የግብፅ መንግሥት እርምጃና መገናኛ ዘዴዎች
ልማት ምንድነው? እውን የወያኔ መንግሥት ልማታዊ ነው? (ታደሰ ብሩ)
ከታደሰ ብሩ
“ሰላም ምንድነው?” በሚል ርዕስ ለፃፍኩት መጣጥፍ ከደረሱኝ በርካታ አስተያየቶች ውስጥ “በነካ እጅህ ልማት ምን ማለት እንደሆነ ብትገልጽልን” የሚለው ጥያቄ ለዚህ ጽሁፍ ምክንያት ሆኗል።
ከአሰልቺ የወያኔ ካድሬዎች ክርክሮች አንዱ “ልማታችን፣ ልማታችን” መሆኑ የማውቀውና በራሴም ላይ ከተራ ማሰልቸት በላይ የመብት ጥሰቶች ያደረሰብኝ ጉዳይ ነው። ወያኔ በአገራችን ላይ ላሰፈነው አገዛዝ ተቀባይነት (ligitimacy) ዋነኛ መከራከሪያው “ለኢትዮጵያ ልማትን ያመጣሁ፤ አሁንም በማምጣት ላይ ያለሁ መንግሥት ነኝ። ለወደፊቱም ኢትዮጵያን ለማልማት ከኔ የተሻለ የለም” የሚል ነው። በዚህ ክርክር ውስጥ (1) ከዚህ በፊት በአገሪቱ ውስጥ ልማት የሚባል ነበር አልነበረም፤ (2) እኔ ልማትን እያመጣሁ ነው፤ ሌላውን ቻሉት፤ እና (3) ለወደፊቱም ከኔ የተሻለ ኢትዮጵያን ማልማት የሚችል የሌለ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ሲባል እኔ ለረዥም ጊዜ በስልጣን መቆየት አለብኝ የሚል መልዕክት አለው። ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ESAT Radio: Sep 03
ትላንት እሁድ ሳይካሄድ የቀረው የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍና ጥያቄዎቹ –ሴፕቴምበር 03, 2013
አሜሪካ በሶሪያ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መቃረቡዋን ተከትሎ የመካከለኛው ምስራቅ እንደገና በጦርነት ሊታመስ እንደሚችል ተሰግቷል።
ነሃሴ ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦባማ አስተዳደር በዜጎቹ ላይ የኬሚካል መሳሪያዎችን በመጠቀም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ባለው የባሽር አላሳድ መንግስት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ሲያስጠነቅቅ ከቆ በሁዋላ በመጨረሻም ፕሬዚዳንቱ፣ ጉዳዩን ለኮንግረስና ለሴኔት አቅርበው ለማስወሰን በመፈለጋቸው ባለፈው ሳምንት የታየው የጦርነት ደመና ዝናቡን ሳያርከፈክፍ መጥፋቱ ይታወቃል።
ይሁን እንጅ ፕሬዚዳንት ኦባማ የዲሞክራት እና የሪፐብሊካን መሪዎችን ከአነጋገሩ በሁዋላ ፣ ሁለቱም መሪዎች የሰጡዋቸው መልሶች አዎንታዊ መሆን፣ አሜሪካ በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ሶሪያን ልትደበድብ ትችላለች የሚለው ግምት አይሏል።
አሜሪካ እና እስራኤል በጋራ የጀመሩት የሚሳኤል ተኩስ ልውውጥ ውጥረቱን እንደገና የጨመረው ሲሆን፣ በዚህ መሀል ኢራን በጦርነቱ ውስጥ እጃን በቀጥታ ካስገባችን አካባቢው በጦርነት ሊታመስ እንደሚችል ብዙዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።
እንግሊዝን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ አገሮች ሶሪያን ለመደብደብ የቀረበውን አማራጭ አይደግፉም። የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ከአሜሪካ ጎን መቆማቸውን ቢያስታውቁም፣ የአገሪቱ ምክር ቤት ድምጽ እንከሚሰጥበት ድረስ በይፋ ጦርነቱን መቀላቀላቸውን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
በመካከለኛው ምስራቅ የሚታየው ውጥረት እየተባባሰ መሄድ የነዳጅ ዋጋን እንዳይጨምረውም ተሰግቷል። በዚሁ ሳቢያ ቀስ በቀስ እያገገመ የሚገኘው የአለም ኢኮኖሚ ተመልሶ ወደ ችግር ሊገባ ይችላል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አባላት የሆኑት ሩሲያና ቻይና የአሜሪካንን እርምጃ በጽኑ ተቃውመዋል።
ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች በድጋሜ ታላቅ ግብዣ ተዘጋጀ
ነሃሴ ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአራት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበትና በኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት የኪነጥበባት ባለሙያዎች፣ ምሁራንና የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን የተሳተፉበት የጉብኝት ፕሮግራም ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 4/2005 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ይህንን መነቃቃትና የገጽታ ግንባታ አጠናክሮ ለመቀጠል ያስችላል የተባለ ታላቅ ድግስ ጳጉሜ 3 ቀን 2005 በሸራተን ሆቴል ተዘጋጀ፡፡
አርቲስቶችና ጋዜጠኞች የተሰባሰቡበት ይህው ቡድን በወቅቱ በሶማሌ ክልል ከጎዴ ጀምሮ እስከ ጅጅጋ ድረስ ጉብኝት ያካሄዱ ሲሆን ይህንን ተከትሎም አብዛኛው የቡድኑ አባላት ቀጣይ የስነጥበብ ዝግጅት በአዲስአበባ ለማድረግ በመስማማት በቅርቡ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡
በአቶ ካሳ ተክለብርሃን የሚመራው የፌዴሬሽን ም/ቤት በዚሁ የተገኘውን ሰፊ መነቃቃትና የገጽታ ግንባታ ይበልጥ ለማዳበር በሚል ሰሞኑን ታላቅ የእራት ግብዣ ጠርተዋል፡፡ በዚህ ግብዣ ላይ የተለያዩ የፌዴራልና የክልል የመንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦች፣ የስነጥበብና የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይገኛሉ ተብሎአል፡፡
በሶማሌ ክልል የተሳካ ጉብኝት መካሄዱን እነአቶ ካሳ ተ/ብርሃን አረጋግጠናል ካሉ በኃላ ቡድኑን ይመሩ ከነበሩት አርቲስቶች መካከል የአቶ ካሳ ተ/ብርሃን የቅርብ ወዳጅ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ሽመልስ ለውለታቸው ብሔራዊ ቲያትርን በስራ አስኪያጅነት እንዲመሩ ተሹመዋል፡፡
በእነአርቲስት ሰርጸፍሬ ስብሃት የሚመራና የአርቲስቶች ቡድንም በቅርቡ በሶማሌ ክልል ላይ ያተኮረ የስነጥበብ ዝግጅት ለማካሄድ ተፍ ተፍ እያለ ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ጥቃት አላደረስኩም ሲል መካዱን ቢቢሲ ዘገበ።
ነሃሴ ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባ ሰማያዊ ፓርቲ ሊያደርገው የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ በሀይል የጨፈለቀው የ ኢህአዴግ መንግስት፤ በርካታ የፓርቲውን አባላት እንዳሰረ ፣ እንደደበደበና እና የጽህፈት ቤቱን ንብረት እንደመዘበረ ፓርቲው መግለጹን ቢቢሲ በትናንት ዘገባው አመልክቷል።
የፓርቲውን ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነትን በመጥቀስ የዜና አውታሩ እንደዘገበው፤ እሁድ ሊካሄድ ለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በፓር ቲያቸው የተዘጋጁ የድምጽ መሣሪያዎች በታጣቂዎች ተወስደዋል፤ ሰልፉም እንዳይካሄድ በሀይል ተቀልብሷል።
ስለጉዳዩ በቢቢሲ የተጠየቁት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚ/ር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማል ድርጊቱ አልተፈጸመም ሲሉ ክደዋል።
አቶ ሽመልስ አክለውም ሰማያዊ ፓርቲ በሰኔ ወር የጠራው ህዝባዊ ተቃውሞ በ1997 ከተደረገውና የመቶዎችን ህይወት ከቀጠፈው ሰላማዊ ሰልፍ በኋላ የተደረገ የመጀመሪያው ነበር::
ፓርቲው በባለፈው የተቃውሞ ሰልፍ የመብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ከእስር እንዲፈቱ የጠየቀ ሲሆን፤ ለ እሁድ ሊያደርገው አስቦት የነበረው ሰልፍ ደግሞ የፓለቲካ ታሃድሶ እንዲካሄድ ጥሪ የሚያደርግ ነበር::
አቶ ሽመልስ -” ማንኛውም ህዝባዊ ተቃውሞ የሚያደርግ አካል ፍቃድ ማግኘት አለበት ፤ሆኖም ባለሥልጣናት ፈቃድ መከልከል አይችሉም፤ ነገርግን ተቃውሞው በሌላ ቦታና ጊዜ እንዲካሄድ መንግሥት የማያወላውል አቋም ሊይዝ ይችላል” ሲሉም ተናግረዋል::
መለስ ከሞቱ በኋላ ሃይለማርያም ደሳለኝ የሚመሩዋት ኢትዮጵያ ባለችበት ቀጣና እስላማዊ አማጺያንን በመዋጋት የአሜሪካ አጋዥ ነች ብሏል-ቢቢሲ።
አቶ ሽመልስ-መንግስት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የተባለውን ነገር አልፈጸመም ብለው ለቢቢሲ በመናገራቸው ብዙዎችን አስገርሟል።
ሰማያዊ ፓርቲ ጳጉሜ 2 ቀን 2005 ዓም የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ላለፉት 2 አመታት ስርአቱን በሀይል ለመፈታተን ከሞከሩት ሁሉ የሀይማኖት እንቅስቃሴዎች ዋነኞቹ እንደነበሩ ኢህአዴግ አስታወቀ
ነሃሴ ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው አዲስ ራእይ በሚባለው ልሳኑ ” ፣ በሀይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እየተዳከሙና እየተጋለጡ መሄዳቸው ባይቀርም ባለፉት ሁለት አመታት ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ ስርአቱን በሐይል ለመፈታተን ከመከሩት የሁከት ሀይሎች ዋነኞቹ ነበሩ ማለት ይቻላል” ብሎአል።
ኢህአዴግ ከአክራሪዎች ጎን በመቆም አመጽ ለማነሳሳት ሞክረዋል ካላቸው ድርጅቶች መካከል ድምጻችን ይሰማ፣ ግንቦት 7 አሜሪካ ድምጽ ሬዲዮና ቢላል ሬዲዮ በዋናነት ተጠቅሰዋል።
በውስጡ ያሉ አንዳንድ የኢህአዴግ አመራሮችም እንዲሁ በሀማኖት ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ችግሩን እያባባሱ በመሆኑ፣ እነዚሁ ባለስልጣናት የመንግስትን ስልጣን አስረክበው ወደ ሰባኪነታቸው እንዲያመሩ እንመክራለን ብሎአል።
መጽሄቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በክርስትና እና በእስልምና ሀይማኖቶች ውስጥ እየታየ ያለውን የአክራሪነት አዝማሚያና ይህን ተጠቅሞ የሚካሄደውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለመግታት መንግስት በየትምህርት ተቋማት ትምህርቶችን መስጠት፣ ለወጣቶች ተገቢውን ስራ በመስጠትና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደላበት ጠቁሟል።
ኢህአዴግ አሁን የሚታየው የሙስሊሙ እንቅስቃሴ እየተዳከመ ቢመጣም ተመልሶ ስርአቱን ሊገዳደር የሚችልበት ምልክት እየታየ መሆኑን ጠቁሟል።
በሌላ ዜና ደግሞ ኢህአዴግ የሚዲያ አደረጃጀቱን በአዲስ መልክ ማዋቀሩ ታውቋል። የፌደራል እና የክልል የመገናኛ ብዙሀንም ከእንግዲህ ወዲህ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በሚሰጡዋቸው አቅጣጫ ፕሮግራሞቻቸውን እንደሚያዘጋጁ ታውቋል። በደቡብ ክልል አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ በአማራ ክልል አቶ አለምነው መኮንን፣ በኦሮምአ አቶ አለማየሁ አቶምሳ በየወሩ ከጋዜጠኞች እና ዋና አዘጋጆች ጋር በመተባበር የዜና ዘገባ አቅጣጫዎችን ይሰጣሉ።
ማንኛውም ጋዜጠኛ ስራውን የሚሰራው እነዚህ የኢህአዴግ አመራሮች በሚሰጡት የትኩረት አቅጣጫ መሰረት እንደሚሆን ከግንባሩ የቅርብ ሰዎች ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።
የሰማያዊ ፓርቲ ፍርድ ቤት ሊሄድ ነው –ሴፕቴምበር 04, 2013
በቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ መስቀል ከሰማይ ወረደ መባሉ አነጋጋሪ ሆኗል
ከአዲስ አበባ የመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተከሰተ በተባለ ተአምር መስቀሉ ወረደ የተባለው ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ከለሊቱ 9፡00 ሰዓት አከባቢ ነሐሴ 23 ቀን 2013 ሲሆን ካህናት አባቶች እና ምእመናን የክርስቶስ ሳምራን የበአል ዋዜማ ማህሌት ቆመው እንዳለ መስቀሉ ወርዷል ተብሏል።
ከስፍራው የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ማህሌት ቆመው የነበሩት አባታኦች ከሰማይ የወረደውን መስቀል ድምጽ ድምፅ ሲሰሙ ካህናትና የቤተክርስቲያን አስተዳደሩ ከቤተመቅደስ ወጥተው ሁኔታውን ሲመለከቱት ብርሀን ከሰማይ እንደወረደና አከባቢውን በብርሀን እንደሞላው ተመልክተዋል ተብሏል። መስቀሉ የጌታ ስቅለት ያለበት ነውም ተብሏል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝቡ ጉዳዩን በጥርጣሬ በማየት እየተነጋገረበት ሲሆን ለማመን የተቸገሩ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ የመስቀሉን መውረድ የሚያምኑ ሰዎችም ቁጥራቸው አናሳ አይደለም።
በቅርብ ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ አንዲት ሴት ድንግል ማርያም ነኝ በሚል ብዙ ሰዎችን አጭበርብራለች ተብላ መታሰሯ ይታወሳል። ከዚያ ቀደምም ባህታዊ ገብረ መስቀል የተባሉ ሰው ራሳቸው ታቦት አስቀብረው ሕዝቡን ‘ራዕይ ታይቶኛልና እዚህ ቦታ ብትቆፍሩ ታቦት ታገኛላችሁ” በሚል በማጭበርበር መጋለጣቸው ይታወሳል።
አንባቢዎች የእናንተ አስተያየት በዚህ ጉዳይ ምን ይመስላል?
