ገዥዎቻችን መከፋፈል ስልጣንን ለሀያ ሁለት አመታት ያፀኑበት ዋና መሳርያቸው ነው። ሁሌም ለማራራቅ አጠንክረው ሲሰሩባቸው ከኖሩት ማህበረሰባዊ ልዩነቶች አንዱ በአገር ቤትና በውጪ አገራት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ መሀከልም ነው። አሁን አሁን ይህ በተጠናከረና በረቀቀ መንገድ እየተሰራበት እንዳለ በግልፅ ይታያል። በወያኔዎች ዘንድ ትላልቆቹን መህበረሰባዊ ልዩነቶች አይደለም ከቅርበት አኳያ የተወሰኑ ዜጎች የሀመረኖ የቀሩት ደግሞ የጎርፍ አሶጋጅ እድርተኛ መሆናቸው እንደ አንድ ልዩነት ይወሰዳል። ወስደውትም በጠረጴዛ ላይ ያስተኙታል። መዶሻና መሮ ይዘው ለማለያየት መቆርቆርን ታላቅ ሞያ አድርገው ይዘውታል። የዳበረ ልምድ አለን ብለው የሚያቅራሩበትም ነው።
በአገር ቤትና በውጪ በሚኖረው ኢትዮጵያዊ መሀል እየፈለፈሉ ያሉት ልዩነት በሁሉም ዘርፍ የተከፋፈለ ማሀበረሰብ እየፈጠርን መሄድ ለአገዛዝ ያመቸናል ከሚለው መነሻ አላማቸው በተጨማሪ ዋናው ጉዳይ በውጪ አገራት መሰረታቸውን አድርገው የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ትግሉ ላይ ሊያሳርፉ የሚችሉትን ጉልበትና ተቀባይነት መቀነስ ነው። ልፅፍብት ያሰብኩት ይህንኑ በድርጅቶቹ ማሀል ሊኖር ስለሚገባው መልካም ግንኙነት ነው።
በውጪ አገራት እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኢትዬጵያዊ የፖለቲካ ድርጅቶች በሙሉ እንቅስቃሴያቸውን ከውጭ ማድረግ ምርጫቸው አይደለም። መሰረታቸውን በውጪ አገራት እንዲያደርጉ ያደረጋቸው የበዙት ተክልክለው ነው፤ የቀሩት ያለውን ያፈና ግዙፍነት ግምት ውስጥ አስገብተው መሰረታቸውን በውጭ አድርግው መታገልን የተሻላ አማራጭ ሆኖ አግኝተውት ነው ብሎ በሁለት መመደብ ይቻላል። ሁለተኛው ምድብ ውስጥ ያሉት የበዙት ለሰባዊ መብት መከበር የተቋቋሙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሲሆኑ ጥቂት ንቅናቄዎችና የፖለቲካ ድርጅቶች አሉብት።
ወያኔ የዳበረ ልምድና ተሞክሮ ያላቸውን ድርጅቶች ለይስሙላ እንኳ ያለውን የህግ አግባብ እንኳ ሳይከተል ነው በአገራቸው ፖለቲካ ተሳትፎ እንዳያደርጉ በጠዋቱ ጀምሮ የከለከላቸው። ሌሎችን በይስሙላው ፓርላማ ፍርደ ገምድል ውሳኔ አግዷቸዋል። ባይከለከሉም ኖሮ አዋጭ አደርገው በመረጡት የትግል አይነት የተነሳ መሰረታቸውን በግላጭ በአገር ውስጥ አድርገው መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ግልፅ ነው። የበዙትና ብሄር ተከል የሆኑት ድርጅቶች ወያኔ ወደ ስልጣን ከመጣ በሗላ በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማድረግ ሞክረው ብዙ መሰዋትነት አስክፈሏቸው በጭራሽ በአገር ውስጥ መቆየት የማይቻሉ መሆኑን አይተው ሌላ አማራጭ ፍለጋ የወጡ ናቸው።
ወያኔዎች መሰረታቸው በውጪ የሆኑ ድርጅቶችን በሙሉ ጦርነት ናፋቂዎች፤ ህገመንግስት ናጆች፤ ፤ ሽብርተኞች፤ ተገንጣዮች፤ የደርግ ርዝራዦች፤ የነፍጠኛ ስርአት ለመመለስ የሚጥሩ አይነት ክሶች ለድፎባቸዋል። ሁሉም ክሶቹ መሰረት የሌላቸውና ሆን ተብሎ ለልዩነት መፍጠርያና ለማሸማቀቂያ ዌያኔ የፈበረካቸው ናቸው። አላማው ድርጅቶቹ እውቀታቸውን፤ ድርጅታዊ ጥንካሬያቸውንና የገንዘብ አቅማቸውን በአገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጋር አቀናጅተው ትግሉ ላይ ጉልበት በሚሆነን መንገድ መጠቀም እንዳይችሉ ለማድረግ ነው። በእርግጥ እስካሁን መሰረታዊ ልዩነት መፍጠር በአይችሉም ተቀናጅተው ትግሉን ለማካሄድ ቴክኒካል የሆኑ እንቅፋቶችን ግን መፍጠር ችለዋል ማለት ይቻላል።
