ ፓርቲ

$
0
0

semayawi partyሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች መልስ ባለማግኘታቸው ለሕዝብ ቃል በገባነው መሠረት በድጋሚ ተቃውሞ ሰልፍ አቅዶ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ ለዚህም ሥራ መሳካት ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ነሐሴ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን፣ መጀመሪያ ባቀረብነው ደብዳቤ ላይ ያልተካተቱ ጉዳዮችን እንድናካትት ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈልን ደብዳቤ ተጠይቀን አስፈላጊውን መልስ አሟልተን ነሐሴ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈ ደብዳቤ አሳውቀናል፡፡
በአዋጁ በግልፅ እንደተደነገገው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግሥታዊ መብት እንደሆነና ማንም ሊከለክለን እንደማይችል በማያሻማ መንገድ ተገልጿል፡፡ ሰልፉን የማሳወቁ ዓላማ የጥበቃ አገልግሎትና አንዳንድ አስተዳደራዊ ድጋፎችን ለማግኘት ነው፡፡ በዚህ አሰራር ውስጥ መንግሥት የጥበቃና የቦታ ችግር ካለ ሰልፉን ለሌላ ጊዜና ቦታ እንዲያደርግ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ በደረሰው በ24 ሰዓት ውስጥ በፅሑፍ መልስ ይሰጣል የሚል ድንጋጌ አለ፡፡ ነገር ግን በመንግሥት በኩል ላቀረብነው የመብት ጥያቄ ምላሽ መሰጠት ሲገባው እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ የመንግሥት መዋቅር ሙሉ በሙሉ በመጠቀምና ዜጐችን አስገድዶ ሰልፍ እንዲወጡ በማስፈረም ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ቀንና ቦታ ሌላ ሰልፍ በተደራቢ በሃይማኖት መቻቻል ስም ህገ መንግሥቱን በመጣስ የሃይማኖት ተቋማትን ለራሱ የድርጅት ፖለቲካ መጠቀሚያና የሰማያዊ ፓርቲን ህጋዊ እንቅስቃሴ ለመግታት እየተጠቀመበት ነው፡፡ ይህ አሰራር እንዲስተካከል መንግሥትን በመግለጫ ብንጠይቅም የተሰጠን ምላሽ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ የሀገሪቱን ህገ መንግሥትና የሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ እንዲሁም ሰልፍ ጠሩ በተባሉ አካላት ግልፅ የሆነና የተቀነባበረ ህገ ወጥ ሴራ ሆኗል፡፡
ስለሆነም በነገው ዕለት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. የምናደርገው ሰላማዊ ሰልፍ ከዚህ ቀደም ያቀረብናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረብ ከመሆን አልፎ የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር አድጓል፡፡ በመሆኑም በመንግሥት የሚደረገው ዓይን ባወጣ ሁኔታ ህግን የመጨፍለቅ ተግባር እንዲቆም ለምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ከጐናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ምንጊዜም የተባበረ የሕዝብ ትግል ያሸንፋል!
ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

አረመኔው የሕወሐትና የደሕንነት ሹም – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

weldesilaseየሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ የነበረው ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ከያዘው ስልጣን መነሳቱን ምንጮች በመጥቀስ ከሁለት ወር በፊት ዘገባ አቅርበን ነበር። በጭካኔው የሚታወቀውና በሙስና የተነከረው ወ/ስላሴ በሙስና ዘብጥያ ወርዷል። በእስር ቤት በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖችን ያሰቃይ የነበረው ወ/ስላሌ ከበረሃ ጀምሮ በርካታ የድርጅቱን ታጋዮች በመረሸን እንደሚታወቅ ባለፈው ዘገባ መገለፁ ይታወሳል። በትግሉ ዘመን የፓርቲው አባለት « ፆታዊ ግንኙነት ስታደርጉ ተገኝታችኋል…» በሚሉና ሌሎች ተልካሻ ምክንያቶች እንዲረሸኑ በበላይ አመራር ውሳኔ የተላለፈባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የፓርቲው አባላት (ታጋዮች) ለመግደል ይጣደፉ ከነበሩት መካከል ኢሳያስና ወ/ስላሴ ዋናዎቹ ነበሩ ። አቶ መለስ ሁለቱን አባላት ወሳኝ በሆነው የደህንነት ቢሮ ቁልፍ ስልጣን የሰጧቸው « አድርጉ » የተባሉትን ያለማመንታት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነበር። ወ/ስላሴ ስልጣን በጨበጠ ማግስት በአንድ ቀን አርባ የቢሮው አባላትን ( መኮንኖች ተብለው ነው የሚጠሩት) እንዳባረረ የገለፁት ምንጮቹ፣ በየጊዜው በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላትን « ተሃድሶውን አልተቀበላችሁም፣ የቅንጅት ደጋፊዎች ናችሁ..» በሚሉና ሌሎች ምክንያቶች ከማባረር – እስር ቤት እስከመወርወር የደረሰ እርምጃ ሲወስድ ቆይቷል። ከመለስ ጋር በሃሳብ ያለተስማሙ ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናትን በገዛ መኖሪያ ቤታቸው በገመድ በማነቅና በስለት በማረድ የጭካኔ ተግባር ያስፈፀሙት ወ/ስላሴና ኢሳያስ መሆናቸውን ተገልጧል። በግፍ የተገደሉት የመገናኛ ሚ/ሩ አቶ አየነውና የቤተመንግስት የደህንነት ሹም አቶ ዘርኡ ናቸው።
መስከረም 2 ቀን 1996ዓ.ም የኢትኦጵ ጋዜጠኛን ቢሮው በማስጠራት ለሁለት ሰአት ያክል ካስፈራራው በኋላ እንደሚገድሉት ዝቶ አሰናበተው። ጋዜጠኛው በ15 ቀን ውስጥ አቋሙን አስተካክሎ፣ የመረጃ ምንጮቹን አሳልፎ ካልሰጠ እንደሚገደል ነግሮ ያሰናበተው አረመኔው ወ/ስላሴ፣ መስከረም 20 ቀን 1996ዓ፣ም ሰባት የፌደራል ፖሊሶችን በማሰማራት ጋዜጠኛው የግድያ ሙከራ እንዲፈፀምበት አድርጓል። ፖሊሶቹ አካሉን ካጎደሉትና ክፉኛ ከደበደቡት በኋላ ድልድይ ውስጥ ወርውረት እንደሄዱ ይታወቃል። በ1997 እና 98 ዓ.ም በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተወሰደውን ጭፍጨፋ፣ እስርና ድብደባ ከጠ/ሚ/ሩ ትእዛዝ በመቀበል ተፈፃሚ ያደረገና ዋና ተዋናይ የነበረው ወ/ስላሴ፥ ዜጎች ያሰቃይበት ወደነበረው ማእከላዊ እስር ቤት ተወርውሯል።

ርዕስ በምርቃት፤ የማን ሙት አመት? (ስለ ሙስሊም ጉዳይ፤ ስለ አገር ጉዳይ)

