Quantcast
Channel: Amharic News & Opinion
Viewing all 13695 articles
Browse latest View live

በበባህርዳር አንድ የፖሊስ ኢንስፔክተር ተገደለ

$
0
0

ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወረዳ ሁለት እየተባለ ለሚጠራው አካባቢ ሀላፊ የነበረው ኢንስፔክተር ምትኩ ዛሬ ጠዋት በመኪና ተገጭቶ ሞቷል።

ድርጊቱን የፈጸሙት ሰዎች እስካሁን ያልተያዙ ሲሆን ፣ ጉዳዩን በመመርመር ላይ የሚገኙት ዋና ኢንስፔተር ውበቱ ለኢሳት እንደገለጹት ድርጊቱ በምን ምክንያት እንደተፈጸመ ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ ነው ብለዋል። በግለሰቡ የተከፉ ሰዎች ሆን ብለው ገድለውት አምልጠዋል ይባላል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ኢንስፔክተሩ እስካሁን ያለን መረጃ ይህንን አያመለክትም፣ ይሁን እንጅ ከምርመራው በፊት ምክንያቱን በውል ለማወቅ አይቻልም ብለዋል።

የከተማው የቀበሌ 13 ነዋሪዎች ፣ ሟቹ የፖሊስ አዛዥ የተለያዩ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ይፈጽም እንደነበርና በድርጊቱ የተበሳጩ ሰዎች ገድለውት እንዳመለጡ ተናግረዋል።


ፕሬዚዳንት ኦባማ በሶሪያ ላይ ለሚወስዱት ወታደራዊ ጥቃት ድጋፍ ለማሰባሰብ እየሞከሩ ነው

$
0
0

ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአገራቸውን ወሳኝ ፖለቲከኞች ድጋፍ ያገኙት ፕሬዚዳንት ኦባማ፣ አለማቀፍ ድጋፍ ለማግኘት የሚያደርጉትን ዘመቻ ዛሬ በስዊድን ጀምረዋል።

አለም ያስቀመጠው ቀይ መስመር አለ፣ያም መስመር ” የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን መጠቀም አይቻልም” የሚል ነው፤ አለም ለዚህ ውሳኔው በጋራ ሊቆም ይገባል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

ከአውሮፓ አገራት መካከል  እስካሁን ድረስ ለአሜሪካ እርምጃ ድጋፏን የገለጸችው ፈረንሳይ ብቻ ናት።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን አሜሪካ የጸጥታው ምክር ቤትን ውሳኔ ሳታገኝ የምትስደውን እርምጃ እንደማይደግፉ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ የአሜሪካን ድርጊት ለመቃወም ስለሚወስዱት እርምጃ ግን የተናገሩት ነገር የለም።

#EthiopianDream: Yes, I also have a Dream!

$
0
0
By Zelalem Kibret
 
Half a century ago one of the great personalities of the 20th century, Dr. Martin Luter King Jr. declare his dream to his America and fellow black citizens of that nation. Three months before Dr. King’s Washington declaration, here in Africa the Organization of African Unity (OAU) was established in Addis Ababa, Ethiopia.

The OAU’s choice of Ethiopia as a head quarter is not an accidental decision; rather it is recognition to Ethiopia’s symbolic status in the heart and minds of Black peoples. Ethiopia defeats European conquerors and able to resist the Scramblers of Africa. The black world who is subjugated, conquered and enslaved by sort water invaders takes this Ethiopia’s resistance as a symbol of defiance and Ethiopia itself as a beacon of Freedom.

But, Fifty Years later the symbolic OAU establishment, the black world is still not free. Ethiopia’s bravery and resistance of foreign colonizers seems in vain to establish a JUST Ethiopia. Because Ethiopia, dreamed by the black world as an inspiration is:

A land of Injustice,
A Land of Inequality,
A symbol of Famine and Hunger,
A land of hopeless wonderers,
A forgotten hellish corner of the world…

Even if Ethiopia inspires many to pursuit their freedom and rights, Ethiopia put a yoke of oppression to its citizens. Ethiopia hangs the bell of Freedom afar. Ethiopia ranks its citizens as first class and second class. Ethiopia built the wall of tyranny and dictatorship that becomes a noise to humanity. The Ethiopia that fence itself with fire to protect its sovereignty set its citizens in a fire ablaze within.
But, I know the dusk will give-up to the dawn and I Dream.

I have a dream that one day Ethiopia will rise up and live out its symbolic status of 'The Beacon of Freedom'.

I have a dream that one day Ethiopia will treat its children with the same and equal treatment.

I have a dream that one day Ethiopia will live within the true meaning of ‘Un museo di Popoli - Museum of Peoples’. No privileged! No condemned!

I have a dream that my Ethiopia will hammer the evil of tyranny and dictatorship and instead, embrace Democracy.

I have a dream that one day the land of Ethiopia, will be hunger free and,

I also have a Dream that one day the spring of justice will quench Ethiopia, who is badly starving of it.