በአገር ውስጥና በውጪ ባሉ ድርጅቶቹ መሀል መፈራራት እያደገ ነው። አገዛዙ ሊከለክልና ሊያስፈራራ የሚችለው በአገር ቤት ያሉ ድርጅቶችን ነው። ስለዚህም አባላትና አመራሮቻቸውን አንዴ ከዚህ አንዴ ከዛኛው ውጪ ካሉ ድርጅት ጋር ሲዶልቱ ይዘናል በሚል ላፈና ምክንያት እየተጠቀመበት ነው ። እነዚህ ህገወጥ የሀይል እርምጃዎቹ ለማሸማቀቂያና እንደመቀጣጫ እንዲያገለግሉ አስቦበት የሚወስዳቸው ናቸው። በተወሰነ መልኩ እየሰራለት ነው ማለት ይቻላል። በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የየድርጅቶቹ አመራሮች በሚሰጧቸው ቃለ መጠይቆች ሁሉ በምንም መንገድ ውጪ ካሉ ድርጅቶች ተባብሮ ለመታገል አይደለም የሚያነካካቸውና አገዛዙ ለምክንያት ደግሞ ይጠቀምባቸዋል ብለው ለሚያስቧቸው ጥያቄዎች የሚሰጧቸው መልሶች ጊዜ ተወስዶባቸው፤ ቃላት ፈልገውና ጥንቃቄ በተሞላበት የሚሰጧቸው መሆናቸው የሚታይ ነው። እንዲህ የሆነበትን ምክንያት የምንረዳውም ቢሆንም ወያንያዊ የሚመስሉበት ጊዜም አለ። አንዳንዴ ምክንያታዊነትና ሀቅ ሲጎድላቸውም ይታያል። በአገር ውስጥ ያለው የበዛው ህዝብ ካንድ በኩልና ተደጋጋሚነት ባለው ሁኔታ ውሸት በየቀኑ የሚመገብ መሆኑ ተጨምሮበት በተቃዋሚዎች በኩሉ ያለው መሽኮርመም ሲጨመርበት በእጅጉ ሊያወናበድ ይችላል የሚል ፍረሀት አለ።
በውጪ ያሉ ድርጅቶቹ ጉዳዩን በማወሳሰብና ያገዛዙን መከፋፈልና ህዝባዊ ተቀባይነት የማሳጣትን ተንኮል ውጤታማ በማድረገ ረግድ አልቦዘኑም። ወይ መፍትሄው ላይ በበቂ እየሰሩበት አይደልም። መሰረታዊ ያልሆኑ ልዩነቶች ጣሪያ እስኪነኩ ሲጮሁ ይሰማሉ። በአገር ቤትና በውጪ መሰረታቸውን ስላደረጉ እንዲሁ በሁኔታዎች አስገዳጅነት ምርጫ ባደረጉት የትግል አይነት ልዩነት ምክንያት መወዛገብ የተለመደ ነው። በአገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶች የሚንቀሳቀሱበት እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ በአግባቡ መረዳት ካለመቻል በሚሰነዘሩ ትችቶችና በየቃለ መጠይቁ በማይጠፉ አላስፈላጊ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ምክንያት ለሰጣ አገባ በር መክፈትን ሊቀንሱት አልቻሉም። በአጠቃላይ ሁሉ በጁ ሆኖ እሱ ብቻ በደንብ መሰማት ቢሚችልበት ሁኔታ ጭንብል የሚለብሱ አሸባሪዎች ወይ ጦርነት ናፋቂ አድርጎ ሊስላቸው እየሰራ ላለ አካል መፍትሄ ይሆናል ብለው የወሰዱት ህዝባችን ይህን ነጭ ውሸት አይገዛምና አልፎ አልፎ አይደለንም አይነት መከላከያ ብቻ ነው። በአገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶችን ጉልበት እንዲሰማቸውና ተቀባይነታቸው እንዲጨምር ማድረግን ስራቸው ሲያደርጉ አይታዩም። እንደውም ባንጻራዊ ማንኳሰሱ ነው የሚበዛው።
አገዛዙ በውጪ ባሉና በአገር ቤት ባሉ ድርጅቶች መሀል ሊያቆም የሚያስበው የልዩነት ግንብ ለመናድ ቀላል የሆነ መፍትሄ ያለው ይመስለኛል። መፍትሄው የሁለትዬሽና ነግር ግን በተናጠል ሊወስዱት የሚቻላቸው ፖለቲካዊ እርምጃዎች ናቸው። ምንም ጉዳት የሌለው ጠቅላላ ያገሪችንን ፖለቲካዊ ችግሮች ተረድቶ ቀናነትን የሚፈልግ ፖለቲካዊ ውሳኔ ግን ነው። አሁን ባለንበት ሁኔታ በጋራ መምከር የሚችሉበት ሁኔታ ስለሌለ በራስ አነሳሽነት በተናጠል የሚደረሰበት ፖለቲካዊ አቋም ነው።
