Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all 13695 articles
Browse latest View live

መርዘኛ የጋዝ ጦር መሣሪያዎች

$
0
0
ሰዎች ካለፈ እጅግ መጥፎ ድርጊት ፣ እስከምን ድረስ ትምህርት ይቀስማሉ? በተለያዩ ዘመናት ያጋጠሙ ሁኔታዎችን ፤ ጦርነቶችን ፤ ወረራዎችን ፤ ውዝግቦችን ስንመረምር ፣ ሰው፤ ጭካኔ የሚያሳይባቸው መሣሪያዎች በሥነ ቴክኑኒክ ተሻሽለው ተሠርተው ከመቅረባቸው…

የኬንያ ፓርላማ በICC ስምምነት ላይ ተከራከረ

$
0
0
የኬንያ ባለስልጣናት በዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት (ICC) ክሳቸው ሊታይ ጥቂት ሳምንታት ሲቀረው፤ የሀገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኬንያ የICC መቋቋሚያ ዉል ፈራሚነቷን ታነሳ ዘንድ ትናንት ሲከራከር ውሏል።…

ኢትዮ-ቤተ እሥራኤላውያንና ኑሯቿዉ

$
0
0
በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላዉያን ባለፉት ሠላሣ ዓመታት እስራኤል ገብተዋል። ይሁንና ቤተ እሥራኤላውያኑን ከሀገሪቱ ኅብረተሰብ ጋ የማዋሀዱ ተግባር ዛሬም ትልቅ እክል ይታይበታል።…

የአሜሪካ ሴኔትና ሶርያ

$
0
0
ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ እና ከፍተኛ ባለስጣኖቻቸዉ የአሜሪካ ምክር ቤት ለፕሬዝደንቱ ሶርያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት የመፈጸም መብት እንዲሰጣቸዉ ጥያቄ ማቅረባቸዉን ቀጥለዋል።…

Amharic News 1800 UTC –ሴፕቴምበር 04, 2013

$
0
0
News, Ethiopians in America, Americana, Democracy and Women and Family…

ፖሊስ 4 የአንድነት አባላትን በአዳማ በማሰር የሚበትኑትን ወረቀት ነጠቀ

$
0
0

አዳማአንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለውን የሰላማዊ ትግል በመቀጠል የፊታችን እሁድ በአዳማ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ መጥራቱ የሚታወስ ሲሆን ለዚህ ሰላማዊ ሰልፍ መሳካት ሕዝብ እንዲያውቅ ወረቀት በመበተን እየቀሰቀሱ የሚገኙ የድርጅቱን አባላት ገዢው ፓርቲ ማዋከቡን ቀጥሏል። በዚህም መሠረት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ እንዳመለከተው በቅስቀሳ ስራ ላይ የነበሩ አራት የአንድነት ፓርቲ አባላት አዳማ ከተማ ውስጥ ታስረዋል።
ፖሊስ ከ5ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን እንደቀማቸው የገለጸው የሚሊዮኖች ድምጽ ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እውቅና ተሰጣችሁ እንጂ በራሪ ወረቀት የመበተን ፍቃድ የላችሁም በሚል
1ኛ. ዳንኤል ፈይሳ፣
2ኛ. ደረጄ መኮንን፣
3ኛ. አስናቀ ሸንገማ
4ኛ ደረጄ ክበበው የተባሉት አባላት ወረዳ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረው ከሰዓታት በኋላ መለቀቃቸውን የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት አስታውቀዋል፡፡ ከትራፊክ ፖሊስ፣ ከፖሊስ፣ ከደህንነት፣ከ ደንብ አስከባሪና ከሚሊሻ የተውጣጡ ስምንት ግለሰቦች የአንድነት አባላትን በማሰሩ ተግባር እንደተሳተፉና የተወሰኑት ደህንነቶችና ፖሊስ የድብደባ ሙከራ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በአዳማ ከተማ ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ስኬታማ የቅስቀሳ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ የሚሊዮኖች ለነፃነት እንቅስቃሴ ገልጿል።

ESAT Radio Sep 04

ሦሪያና አሜሪካ በዓለምአቀፍ መድረኮች –ሴፕቴምበር 04, 2013

$
0
0
President Obama, Syria, g20, Sweeden…

የኢትቪ ሽርፍራፊዎች (በሃብታሙ አያሌው)

$
0
0

በሃብታሙ አያሌው (የአንድነት ፓርቲ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ)

እንደ መግቢያ

Habitamu Ayalew

ሃብታሙ አያሌው

የፀረ ሽብረ አዋጅና የፓርቲዎች አቋም ሲል ወይም ኢ.ቲ.ቪ በላከው ደብዳቤ መስረት የሶስት ሰዓታት በእጅጉ የተጋጋለ ውይይት ከተካሔደ በኋላ ውይይቱ በዜና እንኳን ሳይዘገብ ከሳምንት በላይ ለሆነ ግዜ በመራዘሙ ተወያይ ፓርቲዎች በተለያየ መንገድ ቅሬታቸውን ሲገልጹ የግል ኘሬስና ማህበራዊ ገፆችም የፓርቲዎቹን ክርክር ኢቲቪ የውሀ ሽታ ሊያደርገው ይችላል ከሚለው መላምት ባሻገር በተለያየ መንገድ አገኘን ያሉትን መረጃም ሲለቅቁ ሰንብተዋል፡፡ አንዳንዶች ተቃዋሚዎች ውኃ የሚቋጥር ኃሣብ ማንሳት እንዳልቻሉ የውስጥ መረጃ አገኘን ሲሉ ሌሎችም በተከራካሪዎች ላይ አለ የሚሉትን የአቅም ማነስ ሳይቀር በመዘርዘር ኢህአዴግ ከውይይቱ ትርማማ ይሆናል ሲሉ ተነበዩ ከዚህ አስተሳሰብ በመጠኑ እንለያለን የሚሉም ውይይቱ ፋይዳ የለውም ኢቲቪ ቆራርጦ መቅኖ ያሳጣዋል ሲሉ ስጋታቸውን ሲገልፁ ስንብተዋል፡፡ ለፓለቲካ ነፅሮት ልዬ ተስጦ ያላቸወ በሳል ተንታኞች በበኩላቸው ኢህአዴግ ውይይት ማድረጉን ለምን መረጠ? ለምን ይህንን ወቅት መረጠ? ውይይቱ ለተቃዋማው ያለው ፋይዳ ምንድነው? አዋጁ እንዲሰረዝና በዚህም ምክንያት የታሰሩ እንዲፈቱ ከማድረግ ባሻገር ይህ አፋኝ ስርአት እንዲለወጥ የትግሉ አቅጣጫ ምን ያህል የተጠና ነው? የሚሉ በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳትና መፍትሔዎችን በማመላከት የበኩላቸወን ጥረዋል፡፡ በጥቅሉ በፀረ ሽብር አዋጁ ዙሪያ የተደረገው ክርክር ለህዝብ እይታ ከመቅረቡ አስቀድሞ አጓጊ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ የብዙዎቹ የሆነው የጋራ ስጋት የሚመነጨው ኢቲቪ በህዝብ እነት ያጣ ድርጅት ከመሆኑ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ በመሆኑ ውይይተ በስርጭት ላይ ውሎ የብዙሀኑን ቀልብ የሳበ ቢሆንም ኢቲቪ ቆርጦባችኋል? የሚለው ጥያቄ ግን አሁንም አላቋረጠም እና ኢቲቪ የሽራረፋቸውን የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ በኩል ላቀብላችሁ ወደድኩ፡፡

ከመሸራረፍ ባህሪው ያልታረመ ቢሆንም ኢቴቪ ገለታ ይደረሰው ለማለት ግን አልሰስትም፡፡ ስለ ሽብር ያወያየን አሸብር ፊሽካ ይዞ ለመዳኘት ስንፈቅድለት ያንን ክብር ትቶ ኳስ አቀባይነት፣ ሲያኘው አጥቂና ተከላካይ እየሆነ ምላስ ቦታ በመርገጡ የተሰማኝን ቅሬታ መግለፁም እውነታ ነውና ነውር የለውም፡፡

አንድ ጋዜጣና ሚዛን አልባ ሆኖ ለሚደግፈው ካራገበ፣ የማይፈልገውን ሃሳብ ከጨቆነና አንዳንዴም ሀሳብን በፈለገው መንገድ ከቆረጠ ጋዜጣኛ ሊባል የሚችልበት ምንም ምክንያት የሌለ ሲሆን በመስኩ ሊገኝ የሚገባውን ጤናማ ውጤት ሁሉ የሚያበላሽ ይሆናል፡፡

ከዚህ እረገድ የኢትቪው አሸብር ጌትነት እራሱን መፈተሽ እና ለሙያው መታመንን መምረጥ ተቀዳሚ ተግባሩ ሊያደርግ የሚገባው ይመስለኛል ይህም በማሳሰብ ሳይሆን ይልቁንም በመምከር ነው፡፡

ሽርፍራፊዎች
ኢቲቪ ለአየር ያበቃው የውይይቱ ክፍል የተቆራረጠ ሀሳብ እና የማጠቃለያ ቅደም ተከተል መዛባት ቢኖረውም ገለታ ይድረስው ለማለት አልሳሳም ያልኩበት ምክንያት አንባቢ እንደሚገነዘበው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ይህውም ቢሆን ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደማግኘት የሚያስገርም በመሆኑ ነው፡፡
1. በአቶ ሸመልስ ከማል የቀረበ አስተያየት
ፍርድ ቤትን ፓሊስን እያጣጣላችሁ በማስረጃ ተረጋግጦ ቦንብ ሊያፈነው የመንግስትን ተቋማት ሊያወድሙ ሲሉ ተይዘው በማስረጃ የተረጋገቀባቸውን ሰዎች ይፈቱ እያላችሁ፣ እንደሰማዕት ከየአደባባዩ ከመጥራትም አልፋችሁ እዚህ ሳይቀር እየደገማችሁበት ባለችሁበት ሁኔታ እናንተ እንዴት ሰላማዊ ታጋይ ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡

የተቆረጠብኝ ምላሽ እነዚህን አሸባሪዎችን ሰማዕት ማስመሰልና ማበረታታት በሙሉ አሸባሪነት ነው፡፡

እናንተ ያስራችኋቸው እኛ ጀግና ሠላማዊ የነፃነት ታጋይ የምንላቸው እና አንዷለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ፣ ሌሊሳ ኣልባና ናትናኤል መኮንን፣ አንዱአለም አያሌው አለም አቀፍ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙና የመሳሰሉትን የታሰሩት ነፃነት የሌላው የፓርቲ አገልጋይ ነው ይሞግቱት በነበረው ፍ/ቤት ነው፡፡ እንደፓርቲ ፍ/ቤት ነጻ እንዳልሆነ እናምናለን ይህም ከእኛ በላይ በመንግስት ተቋም በተደረገ ጥናት የተረጋገጠ ነው፡፡ በዚህ ታማኝና ነጻ ባልሆነ ፍ/ቤት አሸባሪ ስለታባሉ እኛ አሸባሪ አንላቸውም፡፡ ለእኛ ጀግኖች ናቸው፡፡

እነዚህ ጀግኖች ፈንጂ ሊያፈነዱ ነበር ተቋማት ሊያወድሙ ነበር የተባሉት በኢቲቪ አኬልዳማ ዶክመንተሪና በኢህአዲግ ባለስልጣናት እንጂ በፍ/ቤት የቀረበባቸው የክስ ቻርጅ እና መረጃ ይህ አይደለም ዛሬም እንደትናንቱ ህዝብ አታታሉ፡፡ በቃ የሚል ጽሁፍ ያለበት ወረቀት ፎቶ አነሳሽ፣ የወንድምህን ደህንነት፣ በስልክ አወራህ፣ ኢሚል ተጻጻፍክ ወዘተ በሚል ተልካሸ ምክንያት ከኢህአዴግ የተለየ አስተሳሰብ በመያዛቸው ምክንያት ብቻ የህሊና እስረኞች ናቸው፡፡

ይህንን ሀቅ መናገር አሸባሪነትን ማበረታታት ነው ብላችሁ ለማሸማቀቅ የምታደርጉት ሙከራ ተቀባይነት የለውም፡፡ ዛሬም ነገም በየአደባባዩ ስማቸውን እንዘክራንለ ነጻ እስኪወጡም እንታገላለን፡፡

2. አቶ ሸመልስ ከማል በሀገር ውስጥ ተከውኖአል ያሉትን የሽብር ተግባር ሲዘረዝሩ የበደኖን ጭፍጨፋ በማንሳን ኦነግ ጨፍጭፎአል ሲሉ ላቀረቡት መከራከሪያ

የተቆረጠው የእኔ ምላሽ
ብዙዎቹ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ደፍረው የማያነሱትን የበደኖ ጭፍጨፋ በማንሳትዎ አቶ ሸመልስን አመስግናለሁ፡፡ የበደኖን ጭፍጨፋ ለኦነግ በማቀበል ዘወር ማለት ግን አይቻልም፡፡ ኦነግ ከሀገር ሳይወጣ አሸባሪም ብላችሁ ሳትፈርጁት በሽግግር መንግስትነት ከህወሀት ኢህአዴግ ጋር ሀገር እየመሩ ባሉበት ወቅት የተፈፀመ ጭፍጨፋ መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ሌላው ይህንን የበደኖ ጭፍጨፋ እርስዎ በመሰሎት መንገድ ሲናገሩት ወንጀል አይደለም ከፖርቲዎ ሞራል ያሰጥዎታል፡፡ ይህንን የበደኖ ጭፍጨፋ ዘርዝሮ በመጻፍ ለእውነት በመትጋቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ክስ ተመስርቶበት ፍ/ቤት እየተመላለሰ ነው፡፡ እንግዲህ ህግ አለ የምትሉት ይህንን ነው፡፡ ለዜጋ ሳይሆን ለካድሪ የሚፈርደውን የእናንተን ህግ የምንሟገተውም ይህ ብልሹ አሰራር እንዲቀየር የህግ የበላይነት እንዲከበርና የስርአት ለውጥ እንዲመጣ እንጂ እናንተ እንደምትፈርጁን ለሁከት አይደለም፡፡
3. አቶ ጌታቸው እረዳ በአንድ ወቅት አስታውሳለሁ ሀብታሙ የማደራጃ አዋጅን ከእኔ በተሻለ ብቃት ይተነትን ነበር አሁን መንገዳችን ለየቅል ቢሆንም ሲሉ ለሰነዘሩት የትናንት አብረን ነበርን ሾርኒ …