ወያኔ የሚገነፍል ድስት ነዉ ኤፍሬም ማዴቦ
ስፖርት በጣም እወዳለሁ፤ ወቅታዊ ዜናና ጥናታዊ ፊልምም አዘወትራለሁ። ከሁለቱ ዉጭ ግን ኢትዮጵያ እያለሁም ሆነ ዛሬ በስደት ኑሮዬ ከቴሌቪዥን ጋር ብዙም አልዋደድም . . . ግን አንዳንዴ እበድ ሲለኝ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ቴሌቪዥን ሆኖ ከመተኛቴ በፊት ኢቲቪ እየከፈትኩ አብዳለሁ። አዎ . . . አብዳለሁ። ሆዴ ያመቀዉ ቁጣና ልቤ የተሸከመዉ የ22 አመት በደል ቀለል የሚለኝ ሳብድ ነዉና ኢቲቪ እየከፈትኩ አብዳለሁ። ምን ላድርግ ተሰድጄ ልበድ እንጂ በወያኔዋ ኢትዮጵያማ እነ በረከት ካልፈቀዱ ማበድም አይቻልምኮ! አደራ እንግዲህ እንደኔ ጠንካራ ቆዳ የሌላችሁና በትንሹም በትልቁም እየተበሳጫችሁ ዕቃ የምትወረዉሩ ሰዎች ኢቲቪን ከመክፈታችሁ በፊት ባንካችሁ ዉስጥ ቴሌቪዥን መግዢያ ትርፍ ገንዘብ መኖሩን አረጋግጡ፤ አለዚያ እዉነትም ማበዳችሁ ነዉ።
ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት የወያኔን ፀባይ በተከታታይ እንዳየሁት የወያኔ ፀባይ ከበቅሎ፤ ከድስት ወይም ከሁለቱም ጋር ተመሳስሎብኛል። በቅሎ የታሰረችበትን ገመድ በጠሰች ቢሉት “በራሷ አሳጠረች” ብሎ መለስ አሉ የበቅሎዋ ጌታ። በቅሎ መታሰሪያዋን በበጠሰች ቁጥር የምትጎዳዉ እራሷን ነዉ፤ ግን በቅሎ በጭራሽ ከስህተቷ አትማርምና ሁሌም ገመዷን እንደበጠሰች ነዉ። አምባገነኑ ወያኔም እንደዚሁ ነዉ። ድስት ሁሉም ባይሆንም አንዳንዱ በጣዱት ቁጥር ይገነፍላል፤ የሚገነፍል ድስት ደግሞ የሚያበላሸዉ እራሱን ነዉ። ወያኔ ድስትም በቅሎም የሚሆነዉ ዕድሜዉን ለማራዘም ነዉ፤ ሆኖም ሲገነፍልም ሆነ ገመዱን ሲበጥስ እድሜዉ ያጥራል እንጂ አይረዝምም።
ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሐይማኖቶች ጉባኤ ይካሄዳል ሲባል ሰምቼ ባለፉት ሁለት አመታት ካልጠፋ ነገር አገራችን የምትታመሰዉ በሐይማኖት ጉዳዮች ነዉና እስኪ ዜናዉን ከምንጩ ልስማ ብዬ ኢቲቪ ላይ አፈጠጥኩ። መቼም ኢቲቪ በብዙ ነገሮች ሊያበሳጫችሁ ይችላል ግን ዛቻ፤ ዉሸትና፤ ዘራፊ ባለስልጣኖች ሲሞገሱ መስማት ከፈለጋችሁ ግን ሌላ ዬትም ቦታ መሄድ አያስፈልጋችሁም በዚህ ኢቲቪ የልባችሁን ያደርስላችኋል።
ወያኔ ስልጣን ይዞ በቆየባቸዉ አመታት ሁሉ ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያ ጨንቋት ያላማጠችበትና ግራ ግብቷት ድረሱልኝ ያላለችበት አንድም ግዜ የለም። ወያኔ ባለፉት ሃያ አመታት ዉስጥ አገራችን ኢትዮጵያን እንዳልነበረች ለማድረግ ያልቆፈረዉ ጉድጓድና ያልሸረበዉ ደባ ባይኖርም ባለፉት ሁለት አመታት ይዞብን የመጣዉ ሸርና ተንኮል ግን የክርስቲያኑንና የሙስሊሙን ማህብረሰብ የአንድ ሺ አራት መቶ አመታት በሰላም አብሮ የመኖር ባህል የሚያደፈርስና አገራችንን አስከፊ የሐይማኖቶች ግጭት ዉስጥ የሚከት አደገኛ ሴራ ነዉ። ለወትሮዉ ፖለቲካዉን በዘር፤በቋንቋና በክልል ቋጥሮ ማዶ ለማዶ የለያየን ወያኔ ዘንድሮማ ጭራሽ የፓርቲ አባልነታችንን ብቻ ሳይሆን የምናመልክበትን የእምነት ቦታና አለም በቃኝ ብለን የምንመንንበትን ገዳም ጭምር አኔ ነኝ መርጬ የማድላችሁ ማለት ጀምሯል። በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ጳጳስ አዉርዶ ጳጳስ ሾሞባቸዋል፤ የወንጌላዉያን ቤ/ክርሲቲያኖችን ፓስተር አንዴ አስታራቂ አንዴ አማላጅ እያደረገ ቤ/መንግሰትና ቃሊቲ መሃል ተላላኪ አድርጎታል፤አሁን በቅርቡ ደግሞ ፊቱን ወደ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በማዞር የራሱን መጅሊስ ሾሞባቸዋል።
ወያኔ ጥንታዊቷን የኦርቶዶክስ ቤ/ክርሰቲያናችንን የአገር ዉስጥና የአገር ዉጭ ሲኖዶስ በሚል በመከፋፈል ወንጌላዉያኑን አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ እኔ ነኝ የማምለክ ነጻነት የሰጠኋችሁ እያለ በማስፈራራት የክርስቲያኑን ህብረተሰብ ለግዜዉም ቢሆን ጭጭ አሰኝቶ እንዳሰኘዉ መቆጣጠር ችሏል። በድርጅታዊ ጥንካሬዉ፤ በምዕመኑ መካከል በገነባቸዉ የግንኙነት መስመሮችና በእምነት ቀናኢነቱ ከክርስቲያኑ እጅግ በጣም በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኘዉ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ግን የወያኔን ፈላጭ ቆራጭነት አልቀበልም ብሎ ወያኔንና ዘረኝነቱን ፊለፊት በመጋፈጥ ላይ ይገኛል። ሰለሆነም ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ ሐይማኖቴን አትንካብኝ በሚለዉ በሙስሊሙ ህብረተሰብና አጎንብሰህ ተገዛ በሚለዉ ወያኔ መካከል በተፈጠረዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት በመታመስ ላይ ትገኛለች። እኔም ሞኝ ይመስል ኢቲቪ ላይ ያፈጠጥኩት ይካሄዳል የተባለዉ የሐይማኖት ጉባኤ ይህንን አገራችን ላይ የተደቀነዉን አደጋ ተመልክቶ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል ብዬ ነበር። ግን የወያኔ ነገር ሁሌም ታጥቦ ጭቃ ነዉና የሐይማኖት ጉባኤ ተብሎ የቀረበዉ ጉድ እንደ አኬልዳማና ጂሃዳዊ ሐረካት ሆን ተብሎ ህዝብን ለማደናገር የተሰራ ድራማ ነዉ እንጂ በችግሮች ላይ ተወያይቶ የመፍትሄ ሃሳብ የሚያቀርብ ጉባኤ አይደለም። በአኬልዳማ ድራማና ሰሞኑን በተካሄደዉ የሐይማኖቶች ጉባኤ መካከል ልዩነት ቢኖር አንዱ የቴሌቪዥን ድራማ ሌላዉ ደግሞ የመድረክ ላይ ድራማ መሆናቸዉ ብቻ ነዉ።
በዚህ የሐይማኖቶች ጉባኤ ተብዬዉ የአዳራሽ ውስጥ ድራማ ላይ የተገኙት አብዛኛዎቹ ተዋንያን የዚያ “የድንጋይ ማምረቻ” ተቋም ዉጤቶች የሆኑ የወያኔ ካድሬዎች፤ የወያኔ ባለስልጣኖችና ኤሳዉ ታላቅነቱን ለምግብ እንደሸጠ የሐይማኖት አባትነታቸዉን ለጥቅም የሸጡ ካህናት ለመሆናቸዉ ምስክር የሚያሻ አይመስለኝም፤ ቴሌቪዥኑ መስኮት ዉስጥ አንደተከበበ አዉሬ የሚቁለጨለጨዉ አይናቸዉ ምስክር ነዉ። ድራማዉን በኢቲቪ ስመለከት ተጠያቂነት የሚባል ነገር የማያዉቁ የወያኔ ባለስልጣኖች እንዳሰኛቸዉ እንደሚናገሩ ስለማዉቅ እነሱ ተናገሩም አልተናሩ ከነሱ ብዙም የምጠብቀዉ ነገር አልነበርም። ይልቁን ጉባኤዉን ስከታተል እጅግ በጣም የገረመኝና የራሴኑ ጆሮ ማመን ያቃተኝ አንድ በሰማይም በምድርም ተጠያቂነት ያለባቸዉ የሐይማኖት አባትና በዋሸ ቁጥር ኩራት የሚሰማዉ በረከት ስምኦን ያደረጉት እንደ ብርሀንና ጨለማ የተቃረነ ንግግር ነዉ። መቼም እርግጠኛ ነኝ የበረከትንና የአባዉን ፊት ሳያይ ንግግራቸዉን ብቻ ያዳመጠ ሰዉ የቱ ነዉ በረከት የትኛዉ ናቸዉ የሀይማኖት አበት ብሎ መጠየቁ አይቀርም። ለሁሉም እኚያ የሐይማኖት አባትና በረከት እንዲህ ነበር ያሉት
የሐይማኖት አባት መንግስት ትዕግስቱን አብዝቶታል . . . . እርምጃ ይዉስድ
በረከት ስምኦን መንግስት ኃይሉ አለዉ ግን መታገሱ ጠቃሚ ነዉ
መቼም አንደህ አይነቱን ጉድ ከጉድም ጉድ የሚያዳምጡ ሰዎች ጆሯቸዉን ሲያማቸዉ፤ ሲበሳጩና አንጀታቸዉ ሲቃጠል ይታየኛል . . ደግሞስ ለምን አይበሳጩ ለምንስ አንጀታቸዉ አይረር? ትዕግስት ምን አንደሆነች የማያዉቃት ወያኔ ለዛዉም በበረከት ስምኦን አፍ መታገሱ ጠቃሚ ነዉ ነዉ ብሎ ሲናገር የትዕግስት አባት የሆነዉን እግዚአብሄርን አገለግላለሁ ባዩ ቄስ “ትዕግስት በዛ እርምጃ ይወሰድ” ብለዉ መንግስትን የሚማጸኑበት ግዜ መጣ . . . ያዉም ስራዉ ዜጎችን መግደል የሆነዉን መንግስት! እግዚኦ! ለመሆኑ አንደ አገርና እንደ ህዝብ ስነምግባራችንና ሀይማኖታዊ እሴታችን እንደዚህ የዘቀጠበት ግዜ ኖሮን ያዉቃል? የወደፊቱን አገር ተረካቢ ትዉልድ በስነምግብርና በግብረገብ አንጾ የማሳደግ ኃላፊነት ያለባቸዉ የሐይማኖት አባት መንግስትን አሁንስ አበዛኸዉ ሂድና ግደል እንጂ የሚሉ ከሆነ ይህ እዉነት ሳይሰማ ያደገ ትዉልድ ስራዉ መግደል ብቻ ሊሆን ነዉኮ . . . አረ እግዚኦ ማረን! እባክህ ማረን!