1. በውጪ ያሉ ድርጅቶች ቢቻል ቢቻል በህብረት ካለሆነም በተናጠል ትልቁን ወይ ሙሉ የሆነ ፖለቲካዊ እውቅና በአገር ውስጥ ላሉ ድርጅቶች በይፋ መስጠት ነው። {በአገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶች ሰላሳ ሶስቱ በሚል በአንድ መሰባሰባቸው አሁን ስራውን አመቺ አድርጎታል}
2. በአገር ውስጥ ያሉ በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በውጪ መሰረታቸውን አድርገው በተለያየ አይነት መንገድ አገዛዙን የሚታገል ድርጅቶች ይህን ምርጫ ማድረጋቸው እንደ አንድ አገራዊ ችግር ማየት መጀመር አለባቸው። መፍትሄ ሰሪ መሆን ነው። እንደ መፍትሄ አቅራቢ መናገርና መተወን መጀምር ነው ብለሀቱ።
የሞኝ ሀሳብ ብላችሁ እንዳታቆሙ ቀጥላችሁ አንብቡኝ። አንዳንዴ ውስብስብና አስቸጋሪ ለሚመስል ችግር ቀላልና የሞኝ የመሰለ መፍትሄ ሊኖረው ይችላል።
በውጪም ሆን በአገር ውስጥ እየታገሉ ያሉ ድርጅቶች የሚታገሉት አገዛዛዊ ስረአት ጥለው አገዛዛዊ ለመሆን አይደለም። የሚመኙ ቢኖሩም እንኳ ከዚህ በሗላ አይቻሉም። በተረፈ የየድርጅቶቹ አገራዊ ፖሊሲ ተመራጭነትና ትክክለኛነት በምርጫ ሂደት በህዝብ የሚዳኝ ስለሆነ ህዘብ የመምረጥ አቅሙን እስኪያገኝ ለግንዛቤ ማሳደጊያ ልንወያይበት የምንችላቸው ናቸው። ድርጅቶች የጋራ ውሳኔ ለማሳለፍም ሆነ እርቀው ሄድው ለመተባበር የግድ ሁሉንም ፖሊሲያዊ ጉዳዬች በጠረቤዛ ዙሪያ እየተወያዩ ቁጭ ብለው ሊስማሙበት የሚገባ አይደልም። ቢሞክሩትም በሁሉም ዘርፍ ፖሊሲዎች ላይ በመነጋገር አንድ የሚያስማማ ተመራጭ ፖሊሲ አያወጡም። በመወያየት አይደለም እሳት ላይ ጥደው ሲቀቅሏቸው ቢኖሩም ልዩነቶቹ ተዋህደው ሁሉ የሚስማማበት አንድ አማራጭ ሀሳብ ብቻ በየዘርፋቸው አይወጣቸውም። የተለያዩ አማራጭ ፖሊሲ ሀሳቦች ሁሌም ይኖራሉ። መኖርም አለባቸው። ከፖሊሲ ልዩነቶች መለስ ያሉት በሙሉ ምርጫ ያደረጉትን የትግል አይነት ጨምሮ እያወጣን ብናያቸው እዴሜያቸው ከአገዛዙ ጋር የሚያበቃ ነው። በአገር ውስጥና በውጪ ባሉ ድርጅቶች አዋጭ የሆነው መንገድ ብዬ ያስቀመጥኩት መፍትሄ ሀሳብ በድርጅቶቹ መሀል ያሉ ከአገዛዙ ጋር ከሚያበቁ ልዩነቶች ተነስቼ ነው።
ወያኔ በአገር ውሰጥና በውጪ አገር ባለው ህዝብ እንዲሁ በአገር ቤትና በውጪ አገራት መሰረታቸውን አድርገው በሚታገሉ ድርጅቶች መሃል ሊያቆም የሚጥረው የልዩነት ግንብ የሚሰራለት ተቃዋሚና የተለየ አይነት አላማና ግብ ይዞ ሚንቀሳቀስ ሌላ አይነት ተቃዋሚ ደግሞ ካለ ነው። አለበለዚያ ባይኖርም እንዳለ አድርጎ በህዝብ ዘንድ መሳል ከቻለ ብቻ ነው። ድርጅቶች መሰረታቸውን አገር ውስጥና ወጪ እንዲሁ ደግሞ በሁለገብ ትግል ወይ በሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ እየታገሉ ስላሉ ብቻ የልዩነት ግንብ ማቆም አይቻለውም። ከቻለ ባጭሩ ያለውን ያላማን እንድነት እንዲሰማና እንዲታይ ማድርግ ድርጅቶቹ አልቻሉም ማለት ነው።