የተቆረጠው የእኔ ምላሽ
የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለተቃዋሚ እውቅና መስጠትና ይበልጠኛል ማለት ሞታቸው ነው፡፡ አቶ ጌታቸው በዚህ መድረክ ከእኔ በተሻለ የመተንተን ብቃት አለህ ብለው ምስክርነት በመስጠትዎ አከብራለሁ አመሰግናለሁ፡፡
ነገር ግን “በእኔ እምነት ከስህተቱ የማይማረው ፈንጂ አምካኝ ብቻ ነው” ሲያመክን ከተሳሳተ ይሞታል የመማሪያ እድል የለውም እርስዎና የኢህአዴግ ባለስልጣናት እንደእኔ ከስህተት ለመማር አልረፈደባችሁም፡፡ አሰላለፋችሁም እንደእኔ ከህዝብ ጋር በማድረግ እንድትማሩ እመክራለሁ፡፡

4. አቶ ሸመልስ ከማል መንግስት ደጋግሞ ቢያሳስባችሁም ከስህተታችሁ ለመማር አልፈለጋችሁም እናንተ ህገ ወጦች ናችሁ፡፡ በማለት ቁጣ ቀላቅለው ለሰነዘሩት ዛቻ

የተቆረጠው የእኔ ምላሽ
አቶ ሸመልስ ሳይቀር መንግስትን የተለየ አካል አድርገው አሳስበናችኋል፣ አደጋ አለው፣ታግሰናችኋል በማለት ለማስፈራራት መሞከር እና ዛቻ መምረጥዎ ያሳዝናል በእርግጠኛነት የምነግርዎ እናንተና እኛ በህግ ፊት እኩል ነን እናንተ ከእኛ የምትለዩት የመንግስት ስልጣን በመያዛችሁ እኛ ደግሞ ነገ መንግስት ለመሆን የምንወዳደር ፓርቲ ነን ሁለታችንም ሊዳኘን የሚገባው ሰርአትና ህግ እንጂ እናንተን አሳሳቢና አስፈራሪ ያደረጋችሁ ማነው? ትልቁ ችግራችሁ ከእዚህ ይመነጫል የተቃወማችሁን ሁሉ ለማጥፋት አሸባሪ የምትለውን ታርጋ መጠቀም የመረጣችሁትም ከዚህ ባህርይ በመነሳት በመሆኑ ሊታረም ይገባል፡፡

ጥቅል ቆረጣ የተካሄደበት
ውይይቱ የተላለፈው በሶስት ክፍል ሲሆን ክፍል አንድ በኢህአዴግ ተጀመረ የመጨረሻ ሰፊ ሀተታ በኢህአዴግ ከቀረበ በኋላ የተቃዎሚዎች ምላሽ ሳይቀጥል ክፍል ሁለት ይቀጥላላ ተባለና ክፍል ሁለትን በአዲስ ጥያቄ በመጀመር የተቃዎሚውን መልስ ሙሉ በሙሉ አስቀረ ክፍል ሁለት ሲጠናቀቅ እንዲሁ በተመሳሳይ ከኢህአዴግ ማብራሪያ በኋላ ያለው የተቃዎሚዎች ማብራሪያ ተቆርጦ በአዲስ ጥያቄ ተጀመረ፡፡ የክፍል ሶስት ማጠቃለያም በኢህአዴግ ማብራሪያ እንዲጠናቀቅ ተደረገ፡፡

የማጠቃለያው ሀሳብ
ውይይቱ ሲጠቃለል የመጨረሻው ተናጋሪ አቶ ሸመልስ ከማል ሆነው ማብራሪያ ሲሰጡ አንቀጽ በአንቀጽ መረጃ ማቅረብ አልቻላችሁም በማለት መከራከሪያ ሀሳብ እንደአጠረንና አንቀጽ ለመጥቀስ እንደተቸገርን በማስመሰል መደምደሚያ አድርገው ሊያጠናቅቁ ሲል የተቃውሞ ሀሳቤን ሰነዘርኩ፡፡ አንቀጽ በአንቀጽ እንወያይ ብለን ስናነሳ አወያዩ የፓለቲካ አቋም ላይ ተወያይተን በአንቀጹ በኋላ እንመለስበታለን በማለት ካቆየ በኋላ ሰአት አልቋል አለን፡፡ ባልተወያየንበት ጉዳይ መረጃ አላቀረባችሁም ብለው መደምደሚያ መስጠቱ ስህተት ነው፡፡ አቶ ጌታቸው ሀብታሙ ትክክል ነው ይህ ያልተወያየንበት በመሆኑ ሁለተኛ ቀጠሮ ተይዞ ውይይት ይጠራ የሚለው ሀሳብ ማጠቃለያ ሆነ፡፡ ለኢቲቪ ሲተላለፍ ግን ይህ ማጠቃለያ ውይይት ተቆርጦ የአቶ ሸመልስ ሀሳብ ወደ መሀል ተወስዶ መሀል ላይ ለማደናገሪያ ገባና ከመሀል የአቶ ጌታቸው ንግግር ተቆርጦ ማጠቃለያ እንዲሆን በማድረግ ኢቲቪ በኤዲንግ ጥበቡ አጠቃለለው፡፡

የግል አስተያየት
የተቆረጡ ሀሳቦች በሚል የማስታውሳቸውን ስጽፍ የሌሎች ተከራካሪዎች ሀሳብ አልተቆረጠም በማለት ሳይሆን በራሳቸው አገላለጽ እንደሚጽፋት በማሰብ ንግግራቸውን እንዳላበላሽ በመስጋት የተውኩት ነው፡፡ የተቆረጡ ሀሳቦችን መጻፍ ያስፈለገውም በርካታ ህዝብ የተቆረጡ ሀሳቦችን ለማወቅ ከአቀረበው ጥያቄ በመነሳት እና ኢቲቪ በጐውን እንዲቀጥልበት እኩይ ተግባሩንም እንዲተው ለመቃወምና ለማስጠንቀቅ እንዲረዳ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

Part 2

Part 2

ኳሧ በእሳቸው እጅ ሣትሆን በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ነች።

$
0
0

ከሎሚ ተራተራ !
መቼም የሰሞኑን ያገራችንን ጉዳይ ሁሉም በየጓዲያውና በየአደባባዩ እየመረመርና እያሰላሰለ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም። ማግኝትና ማጣት እንደሚያልፉ ሁሉ፤ መግፋትና መገፋትም አልፎ ታሪክ መሆኑ አይቀሬ ነው። እንደው እኔም በጓዳዬ ሆኜ ወደሖላ በመመለሰ የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ መቃኝት ሰጀምር፤ አንድ አሰገራሚ ነገር ትዝ አለኝ፤ ይኸውም ትዝ ይላችሁ እንደሆን ከምርጫ 97 ሦሰት አመት በፊት በአዲሰ አበባ ዩንቨርሰቲ ማእከል ተከናውኖ በነበረው ሰብሰባ ሟቹን መለስን ያፋጠጠው ምሁር የተናገረው ቃል………እንዲህ ነበር ያለው፡ እንዲህ…….. “”አሁን ምንድነው ልናደረግ የምንችለው ? ኳሶ በእርሦ ቁጥጥር ሰር ሰላለች የእርሶን ቅንነት ብቻ እንዳይነፈጉን ነው።”” ነበር ያለው።
የኳሰ ነገር፤ ኳሦ ከሳችው እጅ በሚያሰደንቅ ሁኔታ ሁለተኛም እጃቸው ላትገባ ምላ ተሰፈንጥራ ወጣች:: የወያኔ መሪዎቸም የኳሰ ሜዳ አሰላለፈም ሆነ አጨዋወት ባለማወቃቸው አጀሬ ኳሰ ባደባባይ አይናቸው እያየ ኳሰ ከእጃቸው አምልጣ በህዝብ ቁጥጥረ ሰር ዋለች። በመዋሏ እጀግ ደሰ ብሎኛል እንኳን ደሰ አላቸሁ።
ታዲያ አሁን ምን ይደረግ? ? ቁምነገሩ እሱላይ ነው። አዎ ኳሰ አያያዝ ይጥይቃል፤ ያጨዋወት ቴክኒክና ያሰላለፍ ሰልት እጀግ አሰፈላጊ ነው። በተለይ አሁን ወያኔ በተለያየ ሁኔታ ማለትም ( በውሰና) ወዘተረፈ…”.ማኖ..”… እየነካ በመሆኑ አሰላለፉ ሁሉ ባለም አቀፍ ደረጃ ምንም አይነት የቡድን መሪ የሌለው ተራ ቡድን እየሆነ በመምጣቱ ሕዝብ የፍጹም ቅጣት ምት( እሪጎሬ) ማግኝቱ አይቅሬ ነው።
የፈጹም ቅጣት ምቱ ግን በምንም አይነት ሁኔታ መሳት የለበትም፤ (ከመረብ መዋል አለበት) ከወዲሁ፤ የፖሎቲካ ድርጀቶችም ሆኑ ደጋፊዎች የእርሰበርሰ መጠላለፍን አቁመው በሰከነ ኢትዮፒያዊነት መንፍሰ ሕዘብን በማሰትባበር ማሊያችንን የኢትዮጲያ ባንዲራ አጥልቀን አሰላለፋችንን አሳምረን የዋንጫውን ግጥሚያ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መዘጋጀት አሰፈላጊ ነው።
የፍጹም ቅጣት ምቱን ማን እንደሚመታው ወሰነን መዘጋጀት ይጠበቅብናል እላለሁ። አራጋቢ…… ወያኔዎች ቢሆኑም የመሃል ዳኛው ግን ሕዝብ በመሆኑ ውጤቱ ያማረ…የነጻነት ጮራ እንደሚፈነጥቅ አልጠራጠርም እናንተም አትጠራጠሩ።.
አለማቀፍ የሚዲያ ዘጋቢዎች ሰለማይጠፉ ለዘገባው አታሰቡ በቻ ለውጤቱ እንዘጋጅ እያልኩ ይቺን አጭር የኳሦ በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ነች መልክቴን አሳተላልፋለሁ። የዋንጫ ባለቤት ለመሆን ያብቃን እያልኩም….ነይ እርግብ አሞራ……ነይ እርግብ….ከሕዝብ,፣ድል..ጋራ…..ነይ..እርግብ…….በማለት እሰናበታለሁ።……..በቸር ይግጠመን፤
ከ ሎሚ ተራ,ተራ Wednesday, September-04-13 MWL200825@yahoo.com
ኳሦ…..በሕዝብ…..ቁጥጥር,,.ሥር ነች;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;ኳሦ…በሕዝብ……..ቁጥጥር….ሥር….ነች !!!!!!!
አሰተያየትም ሆነ ጥያቄ ቢኖራችሁ፦በዚህ ኢሜል አድራሻ ብትልኩ መልካም ነው። MWL200825@yahoo.com
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!

ፖለቲካ ሳይንስ ነው ወይ? ፖለቲካ ምሁራዊነት ያስፈልገዋል ወይ?

$
0
0

ፈቃዱ በቀለ

መግቢያ
በዚህ አርዕስት ላይ ለመጻፍ ከአሰብኩ ረዥም ጊዜ ሆነኝ። እንደሚታወቀው አንድ ጥናታዊ ጽሁፍ ለማቅረብ ቀላል አይደለም። የመንፈስ ርጋታን የሚጠይቅ ብቻ ሳይሆን፣ ለአንባቢ የሚቀርበው ጽሁፍ ከርስ በርስ ቅራኔዎች የተላቀቀና አሳማኝ እንዲሆን አድርጎ ለመጻፍና ለማስነበብ ረዥም ጊዜን ይፈጃል። ብዙ ዕውቀትንና ምርምርን ይጠይቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሐምሌ ጨረቃ – አንዷለም አራጌ ዋለ (ከቃሊቲ ማጎሪያ)

$
0
0

አንዷለም አራጌ ዋለ (ከቃሊቲ ማጎሪያ)

ክፍል ሁለት

Andualem-Aragie

አንዷለም አራጌ ዋለ

በሀገሬ ሰማይ ስር በሚደረገው የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ከኢዴፓ እስከ አንድነት ፓርቲ ድረስ በመሳተፍ ለአስራ ሶስት ዓመታት ያህል የምችለውን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ፡፡ ይህ ኩነትም የፓርቲዎችን ጓዳ ፈትሼ ግንዛቤ እንዳገኝ ስላመቻቸልኝ፣ በቀጣይ ህዝባችን የፖለቲካና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ነፃነቱን እንዳያገኝ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

1. እንደ ገዥው ፓርቲ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችም ከኋላቀሩ የፖለቲካ ባህላ የተላቀቁ አለመሆናቸው ነው፡፡ እናም አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማስጀመር ከመስራት ይልቅ ሳያውቁት ከዘመነ-መሳፍንት የተቀዳውን የፖለቲካ ባህል በተሻለ ተግባራዊ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ዛሬም ይታያሉ፡፡

2. የእስከ ዛሬውን የከሸፈ ሂደት የገመገመና የኢትዮጵያን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ከተጫነበት የጭቆና ቀንበር ለማላቀቅ የሚያስችል በውል የታሰበበትና የተጠና የፖለቲካ ቀመር እጦት በተቀቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ በጉልህ ይንፀባረቃል፡፡

3. የማያምኑበትን መቃወም ተገቢ የሆነውን ያህል የየራሳችንም ህፀፆች ያለርህራሄ ማየት፣ አይቶም ነቅሶ ማውጣት ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን በተቃዋሞ ጎራ ባለነው ፖለቲከኞች ላይ ይህንን የማድረግ ችግር ይታይብናል፡፡ ህፀፆችን ቀድሞ ማየቱ ከሌላ ወገን የሚሰነዘረው ነቀፋ ምክንያቱን ለመረዳት እድል ይሰጣል፡፡ በትችት ከመሰበርም ይታደጋል፡፡

4. ከ1960ዎቹ ጀምሮ የኢትዮጵያ ፓርቲዎች መለያ ከሆኑት አንዱ ‹ግትርነት› መሆኑ አከራካሪ አይመስለኝም፡፡ ይህ ሁኔታ በፓርቲዎች መካከል ብቻ ሳይሆን፣ በራስ ፓርቲ አባላት ውስጥም የሚፈጠሩ ችግሮች ከግትርነት የሚነሱ ናቸው፡፡ ‹‹መሸነፍ››፣ ‹‹ማሸነፍ››፤ ‹‹መንበርከክ››፣ ‹‹ማንበርከክ›› በሚለው የጫወታ ህግ ታስረን በቆምንበት ስንረግጥ በአስከፊው የመከራ ዘመን እንድንቆይ አድርጐናል፡፡ ችግር የመፍቻ ስልትም ሆነ ባህል አላዳበርንም፡፡ እንዲያውም የትግሉ እንቅስቃሴ ከአገዛዙ ጋር መሆኑ ቀርቶ በእኛ መካከል ሆኗል፡፡