To fulfill my dreams,

Let freedom ring from the beautiful lowlands of Dalol to the Mighty Semen Mountains,
Let freedom ring from the mysterious peaks of Bale to the heavenly Forests of Gambella!
Let freedom ring from the giant Stale of Axum to the marvelous walls of Jegol.
Let freedom ring from the rift valleys of Ethiopia to the endless fields of Ogadane.
Let freedom ring from every house of 70 Million Ethiopian farmers to the skies of every urban dwellings.

Yeah, We Shall Overcome!

* Inspired by Dr. King’s ‘I Have a Dream’ Treatise.

የአንድነት ፓርቲ የጠራው የአዲስ አበባው ሰላማዊ ሰልፍ ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በደመቀ ሁኔታ በጥምረት ይደረጋል!

$
0
0

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል መሪ ቃል የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ መስከረም 5/2006 በአዲስ አበባ በሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል፡፡ፓርቲው በተለያዮ የአገሪቱ ክፍሎች ያደረጋቸውን ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በአንክሮ ሲከታተሉ የቆዮት 33 ፓርቲዎች በአዲስ አበባ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በጋራ ለማድረግ ስምምነታቸውን በመግለጽ በዛሬው ዕለት በአንድነት ዋና ጽ/ቤት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
33 ፓርቲዎችን በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ ሔርጫፉ አዴሎ ‹‹አንድነት በህዝባዊ ንቅናቄው ሲያነሳቸው የነበሩ ጥያቄዎች አንድነትን ብቻ የሚመለከቱ አይደሉም ፡፡እኛም የምንታገልላቸው እንዲመለሱ የምንፈልጋቸው ጥያቄዎች በመሆናቸው ትግሉን በአንድነት ለማደረግ ስምምነት ላይ ደርሰናል››ብለዋል፡፡
የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ ስዮም መንገሻ ‹‹አንድነት በአብሮነት የመስራት ስስት የለበትም፡፡እንኳን ከ33 ፓርቲዎች ጋር ይቅርና በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገል ፓርቲ ጋር በሙሉ ለመስራት በራችን ክፍት ነው፡፡››በማለት የፓርቲውን አቋም አንጸባርቀዋል፡፡
አንድነት ፓርቲ በጎንደር፣በደሴ፣በአርባ ምንጭ፣በባሌ ሮቢ፣በወላይታ፣በፍቼና በሌሎች ከተሞች ባደረጋቸው ሰላማዊ ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ያጋጠሙትን የመብት ረገጣዎቸ፣ኢ ህገ መንግስታዊ ጥሰቶች፣ድብደባዎችና ህገ ወጥ እስራቶች በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ይፋ አድርጓል፡፡በፍቼ ድብደባ የደረሰባቸው የፓርቲው ሁለት አባላት ነብዮ ባዘዘውና መሳይ ትኩ በአካል በመቅረብ ለጋጠኞች የደረሰባቸውን ድብደባ አስረድተዋል፡፡እጁ ላይ በድብደባው ምክንያት ስብራት የደረሰበት መሳይ በፋሻ የተጠቀለለ እጁን በማሳየት ‹‹ሁላችንም እናንተ ጋዜጠኞችም ባላችሁ መሳሪያ እስክሪብቶ እውነቱን በመጻፍ ይህንን አምባገነን ስርዓት መታገል ይጋችኋል››ብሏል፡፡
33 ፓርቲዎች በወርሃ መስከረም ቀጠሮ ስለያዙበት የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ያወጡት መግለጫ የሚከተለው ነው፡፡
- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5593#sthash.1nJUhpR6.dpuf934939_487240494685925_524628143_n

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የ3ወር መርሃ-ግብር በታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል!! በአንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

$
0
0

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴ የበለጠ ተጠናክሮ ህዝቡ የትግሉ መሪ ተዋናይና ባለቤትነት እንዲረጋገጥ ላለፉት ሶስት ወራት ፓርቲያችን ባስቀመጠው ስትራቴጂ እቅድ መሠረት ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ ቆይቱዋል፡፡
በሃገራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ማለትም ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መረገጥ ፓርቲያችን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል ሰኔ 13 ቀን 2005 በይፋ ለጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ፖለቲካዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡

ሕዝባዊ ንቅናቄው በእቅድ መመራት ከመጀመሩ በፊት ሀገራችን የምትገኝበትን ነባራዊ ሁኔታና የህዝባችን ተጨባጭ ኑሮ ላይ ጥናት በማድረግ የመፍትሄ አማራጮችን ማቅረቡ የፓርቲያችን አብይ ጥያቄ ሆኖ መገኘቱም የንቅናቄውን ወቅታዊነት ያገናዘበ አድርጎታል፡፡ በእቅዳችን መሰረት በመላው ሃገሪቱ ለመጀመሪያው ዙር በተመረጡ ቦታዎች ያደረግናቸው ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በአባሎቻችን፤ በደጋፊዎቻችንና በህዝባችን ጠንካራ ትግልና መስዋእትነት ንቅናቄው የተሳካ ሲሆን ፓርቲያችን ለተከፈለው ዋጋ ሁሉ አድናቆቱን ይገልፃል፡፡

በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በመታገዝ የፀጥታ ኃይሎች እንቅስቃሴዎቻችንን ለማጨናገፍ ከህግና ሥርዓት ውጪ ማስፈራራት፤ ማሸማቀቅ፤እስራትና ድብደባ በአባሎቻችን ላይ ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የቅስቀሳ ቁሳቁስም በአካባቢ የፀጥታ ሰራተኞች ተዘርፈውብናል፡፡ እንዲሁም ህዝብ በነፃ አስተሳሰብ አማራጩን እንዳይከተል በአካባቢ ካድሬዎችና አመራሮች ማስፈራራትና ዛቻ ደርሶበታል፡፡ መርሃ ግብሩም ከተፈፀመ በኃላም ቢሆን ህዝባዊ ንቅናቄውን የተቀላቀሉ ዜጎቻችን በመኖሪያ ቀያቸው ሰርቶ የማደርና በነፃነት የመኖር መብታቸው አደጋ ላይ ነው በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዘብን በማሸማቀቅ እንደሆነ መገንዘብ ችለናል፡፡ ከህግ ውጭ የገጠሙን መንግስታዊ ተፅእኖዎች ሁሉ ነፃነቱን በተነፈገውና በለውጥ ፈላጊው ህዘባችን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተልኮአችን ሊሳካ ችልዋል፡፡

የሚሊዮኖችን ድምፅ ለማሰባሰብ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያሉ ዜጎቻችን በንቃትና በቁጭት የተሳተፍበት በመሆኑ አመርቂ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ፊርማ የማሰባሰቡ መርሃ ግብር የሚቀጥል ይሆናል፡፡የህዝባዊ ንቅናቄው የመጀመሪያው ዙር መርሃ ግብር በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ መስከረም 5ቀን 2006 በሚደረገው ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እስካሁን ካደረግናቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች ልዩ የሚያደርገው የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይሁንታ ያገኘና ሰላማዊ ሰልፉን በባለድርሻነት የተሳተፉበት መሆኑ ነው፡፡

በአንፃሩ ገዢው ፓርቲ እስካሁን ካወጣቸው አፋኝ ህጎች በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጠናክሮ የመጣውን ህዝባዊ የፖለቲካ ተቃውሞ የበለጠ ለመደፍጠጥ አሳሪ ደንቦች ለማውጣት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተንቀሳቀሰ ለመሆኑ ከገጠመን መልካም አስተዳደር እጦት መገንዘብ ችለናል፡፡
የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ በጠሩት በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የነፃነት ድምፁን እንዲያሰማ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

“የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት”
የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች

ነሐሴ 30 ቀን 2005
አዲስ አበባ934939_487240494685925_524628143_n

የደሴ ፖሊሶች የግፍ ድርጊት – ፍኖተ ነጻነት

$
0
0

አቶ ብስራት አቢ የአንድነት ፓርቲ የደብበ ወሎ ዞን ሰብሳቢ

ዛሬ ነሃሴ 30 በምኖርባት ደሴ ከተማ በተለምዶ ባምቧ ውሃ የተባለው አካባቢ በአንድ መዝናኛ በረንዳ ላይ ከጓደኞቼ ጋር ተቀምጠን እየተጫወትን ነው፡፡ ሰዓቱ 9፡30 ይሆናል፤ ጎዳናው ላይ አንድ የገጠር አለባበስ የለበሰ ሰው ከፖሊሶች ጋር ለፀብ ሲገባበዝ ተመለከትኩት፡፡ ሰውየው ጠጥቷል እናም ፖሊሰቹን ለመተናኮስም ቃጥቶታል፡፡ ፖሊሶቹ የወሰዱት እርምጃ ግን ፍፁም ህግን አስከብራለሁ ከሚል አካል የሚጠበቅ አልነበረም፡፡ ከፖሊስነትም ባለፈ ማዕረግ የደረደሩት ፖሊሶች ሰውየውን በያዘው ቀርከሃ እየተቀባበሉ ቀጥቅጠውት እግርና እግሩን ይዘው መሬት ለመሬት እየጎተቱ በአቅራቢያቸው ወዳለው 4ኛ ፖሊስ ጣቢያ ይዘውት ገቡ፡፡ በግምት ከ1 ሰዓት ቆይታ በኋላ ሰውየው በውሀ ርሶ አንድ እግሩ ለመርገጥ እየተቸገረ ወጣ፡፡ በጣቢያው ውስጥ ምን እንደደረሰበት ለመገመት አልተቸገርኩም፡፡ ግፍ የደረሰበት ሰው ሰክሮ ከፖሊሶች ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባቱ ትክክል አይደለም፤ ሆኖም የሰውየው ስህተት/ጥፋት በምንም አይነት መልኩ ፖሊሶቹ ለፈፀሙት የግፍ ድርጊት ማስተባበያ መሆን የለበትም፡፡
ይህን ግፍ የፈፀሙት ፖሊሶች የደሴ ፖሊሶች ሙሉ ለሙሉ ወከሉም አልወከሉም የሰውን ልጅ እንደከብት መሬት ለመሬት እየጎተቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሲያስገቡ “አረ በህግ” የሚል አንድ ፖሊስ እንኳ መጥፋቱ የ4ኛ ፖሊስ ጣቢያን ባልደረቦች እንደተቋምም ለመውቀስ እገደዳለሁ፡፡ የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብሩ ተዋርዶ ግፍ ሲፈፀምበት እንደመመልከት ምን ልብ የሚሰብር ነገር ይኖራል?
በትግላችን ሰብአዊ መብት የተከበረባት ኢትዮጵያን በቅርቡ እውን እናደርጋለን!!