ልጅ እያለሁ አንድ በኃይሉ እሼቴ የሚባል “መሆኑ ይገርማል የተገላበጦሽ አህያ ወደሊጥ ዉሻ ወደ ግጦሽ” ብሎ የዘፈነ አለግዜዉ የተፈጠረ ዘፋኝ ነበር . . ያኔ የማይመስል አባባል ይመስለኝ ነበር፤ ይሄዉና ዘመን ቆጥሮ ደረሰ። በረከት ስምኦንን በተመለከተ ያንን ንግግር ከልቡ ይናገረዉ ወይ ለማሽሟጠጥ አላዉቅም ሆኖም በረከት ያዉ በረከት ነዉና ስለሱ ምንም የምለዉ የለኝም። እኚያ የሐይማኖት አባት ግን ይህንን አሳፋሪ ንግግር የተናገሩት ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ያንን ለትዉልድ ሁሉ ኩራት የሆነዉን ታሪካዊ ንግግር በተናገሩበት ከተማ ዉስጥ ነዉና አሳቸዉ ያለ እፍረት አፋቸዉን እንደከፈቱ እኔም በድፍረት አፌን አከፍትባቸዋለሁ . . . ምን ላድርግ 1ኛ ሳሙኤል 2፡1 ላይ “አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ” ይላልኮ አባ እራሳቸዉ ያስተማሩኝ ቅዱስ መጽሐፍ። ለሁሉም “እናቷን ምጥ አስተማረች” እንዳይሆንብኝ እንጂ እኚያ ወያኔን “ምነዉ መንግስት ትዕግስት አበዛ” ብለዉ ያወገዙት አባት ተሸክመዉ የሚዞሩትን መ/ቅዱስ አንብበዉት ከሆነ እዚያ ቅዱስ መጽሐፍ ዉስጥ ትዕግስት የሚለዉ ቃል 33 ግዜ ተጠቅሷል። “አትግደል” የሚለዉ ትዕዛዝ ደግሞ ከአስርቱ ትዕዛዛት አንዱ ሲሆን ቅዱስ ታቦቱ ላይም የሰፈረ ቃል ነዉ። መጽሐፍ ቅዱስ ትዕግስትን አስመልክቶ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 25፤15 ላይ “በትዕግስት ማግባባት ታላቅ ተቃወሞን ያበርዳል፤መሪዎችን ሳይቀር በሃሳብ እንዲስማሙ ያደርጋል” ይላልኮ! ለመሆኑ ትዕግስቱን ተትህ ግደል እንጂ ብለዉ ወያኔን የተማፀኑት የሐይማኖት አባት የኦርቶዶክስ አባ ናቸዉ፤ የካቶሊክ ካርዲናል፤ የፕሮቴስታንት ፓስተር ወይስ በሐይማኖት ስም የመጡ የወያኔ ካድሬ? ማናቸዉ እኚህ ታገሱ ፤ ትዕግስትን ገንዘባችሁ አድርጉ፤“መግደል” ኃጢያት ነዉና ሰዉ አትግደሉ ብለዉ ማስተማር ሲገባቸዉ የተገላቢጦሽ “ግደል” እያሉ የሚማጸኑ የሐይማኖት ሰዉ?
ኢትዮጵያዉያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ያነሱትን የመብትና የነጻነት ጥያቄ በተመለከተ ፖለቲካና ሐይማኖት፤ካድሬነትና ቅስና ተቀላቅሎባቸዉ ግራ ተጋብተዉ ህዝብን ግራ ከሚያጋቡ ሰዎች አንዱ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ነዉ። ኃ/ማሪያም ደሳለኝ እንደ መለስ ዜናዊ ምላስ እንቆርጣለን ብሎ እንዳይዝት እንኳን ምላስ ለመቁረጥ ቤ/መንግስት ከመግባቱ በፊት በነጻነት ያመልከዉ የነበረዉን አምላኩን ለማምለክም የወያኔ ፈቃድ ያስፈልገዋል። ደሞ ምንም ቢሆን ሰዉዬዉ የአገር መሪ ነዉና ችግሮችን እፈታለሁ በሚል ሚዛናዊ እርምጃ ልዉስድ ቢል እሱ እራሱ በስልክ እየታዘዘ የሚሰራ ሰዉ ነዉ። መቼም በወያኔዋ ኢትዮጵያ እንዲህ አይነቱ ነገር አይታሰብም እንጂ ኃ/ማሪያም ዳሳለኝ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳዉን ጥያቄ ከሐይማኖት፤ከባህልና ከስነምግባር አንጻር አይቶ ትክክለኛ ጥያቄ ነዉ ብሎ ጥያቄዉን ለመመለስ ቢሞክር እንኳን ብዙም ሳይቆይ “እንደወጣች ቀረች” ተብሎ ይተረትበታል አንጂ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ህዝባዊ ጥያቄዎችን መመለስ ቀርቶ እሱ እራሱ ያሻዉን ጥያቄ መጠየቅም አይችልም ። እንግዲህ ይህ እራሱን መሆን የተሳነዉና ሦስት ቅርቃሮች ዉስጥ ገብቶ የተቀረቀረዉ ኃ/ማሪያም ነዉ አንዴ ተጨማሪ የኃይል እርምጃ እንወስዳለን፤ አንዴ የሙስሊሙ ጥያቄ የሸሪአ ጥያቄ ነዉ፤ ይባስ ሲለዉ ደግሞ ከሙስሊሙ ትግል ጋር የተባበረ ሁሉ ሽብርተኛ ነዉ እያለ ያልተጻፈ መጽሐፍ የሚያነብበዉ። ለመሆኑ ይህ ጧትና ማታ የጓድ መለስን ራዕይ ተግባራዊ እናደርገለን እያለ የሚዘምረዉ ኃ/ማሪያም “ተጨማሪ የኃይል እርምጃ እንወስዳለን” ሲል የጌታዉን ራዕይ ተግባራዊ ማድረጉ ይሆን?
ባለፉት ሦስት ሳምንታት በተለይ ባለፈዉ ቅዳሜ በወያኔ ጌቶቹ እየተመራ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የወሰዳቸዉ ፀረ ህዝብና ፀረ አገር እርምጃዎች ለኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ኢትዮጵያ ዉስጥ በመካሄድ ላይ ያለዉን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለሚከታተሉ አገሮች ያረጋገጠዉ ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን ዘረኛ ስርዐት ለማስወገድ የሚከተለዉን እስትራቴጂ በጥልቀትና በስፋት መመርመር እንዳለበት ነዉ። እስካዛሬ እንዳየነዉ ወያኔ በልመናም፤ በሰላማዊ ትግልም፤ በአመጽም ሆነ በሌላ በምንም አይነት መንገድ እንድንታገለዉ የማይፈልግና እኔ ብቻ ዝንተ አለም እንደገዛኋችሁ ልኑር የሚል ልቡ ያበጠ አምባገነን ነዉ። ህዝባዊ ተሳትፎን በተመለከተ የወያኔ ፍላጎት አንድ ብቻ ነዉ፤ እሱም በዚያ እሱ እንደ ቤቱ ጓዳ በሚቆጣጠረዉና በየአምስት አመቱ በሚደረገዉ ምርጫ እንድናጅበዉ ብቻ ነዉ። ከዚህ ዉጭ ዲሞክራሲና መብት የሚባል ቃል ስሙን ያነሳ ሰዉ ወይ ይታሰራል፤ ይደበደባል፤ከአገር ይሰደዳል አለዚያም ይገደላል። የወያኔና የእኛ ሠላማዊ ትግል በይዘትም በቅርጽም እጅግ በጣም የሚለያይ ይመስለኛል። የወያኔ ሠላማዊ ትግል እኔን ብቻ ስሙኝ ወይም በየአምስት አመቱ በምርጫ አጅቡኝ ነዉ። እኛ ሠላማዊ ትግል የምንለዉ ደግሞ መብታችን ይከበር ብለን ባሰኘን ግዜና ቦታ የተቃዉሞ ሠልፍ ማድረግ፤ የስራ ማቆም አድማ ማድረግና ወያኔ ህገመንግስቱን የሚጻረር መመሪያና ህግ ሲያወጣ በፍጹም አንቀበልም ብለን በህዝባዊ እምቢተኝነት ማመጽ ነዉ። ይህንን አድርገን ቢሆን ኖሮ ዛሬ እስክንድርን፤ አንዱአለምን፤ ርዕዮትንና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሠላማዊ ዜጎችን ቃሊቲ የወረወረዉ ህግ አይኖርም ነበር። ሠላማዊ ትግል የሚባለዉ እንደዚህ አይነቱ ትግል ነዉና ወያኔን ማፋጠጥ ያለብን በዚህ አይነቱ ትግል ነዉ፤ ካለዚያ የትግላችንን እስትራቴጅ ፈትሸን ለግዜዉ የወያኔን ጥቃት ባይመጥንም ወያኔ ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት ሁለቴ እንዲያስብ የሚያደርግ የትግል እስትራቴጅ መንደፍ አለብን። ከዚህ በተጨማሪ ወያኔን በመሳሪያ ለመፋለም የቆረጡ ኃይሎችን ቢቻል መደገፍ አለዚያም ጣታችንን እነሱ ላይ መጠንቆሉን ማቆም አለብን።
ከሰዐት በኋላ ረፋዱ ላይ ከስራ ወጥቼ ቴሌቪዥኑ ፊት ስደቀን የአገሬ የኢትዮጵያ ነገር አይኔ ላይ ይመጣና አንዳንዴ ግርም ይለኛል፤ አንዳንዴ ይጨንቀኛል፤ አንዳንዴም ይነድደኛል። የከሰሞኑ ግን አታምጣ ነዉ። አግራሞቱም፤ ጭንቀቱም፤ ንዴቱም እንደ ክፉ መንፈስ በአንዴ ተከመሩብኝ። መቼም የኢትዮጵያ ነገር የማይገርመዉ ኢትዮጵያዊም ሆነ የዉጭ አገር ሰዉ ያለ አይመስለኝም፤ ደግሞስ የኢትዮጵያ ነገር ለምን አይገርምም? መንግስት ተብዬዉና አገር እመራለሁ ባዩ ወያኔ የምትወደዉ እንድዬ ልጇ እንደሞተባት አሮጊት አመት ጠብቆ ተዝካር ሲያወጣ . . . . ጎበዝ ለመሆኑ ተዝካር የሚያወጣ መንግስት አይታችሁ ወይም ሰምታችሁ ታዉቃላችሁ? አኔ እንኳን መስማት አስቤዉም አላዉቅም። የሚገርመዉ ወያኔ ያንን የፈረደበትንና የዛሬ አመት እያስፈራራ በጉልበት ያስለቀሰዉን ህዝብ ብቻ ሰብስቦ የጌታዬን ተዝካር አዉጡልኝ ቢል ኖሮ ነገሩ እኛዉ በእኛ ነዉና ስቀን ዝም እንል ነበር፤ ግን ጉደኛዉ ወያኔ ተዝካር ድረሱልኝ ብሎ የጠራዉኮ የጎረቤት አገር መሪዎችን ጭምር ነዉ። የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነኝና ተዝካር ለሟቹም ለቋሚዉም አይጠቅምም ብዬ አምናለሁ፤ ሆኖም ተዝካር ትክክለኛ ነገር ነዉና መዘከር አለበት የሚሉ ወገኖች ተዝካር የማዉጣት መብታቸዉ እንዲከበር ሽንጤን ገትሬ የምታገል ሰዉ ነኝ። ግን የኢትዮጵያ መንግስት ሲባል የኦርቶዶክሱ፤ የሙስሊሙ፤ የጴንጤዉ፤ የካቶሊኩና የሌሎቹም የዬትኛዉም አይነት እምነት ተከታዮችና ስለሐይማኖት ግድ የሌላቸዉም ሰዎች መንግስት ስለሆነ ተዝካር ማዉጣጥ ቀርቶ ስለተዝካር መልካምነትም ሆነ መጥፎነት መናገርም የለበትም የሚል የፀና እምነት አለኝ። በረከት ስምኦንና ሽመልስ ከማል አይገባቸዉም አንጂ የሚገባቸዉ ቢሆን ኖሮ ሐይማኖትና መንግስት ተቀላቀሉ የሚባለዉ እንደዚህ መንግስት በአገር አቀፍ ደረጃ ተዝካር ሲያወጣ ነዉ አንጂ ሐይማኖትና ፖለቲካ ሲነካኩ አይደለም፤ እነሱማ መነካካት አለባቸዉ፤ የአገሪቱ ህገመንግስትም ይህንን አይከለክልም።
ሌላዉ ከሰሞኑ ያየሁት የወያኔ ጉድ . . . ማንን እንደሚቃወም ባላዉቅም ወያኔ ሠላማዊ ሠልፍ የሚወጣ ብቸኛዉ የአለማችን መንግስት ነዉ። ወገኖቼ ይህ ጉድ ካልገረመን፤ ካልጨነቀንና ካልነደደን ሌላ ምን. . . ምን . . . . ምን! ደግሞኮ የ39 አመቱ ጎልማሳ ወያኔ ሠላማዊ ሠልፍ የጠራዉ ገና በእግሩ መሄድ ካልጀመረዉ ከሠማያዊ ፓርቲ ገር ሽሚያ ገብቶ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ መንግስት በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለአገሪቱ ደህንነት ሲባል ካላገደ በቀር ሠላማዊ ሠልፍ ማድረግ ህገመንግስታዊ መብት ነዉ፤ወይም ዜጎች ሠላማዊ ሠልፍ ለመዉጣት ማሳወቅ እንጂ ፈቃድ መጠየቅ አያሻቸዉም። ወያኔ ሠማያዊ ፓርቲ የጠራዉን ሠልፍ ለጸጥታ ወይም ለሌላም ጉዳይ ብሎ እንዳይካሄድ ቢፈልግ ኖሮ ብቸኛዉ አማራጭ ወይ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር መደራደር አለዚያም ፍርድ ቤቶች የራሱ ንበረቶች ቢሆኑም ለይስሙላም ቢሆን እዚያ መሄድና ፍርድ ቤቱን ማሳመን ነበረበት እንጂ ልቡ እንዳበጠ የመንደር ዉስጥ ወጠጤ በተራ ዝርፊያና ድብደባ ላይ አይሰማራም። መንግስት ማለት ያሰኘዉን ነገር ሁሉ የሚያደርግ ተቋም አለመሆኑን ወያኔም ሆነ ወያኔ በተተቸ ቁጥር ምጣድ ላይ እንደቆየ ተልባ የሚንጣጡት ደጋፊዎቹ ሊረዱት ይገባል።
ባለፈዉ ቅዳሜ ወያኔ ከሠማያዊ ፓርቲ ጋር ሠልፍ ልዉጣ አትወጣም በሚል በገባዉ እሰጥ አገባ በህግም በሃሳብም በሠማያዊ ፓርቲ በመሸነፉ የተሸናፊዎች ብቸኛ መሳሪያ የሆነዉን ጉልበትና በህግ ያልተገደበ ኃይል በመጠቀም የሠማያዊ ፓርቲ መሪዎችን በቆመጥና በሰደፍ ሲደበድብ ዉሏል፤ የፓርቲዉን ጽ/ቤት ሰብሮ በመግባት ንብረት ሰርቋል እንዱሁም ፓርቲዉ በህጋዊ መንገድ የተከራየዉን ጽ/ቤት ከብቦ አካባቢዉን የጦርነት ወረዳ አስመስሎታል። መስበር፤ መዝረፍ፤ ሠላማዊ ዜጎችን መደብደብና የአካባቢን ጸጥታ መንሳት . . . . ለመሆኑ ማነዉ ሽብርተኛዉ? አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ አለማችን ብዙ አምባገነን መሪዎችን አስተናግዳለች፤ እንደ ወያኔ አይነቱ ተራ ዱሪዬና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ንፍጣቸዉን የተናፈጡበትን መሀረብ ጭምር የሚሰርቅ ተራ ሌባ የሆነ ስርዐት ግን ዬትም አገር ዉስጥ ታይቶ አይታወቅም። ይህ ስርዐተ አልበኛ የሆነ የወንበዴ አገዛዝ ከአሁን በኋላ የሚወስደዉ እርምጃ ለሁላችንም ግልጽ የሆነ ይመስለኛል፤ ትናንት በአንዱ አለም አራጌ፤ በእስክንድር ነጋ፤ በበቀለ ገርባና ኦብላና ሌሊሳ ላይ የተመሰረተዉ የግፍ ከስ ዛሬ በሠላማዊ ፓርቲ መሪዎች ላይ መመስረቱ አይቀርም፤ የሚያሳዝነዉ በሠማያዊ ፓርቲ መሪዎች ላይ መረጃ ሆነዉ የሚቀርቡት እነዚሁ ባለፈዉ ቅዳሜ ከፓርቲዉ ጽ/ቤት የተዘረፉት የፓርቲዉ ህጋዊ ሰነዶች ናቸዉ። እንገዲህ ያታያችሁ . . . ከሳሾቹ ሌቦች፤ ዳኞቹ ሌቦች ምስክሮቹ ሌቦች፤ ማስረጃዉም በሌብነት የተሰበሰበ ማስረጃ ነዉ . . . “እዛዉ ሞላ እዛዉ ፈላ” . . . እንደዚህ ነዉ የወያኔ ነገር … ሁሉም ነገር በሌብነት!