5. የተወሰኑ ሰዎች ‹‹በሰላማዊ ትግል›› ውስጥ ቢሆኑም ‹‹በዚህ መንገድ አገዛዙን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም›› የሚል እምነት ስላደረባቸው በግማሽ ልብ የሚያደርጉት ትግል ትርጉም ያለው አስተዋፆ እንዲያበረክቱ አላስቻላቸውም፡፡ ሰላማዊ ትግል ራሱን የቻለ ትልቅ እምነት መስጠትና ስነ-ምግባር ያለው መሆኑን ይዘነጋሉ፡፡

6. አንዳንድ የተቃዋሚው የትግል ጐራን የሚቀላቀሉ ግለሰቦች በስሜት ብቻ በመመራት አባል የሚሆኑበት አገጣሚ ብዙ መሆኑ ለተደራጀ ትግል እንቅፋት ሆኗል፡፡ ይህንን በምሳሌ ለማስረዳት ከአንድ የቀበሌ ካድሬ ጋር ስለተጣሉ ብቻ አባል የሚሆኑ ሰዎች፣ አገዛዙን ለመቀየር የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ከፍሎ ከማሸነፍ ይልቅ እልሃቸው ሲበርድ የውሃ ሽታ ሆነው መቅረታቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

7. አገዛዙ አንዳንድ ጠንካራ አባላትና አመራር ላይ ጥቃት ማድረስ ሲጀምር ተደናግጦ ማፈግፈጉም ሌላ ችግር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የነፃነት ትግል አልጋ በአልጋ እንደሆነ ከመጠበቅ የሚመነጭ ይመስለኛል፡፡

8. የፓርቲ አባላት ከአመራር እስከ ተራ አባላት፣ ከገጠር እስከ ከተማ ንቃተ-ህሊናቸውን የሚያዳብሩና የርዮተ-ዓለም ትጥቆችን የሚያስታጥቁ ስልጠናዎችንና የውይይት መድረኮችን የመፍጠር ችግርም ተጠቃሽ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ድንገተኛና በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት እንቅቅስቃሴ ይደረጋል ውጤቱም አመርቂ አይሆንም፡፡

9. የዓለም አቀፍ ሰላማዊ ትግል ተሞክሮዎችን ከኢትዮጵያ ታሪክ፣ ፖለቲካ፣ ባህል እና ተጨባጭ ወቅታዊ ሁኔታዎች አንፃር ተቃኝተው ተግባራዊ የሚያደርጉበትን ሁኔታ የመፍጠር ችግር ይታያል፡፡

10. የቁርጠኝነት ችግር፡- የአገዛዙ አውራዎች ወጥተው በመገናኛ ብዙሃን ፉከራና ቀረርቶ ሲያሰሙ ተደናግጦ ወደዋሻ መግባትና የትግሉን ሙቀት ማቀዝቀዝም እንዲሁ መፍትሄ የሚፈልግ ጉዳይ ነው፡፡

11. በእቅድ የመመራት ችግር፡- በገዥው ፓርቲ ትንኮሳ ወይንም መግለጫ ላይ ተመስርቶ የእሳት አደጋ ስራ መስራት፡፡

12. ተቀባይነት ያለውና ህዝብ በቀላሉ የሚረዳው አስተሳሰብ፣ ታማኒነት ያለው ንግግር የተጨባጭ ተግባር ባለቤት ያለመሆን ችግር፡፡

13. ተጠራጣሪነት፡- አብሮ ታግሎ ለውጤት ለመብቃት መተማመንን መፍጠር የመጀመሪያው ተግባር ሊሆን ሲገባው መተማመን በጎደለበት ሁኔታ ፓርቲዎች አብረው ለመስራት ቢሞክሩም ሩቅ መገዝ አይችሉም፡፡ አሉባልታ ከግልፅነት ይልቅ እድል ይሰጠዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ትግሉ ያለባለቤት ይቀመጣል፡፡

14. መናናቅ፡- ጥቂት ንብረትና ጥቂት አባላት ያሏቸው ፓርቲዎች ከሌሎች ፓርቲዎች በጥቂቱ መሻላቸው ትግሉን ያጠናቀቁ ያህል ይኮፈሳሉ፡፡ በሌላ ወገን ያሉትም ጉድለቶችን በማስተካከል ወደፊት በትጋት ሊፋታ ሲገባ ስራቸውን ትትው መዘላለፍ ውስጥ ይገባሉ፡፡

15. የፓርቲ አመራሮች ታላቅ የመሆን ቅዠት፡- ከዘመነ-መሰፍንት የተቀዳው የፖለቲካ ባህላችን ብዙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን በማስጎምዠት እንቅልፍ ይነሳናል፡፡ የፕሮግራም ሆነ የአሰራር ልዩነት ሳይኖር ለስልጣን በሚደረግ ፍልሚያ ፓርቲን የሚያህል ተቋም ለሁለት ይከፍሉታል፡፡ በቲኒኒሽ ቢሮዎች ትልልቅ ሽኩቻዎች ይደረጋሉ፡፡ ትልልቅ ስም ያላቸው አመራሮች በጥቃቅን ጉዳይና ከስልጣን ጋር በተያያዙ ችግሮች ተጠልፈው ይወድቃሉ፡፡ የማያበራ ችግርም ይፈጠራል፡፡ ዓላማችን ትልቅነት እንኳ ቢሆን ትልቅ መሆን የሚቻለው በአስተሳሰብና በተግባር ልቆ በመገኘት እንጂ በብልጣ ብልጥነት ሊቀ-መንበር ተብሎ በመሰየም አለመሆኑን ይዘነጉታል፡፡

16. የሰላማዊ ትግልን ባህሪያት የትግል ስልቶችና ግቦቹን በሚገባ አለመተንተን ወይንም ግልብ በሆነ ግንዛቤ ተመስርቶ መንቀሳቀስ፡- ከ1960ዎቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ የሀገራችን የፖለቲካ ትግል በሰላማዊ መንገድ ወጣ ገባ እያለም ቢሆን ተሞክሯል፡፡ በኢህአዴግ የ22 ዓመታት አገዛዝም ለቁጥር የሚያታክቱ ፓርቲዎች በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን ብለው ቢደራጁም አብዛኛው የትግሉን ባህሪ አለማወቃቸው በትብብር የሚመጣ ውጥን አዘግይተዋል፡፡

17. ትግሉን የህዝብ የማድረግ ችግር፡- በሀገራችን በተደረጉ የሰላማዊ ትግል ሙከራዎች ላይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚያነሷቸው አጀንዳዎችን የሕዝብ በማድረግ እንዲታገልባቸው ሲያደረጉ አይታይም፡፡ ትግሉ ግብ ሊመታ የሚችለው ህዝቡ በትግሉ ከልብ አምኖ መታገል ሲችል ነው፡፡ ሆኖም ወደ ህዝብ ባለመውረዱ ጥቂት አመራሮች ሲታሰሩ ወይንም ቢሮዎች ሲዘጉ ትግሉም የመዳፈን አዝማሚያ ሲያሳይ አስተውለናል፡፡

18. የተፅኖ ማዕከሎች ያለመኖር፡- ተቃዋሚ ፓርቲዎች እራሳቸው አፈና ውስጥ ሆነው የአፈና ቀንበር ለመስበር የሚሰሩ በመሆናቸው የአቅም ውሱንነቶች አለባቸው፡፡ ስለዚህ ያላቸውን የገንዘብና የሰው ሃይል አብቃቅተው የተሳካ ትግል ማድረግ ይችሉ ዘንድ የተወሰኑ የተፅኖ ማዕከላትን መፍጠር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ደቡብ ህበረት በ1992 ዓ.ም. ብሔራዊ ምርጫ ሃድያ አካባቢ ያደረገው ተጋድሎ ለተነሳው ሃሳብ ጥሩ ምሳሌ ይመስለኛል፡፡

19. ትኩረት የተነፈገው የፓርቲዎች የገንዘብ የማሰባሰቢያ ስትራቴጂ፡-  በገንዘብ አቅርቦት ምክንያት በርካታ እቅዶች ወደተግባር ሳይለወጡ ይቀራሉ፡፡ በየክፍለ ሀገሩ ራሳቸውን ለመስዋዕትነት ያዘጋጁ አባሎቻቸውን ከማዕከል ጋር ግንኙነት እንዲኖራቸው በማድረግ ትግሉን አጠናክሮ ከመግፋት ይልቅ የቢሮ ኪራይ እንዲላክላቸው በመወትወት ጊዜያቸውን ሲያባክኑ ይታያሉ፡፡ በሂደትም እየተሰላቹ ከትግሉ ያፈገፍጋሉ፡፡ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ የገንዘብ ጥያቄን በማያሻማ መልኩ መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ይኽንን ማድረግ ሳይቻል በሰላማዊ ትግል ብዙ ርቀት መሄድ አይቻልም፡፡ የሚኖረው ዕጣ ፈንታ እንደአንዳንዶቹ ፓርቲዎች ጓዝን ጠቅልሎ ቀለብ ለማስፈር ለገዥው ፓርቲ ማደር ነው፡፡

ከሞላ ጎደል የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቀይደው የያዙና ሰላማዊ ትግሉን ወደፊት አላራምድ ካሉ ችግሮች ውስጥ እነዚህ ዋነኞቹ ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ እናም ፓርቲዎቹ በሰላማዊ ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነቱ ባለቤት እንዲሆን በሚያስችል መንገድ ለመምራት ከዚህ አንፃር ራሳቸውን ቢፈትሹ የተሻለ ነው፡፡

ይህንን ሀሳብ ከጠባቡ የእስር ክፍሌ የላኩት ፓርቲዎች፣ አመራሮቻቸውና አባላቻቸው እንዲዳከሙ ወይም ተነሳሽነታቸውን አኮስሼ ከጫወታ ለማስወጣት ከመፈለግ ሳይሆን የተሻ አቅምና ስትራቴጂ አዳብረው ለውጤት እንዲበቁ ብሎም የኢትዮጵያን ህዝብ ከአፈና አዙሪት ለማውጣት እንዲችሉ ከልቤ በቅንነት በመመኘት መሆኑን እንደምትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ሌላው መረሳት የሌለበት እውነታ በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በተለያዩ የሀላፊነት ደረጃ ባሳለፍኳቸው እስራ ሶስት ዓመታት በፓርቲም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ለታየው ድክመት እኔም ሀላፊነት የምወስድ መሆኔን ነው፡፡ እንዲሁም ካሉብኝ ውሱንነቶች አንፃር አቀራረቤ የጅምላ በመሆኑም ምንም እንኳን በአጠቃላይ የዴሞክራሲ ትግሉ ላይ በተናጠል ለውጥ ማምጣት ባይችሉም ሁልጊዜም የተሻለ የተደራጀ፣ የተሻለ ዴሞክራሲያዊ አሰረራር የነበራቸው ፓርቲዎች እንደነበሩ አይካድም፡፡ እናም ሁሉንም በአንድ አይነት ደረጃ ማስቀመጥ እንዲመጣ ለምንሻው መሻሻልም በጐ አስተዋፆ እያበረክትም፡፡ በግለሰብ ደረጃ ቢሆን ሁሉንም አንድ ቅርጫት ውስጥ መወርወር ተገቢ አይደለም፡፡ ለስልጣን የማይቋምጡ፣ ቀን ከሌት ሰርተው የማይሰለቹና ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ችግር ቅድሚያ የሚሰጡ (በጣም ጥቂት ቢሆኑም) ግለሰቦች መኖራቸውን በዚህ አጋጣሚ ማስታወሱ ተገቢ ነው፡፡ የዚህ ፅሁፍ አላማም እንዲህ አይነት ግለሰቦች ተበራክተው ወደ ስብስብ ደረጃ እንዲደርሱ ማበረታታት ነው፡፡

የሆነ ሆኖ ከፍ ብዬ ያነሳዋቸው ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ ውል አልባ ያደረጉ ችግሮችን መፍታት ለነገ የማይባል ስራ ነው፡፡ ይህን ዓላማ ከግብ ለማድረስም ከዚህ በታች የምጠቅሳቸው ነጥቦች አስፈላጊ ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡

1. በየጊዜው ለምናስመዘገባቸው ለውጦች እውቅና በመስጠት በተገኘው ድልም  እየተበረታታን ነፃነት እኛ እስከታገልን ድረስ በተጨባጭ የምናሳካው ግብ መሆኑን ማመን፡፡

2. አገዛዙን ለማሸነፍ ተቀዳሚው ተግባር ራሳችንን ማሸነፍ መሆኑን ተገንዝቦ ህዝብን ከስሜት በፀዳ መልኩ በሀላፊነት ስሜት ማደራጀትና ለውጤት ለማብቃት መስራት፤

3. ሰላማዊ ትግል ለውጤት የሚበቃው በዕውነት፣ በፍቅርና ከዚያም በሚመነጭ ፅናት ላይ ተመስርተን ተግባራዊ ስናደርገው መሆኑን መገንዘብ፤

4. ገዥዎች በአፈ-ሙዝ ስጋን ሊገድሉ ሲያደቡ፣ ክፉ ሃሳባቸውንና ተግባራቸውን በአሳማኝ ምክንያቶችና በተገራ ሰብዕና ላይ ተመስርቶ ለመለወጥ መስራት፡፡

5. ፍርሃትን መግደል፡- ፍርሃትን ማሸነፍ ባልቻልን ቁጥር ሰላማዊ ታጋዮች የመሆን ዕድላችን በዚያው መጠን መቀነሱ አይቀሬ ነው፡፡ የፍርሃት እስረኞች በሆንን ቀጥር አገዛዙ የጭቆና ሰንሰለቱን ለማጥበቅ ስለሚበረታ ፍርሃትን ግዴታ ማሸነፍ ያስፈልጋል፡፡ የአገዛዙን ቁንጮዎችም ሆነ ማንኛውንም ሃላፊ መፍራትና ክብሩን ማዋረድ አያስፈልግም፡፡ ትግሉ የእነርሱ አይነት የህዝብ ጌቶች ለመፍጠር ሳይሆን የህዝብ አገልጋዮችን ለመፍጠር ነውና፡፡