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት934939_487240494685925_524628143_n

- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5595#sthash.NC76bcCe.dpuf

UTC 16:00 የዓለም ዜና 050913

የሐምሌ ጨረቃ –አንዷለም አራጌ ዋለ (ከቃሊቲ ማጎሪያ)

$
0
0

አንዷለም አራጌ ዋለ Andualem Aragie Walleክፍል ሁለት

በሀገሬ ሰማይ ስር በሚደረገው የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ከኢዴፓ እስከ አንድነት ፓርቲ ድረስ በመሳተፍ ለአስራ ሦስት ዓመታት ያህል የምችለውን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ። ይህ ኹነትም የፓርቲዎችን ጓዳ ፈትሼ ግንዛቤ እንዳገኝ ስላመቻቸልኝ፣ በቀጣይ ህዝባችን የፖለቲካና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ነፃነቱን እንዳያገኝ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው ለማቅረብ እወዳለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...


የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔና ርእስ አስለዋጭ መሳዩ አሳሳቢ ጉዳይ

$
0
0
የቡድን 20 ሃገራት የ 2 ቀናት ጉባዔ፣ ዛሬ በሴንት ፒተርስበርግ ፣ ሩሲያ ተጀምሯል። ጉባዔው፤ በዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ለመወያየትና በተለይም ባለፉት 5 ዓመታት ፣…

የጀርመን የምረጡኝ ክርክር መድረክ

$
0
0
ሶስት ሳምንት ግድም የቀረዉ የፌደራል ጀርመን ምርጫ የአገሪቱን ፖለቲከኞች፤ በየመድረኩ እያፎካከረ እና እያተቻቸ ፤የቃላት ጦርነቱ እየተጋጋለ፤ ህዝቡ የምርጫዉን ቀን በመጠባበቅ ላይ ነዉ።…

Amharic News 1800 UTC –ሴፕቴምበር 05, 2013

$
0
0
News, Cultural Mosaic, Kebele Lives and Environment or Tech…

አወዛጋቢው የጊቤ ግድቦች ጉዳይ

$
0
0
በየዓመቱ ከ 11 በመቶ በላይ ዕድገት እያስመዘገብኩ ነው የሚለው የኢትዮጵያ መንግሥት የኃይል ፍላጎቱን ለማሙዋላት በስፋት ከተያያዛቸው ፕሮጀክቶች መካከል ኣንዱ የጊቤ ወንዝን ተከትለው የሚገነቡት የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች ሲሆኑ…

ESAT Radio: Sep 05

$
0
0
  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ኬንያ ከአለማቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አባልነት ለመልቀቅ ወሰነች

$
0
0

ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ ከአምስት አመታት በፊት የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ በሞቱ ከ1ሺ በላይ ዜጎች የአሁኑ አገሪቱ መሪ ኡሁሩ ኬንያታና ምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ በሰው ልጆች ላይ በተፈጸመ ወንጀል በአለማቀፉ ፍርድ ቤት ተጠያቂዎች ሆነዋል።

ሁለቱም መሪዎች ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ በሚታወቅበት ሰአት አገራቸውን ከፍርድ ቤቱ አባልነት በማስወጣት ራሳቸውን ከጠጠያቂነት ለማዳን የወሰዱት እርምጃ የአገሪቱን ተቃዋሚዎች አስቆጥቷል።

ሁለቱ መሪዎች ከፍርድ ቤቱ ጋር የማይተባበሩ ከሆነ ፍርድ ቤቱ የእስር ማዘዣ እንደሚያወጣ    አስታውቋል።

ለታሰሩት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎችና ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ረዥም ቀጠሮ ሰጠ።

$
0
0

ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በሽብርተኝነት በከሰሳቸውና ጉዳያቸው በመታየት ላይ ባለው የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ በፍርድ ቤት ረዥም ቀጠሮ መሰጠቱ አነጋጋሪ ሆነ።

የኢሳት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ እንዳጠናቀረው መረጃ  ታሳሪዎቹ ብይን ለመስማት  ከ3 ወር በላይ መጠበቅ አለባቸው።
በሐምሌ ወር  2004 ኣመተ ምህረት የፈጠራ ሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው ላለፉት ሀለት ኣመታት በእስር ላይ በሚገኙት የሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ የሃይማኖት አባቶችና ጋዜጠኞች  ብያኔ ለመስጠት  ጉዳያቸውን ሲያስችል የቆየው ፍ/ቤት  ለህዳር 23/2006 ቀጠሮ  ሰጥቷል።