ማናም እንደሚረዳው ችግር የሆነው በድርጅቶቹ መሃል ያለ ያላማና የግብ ልዩነት መኖሩ አይደለም። በአገር ውስጥ እያታገሉ ያሉ ድርጅቶች አፈሙዝ ተደቅኖባቸው ስለሚንቀሳቀሱ በውጪ ካሉ ድርጅቶች ጋር ያላቸውን ያለማ አንድነት እንዲሰማ አድርገው ለማወጅ ተቸግረዋል። በውጪ ያሉ ድርጅቶች ደግሞ አስፈላጊነቱ እስካሁን አልዞረላቸውም። ሲጀመር ወያኔ ለሚያቀርባቸው የፈጠራ ክሶችን ለመከላከል ከመሞከር አዋጩ መንገድ የነበረው አገር ውስጥ ካሉ ድርጅቶች ጋር ያለውን ያላማ አንድነት እንዲሰማና የሚታይ ማድረጉ ነበር። ወደፊትም ይህን ሀሳብ ጠቃሚ ሆነው አግኝተውት ሊጠቀሙበት ካሰቡ አንድነታቸውን አለም እንዲያውቀው የማድረጉንና ከፍተኛውን ፖለቲካዊ እውቅና በአገር ውስጥ ላሉና በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለሚታገሉ ድርጅቶች የመስጠቱን የመጀምርያውን ፖለቲከዊ እርምጃ መውሰድ ያለባቸው በውጪ ያሉ ተቃዋሚዎች መሆን አለባቸው።
መሰረታቸው በውጪ ከሆኑ ድርጅቶች የሚጠበቀው ሙሉ ፖለቲካዊ እውቅናና ለህጋዊ ተቃዋሚዎች ጉልበት መስጠት።
- ችግራችን ስልጣን ላይ ካለው አንባገነናዊ አድሏዊ ጨፍጫፊ ፓርቲ ጋር ነው። ገዢው ፓርቲ በአገራችን ፖለቲካ እንዳንካፈል ከልክሎናል። መሰረታችን በውጪ አድርግን የምንታገለው ገዢው ፓርቲ ስልጣን ላይ እስካለ ብቻ ነው። በቀጣይ በአገር ውስጥ ያሉ ህጋዊ ተቃዋሚ ድርጅቶች ከሚያቆሙት መንግስት ጋር በሰላማዊና የአገሪቷ ህግ በሚያዘው መሰረት በአገራችን ገብተን በሰላማዊ የፖለቲካ ውድድር ውስጥ እንካፈላለን።
- ስልጣን ላይ ባለው አገዛዝ አንባገናኒወነት ምክንያት ተገደን ምርጫ ያደረግነውን የትግል መንገድ አገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስልጣን የያዙ እለት የምናቆመው ነው። የመንግስት ስልጣን ይዘው አይደለም ከዛም በፊት በተቀናቃኝ ፓርቲነትም ደረጃ ሆነው ህዝብ አለምንም ጣልቃ ገብነትና ወከባ በሚደረግ ምርጫ የሚፈልገውን መንግስት መምረጥ አሁን ይችላል ብለው ማረጋገጫ መስጠት ከቻሉና ለደህንነታችንና ላጠቃላይ ሂደቱ ሀላፊነት የመስጠት አቅሙ ሲገነቡና ሀይላቸውን ልናየው ስንችል እንዲሁ እነሱም ሀላፊነት እንወስዳለን ሲሉ ላሁኑ ምርጫ ያደረግነውን ትግል እርግፍ አድርገን ትተን በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ በመርጫ ለመሳተፍ መሰረታችንን በአገር ቤት እናደርጋለን።
-በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ አገር ቤት እየተንቀሳቀሱ ያሉት ድርጅቶች የያዙት አገራዊ እራአይ ላገራችን የሚጠቅም ነው። በኢትዮጵያችን ዲሞክራሲያዊ ስረአትን ማስፈንና አገሪቷን የተሻለ የእድገት ደረጃ ላይ ማድረስ በደንብ ይችላሉ። ህዝባችንን ወደ ብልፅግና ለመውሰድ በሚያደርጉት ሁሉ መቶ በመቶ አብረናቸው ነን። ሙሉ እገዛችን ይኖራቸዋል።
- በአገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶችንም ሆነ በየድርጅቶቹ ስር ሆነው ለለውጥ እየታገሉ ያሉ ዜጎቻችን ሆን ብለው አገራቸውንና ህዝባቸውን የሚጎድ አይደሉም። የአገራችን ሉአላዊነትና ጥቅሟን በማስጠበቅ ረገድ አሁን በተቃዋሚነት ሆነው ሆነ መንግስት ቢሆኑ በሚወስዷቸው እርምጃዎች እናምናቸዋለን። ተሳስተው ጎጂ ሊሆን የሚችል አቋም ወይ እርምጃ ሊወስድ ቢያስቡ እንኳ ቁጭ ብለን መክረን ለመተራረም አገር ውስጥ በሰላምና በህጋዊ ምንገድ ከሚታገሉ ድርጅቶች ጋር በደንብ እንችላለን።
- በአገራችን የልተመለሱና እየጨመሩ የሄዱትን መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች በበቂ ለመመለስ አገዛዙ አልቻለም። አገር ቤት በሰላምና በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ድርጅቶች ግን ሊመልሷቸው ይችላሉ። እስካሁን በአገሪቷ ወስጥ በተለያየ ጊዜ የሚፈጠሩ ችግሮችን የሚያዩበትና መፈታት አለበት የሚሉበት መንገድ በተጨማሪም ቅሬታዎች መያዝ አለባቸው ብለው የሚያቀርቧቸው የመፍትሄ ሀሳቦች የሚስማሙን ናቸው። ለወደፊቱም በዚህ አይነት ጉዳይ ላይ እየተመካከርን ተስማምተን መስራት እንችላለን።