6.  ሰላማዊ ትግል ለውጤት የሚበቃው ከበቀልና ግብታዊ ከሆኑ እርምጃዎች እራሳችንን ስናፀዳ ነው፡፡ አላማችን የማንም ክብር የማይደፈርባትና የሁላችንም ሉዓላዊነት የሚከበርባት ልጆቻችንም በኩራት የሚኖሩበትን ሀገር መፍጠር ነው፡፡

7. የአገዛዙ የአፈና እርምጃዎችና በህዝብ ዘንድ ሽብርን ለመንዛት የሚያደርጋቸው የሀሰት ዶሴዎች ለተጨማሪ ትግል መነሳት እንዳለብን የሚያስገነዝቡ እንጂ ፈፅሞ ወደኋላ እንድናይ የሚያደርጉን አለመሆናቸው፡፡

8. በየጊዜው የአቋማችንን፣ የትግል ስልታችንን ትክክለኛነት መፈተሽ በወቅቱም እርምት መውሰድ ወሳኝ ነው፡፡

9. ሁልጊዜም ቢሆን ተሳስተን ገዥዎቻችን መጠላት፣ ለበቀል መዘጋጀትም ሆነ በእነርሱ ላይ በመዛት ወደፊት በሚመጣው ንጋት ስጋት እንዲገባቸው ማድረግ አያስፈልግም፡፡ አይገባምም፡፡

10. አገዛዙ ለህዝብ ፈቃድ ለመገዛት ተነሳሽነት ሲወስድ ማበረታታት እንጂ እንደተዳከመና እንደተንበረከከ እንዲሰማው ማድረግ ተገቢ አይደለም፡፡

11. የኢትዮጵያን ህዝብ ለዘመናት ከስብዕና ሚዛን ያወረደውን የጭቆና ስርዓት መታገል የህይወት ዘመናችን ዓላማ አልፋና ኦሜጋ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በግለሰብ ደረጃ ያሉን ህልሞችና ጥቅሞች ሊሳኩ የሚችሉት ትልቁ ችግራችንን በጋራ ስንፈታ ነው፡፡ ሁለንተናችን አንድ ላይ የተገመደ መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት አይገባንም፡፡

12. በረጅሙ ታሪካችን ተሳክቶ የማያውቀውን የድሎች ሁሉ አውራ ማስመዝገብ የምንችለው ትግሉ የሚጠይቀውን የመስዋዕትነት ደረጃ ከወዲሁ ተረድተን በስነ-ልቦናም ስንዘጋጅ ነው፡፡ ምናልባት አንዳንዶቻችን የትግሉ ፍሬ ተቋዳሾች ለመሆንም እንደርስ ይሆናል፤ መንገዳችን ላይ መታሰርና መንገላታት ብቻ ሳይሆን ሞትም አድፍጦ ሊጠብቀን ይችላል፡፡  ይኽንንም አውቀን በቁርጠኝነት መግፋት ብቻ ነው ያለን አማራጭ፡፡

13. ሁልጊዜም በአቋራጭ እና የትግል አጋሮቻችን መስዋዕት በማድረግ ለውጤት ለመብቃት መሞከር አይገባንም፡፡ ትግላችን ግልፅነትና ንፅህና የተሟላ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ነገ ልንፈጥር የምንመኘውን መልካም ነገር፣ ዛሬ በምናደርገው መልካም ተግባሮች የተሞላ መሆን ማስመስከር አለብንና፡፡

14. የአገዛዙን ባህሪዎችና ‹‹የእግር ቆረጣ›› ስልቶች ቀድሞ በመረዳት የተጠና አፀፋዊ እርምጃ ለመውሰድ አስቀድሞ መዘጋጀትም ያስፈልጋል፡፡

15. በዘረኝነት ወጥመድ ተጠልፎ ላለመውደቅ መጠንቀቁም ተገቢ ይመስለኛል፡፡ አገዘዙ ስልጣን ላይ መቆየት እስከቻለ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘረኝነት ወረርሽኝ ቢጠቀም አንዳች ቅሬታ የሚገባው አይመስልም፡፡ ያዝ ለቀቅ እያደረገ ሲንቀሳቀስ እንደምናየው ስልጣኑን የሚነቀንቅ ከመሰለው የሃይማኖት አሊያም የዘር ግጭት ቀስቅሶ መልሶ እራሱን ግጭት አርጋቢና መፍትሄ ፈላጊ አድርጐ ለማቅረብ ይሞክር ይሆናል፡፡ በእኛ በኩል ሊያዝ የሚገባው ግልፅ አቋም በየትኛውም ዘመን ቢሆን አንዱ ህዝብ ሌላውን ጨቁኖ ባለማወቁ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በየትኛውም ወቅት ቢሆን ኢትዮጵያውያን አማኞች የወንድሞቻቸውን የማምለክ ነፃነት ተጋፍተው አያውቁም፡፡

ሕዝብ በጋራ የአምባገነን መሪዎች የአፈና ሰለባ ነው፡፡ ሰውን በአስተሳሰቡ እንጂ በዘሩ መመዘን የጀመርን ቀን ያን ጊዜ ከሰብዓዊነት ሚዛን እንወጣለን፤ ከስልጣኔ ሃዲድ እንስታለን፡፡ የሰላማዊ ትግል የመጨረሻ ግብ ፍቅር፣ ወንድማማችና አስተማማኝ ነፃነት ሆኖ ሳለ ለዘረኝነት እድል በሰጠን መጠን የትግላችን አላማ ይከሽፋል፡፡ ዘረኝነት ኢሰብዓዊነት ነው፡፡ ዘረኝነት ከትንሽና ክፋት ከተጠናወተው ሰብዕና የሚመነጭ መርዝ ነው፡፡ በዘረኝነት ሰንሰለት ተጠፍንገን ለውጤት ለመብቃት ብንሰራም ፈጣሪም ከእኛ ጋር አይቆምም፤ ዓላማው በሰው ልጆች መካከል ፍቅርና አንድነት እንጂ ጥላቻና መለያየት አይደለም፡፡ ጊዜም ከእኛ ጋር አይተባበርም፡፡ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እኩልነት፣ ነፃነትና ክብር ከልብ ስንቆም ያን ጊዜ የፈጣሪ ሀያል ክንድ ከእኛ ጋር ይሆናል፡፡

16. ሚስጥራዊነትና ሰላማዊ ትግል ጋብቻ ሊፈፅሙ አይገባም፡፡ የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ ውጤታቸውም ጭምር በይፋ ማወቅ ለሚፈልግ ሁሉ ግልፅ ማድረግ ይገባል፡፡ አገዛዙ እንኳን በሚስጥር የሚደረግ እንቅስቃሴ አግኝቶ በይፋ የሚደረጉ የትግል እንቅስቃሴዎችንም እስካልተመቹት ድረስ አይኑን በጨው ታጥቦ የሽብር ካባ እየደረበ ትግሉን ለማምከን ሲሞክር እያየን ነው፡፡ የአገዛዙ ክፉ ሃሳብና ተግባር እንዳለ ሁኖ ግልፅነት በህዝብና በትግሉ መካከል ያለውን ቁርኝት ያጠብቀዋል፡፡ ህዝቡም የፕሮፓጋንዳ ሰለባ እንዳይሆን ይረደል፡፡ ስለዚህ በምንም አይነት መልኩ ከመጋረጃ ጀርባ የሚደረጉ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች ሊኖሩ አይገባም፡፡

17. የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች ትኩረት በማዕከል በሚደረግ ዝግጅት ብቻ ሳይሆን በየአካባቢው ያሉ አባላት አጠገባቸው ባሉ አመራሮች አማካኝነት በተጨባጭ ችግሮች፣ በእውቀትና በጥሩ ዝግጅት ላይ የተመሰረቱ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ሲችሉ ለትግሉ ግብዐት ይሆናሉና፡፡ ሌሎች የፓርቲ ቅርንጫፎችም ከእነርሱ ተሞክሮ እንዲወሰዱ ማድርግ በተቻለ መጠንም በየቦታው ያሉ አባላትና ነዋሪው ህዝብ ስለሰላማዊ ትግል ተጨባጭ ትምህርት በመቅሰም እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

18. የሰላማዊ ትግል ፈርጦች የሆኑት ማህተመ ጋንዲና ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር በተለያየ ወቅት የተናገሩትን ተመሳሳይ ይዘት ያለውን ሃሳባቸውን አፅንዎት ሰጥተን ልንወስደው ይገባል፡፡ ማህተመ ጋንዲ ‹‹ማንም ሰው ያለፈቃዱ አንዳች ነገር እንዲያደርግ ምንም አይነት ምድራዊ ሃይል ሊያስገድደው አይችልም፡፡›› ሲሉ፣ ዶ/ር ኪንግም ‹‹እስካልተጐነበስን ድረስ ማንም ሊጋልበን አይችልም፡፡›› ማለቱ ይታወሳል፡፡ ይህ አንድ አይነት መልዕክት የሚያስተላልፈው የሁለቱም የነፃነት ታጋዮች አባባል በየትኛውም ሀገር በጭቆና ቀንበር ስር ለሚማቅቅ ህዝብ የሚሰራ እውነታ ነው፡፡ ስለዚህም ከቆምንለት ህዝባዊ፣ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የተመሰረተባት የወንድማማችነት፣ የፍቅርና የነፃነት ማማ የሆነች ሀገር የመገንባት ግባችን ሊመልሰን የሚችል አንዳች ሃይል እንደሌለ ተገንዝበን በፅናትና በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይገባናል፡፡

እንደ መውጫ

ከመተኛት አልፎ እንደ ልብ መንቀሳቀስ በማይቻልበት ጠባብክ የእስር ክፍሌ ሆኜ ጎኔን ወለል ላይ፣ ጆሮዬን ወደምድር አስጠግቼ ልዳበስውና ልጨብጠው የማልችለውን ድምፅ ላደምጥ ሞከርኩ፤ እናም የአለፈው እና የአሁኑን የዘመን ዱካ ከእነአፈ እና ግሳንግሱ እየራቀ ሲሄድ፤ የመጭው ዘመን የነፃነት ድምፅና ጭቆናን የማይቀበል ትውልድ ኮቴ እየቀረበ ሲመጣ ይሰማኛል፡፡ ይህ ድምፅ ዕውን እንዲሆን ጊዜውም እንዲፈጥን፣ አባቶቻችን የዳር ድንበር ነፃነት ለማስከበር እንደዘመቱት እኛም የሰላም፣ የፍቅር፣ የወንድማማችነትና የፅናት ሰይፍ ታጥቀን የመትመም ለነገ የማያድር ሀላፊነት አለብን፡፡

ጉዞአችን ምንም ያህል አዝጋሚና በውጣ ውረድ የተሞላ ቢሆንም የምንወዳትን አዛውንት ሀገራችንን ከዘመናት የስቃይ ፅንሷ ነፃነትን የምትገላገልበት ወቅት ስለመቅረቡ ለሰከንድም አልጠራጥርም፡፡ የሐምሌና ነሐሴ ድቅድቅቅ ጨለማ፣ አጥንት ሰብሮ የሚገባ ብርድ ያኮራመታቸው እፀዋት በመስከረም ወር ከአፅናፍ አፅናፍ በሚዋኘው የብርሃን ጅረት ሁለንተናቸው ተፍታቶ ለአይን የሚማርኩ የተፈጥሮ ፀጋዎች መሆናቸውን በኩራት እንደሚያውጁ ሁሉ፣ ኢትዮጵያውያንም ዕድሜ ጠገቡን የአገዛዝ ቀንበር ከጫንቃችን አውርደን በመጣል፣ ሀገራችን ከዳር ድንበር ነፃነት ጋር ብቻ ተያይዛ የምትጠቀስ አለመሆኗን በተጨባጭ በማረጋገጥ በኩራት በሀገራችን መኖር እንጀምራለን፡፡ ሀገራችን የሰብዓዊ ክብር ማማ የምትሆንበት ዘመን እነሆ እየገሰገሰ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ያ ዘመን በመሬታችን ሲደርስ ‹‹ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና…›› የሚለውን የኩኩ ሰብስቤ ዜማ ከተወሰኑ የግጥም ማስተካከያዎች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን ከልብ መዘመራችንም አይቀሬ እንደሆነ አምናለሁ፡፡

አዛውንቷ ሀገራችን የሰብዓዊ ክብር ማማ፣ ‹‹የአፍሪካ ገናና›› ትሆን ዘንድ ነፃነትን በእርጋታ፣ በትዕግስትና አስተዋይነት በተሞላበት ሁኔታ የምናዋልድ ጥበበኛ ሀኪሞ ልንሆን ይገባናል፡፡ ሀገራችን በተለያየ ወቅት ነፃነትን ብታረግዝም ፅንሱን ከእነነፍሱ ለማዋለድ እስከዛሬ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ያልተሳኩ ነፃነትን የማዋለድ ጥረቶችም በባለታሪኳ ሀገራችን ላይ አገዛዙ እረግጦ በመግዛት ለመቀጠል የሚያደርገው የሞት ሽረት ትግል ሲጨመርበት፣ ሀገራችንን ፈፅሞ ወደ ማንመኘው የውድቀት አፋፍ ይዟት እንዳይወርድ ጥብቅ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ ይኽን ማድረግ ካልቻልን በምክንያት የማንመራ፣ በስሜትና ኋላቀርነት አረንቋ የምንዳክር ልጆቻችን የሚያፍሩብን፣ መጭው ትውልድ የሚወቅሰን አባቶች እንዳንሆን ስጋቴ ፅኑ ነው፡፡

ስለዚህ በድቅድቁ የጭቆና ሌሊት ላይ ለዘላለም የማትጠልቅ የነፃነት ፀሐይ እስትከሰት ትግላችን ሊቀጥል የገባዋል፤ በድቅድቁ የአፈና ሌሊት ጨረቃ ያለማቋረጥ እስክትሰለጥን ጤፍ የሚያስለቅም ጣፋጭ ፍቅር የሚያስኮመኩም፣ ዜጐች ያለአንዳች ስጋት የሚመላለሱበትና የዱር አራዊትም ጭምር ለአደን ያለመከልከል እንዲወጡ የሚያስችል ብርሃኗን በምድራችን ላይ እስክትረጭ ትግላችን ከቀድሞ በበለጠ ደረጃ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፤ ሀገራችን የረጅም ዘመን እርግዝናዋን በሰላም ተገላግከላ የምድር ሁሉ ፈርጥ እስክትባል ድረስ የነፃነትንና የወንድማማችነት ንጋት የተራባችሁ ኢትዮጵየውያን ሁሉ የፍቅርና የፅናት ዝናራችሁን ታጥቃችሁ ትግላችሁን ቀጥሉ፡፡ አዎ! ነፃነት እንደቀትር ብርሃን ፍቅርም እንደሃይለኛ ጅረት የሀገራችን ምድር ሞልቶ ይፍሰስ!! ነፃናት፣ ነፃነት፣ ነፃነት፤ እደግመዋለሁ አሁንም ነፃነት!!!