ለአራት ወራት ያህል በማእካላዊ  ወንጀል ምርመራ  ሲገረፉና ሲሰቃዩ ቆይተው በህዳር 2005 በአዲሱ የጸረ ሽብር ሕግ ክስ በተመሰረተባቸው  በነዚሁ እስረኞች ላይ እሰካሁን ድረስ  በከሳሻቸው አሰማኝና በቂ ማስረጃ ሊቀርብባቸው  አልቻለም።

ለረዥም ጊዜ በተጓተተው የችሎት ሂደት የአቃቤ ሕግ  አሉኝ ያላቸውን ሰነዶችና የሰው ምስክሮች  ቢያቀርብም፤ፍርድ ቤቱ  በቂ ማስረጃ ሊቀርብ አለመቻሉን እየተመለከተ ብይን ለመስጠት ለህዳር 23/2006 ቀነ ቀጠሮ መ ስጠቱ ቤተሰቦቻቸውንና ደጋፊዎቻቸውን ሁሉ ያስቆጣ ሆኗል።

“የብይን ቀጠሮ ለመስጠት እንዲህ የረዘመ ጊዜ መስጠት ለምን እንዳስፈለገ ይገባናል፡፡ በዋነኝነትም ታሳሪዎቹን በጊዜ ርዝመት ጠንካራ መንፈሳቸውን ለማዳከምና በዚያውም ፖለቲካዊ ውሳኔ የሚሰጥበትን የፍርድ ሂደት ለማመቻቸትና የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ለመስራት ነው፡፡ የፍርድ ሂደቱ ይህ ነው በሚባል ማስረጃ ሳይመረኮዝ ለአስር ወራት ያክል ቢዘልቅም የችሎት ሂደቱ በፖለቲካዊ ውሳኔዎች የተሞላ ሆኖ ቆይቷል፡፡ አሁን ባለው የችሎት ሂደት ከዚህ በላይ መዝለቅ ባለመቻሉ ችሎቱ ተጨማሪ ጊዜያትን ፖለቲካዊ ውሳኔ ለመስጠት ነው ቀጠሮው የተራዘመው”ብለዋል-ደጋፊዎቻቸው በሰጡት አስተያየት።

ታሳሪዎቹ  የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ የሃይማኖት ሊቃውንት፣ ጋዜጠኞችና አርቲስቶች በአሰልቺና ከሚዲያና ቤተሰብ እይታ ውጪ እንዲሆን በተደረገው የችሎት ሂደት በጣም በርካታ አሳፋሪ ድርጊቶችን ሲመለከቱና ሲታዘቡ መቆየታቸውም ተነግሯል።

አቃቤ ሕግ  በታሳሪዎቹ ላይ 197 ምስክር አለኝ ብሎ ማቅረብ የቻለው 80 ምስክር ብቻ ሲሆን፤ የመንግስት አቃቤ ሕግ  የነበረው አቶ ቴዎድሮስ ባህሩ በቅርቡ  ከአገር ሸሽቶ አሜሪካ መግባቱ ይታወሳል።


የአርበኞች ግንባር አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

$
0
0

ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን ነዋሪ የሆኑት ጸጋው አለሙ፤ ዋስይሁን ንጉሱ፤ ጎዳዳው ፈረደ፤ ማማይ ታከለ እና ተገኝ ሲሳይ የተባሉት ሰዎች በኤርትራ ስልጠና ካገኙ በሁዋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ በትግራይ ክልል ማካይዳ ከተማ መያዛቸውን ፋና ዘግቧል።

ተከሳሾች  ኤርትራ እና አውሮፓ ከሚገኙ የአሸባሪው ድርጅት የተለያዩ አመራሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር አባላትን እየመለመሉ ወደ ኤርትራ መላካቸውን ገልጾ ፣ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት ተረኛ ችሎት ከጸረ ሽብር ህጉ አንጻር የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ ክሱን ለማሰማት ለጥቅምት 7 2006 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ዜጎች ከአርበኞች ግንባር፣ ከግንቦት 7፣ ኦነግና ኦብነግ ጋር በተያያዘ በቃሊቲና በሌሎችም እስር ቤቶች በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ። መንግስት እነዚህን ድርጅቶች በአሸባሪነት መፈረጁ ይታወቃል።

በኢትዮጵያ ከሚሊዮን በላይ በልመና የሚተዳደሩ ሰዎች አሉ ተባለ

$
0
0

ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆች ሲል ባስጠናው እና በዓመቱ መጠናቀቂያ በወርሐ ጳጉሜ ይፋ በሚያደርገው መረጃ እዳመለከተው የልመና ተዳዳሪነት በሐገሪቱ ላይ ጥቁር ጥላውን እያጠላበት ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ የቱሪስቶች የደህንነት ስጋት ከመሆን ባለፈ ለዜጎችም መትረፋቸውን ገልጿል።