- አገዛዙ ከኛ ጋር መደራደር የሚያስፈልግበት ሁኔታ ብዙም አይታየንም። አገር ውስጥ ካሉትና ሰላማዊና ህጋዊ የሆኑትን ድርጅቶች ጥያቄ መመለስ ከቻለና የሚደሰቱበትን ስምምነት መቋጨት ሲችል በርግጠኛነት የበዛው ጉዳይ በቀጥታ ከኛም ጋር የሚያስማማው ነው የሚሆነው።
- በአገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶች እያደረጉት ያለውን ህጋዊና ሰላማዊ ትግል የምንደግፈው ነው። በጣም በአአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ለውጥ ለማምጣት እየጣሩ እንዳሉ ብናውቅም አፈናውን ሊቋቋሙት እስከቻሉ ሰላማዊና ህጋዊ ትግላቸውን ብቻ አጠንክረው እንዲቀጥሉ እንሻለን።
ሙሉ እውቅናው ይህንን አይነት መምሰል አለበት። በአዋቂዎች ሊከሸን ሊጨመርበት ሊቀነስ ይችላል። ይህ ፖለቲካዊ እርምጃ መሰረታቸውን በውጪ አድርገው በየትኛውም አይነት ትግል እየታገሉ ያሉ ድርጅቶች ትግላቸውን አሁን በሚያካሂድበት መንገድ ለመቀጠል ሳንካ አይሆንም። እንደውም አጠንክረው እንዲቀጥሉ ያግዛል። ይህ ፖለቲካል እርምጃ በየትኛውም መንገድ ትግሉን የሚጎዳበት ወይ በሂደት ድርጅቶችን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከትበት መንገድ ቢኖረው ኖሮ አይቀርብም ነበር። አንባቢ ይህ እርምጃ በየትኝውም አቅጣጫ ያልታዩ ጦሶች ልታዩበት ከቻላችሁ ግን ሁሌም ብታሳዩ ጠቃሚ ነው። በተረፈ ደርጅቶች አገላብጠው ሳያዩት አይገለገሉበትም።
በአገር ቤት ያሉ ድርጅቶች የመተባበር ሚስጥሩ የተገለፀላቸው ይመስላል። በተቃዋሚዎች መሃል የኔ ይሻላል የምርጫ ፖለቲካ የትም እንደማያደርስ ገበቷቸዋል። የሚገርመው የፉጉም ቢሆን የምርጫ ጉዳይ ውስጥ ያሉትና ለምርጫ ቅርብ የሆኑት ግን እነሱ ናቸው። በርግጥ በተመሳሳይ ለችግሩና ለዱላው ቅርብ መሆናቸው ሳያግዛቸው አልቀረም። እስካሁን በውጪ ሆነው የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በጋራ ትግሉን የሚያካሂዱበትን አንድ አይነት ትብብር ማቆም ግን አልቻሉበትም። ችግር የሆነው ትግሉን አስተባብሮ በተቀናጀ መልክ ማስኬድ አለመቻላቸው ብቻ ግን አይደልም። ትግሉ በዚህ አይነት ፖለቲካዊ ውሳኔዎችም መታገዝ ነበረበት። የጋራ መድረክ ማቆም ስላልቻሉ ብዙ የዚህ አይንት የጋራ ውሳኔን የሚፈልጉ ጉዳዬች ውሳኔ የሚሰጥባቸው አጥተው ተወዝፈው ነው ያሉት። ትግሉን ደግሞ ወደፊት እንዳይሄድ ቀፍድደው ይዘውታል። ድርጅቶች በተናጠል የተወሰኑት ላይ ውሳኔ ለማድረግ ቢሞክሩም አይሰራም። አንዳንዶቹ ደግሞ በበቂ ውጤታማ አይሆኑም። አገር ውስጥ ላሉ ህጋዊና ሰላማዊ ድርጅቶች ጉልበት የሚሆናቸውን ሙሉ እውቅና የመስጠቱ ጉዳይ ላይ ግን ተባብረው ቢያደርጉት ይመረጣል እንጂ በተናጠል ቢያደርጉትም በደንብ የሚሰራ ነው። በይበልጥ በአገር ውስጥ ፖለቲካ እንዳይሳተፉ የታገድና የተከለከሉ ሁለገብ ትግልን ምርጫ ያደረጉ ድርጅቶች አፅኖት ሰተው ሊያስቡበት የሚገባ ነው።