$
0
0

muslim and christian
ሁለት ዓመት ሊሞላው እየተንደረደረ ያለው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ንቅናቄ ሂደት በተለያየ ወቅት የተለያዩ ጎላ ብለው የሚታዩ ክስተቶችን እያስተናገደ አሁን ላለበት ደረጃ ደርሷል። እነዚህ ጎላ ያሉ ክስተቶች አንዳንዴ ብቅ የሚሉት ከወደ መንግስት በኩል ሲሆን እኔም ጨረፍ አድርጌ ለማለፍ የምሞክረው ይህንኑ ከመንግስት በኩል ጎላ ብሎ ብቅ ያለውን ወቅታዊ ዘመቻ ነው። እንደሚታወቀው ይህ የሙስሊሙ የመብት ጥያቄ ወደ መጀመሪያ አካባቢ ከመንግስት እውቅና ተነፍጎት ለጥቂት ጊዜ ከቆየ በኃላ የህዝቡን አካሄድ “ሸውደን” ማለፍ አንችላለን በሚል ድምዳሜ “ሰላማዊና ህገመንግስታዊ ” ስለመሆኑ ከመንግስት በኩል ይፋዊ ያልሆነ (በቃልና በደብዳቤ) ሙገሳ “ተችሮለት” ከመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴው ጋር “ንግግር” ተጀመረ። በቅፅበትም መንግስት በይፋ እውቅና ያልተሰጣቸውን እነኚሁ ጥያቄዎች “ትክክለኛ” መሆናቸውንና “በአጥጋቢ ሁኔታ መመለሳቸውን” በይፋ በመገናኛ ብዙሃን ማስለፍለፍ ጀመረ። በተጓዳኝም ሰላማዊ የነበሩት የኮሚቴው አባላት ባንድ ጀንበር የ “አሸባሪነት ” ካባ ተደረበላቸው። ይሄ ኮሚቴውን “የመነጠል” ዘመቻ እስከ ቀትር አላስጉዝ ሲል: ወዲያው ጥያቄው “የጥቂት አክራሪዎች” ስለመሆኑና “ሰፊው ሙስሊም” ሕብረተሰብ ከመንግስት ጋር ስለምሆኑ ሰፊና ረጅም ዘመቻ ተከፈተ። ሙስሊሙን የመከፋፈል መሆኑ ነው። በዚህም ወቅት አንዳንድ ግልሰቦችን የተለያየ ቆብ አስለብሰው በቴሌቪዥን ላይ እያመጡ ስለ መንግስት ጥሩነት አስለፈፉ። እነዚሁን ግለሰቦች አንዴ ኮፍያ አንዴ ጥምጣም አንዴ ጋቢ አንዳንዴም አረንጉአዴ ነገር እያለበሱ: ሲላቸው “አንዳንድ ያዲሳባ ወይንም የምንትስ አካባቢ” ነዋሪዎች: ሲላቸው ደግሞ “የታወቁ የሃይማኖት ምሁራን” ወይንም ያገር ሽማግሌ: ገፋ ሲልም “የአህሉ ሱና ወልጀመአ” አባላት እያሉ ያቀርቧቸው ነበር። “የአህሉ ሱና ወልጀመአ” ማለት መንግስት “አህባሽ” የምትለዋን መገለጫ ለመደበቅ የዘየዳት የሽወዳ ቃል መሆኗ ነው። የሚገርመው አነዚሁኑ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦችን በስብሰባውም በቃለመጠይቁም በውይይቱም ባውደጥናቱም “በግንዛቤ ማስጨበጫውም” በወዘተውም በሁሉም ላይ ተናጋሪ መሆናቸው ነው። አንዳንዶች ምነው መንግስታችን ስንት ድራማ መስራት እየቻለ ለዚህ የሚሆኑ ሌሎች ሰዎችን መጨመር አቃተው? ይሉ ነበር። (በቅርብ ግዜ እንደወጡ ዘገባዎች ከሆነ መንግስት ሰላዮቹን እስራኤል ድረስ እየላከ በእስልምና ትምህርት አሰልጥኗል።)
ይሄው ረጅም ግዜ የወሰደው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ትንሽ እንኳ ጠብ ብሎ መንግስት የፈልገውን የመከፋፈል ሴራ ሊያሳካ ይቅርና ይብሱኑ ሙስሊሙ ኅ/ሰብ “ይሄ ነው ወይ መንግስት?” “እነዚህ ናቸው ወይ ያገር መሪዎች?” እያለ ይጠይቅ ገባ። በተያያዥነትም ተጠናክሮ የቀጠለው የፖሊስ ወከባ፣ አይን ያወጣ ዝርፊያ (በተለይም የኪስ ገንዘብ ነጠቃና የሞባይል ስልኮች ቅሚያ) እና ቅጥ ያጣው መረን የለቀቀው የደህንነቶች ዛቻና ማስፈራሪያ (intimidation) በሥራና በንንግድ ቦታ እየመጡ ማሸማቀቅ፣ በየቢሮው እየገቡ የፌስቡክ አካውንቶችን አስገድዶ ማስከፈት በተለይም ባንድ ወቅት በሰፊው ሲያኪያሄዱት የነበረው የሌሊት ቤት ሰበራና ዝርፊያ ከሁሉም በላይ ተጠናክሮ የቀጠለው እስር፣ ቶርችና ግዳያ: ሙስሊሙን ኅ/ሰብ ከማበሳጨትና ከማሳዘን አልፎ: የመብት ትግል ሙቀትን ከሩቁ የሚሸሹ፣ ከመንግስት ጋር “መነካካትን” የማይፈልጉ፣ እንዲሁም መጀምሪያ አካባቢ በመንግስት ተደናብረው የነበሩ ዜጎችን እስከነአካቴው ጥርግርግ ብለው ትግሉን እንዲቀላቀሉ አድርጓቸዋል። የመንግስት ምኞት በዚህ ዘመቻ የትግሉን “አንቀሳቃሾች ማደንና” በጊዜ ሂደት መረቡን በጣጥሶ ትግሉን ማዳከምና ማክሰም ቢሆንም የሆነው ግን ተቃራኒው ነበር። ከአመት በፊት መሪዎችን በማሰር ትግሉን ለማዳፈን ያሰበው መንግስት በድጋሚ በዚህ ዘመቻውም ሊሳካለት አልቻለም። መንግስት በሙስሊሞች ላይ ሲያሴር የነበረውን “የመከፋፈል” አጀንዳ አንዳልተሳካለት ያረጋገጠው ክስተት የታየው በቅርቡ በተከበረው የኢድ በዓል ላይ ያካሄደው የጅምላ (indiscriminate) ጭፍጨፋ ሲሆን ሴት፣ ሕፃን፣ አሮጊት፣ ሽማግሌ ሳይል ለስለላና ለጥቆማ የላካቸውን ጀሌዎቹን ሳይቀር ያለርህራሄ የደበደበት ሂደት ነበር።
መንግስት በሙስሊሞች ላይ ያለውን ካርታ ተጫውቶ ጨርሷል፣፣ አሁን የሚቀረውን የመጨረሻ ካርድ በክርስቲያኑ ሕብረተሰብ ላይ መዟል። የወያኔ ውሸት ፍርድ ቤት እንኩአን ለድራማ አይመችም ብሎ ውድቅ ያደረገውን “ጥያቄው እስላማዊ መንግስት መመስረት ነው” የምትለዋ ቧልት፣ “በጠቅላይ ሚንስትርነት ማዕረግ ተመድቤ እየሰራሁ ነው” በሚሉት ግለሰብ (አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ) አጋፋሪነት አንደገና ተቀስቅሳ ክርስቲያኑን ለማስበርገግ ሰፊና የተቀናጀ ዘመቻ ተጀምሯል። (እዚህ ጋር የኬንያው ፕሬዝደንት ለረመዳን ሙስሊም ዜጎቻቸውን እንኩዋን አደረሳችሁ ለማለት አብረው የረምዳን አፍጥር መዓድ ሲቋደሱ፣ የኛው “መሪ” ግን ለኢድ በዓል በዋልታ በኩል ያስተላለፉት መልክት “ዋ! እንገላለን” አይነት መሆኑ ከኬንያ ጋር ያለንን ርቀት ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ወደጉዳያችን፣) ይህ እጅግ አደገኛ የወያኔ “የክፉ ቀን” ካርድ በብዙዎች ዘንድ አንዲህ በቀላሉ ይመዘዛል የሚል ግምት አልነበረም። እነዚህ ጨቋኞች የፈልጉትን ለማግኘት አገሪቱ ዶግ አመድ ብትሆን ደንታም እንደሌላቸው በግልፅ የታየበት ወቅት ላይ ደርሰናል።ይህ ዘመቻ በአገር ውስጥና በውጭ ኢትዮጵያውያን በብዛት በሚገኙበት አካባቢ በስፋት አንዲካሄድ የታቀደ ሲሆን፣ በአገር ውስጥ አንደነ ሪፖርተር፣ አዲስ አድማስ፣ ሰንደቅ አና ሌሎችም ጋዜጦች ልክ አንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በቅንጅት እየሰሩበት ነው። እንደምታስታውሱት አንዴ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውጭ አገር ዕረፍት ላይ ናቸው ሲላቸውም ቤተመንግስት ውስጥ እያገገሙ ነው፣ ክብደት የቀነሱት በአዲሱ ዳይት ነው፣ ነገ አዲሳባ ሊገቡ ነው ወዘተ በማለት ህዝብን እንዲያደናግሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ሲወጡ የነበሩ ጋዜጦች፣ አሁን ደግሞ አዲሱን ተልዕኮዋቸውን ለመወጣት አየሰሩ ይገኛሉ።