በመገባደድ ላይ ባለው በ2005 ዓ.ም ብቻ በአማራ ክልል ከሶስት መቶ ሺ ፣ በትግራይ ከሁለት መቶ ሺ በላይ ዜጎች  በየቤተ ክርስቲያኑ እና በየቤተ እምነቱ ተጠልለው ሲለምኑ፤ ደቡብ እና ሐረሬም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ለማኞች ይገኛሉ። በአዲስ አበባም በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ለማኞች በከተማዋ እንደሚገኙ ይታወቃል።

በኢትዮጵያ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሲኖሩ  8 ሚሊዮን የሚጠጉት ደግሞ በሴፍትኔት ወይም ምግብ ለስራ ታቅፈዋል።

ሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፉን አራዘመ

$
0
0

ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የህግ ክፍልና የተቃውሞ ሰልፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ይድነቃቸው  ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የመስተዳድሩ ባለስልጣናት ቀኑ የበአል ዋዜማ በመሆኑ እና  የንግድ ድርጅቶችም እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት በመሆኑ ሰልፉን ለማስተናገድ እንደማይችሉ በመግለጻቸው ለማራዘም እንደወሰኑ ገልጸዋል።

አንድነት ፓርቲ መስከረም 5፣ 2006 ዓ/ም  የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በመኖሩ በሳምንቱ ሰልፉን ለማካሄድ መወሰናቸውን አስተባባሪው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መስከረም 5 የጠራውን ሰልፍ 33ቱ ፓርቲዎች ድጋፋቸውን በመስጠት በጋራ ለመቀላቀል መወሰናቸውን ፓርቲውና 33ቱ ፓርቲዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ፓርቲዎቹ እንዳሉት ባለፉት 3 ወራት አንድነት ፓርቲ ያወጣው ህዝባዊ ንቅናቄ  የመጀመሪያው ዙር መርሃ ግብር በአዲስ አበባ  መስከረም 5ቀን 2006 በሚደረገው ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል ፡፡

ፓርቲው እንደሚለው የመስከረም 5ቱ ሰላማዊ ሰልፍ የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ይሁንታ ያገኘና ሰላማዊ ሰልፉን በባለድርሻነት የተሳተፉበት በመሆኑ ልዩ ነው።

ፓርቲው ባለፉት 3 ወራት የተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች ከፍተኛ መስዋትነት የጠየቁ ቢሆንም የተሳኩ ነበሩ ብሎአል። ፓርቲው በተንቀሳቀሰባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዝብን በማሸማቀቅ እንደሆነ መገንዘብ መቻሉንም ድርጅቱ አክሎ ገልጿል።

በሌላ በኩል ደግሞ ፓርቲው በአዳማ/ናዝሬት በመጪው እሁድ ለሚያካሂደው ተቃውሞ የቅስቀሳ ወረቀቶችን ለመበትን የሚስለውን ፈቃድ ከወረዳ ባላስልጣናት ለማግኘት ዛሬ  ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። መንግስት በድብቅ ለሁሉም ወረዳዎች ባወረደው መመሪያ የፖለቲካ ድርጅቶች የተቃውሞ ሰልፍ ፈቃድ ቢያገኙ እንኳ፣ ከወረዳዎች የቅስቀሳ ወረቀቶችን ለመበትን ግድ ፈቃድ ማግኘት አለባቸው።

በትናንትናው እለት በቅስቀሳ ስራ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላት ተይዘው ለአጭር ሰአታት ታስረው ተለቀዋል።

በሰማያዊ እና በአንድነት ፓርቲዎች ላይ እየደረሰ ያለው እስርና እንግልት በቀጠለበት ሰአት አለማቀፉ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል መንግስት በህገመንግስቱ የሰፈሩ የዜጎችን መብት እንዲያከብር ጠይቋል።

ሰማያዊ ፓርቲ በመስቀል አደባባይ የጠራውን ሰልፍ ወደ መስከረም 12 ማዘዋወሩን አስታወቀ

$
0
0

blue party(ዘ-ሐበሻ) ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ለጷጉሜ 2 ቀን 2005 ጠርቶት የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ ወደ መስከረም 12 ቀን 2006 ማስተላለፉን ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ አስታወቀ።
ፓርቲው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ “ሰማያዊ ፓርቲ ለነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጠርቶት የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በመንግስት ታጣቂ ኋይሎች ሕገ-አራዊት እርምጃ ከተደናቀፈ በኋላ ፓርቲያችን ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ጳጉሜ 2 ቀን 2005ዓ.ም ሠልፉ በድጋሚ እንደሚካሔድ አስታውቋል፡፡ ሠልፉ የተሳካና ሰላማዊ እንዲሆን በፓርቲ በኩል ልዩ ልዩ ተግባራት ከመከናወናቸው ጎን ለጎን አስፈላጊው የጸጥታ ጥበቃና የአስተዳደር ድጋፍ እንዲሰጠን በህጉ መሰረትም ሠልፉ እውቅና እንዲያገኝ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሰወቂያ ክፍል ነሐሴ 27 ቀን 2005ዓ.ም ደብዳቤ ለማስገባት በአካል ተገኝተን ጠይቀናል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ክፍል ደብዳቢያችንን ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡” ካለ በኋላ ‘በፓርቲው በኩል በሁኔታው ተስፋ ባለመቁረጥ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል የማሳወቂያ ደብዳቤውን ከላይ በተጠቀሰው ቀን የላክን ሲሆን ውጤቱ ግን አሁንም በፖስታ ቤት በኩል የተላከውን ደብዳቤ በእንቢተኝነት አለመቀበል ሆኗል፡፡ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በአስተዳደሩ ፅ/ቤት በመገኘት ከተለያዩ ኃላፊዎች ጋር ለመነጋገር እረጅም ሰዓት የወሰደ ከቢሮ ቢሮ መንከራተት የተሞላበት ደጅ ጥናት ካደረጉ በኋላ በመጨረሻም በከንጺባ ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ም/ኃላፊ ጋር ለመነጋገር ተችሏል፡፡” በማለት ሰልፉን ለማራዘም የወሰነበትን ምክንያት ያብራርል።
“በዚህም ውይይት የጳጉሜ አምስቱ ቀናት በከተማው አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ እድል ለመፍጠርና እራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ በየዓመቱ አስቀድሞ በከተማው ማዕዘናት ያሉ ቦታዎች ለዚህ አገልግሎት ስለሚያዙ በነዚህ ቀናት የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ የማይችሉ መሆኑን አበክረው ገልጸውልናል፡፡ ፓርቲው በከንቲባ ጽ/ቤቱ የቀረበውን ምክንያት ከመረመረ በኋላ የበዓሉ ዋዜማና የዘመን መለወጫ በዓል ካካፋ በኋላ ባሉት ቀናት ሰልፉን ለማድረግ በመወሰን ለጳጉሜ 2 ቀን 2005 ዓም ጠርቶት የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ ወደ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡ የዚህን ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ወዲያውኑ ለሚመለከተው ክፍል በማቅረብ የሰልፉ ማሳወቂያ ደብዳቤ ቀሪ ላይ በማስፈረም ገቢ አድርጓል፡፡” ያለው ሰማያዊ ፓርቲ “በመሆኑም ከለይ በተጠቀሰው ምክንያት ሠልፉ ወደ መስከረም 12 ቀን 2006ዓ.ም መተላለፉን እየገለጽን ከዚህ በፊት የጠራናቸው የተቃውሞ ሰልፎች የተሳኩ እንዲሆኑ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሲቪክ ማሕበራትና በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ላደረጋችሁት ድጋፍ ፓርቲያችን ምስጋናውን እያቀረበ፤ አሁንም ቀጣዩ ሠልፍ በታሰበለት ዓላማ መሠረት የተሳካ እንዲሆን የተለመደ ድጋፋችሁን እንድታደርጉ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡” ብሏል።

‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚያስተኛ አይደለም›› – (አቶ ስብሓት ነጋ)

$
0
0

(ኢትዮ-ምኅዳር ቅጽ 01 ቁጥር 34፤ ረቡዕ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋራ በመተባበር በአዲስ አበባ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ከነሐሴ ፳፩ – ፳፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ‹‹የሃይማኖቶች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት በማጎልበትና ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በማክበር የሀገራችንን የሕዳሴ ጉዞ ለማሳካት እንረባረባለን›› በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ ላይ ‹አቦይ› ስብሐት ነጋ በመገኘት አነጋጋሪ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡ አንጋፋው የህወሓት/ኢሕአዴግ መሥራችና የጀርባ ሰው የሚገልጹት ሐሳብ የመንግሥትን ቀጣይ ርምጃ ያመላክታል በሚል በአጭሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
sebehat nega  mehedar
አክራሪነት ይዘቱ ሃይማኖታዊ እንዳልኾነ ሕዝቡም የተገነዘበው ጉዳይ መኾኑ ተደጋግሞ ተገልጧል፡፡ ሃይማኖትን የፖሊቲካ መድረክ የሚያደርጉት የሽብርተኝነት ተግባር ለመፈጸም መኾኑ ግልጽ የኾነልን ይመስለኛል፡፡

አክራሪነትና ጽንፈኝነት በሃይማኖት ውስጥ ማስገባት የመጀመሪያው አደጋ ሲኾን በዚህ ኹኔታ ሃይማኖቱም ሃይማኖት አይኾንም፡፡ አማኞች፣ አክራሪነትና ጽንፈኝነት በየሃይማኖታቸው ውስጥ ሲታይ ሃይማኖታቸው አደጋ ላይ እንደወደቀ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን (የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ) እንዳለውም፣ በጣም አስደናቂ የኾነውን የኢትዮጵያ ዕድገት ማደናቀፍ ከማንኛውም ወንጀል በላይ በሕዝብ ላይ ከባድ ወንጀል መፈጸም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለብዙ ዓመታት ሲሠቃይ የነበረ በመኾኑ አሁንም ሕዝቡን ለሥቃይ መዳረግ ተወዳዳሪ የሌለው ወንጀል ነው፡፡

