በተያዬ ጊዜ ሰማያዊ ፓርቲን የሚመለከት በርካታ ጽሁፎችን ለማየት ሞከርኩ ሁሉም ሰማያዊ ፓርቲን የሚወቀሱ ሆነው አገኘኋቸው፡፡ እኔ በእርግጥ ሰማያዊ ፓርቲ በተደጋጋሚ ብቻውን በመሄድ የዚህን ሀገር ትግል እንደሚለውጥ ሲናገር መስማቱ የዕለት ተዕለት ጉዳይ ሆኖ ቢሰነብትም ቅሉ በእነርሱ ከመቀየም ፓረቲውን ወደፓረቲ ደረደጃ እንዲድግ ቢሰራ ጥሩ ነው እላለሁ፡፡ ይህንን የሰማያዊ ፓርቲ የተናጠል ጉዞ ደግሞ በርካቶች የጠሉት ይመስላል፡፡ እኔ ግን ሰማያዊ ፓርቲን ወደ ፓረቲነት ማምጣቱ ከወቀሳ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ በፓርቲው ውስጥ ያሉት ታጋዮች ዕድሜ ከገንዛቤ ገብቶ ሁላችንም በአንድነት ፓርቲውን ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ እንዲችሉ ልጆቹን ማገዝ ያስፈልጋል፡፡ እኔ እንደሚመስለኝ ልጆቹ የግንዛቤ ችግር እንጂ ኢተዮጰያዊነት ላይ ችግር ያለባቸው አይመስለኝም፡፡
ለምሳሌ አንድ የተቃሚ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ካዘጋጀ ያንን መደገፍ ሲገባ በዚያን ዕለት ሰልፉን አንድ ላይ ሆኖ መተጋገዝ ተገቢ ሆኖ እያለ፣ በዚያው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ ለብቻ ለማድረግ መሞከር የብቃት ችግር እንጂ የክፋት አደለደም እላለሁ፡፡
ምክንያቱም ሰልፉን አልተቃወሙም ። ነገር ግን በአንድ ከመሰለፍና ትግሉን ከማጠናከር ለብቻ መሄድ መምረጣቸው በራሱ ራስ ወዳድነት ስለሚታይበት ማለቴ ነው፡፡ ልጅ ሊሮጥ ቢችልም አባቱን ሊቀድም እንደማይችል የሀገራችን ብሂል ያስረዳል፡፡ ግን መቅደም ባይችልም ሮጦ ጉልበቱን እንዳይጨርስ የማይጠቅም ሩጫ እንዳይሮጥ ልጁን መምከር እንደሚያስፈልግ ሁሉ ፓርቲውን ከማውገዝ እንዲበቃ ማገዝ ተገቢ ይመስለኛል፡፡
እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ የሚልን ሰው የተሸለ አዋቂ እንዳለ ማሳየት ከኔ በቀር ሌላ ሰው የለም የሚልን ሰው አቲካራ ከመግጠም በአጠገቡ ያሉትን ሰዎች እንዲታዩት ዓይኑን መግለጥ ያስፈልጋል፡፡
እኛ ለዴሞክራሲ እንጂ ለሥልጣን መታገል ያለብን አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ዶዘር በሰራው መንገድ አይሄድም አንድ መንገድ ሲሰራ የመጀመሪያ መንገድ ጠራጊ ዶዘር ነው፡፡ ሆኖም መንገዱ ተሰርቶ ካለቀ በሁዋላ ዶዘር በሰራው መንገድ ላይ ተጭኖ ያልፋል፡፡ እንደዚሁም አሁን ያለን እኛ ለቀጣዩ ትውልድ ነጻነት መታገል እንጂ ዛሬውኑ ለውጡ ሲመጣ እኔ የመጀመሪያው ባለሥልጣን እንሆናለን ብለን ካሰብን ትግሉ ከአምባገነኖች ጋር ሳይሆን እርስ በርስ ይሆንና የህዝቡን ትግል መና እናስቀረዋለን፡፡