muslimየዛሬ ዓመት አካባቢ“እነ አሕመዲን ጀማል ይቅርታ ጠየቁ” በሚል ርዕስ “አሕመዲን ጀማልን ጨምሮ በእስር በሚገኙት ሥምንት አባላት ፊርማ ደብዳቤው ለምክር ቤቱ እንደደረሰም ምንጮች ተናግረዋል፡፡” በማለት ስለታሰሩት የሙስሊም ኮሚቴ አባላት ሕዝቡን ለማደናገር የሞከረው አዲስ አድማስ ዘንድሮ ደግሞ “በ22 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ያስተዳደረ ሙስሊም የለም” የሚል መፈክር ሙስሊሞች ይዘው ወጡ ብሎናል። ጥያቄው “የስልጣን” ለማስመሰል ሆን ተብላ የተጨመረች መሆኗ ነው። ሪፖርተር ደግሞ በበኩሉ በ”ክቡር ሚኒስትር” አፃፃፍ ዘይቤ አይነት (satire) “የሙስሊሞች ፖለቲካዊ ጥያቄዎችና ፖለቲካዊ መፍትሔዎች” በሚል ርዕስ የፈበረክውን ልብወለድ “እውነት” አስመስሎ ለማቅረብ ሞክሯል። ይህንን የወያኔ ዘመቻ ልዩ የሚያደርገው በውጭ ያሉ የስርዓቱ ደጋፊና በመንግስት በጀት የሚደግፉ ድረገፆችና ሬድዮችን አቀናጅቶ መንቀሳቀሱ ነው። እነዚህ ድረገፆችና ሬዲዮ ፕሮግራሞች ከፍተኛና ሀልፊነት የጎደለው የስም ማጉደፍ ዘመቻ በሙስሊሙ ወገናችን ላይ የከፈቱ ሲሆን ግልፅ የሆነ የሙስሊም ጥላቻ “በአክራሪ” ስም ይሰበክባቸዋል። በተለይም በየድረገፆቹ አስተያየት መስጫ አምዶች ላይ ስማቸውን ቀያይረው እስላምና ሙስሊሞች ከምድረገፅ መጥፋት አንዳለባቸው በግልፅ ይወተውታሉ።ክርስቲያኑን ሕብረተሰብ ልትታረድ ነው እያሉ ከማስፈራራት አልፈው ትግራይ ኦንላይን በተባለው ድረገፅ “ተነስ” ተደራጅ ሳትቀደም ቅደም የሚል ግልፅ የጥፋት ጥሪ አስተላልፈዋል። ባንድ ወቅት የሙስሊሙን ጥያቄ ከዓባይ ግድብ፣ ግብፅና ናይል ፖለቲካ ጋር ለማሳሳብ ሌት ተቀን ሲታትሩ የነበሩ አሁን ፊታቸውን በቀጥታ ሙስልሙን ወደማጥቃት አዙረዋል። በተለያዩ የኢንተርኔት ገፆች የተገኙ ከእውነት የራቁና ምንም ሳይንሳዊ መስረት የሌላቸው “ጥናታዊ ፅሁፎች” በአማርኛ እየተተረጎሙ በድምፅና በፅሁፍ ያቀርባሉ። በተለያየ ወቅት “ከፓልቶክ” መድረክ ላይ “ተቀዱ” የተባሉ በማን አንደተንገሩ የማይታወቁ አፀያፊ ንግግሮች ከባዕድ አገር ከተፈፀሙ ቪድዮች ጋር እየተቀናበሩ ክርስቲያኑን የማስበርገግና ፍትሃዊ የሆነውን የሙስሊሙን ጥያቄ የማጠልሸት ዘመቻ ላይ ውለዋል። በአሜሪካን አገር በአክራሪ ነጭ ዘረኞች በሚመሩ ቤተክርስቲያናት አማካይነት በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ፈሶባቸው የሙስሊም ጥላቻን ለማስፋፋት የሚሰሩ የተለያዩ ፅሁፎችና የሚዲያ ውጤቶች ላገራችን ሕዝብ እየተፈተፈቱ ያቀርባሉ።
ወያኔን ወደዚህ አደገኛ ውሳኔ ካደረሱት ነገሮች መካከል ሁለቱን አሁን መጥቀስ እፈልጋለሁ። አንደኛው የሙስሊሙን ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ማዳፈን እንደማይችል ድምዳሜ ላይ በመድረሱ ሲሆን፣ እንቅስቃሴውን ለመምታት ሰላምዊ ሂደቱ መደናቀፍ አለበት ብሎም ያምናል። እስካሁን ድረስ እልህ አስጨራሽ ትንኮሳዎችን ተቋቁሞ ሰላማዊነቱን ማስጠበቅ የቻለውን የሙስሊሞች ትግል ወደ አገራዊ ብጥብጥና የሃይማኖት ግጭት ካመራ ፣ መንግስት “ሰላምን” በማስጠበቅ ሰበብ የገደለውን ገድሎ (የፖለቲካ ተቃዋሚውንም ጭምር) የቀረውን ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛ ማድረግ እችላለሁ፣ ፣ በተጨማሪም ከምዕራባውያን “ለፀረሽብር ትግሉ” የማይነጥፍ ገንዘብና መሳሪያ አገኛለሁ። እንዲሁም ማንኛውም የፍትህ የዲሞክራሲና የእኩልነት ጥያቄዎች እስከወዲያኛው ተዳፍነው ይቀራሉ ከሚል ቅዥት ሲሆን። ሁለተኛውና ተያያዥ የሆነው ምክንያት ደግሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይህን የሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል የመኮረጅና የመደግፍ አዝማሚያ መንግስትን በጣም ስጋት ላይ ስለጣለው ነው። ለዚህም ነው የመንግስት ባለስልጣናት ከሀይለማርያም ደሳለኝ እስከ ሽመልስ (ሼምየለሽ) ከማል ስለ “ፓርቲዎችና አክራሪዎች ጋብቻ” የሚያወሩት። ይህ ክርስቲያኑን የማስበርገግና የማነሳሳት ዘመቻ ፓርቲዎች ላይ ተፅዕኖ የማሰደርና ከሙስሊም ወገናቸው እንዲርቁና በተቃራኒውም እንዲቆሙ ግልፅ የሆኑ ጥሪዎች የተካተቱበት ነው። ይህው በክርስቲያኑ ላይ የተከፈትው የማስፈራራት ዘመቻ በሙስሊሞች ላይ የሚያርፈውን የግፍ ዱላ በማጠናከር የሚታገዝ ነው። ሙስሊሙን በበለጠ የማጥቃት አጠቃልይ ዘመቻ በቅርቡ የተጀመር ሲሆን እስርና ግድያውን ለማስፋፋት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ከራሱ ከመንግስት ባለስጣናት አፍ እየተነገር ነው።አቶ ኃይለ ማርያም “ትግስታችን አልቁዋል” ሲሉ አቶ በረከት ደግሞ ህዝቡ መንግስት ቦንብና መትረየስ አንዳለው አያውቅ ይመስል “መንግስት ኃይል አለው ጉልበት አለው” ብለዋል። (አይዝዎ አቶ በረከት ሳር ሳይሆን የሰው ሕይወት አጭዳችሁ ለዚህ መብቃታችሁ; እሱንም ለማስጠበቅ ባደባባይ መቶዎችን እንደረሸናችሁ ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል።) ሙስሊሙ በግፍ ብዛት ሲማረርና የወገን ያለህ ሲል ክርስቲያኑ ደግሞ ሙስሊም ወገኑን ይብሱኑ እንዲፈራው፣እንዲጠላው ጭራሹንም “ይገባቸዋል” እንዲልና አመቺ ሆኖ ሲገኝም በጥቃቱ እንዲተባበር ለማድረግ ያለመ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ነው። ይህ የመንግስት እቅድ ከተሳካ በክርስቲያኑና ሙስሊሙ ሕብረተሰብ መካከል ሊፈጠር የሚችለው የሃሳብ ልዩነትና ተቃርኖ ምን አይነት አስቃቂ ጉዳት ባገራችን ላይ ሊያደርስ እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ስለዚህም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይህንን መሰሪ ተንኮል ላገሪቱና ለራሱ ደህንነት ሲል በአንድነት በመቆም ማክሸፍ መቻል አለበት።
ምርቃት
የማን ሙት ዓመት? የማን ራእይ?

ሰሞኑን የመንግሥትና ደጋፊ ሚዲያዎችን ያጨናነቀው የታላቁ መሪ ሙት ዓመት ዝክር ነበር። ይህ ወደ ወር አካባቢ የፈጀው ሽርጉድ የመንግስትንና የህዝብ የስራ ሰዓትን ከመሻማት አልፎ የዕለት ተለት እንቅስቃሴዎችን አስተጓግሎ እንዲሁም ጥቂት የቀሩ ራዕዮችን ለአቶ መለስ አስረክቦ ቀዝቀዝ እያለ ያለ ይመስላል። እኔ አንዳንዴ ሳስበው ያለ መለስ ራእይ ያገራችን ግብርና ኢንዱስትሪ ትምህርት ጤና ሙዚቃ ጥበብ ሚሊተሪ አንደው ሁሉ ነገራችን የት ይሆን አንደነበር ሳስብ “ይዘገንነኛል”፣ በምድር ሳሉ ያላየናቸው “ራዕዮች” ወደዚያኛው ከሄዱ በኋላ መዥጎድጎዳቸውም አንዲሁ ። እድሜ ለሳቸው (ፅ ፅ! ይቅርታ ሞተዋል ለካ? ለነገሩ አንድ ግለስብ በቴሌቪዥን ቀርቦ ከገድላቸው አንዱ የሆነውን ” አህሉ ሱና ወልጀመአ ማህበር ያቋቋሙልን” ብሎ ሲያሞግስ “ገነት” መግባታቸውን መስክሮልናል።) አዎን እድሜ ለሳቸው ያገሪቱን ወታደራዊ ሃያል አሽመድምደው “ለጠላት” ካገለጧት በኋላ፣ ለምን ዝግጅት አልነበረም? ተብለው ሲጠየቁ፣ ያው እንደተለምደው በቃላት አክሮባት ጥበባቸው ፣ “በቴክኒክ ዝግጁ ባንሆንም በታክቲክ ግን የተሻለ አቅም ፈጥረናል” ሲያብራሩም “ደካማ ወታደርና የዛገ ታንክ ቢኖረንም ለዚያ ይወጣ የነበረውን ለልማት በማዋልችን የተሻልን ነን” አሉንና 80 000 ወጣት ዜጎችን አስጨርሰው በብዙ ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ያገር ገንዘብና ሀብት አስባከኑ። ለጦርነቱ ከወጣው አጅግ ባነሰ ገንዘብና ያለምንም ሊባል በሚችል የሰው ይህወት ጠንካራ መከላከያ ቀድሞውኑ ቢኖር ኖሮ ያሁሉ ሕልቆመሳፍርት ሕይወትና ንብረት ባልተማገደ ነበር። ይህንን ለማወቅ ላቅምአዳም/ሔዋን መድረስ ብቻ በቂ ነበር። እንግዲህ እኒህ ጠቅላይ ነበሩ የወታደራዊ መሃንዲስ ባለራእይነት የተሸለሙት። እሺ ይሁን ግድ የለም፣ ግን የጋሽ ዘበርጋን ራእይ (ምኞት) ለጠቅላዩ ሲሰጥብኝ ግን አኔ በቃ! ብያለሁ።
ነገሩ አንዲህ ነው፣ ያደኩበት ሰፈር የማገዶ እንጨት በሸክም የሚያመጡ አቶ ዘበርጋ የሚባሉ ሰው ነበሩ፣ አፈሩ ይቅለላቸውና። ናም ያዲሳባ ደን እየተመንጠረ የሳቸውም ጉዞ አየራቀ መጣ። ከእድሚያቸው መግፋት ጋር በቀን ሁለቴ መሄድ እያቃታቸው መጣ። ያኔ ጋሽ ዘበርጋ ተመኙ በጣም ተመኙ ሃስብና ራዕያቸው ሁሉ የሰፈራችን ሜዳና ጋራ በደን ለመሸፈን፣(የዛሬን አይርገውና ያኔ ብዙ ክፍት ቦታና ሜዳ ነበር በየሰፈሩ) አሳቸው ወደጫካ ከሚሄዱ ጫካውን ወደራሳቸው የማምጣት “ራእይን ሰንቁ”። ብዙዎች በድህነታቸውና ባለመማራቸው የሚንቋቸው ጋሽ ዘቤክስ፣ ለብቻቸው ከቀበሌ ከፍተኛ እየተመላለሱ፣ ጠማሞቹን የቀበሌ ሹማምንት አሳምነው ራእያቸውን አሳኩ። ሜዳውን ሁሉ አስፈቅደው ችግኝ በችግኝ አደረጉት። እኛም በልጅ ልባችን እየረገምናቸው የሰፈራችንን ሜዳ ለችግኝ አስረክበን ኳስ ለመጫወት ሩቅ መሄድ ጀመርን። እናም ጠቅላዩ በሞቱ ባመቱ የጋሽ ዘቤ ራእይ እንዲሁ ለሌላ ሲሰጥ የኛ ሰፈር ልጆች ዝም ብለን አናይም! አራት ነጥብ። እኔ ምለው? ጠቅላዩ “ሞቱ” ከተባለ ጀምሮ በየሚዲያው በየቢሮው በየሰብሰባው በየመንገዱ በየወረዳ በኤምባሲዎች ጭምር ፎቶዋቸና ራእያቸው፣ እንዲሁመ የግብርና የኢንዱስትሪ የትምህርት የጤና የሙዚቃ የስነጥበብ የሚሊተሪ እንደው የሁሉም መሃንዲስ ተደርገው እየቀረቡ፣ አሁን “በቁም” ያሉት ሚኒስትር አንድም ቦታ ወይ ስማቸው ወይ ፎቶዋቸው ወይ “ራአያቸው” ሳይነሳ ዓመቱ ሲከበር፣ አሁንም እኔ ምለው የማን ሙት ዓመት ነው “አያከበርን” ያለነው? ማን ነው አንደሙት ስሙ የተርሳው? ማንንስ ነው አንደ ሕያው በየቀኑ የሚወሳው? ኧረ ለመሆኑ በየትኛው አገር ነው ያለው ተረስቶ የሞተው የሚነሳው? ህወሓት በሚመራው።
ሰላሙ ነኝ ቸር ያሰማን!