አጭር ማስታወሻ የሰማያዊ ፖርቲ የተቃውሞ ሠልፍ

$
0
0

ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ)ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ)

ነኀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው፤ ይሁን እንጂ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት እንደሰፈር ጉልበታኛ ድንኳን ሰባሪ ዘው ብሎ በኃይማኖት ሰበብ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ቀንና ሰዓት እንዲሁም ቦታ በሕግ አግባብ ሣይሆን በጉልበት ሠልፍ መሰል ሠልፍ ማካሄዱ የሚታወቅ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስብሓት ነጋ ጥፋቷን ስለሚመኙላት ቤተ ክርስቲያንና መግደያ ብትር ሊያደርጉት ስለሞከሩት ማኅበረ ቅዱሳን ይወተውታሉ

$
0
0
  • ስብሓት የንግግራቸው መነሻ ያደረጓቸውና ወጣት ሲሉ የጠሯቸው መነኩሴ ማን ናቸው?

Ethio-Mihdar Flag of the day

‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚያስተኛ አይደለም

/አቶ ስብሓት ነጋ/

(ኢትዮ-ምኅዳር ቅጽ 01 ቁጥር 34፤ ረቡዕ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋራ በመተባበር በአዲስ አበባ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ከነሐሴ ፳፩ – ፳፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ‹‹የሃይማኖቶች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት በማጎልበትና ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በማክበር የሀገራችንን የሕዳሴ ጉዞ ለማሳካት እንረባረባለን›› በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ ላይ ‹አቦይ› ስብሐት ነጋ በመገኘት አነጋጋሪ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡ አንጋፋው የህወሓት/ኢሕአዴግ መሥራችና የጀርባ ሰው የሚገልጹት ሐሳብ የመንግሥትን ቀጣይ ርምጃ ያመላክታል በሚል በአጭሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

Sebhat Negaአክራሪነት ይዘቱ ሃይማኖታዊ እንዳልኾነ ሕዝቡም የተገነዘበው ጉዳይ መኾኑ ተደጋግሞ ተገልጧል፡፡ ሃይማኖትን የፖሊቲካ መድረክ የሚያደርጉት የሽብርተኝነት ተግባር ለመፈጸም መኾኑ ግልጽ የኾነልን ይመስለኛል፡፡

አክራሪነትና ጽንፈኝነት በሃይማኖት ውስጥ ማስገባት የመጀመሪያው አደጋ ሲኾን በዚህ ኹኔታ ሃይማኖቱም ሃይማኖት አይኾንም፡፡ አማኞች፣ አክራሪነትና ጽንፈኝነት በየሃይማኖታቸው ውስጥ ሲታይ ሃይማኖታቸው አደጋ ላይ እንደወደቀ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን (የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ) እንዳለውም፣ በጣም አስደናቂ የኾነውን የኢትዮጵያ ዕድገት ማደናቀፍ ከማንኛውም ወንጀል በላይ በሕዝብ ላይ ከባድ ወንጀል መፈጸም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለብዙ ዓመታት ሲሠቃይ የነበረ በመኾኑ አሁንም ሕዝቡን ለሥቃይ መዳረግ ተወዳዳሪ የሌለው ወንጀል ነው፡፡

በማንኛውም ሃይማኖታዊ አክራሪነት እና ጽንፈኝነት፣ በምንም ዐይነት ኹኔታ አንድም ሰው ለአንድ ደቂቃ እንኳ ተዘናግቶ መተኛት የሌለበት ሲኾን በተለይ ይህን ነገር በጥብቅ በሁሉም መንገድ መታገል አለብን፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ያለውን ዕድገት የሚቀናቀነው የውጭ ተቀናቃኝ ነው፡፡ የእነዚህን ተቀናቃኞች ዓላማ በመያዝ በአክራሪነትና በጽንፈኝነት መልክ ታላቅ ክሕደት መፈጸም ከባድ አገራዊ ክሕደት ነው፡፡ የውጭ ጠላት ቀላል ስላልኾነ አንድም ሰው ሳይቀር በጣም ተጠናክረን መመከት ይገባል፡፡ ሕገ መንግሥቱን መሠረት ያደረገ የፖሊቲካ ልዩነት ሊኖር ይችላል፤ ሕገ መንግሥቱን የመጣስ ዝንባሌ ግን እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ መንግሥቱ ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያጸደቀው የራሱ ሕገ መንግሥት ስለኾነ ሕዝብ በመራራ ትግል ያጸደቀውን ሕገ መንግሥት መጣስ የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል ነው፡፡

በዚህ ስብሰባ ከፍተኛ ግንዛቤ መያዙ በጣም የሚያስደስት ነው፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ ተስፋ ነው፡፡ ለውጭ ጠላት ደግሞ ሲጠብቀው የነበረ ብጥብጥ መቅረቱ ሕዝብን የሚያስደስት፣ ጠላትን ደግሞ የሚያሳፍር ነው፡፡

ሌላው ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተነሣ ነበር፡፡ አንድ አባታችን ካነሧቸው ብዙ ነገሮች አንዱ፣ ‹‹መንግሥት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጁን ያስገባል›› የሚል ነው፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ በእስልምናም ይኹን በኦርቶዶክስ እጁን አያስገባም፡፡ በዚህ ጉዳይ የመጀመሪያ ተጠያቂው እምነቱ ነው፡፡ ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም? ሁለተኛው ተጠያቂ ደግሞ መንግሥት ይኾናል፡፡

ስለዚህ በሩን ከፍቶ ሲያንቀላፋ መንግሥት እጁን ካስገባበት እምነቱ ይጠየቃል፡፡ ይኹን እንጂ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት እጁን እንዳላስገባ መቶ በመቶ አምናለኹ፡፡ አንዳንድ የመንግሥት ሰዎች ግን እጃቸውን አስገብተው ሊኾን ይችላል፡፡ ስለዚህ እነዚህን መመከት ነበረበት፡፡ በመጀመሪያ ተጠያቂው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ራሱ ሲኾን እጃቸውን ያስገቡ ሰዎች ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ተጠያቂ ይኾናሉ፡፡

ሁለተኛ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ወጣት*የተነሣ ሐሳብ አለ፡፡ አክራሪነት አደጋ ነው ብሏል፡፡ በኋላ በእስልምና ሃይማኖት አካባቢ በአንዳንድ ሰዎች የሚታየው አክራሪነት አደጋ ነው፤ ዋናው ግን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተቀበረው ፈንጅ ነው ትልቁ የአክራሪነት አደጋ ብሏል፡፡ አክራሪነት ማለት እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ማዋል፣ እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ክፍት ማድረግ ማለት ነው፡፡

አንዳንድ ማኅበራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የፖሊቲካ መድረክ እያደረጓት ነው፤ ማኅበሩ** እንኳ ባይኾን አንዳንድ ሰዎች ብሎ ጠቅሷል፡፡ ይህን ተጠንቅቆ ያቀረበው ይመስለኛል፡፡ ማኅበሩ ነው አክራሪ ወይስ በማኅበሩ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ናቸው? መጣራት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማኅበር ያሉ አንዳንድ ሰዎች ማኅበሩ ጤናው የተበከለ እንዳይኾን ማጣራት፣ ተጠንቅቆ መያዙ፣ እንደተባለው ፈንጅ ከኾነ አስቸጋሪ ነው፡፡ ወጣቱ* እና ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም (የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር) ሁለቱም ከባድ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

እንደተባለው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በእውነት የፖሊቲካ መድረክ እየኾነች ከኾነ፣ በዚህ አገር የትኛው አክራሪነት ነው ከተባለ፣ ትልቁ አደጋ ያለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነው የተባለው ትክክል ነው ወይስ ትክክል አይደለም የሚለው መጣራት የሚኖርበት ቢኾንም በሁለቱ ሰዎች የተጠቆመው ግን የሚያስተኛ አይደለም፡፡ ከእምነቱ ቦታ የኾንም መተኛት የለብንም፤ የሌሎች እምነት አማኞችም መተኛት የለባቸውም፡፡

 *                    *                 *

ሐራዊ ማስታወሻ፡-

*አቶ ስብሓት ወጣቱ ሲሉ የጠሯቸው የስብሰባው ተሳታፊ ከከምባታ ሐዲያ ጉራጌና ስልጤ አህጉረ ስብከት ከሚገኘው ሃላባ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትና ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የመጡ አባ ዮናስ የተባሉ መነኩሴን ነው፡፡ እኒህ ስመ መነኮስ እንደ በጋሻው ደሳለኝ ላሉ ሕገ ወጥ ሰባክያን ዐውደ ምሕረት በመፍቀድና ምእመኑን ሰላም በመንሳት በወረዳው የማኅበሩ ጽ/ቤት እንዲዘጋ ያደረጉ፣ ከትምህርቱም ከግብረ ገቡም የሌሉበት ግለሰብ ናቸው፡፡

መንግሥት አካሂደዋለኹ በሚለው የፀረ አክራሪነት ትግል አጋር መስለው የተጠጉ ግለሰቦች [የደብር አስተዳዳሪ ለማሾም 60,000 ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው 60 ጎራሽ የተባሉትንና ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተነሥተው ወደ መ/ፓ/ጠ/ቤተ ክህነት የትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ምክትል ሓላፊነት የተዛወሩትን የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢን ርእሰ ደብር በሪሁ አርኣያን ይጨምራል]  ያላቸውን አግባብነትና የሚሰጡትን መረጃ ትክክለኛነት (ቅንነት) ማጤን ይገባዋል፡፡

አቶ ስብሓት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚያራምዱትና በልዩ ልዩ ዘገባዎች ሲገለጽ የቆየው አቋማቸው በተለይ ከ፳፻፩ ዓ.ም ጀምሮ በሚገባ ይታወቃል፡፡ ‹‹ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም?›› ማለታቸው በአባባል ደረጃ ተገቢ ቢኾንም እርሳቸው የጠቀሱትን ሕገ መንግሥታዊ መብት ለማስከበር ቢያንስ በግንቦት ፳፻፩ ዓ.ም በመጠኑ የሞከሩ ብፁዓን አባቶች ምን እንደደረሰባቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን የምንለው ሊቃነ ጳጳሳቱን ልናመሰግናቸው ፈልገን ወይም አቶ ስብሓት እንዳሉት ‹‹በሩን ከፍቶ ያንቀላፋ የለም›› ለማለት አይደለም፡፡ በሌላ መድረክ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ ኹኔታው ምሬታቸውን በገለጹበት ወቅት ‹‹ብትሰየፉስ!›› ያሏቸው የመከራቸው ፍጻሜ ገና መኾኑን ስለሚያሳይ፡፡

አቶ ስብሓት ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ ለውጥ በቅ/ሲኖዶሱና በቀድሞው ፓትርያርክ መካከል የተደረገው የውስጥ ትግል በተጧጧፈበት ወራትና ከዚያም ወዲህ በእጅጉ ይጠሏቸው ነበር የሚባሉትን የቀድሞውን ፓትርያርክ ከመንበራቸው ለማስወገድ ማኅበሩ በቅ/ሲኖዶስ ዕውቅና ካገኘበት የአገልግሎት ዓላማና ስልት ውጭ ሚና ለመስጠትና መሣርያ ለማድረግ የገፋፉበት ኹኔታ በማኅበሩ ቀጣይ ህልውና ላይ ያላቸውን ፍላጎት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ እንደነበር ይነገራል፡፡

ግፊታቸው በወቅቱ በማኅበሩ ጥቂት አመራሮች መካከል ልዩነት ፈጥሮ እንደነበር የሚገለጽ ቢኾንም ተቀባይነት ያገኘ ግን አልነበረም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹የቤተ ክህነት ዕዳ ነው›› በማለት ‹‹የተቃዋሚ ፖሊቲካ መድረክነት›› እንደሚታይበት ወዘተ ባለፈው ዓመት የፍትሕ ጋዜጣ ጽሑፋቸው የሰነዘሩበት ሒስም የዚያ ማወራረጃ እንደኾነ ይታሰባል፡፡

ማኅበሩ ከተመሠረተበት ዓላማና ከሚፈለግበት አገልግሎት አኳያ በድክመት የሚተችበትና ገና ብዙ እንደሚቀረው የብዙዎች እምነት ቢኾንም በሰሞኑ ስብሰባ አቶ ስብሓት ወጣቱ  ባሏቸው አባ ዮናስ ጥቆማ በኩል አልፈውና የአባ ዮናስን ንግግር አጉነው ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሰጡት አስተያየት ወይ አቅጣጫ መነሻው ጥላቻ የወለደውና ቅንነት የጎደለው መረጃ እንደኾነ የመረጃው ጠቋሚ ሰው ስለ ማኅበሩ ባላቸው አቋምና በወረዳቸው ከማኅበሩ አባላት ጋራ ባላቸው ግንኙነት መረዳት አያዳግትም፡፡

መንበረ ፓትርያርኩን በመወከል በስብሰባው እንዲገኙ ጥሪ ከተደረገላቸው 50 ተሳታፊዎች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን በዋና ጽ/ቤቱ ደረጃ እንደማኅበር እንዳልተጋበዘና ይህም በአክራሪነት ከተካሄደው ፍረጃ ጀምሮ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡበት እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡

አባ ዮናስ ከእውነት የራቀ ጥቆማቸውን፣ አቶ ስብሓትም በዚሁ ላይ የተመሠረተ አስተያየታቸውን/አቅጣጫቸውን በሰጡበት መድረክ ሊቃነ ጳጳሳቱ አቡነ ገብርኤል፣ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ አቡነ ኄኖክ፣ አቡነ ጎርጎሬዎስ በአጸፋ የመናገርና ምላሽ የመስጠት ዕድል ተነፍገዋል፡፡ ይኸው የስብሰባው አካሄድ ከአዳራሹ ውጭ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱና በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች መካከል በከፍተኛ ደረጃ አጠያይቆ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ በውይይቱ ቤተ ክርስቲያን ከአክራሪነት አንጻር የተገለጸችበትንና ማኅበሩን አስመልክቶ የተሰነዘሩ ሐሳቦችን መንበረ ፓትርያርኩ በቀላሉ እንደማይመለከተውና በጥብቅ እንደሚነጋገርበት ሊቃነ ጳጳሳቱ ለሚኒስቴሩ ሓላፊዎች እንዳሳሰቧቸውም ተገልጧል፡፡