ባለፈዉ ቅዳሜ ወያኔ ከብዕርና ከመጽሐፍ ዉጭ እጃቸዉ ሌላ ምንም ነገር ጨብጦ የማያዉቀዉን ነፃነትና ፍትህ ናፋቂ ወጣቶች ወራሪ ጠላትን ለማጥቃት በሰለጠኑ የልዩ ኮማንዶ ኃይሎች ሲደብድብ ዉሏል። ሴቶች እህቶቻችንን ባዕዳን አረቦች ከሚያድርሱባቸዉ የአካልና የሂሊና ጉዳት እጅግ በጣም በከፋ መልኩ ተድብድበዋል፤ ክብራቸዉንና ሰብእናቸዉን በሚያንቋሽሽ ስድብ ተሰድበዋል። ከሁሉም የሚያሳዝነዉ ወጣት ሴቶቻችን ልብሳቸዉን እንዲያወልቁ ተደርገዉ በዉስጥ ሱሪያቸዉ ብቻ ጭቃ ዉስጥ እንዲንከባሉ ተደርገዋል። በቀጥታ ከዲስ አበባ በደረሰኝ መረጃ መሠረት የወያኔ ደነዝ አግአዚ ቅልቦች በ1997ቱ ምርጫ ማግስት በግልጽ የነገሩንን ቃል አሁንም በማያሻማ መልኩ አስረዉ እየደበደቡ በሚያሰቃዩዋቸዉ የሠማያዊ ፓርቲ አባላት ፊት አንደዚህ ሲሉ ደግመዉታል -
እንገዛችኋለን . . . መግዛት ብቻ ሳይሆን እንረግጣችኋለን!! ደማችንን አፍስሰንና አጥንታችንን ከስክሰን የያዝነዉን ስልጣን አሁንም እንሞትለታለን እንጂ በፍጹም አንለቅም። በሠላማዊ ትግል ስልጣን መያዝ ቀርቶ ከዛሬ በኋላ እኛ ሳንፈቅድላችሁ ከቤታችሁም አትወጡም። ስለህግ አታዉሩ ህግ ማለት እኛ ነን።
ዉድ ኢትዮጵያዉያን ለወያኔ ጅላጅሎችና ጋጠወጦች የማንገዛና የማንረገጥ መሆናችንን ብቻ ሳይሆን ታቦት ተሸክመዉ እባካችሁ ማሩን ብለዉ እስኪለምኑን ድረስ መርገጥ ማለት ምን ማለት መሆኑን ማሳየት የምንችል መሆናችንን በተግባር ማሳየት አለብን። ለአገራቸን ግድ ከሌላቸዉ፤ ታሪካችንን ከናቁና ለሰብዕናችንና በተለይም ለሴት እህቶቻችን ክብር ከሌላቸዉ እኛስ እነዚህን አዉሬዎች ለምን መታገስ አለብን፤ ለምን መሸከም አለብን ለምንስ እነሱ አድርጉ የሚሉንን ማድረግ አለብን? የታለ ያ ባርነትን የሚጸየፈዉ ኢትዮጵያዊታችን? የታለ ያ ጥቃትን በፍጹም የማይቀበለዉ ኢትዮጵያዊ ወኔያችን? የታለ ያ “እታለም” ስትደፈር ዱር ቤቴ ብሎ የሚሰደደዉ ኢትዮጵያዊ ማንነታችን? የታለ ያ በ1970ዎቹ የትግል ጓዱ በደርግ ባንዳዎች እጅ እንዳይወድቅ ሲል ብቻ ፖታሲየም ሳይናይድ እየቃመ የሞትን ፅዋ የጨለጠዉ ኢትዮጵያዊ ጅግንነታችን. . . የታለ? . . .የታለ? . . .የታለ? የወያኔ ዘረኞች ረግጠዉ ሊገዙን ሞተዋል፤ ዛሬም ይህ ረጋጭ ስርአታቸዉ እንዲቀጥል ለመሞት ቆርጠዋል? እኛስ ምነዉ ላለመረገጥ፤ ላለመገዛትና እህቶቻችንና
ወንድሞቻችን በዘረኞች እንዳይገደሉ ስንል የማንሞተዉ ለምንድነዉ? ጎበዝ እኔ አልሞትም ብንልም በቁማችን ሞተናልኮ፤ አንዱኑ በክብር እንሙትና ለወገኖቻችንና ለአገራችን ቤዛ እንሁን አንጂ!
የኢትዮጵያ ህዝብ ህግ አክባሪ ህዝብ ነዉ፤ ሆኖም ወያኔ የራሱን ህገመንግስት ጥሶ በህግ ያልተገደበ ኃይል ሲጠቀም ወይም ህጉን የጻፈዉ አካል እራሱ ያላከበረዉን ህግ ማክበር ሞኝነትና እራስን ለጥቃት ማጋላጥ እንጂ ህግ አክባሪነት አይደለም። እኛ ኢትዮጵያዉያን ከበስተጀርባዉ የማስፈጸሚያ ኃይል የሌለዉ ህግ እንደማይጠቅመን ሁሉ ህግ የማይገዛዉ ልቅ የሆነ ኃይልም ይጎዳናል እንጂ በፍጹም አይጠቅመንም። ስለዚህ እንደ አገርና እንደ ህዝብ መቀጠል ከፈለግን በህግ ያልተገደበ ኃይል የጨበጡ የወያኔ ዘረኞችን ወይ ህግ እንዲገዛቸዉ ማስገደድ አለዚያም ማስወገድ አለብን። በህግ አክባሪነትና በስርአተልበኝነት መካከል ምንም አይነት ማመቻመች ወይም ድርድር ሊኖር አይገባም።
ከዉጭ ራቅ ብሎ ለተመለከተዉ የወያኔ አገዛዝ ሽብርተኝንትን ለማጥፋት ወይም ለመቆጣጠር ከአቅሙ በላይ ሽር ጉድ ሲል ይታያል፤ ነገሩ “ላም ባልዋለችበት ኩበት ለቀማ” ሆነ እንጂ ወያኔ ሽብርተኝነት ከኢትዮጵያ መጥፋቱን ለማረጋገጥ ከፈለገ ማድረግ ያለበት ነገር አንድ ብቻ ነዉ፤ እሱም ሳይዉል ሳይድር ዛሬዉኑ የኢትዮጵያን ህዝብ ማሸበሩን ማቆም ነዉ። ሽብር እየፈጠሩ የአገርን ሠላምና ጸጥታ አስከብራሁ ማለት የለየለት ምግባረብልሹነት የመሆኑን ያክል ህዝብን በመግደል የተካነ መንግስትን ምነዉ ዝም አልክ ግደል እንጂ ብሎ መማጸንም ምግባረብልሹነት ብቻ ሳይሆን አማኑኤል የሚያስኬድ የዕምሮ በሽታ ነዉ። በዚህ አጋጣሚ የሠማያዊ ፓርቲ መሪዎችን፤ አባላትንና ደጋፊዎችን ትክክለኛዉን ሠላማዊ ትግል አሳይታችሁኛልና ባርኔጣዬን አንስቼ ለእናንተ ያለኘን አድናቆት መግለጽ እወዳለሁ። የቆማችሁለትን የፍትህ፤ የነጻነት፤ የዲሞክራሲና የእኩልነት እሴቶች እንደ ጦር የሚፈሩ ጉግማንጉጎች በሚወስዱት የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ ተደናግጣችሁ ከቆማችሁለት ትክክለኛ አላማ ወደ ኋላ እንደማትሉ እርግጠኛ ነኝ። እዉነትና የእትዮጳያ ህዝብ ከእናንተ ጋር ነዉና ማሸነፋችን የተረጋጋጠ ነዉ . . . ኑ ተነሱ የወያኔን ሽብርተኝነት አብረን እንዋጋ!
ebini23@yahoo.com
የአራተኛው የበይነመረብ ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ –“ኢትዮጵያዊ ሕልም፤ ኑ አብረን እናልም!”
ዞን 9 ኢ-መደበኛ የአራማጆች እና የጦማሪያን ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ማኅበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ የተለየ እና ወገናዊ ያልሆነ ተረክ ለመፍጠር እየሰራ የሚገኝ የወጣቶች ስብስብ ነው፡፡ ይህንን የምናደርግበት ዋና አላማ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገሪቷ ጉዳይ ያገባኛል ብለው ውይይት የማድረግ ባህል እንዲያሳድጉ በማድረግ ሀገሪቷን በሁሉም መስኮች ወደተሻ ለደረጃ የሚያደርሱ ሃሳቦች እንዲወለዱ ለማመቻቸት ነው፡፡
የተከበራችሁ የዞን9 ነዋሪዎች፣ በ2005 ዓ.ም ሊደረጉ ከታቀዱት አራት የበይነ መረብ ዘመቻዎች አራተኛው እና የመጨረሻው ዘመቻ ነገ ሐሙስ ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም እስከ ቅዳሜ ጳጉሜን 2 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል፡፡ አራተኛው ዘመቻ ‹‹#ኢትዮጵያዊ_ሕልም፤ ኑ አብረን እናልም!›› በሚል ርዕስ መላው ኢትዮጵያውያንን ኢትዮጵያ ሆና ማየት የሚፈልጉትን እና እዚያ ለመድረስ መደረግ አለበት የሚሉትን የሚያካፍሉበት ይሆናል፡፡
የረጅም ታሪክ፣ የውብ ባሕል እና ማንነቶች ባለቤት በሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ ዜጎቿ እርስ በርስ ተስማምተው እና ሁሉንም ዕኩል ባሳተፈ መልኩ ሀገሪቷን ለመገንባት ከሚያስችሉት ግብዓቶች መሐከል የጋራ ሕልም መኖሩ ዋነኛው ነው፡፡ ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ አራተኛው የበይነመረብ ዘመቻ ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያ ያላቸውን የወደፊት ተስፋ እንዲጋሩ መድረክ ለመፍጠር ይጥራል፡፡
የዘመቻው ዋና ዓላማዎችም፤ ሁሉንም አካታች፣ ለሁሉም ምቹ፣ ለሁሉም ዕኩል ዕድል የምትሰጥ ኢትዮጵያን ለማመለካከት፣ የቋንቋ እና ባሕላዊ ኅብርን አስፈላጊነት እና ጥቅም ለማመላከት፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፍትሕን ለማምጣት የሚበጁ አመለካከቶችን ለማስረጽ፣ ሃይማኖታዊ መቻቻልን ለመስበክ እና በተለይም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊኖርባት የሚፈልጋት፣ ተሰዶ የማይወጣባት፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ዕኩል የሚታዩባት፣ የሚጠቀሙባት እና የሚጠቅሟት ኢትዮጵያን ማለም እንዲቻል ማድረግ ይሆናሉ፡፡
ዘመቻው በዋነኛነት የሚካሄደው ‹‹ፌስቡክ›› እና ‹‹ትዊተርን›› በመጠቀም ይሆናል፡፡ ዜጎች ለሀገሪቷ ያላቸውን ሕልም በተመለከተ እራሳቸውን እንዲጠይቁ እና እንዲወያዩ የሚያስችሉ የተለያዩ ጽሑፎች በጦማራችን ይወጣሉ፡፡ በሁለቱ ማኅበራዊ አውታሮች ላይ ለዚሁ ዘመቻ ሲባል የተዘጋጁ አጫጭር ጽሑፎች ይሰራጫሉ፡፡ ዘመቻውን የሚመለከት ‹ባነር› ተዘጋጅቶ ዘመቻው በሚቆይባቸው ቀናት የተለያዩ ፕሮፋይል ምስሎችም ተዘጋጅተው የሽፋን ምስል እና የፕሮፋይል ፎቶ ይሆናሉ፡፡
ኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጎቿ ምቹ፣ ሁሉም ዜጎቿ ካለምንም የጥላቻ ስሜት እርስ በርስ ተደጋግፈው ሰብኣዊና ቁሳዊ የሀገር ግንባታ ላይ ብቻ የሚያተኩርበት እና የበለጠ የምታኮራ ሀገር ሆና ማየት የምትፈልጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በዚህ ዘመቻ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ሕልማችሁን እንድታጋሩ እና የሌሎችን ሕልም እንድትጋሩ እንጋብዛለን፡፡
ስለሚያገባን እንጦምራለን!!!