የአባይ ቦንድ ሽያጭ በጉተምበርግ ከሸፈ፤ ድብድብ ተነሳ (Video)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የኢሕአዴግ በየሃገሩ እየጠራው የነበረው የአባይ ቦንድ ሽያጭ በመክሸፍ ላይ ይገኛል። በየከተማው ስብሰባው እየተበጠበጠ በመበተን ላይም ነው። ባለፈው ሳምንት በሚኒሶታ የአባይ ቦንድ ሽያጭ ሳይጀመር የተበተነ ሲሆን በዚህ ሳምንት ደግሞ በጉተምበርግ ኢትዮጵያውያን የአባይን ቦንድ ሽያጭ አክሽፈዋል። የቦንድ ሽያጩ በተጠራበት አዳራሽ በመግባት በተነሳው ተቃውሞ ድብድብ ተነስቶ የነበረ ሲሆን ሕዝቡ ወንበሮችን አንስቶ ወርውሯል። ሕዝቡ ስብሰባውን ከተቆጣጠረውና የኢሕ አዴግ ተወካዮችን ከአዳራሹ ካባረረ በኋላ “ኢትዮጵያ ሀገራችን…” እያለ ሲዘምር ይታያል። ቪድዮውን ይመልከቱ።

የፌደራል ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ደበደበ፣ ተቃውሞ ሰልፉን አደናቀፈ

$
0
0

ከርእየ- ሁለንተና ከአዲስ አበባ
semayawi partyዛሬ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ. ም ሠማያዊ ፓርቲ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ገዥው ፓርቲ ለማደናቀፍ ከፍተኛ ውዥንብር፣ ድብደባና ሁከት ፈፀመ፡፡ ከ3 ወር በፊት ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ. ም ባደረገው የተቃውሞ ሰልፍ፡- ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የሀይማኖት ተወካዮች፣ በግፍ የታሰሩ ዜጎች ባስቸኳይ እንዲፈቱ በስብሰባው ያሳወቀ ሲሆን ምላሽ ባለማግኘቱ ነው ሰልፍ የጠራው፡፡
ይሁንና ገዥው ፓርቲ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሚል መልምሎ ባስቀመጣቸው ካድሬዎቹ አማካኝነት የተቃውሞውን ስብሰባ ያደናቀፈ ሲሆን በ25/12/05 ዓ. ም ምሽት ወታደሮቹን ልኮ በቢሮው ውስጥ የነበሩትን አመራሮችና ደጋፊዎችን ደብድቧል፡፡ አቶ ማርቆስን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ክፉኛ ተደብደበው በ5 እስር ቤቶች ከፋፍሎ ካሰረ በኋላ ከምሽቱ 5፡00 ፈቷቸዋል፡፡ ኢንጅነር ይልቃልም ታስረው ተፈተዋል፡፡ ዛሬ ጠዋት 12፡ 00 ጀምሮ በጽ/ ቤቱ ከፍተኛ ቅስቀሳ የነበረ ሲሆን ወታደሮች በህገ ወጥ ገብተው በማስቆም ፖስተሮችን በመቅደድ፣ ጀኔሬተሮችን በመቀማት፣ ከፅ/ ቤታቸው እንዲወጡ አድርገዋል፡፡
በአንጻሩ በሀይማኖት ተቋማት ስም የጠራው ስብሰባ፡- እድሮች፣ የቀበሌ ነዋሪዎች፣ የቀጠና ካድሬዎች፣ በአነስተኛና ጥቃቅን ያደራጃቸው፣….በሎንችና፣ በአዜብ ቀንዶ፣ በአሮጌ አውቶቡሶች በመጓጓዝ መስቀል አደባባይ ከተገኙ በኋላ ያለምንም ተልእኮ ተበትነዋል፡፡ አብዛኞቹ በእግራቸው ተመልሰዋል፡፡ አላማው የሰማያዊ ፓርቲን የተቃውሞ ሰልፍ ማደናቀፍ ብቻ ነበር፡፡
ይህ የገዥው ፓርቲ ግፍ በዜግች ላይ ከፍተኛ ቁጣና እምቅ እልህ አንደሚፈጥር ታውቋል፡፡


በዛሬው ሰልፍ ላይ ከወጡት መካከል ከ200 በላይ ሙስሊሞች ታሰሩ

$
0
0

Muslim Etiopia 1

Muslim Etiopia 2

Muslim Etiopia 3

Muslim Etiopia 4

Muslim Etiopia 5(ዘ-ሐበሻ) ኢሕአዴግ በሃይማኖቶች ጉባኤ ስም ሽብርተኝነትንና አክራሪነትን ለመቃወም የጠራው ሰልፍ ላይ ፖሊስ ሙስሊሙን ብቻ እየመረጠ ማሰሩን ድምፃችን ይሰማ በፎቶ ግራፍ ጭምር ባወጣው መረጃ አስታወቀ። “ኢሕአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ እንዲገኝ በየወረዳው አውቶቡስ የተዘጋጁ መሆኑ ሲታወቅ አውቶብሶችን ደልድለው ሰውን ያስገቡት የወረዳ ሀላፊዎች ናቸው፡፡ የአውቶብሶቹ ወጪዎች የተሸፈነውና ስምሪት የተደረገው በመንግስት ሲሆን የሰልፉ አዘጋጅ የተባለው የአዲስ አበባ የሃይማኖቶች ጉባኤ የሚባል “አሻንጉሊት” እንዳልታየ ድምጻችን ይሰማ ገልጿል። ኢሕአዴግ በዛሬው ሰልፍ 1 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ወጣልኝ ቢልም አብዛኛው ሰልፈኛ ከድምጻችን ይሰማ የመጡ ናቸው።

በተለይ በመጨረሻው ሰዓት ላይ ድምጻችን ይሰማ ኢሕአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ ተገኝቼ “እኔም አክራሪነትን እንደምቃወም እገልጻለሁ” ባለው መሠረት በርከት ያሉ ሙስሊሞች ወደ መስቀል አደባባይ የተመሙ ቢሆንም ከመንገድ ላይ ፌደራል ፖሊሶች በመቆም ሙስሊሞቹን እየመረጡ ወደ ሰልፍ እንዳይሄዱ ሲያደርጉ እንደእዋሉ የአይን እማኞች ገልጸዋል። ከፖሊስ ተርፈው በመስቀል አደባባይ የተገኙት ሙስሞች ደግሞ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ እጃቸውን ወደ ጆሯቸው ባስጠጉ ቁጥር የደህንነትና የፖሊስ አካላት ለምን እጃችሁን አስጠጋችሁ እያሉ ውክቢያ ሲፈጽሙ ነበርና “ለምን ወደዚህ ሰልፍ መጣችሁ?፡ በሚል ሲያዋክቧቸው እንደዋሉ ተዘግቧል። ፖሊሶቹ ስም እየጠየቁ የሙስሊም ስም ያለውን ይመልሱ እንደነበርም ከተገኙት መረጃዎች ለማቀቅ ተችሏል።

