
እነ እስከማውቀው ድረስ የትዊተር አካውንታቸው አልተጠለፈም። ምንሊክ ሳልሳዊ
ሰሞኑን በብአደን ውስጥ የተነሳውን የአቶ አለምነህ እና ተያያዥ የለውጥ ጉዳይ እና የአይሮፕላን ጠለፋ/ እገታ በኢሕአደግ አባላት የተነሱትን እና ሕዝቡ የሚያሰማውን ጉምጉምታ አቅጣጫ ለመቀየር የተደረገ ወያነያዊ የማዘናጊያ ስልት ነው።
ኢትዮጵያውያን ባህላችንን እና የወንጀለኛ መቅጫ ህጋችንን ከድሮም ስለምናውቀው ወይዘሮዋ የተነፈሱ አሊያም የጻፉት ራሳቸው መሆናቸውን በቂ ማረጋገጫዎች ከመኖራቸውም በላይ እነው ራሰ በትዊተር ገጻቸው ላይ መልስ ከመስጠት አንስቶ በግል በመልእክት ሳናግረቸው ያመኑበት መሆኑን አረጋግጠው ሳለ የወያነ መንግስት የሳቸውን ጉዳይ መነጋገሪያ አድርጎ የሰሞኑን ህዝባዊ ጥያቀዎችን በመሸፋፈን ለማዘናጊያነት የተጠቀሙበት ስልት ነው። የትዊተር ገጻቸውን ራሳቸው ዘጉት እንጂ አልተጠለፈም ሃሰት ነው።
ፌስቡክ እና ትዊተር በፍጹም ሊጠለፉ የማይችሉ ሶሻል ኔትወርኮች ናቸው ፣ ያልተማረውን ሰው ያታሉት ...https (Hypertext Transfer Protocol Secure ደዲኬቲቭ ሰርቨር የሚባለው ሰርቨር ያላቸው ሲሆን በማይክሮ ሰከን ሁሉንም መረጃዎች ገልብጦ ለማውጣት ፈጣን የሆነ ቅልጥፍና ያለው እና ጠላፊዎች ሲመጡ ለሰኩሪቲ ሲስተም ፕሮቶኮል ኢንጂኒየር የሚጠቁም ኢለመንት ወይንም ኮድ አላቸው ስለዚህ ምንም ነገር ሊደረግ የማይችል ነገር ነው ፣........ እንደ እኛ አይነት ዌብ ሳይት ያላቸው ሰዎች ቢሉ ይቻላል :: ምክንያቱም የምንጠቀመው የተከራየ ሰርቨር ሲሆን የፈለገ ደዲኬቲቭ ሰርቨር ብንጠቀም በአንድ ሰርቨር ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዌብ ሳይቶች ስለሚሞሉበት ለማመልከት ይቸግረዋል ...የነ ትውተር እና ፌስቡክ ግን እራሱን የቻለ ሰርቨር ያላቸው ትልቅ ድርጅት ነው ፣እንደዚያማ ቢሆን ኖሮ እንደ እነ ቢቢሲ እና ሲኤን ኤን ያሉ የመረጃ ድርጅቶች ኤፍቢአይን ጨምሮ ትውተር ባልተጠቀሙ ነበር !
አይሮፕላን ተጠለፈ የአቶ አለምነህ ድምጽ ተጠለፈ የወይዘሮ ዘነቡ አካውንት ተጠለፈ ..... አሁን የቀረው ማነው...? ? ? ምንሊክ ሳልሳዊ