ዞን9
Press Release for the Fourth Online Campaign “Ethiopian Dream – Let us all dream it together”
Zone9 is an informal group of young Ethiopian activists and bloggers working together to create an alternative independent narration of the socio-political conditions in Ethiopia and thereby foster public discourse that will result in emergence of ideas for the betterment of the Nation.
In an effort to meet our objectives, we have conducted three different online campaigns that we believe have informed citizens and called for good governance. The fourth and last of the Ethiopian year 2005 campaign will be held under the motto “Ethiopian Dream – Let us all dream it together” between 5th-7th of September, 2013.
Our country Ethiopia is home of rich history, beautiful cultures and identities. Having and recognizing our differences, the presence of an all-inclusive shared national dream is a crucial element in the nation building effort. It is in this view that the 4th online campaign will try to create a stage for all Ethiopians to envision a better Ethiopia.
Among the major objectives of the campaign are: ·
a) to envision an all-inclusive country, equal to Ethiopians from all walk of life and background and accommodative of all cultures and identities,
b) to seek for ways that encourage and look for just economic, social and political progress in the country,
c) to preach for religious tolerance and
d) to envision Ethiopia that all Ethiopians aspire to live in and none desire to leave behind.
The campaign mainly will be held on Twitter and Facebook. Articles, that motivate citizens to question themselves and discuss their dream for the country, will be published on our blog. Status updates and tweets (containing unique hashtag #EthiopianDream is developed for the purpose) will be circulated. Banners will be developed to be used as a profile picture throughout the campaign period.
Dear all Ethiopians who want to see Ethiopia an even more proud nation that is equal to all, where citizens work together focusing on human and national development without any negative feeling for each other; you all are invited to join the campaign to sharing your dream and sharing others’ dream.
Zone9
We blog because we care!!!
ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ይቅርታው ተቀባይነት እንዳላገኘ የሚገልጽ ደብዳቤ ከፍትህ ሚኒስቴር ደረሰው
በፋኑኤል ክንፉ (ሰንደቅ ጋዜጣ) በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ለፍትህ ሚኒስቴር በይቅርታ እንዲፈታ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አለማግኘቱን ከፍትህ ሚኒስቴር በደብዳቤ እንደተገለፀላቸው ባለቤቱ አስታወቁ።
የጋዜጠኛ ውብሸት ባለቤት ወይዘሮ ብርሃኔ ተስፋዬ ለሰንደቅ እንደገለጹት፤ “ባለፈው ማክሰኞ ዕለት ከፍትህ ሚኒስቴር የይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት በተፃፈ ደብዳቤ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ፈርሞ ተረክቧል። በደብዳቤው የጠየቀው ይቅርታ እንዳልተፈቀደለት በሁለት መስመር ከመግለፁ ባለፈ ይቅርታው ለምን ተቀባይነት እንዳላገኘ የሚገልፅ ኀሳብ አልያዘም” ብለዋል።
አያይዘውም፣ “ከዚህ በፊት የአቶ ኤልያስ ክፍሌ እህት የሆኑት ወ/ሮ ሂሩት ይቅርታ ተቀባይነት ሳያገኝ ሲቀር ምክንያቱ ተገልፆ ነበር። ለውብሸት ግን ምክንያቱ አልተገለጸም። ጉዳዩን ለማወቅ ለፍትህ ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቤ ነበር። የውብሸት ደብዳቤ ወጪ ተደርጓል። አድራሻው ለማረሚያ ቤት ስለሚል እኛ ምን እንደተፃፈ አላወቅንም። ስለዚህም ማረሚያ ቤት ጠይቂ ብለውኛል። ማረሚያ ቤት የመጣው ደብዳቤ ሁለት መስመር ላይ የሰፈረ ነው። ይዘቱም የይቅርታ ጥያቄው ተቀባይነት አላገኝም የሚል ነው” ሲሉ ለሰንደቅ ገልፀዋል።
ጋዜጠኛ ውብሸት ከታሰረ ሁለት አመት ከሶስት ወራት የሞላው ሲሆን፤ የተፈረደበት የእስር መጠን አስራ አራት ዓመት ነው። ጋዜጠኛ ውብሸት የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነው።¾
Art: የዘመኑ ቀልብ ቀልባሽ ድምጻዊያኖች
በተስፋሁን ብርሃኑ
ዘመናዊ ሙዚቃ በኢትዮጵያ ከተጀመረ አራት አስርት ዓመታትን አሳልፏል፡፡ በነዚህ ዓመታት በርካታ ዘመን አይሽሬ ድምፃውያን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ነግሰውበታል ዘመን አይሽሬ ከሚባሉት ድምፃውያን በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ድምፃውያን መካከል ጥላሁን ገሠሠ፣ ሚኒሊክ ወስናቸው፣ መሀሙድ አህመድ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ አስቴር አወቀ፣ ኩኩ ሰብስቤ ከብዙ በጥቂቱ ናቸው፡፡
በቀደሙት ዓመታት የነዚህ ድምፃውያን ስራዎች በሰፊው ይደመጡ ነበር፡፡ ካሴቶቻቸውም በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትን አግኝቶ ነበር ምክንያቱ ደግሞ የግጥሙ ይዘት ዜማውና ድምፃውያኑ የእውነት ዘፋኞች በመሆናቸው ሙዚቃቸው አሁን ድረስ ከመደመጡ ባሻገር ለአዳዲስ ድምፃውያን የድምጽ ማሟሻ እየሆናቸው ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እነዚህ ድምፃውያን ለገንዘብና ለዝና ሲሉ ሳይሆን የእውነት ሙዚቃ ጠርታቸውና መርጣቸው በመሆኑም ጭምር ነው፡፡
አሁን አሁን ገና ለገና ገንዘቡንና አጋጣሚውን ያገኙ በርካታ ድምፃዎያን ነን ባዮች ግራ የገባው ግጥምና ዜማ ይዘው በመምጣታቸው በርካታ የሙዚቃ ወዳጆችን የኢትጵያ ሙዚቃ ወደየት እየሄደነው እንዲሉ እያስገደዳቸው ነው፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በአዳዲስ ድምፃውያን የሚወጡ ሙዚቃዎች አንድ ዓይነት ማለት ይቻላል ሴቶችን የሚያባብሉ፣ ብሶቶችና ‹‹የዛሬን ተደሰት የነገን ነገ ያወቃ›› የሚል መንፈስ በመያዛቸው አገር ተረካቢውን ወጣት ምንም እንዳይሰራና የጨለምተኛ አስተሳሰብ እንዲያዳብር እያደረጉት እንደሚሄዱ ምንም አያጠያይቅም፡፡ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ብዙ ሺህ ኮፒዎች ከአንድም ሁለት ጊዜ የተሸጡለትና የቀደሙትን
ዘመን አይሽሬ ድምፃውያንን ይተካል የሚባልለት ቴዲ አፍሮ /ቴዎድሮስ ካሳሁን/ ከሰባት ዓመታት በኋላ በ2004ዓ.ም ሚያዚያ ወር ላይ ካወጣው ‹‹ጥቁር ሰው›› አልበም በፊት በርካታ ነባርና አዳዲስ ድምፃውያን ስራዎቻቸውን ለአድማጭ ቢያቀርቡም የበርካታ ሙዚቃ አፍቃሪያንን ቀልብ መግዛት ሳይችሉ ቀርተው ነበር፡፡ ይህ ጥቁር ሰው› አልበም በእውነትም እጅግ ተቀዛቅዞ የነበረውን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ አነቃቅቷል ማለት ይቻላል ምክንያቱ ደግሞ ካሴቱ ከወጣ ሰዓት ጀምሮ በሰልፍ ተሽጧል በሙሉ ማለት ይቻላል ዘፈኖቹ ታሪክን፣ አንድነትን ፍቅርን በመስበኩ በእጅጉ ተወዶ ነበር ብራቮ ቴዲ፡፡
በዚህ በያዝነው 2005 ዓ.ም በርካታ አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን ስራዎቻቸውን ለአደማጭ አቅርበዋል፡፡ ነገር ግን በለስ ቀንቷቸው የአድማጮችን ቀልብ የገዙት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው በዚህ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት በቀሩት ዓመት ከተወዳጅ ድምፃውያን መካከል ጃሉድ፣ አቤል ሙሉጌታ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ጃኖ ባንድ፣ ፀጋዬ እሸቱ የቀደመውን ዜማዎቹ እንደ አዲስ ያቀረበበት እንዲሁም አሁን በሰፊው እየተደመጠ ያለው ‹‹ስጦታሽ›› የሸዋንዳኝ ሀይሉ ካሴት በእጅጉ የሙዚቃ አፍቃሪያንን ቀልብ ገዝቷል፡፡ በዚህ በያዝነው ነሐሴ ወር ሌላ አዲስ አልበም ወጥቶ በሰፊው እየተደመጠ ይገኛል፡፡ ‹ሲያ ሲያ› ፣ ‹አልችልማ› በሚባል ክሊፓቹ ከፍተኛ ዝናን ያገኘው ተመስገን ገ/እግዚሐብሄር /ተሙ/ አዲስ ካሴት አሳትሟል የመጀመሪያ ካሴቱን በራሱ ወጪ አሳትሟል፡፡ ይህ ካሴት በወጣ በአጭር ጊዜ የመጀመሪያው ህትመት በጥቂት ጊዜያት ተሽጠው በማለቃቸው በድጋሚ እንደታተመ ተነግሯል፡፡ በሌላ በኩል ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት በቀሩት በዚህ ዓመት በርካታ ነባርና አዳዲስ ድምፃውያን ስራዎቻቸውን ለአድማጭ አቅርበዋል፡፡ ካሴቶቻቸውን አውጥተው ብዙም ተደማጭነትን ካላገኙት ተወዳጅ ድምፃውያን መካከል አስቴር ከበደ፣ ነፃነት መለሰ፣ አበባ ደሳለኝ፣ ይገኙበታል፡፡ ከዓስር ዓመት በፊት የህበረተሰቡ አዲስ ካሴት ሲወጣ የመግዛት ዝንባሌው በእጅጉ ከፍተኛ ነበር ለማለት ይቻላል አሁን አሁን ግን
አዳዲስ የሚወጡ ካሴቶችን በተለያዩ ሚዲያዎችና ድህረ ገጾች ካሴቶቹ በወጡ በጥቂት ቀናት በመለቀቃቸው ምክንያትና በዘፈኖቹ ጥራት አብዛኛው ህብረተሰብ አዲስ ካሴት ገዝቶ የማዳመጥ አዝማሚያ አይስተዋልም፡፡ የህብረተሰቡ ካሴት ገዝቶ የማድመጥ ባህሉም ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰና ነጠላ ዜማዎችን ብቻ የማየትና
የማድመጥ አዝማሚያ እያሳየ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ መሀልም አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን አንዳንዶቹ ስራዎቻቸውን ማቅረባቸው አልቀረም ከነዚህ ውስጥ ታዲያ በግጥሞቹ በሳልነትና በድምፁ እስከ አሁን እየተደመጠ ያለው አቤል ሙሉጌታ አንደኛውነው፡፡
ይህ ወጣት ድምፃዊ በቤተክርስቲያን አካባቢ በማደጉ ለግጥምና ለዜማ እንዲሁም ለድምፅ ታላቅ አስተዋጽኦ እንዳደረገለት ይመሠክራል አንጋፋው ፀጋዬ እሸቱም ከቀድመው ተወደውለት ከነበሩት ሙዚቃዎቹ መካከል መርጦ በሙሉ ባንድ ያወጣው ካሴትም እጅግ ተወዶለታል፡፡ ከሰባት ዓመት በኋላ ‹‹ ስጦታሽ›› በተሰኘው አዲስ
አልበም የመጣው ሸዋንዳኝ ሀይሉ አንጀት የሚያርስ ሙዚቃ እንደሰራ ብዙ የሙዚቃ አፍቃሪያንና የሙዚቃ ባለሙያዎች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ በዚህ አልበም ውስጥ በርካታ ስመጥር ገጣሚያን የተሳተፉበት ሲሆን እንደከዚህ ቀደሙ የቴዲ አፍሮ ግጥም በአልበሙ ተካቷል፡፡ ወጣቱ ድምፃዊ ተመስገን ገ/እግዚሐብሄር
ተሙ ሌላው 2005 ዓ.ምትን ካደመቁት ድምፃውያን መካከል አንዱ ነው ይህ ወጣት ድምፃዊ በሦስት ነጠላ ዜማዎቹ የብዙ ሙዚቃ አፍቃሪያንን ቀልብ ገዝቶ ቆይቶ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በአዲስ አልበም ብቃቱን አሳይቷል፡፡ ካሴቱ በወጣ በጥቂት ቀናት ለሁለተኛ ጊዜ የታተመለት ይህ ድምፃዊ ሙሉ የካሴቱን ወጪ በራሱ ማሳተሙ ለሙዚቃው የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን አስመስክሮለታል ይህን ካሴት በርካታ አቀናባሪዎች የሰሩት ሲሆን ማስተሩን ታዋቂው አበጋዝ ሺዌታ ሰርቶለታል፡፡ በ2005 ዓ.ም እጅግ ካሴቶቻቸው የተደመጠላቸው ጃሉድ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ፀጋዬ እሸቱ፣ ሸዋንዳኝ ሀይሉ እንዲሁም ተመስገን ገ/እግዚሐብሄር ነበሩ፡፡ በሚቀጥለው ዓመት በርካታ አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን ስራዎቻቸውን ጨርሰው ለማውጣት በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡
ኤርያልን የገደለው!!!! ………
(ቴዲ ከአትላንታ)
ኤርያል ካስትሮ ከአስር ዓመት በፊት ሶስት አሜሪካውያን ወጣት ሴቶችን አፍኖ ቤቱ አስቀመጠ። ለ 10 ዓመት ያህልም የፈለገውን እያደረገ ሲያሰቃያቸው ኖረ። ዋጋ የማይተመንለትን ወጣትነታቸውን ወሰደባቸው (ሰረቃቸው)፣ በዚያ ጨለማ በምድር ቤቱ ውስጥ አስቀምጧቸው አስር ዓመት ያህል ሲቆዩ ፣ እንወጣለን ብሎ ማሰብ ረስተው ነበር። ቦ ጊዜ ለኩሉ (ለሁሉም ጊዜ አለውና) አንድ የተመረጠች ቀን ምክንያት ተፈጥሮ ነጻ ወጡ።
ከዚያ ኤርያል ካስትሮ ተያዘ፣ አሜሪካም የቀረውም ዓለም ጉድ አለ ! ጨካኙ ካስትሮ ፍርድ ቤት ቀረበ፣ የገዛ ወንድሞቹና ልጁ ሳይቀሩ አይንህን ላፈር አሉት፣ የሰው ዓይንና ርግማን ሳይገድለው ቀረና፣ ፍርድ ቤት ቀርበ ውሳኔ ተሰጠው፣ የፍርድ ቤቱም ውሳኔ – ሞትን አስቀረና ዕድሜ ይፍታህ ፈረደበት። እዚያም ሞትን አመለጠ። ከዚያ እስር ቤት ገባና የ እስር ኑሮውን ሀ ብሎ ጀመረ። ለካ ከዚህ ሁሉ ከውጭ ሊመጣ ይችል ከነበረው የሞት ፍርድ ያምልጥ እንጂ፣ ህሊናው ፈርዶበት ነበር። ከሁሉም የህሊናው ፍርድ፣ ጸጸቱ፣ የጥፋተኝነት ስሜቱ፣ የበደለኝነት ግለቱ አላስቀምጥ ቢለው …..፣ የ እስር ቤት ምግብ እየበላ፣ ቴሌቪዥን እያየና ካርታ እየተጫወተ መኖር ሲችል ዛሬ ንጋት ላይ ራሱን አንቆ የራሱን ህይወት አጠፋ ተባለ።
…. በምንሰራው ግፍና በደል ከሌላው ዓለም ፍርድ እናመልጥ ይሆናል፣ ከራስ ህሊና ግን የት እናመልጣለን? ሰዎች ላይ ግፍና በደል ሰርተን ፣ አገር በመቀየር ፣ በገንዘብ ፍርድ በመግዛት፣ ስማችንን በመቀየር፣ በትልቅ ግንብ በመከለል የምናመልጥ ይመስለን ይሆናል፣ ትልቁ ፈራጅ ህሊናችንን ግን የትም አናመልጠውም። በደል፣ ግፍ፣ ተንኮል፣ ምቀኝነት …. ይቅርብን። ነገ የሚጸጸተንን ዛሬ ለምን እናደርጋለን ?