በመስቀል አደባባይ ከተገኙት ሙስሊሞች ውስጥ ቁጥራቸው ወደ ከ200 ባልይ የሚሆኑትን ፖሊስ ይዞ ያሰረ ሲሆን ሰልፉ እስኪጠናቀቅ ድረስ በኢግዚብሽን ማዕክል አስሯቸው ከቆየ በኋላ በአውቶቡስ ወዳልታወቅ ሥፍራ እንደወሰዳቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገችው ሙከራ እስካሁን እነዚህ ሙስሊሞች ያሉበት ያልታወቀ ሲሆን ምናልባትም “ሽብር እና ሁከት ለመፍጠር” በሚል መንግስት አንድ ድራማ በመሥራት ክስ ሊመሰርትባቸው እንደሚችል ታዛቢዎች ይናገራሉ።

ዛሬ ኢሕአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ በመገኘት “የትኛውንም አይነት አክራሪነት እንደማንቀበልና እንደምናወግዝ ዛሬ በድጋሚ በተግባር አሳይተናል” ብሏል ድምጻችን ይሰማ ከሰልፉ መጠናቀቅ በኋላ።

በሌላ በኩል ከሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ራድዮ ፋና የዛሬውን ሰልፍ በማስመልከት ያቀረበው ዘገባን ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ በሚል እዚህ አምጥተነዋል።

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አክራሪነትንና ሽብርተኝነትን በመቃወም አደባባይ ወጡ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 26 ፣ 2005 (ኤፍ. ቢ. ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በአስሩም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች አክራሪነትና አሸባሪነትን በመቃወም ዛሬ በመስቀል አደባባይ ሰለማዊ ሰልፍ አካሄዱ።

ሰለማዊ ሰልፉን የጠራው የአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖትች ጉባኤ ጽህፈት ቤት ሲሆን ፥ ለዛሬ ማለዳ በተጠራው ሰለፍ ላይ ቁጥሩ ከአንድ ሚለየን የሚልቅ ሕዝብ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተሳተፏል።

የማለዳው ዝናብና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ሳይበግረው ከአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም አቅጣጫዎች በመትመም መስቀል አደባባይ የተገኙ ነዋሪዎች “ ሕገ መንግስታችን በአክራሪዎችና ደጋፊዎቻቸው አይናድም ” ፣ “ አክራሪነት ቻው ቻው ” ፣ “በኪራይ ሰብሳቢዎች ስር የተጠለሉ አክራሪዎችን አንሻም” ፣ “የምንፈልገው ሰላምና ሰለም ብቻ ነው ” ፣ “ መንግስት በአክራሪዎችና አሸባሪዎች ላይ አስፈላጊውን እርርምጃ ይውሰድልን ” ፣ ” የፀረ ሽብርተኝነት ህጉን እንደግፋለን ” የሚሉና ሌሎች በርከት ያሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

ከአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖትች ጉባኤ ጽህፈት ቤት የተወከሉ የክርስትናና የእስልምና ሃይማኖቶች አመራሮች ለሰልፈኞቹ ባሰሙት ንግግር ነዋሪዎቹ የጽህፈት ቤቱን ጥሪ አክብረው በመገኘታቸው አመስግነው ሰልፉ ኢትዮጵያ የምትታወቅበት መቻቻል አንድናትና እኩልነት በድጋሚ የተረጋገጠበት መሆኑን አመልክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ዲሪባ ኩማም ባሰሙት ንግግር መንግስት የነዋሪዎችን ጥያቄ በማክበር በአሸባሪዎችና አክራሪዎች ላይ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሰላማዊ ሰልፉ ተሳፊዎች በሰልፉ ጠሪዎችና በክብር እንግዶች የተላለፉ መልዕክቶች ከሰሙ በኋላ የኢትዮጵያን ህዝብ መዝሙር በመዘመር ወደየመጡበት ተመልሰዋል።

ዴሞክራሲ በተግባር: ‘ሰላማዊ ሰልፍ መከልከል!’

$
0
0

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

ዛሬ እሁድ ነሓሴ 26, 2005 ዓም ሰማያዊ ፓርቲ (ና ሌሎች ድርጅቶች) በአዲስ አበባ ከተማ ሰለማዊ ሰልፍ መጥራቱ ሰምተን ነበር። በሕገ መንግስታችን መሰረት ዜጎች ወይ ድርጅቶች ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲፈልጉ የአከባቢው አስተዳደር ማሳወቅ (ከተቻለም ማስፈቀድ) ይጠበቅባቸዋል። ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ ግን ሕገመንግስታዊ መብታቸው ነው።

የሰማያዊ ፓርቲ የሰልፍ ጥሪ ተከትሎ መንግስት በሀይማኖታዊ ጉዳዮች ዙርያ በተመሳሳይ ቀን የሆነ ሰልፍ ነገር ዘመቻ መጥራቱ ተሰማ። በ አንድ ከተማ በተመሳሳይ ቀን ሁለት ተቃራኒ ሰልፎች ስለመካሄዳቸው ስናብሰለስል መንግስት ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ለማድረግ እንደማይፈቀድለትና ካደረገ እርምጃ ሊወሰድበት እንደሚችል ትናንት ከወጣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ መረዳት ይቻላል።

ሰለማዊ ሰልፍ (የተለየ ሁኔታ ካላጋጠመ በቀር) በመንግስት አዋጅ ወይ በተቋሞች መግለጫ ሊከለከል አይችልም፤ ምክንያቱም የዜጎች መብት መሆኑ በሕገ መንግስቱ ተቀምጧል። ሕገመንግስት ደግሞ የሁሉም ሕጎች የበላይ ነው።

መንግስት የተቃዋሚ ሰልፉ ከለከለው (ቢያንስ በፖሊስ መግለጫ)። ራሱ መንግስት የጠራው ሰልፍ ግን ይካሄዳል ማለት ነው። ‘እኔ ስልጣኑ ስላለኝ ሰልፍ መጥራት እችላለሁ፤ እናንተ ዜጎች ግን አትችሉም ‘ እያለን ነው። ዴሞክራሲ በተግባር እንዲህ ነው። የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀፅ 30፣ “ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፤ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና፤ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡” ብሎ ይደነግጋል።

blue party……………..

መንግስት ፍቃድ መከልከሉ የሀገራችን ሕገመንግስት የጣሰ ነው። መንግስት የራሱን ሕገመንግስት በራሱ ከጣሰ ዜጎች መንግስት የጣሰውን ሕገመንግስት እንዲያከብሩ እንዴት ማስገደድ ይቻለዋል? ዜጎች ብቻ ሕገመንግስቱ ቢያከብሩ እንዴት ዉጤት ማምጣት ይቻላል? በዴሞክራሲያዊ ሀገር ሕገመንግስት የበላይ ሕግ ነው፤ በመንግስትም በዜጎችም መከበር አለበት። ሕገመንግስቱን በመጣስ ኢህኣዴግ የሚመራው የኢትዮዽያ መንግስት ከሕግ በላይ እየሆነ ነው። መንግስት ሕግን በሚጥስበት ሀገር ዴሞክራሲ አለ ማለት አይቻልም። ዴሞክራሲ ከሌለ የኢትዮዽያ መንግስት ‘አምባገነን ነው’ ብንል እንዴት ስሕተት ሊሆን ይችላል?

መንግስት አምባገነን ከሆነ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚገነቡበት አጋጣሚ ለመፍጠር ብንቀሰቅስ ኃጥያት ይሆናል? መሪዎቻችን ለስልጣን ሲታገሉ ለዴሞክራሲ ግንባታ ብንታገል መልካም አይደለምን? ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ ህዝቦች ሓሳባቸውንና ያላቸው ቅሬታ (በመንግስት ይሁን በሌላ) የሚገልፁበት መድረክ እስከሆነ ድረስ የዴሞክራሲያዊ አሰራር መገለጫ ይሆናል ማለት ነው።

ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ የዴሞክራሲ መገለጫ ከሆነ ታድያ ለምን ሰለማዊ ሰልፍ እንፈራለን? ሰለማዊ ሰልፍ ባለመፍቀድ የህዝብን ብሶት ያቃልላል ያለው ማነው? ህዝብን ማፈን የህዝብን ቅሬታ እንዲጨምር እንደሚያደርግና ህዝቡ ሌላ አማራጭ (ሰለማዊ ያልሆነ መንገድ) ተጠቅሞ ፀረ መንግስት ሊነሳ እንደሚችል ኢህኣዴጎች ከደርግ አገዛዝ ትምህርት አለመቅሰማቸው ግርም ይለኛል። ሰለማዊ መንገድ መዝጋት የሃይል ወይ የዓመፅ መንገድ መክፈት ማለት ነው።

(ኢሕአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ የተገኘ አንድ ሙስሊም በፖሊስ ተይዞ ሲዋከብ)

(ኢሕአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ የተገኘ አንድ ሙስሊም በፖሊስ ተይዞ ሲዋከብ)