በውጪ ያሉ ድርጅቶች ወደፊትም ቢሆን ተቀምጠው መምከር ከቻሉ የሚነጋገሩበትን ጉዳይ መምረጥ አለባቸው። በፖሊሲ ጉዳይ ላይ፤ ምርጫ በሚያደርጉት የትግል አይነት፤ አገራዊ ፍልስፍና ጨምቆ ለማውጣት፤ በበዛ ሁኔታ ሽግግር ጉዳይ ላይ ወይ ከወያኔ በሗላ የሚኖሩ ችግሮች መፍትሄ ለማስቀመጥ ባይሆን እመረጣለው። ምክንያቱም አሁን ስለማይቻልና ለነዚህ በቂ ጊዜ ስላለ ብቻ ነው። ማሸነፍ ለሚባለው ዋና ጉዳይ እሩቅ ነው ያለነው። ማሸነፍ እንደሚችሉ እርግጠኛ ሳይሆኑና ሳይቃረቡ በዚህ አይነት ታላቅ አገራዊ ቁም ነገሮች ላይ የሚያስማማ ነገር ላይ መድረስ እንደስካሁኑ ወጡ ሳይወጠወጥ እየሆነ የምር ሊወሰድት አልተቻለም። እስቲ ትግሉን አቀናጅተው አሸናፊ የሚያደርጉበት ብለሀት ላይ ለማነጋገር ይጀምሩ። በርግጠኛነት ይስማማሉ። ተቀራርበው መስራት ሲጀምሩ ደግሞ ተራራ አድርገው የሚወስዷቸው ጉዳዬች መስመር እየያዙ እየጠፉ ይሄዳሉ።
በተረፈ ሌላ አይነት በአገር ውስጥና መሰረታቸውን በውጪ ያደረጉ አጋር ድርጅቶች መሀል ወያኔ ሊገነባው የሚያስበውን ግንብ ሊያፈርሱበት የሚችሉበት፤ ትግላቸውን ሊያስተባብሩበትና ሊያቀናጁበት የሚችሉባቸው መንገዶች ይኖሩ ይሆናል። ይሰሩ ይሆናል ብዬ ያየሗቸው ብለሀቶች በሙሉ አሁን ባለው ያገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታ ትግሉን የሚያወሳስቡበት ጎን አላቸው። በርግጥ በምርጫ 97 ትልቅ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የብዙ ድርጅቶች የተካተቱበት ህብረት ጥሩ ድልድይ ሆኖ ሲያገለግል ነበር። በነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ህልውናውን በአገር ውስጥ ለማስቀጠል በቂ ጥረት ተደርጎ ቢሆን እንዴት ጠቃሚ ነበር። አሁንም ተመሳሳይነት ያለው ትብብር ከተቻለ መሞከሩ አይከፋም። ሁሉም ድርጅቶች ባይሆኑ የዚህ አይነት ትብብር ለማቆም የሚችሉ ድርጅቶች በውጪ አሉ።
በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች መፍትሄ ሰሪ፤ አቅራቢና ተዋኝ መሆን አለባቸው ።
ህጋዊ ተቃዋሚ መሆን ማለት ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ ቀጣይ መንግስት ለመሆን እየሰራና እየተዘጋጀ ያለ አካል ማለት ነው። አገር ቤት ያሉ ህጋዊ ተቃዋሚ ደርጅቶቻችን በአሉበት የከፋ አፈና ውስጥም እንደቀጣይ መንግስት ለመተወን የሚቻልበት እድሉ አለ። ህጋዊ ተቃዋሚ ሆነው እስከቀጠሉ አማራጭ ሆኖ መታየትን የግድ አሳምረው ሊሰሩት ይገባል። እስከእስካሁኑ እንደ ቀጣይ መንግስት ሲተውኑ ግን አይታይም። በህዝብ አመኔታንና አማራጭ እየሆኑ መታየት የሚጀምሩት እንደ ቀጣይ መንግስት መተወንን ሲጠበቡበትና የሚታይ እየሆነ ሲሄዱ ብቻ ነው። እስካሁን ስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ አጋላጭ የህዝብ ብሶት አቅራቢ በቃ ተቃዋሚዎች ብቻ ናቸው። ዋንኛው ምክንያት ቀጣይ መንግስት የመሆኑን ጉዳይ ህዝብ ሊያጤነው በሚችል ደረጃ ለነሱም እርቆ የሚታያቸው መሆኑ ነው። ይህ መቀየር አለበት። በእርግጥ አፈናውን ያልተባበረ ተቃዋሚ የነበሩ መሆናቸው የራሱ አስተዋፆ አድርጓል።
ለምሳሌ የእስልምና እምነት ዜጎቻችን በጣም ቀላል የመብት ጥያቄዎች አንስተዋል። አገዛዙ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሙሉ አሸባሪ ሲል ሰይሞ ጥያቄያቸውን መመለስን መደፈር አድርጎ ወስዶታል። አሸባሪዎች ብዬ በገፍ ገድዬና አስሬ ጭጭ አሰኛቸዋለው የሚለውን መንገድ ምርጫው አድርጓል። በሌላ በኩል ተቃዋሚዎች የስልምና እምነት ተከታይ ዜጎች ያነሷቸው ጥያቄዎች ቀላል የመብት ጥያቄዎች መሆናቸውን ይስማማሉ። መንግስት ቅራኔውን ሊፈታ ያሰበበት የሀይል መንገድ ያወግዛሉ። ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ እያቀረቡ እንደሆነም መስክረዋል።