ኑሮ በካንጋሮ ምድር(፪)
“ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ኦሮሞ ሙስሊም ይሆናል የሚል ግምት አለኝ” – የፓርላማው አባል አቶ ግርማ ሰይፉ
ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ አባል የሆኑት የተከበሩ ግርማ ሰይፉ ከሎሚ መጽሔት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አውግተዋል፡፡ ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎች ግንዛቤ እንደወረደ አስተናግዳዋለች።
ሎሚ፡- የዘንድሮው ፓርላማ ምን ይመስል ነበር;
ግርማ፡- ባለፈው አንድ ጋዜጣ ጠይቆኝ ነበረ፤ እንዴት ነበር ሲለኝ አሠልቺ ነው ስለው…እንዴት እንደዚህ ይላሉ ከሰለቸዎ ለምን ለቀው አይወጡም የሚል አስተያየት ሰምቼ ነበር፡፡ እንዲህ እያሉ ቅሬታ የሚያቀርቡ ሰዎች ለምን ጥለውት አይወጡም? ከሰለቻቸው አዛ ቁጭ ብለው ደሞዝ ይበላሉ? የሚል ነገር አለ፡፡ የኔ አስተሳሰብ ግን ሌላ ነው፡፡ በእንደዚህ አይነት አሠልቺ ሁኔታም ቢሆን ነጥብ ማስያዝ የምንችልበትን ስራ መስራት አለብን፡፡ እኔ አሠልቺ ነው ያልኩበት ምክንያት፣ ኢህአዴግን አውቀኸው ገብተህ ምንም ነገር እንደማይመጣ…ለምሣሌ አዋጅ ሲቀርብ እንደሚፀድቅ ታውቃለህ፤ አዋጁ ላይ የኔ የግሌ አስተያየቶች አሉ፡፡ እነዚህን አስተያየቶች ይዘህ ሄደህ ለመቀየር የሚያስችል አቅም አለመኖሩን ስታይ ትሰላቻለህ፡፡ ይህን ለመግለፅ ነው አሰልቺ ነው ያልኩት፡፡ ሦስቱም አመታት የመጡ አዋጆች በሙሉ የሚፀድቁበት ነበር፡፡ በዚህ አመት በነበረው ፓርላማ፣ ሀሣቦች መነሣት ጀምረው ነበር፡፡ በቀረቡት ጉዳዮች ላይ ሣይሆን እንዲሁ ውይይቱን ሞቅ ደመቅ የማድረግ ሁኔታ ነበር፡፡ ከዛ በፊት ጠያቂው እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ ይሄ ብቻ አይደለም፤ እነሱም አንዳንድ ለታሪክ የሚሆኑ ነገሮች እያስመዘገቡ መሄድ ጀምረው ነበር፡፡ እንደዚህ አይነት ነገሮች ይመዘገባሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች ልዩ ያደርጉታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በፓርላማው መዝጊያ አካባቢ አንድ የተወካዮች ም/ቤት አባል ያለመከሰስ መብት ለማንሣት የተደረገው ነገር “አስቆጭ” ነበር፡፡ እና ‹‹እንዳይከሰስ›› የሚለውን ነገር አስተካክለው እንዲመጡ፣ እንደዛ ካልሆነ እንዳይሆን ብለው ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞ የተነሣበት ሁኔታ ነበር፡፡ በማግስቱ ባልታወቀና ባልተለመደ ሁኔታ ተገልብጦ ሌላ ነገር ተፈጠረ፡፡ ለምን ተከሰሱ ለምን እንደዚህ ሆኑ አይደለም፡፡ ፖለቲካው ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅና የሚቆይ ነው፡፡ አንዳንድ ትንተና የሚሰጡ ሰዎች አሉ፡፡ ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ በስራ አስፈፃሚ ደረጃ እኩል ነው፡፡ በምክር ቤት ደረጃ ግን እኩል አይደለም፡፡ ስለዚህ እኩል በሆኑበት የስራ አስፈፃሚ ደረጃ የሚወሰነው ውሣኔ፣ በም/ቤቱ እኩል ያልሆነ ወንበር ያላቸው ሰዎች መወሰን አለባቸው የሚለው ነገር በትክክልም የህገ-መንግስትና የሕዝብ ውክልናን ይዘው ምክር ቤት የገቡትን ሰዎችን የሚጐዳ ነው፡፡ ባላቸው ድምፅ እኩል መልስ የማይሰጡበት ስለሚሆን ማለት ነው፡፡ እነዚህ የዚህ አመት የፓርላማ ጨዋታዎች ነበሩ፡፡
ሎሚ፡- ከጠ/ሚ መለስ ሞት በኋላ ፓርላማው መቀዝቀዝ ታይቶበታል ይላሉ;
ግርማ፡- መቀዛቀዝ ነው መነቃቃት…;
ሎሚ፡- እርስዎ ቢመልሱት አይሻልም?…
ግርማ፡- ጠ/ሚኒስትሩ ከሞቱ በኋላ ፓርላማው ተነቃቅቷል የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ከሞቱ በኋላ ፓርላማው ተኝቷል የሚሉም አሉ፡፡ ተፋዟል የሚሉም እንዲሁ አሉ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ይሰጧቸው የነበሩ ትንሽ “ድምቀት” መሳይ መልሶች አንዳንዴ ፓርላማውን የሚያስቁ ወይም ደግሞ የሚያሸማቅቁ ነበሩ፡፡ ግን በሙሉ ልብና ስልጣን ባለመኖራቸው ተቀዛቅዟል የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ ሁለተኛው ቡድን ደግሞ ጠ/ሚ መለስ ከሞቱ በኋላ የፓርላማው አባላት የተለያዩ ሀሣቦችን በስፋት የማንሸርሸር አዝማሚያ ታይቶባቸዋል ይላል፡፡ እውነቱን ለመናገር በመለስ ጊዜ የስራ አስፈፃሚ አካሎቹ ትንሽ ሸምቀቅ ብሎ የመምጣት ሁኔታ ይታይባቸው ስለነበር አሁን ተነቃቅቷል የሚል ነገር አለ፡፡ ለኔ ሁለቱም ትርጉም የላቸውም፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ መጥተው ደመ ሞቃት የሆነ መልሣቸውን የሚናገሩበት ነገር አለመኖሩ ለኔ የተለየ አይደለም፡፡ “ለኔ የቀረብኝ ነገር ብዬ የማስበው ነገር የለም፡፡” የምጠብቀው ነገር ስላልሆነ ማለት ነው፡፡ እኔ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር የምጠብቀው በእውነት የሚመጥን፣ ረጋ ያለ፣ ነጥብ ያለው መልስ እንጂ ተረት ተረት እያነሱ፣ የፈለጉትን እያሉ በተለይ ደግሞ ለልጆችም ጭምር የማይመጥን ቃላት እንዲናገሩ አልፈልግም፡፡ ከዚህ አንፃር የጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሣለኝን እመርጣለሁ፡፡ ያው እሣቸውም ሲናገሩ የሚፈልጉት ነገር ያለ ቢመስልም፣ እሱ እንዲታረም እየጠየቅኩ ቁጥብነታቸውንን ነው የምወደው፡፡ ፓርላማው ተቀዛቅዟል የሚለው ብዙም ትኩረት አይሰጠኝም፡፡ መሟሟቁ ትርጉም ከሌለው ተጠያቂነትን የማያመጣ ከሆነ ቢቀዛቀዝስ?…ፓርላማ ዋና ስራው የሕዝብን ተጠያቂነት ማምጣት ነው፡፡ የሕዝብ ወኪል የሆነ ፓርላማ ፈፃሚ አካሎችን መጠየቅ አለበት፡፡ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ያጠፉ ሰዎች አይ ምንም አይደለም እየተባሉ የሚታለፉበት ሁኔታ መኖር የለበትም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እርምጃ መውሰድ እስካልቻለ ድረስ ሁሉም ጥያቄ ጠይቆ ቢወጣ፣ ምንም ለውጥ አልመጣም፡፡ እኔም አንዱ ሆኜ እጠይቃለሁ፡፡ እነሱም 300 ሆነው ጥያቄ ጠይቀው ለውጥ የማይመጣ ከሆነ ምን ትርጉም ይኖረዋል? ስለዚህ አንድ እኔ እበቃ ነበር፡፡ ፓርላማው የሕዝብ ውክልና የሚኖረውው፣ ትክክል የሚሆነውም ተጠያቂነት ሲኖረው ብቻ ነው፡፡ እያንደንዳችን መታገል አለብን፡፡ በፀሎት ከሆነ በፀሎት፣ ሌላ መንገድም ካለ ደግሞ ሌላ መንገዶችን እየተጠቀሙ ፓርላማው በሚቀጥለው የተሻለ እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች ልንሰራ የሚገባን ይሄን ነው፡፡ አሁን ባለው ፓርላማ ግን ይሄ ይሻሻላል ብዬ አልጠብቅም፡፡
ሎሚ፡- በርግጥ ለብቻዎ ፓርላማ መግባትዎ የፈጠረው ተፅዕኖ አለ;
ግርማ፡- ምን ዓይነት ተፅዕኖ;
ሎሚ፡- ለብቻዎ ስለገቡ የተፈጠረ ነገር አለ;
ግርማ፡- እኔ ምንም እንዲፈጠር አይደለም ፓርላማ የገባሁት፡፡ ምክር ቤቶች ሁለት ዋና ዋና ተግባራት አላቸው፡፡ ህግ ማውጣት፣ አስፈፃሚ አካላትን መቆጣጠር ነው፡፡ የነዚህ ሁለቱ ስራዎች ሕግ በማውጣት አስፈፃሚ አካላትን መቆጣጠር ነው፡፡ ህግ በማውጣቱ ረገድ መቶም ሆነን ብንገባ ህግ የማውጣት ስልጣን የሚኖረው አብላጫ መቀመጫ የያዘው ነው፡፡ ግን ስምምነት ይደረጋል፡፡ ሌሎቹም ቢሆኑ ድምፃቸው ለአብላጫው ባይደርስም እንደዚህ አይነት ነገር ያደርጋሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡ ‹‹ብሎክ ስቲንግ›› በሚታሰብበት ቦታ ነው፡፡ ይህ በሌለበት ሁኔታ በፓርላማ ውስጥ የሚገቡ ሰዎች በሕገ መንግስቱ መሠረት ተጠያቂነታቸው ለመራጩ ሕዝብ ነው የሚሆነው፡፡ በዚህ አይነት የሚመረጡ ቢሆን ኖሮ እኔ ጥሩ ሀሣብ ባቀርብ ለጥሩ ሀሣብ ይገዙና እዛ ውስጥ ያሉ ሰዎች ይመረጣሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ተፅዕኖ አሣድሪያለሁ ብዬ ላስብ እችላለሁ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ኢህአዴግ ድምፃችንን የመዝጋት ሁኔታ ነው የሚጠቀመው፡፡ የፓርቲውን ብቻ አይደለም፤ የአጋሮቹን ስብስብ ጭምር ነው የሚጠቀምበት፡፡ ስለዚህ ከዚህ አንፃር ለውጥ አመጣለሁ ብዬ አስቤ አይደለም የገባሁት፡፡ ያመጡት ሁሉ ነው የሚፀድቅላቸው፡፡ ፓርላማው 15 ቋሚ ኮሚቴዎች አሉት፡፡ ከነዚህ 15 ቋሚ ኮሚቴዎች ውስጥ እኔ ልሣተፍ የምችለው አንድ ቋሚ ኮሚቴ ውስጥ ነው፡፡ የምሠራበት ቋሚ ኮሚቲ ውስጥ 16 ሰዎች አሉ፡፡ አንድ ነኝ፤ ስለዚህ እዚህም ውስጥ በድምፅ ብልጫም ይሁን… በእውነቱ እኛ ድምፅ ሰጥተን ስለማናውቅ አብዛኛው በስምምነት የሚያልፍ ነው፡፡ ስለዚህ ይሄ ነው የሚባል ተፅዕኖ አመጣለሁ ብዬ ገምቼ አላውቅም፡፡ በዋነኝነት የኔ ስራ ኢህአዴግ አንድ ሕዝብን የሚመለከት ጉዳይ በሚያመጣበት ጊዜ፣ የሕዝብ ስሜት ይሄነው ብዬ ይኸኛውን ነገር ለማሣየት ነው፡፡ አላየንም ነበር እንዳይሉ፤ አልሰማንም ነበር እንዳይሉ ማለት ነው፡፡ ሰምተው በራሣቸው አንግል እንደወሰኑ እንዲያውቁት ነው ፓርላማ የገባሁት፡፡ ከዚህ አንፃር ተሣክቶልኛል፡፡ በታሪክ ውስጥ ሊመዘገቡ የሚችሉ ኢህአዴግ እየሰማ አውቆ ሳያስተካክላቸው ያወጣቸው አዋጆች አሉ፡፡ እንግዲህ የታሪክ ፍርድ ነው፡፡ ተፅዕኖውም የሚለካው ያኔ ነው፡፡