እኛ የምንፈልገው ግን የዓመፅ መንገድ ሳይሆን ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ነው። ኢትዮዽያ በሃይል ስልጣን የመያዝ የብዙ ዓመት ልምድ አላት። እስካሁን ድረስ የኢትዮዽያ ገዢዎች ስልጣን የያዙት በሃይል ነው። ባለስልጣናቱ (ሰዎቹ) ይቀያየሩ እንደሆኑ እንጂ ፖለቲካዊ አገዛዛቸው ተመሳሳይ ነው፤ ስልታቸው ጭቆና ነው። የሚገለገሉበት ስልጣን ከህዝብ ተውሰው የያዙት ሳይሆን በጠመንጃ አፈሙዝ የነጠቁት ነው፤ ለዚህም ነው ለስልጣናቸው እንጂ ለህዝብ ነፃነት ግድ የሌላቸው።

ሰለማዊ ሰልፍ የምንፈራበት አንድ ምክንያት ሊኖር ይችላል። ይሄም ‘ሰለማዊ ሰልፉ’ እንደስሙ ‘ሰለማዊ’ ላይሆን ይችላል። መፍትሔው ግን ቀላል ነው። በሕገ መንግስቱ የተቀመጠ ‘ሰለማዊ ሰልፍ’ ነው። ሰዎቹም የጠሩት ‘ሰለማዊ ሰልፍ’ ነው። ፍቃድ የተጠየቀው ‘ለሰለማዊ ሰልፍ’ ነው። መንግስት ይሄንን ፍቃድ መስጠት ነበረበት። ሰልፉ ሰለማዊ መሆኑ ቀርቶ የዓመፅ መንፍስ ከታየበት ‘ሕገ ውጥ ሰልፍ’ እየሆነ ነው ማለት ነው። በዚህ ግዜ መንግስት ‘ሕገመንግስቱን ለማስከበር’ ጣልቃ ሊገባ ይችላል። ‘ሕገ ወጥ ድርጊት’ የፈፀመ አካል ካለ ወደ ሕግ ቀርቦ በሕግ ይፈረዳል። (የሕግ የበላይነት ይከበራል)።

ገና ለገና ‘ዓመፅ ሊቀሰቅሱ ይችላሉ’ በሚል ስጋት (ይህን ያልኩበት ምክንያት መንግስት ዓመፅ ፈርቶ ካልሆነ በቀር ሰለማዊ ሰልፍ የማይፈቅድበት አሳማኝ ምክንያት ስላልመጣልኝ ነው) ሰለማዊ ሰልፍ መከልከል የዜጎች መብት መጣስ ስለሆነ አግባብነት የለውም። ባጭሩ መንግስት በሕገወጥ ተግባር ተሰማርተዋል ማለት ነው።

ሰለማዊ ሰልፍ መጥራት የመብት ጥያቄ እንጂ የአቋም ጉዳይ አይደለም።

ዓፈና ዓመፅን ይወልዳል።

War criminal or hero: The legacy of Ethiopia’s late dictator Meles Zenawi

$
0
0

War criminal or hero: The legacy of Ethiopia's late dictator Meles Zenawi

አውስትራልያዊው ‹የቋራ ሰው›

$
0
0
የኢትዮጵያን ነጻነት ስናስብ ልንዘክራቸው የሚገቡ፣ ለሀገሪቱ ደማቸውን ያፈሰሱ፣ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የታገሉ፤ ለነጻነቷ ሲሉ ከገዛ መንግሥታቸው ጋር የተሟገቱ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን የከሰከሱ አያሌ የሌላ ሀገር ሰዎች አሉ፡፡ በተለይ ዛሬ ኢትዮጵያዊነት ቆሻሻ እንደ ነካው ልብስ በሚገፋበት ጊዜ ለኢትዮጵያዊነታችን ዋጋ የከፈሉትን ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ሰዎች ማስታወስ ግድ ይለናል፡፡
እዚህ አውስትራልያ መጥቼ ካገኘኋቸው መጻሕፍት አንዱ ‹ተልዕኮ 101 - Mission 101› የተባለ ዱንካን ማክናብ(Duncan Mcnab) በተባለ ሰው የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ ማክናብ መርማሪ(detective) ፖሊስ፣ የግል የምርመራ ሥራ (Investigator) ባለሞያ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ የነበረ አውስትራልያዊ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በእንግሊዝ ወታደራዊ ተልዕኮ ውስጥ በመሰለፍ ለኢትዮጵያ ነጻነት የታገሉ አራት አውስትራልያውያን ወታደሮች ታሪክ ቀርቧል፡፡ ከአራቱ አንዱ የዱንካን ማክናብ አጎት ነበረ፡፡