ይህ ከሆነ ታዲያ በዚህስ መንገድ አስተናግደውትስ ቢሆን። የእስልምና እምነት ተከታይ ዜጎች ያነሷቸው ጥያቄዎች አንድ ሁለት ብለው ዘርዝረው እነዚህ ናቸው። እነዚህ ቀላልና ህጋዊ የመብት ጥያቄዎች ናቸው። በተጨማሪም ጥያቄዎቹ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የቀረቡ ስለሆኑ ገዥው ፓርቲ በአስቸኳይ ሊመልስላቸው ይገባል። እንደግመዋለን በአስቸኳይ ሊመልስላቸው ይገባል። ገዥው ፓርቲ ደም ካላፈሰስኩበት የሚለውን ችግር በኛ በኩል በርግጠኝነት በቀላሉ ሰላማዊ መፍትሄ ልንሰራለት የምንችለው ነው። የስልምና እምነት ተከታይ ዜጎቻችን ያቀረባችሗችሗቸውን ጥያቄዎች ሲጀመር ጥያቄ መሆን አልነበረባቸውም። ለነዚህ ጥያቄዎች ይህን ያህል መታገላችሁ ያስቆጨናል። በኛበኩል ሁሉንም ጥያቄዎች በጠየቃችሁት መሰረት እንመልሳቸው ነበር። ስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ በመግደልና በገፍ ሰብስቦ በማሰር ጥያቄዎቹን አዳፍናለሁ ካለ የሀይሉን መንገድ ምርጫው ስላደረገና ስለፈለገ ብቻ እንጂ ጥያቄዎቹ ሊመለሱ የማይችሉ ስለሆኑ ወይ የሊሎች ዜጎችን መበት በምንም መንገድ የሚጋፋ ሰለሆነ እንዳልሆነ እውቀናል። እዚህ ጉዳይ ላይ ህዝባችንም ግንዛቤ እንዲኖረው እንፈልጋለን። እነዚህን ቀላል የመብት ጥያቄዎች በሀይል ሊፈታ ማሰቡ በራሱ ገዥው ፓርቲ የማስተዳደር ችሎታ እንዴሌለው በግልፅ የሚያሳይ ነው። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ መብታቸውን የጠየቁ የስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችሁ ድህንነት መንግስት እወስዳለው በሚለው እርምጃ ምክንያት እጅጉኑ የሚያሳስብ ደረጃ ላይ መድረሱን ይገንዘብ። ሂደቱንም አፅኖት ሰጥታችሁ ተከታታሉ። በሚችለው አቅም የመንግስትን የእብደት እርምጃ ለማስቆም መሞከር አለበት። በኛ በኩል ስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ እነዚህን ቀላል የመብት ጥያቄዎች መልሶ ችግሩን መፍታት ከከበደው ንፁሀን ዜጎችን ያላአግባብ ከሚፈጅ ስልጣኑን በቶሎ በህዝብ ለተመረጠ መንግስት አሁኑነ እንዲያስረክብ እንጠይቃለን። መንግስት በማን አለብኝነት ሊፈፅም የሚያስበውን ወንጀል አምርረን የምንታገለው መሆኑን ግልፅ እናደርጋለን። የሚል አንድምታ ኖሮትስ ቢሆን።
በሁለቱ አቀራረብ ላይ ያለው ልዩነት እስካሁን ተቃዋሚዎች የያዙት አቋም ስህተት መሆኑ አይደለም። ነግር ግን እዚህ ቀላል ጉዳይ ላይ እንኳ እነሱ እንዴት ችግሩን እንደሚፈቱት ወይ መፍትሄ ይሰሩለት እንደነበር አልፈውታል። አገዛዙ ለመፍጀት ቀጠሮ ሰጥቶ እያለ እንዲህ ብለህ እንዳትገድል መሆን ሲገባው ሁሉም እስኪጨፍጭፍ ጠብቀው ነው ያወገዙት። የሁሉንም ድርጅቶች መግለጫዎች ከመረመርን ይዘታቸው አገዛዙን የመጨፍጫፍ አባዜ በበቂ አያሳዩም። ሁሉም ዜጋ ችግሩን እንዲከታታል መፍትሄውም ላይ በንቃት እንዲሳተፍ አይጋብዙም። የመግለጫዎቹ ይዘት አገዛዙን አያገልም። አንዳንዶቹ እንደውም ሆን በሎ ችግር ከሚፈጥር አካል መፍትሄ አፅኖት ሰጥተው ይጠይቃሉ። በአጠቃላይ ጥሩ ተቃዋሚ እንጂ ቀጣይና አማራጭ መንግስት አድርጎ አላሳያቸውም። በህዝብ ዘንድም አመኔታንና አማራጭ ሆኖ የመታየት የፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ ይህን አይነቱ የእስካሁኑ አያያዛቸው አልጠቀመም። ተቃዋሚዎች ችግሩን እነሱ የሚፈቱበትን መንገድ ግልፅ ብሎ በሚታይ መንገድ ቢያካትቱ ኖሮ ጅራፍ እራሱ ገርፎ አይነት በገደላቸው፤ ባሰራቸውና በቀጠቀጣቸው ንፁሀን ሊሸማቀቁ በተገባ ነበር። የልብ ልብ ባንሰጣቸው ንፁሀንን መግደላችሁ አግባብ አይደለም ያሉትን ተቃዋሚዎች ተመልሰው ተሞዳመዳችሁ ብለው ሊያሸማቅቁ ባልዳዳቸው ነበር። ፈራ ተባ እየተባለ የሚደረግ ነግር ጦሱ ብዙ ነው። ነገ ደግሞ በዚሁ ሰበበ ከውስጣቸው የተወሰኑትን አገዛዙ አስሮ ማሰቃየቱ አይቀርም።
ለማንኛውም ወደ ጀመርኩት ጉዳይ ልመለስና መሰረታቸውን በውጪ አድርገው ለለውጥ እየታገሉ ያሉ ወይ የተለየ የትግል አይነት ምርጫ ያደረጉ ድርጅቶችን በሚመለከት በህጋዊ መንገድ በአገር ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ድርጅቶች የመናገር እድሉን ባገኙ ወይ በተጠየቁ ቁጥር ሁኔታው የተፈጠረበትን ምክንያትና ያለውን እውነታ እንቅጭ እንቅጩን እንዲሰማ አድርገው ደጋግመው ከመናገር ጎን ለጎን በዋናነት ማድረግ ያለባቸው እንደቀጣይ መንግስት የራሳቸውን መፍትሄ አቅራቢ፤ ሰሪና ተዋኝ መሆን ነው። አገዛዙ መፍትሄ አድረጎ ከያዘው ህግ ማምረት፤ ጦርነት ማወጅ፤ ፊልም መስራት፤ መግደልና ማሰር የተለየ ሰላማዊ መፍትሄ አለን ነው ብለሀቱ። የጎደለውም ይህ ነው።
ዜጎች የሀይሉን መንገድ የመረጡት አፋኝና ጨካኝ አንባገነን ስለሆንክ ነው። ከዜጎች ጋር ገባሁበት የምትላቸው ችግሮች ባንተ አንባገነናዊነት ምክንያት የተፈጠሩ ናቸው። ሰላማዊ መፍትሄ መስራት ካልቻልክ ስልጣኑን ላኛ አሳልፍ። እኛ ሰላማዊ መፍትሄ ልንሰራበት ቀላላችን ነው የሚመስሉ አገላለፆች በዝተው መሰማት አለባቸው። እነዚህ ሁሉ በጭራሽ ያልተጋነኑም እውነትነትም ያላቸው ናቸው። ለነገሩ ግን የፖለቲካ ትግል ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው የቃላት ጫወታ መጫወቱን እወቁበት። ችግሩ ላይ አውደ ጥናቶች፤ የምክክር መድረኮችን በተደጋጋሚ አዘጋጁ። ምሁራኖችን ጋብዙ፤ ህዝብን አወያዩ ባጠቃላይ የመፍትሄ ተቃዋሚ ሁኑ።
የተከበሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በኢሰት ራዲዮ ቀርበው ከህዝብ ለቀረበላቸው ጥያቄ ቀጥተኛ መለስ በሚሰጡበት ጊዜ ዛሬ መፍትሄ ብዬ በአቀረብኩት እነዚሁ ጉዳዬች ላይ የመጠየቅ እድሉን አግኝቼ ነበር። በጊዜውም ጥያቄውን ያቀረብኩት አጥጋቢ መለስ ያኔውኑ ይሰጡበታል ብዬ ሳይሆን ሀሳቡ ህዝብ ዘንድ ይድረስ። ይዘውትም ይሄዳሉ በማለት ነው። በርግጥ በጊዜው ቀዳሚ የመፍትሄ እርምጃ አገር ውስጥ ካሉ ህጋዊ ድርጅቶች ሊፈልቅ ይችላል ወይ ያንድ ወገን ብቻ መፍትሄ አለው የሚል የተሳሳተ እይታም ነበረኝ።
ጥያቄው የነበረው። አገዛዙ በውጪ ሆነውና በተለየ መንገድ የሚታገሉትን ድርጅቶች ጦርነት ናፋቂ አሸባሪ እያለ እየወነጀለ ነው። በዚህ ሰበብ በህጋዊ መንገድ መብታቸውን የሚጠይቁ ዜጎችን ያናንተንም አባለት ጨምሮ አስሮ እያንገላታ ነው። ወያኔ ይህን ችግር አስሬ ገድዬ እፈታለው ብሏል። እንደቀጣይ መንግስትና ህጋዊ ተቃዋሚ ወያኔ ከሚከሳቸው ድርጅቶች ጋር ሰላማዊ መፍትሄ ለምን ለማስቀመጥ አትሞክሩም። ይህንን ሰል በጭራሽ በድብብቆሽ የሚሰራውን አይደለም። እንደ አንድ አገራዊ ችግር አይታችሁት በግልፅ መፍትሄ ልትሰሩለት ስለሚገባ ጉዳይ ነው የሚል ነበር።