ሎሚ፡- ከፕ/ር በየነ ጋር ያለዎት ልዩነት ምንድን ነው;
ግርማ፡- በእኔና ፕ/ር በየነ መካከል አለ የሚባል ልዩነት ካለ እኔ ፓርላማ መግባቴ ነው፡፡ ፓርላማ መግባቴ ልክ ነው እላለሁ፡፡ ፕ/ር በየነ ደግሞ የኔ ፓርላማ መግባት ልክ አይደለም ብለው ያምናሉ፡፡ ይሄም ልዩነት ተገቢ ነው፡፡ ችግር የለውም፡፡ ተገቢ የማይሆነው “ፓርላማ ግርማ የገባው ኢህአዴግ አስመርጦት ነው” የሚለው ነው፡፡ ኢህአዴግ አስመርጦኝ ከሆነ ፓርላማ የገባሁት፣ እሣቸው ፓርላማ ሲገቡ ኢህአዴግ አስመርጧቸው ነበር ወይ? ነው የምለው፡፡ እነዚህ ናቸው ልዩነቶቻችን፡፡ እኔ ደግሞ ለነዚህ ልዩነቶች ብዙ ጊዜ መልስ ሰጥቼ አላውቅም ነበርና በጣም ሲደጋገም መልስ መስጠት በነበረብኝ ጊዜ መልስ ሰጥቻለሁ፡፡ እንጂ ሌላ የሀሣብ ልዩነት የለንም፡፡ ፓርላማ መግባት አለብኝና ፓርላማ መግባት የለብኝም በሚለው ልዩነት እከራከራለሁ፡፡ ችግር የለብኝም፡፡ ያለስምህ ስም ሲሰጡህ ግን ትክክል አይደለም፡፡ የዛኔ ነው ፓርላማ የገባሁት በኢህአዴግ ድራማ አይደለም ያልኩት፡፡ ኢህአዴግ ብዙ ድራማ ይሰራል፡፡ ይህንን ድራማ ግን አልሰራም ስላቸው ማመን አለባቸው፡፡ ካለመኑ ግን እኔ የመድረክ አባል ድርጅት መሪ ነኝ፡፡ ያ ድርጅት የመድረክ አባል ነው፡፡ ስለዚህ መድረክ ውስጥ ኢህአዴግ አለ ማለት ነው፡፡ በኢህአዴግነት የሚያስፈርጀኝ መረጃ ካላቸው ለመድረክ አቅረበው ከኢህአዴግ ጋር የሁለትዮሽ ጥምረት አንፈጥርም ብለው ወይ እኔ እንድወጣ ወይ ደግሞ ያ ፓርቲ እንዲወጣ ማድረግ አለባቸው፡፡
ሎሚ፡- በአሁኑ ወቅት ከመለስ ሞት በኋለ ያለውን ኢህአዴግ እንዴት ይመለከቱታል?…እንደሚታወቀው አንደኛ አመታቸው እየተዘከረ ነው፡፡ እናም የአንድ አመት ቆይታው ምን ይመስል ነበር;
ግርማ፡- ይሄ ጥያቄ ለኢህአዴግ ለራሱ አይሻልም ነበር? ….(ሳቅ)….እንዴት ከረማችሁ ማለት ለእነሱ ነው፡፡…. ጠ/ሚኒስትሩ ከሞቱ በኋላ ኢህአዴግ ቤቱን በጣም ይቆጣጠር የነበረበት አመት ነው፡፡ ሁሉን በእጁ ጠቅልሎ ይዞ ይመራ የነበረ አባት ሲሞት የሚፈጠር ቀውስ አለ አይደል፡፡ ውይ ቢዝነሱን ማን ይምራው; ልጆቹ እንዴት ይሁኑ; የውርስ ጉዳይ እንዴት ይሁን; ኢህአዴግ እንደዛ ነው የሆነው፡፡ ቤቱን ቀጥ አድርጐ የያዘ ጥሩ አባት የነበራቸውን እና ውርሱ ይሄ ይሄ ነው ብሎ በትክክል ሣያስረክብ ድንገት የሞተባቸውን ቤተሰቦች አስብና ኢህአዴግን በዛ መልኩ ተመልከተው፡፡ በይፋ ያልወጣ ይመስላል እንጂ በውርስ በምናምና የሚጣሉበት ሁኔታ አለ፡፡ እኔ ነኝ የአባትን ‹‹ሌጋሲ›› የምወስደው፤ እኔ ነኝ ይህን የማደርገው እያሉ የሚጣሉበት ሁኔታ አለ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ኢህአዴግ እንዳለ ሆኖ ህወሓት የበኩር ልጅ በመሆኑ ብኩርናውን የሚመጥን ደረጃ ላይ አይደለም የሚገኘው፡፡ ድንገት ነው የሞቱባቸው፡፡
ሎሚ፡- የስልጣን አወቃቀሩን እንዴት ይመለከቱታል;
ግርማ፡- የፓርቲ መዋቅሩን ከዚህ በፊት በግልፅ ነው ያስቀመጥኩት፡፡ እውቀትን መሠረት አድርጐ አይደለም፡፡ ፓርርቲን መሠረት አድርጐ ነው እየተከፋፈለ ያለው፡፡ ይህንን ነው ቅድምም ያልኩህ፡፡ ‹‹ውርሱ›› በትክክል ያልተከፋፈለበት ሁኔታ አለ፡፡ በውርስ ጉዳይ ጠብ አለ፡፡ በትክክል የተከናወነ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ድሮ በኔ እምነት ጠ/ሚኒስትሩ በደንብ ጠቅላይ ነበሩ፡፡ አሁን ግን በእውነት የቡድን አመራር ነው ያለው ብዬ አምናለሁ፡፡ ይሄ የቡድን አመራር በሁሉም ስር ነው ያለው፡፡ ይሄን በቀጥታ የምታየው አዲስ አበባ ውስጥ ነው፡፡ አዲስ አበባን የሚያስተዳድረው ኃላፊነት ያለው ከንቲባ አይደለም፡፡ ኮሚቴ የሚያስተዳድርበት ሁኔታ አይነት ነው ያለውና፡፡ ያው ኮሚቴ ደግሞ በማስ (በሒሳብ) ነው የሚሰራው፡፡
ሎሚ፡- የእናንተ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎችም በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች አሉ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ዓይነት እንቅስቃሴዎች እያደረጋችሁ ነው? እንቅስቃሴዎቻችሁስ ምን ዓይነት ምላሽ እያገኙ ነው (ከኤምባሲዎች);…
ግርማ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ከኤምባሲዎች እኛ ምንም አንጠብቅም፡፡ ጉዳያቸውንም የሚከታተል ኤምባሲ መኖሩን አናውቅም፡፡ በኛ ደረጃ ሚና አላቸው ብለን አናምንም፡፡ አዎ! ያውቃሉ፡፡ ለዚህች ሀገር የሚሰሩት ነገር እንዳላቸው እናውቃለን፡፡ ከዛ ውጭ ግን ሚና አላቸው ብለን አናምንም፡፡ ከኛ አንፃር ትግል ውስጥ ሲገባ እስር እንዳለ እናውቃለን፡፡ እነዚህ ታሳሪዎች በሚታሰሩበት ጊዜ ምን እንደሚጠብቃቸው እናውቃለን፡፡ ተከታይም የሚገባው ሰው ምን እንደሚጠብቀው ያውቃል፡፡ ዋናው ስራ የእስረኞች ጉዳይ አይደለም፡፡ የፖለቲካ ጉዳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የሁላችንም እስር ቤት ሆና ባለችበት ሁኔታ ላይ ሌሎች የተወሰኑ ሰዎች እስር ቤት ውስጥ ስለገቡ የተለየ የምናደርገው እንቅስቃሴ የለም፡፡ እነዚህ ፖለቲከኞች የፖለቲካ እስረኞች መሆናቸው እንዲታወቅ፣ ያለጥፋት የታሰሩ መሆናቸው እንዲታወቅ ብዙ እንቅስቃሴዎች እናደርጋለን፡፡ በማህበራዊ ዘርፍ ደግሞ ሌላው ቀርቶ ቤተሰቦቻቸው ማህበራዊ ችግር ውስጥ እንዳይወድቁ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ እንዲቻል የሕዝብ ግንኙነት ስራዎችን እንሰራለን፡፡ ከዛ ውጭ ግን ዋናው መፍትሄ የሚገኘው እስረኞች ይፈቱ በሚል መፈክር አይደለም፡፡ አጠቃላይ የስርዓቱ፣ ስርዓት መያዝ ነው መፍትሄ የሚያመጣው ብለን ስለምናምን ነው ትግል የምናደርገው፡፡ እስረኛ የማስፈታት ትግል አናደርግም፡፡ ምናልባትም ይህን አቅጣጫ እንደ አቅጣጫም ያስቀመጠው አንዱአለም ነው ብል ስህተት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት ብርቱካን ታስራ ፖለቲካው በሙሉ ‹‹ብርቱካን ትፈታ›› እስከሚመስል ድረስ የተደረገበት ሁኔታ ነበርና ነው፡፡ አሁን ፖለቲካችንን በሙሉ አንዱአለም ይፈታ የሚል ብናደርገው አንዱአለም ከኛ ጋር ይጣላል፡፡ ስለዚህ እኛ ደግሞ አንዱአለምን ማስቀየም አንፈልግም፡፡ የአንዱአለም ትግል ስርአቱ ስርአት እንዲይዝ እንጂ የተለየ ነገር በእስረኞች ላይ እንድናደርግ አይደለም፡፡ ግን የሕግ ጉዳዮቻቸውን እንከታተላለን፡፡ ለታሪክ የሚመዘገቡ ነገሮችን ማለት ነው፡፡
ሎሚ፡- የአውሮፓ ሕብረት የሰብዓዊ መብት ተወካዮች እንዲሁም የአሜሪካ ከፍተኛ ሹማምንት (የቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደርን ጨምሮ) ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፤ እነሱን የማግኘት እድል አላጋጠማችሁም;
ግርማ፡- ያገኘናቸው ሰዎች አሉ፤ እኔ አልነበርኩኝም እንጂ፡፡
ሎሚ፡- ምን አዲስ ነገር ነበረው;
ግርማ፡- ምንም የለውም፡፡ በይፋ የሰጡት መግለጫ ነው፡፡ የተረጋገጠው ነገር ግን እኛ እስር ቤት ስንሄድ የሚደርስብን ውክቢያና እንግልት እነሱም ላይ ስልታዊ በሆነ መንገድ መከናወኑ ነው፡፡ እኛን አያምኑንም ነበር፡፡ እስረኞችን መጠየቅ ተከለከልን ስንል ውሸት ሊመስላቸው ይችላል-ውጭ ያሉ ሰዎች፡፡ አሁን ግን በትክክል በዘዴ እነሱንም እንዳይጐበኙ እንዳደረጓቸው አይተው ሄደዋልና ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ እኛ ግን ዕለት በዕለት የምናየው ነገር ነው፡፡
ሎሚ፡- እንደሚታወቀው የሙስሊሙ ጉዳይ በጣም እየሰፋ መጥቷል፣ ላለፈው አንድ አመት የነበረው ሁኔታ በሰላማዊ ተቃውሞ የተገደበ ነበር፡፡ አሁን ግን ደም የፈሰሰበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ የመንግስትን እርምጃ እንዴት ያዩታል? መፍትሔውስ ምንድን ነው ይላሉ;
ግርማ፡- መፍትሄው ውይይት ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ ሌላ መፍትሄ የለውም፡፡ በኢሳት ቴሌቭዥን አንድ ቃለ-መጠይቅ በዚህ ጉዳይ ላይ እያየሁ ነበር፡፡ ልክ እኛ እዚህ ሀገር ውስጥ የሚገጥመንን አይነት የሙስሊም መሪዎችንም የሚገጥማቸው ሁኔታ አለ፡፡ በሙስሊሙ ውስጥ ያለውን የኃይማኖት ጥያቄ ለምንድነው ወደ ሕብረተሰቡ ወስዳችሁ ፖለቲካ የማታደርጉት ተብለው ይጠይቃሉ፣ ተጠይቋል፡፡ ተመሳሳይ የሆነ ጥያቄ እኛም ጋር የመጣ አለ፡፡ ለምንድነው የሙስሊሙን ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳይ አድርጋችሁ የማታራግቡት ተብለን ተጠይቀናል፡፡ እነዚህ ሁለቱም ትክክል አይደሉም፡፡ እኛም ይህንን አጀንዳ አድርገን የፖለቲካ ስራ ለመስራት እቅድም ፕሮግራምም የለንም፡፡ በጣም ደስ ያለኝ ነገር ከነሱም በኩል ይህ ነገር የለም፡፡ ይህንን ኮረንቲ ለማገናኘት ግን ኢህአዴግ ተግቶ እየሰራ ነው፡፡ ኢህአዴግ ግን ገብተውበታል እያለ በሌለንበት ቦታ ውስጥ እያገናኘን ሰበብ መፍጠር ይፈልጋል፡፡ ከኛ አንፃር የመርህ ጉዳይ ነው፡፡ የፖለቲካ ጥያቄ በሚነሣበት ቦታ ላይ ሙስሊሞች መብታችን ተጣሰ ብለው ሀሣባቸውን ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ አንድነት በጠራው ስብሰባ ላይ ለምን ሙስሊም ተገኘ ብለው ይንጫጫሉ፡፡ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ አይደለም እንዴ; አንድነት በጠራው ስብሰባ ላይ ሙስሊም መምጣቱ እኛን ያስደስተናል፡፡ ለምን ከዚህ በፊት በብዛት የማይሣተፉ የነበሩ ሙስሊሞች አሁን መብታቸው በደንብ እየተነካ ስለሆነ በፖለቲካ ፕሮግራሞች ላይ መንቀሣቀስ ጀምረዋል፡፡ ምርጫ በመስጊድ እናድርግ ማለት ምን ስህተት አለው; በመስጊድ አይደረግም የሚለውን ክርክር እነሱ ናቸው ከመጅሊሣቸው ጋር መነጋገር ያለባቸው፡፡ መንግስት ምን አግብቶት ነው በዚህ ላይ መግለጫ የሚሰጠው፡፡ መንግስት ምን አግብቶት ነው አህባሽ፣ ሰለፊ ምናምን እያለ ማብራሪያ የሚሰጠው?