በዚህ መጽሐፍ ላይ ከአራቱ ወታደሮች ጋር ታሪኩ ተያይዞ የቀረበ አንድ ሌላ ሰው አለ፡፡ ይህ ሰው የተወለደው እኤአ ኖቬምበር 25 ቀን 1877 ዓም በደቡብ ብሪዝበን(አውስትራልያ) ነው፡፡ አያት ቅድመ አያቶቹ ትንግርታዊ ጉዞ የሚወዱ(adventurers) ነበሩ፡፡ አያቱ ከእንግሊዟ ዌልስ በ1800ዎቹ ነበር ወደ አውስትራልያ የገባው፡፡ በምሥራቅ አውስትራልያ ከ117ሺ ሄክታር በላይ መሬት የነበረው ሀብታም አሳራሽ ነበረ፡፡ በኋላ ግን ወደ እንግሊዝ ተመልሶ በሄርፎርድ ሻየር ኑሮውን ቀጠለ፡፡ ልጁን አርኖልድንም በአዳሪ ትምህርት ቤት አስተማረው፡፡
በ1896 አርኖልድ እንግሊዝን ተወና ወደ አውስትራልያ መጥቶ በቤተሰቡ እርሻ ላይ መሥራት ጀመረ፡፡ በከተማ በሚገኘው ዘመናዊ ቤት ከመኖር ይልቅ በገጠር በነበረው የገበሬዎች ቤት ውስጥ በመኖርና አኗኗሩን ሁሉ እንደ ገበሬዎቹ በማድረግ የተለየ ሕይወት የመኖርን ዘይቤ እንደ አያቶቹ ተካነበት፡፡ ‹ቋረኛው› አርኖልድ ዊንሆልት እንግዲህ የዚህ ሰው ልጅ ነበር፡፡
ዊንሆልት ሲፈጥረው የትግል ሰው ነው፡፡ መከራ ባለበት ቦታ ገብቶ መታገል የሚወድ፡፡ በ1899 እኤአ በደቡብ አፍሪካ የቦር ጦርነት ሲፈነዳ የቤተሰቡን ሀብት ትቶ እንዲያውም ለፈረስ መግዣ እንዲሆነው የተወሰነውን ሽጦ በኩይንስ ላንድ ጦር ወስጥ በመመዝገብ በ1900 ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄደና ለለስምንት ዓመት በውጊያ ላይ ቆየ፡፡ ጦርነቱ ሲፈጸምም ወደ አውስትራልያ ተመልሶ የቤተሰቡን ሀብት ማስተዳደር ጀመረ፡፡ ከሀብቱ ጎን ለጎን በኩዊንስ ላንድ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ለግዛቲቱ ሕግ አውጭ ምክር ቤት በ1909 ተመርጦ ነበር፡፡ ከዚያም በኋላ በ1913 እኤአ ወደ አፍሪካ ተመልሶ በደቡብና በደቡብ ምእራብ አፍሪካ ውጊያዎች ላይ በፈቃደኛነት ተሳትፏል፡፡ እንዲያውም በናሚቢያ በረሃ እያለ በአንበሳ እስከ መነከስ ደርሶ ነበር፡፡
በዚህ መካከል በ1928 ዓም ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን ወረረ፡፡ ዊንሆልት ይህ ነገር በጣም ነበር ያሳሰበው፡፡ በአንድ በኩል የኢትዮጵያ መወረር፤ በሌላ በኩል ሞሶሎኒ በአፍሪካ ለነበሩ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች አደጋ መሆኑ ልቡን ገዝቶታል፡፡ ጦርነቱን በቅርብ ለመረዳት እንዲችል የብሪዝበኑ ኮርየር ሜይል ጋዜጣ የጦርነት ሪፖርተር አድርጎ ወደ ምሥራቅ አፍሪካ እንዲልከው አደረገ፡፡ በኖቬምበር 22 ቀን 1935 እኤአ ከአውስትራልያ ወደ አፍሪካ በመርከብ አመራ፡፡ በኤደን በኩል አድርጎ ጅቡቲ፣ በጅቡቲ በኩልም በባቡር ተሣፍሮ አዲስ አበባ ገባ፡፡ ኢምፔሪያል ሆቴልም ዐረፈ፡፡
አርኖልድ ዊንሆልት
ዊንሆልት በኢትዮጵያ አርበኞች የአልበገር ባይነት ውጊያ መንፈሱ ተማርኮ ነበር፡፡ እርሱ በደቡብ አፍሪካ፣ በናሚቢያና በአንጎላ የተዋጋው የደፈጣ ውጊያ ስልት በኢትዮጵያ አርበኞች ሲተገበር ማየቱ እንዲቀላቀላቸው ይገፋፋው ነበር፡፡ ዊንሆልት ስለ ደፈጣ ውጊያ አንብቧል፣ ሠልጥኗል፤ በተግባርም ሠርቶበታል፡፡ የደፈጣ ውጊያም ይማርከዋል፡፡ ይህንን የአርበኞች ውጊያ ለመረዳትና ለመዘገብ ግን አልቻለም፡፡ ጣልያኖች ጋዜጠኞች ከአዲስ አበባ እንዲወጡ አይፈቅዱም ነበር፡፡
ዊንሆልት ይህ ነገር መንፈሱን አላረካው ሲል የቀይ መስቀል ሾፌር ሆኖ በመቀጠር ወደ ገጠሮች ለመሄድ ወሰነ፡፡ በ1936 እኤአ የፈለገውን ሥራ አገኘው፡፡ በዚህ ሥራው አማካኝነት በአዲስ አበባ ለነበረው የእንግሊዝ ሌጋሲዮን መረጃ ከማቀበሉም በላይ ጦርነቱን በቅርብ ለመረዳትም ቻለ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ጦርነቱ ዜና መሆኑ አበቃ፡፡ ዊን ሆልትም ወደ አውስትራልያ ተመለሰ፡፡
ዊንሆልት በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ጠባይ ባይደሰትም የኢጣልያ ወረራ ግን ትክክል አልነበረም ብሎ ያስብ ነበር፡፡ በወቅቱ የነበሩት ኃያላን ሀገሮች ለኢትዮጵያ ጥያቄ ተገቢ መልስ አለመስጠታቸውም አሳዝኖታል፡፡ ይህንን ስሜቱን ኮርየር ሜይል ለተሰኘው ጋዜጣ እየጻፈ ቢልክም ዋና አዘጋጁ ግን ለማተም ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ዊንሆልት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሞሶሎኒንና የእንግሊዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ቻምበርላይንን ያወግዝ ነበር፡፡ ጋዜጦች የነፈጉትን ዕድል የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት ይወጣ ነበር፡፡ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ ይናገራል፡፡
በ1937 እኤአ ዊንሆልት አውስትራልያን ለቅቆ እንደገና ወደ የመን አመራ፡፡ በየመን ዋና ከተማ ኤደን ያገኛቸውን የእንግሊዝ ታላላቅ ወታደራዊ ባለ ሥልጣናትንም ኢትዮጵያን ለማገዝ እንግሊዝ ጦር ማዝመት እንዳለባት መወትወት ጀመረ፡፡ በተለይም የአርበኞችን የደፈጣ ውጊያ በመጠቀም ጣልያንን ሰላም መንሣትና በመጨረሻም ማስወጣት አለብን የሚለውን ሃሳቡን በተደጋጋሚ ለማሳመን ይጥር ነበር፡፡ የየመን ቆይታው አልሳካ ሲለውም ወደ ለንደን አምርቶ ከእንግሊዝ የዲፕሎማሲና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ጋር በሃሳቡ ተነጋገረ፡፡ ማንም ግን ትኩረት ሊሰጠው አልወደደም፡፡ ዊንሆልት በዚያ እያለ ታዋቂዋ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሲልቭያ ፓንክረስት ለምታሳትመው New Times – Ethiopian News ዋና የጽሑፍ አበርካች ሆኖ ነበር፡፡
 በተለይም በአፕሪል 16 ቀን 1938 እንግሊዝና ጣልያን ‹የአንግሎ ጣልያን› ስምምነትን ሲፈራረሙ ዊንሆልት በጣም አዘነ፡፡ ለንደንንም ለቅቆ ወደ የመን ተመለሰ፡፡ ከየመንም አገሩ አውስትራልያ ገባ፡፡ በየሄደበት ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ መናገርና መቀስቀስም ዋና ተግባሩ ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ ጉዳይም የመተዳደርያ ሥራውን እስከ ማስረሳት አደረሰው፡፡
በዚህ መካከል እንግሊዝና ጀርመን እየተቃቃሩና ወደ ጦርነት እያመሩ ሄዱ፡፡ የአውስትራልያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ሜንዝየስም በጀርመን ላይ ጦርነት ዐወጀ፡፡ ዊንሆልት ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ ወሰደው፡፡ ፊቱንም ወደ አፍሪካ ለመመለስ እንዲችል አበቃው፡፡ ሴፕቴምበር 27 ቀን በ1935 እኤአ በ62 ዓመቱ ከአውስትራልያ ለቅቆ ወደ ሲንጋፖር፣ ከዚያም ወደ ኤደን አመራ፡፡ በዚያም አንድ አፓርትመንት ተከራይቶ ዐረብኛና አማርኛ የሚችል ተርጓሚ ቀጠረ፡፡ ለሲልቭያ ፓንክረስት የሚልከውን ጽሑፍ ሳያቋርጥ ያገኛቸውን አካላት ሁሉ የኢትዮጵያ አርበኞችን ስለመርዳትና በእነርሱም አማካኝነት ጣልያንን ድል ስለማድረግ ያማክር ነበር፡፡
ይህ ጥረቱ ውጤት በማምጣቱ የተነሣም በሜይ 1940 ሃሳቡን ተግባራዊ ለማደረግ የሚያስችል ደብዳቤ ከእንግሊዝ ወታደራዊ ባለ ሥልጣናት ደረሰው፡፡ ዊንሆልትም እየፈነደቀ በ62 ዓመት እድሜው እንደገና ወደ ውትድርና ተመለሰ፡፡ በጁን 17 ቀን 1940 እኤአ ከየመን ወደ ሱዳን ካርቱም በረረ፡፡
ምንም እንኳን ለንደን ለሚገኙት ለቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ የተገለጠ ነገር ባይኖርም እንግሊዞች ግን እያሠጋቸው የመጣውን የጣልያኖችን ኃይል ከምሥራቅ አፍሪካ ለማስወጣት ምሥጢራዊ ዕቅድ በማዘጋጀት ላይ ነበሩ፡፡ ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያን አርበኞች በማገዝ ጣልያኖችን ሰላም መንሣትና በመጨረሻም እንዲወጡ ማደረግ በብዙዎቹ ባለሞያዎቻቸው የታመነበት ዕቅድ ሆነ፡፡ ይህ ዕቅድ ዊንሆልት በተደጋጋሚ ሲወተውተው የነበረ ዕቅድ ነበረ፡፡ እንግሊዞች ይህንን ዕቅድ የተሳካ ለማድረግ በሕንድና በመካከለኛው ምሥራቅ ያገለገለውን በተለይም ደግሞ በምድረ ፍልስጤም እሥራኤልን በመርዳት የተሳከለት ሥራ የሠራውን፣ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላም ወደ ኢትዮጵያ ክርስቲን ከምትባለው ባለቤቱ ጋር መጥቶ ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን ኑሮ የጀመረውን ዳን ሳንፎርድን ነበር የመረጡት፡፡ ሳንፎርድ ስለ ኢትዮጵያ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ ይቆረቆር የነበረ፤ ከብዙዎቹ የዘመኑ መሳፍንትና መኳንንት ጋርም መልካም ግንኙነት የነበረው፤ በንጉሠ ነገሥቱ ዘንድም መታወቅንና መከበርን ያተረፈ ሰው ነበር፡፡