የሐምሌ ጨረቃ አንዷለም አራጌ ዋለ (ከቃሊቲ ማጎሪያ)

$
0
0

በሀገሬ ሰማይ ስር በሚደረገው የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ከኢዴፓ እስከ አንድነት ፓርቲ ድረስ በመሳተፍ ለአስራ ሶስት ዓመታት ያህል የምችለውን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ፡፡ ይህ ኩነትም የፓርቲዎችን ጓዳ ፈትሼ ግንዛቤ እንዳገኝ ስላመቻቸልኝ፣ በቀጣይ ህዝባችን የፖለቲካና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ነፃነቱን እንዳያገኝ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

1. እንደ ገዥው ፓርቲ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችም ከኋላቀሩ የፖለቲካ ባህላ የተላቀቁ አለመሆናቸው ነው፡፡ እናም አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማስጀመር ከመስራት ይልቅ ሳያውቁት ከዘመነ-መሳፍንት የተቀዳውን የፖለቲካ ባህል በተሻለ ተግባራዊ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ዛሬም ይታያሉ፡፡

2. የእስከ ዛሬውን የከሸፈ ሂደት የገመገመና የኢትዮጵያን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ከተጫነበት የጭቆና ቀንበር ለማላቀቅ የሚያስችል በውል የታሰበበትና የተጠና የፖለቲካ ቀመር እጦት በተቀቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ በጉልህ ይንፀባረቃል፡፡

3. የማያምኑበትን መቃወም ተገቢ የሆነውን ያህል የየራሳችንም ህፀፆች ያለርህራሄ ማየት፣ አይቶም ነቅሶ ማውጣት ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን በተቃዋሞ ጎራ ባለነው ፖለቲከኞች ላይ ይህንን የማድረግ ችግር ይታይብናል፡፡ ህፀፆችን ቀድሞ ማየቱ ከሌላ ወገን የሚሰነዘረው ነቀፋ ምክንያቱን ለመረዳት እድል ይሰጣል፡፡ በትችት ከመሰበርም ይታደጋል፡፡

4. ከ1960ዎቹ ጀምሮ የኢትዮጵያ ፓርቲዎች መለያ ከሆኑት አንዱ ‹ግትርነት› መሆኑ አከራካሪ አይመስለኝም፡፡ ይህ ሁኔታ በፓርቲዎች መካከል ብቻ ሳይሆን፣ በራስ ፓርቲ አባላት ውስጥም የሚፈጠሩ ችግሮች ከግትርነት የሚነሱ ናቸው፡፡ ‹‹መሸነፍ››፣ ‹‹ማሸነፍ››፤ ‹‹መንበርከክ››፣ ‹‹ማንበርከክ›› በሚለው የጫወታ ህግ ታስረን በቆምንበት ስንረግጥ በአስከፊው የመከራ ዘመን እንድንቆይ አድርጐናል፡፡ ችግር የመፍቻ ስልትም ሆነ ባህል አላዳበርንም፡፡ እንዲያውም የትግሉ እንቅስቃሴ ከአገዛዙ ጋር መሆኑ ቀርቶ በእኛ መካከል ሆኗል፡፡

5. የተወሰኑ ሰዎች ‹‹በሰላማዊ ትግል›› ውስጥ ቢሆኑም ‹‹በዚህ መንገድ አገዛዙን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም›› የሚል እምነት ስላደረባቸው በግማሽ ልብ የሚያደርጉት ትግል ትርጉም ያለው አስተዋፆ እንዲያበረክቱ አላስቻላቸውም፡፡ ሰላማዊ ትግል ራሱን የቻለ ትልቅ እምነት መስጠትና ስነ-ምግባር ያለው መሆኑን ይዘነጋሉ፡፡

6. አንዳንድ የተቃዋሚው የትግል ጐራን የሚቀላቀሉ ግለሰቦች በስሜት ብቻ በመመራት አባል የሚሆኑበት አገጣሚ ብዙ መሆኑ ለተደራጀ ትግል እንቅፋት ሆኗል፡፡ ይህንን በምሳሌ ለማስረዳት ከአንድ የቀበሌ ካድሬ ጋር ስለተጣሉ ብቻ አባል የሚሆኑ ሰዎች፣ አገዛዙን ለመቀየር የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ከፍሎ ከማሸነፍ ይልቅ እልሃቸው ሲበርድ የውሃ ሽታ ሆነው መቅረታቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

7. አገዛዙ አንዳንድ ጠንካራ አባላትና አመራር ላይ ጥቃት ማድረስ ሲጀምር ተደናግጦ ማፈግፈጉም ሌላ ችግር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የነፃነት ትግል አልጋ በአልጋ እንደሆነ ከመጠበቅ የሚመነጭ ይመስለኛል፡፡

8. የፓርቲ አባላት ከአመራር እስከ ተራ አባላት፣ ከገጠር እስከ ከተማ ንቃተ-ህሊናቸውን የሚያዳብሩና የርዮተ-ዓለም ትጥቆችን የሚያስታጥቁ ስልጠናዎችንና የውይይት መድረኮችን የመፍጠር ችግርም ተጠቃሽ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ድንገተኛና በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት እንቅቅስቃሴ ይደረጋል ውጤቱም አመርቂ አይሆንም፡፡

9. የዓለም አቀፍ ሰላማዊ ትግል ተሞክሮዎችን ከኢትዮጵያ ታሪክ፣ ፖለቲካ፣ ባህል እና ተጨባጭ ወቅታዊ ሁኔታዎች አንፃር ተቃኝተው ተግባራዊ የሚያደርጉበትን ሁኔታ የመፍጠር ችግር ይታያል፡፡

10. የቁርጠኝነት ችግር፡- የአገዛዙ አውራዎች ወጥተው በመገናኛ ብዙሃን ፉከራና ቀረርቶ ሲያሰሙ ተደናግጦ ወደዋሻ መግባትና የትግሉን ሙቀት ማቀዝቀዝም እንዲሁ መፍትሄ የሚፈልግ ጉዳይ ነው፡፡

11. በእቅድ የመመራት ችግር፡- በገዥው ፓርቲ ትንኮሳ ወይንም መግለጫ ላይ ተመስርቶ የእሳት አደጋ ስራ መስራት፡፡

12. ተቀባይነት ያለውና ህዝብ በቀላሉ የሚረዳው አስተሳሰብ፣ ታማኒነት ያለው ንግግር የተጨባጭ ተግባር ባለቤት ያለመሆን ችግር፡፡

13. ተጠራጣሪነት፡- አብሮ ታግሎ ለውጤት ለመብቃት መተማመንን መፍጠር የመጀመሪያው ተግባር ሊሆን ሲገባው መተማመን በጎደለበት ሁኔታ ፓርቲዎች አብረው ለመስራት ቢሞክሩም ሩቅ መገዝ አይችሉም፡፡ አሉባልታ ከግልፅነት ይልቅ እድል ይሰጠዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ትግሉ ያለባለቤት ይቀመጣል፡፡

14. መናናቅ፡- ጥቂት ንብረትና ጥቂት አባላት ያሏቸው ፓርቲዎች ከሌሎች ፓርቲዎች በጥቂቱ መሻላቸው ትግሉን ያጠናቀቁ ያህል ይኮፈሳሉ፡፡ በሌላ ወገን ያሉትም ጉድለቶችን በማስተካከል ወደፊት በትጋት ሊፋታ ሲገባ ስራቸውን ትትው መዘላለፍ ውስጥ ይገባሉ፡፡

15. የፓርቲ አመራሮች ታላቅ የመሆን ቅዠት፡- ከዘመነ-መሰፍንት የተቀዳው የፖለቲካ ባህላችን ብዙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን በማስጎምዠት እንቅልፍ ይነሳናል፡፡ የፕሮግራም ሆነ የአሰራር ልዩነት ሳይኖር ለስልጣን በሚደረግ ፍልሚያ ፓርቲን የሚያህል ተቋም ለሁለት ይከፍሉታል፡፡ በቲኒኒሽ ቢሮዎች ትልልቅ ሽኩቻዎች ይደረጋሉ፡፡ ትልልቅ ስም ያላቸው አመራሮች በጥቃቅን ጉዳይና ከስልጣን ጋር በተያያዙ ችግሮች ተጠልፈው ይወድቃሉ፡፡ የማያበራ ችግርም ይፈጠራል፡፡ ዓላማችን ትልቅነት እንኳ ቢሆን ትልቅ መሆን የሚቻለው በአስተሳሰብና በተግባር ልቆ በመገኘት እንጂ በብልጣ ብልጥነት ሊቀ-መንበር ተብሎ በመሰየም አለመሆኑን ይዘነጉታል፡፡

16. የሰላማዊ ትግልን ባህሪያት የትግል ስልቶችና ግቦቹን በሚገባ አለመተንተን ወይንም ግልብ በሆነ ግንዛቤ ተመስርቶ መንቀሳቀስ፡- ከ1960ዎቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ የሀገራችን የፖለቲካ ትግል በሰላማዊ መንገድ ወጣ ገባ እያለም ቢሆን ተሞክሯል፡፡ በኢህአዴግ የ22 ዓመታት አገዛዝም ለቁጥር የሚያታክቱ ፓርቲዎች በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን ብለው ቢደራጁም አብዛኛው የትግሉን ባህሪ አለማወቃቸው በትብብር የሚመጣ ውጥን አዘግይተዋል፡፡

17. ትግሉን የህዝብ የማድረግ ችግር፡- በሀገራችን በተደረጉ የሰላማዊ ትግል ሙከራዎች ላይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚያነሷቸው አጀንዳዎችን የሕዝብ በማድረግ እንዲታገልባቸው ሲያደረጉ አይታይም፡፡ ትግሉ ግብ ሊመታ የሚችለው ህዝቡ በትግሉ ከልብ አምኖ መታገል ሲችል ነው፡፡ ሆኖም ወደ ህዝብ ባለመውረዱ ጥቂት አመራሮች ሲታሰሩ ወይንም ቢሮዎች ሲዘጉ ትግሉም የመዳፈን አዝማሚያ ሲያሳይ አስተውለናል፡፡

18. የተፅኖ ማዕከሎች ያለመኖር፡- ተቃዋሚ ፓርቲዎች እራሳቸው አፈና ውስጥ ሆነው የአፈና ቀንበር ለመስበር የሚሰሩ በመሆናቸው የአቅም ውሱንነቶች አለባቸው፡፡ ስለዚህ ያላቸውን የገንዘብና የሰው ሃይል አብቃቅተው የተሳካ ትግል ማድረግ ይችሉ ዘንድ የተወሰኑ የተፅኖ ማዕከላትን መፍጠር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ደቡብ ህበረት በ1992 ዓ.ም. ብሔራዊ ምርጫ ሃድያ አካባቢ ያደረገው ተጋድሎ ለተነሳው ሃሳብ ጥሩ ምሳሌ ይመስለኛል፡፡

19. ትኩረት የተነፈገው የፓርቲዎች የገንዘብ የማሰባሰቢያ ስትራቴጂ፡- በገንዘብ አቅርቦት ምክንያት በርካታ እቅዶች ወደተግባር ሳይለወጡ ይቀራሉ፡፡ በየክፍለ ሀገሩ ራሳቸውን ለመስዋዕትነት ያዘጋጁ አባሎቻቸውን ከማዕከል ጋር ግንኙነት እንዲኖራቸው በማድረግ ትግሉን አጠናክሮ ከመግፋት ይልቅ የቢሮ ኪራይ እንዲላክላቸው በመወትወት ጊዜያቸውን ሲያባክኑ ይታያሉ፡፡ በሂደትም እየተሰላቹ ከትግሉ ያፈገፍጋሉ፡፡ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ የገንዘብ ጥያቄን በማያሻማ መልኩ መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ይኽንን ማድረግ ሳይቻል በሰላማዊ ትግል ብዙ ርቀት መሄድ አይቻልም፡፡ የሚኖረው ዕጣ ፈንታ እንደአንዳንዶቹ ፓርቲዎች ጓዝን ጠቅልሎ ቀለብ ለማስፈር ለገዥው ፓርቲ ማደር ነው፡፡

ከሞላ ጎደል የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቀይደው የያዙና ሰላማዊ ትግሉን ወደፊት አላራምድ ካሉ ችግሮች ውስጥ እነዚህ ዋነኞቹ ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ እናም ፓርቲዎቹ በሰላማዊ ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነቱ ባለቤት እንዲሆን በሚያስችል መንገድ ለመምራት ከዚህ አንፃር ራሳቸውን ቢፈትሹ የተሻለ ነው፡፡

ይህንን ሀሳብ ከጠባቡ የእስር ክፍሌ የላኩት ፓርቲዎች፣ አመራሮቻቸውና አባላቻቸው እንዲዳከሙ ወይም ተነሳሽነታቸውን አኮስሼ ከጫወታ ለማስወጣት ከመፈለግ ሳይሆን የተሻ አቅምና ስትራቴጂ አዳብረው ለውጤት እንዲበቁ ብሎም የኢትዮጵያን ህዝብ ከአፈና አዙሪት ለማውጣት እንዲችሉ ከልቤ በቅንነት በመመኘት መሆኑን እንደምትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ሌላው መረሳት የሌለበት እውነታ በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በተለያዩ የሀላፊነት ደረጃ ባሳለፍኳቸው እስራ ሶስት ዓመታት በፓርቲም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ለታየው ድክመት እኔም ሀላፊነት የምወስድ መሆኔን ነው፡፡ እንዲሁም ካሉብኝ ውሱንነቶች አንፃር አቀራረቤ የጅምላ በመሆኑም ምንም እንኳን በአጠቃላይ የዴሞክራሲ ትግሉ ላይ በተናጠል ለውጥ ማምጣት ባይችሉም ሁልጊዜም የተሻለ የተደራጀ፣ የተሻለ ዴሞክራሲያዊ አሰረራር የነበራቸው ፓርቲዎች እንደነበሩ አይካድም፡፡ እናም ሁሉንም በአንድ አይነት ደረጃ ማስቀመጥ እንዲመጣ ለምንሻው መሻሻልም በጐ አስተዋፆ እያበረክትም፡፡ በግለሰብ ደረጃ ቢሆን ሁሉንም አንድ ቅርጫት ውስጥ መወርወር ተገቢ አይደለም፡፡ ለስልጣን የማይቋምጡ፣ ቀን ከሌት ሰርተው የማይሰለቹና ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ችግር ቅድሚያ የሚሰጡ (በጣም ጥቂት ቢሆኑም) ግለሰቦች መኖራቸውን በዚህ አጋጣሚ ማስታወሱ ተገቢ ነው፡፡ የዚህ ፅሁፍ አላማም እንዲህ አይነት ግለሰቦች ተበራክተው ወደ ስብስብ ደረጃ እንዲደርሱ ማበረታታት ነው፡፡