በማንኛውም ሃይማኖታዊ አክራሪነት እና ጽንፈኝነት፣ በምንም ዐይነት ኹኔታ አንድም ሰው ለአንድ ደቂቃ እንኳ ተዘናግቶ መተኛት የሌለበት ሲኾን በተለይ ይህን ነገር በጥብቅ በሁሉም መንገድ መታገል አለብን፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ያለውን ዕድገት የሚቀናቀነው የውጭ ተቀናቃኝ ነው፡፡ የእነዚህን ተቀናቃኞች ዓላማ በመያዝ በአክራሪነትና በጽንፈኝነት መልክ ታላቅ ክሕደት መፈጸም ከባድ አገራዊ ክሕደት ነው፡፡ የውጭ ጠላት ቀላል ስላልኾነ አንድም ሰው ሳይቀር በጣም ተጠናክረን መመከት ይገባል፡፡ ሕገ መንግሥቱን መሠረት ያደረገ የፖሊቲካ ልዩነት ሊኖር ይችላል፤ ሕገ መንግሥቱን የመጣስ ዝንባሌ ግን እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ መንግሥቱ ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያጸደቀው የራሱ ሕገ መንግሥት ስለኾነ ሕዝብ በመራራ ትግል ያጸደቀውን ሕገ መንግሥት መጣስ የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል ነው፡፡

በዚህ ስብሰባ ከፍተኛ ግንዛቤ መያዙ በጣም የሚያስደስት ነው፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ ተስፋ ነው፡፡ ለውጭ ጠላት ደግሞ ሲጠብቀው የነበረ ብጥብጥ መቅረቱ ሕዝብን የሚያስደስት፣ ጠላትን ደግሞ የሚያሳፍር ነው፡፡

ሌላው ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተነሣ ነበር፡፡ አንድ አባታችን ካነሧቸው ብዙ ነገሮች አንዱ፣ ‹‹መንግሥት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጁን ያስገባል›› የሚል ነው፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ በእስልምናም ይኹን በኦርቶዶክስ እጁን አያስገባም፡፡ በዚህ ጉዳይ የመጀመሪያ ተጠያቂው እምነቱ ነው፡፡ ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም? ሁለተኛው ተጠያቂ ደግሞ መንግሥት ይኾናል፡፡

ስለዚህ በሩን ከፍቶ ሲያንቀላፋ መንግሥት እጁን ካስገባበት እምነቱ ይጠየቃል፡፡ ይኹን እንጂ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት እጁን እንዳላስገባ መቶ በመቶ አምናለኹ፡፡ አንዳንድ የመንግሥት ሰዎች ግን እጃቸውን አስገብተው ሊኾን ይችላል፡፡ ስለዚህ እነዚህን መመከት ነበረበት፡፡ በመጀመሪያ ተጠያቂው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ራሱ ሲኾን እጃቸውን ያስገቡ ሰዎች ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ተጠያቂ ይኾናሉ፡፡

ሁለተኛ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ወጣት*የተነሣ ሐሳብ አለ፡፡ አክራሪነት አደጋ ነው ብሏል፡፡ በኋላ በእስልምና ሃይማኖት አካባቢ በአንዳንድ ሰዎች የሚታየው አክራሪነት አደጋ ነው፤ ዋናው ግን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተቀበረው ፈንጅ ነው ትልቁ የአክራሪነት አደጋ ብሏል፡፡ አክራሪነት ማለት እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ማዋል፣ እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ክፍት ማድረግ ማለት ነው፡፡

አንዳንድ ማኅበራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የፖሊቲካ መድረክ እያደረጓት ነው፤ ማኅበሩ** እንኳ ባይኾን አንዳንድ ሰዎች ብሎ ጠቅሷል፡፡ ይህን ተጠንቅቆ ያቀረበው ይመስለኛል፡፡ ማኅበሩ ነው አክራሪ ወይስ በማኅበሩ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ናቸው? መጣራት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማኅበር ያሉ አንዳንድ ሰዎች ማኅበሩ ጤናው የተበከለ እንዳይኾን ማጣራት፣ ተጠንቅቆ መያዙ፣ እንደተባለው ፈንጅ ከኾነ አስቸጋሪ ነው፡፡ ወጣቱ* እና ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም (የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር) ሁለቱም ከባድ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

እንደተባለው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በእውነት የፖሊቲካ መድረክ እየኾነች ከኾነ፣ በዚህ አገር የትኛው አክራሪነት ነው ከተባለ፣ ትልቁ አደጋ ያለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነው የተባለው ትክክል ነው ወይስ ትክክል አይደለም የሚለው መጣራት የሚኖርበት ቢኾንም በሁለቱ ሰዎች የተጠቆመው ግን የሚያስተኛ አይደለም፡፡ ከእምነቱ ቦታ የኾንም መተኛት የለብንም፤ የሌሎች እምነት አማኞችም መተኛት የለባቸውም፡፡

Viewing all 13695 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>