…ይሄንን እነሱ ያብራሩ፤ እነሱ ይህንን እንዲያደርጉ መተው ነው፡፡ ከዚህ ቀደም አሸባሪ ድርጅት ምናምን ሲሉ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ የተወሰነ ማሻሻያ አድርገውበታል፡፡ “አክራሪ” ወደሚል መጥተዋል፡፡ አክራሪ ብለው አታክርሩ ተብሎ ለመነጋገር የሚቀል ከሆነ ወደ ቀለል ወዳለው መምጣታቸው ክፋት አለው ብዬ አላምንም፡፡ ስለዚህ አሁንም ቢሆን አክርረዋል የተባሉት ሰዎች ጋር አታክርሩ ተብለው መነጋገርና መፍትሄ ማበጀት ነው፡፡ መፍትሄው ሁሉንም ላያስደስት ይችላል፡፡ ግን መፍትሄ እያበጀንለት ነው ብለው መናጋር ቢጀምሩ አብዛኛው ሙስሊም ይሄ የመነጋገሩ ነገር ያበርደዋል፡፡ በሰላም ሶላታቸውን ሰግደው የሚመለሱበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ከዛ ውጭ አንዳንዶቹ ለምንድነው በሶላት ሰዓት ላይ ሌላ ጥያቄ የሚያቀርቡት ይላሉ፡፡ ሶላታቸውን በስርዓት ነው የሚሰግዱት፡፡ ሶላታቸው ካለቀ በኋላ ግን በአጋጣሚ የሚገናኙበት ቦታ ያ ስለሆነ መልዓክታቸውን ለማስተላለፍ ቢጠቀሙበት ጥፋቱ አይታየኝም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ፖለቲካ ርኩስ ነው ያለው ማነው; ስለዚህ መብታቸውን፣ የእምነት ጥያቄያቸውን ከመስጊድ ውጭ የት ያቅርቡ? የፖለቲካ መሪዎች ቢሮ መጥተው ነው የሚያቀርቡት; ቆይ መጂሊሱ ይለወጥ ብለው አንድነት ፓርቲ ቢሮ ቢሰበሰቡ ምንም ትርጉም የለውም? በእርግጠኝነት የምነግርህ አንድነት ፓርቲ እንደ ፓርቲ እንደዚህ አንድ አጀንዳን ይዞ እዛ ላይ ገብቶ የፖለቲካ ጉዳይ ለማድረግ አይፈልግም፡፡
ሎሚ፡- ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ከዋልታ ጋር ቃለመጠይቅ አድርገዋል፡፡ በቃለ መጠይቁ ላይ አንዳንድ ፓርቲዎችን ከሙስሊሙ ጉዳይ ጋር አያይዘው ተናግረዋል፤ ይህን እንዴት ያዩታል;
ግርማ፡- የፈለጉትን አንዳንድ ፓርቲ ሊገምቱ ይችላሉ፡፡ የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በፓርላማ ከሻዕቢያ ጋር እንደምትሰሩ ማስረጃ አለን፤ የእንትና ተላላኪ ምናምን ይሉ ነበር፡፡ የዛኔ ምን አይነት ደካማ መረጃ ነው ያላቸው ብለን ነው እንጂ የምንጠራጥራቸው ብዙም በዚህ ጉዳይ አንረበሽም፡፡ አሁንም እንደዚህ ያደርጋሉ የሚሉ ከሆነ እኛ በመርህ ነው የምንሰራው፡፡ ከመርህ ውጭ የምንሆነው ነገር የለም፡፡ ከዚህ መርህ ውጭ ሰዎች ቢጠረጥሩ፣ ሲጠራጠሩ ቢውሉ የሚደክሙት እነሱ ናቸው፡፡ ይሄ ማለት ግን እኛ ላይ እንቅፋት የለውም ማለት አይደለም፡፡ እንቅፋቶች ይፈጥራሉ፡፡ አሁን ፋንፍሌቶች እንበትናለን፤ የእለት ተእለት የፖለቲካ ስራዎች እየሰራን እያለ ፖሊሶች በየመንገዱ ላይ ይይዙህና ‹‹እናንተ አሸባሪዎች›› ምናምን ይላሉ፡፡ ቀልዴን እንዳይመስልህ፡፡ ‹‹አሸባሪዎች›› ይሉናል፡፡ በምን አይነት የፖሊስ አስተሳሰብ ውስጥ አንዳለን የሚያሣይ ነው፡፡ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት የሚለውን ፕሮግራም መጀመራችን የኢትዮጵያን የፖሊስ ተቋም እንድንታዘብ አድርጎናል፡፡ እያንዳንዱ የፖሊስ ተቋም ሕገ መንግስቱን ጥንቅቅ አድርጐ ቃል በቃል ማወቅ አለበት፡፡ ትራፊኮች ታርጋ ቁጥር ለቅመው እንደሚይዙት ፖሊሶችም ሕገ መንግስቱን ጠንቅቀው ሊያውቁ ይገባል፡፡ ግን ኮከብ ትከሻቸው ላይ ያደረጉ በሙሉ የፀረ ሽብር ህጉን ለምን ትቃወማላችሁ? ‹‹አሸባሪዎች›› ናችሁ ይሉናል፡፡ ይሄማ ህገ መንግስቱን መናድ ነው ይሉናል፡፡ ተመልከት፤ ህገ መንግስት እንዴት እንደሚናድ እንኳን አያውቁም፡፡ ሎሚ፡- በመስከረም ወር የፓርላማው የመጀመሪያ ስራ ርዕሰ ብሔር መምረጥ ነው፡፡ ሦስት ሰዎች ለፕሬዚዳንትነት ተገምተዋል፡፡ አንደኛ ዶ/ር አሸብር፣ ሁለተኛ ኃይሌ ገ/ስላሴ እንዲሁም ሶሎሜ ታደሰ፤ ይሄን እንዴት ያዩታል? በተለይ ኃይሌ እንደሚሆን ነው በርግጠኝነት እየተነገረ ያለው፡፡ እርስዎ በፓላማ ካለዎት ቆይታ ከሚያዩት የኢህአዴግ አሠራር ምን ይገምታሉ;
ግርማ፡- ዶ/ር አሸብር አይሆኑም፡፡ እኔ ድሮም ይሆናል የሚል ግምት የለኝም፡፡ በጣም ብዙ ሰዎች ናቸው በእሱ ጉዳይ የሚሳሳቱት፡፡ የአሁኑ ፕሬዚዳንት የግል ተወዳዳሪ ስለነበሩ አሁን ያለው የግል ተወዳዳሪ ዶ/ር አሸብር ስለሆነ፣ በዚህ ምክንያት እሱ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ይንጸባረቃል፡፡ ዶ/ር አሸብር ፕሬዚዳንት አይሆንም ስልህ እሱ አይፈልግም ማለት አይደለም፡፡ እሱ ሊፈለግ ይችላል፤ ግን አይሆንም፡፡ ቅድም እንዳልኩህ የስልጣን አወቃቀሩ ፓርቲን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ስለዚህ ከደቡብ የሚሆንበት ሁኔታ ሚከብድ ነው፡፡ ጠ/ሚኒስትሩም ከደቡብ፣ ፕሬዚዳንቱም ከደቡብ ሲሆን የኃይል ሚዛኑ ወደታች ይወርዳል፡፡ በዚህ ቀመር ስለሚሰሩ ዶ/ር አሸብር የሚሆን አይመስለኝም፡፡ ይሄ የኔ ግምት ነው፡፡ ኃይሌ የመሆን ዕድል ይኖረዋል፡፡ ኃይሌ ለዚህች ሀገር ከዚህ የበለጠ ሊሣተፍ የሚችልበት ሌላ ቦታዎች አሉት፡፡ ባለፈው አንድ ጋዜጣ ላይ ሪዞልቱን ቢያስተዳድር ይሻላል ብሏል፡፡….አዎ ሪዞልት ማስተዳደር የበለጠ ለዚህች ሀገር የሚጠቅም ስራ ነው፡፡ ወይም በአመት አንድ ማራቶን የበለጠ ሊሆን ይችላል፡፡ በሚቀጥለው ምርጫ ተወዳድሬ ምክር ቤት እገባለሁ ብሏል፡፡ ኃይሌ ፕሬዚዳንት ከሆነ በፕሮቶኮል ታጥሮ ምንም ስራ አይሰራም ማለት ነው፡፡ በዶ/ር ነጋሶ ጊዜ አንበሳ ጊቢ ነበር የሚባለው፡፡ አንበሳ ጊቢ ገብቶ ከአንበሶች ጋር ተቀምጦ ምን አይነት ሕይወት እንደሚኖር አስበው እስኪ፡፡ ለኃይሌ ይሄ አይመጥነውም፡፡ ስለሰሎሜ አስተያየት መስጠት አልፈልግም፡፡ ግን ሌላ አማራጭ ሞልቷል፡፡ ኦህዴድ ብዙ ቦታዎችን አላገኘንም ከሚለው ቅሬታው አንፃር የፕሬዚዳንትነቱ ቦታ ለኦሮሞ ሊሰጥ ይችላል የሚል ግምት አለኝ፡፡ ኦሮሞ ብቻም አይደለም፤…ፕሬዚዳንቱ የኦሮሞ ሙስሊም ሊሆን ይችላል የሚል ግምትም አለኝ፡፡ ምናለ ለአንድ ሱማሌ ቢሰጠው? ለአፋር ቢሰጠው? ለቤንሻንጉል ቢሰጠው? ከአጋር ድርጅቶች ለአንዱ ቢሰጥ ምን አለበት? ልክ ለግል ተወዳዳሪ ለግርማ ወ/ጊዮርጊስ እንደተሰጠው ከአጋር ድርጅቶች ለአንዱ ቢሰጠውስ? ግን ፖለቲካዊ አማራጭ አለው፤ ትልቁ ግምቴ ግን ፕሬዚዳንት ሊሆን የሚችለው ኦሮሞ ሙስሊም ነው፡፡
በደቡብ ኮርያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በዛሬው እለት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በ ሰውል ኣካሄዱ።
ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የማያባራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም በደቡብ ኮርያ ፕሬዚደንት ጽ/ ቤት ፊት ለፊት ፕሬስ ኮንፈረንስ በማድረግ የኮርያ መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥር ተማጽነዋል። ለ ደቡብ ኮርያ ፕሬዚደንት ፓርክ ግን-ሄ ደብዳቤም ኣስገብተዋል።
ሰልፈኞቹ ለደቡብ ኮርያ UNHCR ተወካይና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ደብዳቤዎችን ያስገቡ ሲሆን በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥሩ ተማጽነዋል።
ከሰልፈኞቹ መሃል ኣብዛኛዎቹ የዘማች ልጆች ሲሆኑ ባለፈው ጊዜ ለስልጠና መጥተው ገዢውን መንግስት በመቃወም ጥገኝነት መጠየቃቸው ኣይዘነጋም።
ዜና ከአዳማ – ፖሊስ 4 የአንድነት አባለትን በማሰር የሚበትኑትን ወረቀት ነጠቀ
በቅስቀሳ ስራ ላይ የነበሩ አራት የአንድነት ፓርቲ አባላት አዳማ ከተማ ውስጥ መታሰራቸው ታወቀ፡፡ ፖሊስ ከ5ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን ቀምቷቸዋል፡፡ ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እውቅና ተሰጣችሁ እንጂ በራሪ ወረቀት የመበተን ፍቃድ የላችሁም በሚል ዳንኤል ፈይሳ፣ደረጄ መኮንን፣አስናቀ ሸንገማና ደረጄ ክበበው የተባሉት አባላት ወረዳ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረው ከሰዓታት በኋላ መለቀቃቸውን የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት አስታውቀዋል፡፡ ከትራፊክ ፖሊስ፣ከፖሊስ፣ከደህንነት፣ከደንብ አስከባሪና ከሚሊሻ የተውጣጡ ስምንት ግለሰቦች የአንድነት አባላትን በማሰሩ ተግባር እንደተሳተፉና የተወሰኑት ደህንነቶችና ፖሊስ የድብደባ ሙከራ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በአዳማ ከተማ ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ስኬታማ የቅስቀሳ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