የሆነ ሆኖ ከፍ ብዬ ያነሳዋቸው ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ ውል አልባ ያደረጉ ችግሮችን መፍታት ለነገ የማይባል ስራ ነው፡፡ ይህን ዓላማ ከግብ ለማድረስም ከዚህ በታች የምጠቅሳቸው ነጥቦች አስፈላጊ ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡

1. በየጊዜው ለምናስመዘገባቸው ለውጦች እውቅና በመስጠት በተገኘው ድልም እየተበረታታን ነፃነት እኛ እስከታገልን ድረስ በተጨባጭ የምናሳካው ግብ መሆኑን ማመን፡፡

2. አገዛዙን ለማሸነፍ ተቀዳሚው ተግባር ራሳችንን ማሸነፍ መሆኑን ተገንዝቦ ህዝብን ከስሜት በፀዳ መልኩ በሀላፊነት ስሜት ማደራጀትና ለውጤት ለማብቃት መስራት፤

3. ሰላማዊ ትግል ለውጤት የሚበቃው በዕውነት፣ በፍቅርና ከዚያም በሚመነጭ ፅናት ላይ ተመስርተን ተግባራዊ ስናደርገው መሆኑን መገንዘብ፤

4. ገዥዎች በአፈ-ሙዝ ስጋን ሊገድሉ ሲያደቡ፣ ክፉ ሃሳባቸውንና ተግባራቸውን በአሳማኝ ምክንያቶችና በተገራ ሰብዕና ላይ ተመስርቶ ለመለወጥ መስራት፡፡

5. ፍርሃትን መግደል፡- ፍርሃትን ማሸነፍ ባልቻልን ቁጥር ሰላማዊ ታጋዮች የመሆን ዕድላችን በዚያው መጠን መቀነሱ አይቀሬ ነው፡፡ የፍርሃት እስረኞች በሆንን ቀጥር አገዛዙ የጭቆና ሰንሰለቱን ለማጥበቅ ስለሚበረታ ፍርሃትን ግዴታ ማሸነፍ ያስፈልጋል፡፡ የአገዛዙን ቁንጮዎችም ሆነ ማንኛውንም ሃላፊ መፍራትና ክብሩን ማዋረድ አያስፈልግም፡፡ ትግሉ የእነርሱ አይነት የህዝብ ጌቶች ለመፍጠር ሳይሆን የህዝብ አገልጋዮችን ለመፍጠር ነውና፡፡

6. ሰላማዊ ትግል ለውጤት የሚበቃው ከበቀልና ግብታዊ ከሆኑ እርምጃዎች እራሳችንን ስናፀዳ ነው፡፡ አላማችን የማንም ክብር የማይደፈርባትና የሁላችንም ሉዓላዊነት የሚከበርባት ልጆቻችንም በኩራት የሚኖሩበትን ሀገር መፍጠር ነው፡፡

7. የአገዛዙ የአፈና እርምጃዎችና በህዝብ ዘንድ ሽብርን ለመንዛት የሚያደርጋቸው የሀሰት ዶሴዎች ለተጨማሪ ትግል መነሳት እንዳለብን የሚያስገነዝቡ እንጂ ፈፅሞ ወደኋላ እንድናይ የሚያደርጉን አለመሆናቸው፡፡

8. በየጊዜው የአቋማችንን፣ የትግል ስልታችንን ትክክለኛነት መፈተሽ በወቅቱም እርምት መውሰድ ወሳኝ ነው፡፡

9. ሁልጊዜም ቢሆን ተሳስተን ገዥዎቻችን መጠላት፣ ለበቀል መዘጋጀትም ሆነ በእነርሱ ላይ በመዛት ወደፊት በሚመጣው ንጋት ስጋት እንዲገባቸው ማድረግ አያስፈልግም፡፡ አይገባምም፡፡

10. አገዛዙ ለህዝብ ፈቃድ ለመገዛት ተነሳሽነት ሲወስድ ማበረታታት እንጂ እንደተዳከመና እንደተንበረከከ እንዲሰማው ማድረግ ተገቢ አይደለም፡፡

11. የኢትዮጵያን ህዝብ ለዘመናት ከስብዕና ሚዛን ያወረደውን የጭቆና ስርዓት መታገል የህይወት ዘመናችን ዓላማ አልፋና ኦሜጋ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በግለሰብ ደረጃ ያሉን ህልሞችና ጥቅሞች ሊሳኩ የሚችሉት ትልቁ ችግራችንን በጋራ ስንፈታ ነው፡፡ ሁለንተናችን አንድ ላይ የተገመደ መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት አይገባንም፡፡

12. በረጅሙ ታሪካችን ተሳክቶ የማያውቀውን የድሎች ሁሉ አውራ ማስመዝገብ የምንችለው ትግሉ የሚጠይቀውን የመስዋዕትነት ደረጃ ከወዲሁ ተረድተን በስነ-ልቦናም ስንዘጋጅ ነው፡፡ ምናልባት አንዳንዶቻችን የትግሉ ፍሬ ተቋዳሾች ለመሆንም እንደርስ ይሆናል፤ መንገዳችን ላይ መታሰርና መንገላታት ብቻ ሳይሆን ሞትም አድፍጦ ሊጠብቀን ይችላል፡፡ ይኽንንም አውቀን በቁርጠኝነት መግፋት ብቻ ነው ያለን አማራጭ፡፡

13. ሁልጊዜም በአቋራጭ እና የትግል አጋሮቻችን መስዋዕት በማድረግ ለውጤት ለመብቃት መሞከር አይገባንም፡፡ ትግላችን ግልፅነትና ንፅህና የተሟላ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ነገ ልንፈጥር የምንመኘውን መልካም ነገር፣ ዛሬ በምናደርገው መልካም ተግባሮች የተሞላ መሆን ማስመስከር አለብንና፡፡

14. የአገዛዙን ባህሪዎችና ‹‹የእግር ቆረጣ›› ስልቶች ቀድሞ በመረዳት የተጠና አፀፋዊ እርምጃ ለመውሰድ አስቀድሞ መዘጋጀትም ያስፈልጋል፡፡

15. በዘረኝነት ወጥመድ ተጠልፎ ላለመውደቅ መጠንቀቁም ተገቢ ይመስለኛል፡፡ አገዘዙ ስልጣን ላይ መቆየት እስከቻለ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘረኝነት ወረርሽኝ ቢጠቀም አንዳች ቅሬታ የሚገባው አይመስልም፡፡ ያዝ ለቀቅ እያደረገ ሲንቀሳቀስ እንደምናየው ስልጣኑን የሚነቀንቅ ከመሰለው የሃይማኖት አሊያም የዘር ግጭት ቀስቅሶ መልሶ እራሱን ግጭት አርጋቢና መፍትሄ ፈላጊ አድርጐ ለማቅረብ ይሞክር ይሆናል፡፡ በእኛ በኩል ሊያዝ የሚገባው ግልፅ አቋም በየትኛውም ዘመን ቢሆን አንዱ ህዝብ ሌላውን ጨቁኖ ባለማወቁ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በየትኛውም ወቅት ቢሆን ኢትዮጵያውያን አማኞች የወንድሞቻቸውን የማምለክ ነፃነት ተጋፍተው አያውቁም፡፡

ሕዝብ በጋራ የአምባገነን መሪዎች የአፈና ሰለባ ነው፡፡ ሰውን በአስተሳሰቡ እንጂ በዘሩ መመዘን የጀመርን ቀን ያን ጊዜ ከሰብዓዊነት ሚዛን እንወጣለን፤ ከስልጣኔ ሃዲድ እንስታለን፡፡ የሰላማዊ ትግል የመጨረሻ ግብ ፍቅር፣ ወንድማማችና አስተማማኝ ነፃነት ሆኖ ሳለ ለዘረኝነት እድል በሰጠን መጠን የትግላችን አላማ ይከሽፋል፡፡ ዘረኝነት ኢሰብዓዊነት ነው፡፡ ዘረኝነት ከትንሽና ክፋት ከተጠናወተው ሰብዕና የሚመነጭ መርዝ ነው፡፡ በዘረኝነት ሰንሰለት ተጠፍንገን ለውጤት ለመብቃት ብንሰራም ፈጣሪም ከእኛ ጋር አይቆምም፤ ዓላማው በሰው ልጆች መካከል ፍቅርና አንድነት እንጂ ጥላቻና መለያየት አይደለም፡፡ ጊዜም ከእኛ ጋር አይተባበርም፡፡ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እኩልነት፣ ነፃነትና ክብር ከልብ ስንቆም ያን ጊዜ የፈጣሪ ሀያል ክንድ ከእኛ ጋር ይሆናል፡፡

16. ሚስጥራዊነትና ሰላማዊ ትግል ጋብቻ ሊፈፅሙ አይገባም፡፡ የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ ውጤታቸውም ጭምር በይፋ ማወቅ ለሚፈልግ ሁሉ ግልፅ ማድረግ ይገባል፡፡ አገዛዙ እንኳን በሚስጥር የሚደረግ እንቅስቃሴ አግኝቶ በይፋ የሚደረጉ የትግል እንቅስቃሴዎችንም እስካልተመቹት ድረስ አይኑን በጨው ታጥቦ የሽብር ካባ እየደረበ ትግሉን ለማምከን ሲሞክር እያየን ነው፡፡ የአገዛዙ ክፉ ሃሳብና ተግባር እንዳለ ሁኖ ግልፅነት በህዝብና በትግሉ መካከል ያለውን ቁርኝት ያጠብቀዋል፡፡ ህዝቡም የፕሮፓጋንዳ ሰለባ እንዳይሆን ይረደል፡፡ ስለዚህ በምንም አይነት መልኩ ከመጋረጃ ጀርባ የሚደረጉ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች ሊኖሩ አይገባም፡፡

17. የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች ትኩረት በማዕከል በሚደረግ ዝግጅት ብቻ ሳይሆን በየአካባቢው ያሉ አባላት አጠገባቸው ባሉ አመራሮች አማካኝነት በተጨባጭ ችግሮች፣ በእውቀትና በጥሩ ዝግጅት ላይ የተመሰረቱ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ሲችሉ ለትግሉ ግብዐት ይሆናሉና፡፡ ሌሎች የፓርቲ ቅርንጫፎችም ከእነርሱ ተሞክሮ እንዲወሰዱ ማድርግ በተቻለ መጠንም በየቦታው ያሉ አባላትና ነዋሪው ህዝብ ስለሰላማዊ ትግል ተጨባጭ ትምህርት በመቅሰም እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

18. የሰላማዊ ትግል ፈርጦች የሆኑት ማህተመ ጋንዲና ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር በተለያየ ወቅት የተናገሩትን ተመሳሳይ ይዘት ያለውን ሃሳባቸውን አፅንዎት ሰጥተን ልንወስደው ይገባል፡፡ ማህተመ ጋንዲ ‹‹ማንም ሰው ያለፈቃዱ አንዳች ነገር እንዲያደርግ ምንም አይነት ምድራዊ ሃይል ሊያስገድደው አይችልም፡፡›› ሲሉ፣ ዶ/ር ኪንግም ‹‹እስካልተጐነበስን ድረስ ማንም ሊጋልበን አይችልም፡፡›› ማለቱ ይታወሳል፡፡ ይህ አንድ አይነት መልዕክት የሚያስተላልፈው የሁለቱም የነፃነት ታጋዮች አባባል በየትኛውም ሀገር በጭቆና ቀንበር ስር ለሚማቅቅ ህዝብ የሚሰራ እውነታ ነው፡፡ ስለዚህም ከቆምንለት ህዝባዊ፣ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የተመሰረተባት የወንድማማችነት፣ የፍቅርና የነፃነት ማማ የሆነች ሀገር የመገንባት ግባችን ሊመልሰን የሚችል አንዳች ሃይል እንደሌለ ተገንዝበን በፅናትና በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይገባናል፡፡

እንደ መውጫ

ከመተኛት አልፎ እንደ ልብ መንቀሳቀስ በማይቻልበት ጠባብክ የእስር ክፍሌ ሆኜ ጎኔን ወለል ላይ፣ ጆሮዬን ወደምድር አስጠግቼ ልዳበስውና ልጨብጠው የማልችለውን ድምፅ ላደምጥ ሞከርኩ፤ እናም የአለፈው እና የአሁኑን የዘመን ዱካ ከእነአፈ እና ግሳንግሱ እየራቀ ሲሄድ፤ የመጭው ዘመን የነፃነት ድምፅና ጭቆናን የማይቀበል ትውልድ ኮቴ እየቀረበ ሲመጣ ይሰማኛል፡፡ ይህ ድምፅ ዕውን እንዲሆን ጊዜውም እንዲፈጥን፣ አባቶቻችን የዳር ድንበር ነፃነት ለማስከበር እንደዘመቱት እኛም የሰላም፣ የፍቅር፣ የወንድማማችነትና የፅናት ሰይፍ ታጥቀን የመትመም ለነገ የማያድር ሀላፊነት አለብን፡፡

ጉዞአችን ምንም ያህል አዝጋሚና በውጣ ውረድ የተሞላ ቢሆንም የምንወዳትን አዛውንት ሀገራችንን ከዘመናት የስቃይ ፅንሷ ነፃነትን የምትገላገልበት ወቅት ስለመቅረቡ ለሰከንድም አልጠራጥርም፡፡ የሐምሌና ነሐሴ ድቅድቅቅ ጨለማ፣ አጥንት ሰብሮ የሚገባ ብርድ ያኮራመታቸው እፀዋት በመስከረም ወር ከአፅናፍ አፅናፍ በሚዋኘው የብርሃን ጅረት ሁለንተናቸው ተፍታቶ ለአይን የሚማርኩ የተፈጥሮ ፀጋዎች መሆናቸውን በኩራት እንደሚያውጁ ሁሉ፣ ኢትዮጵያውያንም ዕድሜ ጠገቡን የአገዛዝ ቀንበር ከጫንቃችን አውርደን በመጣል፣ ሀገራችን ከዳር ድንበር ነፃነት ጋር ብቻ ተያይዛ የምትጠቀስ አለመሆኗን በተጨባጭ በማረጋገጥ በኩራት በሀገራችን መኖር እንጀምራለን፡፡ ሀገራችን የሰብዓዊ ክብር ማማ የምትሆንበት ዘመን እነሆ እየገሰገሰ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ያ ዘመን በመሬታችን ሲደርስ ‹‹ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና…›› የሚለውን የኩኩ ሰብስቤ ዜማ ከተወሰኑ የግጥም ማስተካከያዎች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን ከልብ መዘመራችንም አይቀሬ እንደሆነ አምናለሁ፡፡