ሳንፎርድና(ግራ) ዐፄ ኃይለ ሥላሴ በደምበጫ ግንባር(ጎጃም)
ዳን ሳንፎርድ አዲስ አበባን ለቅቆ ወደ እንግሊዝ የተመለሰው ጣልያኖች ኢትዮጵያን ሲወርሩ ነበር፡፡ አሁን ከጡረታ ተጠርቶ የዚህ የኢትዮጵያ ተልዕኮ መሐንዲስ እንዲሆን ተደረገ፡፡ መጀመሪያ ወደ ካይሮ ከዚያም ወደ ካርቱም በመምጣት ከሌሎች የውትድርና ባለሞያዎች ጋር ዕቅዱን ነደፈ፡፡ ዊንሆልት ካርቱም የደረሰው በዚህ ጊዜ ነበር፡፡ ዳን ሳንፎርድ በጎጃም በኩል ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ከአርበኞች ጋር ሆኖ ጣልያንን ለመውጋት ሲያስብ በደቡብ አፍሪካው የደፈጣ ውጊያ ጊዜ አንድ እጁ ጉዳት የደረሰበት ዊንሆልት እዚያው ሆኖ እርሱም ከአርበኞች ጋር ተቀላቅሎ የደፈጣ ውጊያ ለመቀጠል እየተሟሟቀ ነበር፡፡
ሳን ፎርድ በገለባት በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለመዝለቅ የነበረው ዕቅድ ጣልያኖች ገለባትን በመያዛቸው ምክንያት ከመተማ 19 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው ሌሞና ተዛወረ፡፡ ጣልያኖችና ባንዳዎች ከቋራ እስከ መተማ ያለውን ቦታ መሽገውበት ነበር፡፡ ከእንግሊዝ የምሥራቅ አፍሪካ እዝ የመጨረሻውን መመሪያ ሲጠባበቅ የነበረው ኮሎኔል ሳንፎርድ በኦገስት 6 ቀን ዶቃ ከሚገኘው ካምፕ 54 በቅሎ፣ 36 አህዮች፣ ስድስት ገመድ አልባ መገናኛዎች፣ 13303 ጠመንጃዎች፣ 3 ሪቮልቨሮች፣ 30 አሮጌ ጠመንጃዎች፣ ከአራት የእንግሊዝ ወታደሮች፣ ከአንድ ሐኪምና ከአንድ የራዲዮ ሠራተኛ ጋር ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ተነቃነቀ፡፡ ሳንፎርድ ዊንሆልትን በዶቃ ካምፕ ትቶት ነበር የመጣው፡፡
በአንድ በኩል ይህ የተደረገው እነ ሳን ፎርድ መንገዱን ከጠረጉ በኋላ ዊንሆልት እንዲከተላቸው በማሰብ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ያን ጊዜ ዊንሆልት ገና የመጓጓዣ አጋሰሶችን አላዘጋጀም ነበርና፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዊንሆልት በዶቃ ካምፕ መገኘት ከሌላኛው መኮንን ከሮኒ ክሊችሌይ ጋር አለመጣጣም አስከትሎ ነበር፡፡ የመረጃ ሰው የሆነው ክሊችሌይ ዊንሆልት አርጅቷል ብሎ አስቧል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ለመዝለቅ ያለውን ጉጉትና ከሲልቭያ ፓንክረስት ጋር ስለሠራው ሥራ ደጋግሞ ማውራቱን አልወደደውም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እርሱ ራሱ በዚያ ጊዜ ጥቂት በእድሜ ገፍቶ የነበረው ሳን ፎርድ ዊንሆልትን ‹አርጅቷል› ብሎ በማሰብ በተልዕኮው ውስጥ ማካተት አልፈለገም ነበር፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ዊንሆልት አንድ እጁ በሚገባ አይሠራም፡፡
ዊንሆልት ግን ሁሉንም ትቶ 11 አህዮችን፣ ስድስት የታጠቁ የኢትዮጵያ ወታደሮችንና አንድ ሱዳናዊ  ምግብ አብሳይ አዘጋጀ፡፡ በ1940 እኤአ፣ ኦገስት 31 ቀን ሳን ፎርድ የሄደበትን መንገድ በመተው ዊንሆት ከመተማ በስተደቡብ ወደ ቋራ አቅጣጫ የሱዳንን ድንበር ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ጀመረ፡፡ በመንገድ ላይ የተወሰኑትን ኢትዮጵያውያን ወታደሮችና ሱዳናዊውን አብሳይ ቀነሳቸው፡፡ ሁለት አገልጋዮችንና ሦስት አህዮችን ብቻ በመያዝ ጠመንጃውን እንደ አገሬው ሰዎች በትከሻው ወደ ታች አጋድሞ ጉዞ ቀጠለ፡፡ ከመነሣቱ በፊት ሊሄድ ያሰበበት መንገድ ለጣልያን ያደሩ ባንዳዎች የሚገኙበት አደገኛ መንገድ መሆኑን ተነግሮት ነበር፡፡ እርሱ ግን አልተቀበለውም፡፡ እንዲያውም መጣቢያ በምትባል ጣቢያ 50 የጣልያን ወታደሮችና 300 የአካባቢው ተወላጅ ባንዶች ካምፕ መሥርተው አካባቢውን እየቃኙ ነበር፡፡
ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ
ዊንሆልት ኦገስት 31 ከሌሎቹ የእንግሊዝ መኮንኖች ተለያይቶ በቋራ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ከዘለቀ በኋላ ድምፁ ጠፋ፡፡ ሳንፎርድም ዊንሆልት ወደ እርሱ ዘንድ አለመድረሱን ገለጠ፡፡ በገለባትና በካርቱም የሚገኙ የእንግሊዝ ሚሲዮኖች ዊንሆልት የት እንደገባ ለማወቅ አልቻሉም፡፡ የዊንሆልት ዜና ከተሰማ 15 ቀናት አለፉ፡፡ ሴፕቴምበር 15 ቀን 1940 ከዊንሆልት ጋር አብረው ሄደው የነበሩ ሁለት ሰዎች  በዶቃ ካምፕ ተገኙ፡፡ በካምፑ የነበሩት ቴሲገርና ላውሬ የተባሉ ሁለት የእንግሊዝ መኮንኖች የዊንሆልትን ዜና ጠየቋቸው፡፡ ኢሳ አቡ ጂያር እንደተናገረው ከሆነ ይመራቸው የነበረው ሰው የጉሙዝን አካባቢ እያቋረጡ እያሉ ጠፋባቸው፡፡ በዚህም ምክያት በመጣቢያ አካባቢ ካምፕ ሠርተው ተቀመጡ፡፡ በዚህ መካከልም አንድ ቀን በድንገት ከአራቱም አቅጣጫ ተኩስ ተከፈተባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ዊንሆልት ጠመንጃውን ለአስተርጓሚው አሸክሞት ነበር፡፡
ሁለቱ አገልጋዮቹ ተኩሱን ሲሰሙ እየሮጡ በየአቅጣጫው ጠፉ፡፡ መሣሪያ ያልያዘው ዊንሆልት ብቻውን ቀረ፡፡ ከዚህ በኋላ ያለውን ኢሳ አቡ ጂያር የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ እርሱ አምልጦ ወደ ዶቃ ገብቷል፡፡ ሁለቱ የእንግሊዝ መኮንኖች ይህንን ሪፖርት ሲያስተላልፉ ሌላ ዘገባ ከገለባት መጣላቸው፡፡ ‹‹ሌፍትናንት ዊንሆልት በብዙ ችግር ወደ ሰራቆ ደርሷል፡፡ ፊታውራሪ ወርቁ ስንቄም አስፈላጊውን ነገር ረድተውት ወደ ጎጃም አምርቷል›› ይላል፡፡ ነገር ግን ዊንሆልት ወደ ጎጃም ዘልቆ ሊታይ አልቻለም፡፡ በኋላ እንደተረጋገጠውም የገለባቱ ዘገባ ትክክል አልነበረም፡፡
ከወራት በኋላ እንግሊዞች በአካባቢው ባደረጉት አሰሳ ዊንሆልት ይጠቀምበት የነበረውን  ሄልሜት፣ የተበጫጨቁ ልብሶቹንና ይዞት የነበረውን ቦርሳ(ኪት) አገኙት፡፡ አሳሽ ጓዱም ዊንሆልት መጀመሪያ ተመትቶ ወደ ጫካ በመግባት በዚያው ሳይሞት እንዳልቀረ ገመተ፡፡
ጦርነቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የዊንሆልት ባለቤት በካርቱም ያለውን የእንግሊዝን ሚሲዮን የባሏን መጨረሻ እንዲያሳውቃት ጠይቃ ነበር፡፡ በጁላይ 8 ቀን 1941 እኤአ ከጋላባት የተነሡ እንግሊዝ ወታደራዊ አሳሾች ዊንሆልት የሄደበትን መንገድ ተከትለው እነዚያ ሁለት አብረውት የተጓዙ ሰዎች ካምፕ ሠራንበት ወዳሉት ቦታ ተንቀሳቅሰው ነበር፡፡ በአካባቢው የተገኙ መረጃዎች እንደጠቆሙት ጣልያኖች የዊንሆልትን መምጣት በማወቃቸው በመንገዱ ተከትለውታል፡፡ በመጨረሻም ካምፑን በመውረር ተኩስ ሲከፍቱባቸው ዊንሆልትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ካምፑን ጥለው ጠፉ፡፡ ጣልያኖችና ባንዶችም ወደ ካምፑ ገቡ፡፡
ከዓይን እማኞችና በጊዜው ከነበሩ የአካባቢው ሰዎች ያገኘውን መረጃ ይዞ አሳሹ ጓድ ከመጣብያ የአራት ወይም የአምስት ሰዓት መንገድ ወደሚርቀውና ከሺንፋ ወንዝ አጠገብ ወደነበረው የዊንሆልት ካምፕ ቦታ ደረሰ፡፡ በአካባቢው በተደረገው ምርመራ የአህዮች አጥንት፣ የተተኮሱ ጥይቶች ቀለሃዎችና የጫማ ቅሬቶች ተለቀሙ፡፡ በአቅራቢያውም የጥርስ መፋቂያና ቦት ጫማ ተገኘ፡፡ ካምፑ ነበረበት ከተባለው 300 ያርድ ርቀት ላይም በመበስበስ ላይ የነበሩ የሰው አጥንቶች ታዩ፡፡ ምናልባትም የቆሰለው ዊንሆልት እዚህ ድረስ ተጉዞ ይሆናል ለሞት እጁን የሰጠው፡፡
ካርቱም የሚገኘው የዊንሆልት የመታሰቢያ ሐውልት 
ይህ ሪፖርት ሲድኒ ሲደርስ የኩዊንስ ላንድ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ኦክቶበር 10 ቀን 1941 እኤአ የዊንሆልትን መሞት በይፋ ዐወጀ፡፡ ቋረኛው የአውስትራልያ ሰውም የኢትዮጵያን ነጻነት ሳያይ ቋራ ላይ ቀረ፡፡ አንደኛው ቋረኛ(ዐፄ ቴዎድሮስ) ለእንግሊዝ እጄን አልሰጥም ብሎ በጀግንነት ሞተ፡፡ ሌላኛው ቋረኛም ኢትዮጵያን ነጻ አወጣለሁ ብሎ በሀገሬው ባንዶች ተገደለ፡፡ ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር እንዲህ ነጭ ከጥቁር ዋጋ ከፍሎባታል፡፡ ኢትዮጵያ እንግሊዞች፣ ኩባዎች፣ አውስትራልያዎች፣ ዐረቦች፣ አይሁድ፣ ሱዳኖች፣ ሩሲያዎች፣ አሜሪካኖች፣ ግሪኮችና ሌሎች ዋጋ ከፍለው ሀገር ያደረጓት ሀገር ናት፡፡ እንኳን የተወለዱባትን ያወቋትን ሰዎች ሕይወት የምታስገብር ሀገር፡፡
 ከፐርዝ ወደ ሜልበርን፣ ኳንታስ አውሮፕላን ላይ

ESAT Radio Sep 01

Viewing all 13695 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>