አዛውንቷ ሀገራችን የሰብዓዊ ክብር ማማ፣ ‹‹የአፍሪካ ገናና›› ትሆን ዘንድ ነፃነትን በእርጋታ፣ በትዕግስትና አስተዋይነት በተሞላበት ሁኔታ የምናዋልድ ጥበበኛ ሀኪሞ ልንሆን ይገባናል፡፡ ሀገራችን በተለያየ ወቅት ነፃነትን ብታረግዝም ፅንሱን ከእነነፍሱ ለማዋለድ እስከዛሬ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ያልተሳኩ ነፃነትን የማዋለድ ጥረቶችም በባለታሪኳ ሀገራችን ላይ አገዛዙ እረግጦ በመግዛት ለመቀጠል የሚያደርገው የሞት ሽረት ትግል ሲጨመርበት፣ ሀገራችንን ፈፅሞ ወደ ማንመኘው የውድቀት አፋፍ ይዟት እንዳይወርድ ጥብቅ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ ይኽን ማድረግ ካልቻልን በምክንያት የማንመራ፣ በስሜትና ኋላቀርነት አረንቋ የምንዳክር ልጆቻችን የሚያፍሩብን፣ መጭው ትውልድ የሚወቅሰን አባቶች እንዳንሆን ስጋቴ ፅኑ ነው፡፡

ስለዚህ በድቅድቁ የጭቆና ሌሊት ላይ ለዘላለም የማትጠልቅ የነፃነት ፀሐይ እስትከሰት ትግላችን ሊቀጥል የገባዋል፤ በድቅድቁ የአፈና ሌሊት ጨረቃ ያለማቋረጥ እስክትሰለጥን ጤፍ የሚያስለቅም ጣፋጭ ፍቅር የሚያስኮመኩም፣ ዜጐች ያለአንዳች ስጋት የሚመላለሱበትና የዱር አራዊትም ጭምር ለአደን ያለመከልከል እንዲወጡ የሚያስችል ብርሃኗን በምድራችን ላይ እስክትረጭ ትግላችን ከቀድሞ በበለጠ ደረጃ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፤ ሀገራችን የረጅም ዘመን እርግዝናዋን በሰላም ተገላግከላ የምድር ሁሉ ፈርጥ እስክትባል ድረስ የነፃነትንና የወንድማማችነት ንጋት የተራባችሁ ኢትዮጵየውያን ሁሉ የፍቅርና የፅናት ዝናራችሁን ታጥቃችሁ ትግላችሁን ቀጥሉ፡፡ አዎ! ነፃነት እንደቀትር ብርሃን ፍቅርም እንደሃይለኛ ጅረት የሀገራችን ምድር ሞልቶ ይፍሰስ!! ነፃናት፣ ነፃነት፣ ነፃነት፤ እደግመዋለሁ አሁንም ነፃነት!!!

የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጥ ሰው ማን ይሁን?

$
0
0

የ2006 ዓ.ም አዲሱን ዓመት ልንቀበል የቀሩን ጥቂት ቀናት ብቻ ናቸው። በየዓመቱ እንደምናደርገው ሁሉ የዚህን ዓመት የዘ-ሐበሻን ምርጥ ሰው ስለምንሰይም የእርስዎን ምርጥ ሰው የሚሉትን በinfo@zehabesha.com ለምን ያንን ሰው ሊመርጡ እንደቻሉ ከትንሽ ማብራሪያ ጋር ይጻፉልን። ውጤቱን በአዲሱ ዓመት ዋዜማ እናሳውቃችኋለን።
ዕውነት ያሸንፋል!!
zehabesha

የቀድሞው ገራፊው የደህነት ሹም በእስር ቤት እየተገረፈ ነው – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

weldesilaseከአዲስ አበባ ፖሊስ ምንጮች አሁን በደረሰኝ መረጃ የአገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊ የነበረው አረመኔው ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ መገረፉን አስታውቀዋል። የአዜብና መለስ ቀኝ እጅ የነበረው ይህ ጨካኝ የደህንነት ሹም በስልጣን በነበረበት ወቅት እነ ጄኔራል አሳምነውን በመደብደብ፣ አይናቸውን በቦክስ በመምታት ከፍተኛ የጭካኔ ተግባር ይፈፅም እንደነበረ ምንጮች አስታውሰዋል። በ1997-98 ዓ.ም በሺህ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ወገኖች እንዲገደሉ፣ እንዲታሰሩና አሰቃቂ ግፍ እንዲፈፀምባቸው ያደረገው ወ/ስላሴ መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል። በርካታ ሰዎች ከመግረፍና ከማሰቃየት ባለፈ በጥይት ደብድቦ ይገድል እነደነበረ አመልክተዋል። የቤተመንግስት የጥበቃ ሃላፊ አቶ ዘርኡ መለስ አንገታቸውን በስለት በማረድ እንዲሁም የመንገድ ት/ሚኒስትሩን አቶ አየነው ቢተውልኝን በገመድ አንቆ የገደለው ወ/ስላሴ መሆኑን ከዚህ ቀደም መገለፁ ይታወሳል። ወ/ስላሴ በትላንትናው እና በዛሬው እለት ሁለት ጊዜ መገረፉን ምንጮች አረጋግጠዋል።

በአንድነት ፓርቲ ላይ የሚደርሰው ወከባ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚታየው ምዝበራ አንድ የፖሊስ ኢንስፔክተር መገደላቸው የእለቱ ዋና ዋና የዜና ርእሶች ናቸው

$
0
0

በአዳማ/ ናዝሬት  የአንድነት ፓርቲ አባላት መዋከባቸው ታውቀ

ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በከተማዋ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ የቅስቀሳ ወረቆቶችን ሲበትኑ የነበሩ ወጣቶች ለአጭር ጊዜ ተይዘው ተፈተዋል። ፓርቲው ሰለማዊ ሰልፍ እንዲአካሂደ ፈቃድ ከተሰጠው በሁዋላ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እንጅ ወረቀት የመበተን ፈቃድ አልተሰጣችሁም በሚል ሰበብ ወጣቶቹ እንዲታሰሩ መደረጉ ታውቋል።

ኢሳት ከኢህአዴግ የአዳማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ባገኘው አስተማማኝ መረጃ ፣ ፖሊሶችና የደህንነት ሀይሎች ፓርቲው የሚያደርገውን ቅስቀሳ እንዲያስተጓጉሉ ተልእኮ ተሰጥቷቸዋል። በኦሮሚያ ክልል ነፍጠኞች ተመልሰው ስልጣን የሚይዙበት እድል ሊፈቀድላቸው አይገባም በማለት የኦህዴድ አመራሮች በመናገር ላይ ናቸው።

ከእነዚሁ ምንጮች ለመረዳት እንደሚቻለው የተቃዋሚ ድርጅቶች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣ በግንባሩ ውስጥ ከሚታየው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ፣ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች አስጨንቋቸዋል። ከሁሉም የኢህአዴግ ድርጅቶች  በኦህዴድ አባላት ዘንድ ከፍተኛ አለመረጋጋትና ተስፋ መቁረጥ እንደሚታይ የሚገልጹት ምንጮች ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋቱንም ይገልጻሉ።

የአንድነት ፓርቲ በናዝሬት የሚያካሂደው ሰልፍ ለኦህዴድ ከፍተኛ ራስ ምታት ሆናል በማለት እነዚሁ ምንጮች ተናግረዋል። በሚቀጥሉት ተከታታይ ቀናትም ወከባው እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

አንድነት ፓርቲ በባሌ ሮቤ ለማካሄድ አቅዶት የነበረው ሰልፍ በኦህዴድ አመራሮች እንዲስተጓጎል መደረጉ ይታወቃል።

የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚ/ር በትላንትናው ዕለት በሒልተን ሆቴል ድንገት በጠራው የእራት ግብዣ አዲሱ ሚኒስትርን ከጋዜጠኞችና የኮምኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር አስተዋወቀ፡፡

$
0
0

ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ አቶ በረከት ስምኦንን በመተካት በሚኒስትርነት ወደ ጽ/ቤቱ የመጡት አቶ ሬድዋን ሁሴንን ያስተዋወቁት አቶ ሽመልስ ከማል ሲሆኑ ሰውየው ከሚዲያ ጋር ባላቸው ቅርበት፣በአንደበተ ርዕቱነታቸው፣በፖለቲካ ዕውቀታቸው የላቁ መሆናቸውን ለጋዜጠኞች በመንገር አስተዋውቀዋቸዋል፡፡

ከሳምንት በፊት ከዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተርነት ተነስተው በመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት በሚኒስትር ዴኤታነት ማዕረግ የተሾሙት አቶ እውነቱ ደበላም በተመሳሳይ መንገድ ተዋውቀዋል፡፡ አቶ እውነቱ ወደ ዱር እንስሳ ዳይሬክተርነት ከመዛወራቸው በፊት የፌደራል ጉዳዮች ባለስልጣን፣ ቀደም ብሎ ደግሞ የኦሮምያ ክልል የደህንነት ክፍል ሀላፊ ሆነው ሰርተዋል።

አቶ እውነቱ ከአንድ ዓመት በፊት በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሃላፊነት በሚሰሩበት  ወቅት ከሙስሊሙ ጋር በተያያዘ በነራቸው የከረረ አቋም ይታወቃሉ፡፡

አቶ ሬድዋን ጽ/ቤቱ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከመግለጽ ባለፈ አዲስ ዕቅድ ያላቸው ስለመሆኑ ያሉት ነገር የለም፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የመንግስትና የግል ሚዲያ መሪዎች፣ጋዜጠኞች፣የፌዴራልና የክልል መ/ቤቶች የኮምኒኬሽን ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

አቶ በረከት ስምኦን የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤትን በደቡብ አፍሪካ አቻ መ/ቤት ሞዴል አስጠንተው ስራ ከጀመሩ በሃላ በየሳምንቱ ዓርብ ለጋዜጠኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ከመስጠት ጀምሮ በየስድስት ወሩ የጠ/ሚኒስትሩን ከጋዜጠኞች ጋር በማገናኘት ለመስራት ሙከራ ያደረጉ ቢሆንም በተለይ የመ/ቤቱ አንድ ሚኒስትር ዴኤታ ከአገር ከኮበለሉ በህዋላ ይህ ጅምር ብዙም ሳይራመድ እንዲቆም መደረጉ ይታወሳል።

ኢህአዴግ በአገሪቱ ያሉ የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ከግንባሩ መሪዎች በሚተላለፍ ወርሀዊ መመሪያ መሰረት ስራቸውን የሚሰሩበትን አዲስ አሰራር ቀይሷል።

የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ገጠመው፡፡

$
0
0

ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩኒቨርስቲው የማስፋፊያ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ መንግሥት በተመደበ 859 ሚሊዮን 514 ሺ 332 ብር ከ42 ሳንቲም በ‹‹CDS consultancy›› ድርጅት አማካሪነት እና በሌሎች 15 ተቋራጮች ከ2001 ዓ/ም እስከ 2003 ዓ/ም ባሉት ጊዚያት  ተጀምሮ በመካሄድ ላይ ነው።

አጠቃላይ ፕሮጀክቶቹን ለማጠናቀቅ የተያዘው የጊዜ ሠሌዳ ዝቅተኛው 2 ወር ከ15 ቀናት ከፍተኛው ደግሞ 49 ወራት ነው፡፡ በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ እየተከናወኑ ከሚገኙ 15 የተለያዩ ግንባታዎች መካከል እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2005 ዓ/ም የሁለት ፕሮጀክቶች  የፊዚካል አፈጻጸም ከ 43  እስከ  45 በመቶ ከደርሰ በኋላ በመቆሙ  ዩኒቨርስቲው በጥሬ ገንዘብ 445 ሚሊየን ብር ለኪሳራ እንዲዳረግ መደረጉን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።

በአሁኑ ስዓት የተቌረጡት ፕሮጀክቶች የሚገኙበት ደረጃ ተገምግሞና በንብረቶች ላይ ቆጠራ ተደርጎ አዲስ ጨረታ በፋካሊቲው ባለቤትነት ለማውጣት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ ይህም አዲስ ጫራታ ዩኒቨርስቲው አስቀድሞ በእቅድ ያልያዘው ተጨማሪ 500 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ወጭ እንደሚጠይቀው ታውቋል፡፡

በዩኒቨርስቲው የተያዙት ሌሎች ፕሮጀክቶችም ከመጠናቀቂያ ጊዚያቸው እንደዘገዩ መረጃው ያመለክታል። የግንባታ ዕቃዎች እጥረት፣ ፣ አንዳንድ ኮንትራክተሮች የተሰጣቸውን ሥራ በወቅቱ አለማከናዎናቸውን ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ አለመኖር ፣ የአንዳንድ ፕሮጀክቶች የማጠናቀቂያ  ወጪ መጨመር እና የክፍያ መዘግየት የፕሮጀክቶችን እድሜ እንዳራዘመ ዩኒቨርስቲው ይገልጻል።

በመላው ኢትዩጵያ የሚገኙ ኮሌጆች እና የዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ጥራት ከሌለው የጫራታ ስርዓት ጋር በተገናኝ በብዙ ሚሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ እንደሚያባክኑ በጄኔራል ኦዲተር መስሪያ ቤት የተሰራ ጥናት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማስፋፊያ ግንባታዎች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሆነ ሙስና እየተፈጸመ መሆኑን የውስጥ ምንጮች ይገልጻሉ። ጸረ ሙስና ኮሚሽን በዩኒቨርስቲው ላይ የጀመረው ምርመራ ይኑር አይኑር ለማጣራት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። በጉዳዩ ዙሪያ የዩኒቨርስቲውን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረግነው ሙከራም እንዲሁ አልተሳካም።

የግንባታው ዘርፍ አደጋ ውስጥ መዘፈቁን እና ለጥቂት ባለስልጣናት እና አንዳንድ ነጋዴዎች መክበሪያ መሆኑን የኢህአዴግ ልሳን የሆነው ዘመን መጽሄት በቅርቡ ዘግባለች።

Viewing all 13695 articles
Browse latest View live

<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>